Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 5

1.

መግቢያ

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት በየዓመቱ የዓለም አክሬዲቴሽን ቀን በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት


በማክበር አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ተደራሽነቱ ለማሰፋት ከሚጠቀምባቸው አመራጮች መካከል አንዱ
በመሆን በልዩ ትኩረት ሲሰራበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ስራ በርካታ ውጤቶች ተመዝግቧል፡፡ ከባለድርሻ
አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የምርትና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ይህንን በውል የተረዳው የአገልግሎቱ የበላይ አመራር የ 2016 በጀት ዓመት “Accreditation: empowering
Tomorrow and Shaping the Future” በሚል ቃል ሰኔ 2 (June 9) የሚከበረው የዓለም አክሬዲቴሽን ቀን
በድምቀት እንደከበር በመወሰን፤ ይህንን ተግባር የሚመራ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡ የተቋቋመውም ኮሚቴ
እንደታሰበው በዓሉን በድምቀት ለማክበር እንደቻል አቅድ በማዘጋጀት፣ ግብዓት በማሰባሰብና በማዳበር
ተግባራት ሳይነጠባጠቡ በአግባቡ እንዲተገበሩ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህም ዕቅድ በውስጡ ዓላማ፣
የሚጠበቁ ውጤቶች፣ የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት፣ በዓሉን ለማክበር የሚያስፈልግ በጀት፣
የሚከናወኑተግባራት መርሃ-ግብር፣ የክትትልና ድጋፍ አግባብ እና የንዑሳን ኮሚቴ አደረጃጀት ተካቶ ቀርቧል፡፡

2. ዓላማ

የዓለም አክሬዲቴሽን ቀን በዓል በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት በማክበር በሂደቱም ከባለድርሻ አካላት ጋር
ተቀናጅቶ መስራት የሚያስችል ስርዓት ማጠናከር፣ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተለያዩ ሚዲያዎች
ማስተዋወቅ፣ ተደራሽነትን ማስፋት እና የምርትና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል አስተዋጾ ለማበርከት ነው፡፡

3. የሚጠበቁ ውጤቶች
 ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ስሜት ተሳትፈዋል፤
 ቅንጅታዊ አሰራር ተገንብቷል፣
 በዓሉን በድምቀት ተከብሯል፣
 የወቅቱን WAD ቴም ያማከለ የመያያ አጀንዳ ቀርቦ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ተፈጥሯል።
 የሚሰጡ የአክሬዲቴሽን አገልግሎቶች ተዋውቀዋል፣
 የምርትና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡

4. የሚከናወኑ ተግባራት
1) የኮሚቴ ዕቅድ ማዘጋጀትና አጸድቆ ወደ ስራ መግባት፤
2) የህዝብ ግንኙነት፣ ስፖንሰር ፈላጊ፣ የፋይናንስና ሎጀስቲክ፣ የመድረክ ዝግጅትና መስተንግዶ ንዑሳን
ኮሚቴዎችን ማቋቋም፤
3) ለንዑሳን ኮሚቴ አባላት ማሳወቅና ኦረንቴሽን መስጠት፤
4) ለበዓሉ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መለየትና ስፖንሰር ማፈላለግ፤
5) ሚዲያዎችን በመለየት፣ ተያያዥ ስራዎችን በማከናወን ከበዓል በፊት፣ የበዓሉ ዕለት እና ከበዓሉ በኋላ
የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ማከናወን፤
6) የሚያስፈልጉ የአገልግሎቶችና ቁሶችን በመለየት ግዥ መፈጸም፤
7) በዓል ማክበሪያ ቦታዎችንና አዳራሾችን መለየትና በዓሉን በሚያጎላ መልኩ ማዘጋጀት፤
8) የበዓሉ ታዳሚዎችን መለየት፣ ጥሪ ማስተላለፍና እንዲገኙ ክትትል ማድረግ፤
9) ፓናሊስቶችን መለየትና እንዲዘጋጁ ማድረግ፤
10) ባነርና ሌሎች ህትመቶችና ማዘጋጀት፤
11) በዓሉን አስመልክቶ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ከአገኙ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት መካከል
በመለየት ለጉብኝት ማዘጋጀትና መጎብኘት፤
12) በዓሉን በድምቀት ማክበር፤
13) አፈጻጸሙን መገምገም፣ ሪፖርት በማዘጋጀት ማቅረብና የምስጋና ፕሮግራም ማዘጋጀት ናቸው፡፡

5. በዓሉን ለማክበር የሚያስፈልግ በጀት

ተ.ቁ ተግባራት መጠን የአንዱ ዋጋ ድምር

1 ለማስታወቂያ ማስነገሪያ

2 ለህትመት

3 ለጋዜጠኞች አበል

4 ለምግብና ለመጠጥ

5 ለአዳራሽ ኪራይ

6 ለሪፍረሽመንት

7 ለፓናሊስት ክፍያ

6. የሚከናወኑ ተግባራት መርሃ-ግብር

የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር የሚከናወንበት ጊዜ ፈጻሚ አካል

1) የኮሚቴ ዕቅድ ማዘጋጀትና አጸድቆ ወደ ስራ መግባት፤ እስከ ግንቦት 2/16 ኮሚቴው


2) የህዝብ ግንኙነት፣ ስፖንሰር ፈላጊና ገቢ አሰባሳቢ፣ የፋይናንስና ሎጀስቲክ፣ ግንቦት 2/2016
የመድረክ ዝግጅትና መስተንግዶ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋም፤
3) ለንዑሳን ኮሚቴ አባላት ማሳወቅና ኦረንቴሽን መስጠት፤ ግንቦት 5/2016

4) ለበዓሉ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መለየትና ስፖንሰር ማፈላለግ፤ ከግንቦት 5-19/2016 የሰፖንስርሺፕ ን/ኮሚቴ

5) መዲያዎችን በመለየት፣ ተያያዥ ስራዎችን በማከናወን ከበዓል በፊት፣ ከግንቦት 2 እስከ ሰኔ የህዝብ ግ/ን/ኮሚቴ

የበዓሉ ዕለት እና ከበዓሉ በኋላ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ማከናወን፤ 15/2016

6) የሚያስፈልጉ የአገልግሎቶችና ቁሶችን በመለየት ግዥ መፈጸም፤ ከግንቦት 8-30/2016 የፋይናንስና ሎጀስቲክ


ን/ኮሚቴ

7) በዓል ማክበሪያ ቦታዎችንና አዳራሾችን መለየትና በዓሉን በሚያጎላ መልኩ ከግንቦት 15-30/2016 የመድረክ ዝግጅትና
መስተንግዶ ን/ኮሚቴ
ማዘጋጀት፤
8) የበዓሉ ታዳሚዎችን መለየት፣ ጥሪ ማስተላለፍና እንዲገኙ ክትትል ከግንቦት 5-30/2016 የህዝብ ግ/ን/ኮሚቴ

ማድረግ፤
9) ፓናሊስቶችን መለየትና እንዲዘጋጁ ማድረግ፤ ከግንቦት 5-9/2016

10) ባነርና ሌሎች ህትመቶችና ማዘጋጀት፤ ከግንቦት 15-30/2016

11) በዓሉን አስመልክቶ የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ከአገኙ የተስማሚነት ምዘና ከግንቦት 15-30/2016

ተቋማት መካከል በመለየት ለጉብኝት ማዘጋጀትና መጎብኘት፤


12) በዓሉን በድምቀት ማክበር፤ ሰኔ 2/2016 ኮሚቴው

13) አፈጻጸሙን መገምገም፣ ሪፖርት በማዘጋጀት ማቅረብና የምስጋና ሰኔ 3/2016


ፕሮግራም ማዘጋጀት፤

7. የክትትልና ግምገማ ሂደት


1. በ 2 ቀን አንዴ ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የክትትል ግምገማ ማካሄድ፤
2. የዝግጅት፣ የትግበራ እና ማጠቃለያ ሪፖርት በማዘጋጀት ማቅረብ፤
3. የተሰጡ ግብረ-መልሶችን በመጠቀም ማሰተካከያ እርምጃ መወሰድ ናቸው፡፡

8. ንዑሳን ኮሚቴዎች እና አባላት


1) የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ
1.1. አቶ አክሊሉ ጌታቸው ሰብሳቢ
1.2. አቶ ሰለሞን ፍስሃ አባል
1.3. ወ/ሮ አዜብ ሰለሞን አባል
2) ስፖንሰር ፈላጊና ገቢ አሰባሳቢ ንዑስ ኮሚቴ
2.1. አቶ ዘውዱ ገ/ሚካኤል ሰብሳቢ
2.2. አቶ ታምራት ኤሬንሶ አባል
2.3. አቶ ጌቴ ብርሃን አባል
2.4. ወ/ሪት ሰናይት አባተ አባል
3) የፋይናንስና ሎጀስቲክ ንዑስ ኮሚቴ
3.1. ወ/ሮ አበበች ታደሰ ሰብሰቢ
3.2. አቶ ዋለልኝ አድማሱ አባል
3.3. ወ/ሮ ቤተልሔም ባዩ አባል
4) የመድረክ ዝግጅትና መስተንግዶ ንዑስ ኮሚቴ
4.1. አቶ ዘውዱ አየለ ሰብሳቢ
4.2. አቶ መሰረት ንጉሴ አባል
4.3. አቶ ወ/ሮ ጌጡ መንጀግሶ አባል ናቸው፡፡

You might also like