Professional Documents
Culture Documents
Human Trafficking Guide Am
Human Trafficking Guide Am
መረጃ መመሪያ
ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ምንድን ነው?
ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚከሰተው አንድ ሰው የሌላን ሰው ጉልበት ወይም ፆታን ለሌላ ሰው ጥቅም ሲቆጣጠር
ነው። በሚኒሶታ ህግ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በማንኛውም መንገድ ሊከሰት ይችላል። በፌደራል ህግ፣ ሕገወጥ የሰዎች
ዝውውር ተጠቂው ስራ ወይም የወሲብ ንግድ አገልግሎቶችን እንዲያከናውን ኃይልን፣ ማታለልን ወይም ማስገደድን
መጠቀም ይጠይቃል። የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች በተለያዩ ምክንያቶች ካሉበት ሁኔታዎች መውጣት
አይችሉም።
የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን ለመቆጣጠር፣ አዘዋዋሪዎቹ በርካታ የተለያዩ ዘዴዎችን ሊጠቀሙ
ይችላሉ፣ የሚከተሉትን ጨምሮ ነገር ግን በዚህ ሳይወስን፡
• ማስፈራራት • ልዩ መብትና የበላይነት
• ማስገደድ እና መቅጣት • የኢኮኖሚ ጥቃት
• ጥቃት (ስሜታዊ ፣ አካላዊ ፣ ወሲባዊ) • ለተጠቂ ቤተሰብ የሚያሳዩት የኃላፊነት ስሜት
• ማግለል • ሰነዶች መከልከል
• መካድ፣ መወንጀል እና ማቃለል
የሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ሙሉ በሙሉ ለይቶ የሚያሳውቅ አንድም ምልክት የለም።
በጣም አስፈላጊው ነገር ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች
ላይ ቁጥጥር የሚደረግበትን አካሄድ መመልከት ነው
ብዝበዛ ምንድነው?
ብዝበዛ የሚከሰተው አንድ ሰው ሌላን ሰውን ያለአግባብ ከሚሰሩት ስራ ጥቅምን ለማግኘት በደል በሚፈጽምበት ጊዜ ነው።
በጥቃት እድራሹና በተጠቂው መካከል እኩል ያልሆነ የኃይል ሚዛን አለ፣ በዝባዡ የኃይል ሚዛኑን ይዟል። ብዝበዛ በአጠቃላይ
በነፃነት እና በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደ መካከለኛ መታየት ይችላል። እነዚህ ሁኔታዎች ተደራራቢ ሲሆኑ እንዲሁም
ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜያት በነጻነትና በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መካከል በተለያዩ የተሞክሮ ሁኔታዎችን ያልፋሉ።
የወሲብ ንግድ ብዝበዛ የሚከሰተው አንድ ሰው ወሲብን በማንኛውም ዋጋ ወይም ዋጋ ያለው ቃል የተገባ ነገር እንደ
ገንዘብ ፣ አደንዛዥ ዕፅ ፣ ምግብ ፣ መጠለያ ፣ ኪራይ ፣ ወይም በቡድን ውስጥ ከፍ ያለ ቦታን በመሳሰሉ ነገሮች ሲለውጥ
ነው። የጉልበት ብዝበዛ ሠራተኞችን አግባብ ባልሆኑ የጉልበት ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን እንዲሁም ክፍያ መከልከል
ወይም ለሠራተኛ ደመወዝ አለመክፈል፣ ወይም የደመወዝ ክፍያ ዝርፊያ (በህግ ወይም በውል ቃል የተገባን ደመወዝ፣
ትርፍ ሰዓት ጨምሮ መከልከልን) ሊያካትት ይችላል።
ግብዓቶች
• Minnesota Safe Harbor (https://www.health.state.mn.us/communities/safeharbor/index.html)
• የMinnesota የአደጋ የመጀመሪያ የቀጥታ መስመር - 866-223-1111