Professional Documents
Culture Documents
የሕማማት ሥርአት
የሕማማት ሥርአት
በእያንዳንዱ የጸሎት ሰአት ውስጥ ያሉ መርኀ ግብሮችን ለማወቅና ለማጥናት እንዲረዳን ከሞላ ጎደል በሁሉም የጸሎት
ሰአታት ውስጥ የማይቀሩትን የጸሎት ክፍሎች በሰባት ከፍለን እንያቸው።
ክፍል 1:አቡን እና ለከ ኃይል
ክፍል 2:ምንባባት
ክፍል 3:ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ
ክፍል 4:ወንጌል
ክፍል 5:ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ
ክፍል 6:ኪርያላይሶን
ክፍል 7:ሰላምታ
የእያንዳንዱ የጸሎት ሰአት አጀማመር እንዲህ ነው:- ዲያቆኑ በሴቶች በር በኩል ቃጭል እያጮኅ ቤትክርስትያኑን ሶስት ጊዜ
ይዞራል
ድንግል ማርያምና ዮሐንስ እያነቡ የጌታን መስቀል የመዞራቸው ምሳሌ ነው።
ዞሮ ሲገባ መዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማርያም
ይደገማል።በመቀጠልም
አንደኛ አቡን በዜማ ይደረስና ለክ ኃይል እየተባለ ይሰገዳል።በመቀጠልም
ሁለተኛ ምንባባት በተከታታይ ይነበባሉ
ሶስተኛ ተአምረማርያምና ተአምረ ኢየሱስ
በተከታታይ ይነበባሉ።
አራተኛ የሰአቱ ወንጌል ይነበባል
አምስተኛ ካህኑ ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ ሲሉ
እግዚኦ ተሳሃለነ እየተባለ ይሰገዳል
ስድስተኛ ኪርያላይሶን እየተባለ ይሰገዳል
ሰባተኛ የሰአቱ የሰላምታ(መልክአ ሕማማት) በዜማ ይቀርባል
በመጨረሻም ለሰአቱ የሚስማማ መዝሙር በሰንበት ት/ቤት ይዘመርና ካህኑ የሰአቱ
ጸሎት ተጠናቋል በሰላም ሂዱ ለሚቀጥለው የጸሎት ሰአት በሰላም ተመለሱ ይላሉ።
ትንሽ ቆይተው የሚቀጥለውን የጸሎት ሰአት
ያስጀምራሉ።እንዲህ እያለ ይቀጥላል።
ሰባቱን የጸሎት ክፍሎች ከዚህ በታች እናያለን።
/////////////////////////////////////////////////
ክፍል አንድ
ርዕስ:-አቡን እና ለከ ኃይል
ቅዱስ ያሬድ ለተለያዩ በዓላት አቡን የሰራላቸው ሲሆን ለሰሙነ ሕማማት የአቡን ዜማ ሰርቶለታል።
ከሰኞ እስከ ሀሙስ በአንድ ሰአቱም ይሁን በሶስት ሰአቱ በስድስት ሰአቱም ይሁን በሌላው የጸሎት ሰአት የሚነበበው ወንጌል
የሰአቱን አቡን ይወስነዋል። ይሄም ማለት የሚነበበው የማቴዋስ ወንጌል ከሆነ የማቴዎስ አቡን ይባላል።የሚነበበው
የማርቆስ ወንጌል ከሆነም የማርቆስ አቡን ይባላል።ለሉቃስ ወንጌል የሉቃስ አቡን፣ለዮሃንስም ወንጌል የዮሃንስ አቡን ይባላል።
አቡን
1::ከሰኞ እስከ ሀሙስ አቡን
ማስታወሻ:-ከሰኞ እስከ ሀሙስ ለከ ኃይል ከመባሉ በፊት የሚባለው አቡን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ ሲሆን።መሪ እና ተመሪ
ካህናት እየተፈራረቁ ያደርሱታል እንደጨረሱም ለከ ኃይልን ይጀምራሉ))
አቡን ዘማቴዎስ
በ፫ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌሉያ
ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኩልክሙ አብያተ ክርትያናት ከመ ዘአክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ፣በወንጌል መንግስት እንዘ ይብል
ክርስቶስ ወልደ ዳዊት አሜን አሜን እብለክሙ እስከ አመ የኅልፍ ሰማይ ወምድር የውጣ እንተ አሐቲ ኅርመታ ወአሐቲ ቅጽረታ
ኢትኅልፍ እምኦሪት ወእምነቢያት እስከ ሶበ ኩሉ ይትገበር ወይከውን ይቤ እግዚእ ዘበእብራይስጢ ልሳን በወንጌለ ማቴዎስ
ብርሃን ዘእምብርሃን።
አቡን ዘማርቆስ
በ፫ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌሉያ
ስምዕዎኬ ለእግዚእነ ኩልክሙ አብያተ ክርስትያናት ከመ ዘእክበሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት፣በወንጌለ መንግስት እንዘ ይብል
ክርስቶስ ወልደ ዳዊት ኢይምሰልክሙ ዘመጻእኩ እሥዐሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት፣ወኢ ከመ እንሥቶሙ አላ ዳእሙ ዘእንበለ ከመ
እፈጽሞሙ ይቤ እግዚእ በወንጌለ ሰላሙ ዐማኑኤል ስሙ ማርያም እሙ።
አቡን ዘሉቃስ
በ፫ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌሉያ
ይቤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዘ ይሜህረነ በወንጌለ ሉቃስ ወባሕቱ ይቀልል ሰማይ ወምድር ይኅልፍ እምትደቅ አሐቲ ቃል
እምኦሪት።
አቡን ዘዮሐንስ
በ፫ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌሉያ
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በወንጌል ለዘመሀረነ በኦሪት ወበነቢያት ለዘናዘዘነ በከመ መሐረነ እግዚእነ ስብሐት
ለእግዚአብሔር ከመ ናምልኮ ለዘፈጠረነ።
#######################
2:: የእለተ አርብ አቡን
ለእለተ አርብ ግን አቡን የተሰራለት ለየጸሎት ሰአቱ
ነው ይሄም ማለት የነግህ አቡን፣የሶስት ሰአት አቡን የስድስት ሰአት አቡን፣የዘጠኝ ሰአት አቡን ፣የሰርክ አቡን ተብሎ ተዘጋጅቷል።
ማስታወሻ:-በእለተ አርብ በአንድ ሰአት በሶስት ሰአት በስድስት ሰአት በዘጠኝ ሰአት በአስራአንድ ሰአት ለከ ኃይል ከመባሉ በፊት
የሚባለው አቡን ከዚህ በታች ተቀምጧል።መሪ እና ተመሪ ካህናት እየተፈራረቁ ያደርሱታል እንደጨረሱም ለከ ኃይልን
ይጀምራሉ
ለከ ኃይል
ለከ ኃይል ለሰአቱ የተመረጠው አቡን ከተባለ በኋላ የሚባል የስግደት ስርአት ሲሆን አቡኑ ቢቀያየርም ለከ ኃይል ተመሳሳይ
ነው።ለጥናት እንዲመቸን ለከ ኃይልን በሶስት እንክፈለው
አንደኛ
ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ዐማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም።
ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ።
እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት።
ማስተዛዘል
መሪ ለአምላክ--ሲል ተመሪ ለሥሉስ---ይላል
መሪ ለማኅየዊ ሲል ተመሪ ለዕበዩ ይላል
መሪ ለእዘዙ ሲል ተመሪ ለመንግስቱ ይላል
መሪ ለሕማሙ ሲል ተመሪ ለመስቀሉ ይላል
//////////////////////////////////////////////
ክፍል ሶስት
ተአምረ ኢየሱስ ወተአምረ ማርያም
በሰሙነ ሕማማት ተአምረ ማርያም እና ተአምረ አየሱስ በአንድ ቀን በትንሹ ሰባት ጊዜ ይነበባሉ።እናንተ በዚህ ሳምንት ወደ
ቤተክርስትያን በምትሄዱበት ጊዜ ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ሲነበቡ ብትደርሱ በመንፈስ በእምነት ቆማችሁ
የምታዳምጡ ሁኑ።ሙሽራም ያለ አጃቢ ያለ ሚዜ እንደማይወጣ እነዚህ ተአምራት ከመነበባቸው በፊት እና ከተነበቡ በኋላ
የሚደረሱ ዜማወች አሉና እነሱን እናጥና
//////////////////////////////////////////////
ክፍል አራት
ርዕስ:-ወንጌል
ቤተክርስትያናችን አራቱን ወንጌላት ለአመት አካፍላ በአንድ አመት ውስጥ ባሉ በያንዳንዱ ቀናት የሚነበቡ የወንጌል
ክፍሎችን ወስና ያስቀመጠች ሲሆን ለየክብረበዓሉ የሚገባውን ምንባብም በሊቃውንቶቿ አመቻችታ አዘጋጅታለች።
በአመት ውስጥ ላሉ ቀናት ወንጌል እንደተሰጣቸው እንዲሁ ደግሞ ለሁሉም ቀናት ከእያንዳንዱ ወንጌል
በፊት በዜማ የሚባል ምስባክም ሰርታለች።የአመቱን ወንጌልና ምስባክ የያዘው መጽሐፍ መጽሐፈ ግጻዌ ይባላል።
እናንተም በዚህ በሰሙነ ሕማማት በሁሉም የጸሎት ጊዜዎች የሚነበበውን ወንጌል እና ምስባኩን ማወቅ እንድትችሉ
ምእራፍና ቁጥሩን ለብቻ አስቀምጥላችኋለሁ።
ሌላው ወንጌል ከተነበበ በኋላ የምናደርሰው ዜማ ሲሆን ይሄም እንደ ወንጌላዊው ይለያያል።የማቴዎስ፣የማርቆስ፣የሉቃስ እና
የዮሃንስ ወንጌሎች ከተነበቡ በኋላ የሚባለውን እንይ
//////////////////////////////////////////////
ክፍል አምስት
ርዕስ:-ኪርያላይሶን
ይህ የስግደት ስርአት ሲሆን ህዝቡ በመሪና በተመሪ ሆኖ እየተቀባበለ በማዜም የስግደት ስርአት የሚፈጸምበት የልመና ጸሎት
ስርአት ነው ።በዚህ የጸሎት ስርአት ውስጥ ስላሉ በአማርኛና በግእዝ ስለማናውቃቸው ቃላት ለመግለጽ ያክል:-
በግብረ ሕማማት መጽሐፍ ውስጥ ከዕብራይስጥ፣ ከቅብጥ እና ከግሪክ ቃላት የመጡና ወደ ሀገራችን ቋንቋ ሳይተረጎሙ ፣እንዳሉ
ለአገልግሎት የዋሉ ቃላት ይገኛሉ ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
1:-ኪርያላይሶን ከግሪክ የመጣ «ኪርዬ ኤሌይሶን»
«ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» ማለት «አቤቱ
ማረን»ማለት ነው።
2:-ናይናን ከቅብጥ የመጣ
ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
3:-እብኖዲ ከቅብጥ የመጣ
ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡
«እብኖዲ ናይናን»ማለት «አምላክ ሆይ ማረን»
4:-ታኦስ ከግሪክ የመጣ
ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡
«ታኦስ ናይናን» ማለት «ጌታ ሆይ ማረን»
5:-ማስያስ ከዕብራይስጥ የመጣ
ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡
«ማስያስ ናይናን»ማለት «መሲሕ ሆይ ማረን»
6:-ትስቡጣ «ዴስፓታ» ከግሪክ የመጣ
ትርጉሙ «ደግ ገዥ» ማለት ነው
ትስቡጣ ናይናን ማለት ደጉ ገዥ ሆይ ማረን።
ከዚህ በኋላ መሪው20 ጊዜ ተመሪው 21ጊዜ በአጠቃላይ 41 ጊዜ በጋራ ኪርያላይሶን እያልን እንሰግዳለን።
ይካ. ስለዚች ቦታ መጽናት በቅዱሳን አባቶቻችን ስም ስለሚጠሩም ቦታዎችና ገዳሞች በውስጣቸውም ስለመኖሩ ሽማግሎች
በጠቅላላም ስለዚህ አለም መጠበቅ ጸልዩ። ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ። የኛንም ኀጢአታችንን ያስተሰርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. በዚች ቦታና በሌሎች ቦታዎች ስለሚገኙ በነፍስ በስጋ ስለታመሙ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ጸልዩ። ጌታ ለኛም ለነርሱም
ሕይወቱን ጤንነቱን ሰጥቶ በጎ ነገርን ያደርግ ዘንድ ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. በባሕር በየብስ በወንዝ በቀላይ በሌላውም መንገድ ሁሉ ስለሚጓዙ አባቶቻችንንና ወንድሞቻችን ጸልዩ። ጌታ በቀና
መንገድ መርቶ በሰላም በደስታ ወደ መኖሪያቸው ይመልሳቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. ከእርሻ ስለሚገኝ ፍሬ ስለ ዛፎችና ስለ ወይኖች በአለምም ውስጥ ፍሬወን ስለምታፈራ ዕንጨት ሁሉ ጸልዩ። ጌታ ባርኮ
አብዝቶ ከጥፍትም ጠብቆ ለፍጻሜ ያደርሳቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. የክርስትያን እምነት ላልተፈፀመላቸው ወገኖቻችን ጸልዩ። ጌታ ይባርካቸው ዘንድ እስከ መጨረሻይቱም ሕቅታ በቀናች
ሃይማኖት ያጸናቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. ሐዋርያት ስላጸኗትና ስለሰበሰቧት ስለ አንዲት ቤተ ክርስትያን ሰላም ጸልዩ። ስለ ሕዝቡም ሁሉ መዳንን ስለ ቦታው ሁሉ
መጠበቅ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. ሊቀ ጳጳሳቱ አባታችን አቡነ ማትያስና ብፁዕ አባታችን አቡነ ሔኖክ በሕይወት በሞት በኑሮም ስለሚደርስባቸው ሁሉ
ጸልዩ። ሕይወታቸውን ጠብቆ ለብዙ ዘመን በመንበረ ስብከታቸው ያፀናቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ ።
ይካ. ምዕመናንን በየስፍራቸው ሁሉ በቸርነት ስለሚያስቡና ለበጎ ነገር ስለሚደክሙ የቀና ሃይማኖት ስላላቸው ሰዎች ሁሉ
ጸልዩ። ጌታ ባርኮ ዋጋቸውን እንዲሰጣቸውና ይቅርታን እንዲያደርግላቸው ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ ።
ይካ. ለቁርባን የሚሆን ስንዴውን ዕጣኑን ዘቢቡን የሚነበብባቸው መፃሕፍትን ሌላውንም የቤተ መቅደስ ዕቃ ሁሉ በመስጠት
ስለሚያስቡ ሰዎች ጸልዩ። ጌታ በመንግስተ ሰማያት የበለጠ ዋጋ ይሰጣቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. በደዌ ሥጋ በደዌ ነፍስ ለደከሙና ለተቸገሩ ለባልቴቲቱም አባት እናት ለሌላቸው ለድኆቹ ልጆችና ለተጨነቀችም ሰውነት
በማናቸውም ቦታ ሁሉ ጸልዩ። ጌታ ራርቶ ይቅር እንዲላቸው። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ
ይካ. በግዞት በምርኮኝነት ተይዘው ለተጨነቁ አገር ለቀው ለተሰደዱ በአጋንንት አሽክላም ለተያዙ ሰዎች ጸልዩ። ጌታ ከግዞት
ከምርኮኝነት ያወጣቸው ዘንድ፤ ይቅርታውንም ሰጥቶ እነርሱንም እኛንም ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ
ይካ.ለነፍሳቸው ይቅርታን እየፈለጉ ክቡር በሆነ በዚህ ስፍራ ስለተሰበሰቡት ሁሉ ጸልዩ። የአምላካችን የጌታችን ይቅርታ ፈጥኖ
ይደረግላቸው ዘንድ ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ ።
ይካ. በዚህ አመት ስለዝናም መዝነም ስለባህርና ስለወንዞችም መምላት ጸልዩ ። እውነተኛ አምላካችን ክርስቶስ በረከቱን ሰጥቶ
እስከ ልካቸው እንዲመላቸው ለምድርም ልምላሜዋን ሰጥቶ ደስ እንዲያሰኛት ሥጋዊን ሁሉ በረድኤት እንዲያፀና ለእንስሳትም
ሁሉ ድኅነትን እንዲሰጥ ጸልዩ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. በጸሎታችን እናስባቸው ዘንድ አስቡን አትርሱን ስላሉን ሰዎች ጸልዩ። እግዚአብሔር በበጎ ያስባቸው ዘንድ በየጊዜውም
ይቅር ይላቸው ዘንድ። የኛንም ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ ።
ይካ. ይህችን ሳምንት ጌታ በበጎ ይፈጽማት ዘንድ ከኛም የጠላትን መፈታተን አርቆ ሰውነታችንን እንዲያድን ይቅር እንዲለን
ጸልዩ። ኃጢአታችንን ያስተሥርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ።
ይካ. ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር እንዲለን ልመናችንንም ተቀብሎ ለዚያ ለፋሲካው እንዲያበቃን የትንሣኤውንም ብርሃን
በፍፁም ደስታ እንዲያሳየን ጸልዩ ኃጢአታችንን ያስተስርይልን።
ይሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ ።
====ሰላምታ ዘሠለስት====
ክርስቶስ ክርስቶስ ክርስቶስ አ ወ ለ ወ እ ተ ጋዳ ጋዳ ጋዳ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
ቅ ቅ ቅ አንተ ወልዳ ለማርያም ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ።
ሰላም ለኪ ማርያም ርግብ ሰማያዊት ሰላም ለኪ።
ወንስር መንፈሳዊት ሰላም ለኪ።
ሥምረተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መላኪ ሰላም ለኪ፡፡
እምትካት ዘኃረየኪ ሰላም ለኪ፡፡
ጊዜ ጸልዮትኪ በጽሐ ከመኢይሙት ገብርኪ።
ቅድሜሁ ስግዲ ወአስተብርኪ። እንዘ ታዘክሪዮ ፃማ ንግደትኪ። ርግብየ የዋሂት ለየዋህ ወልድኪ።
ስብሐት ለከ እዔምኅ አእጋሪከ በጊዜ ሰለስቱ ሰዓት ቅድመ ጲላጦስ ዘቆማ። ኢየሱስ ጠቢብ ወንጉሠ ፌማ። ዘአድክምከ
ኅይለ መስቴማ። ስብሐት ለከ። እንዘ ይሰልቡ ልብሰከ ወክዳነከ ፀዓዳ። እንተ አልበሱከ ከለሜዳ። ኢየሱስ ንጉሠ ይሁዳ።
ስብሐት ለከ።
ተፈፀመ ብከ እግዚኦ ቃለ ዳዊት ንጉሥ። ሶበ ተካፈሉ በእፃ ወፋስ። ልብስከ ልብሰ ሞገስ። ስብሐት ለከ።
ማህበራነ አይሁድ አሜሃ አዕጽምቲከ ኈለቁ። ወዲበ ገጽከ ምራቀ ወረቁ። ላእሌከ እንዘ ይሣለቁ። ስብሐት ለከ ።
እፎ መጦከ ዘባነከ ለጥብጣቤ መቅሠፍት መፅዕቅ። ገጽከኒ ተውክፈ ሐፍረተ ምራቅ። ዘአዕሩግ ወዘደቂቅ። ስብሐት ለከ።
አዕርግ ለነ እግዚኦ በጊዜ ፫ ሰዓት። ዘአቅረብነ ለከ መሥዋዕተ ስብሐት። ከመ ሠርዑ ሐዋርያት። ስብሐት ለከ።
ኀበ ሐዋርያት ኅብሩ በጽርሐ ጽዮን አንግልጋ። ዘፈኖከ ሎሙ መንፈሰ ጸጋ። ፈኑ ለነ እንበለ ንትጋ ያኀድገነ ምግባረ ዘሥጋ።
ሥሉስ ቅዱስ ጠበብት ፫ ሰዓት። አዳምሃ በሳድስ ዕለት። ዘፈጠርክሙ እንበለ ሞት። ግናይ ለክሙ።
ድኅረ ተፈጥሮቱ ለሰብእ በኈልቈ ዕለታት 40ዓ። እለ ታብእሉ ወታነድዩ ሰብአ። መጽሐፍ ከመ አይድዓ ግናይ ለክሙ።
ለሐዋርያት ሥላሴ በጊዜ ሰዓት ፫ቱ በልሳን 72 ሥላሴክሙ ዘትከሥቱ ግናይ ለክሙ።
ለጻላኤ ብርሃን ሰብአ ከመ ዘእኩይ ምግባር እለ ትኔጸሩ ወተአምሩ። ሥላሴ ዘትምሕሩ። ግናይ ለክሙ።
ድኅረ ስብኮ ላህም ዓቀመ በደብረ ኰሬብ መካን። ካህን አሮን ወምእመን። ዘመሐርክምዎ ለአሮን ካህን። መሐሩኒ ሥላሴ
ኄራን ግናይ ለክሙ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር በል ወጸሎተ ሃይ በል።
====ሰላምታ ዘቀትር=====
ሰላም ለኪ ማርያም ቡርክት በአፈ ኩሉ ፍጥረት። ታቦት አንቲ ዘሙሴ ጽላት። ዘሕግ ወዘ ሥርዓት። ሰላም ለኪ።
ገይበ ብሩር ጽሪት ወመቅድሐ ጽሩይ ኅሊብ። ማርያም መሶብ ዘመና ልሁብ። እንተ ፆርኪ ሲሳየ ሕዝብ። ሰላም ለኪ።
ትርሢተ ቤቱ ሠናይ ለነቢይ ሐጌ። ወወለት አንቲ ዘሰሎሞን ሐርጌ። ማርያም ዘመነ ጽጌ። ሰላም ለኪ።
እመ ቅድዉ በግዕ ዘቀተልዎ በግፍዕ። ወደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ ረድዕ። ማርያም ዘመነ ፍግዕ። ሰላም ለኪ።
ኦርያሬስ ሰማይ ልብስኪ ወአሳዕንኪ ዕብላ። ጽጌ ደንጐላት ቀይህ ዘምድረ ቈላ። ማርያም ዘመነ ተድላ። ሰላም ለኪ።
በመድበለ ማኅበር ጽፉቅ እዌድሰኪ በጻህቅ። ከመ ትምዓድኒ ነገራተ ጽድቅ። ማርያም ዘመነ እርቅ። ሰላም ለኪ።
ተደንግሎ ሥጋ ወነፍስ ለባሕቲትኪ ኮነ። እመኒ በጐል ወልድኪ ሕፃነ። ኢረስሐ ወኢማሰነ። ሰላም ለኪ።
እሙ በሊዮ በእንቲአየ ለፍሬ ከርሥኪ እምኖዲ። ላዕሌሁ ምሕረተ ኢታጐንዲ። እመ አኅዘንኪ ብእሲ አባዲ። ቤዛ ነፍሱ
ንጽሕየ እፈዲ።
ስብሐት ለከ ኦዘተፈኖከ ኢየሱስ ጻድቅ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት። እንዘ ኢትከውን አንተ ገባሬ እኪት። ከመ ትሥዓር ቀኖተ ሞት።
ስብሐት ለከ
እፎ ሰፋሕከ አዕዳዊከ ወተሰቀልከ በዕጸ። ዕፁተ ቀላያት ታርኁ አምሳለ አንቀጽ። ዘሰፋሕከ በብሔረ ግብፅ። ስብሐት ለከ
ፀሐይ ብሩህ አሜሃ ጊዜ ቀትር ፀልመ። ወወርኅኒ ጽዱል ተመሰለ ደመ። ትንቢት ከመ ቀደመ። ስብሐት ለከ
ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ። ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ። ተሰቀልከ ከመ ዐቡስ። ስብሐት ለከ
ኀዘነ ማርያም እምከ ነጺረከ ለዘታፈቅሮ ሐዋርያ። ትቤሎ እምከ ነያ። ከመ ትናዝዝ ብዝኃ ብካያ። ስብሐት ለከ
ዘሰአልከ ማየ እምነ ሣምራዊት ብእሲት። ከመ ትፈጽም ኩሎ ነገረ ትስብእት። እንዘ አንተ ማየ ሕይወት። ስብሐት ለከ
ሕጽረነ ወትረ እግዚኦ ለደቂቀ ዛቲ ማኅበር። በመስቀልከ መግረሬ ፀር። እምድድቅ ወእምጋኔነ። ቀትር። ወእምኩሉ ዘይመጽእ
ግብር።
ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ዕሩያነ አካል ወገጽ። ዘአስተራአይክሙ እንበለ ሕፀፅ። ጊዜ ቀትር በታህተ ዕፅ ግናይ ለክሙ።
ለንግስክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ። ቤተ ገብርክሙ እንዘ ትገይሡ። አጋእዝት ዘትሤለሱ። ግናይ ለክሙ።
በላእለ ማርያም ድንግል ሥላሴክሙ ተረክበ። በዮርዳኖስ ቅድመ ወበታቦር ካዕበ። ወንጌል ከመ ነበበ። ግናይ ለክሙ።
ለቤተ ክርስቲያን ሥላሴ አናቅጺሃ አንትሙ። ሱራፌልኒ በቅዳሴሆሙ። ይኤምሩ ግፃዌክሙ። ግናይ ለክሙ።
ፈጣርያነ ፀሐይ ወወርኀ አጋእዝትየ ሥላሴ። ዘነፀሩክሙ ኤልያስ ወሙሴ። በክብር ወበውዳሴ። ግናይ ለክሙ።
ጠፈረ ቤትክሙ ማይ ዘኀብሩ በረድ። የአኮቱክሙ ኀሩያን አንጋድ። በስኢል ወበሰጊድ። ግናይ ለክሙ።
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ፩ዱ ፫ቱ ። ዘተአንገድክሙ ኀበ ሐይመቱ። ለአብርሃም ጊዜ ዕብሬቱ። ግናይ ለክሙ።
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እምኔክሙ ፩ዱ። እንበለ ሩካቤ ወዘርእ እምድንግል ማኀፈዱ። ዘተወልደ በፈቃዱ። ግናይ
ለክሙ።
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ለዝክርክሙ ሕይወት። ሶበ ከናፍርየ እከሥት። ስመ ዚአክሙ በኩሉ ሰዓት። ይስማዕ
እምአፉየ ወይደንግፅ ሞት።
====ሰላምታ ፱ቱ ሰአት====
ሰላም ለኪ ማርያም እክል መጽንዒት ኃይል ቅቡዓ ብርሃኑ ለገጽ ሰላም ለኪ። ስቴ ወይን ዘነፈርዓዕ ሠርጐ ክብር ወአራዝ
ሰላም ለኪ።
ወመቅደስ ቤተ ትእዛዝ ለአሣዕንኪ ወርኅ ሰላም ለኪ።
ወለአክሊልኪ ጐሐ ጽባህ ሰላም ለኪ።
ደመና ዝናም ንጽሕት ሰላም ለኪ።
ዘይከውን ለቅድሳት ሰላም ለኪ።
ደብረ መድሃኒቱ ለኖህ ሰላም ለኪ።
ዘአድኃንኪዮ እማየ አይኅ ሰላም ለኪ።
ሐይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ ።
ዘኮንኪዮ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ።
ቤዛዊተ ኵሉ አለም ሰላም ለኪ።
ሰፋኒት በአርያም ሰላም ለኪ።
ወለተ ኢያቄም ወሐና ሰላም ለኪ።
ሥርጉት በቅድስና ሰላም ለኪ።
ያስምዓኒ ቃለ ፍሥሐ ጊዜ አኃዝን ወአስቈቁ
ሣህልኪ ይምጻእ እምሥራቁ ለእሳት ኃዘን እስከነ ይቈርር ሞቁ ማርያም ለኃጥእ ጽድቁ
ስብሐተ ለከ አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ወትረ ወኢትኅድገኒ ዘልፈ እስመ አንተ ትቤ እንዘ ትከስት አፈ ከመ ትፈፅም ሕገ
ዘተጽሕፈ ስብሐት ለከ።
ጊዜ ትወጽእ ነፍስከ እስከ ይሰማዕ ኲለሄ ኦ ዘትቤ ኤሎሄ ኤሎሄ ኢየሱስ አምላከ ርኅራኄ ስብሐት ለከ።
ከመ ታስትየነ ለነ ደመ ገቦከ ነባቤ እንተ አስተዩከ ሐሞተ ወከርቤ ጸማዕኩ በጊዜ ትቤ ስብሐት ለከ።
ድኅረ ሰለጥከ መዊተ በመልዕልተ መስቀል ዐልቦ እንዘ ኃጢአት ላዕሌከ አልቦ ኢየሱስ ርጉዘ ገቦ ስብሐት ለከ።
ስታየ ጽሙጓን ይኩን ወዘያረስዕ ትካዘ ማይ ምስለ ደመ ውኅዘ ገቦከ ጊዜ ተረግዘ ስብሐት ለከ።
ኖላዊነ ኄር ወዐቃቢነ ጽኑዕ እንተ ተሰቀልከ መልዕልተ ምሥዋዕ ኢየሱስ ቤዛ አባግዕ ስብሐት ለከ።
ተወከፍ ሊተ እግዚኦ ከመ ቁርባን ጥሉል በበሱባዔ እንዘ እከፍል ዘአቅረብኩ ለከ ኊልቈ ኢዮቤል ስብሐታተ ከመ አንሰ እክል
ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ጠበብተ ፯ቱ አብያት እለ በላዕክሙ ውሣጤ ሐይመት ፩ደ ኅብስተ ትሥልስት ግናይ ለክሙ።
ድኀረ በላዕክሙ ላህመ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም።ዘበኃይልክሙ ሐይወ ላህም ።ሥላሴ ክቡራነ ስም ግናይ ለክሙ ።
ዘኢትቀሥፉ ወትረ ወኢትትመዓዑ ዘልፈ።እንዘ ሰብእ ይገብር ኃጣውአ እልፈ። በመፅሐፍ ከመ ተጽሕፈ ግናይ ለክሙ።
ከመ ባሕር ስፉሕ ወከመ እሳት ፅዱል ዘሀለ ወክሙ ትስልስተ አካል።ሥላሴ ዕደወ ኃይል ግናይ ለክሙ ።
ድኅረ ልቡናሁ ጼወወ ፍቅረ አሐቲ ብእሲት። ለዘወጽአ ረድዕ እምሃይማኖት።ዘመሐርክምዎ በ፳ዕለት መሐሩኒ ሥላሴ
ነገሥት።
ስብሓት ለእግዚአብሔር ወጸሎተ ሃይማኖት በል።