Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 20

በቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት

የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን


የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ

ነሀሴ 2015 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ማውጫ

1
መግቢያ.............……………………………………………………………………………………..3
ክፍል አንድ….........................................................................................................................................3
የ 2015 በጀት ዓመት ዕቅድ መነሻ ሁኔታዎች..................................................................................................4
ክፍል ሁለት..........................................................................................................................................6
የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ፤ ዕሴቶች፣ ራዕይ፣ ስትራቴጂክ ግቦች...................................................................................6
ክፍል ሶስት...........……………………………………………………………………………………8
የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ.......................................................................................................................8
ክፍል አራት........................................................................................................................................16
የቡድኑ የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች፣……………….............16
ክፍል አምስት……………………………………………………………………16
ለቡድኑ ለ 2016 እቅድ ማስፈጸሚያ በጀት……………………………………………………16

ክፍል ስድስት......................................................................................................................................17
ስጋቶችና የሚወሰዱ እርምጃዎች …………………………………………………………… 17
ክፍል ሰባት.........……………………………………………………………………………………17
ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ድጋፍ የሚጠይቁ ጉዳዮች.......................................................................................17
ክፍል ስምንት......................................................................................................................................18
የክትትልና ግምገማ ዕቅድ........................................................................................................................18
ክፍል ዘጠኝ
የ 2016 በጀት ዓመት እቅድ ድርጊት መርሀ ግብር …………………………………… 20

2
መግቢያ
የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት ተጠሪ ከሆኑ ቡድኖች አንዱ ሲሆን የተሰጠውን ተልኮ
ለመወጣት ቡድኑ ከቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት የተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች በስሩ የሚገኙ ሠራተኞች በማሰተባበር
ለቅርንጫፉ የሚያስፈልገውን የዕቃና አገልግሎት በሚሰጠው ውክልእና በመንግስት የግዢ መመሪያ ለስራው
የሚያሰፈልገውን በጀት እና እቅድ አዘጋጅቶ በማፀደቅ መግዛት አና የኮርፖሪሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደሪያ መመሪያ
መሰረት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ የማሟላት፣የማስተዳደር እና የማሰራጨት ኃላፊነቶች ያሉበት ሲሆን የግዥና
ንብረት አስተዳደር ስራዎች በመንግስት አሰራር መሰረት ይፈጽማል፡፡

ቡድኑ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሠጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የ 2016 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ዕቅድ ከቅርንጫፍ
አንድ ጽ/ቤት ከተዘጋጀው መነሻ ዓመታዊ የውጤት ተኮር እቅድ ካስኬድ በማድረግ የ 2016 በጀት ዓመት
የቅርንጫፉን የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውጤት ተኮር ዕቅድ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር የተዘጋጀ
ነው፡፡

የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዘጠኝ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በክፍል አንድ የዕቅዱ
መነሻ ሁኔታዎች፣ በክፍል ሁለት የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ፣ ራዕይና ዓላማ፣ የእቅዱ አፈፃፀም አቅጣጫዎች፣
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ውጤቶች እንዲሁም ስትራቴጂያዊ ግቦች ተቀምጠዋል፡፡ በክፍል ሦስት
የ 2016 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ዕቅድ ታሳቢዎችና ምቹ ሁኔታዎች፣ስትራቴጂክና ኦፕሬሽናል ግቦች እና ዋና
ዋና ተግባራት፤ በክፍል አራት የቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት የ 2016 በጀት ዓመት የአፈፃፀም አቅጣጫዎች፣ በክፍል
አምስት ለቡድኑ የታቀደ በጀት፣ በክፍል ስድስት የዕቅዱ ስጋቶችና ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች፣ በክፍል
ሰባት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚጠበቁ ድጋፎች እና በክፍል ስምንት የክትትልና ግምገማ ዕቅድ ክፍል ዘጠኝ የቡድኑ
እቅድ መርሃ ግብር ተካተው ቀርቧል፡፡

ክፍል አንድ
የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ መነሻ ሁኔታዎች
1.1 የ 2016 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተግባርና ኃላፊነት እንደመነሻ

የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ከቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት የተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶች በስሩ የሚገኙ
ሠራተኞች የማሰተባበር ለቅርንጫፉ የሚያስፈልገውን የዕቃና አገልግሎት በሚሰጠው ውክልና በመንግስት

3
የግዢ መመሪያ ለስራው የሚያሰፈልገውን በጀት እና እቅድ አዘጋጅቶ በማፀደቅ አና የኮርፖሪሽኑ ግዥና
ንብረት አስተዳደሪያ መመሪያ መሰረት የማሟላት ኃላፊነቶች ያሉበት ሲሆን የግዥና ንብረት አስተዳደር
ስራዎች በመንግስት አሰራር መሰረት ይፈፅማል በስሩ ያሉትን ፈሚዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት
ይገመግማል፣ድጋፍና ክትትል በማድረግ ግብረመልስ የመስጠት ሲሆን ይህን ተግባርና ኃላፊነት የቅርንጫፉ
የ 2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት እንደመነሻ ተወስዷል፡፡

1.2 የቡድኑ የ 2015 እቅድ አፈፃፀም እንደ መነሻ


በቡድኑ ስር የሚገኙ የሰው ኃይል፣ አሠራርና አደረጃጀት በመፍጠር አገልግሎት የመስጠት አቅሙን
በማሳደግ የቅርንጫፉን አገልግሎት አሰጣጥ ሊያሻሽልና ውጤታማ ሊያደርግ የሚያስችል ግልጽነትና
ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬሽኑ ሀብትና ንብረት ከብክነት የፀዳ እንዲሆን
የማስቻል፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር፣ መረጃ አያያዝና አጠባበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ
እንዲሆን በማድረግ ውጤታማና ቀልጣፋ የሆነ የግዥና ንብረት አቅርቦቱን ወቅታዊ በማድረግ
የአገልግሎት ደረጃ በማሳደግ የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ ነው፡፡

1.3 የቡድኑ ሠራተኛ ሁኔታ


ሠራተኛ በ 2015 በጀት አመት ስራውን በተረጋጋ ሁኔታ ማከናወን ችሏል፡፡ ይህም ኢንዱስትሪያዊ ሰላሙ
ከቀድሞው ጊዜ ይልቅ እየተሻሻለ እና ከአመራሩ ጋር በመቀራረብ ቀና የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ያስቻለ ነው፡፡
ይህ ማለት ሙሉ ለሙሉ ሠራተኛው ወደሚፈለገው ደረጃ ደርሷል ማለት አይደለም፡፡ በአንዳንድ ሠራተኞች
ላይ የሚንጸባረቁ የስነ ምግባር ችግሮች፣ በክፍተትነት የምንወስዳቸውና በ 2016 ልናርማቸው የሚገቡ
ድክመቶቻቸችን ናቸው፡፡ በመሆኑም በ 2016 በጀት አመት የቡድኑ ስራ በተሻለ ሁኔታ ለመፈጸም ጠንካራ
የስራ ባህል ሊኖረን፣ የተሰጠንን ተልእኮ በብቃት እና ስነምግባር በተሞላበት፣ በዲሲፒሊን እና በቡድን መንፈስ
እንዲሁም የመንግስትን የስራ ሰአት ለመንግስት ስራ ብቻ በማዋል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ሀላፊነት
ለመወጣት ዋነኛ ባለድርሻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህም ሰራተኛው በዲሲፒሊን ታንጾ የእለት ተእለት
ስራዎችን በብቃት እንዲወጣ የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል ከማድረግ ይጠበቃል፡፡

1.4 የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዋና ተግባርና ሃላፊነት

 የቡድኑን በጀት እና ዕቅድ ያዘጋጃል፣


 ለቅርንጫፉ የሚያስፈልገውን የዕቃና አገልግሎት በሚሰጠው ውክልና በመንግስት የግዢ መመሪያ መሰረት
ይፈጽማል፣
 ንብረት አስተዳደሪያ መመሪያ መሰረት ንብረቶችን ያስተዳድራል ያሰራጫል፣

4
 የቋሚና አላቂ እቃዎች ንብረት ቆጠራ ያከናውናል፣
 የሚወገዱ ንብረቶችን ያስወግዳል፣
 አፈፃፀሙን ይገመግማል፣ የአፈፃፀም ሪፖርት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ያቀርባል፣
1.5 የውስጥ አሰራር ዕይታ አፈጻጸም፣
ከግዥ አኳያ በማእከል እና በቅርንጫፍ ግዥዎች ተፈጽመው ለስራ እንዲውሉ ሲደረግ የንብረት አስተዳደር
ስራዎችም ያከናውናል፡፡

ከ 2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ትምህርት ሊወሰድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች/Lessons Learnt/፣

 ሁሉም ለጋራ አላማ እንዲቆም የማድረግ ስራ በበላይ አመራሩ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራ በቅርንጫፉም ውጤታማ
የኢንዱስትሪ ሰላም ማስፈን መቻሉ፡፡
 ጠንካራ የክትትል እና የድጋፍ ስርአት በመዘርጋት እና ስራ ላይ በማዋሉ በእቅዱ እና ከእቅዱ በላይ እንዲፈጽሙ ማድረግ
መቻሉ፣
 በኮርፖሬሽኑ እጅ ያልነበሩ እና ከኮርፖሬሽኑ እጅ የወጡ በርካታ ቤቶችን እና ይዞታዎችን ወደ ኮርፖሬሽኑ በመመለስ
የቅርንጫፉን ሀብት ከብክነት እንዲጠበቅ መደረጉና በፍርድ ቤት የማሸነፍ አቅም እየጎለበተ መሆኑ ፣
 በደንበኞች ተሳትፎ የጥገና ስራ በስፋት መሰራቱ
 ከደንበኞች ጋር በተቀናጀ ሁኔታ የመስራት ባህል እየጎለበተ መሆኑ፣
ክፍል ሁለት
የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ፤ ዕሴቶች፣ ራዕይ፣ ስትራቴጂክ ግቦች
2.1 ተልዕኮ፣
ለኮርፖሬሽኑ ደንበኞች ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በተመጣጣኝ የኪራይ ዋጋ በማቅረብና በማስተዳደር በቤት ፍላጎትና
አቅርቦት መካከል የሚታየውን የገበያ ጉድለት በማሟላት ሂደት አስተዋጽዖ ማድረግና ተወዳዳሪና አትራፊ መሆን፡፡

2.2 ዕሴቶች

ታማኝነት (Integrity) ኃላፊነታችንን በመወጣት ሂደት ወጥና ተቀባይነት ያለው አቀራረብ ይኖረናል

ውጤታማነት (efficiency) የምንሰጠውን አገልግሎት በዕውቀት የተመሰረተና በወቅቱ በመስጠት


ደንበኞቻችንን እናረካለን

ፍትሃዊነት (Fairness) የምንሰጠው አገልግልግሎት ያለአድሎ እናቀርባለን

ግልጽነት (Transparency) ኮርፖሬሽኑ የሚሰጠውን አገልግሎት በተመለከተ ትክክለኛ፣ ወቅታዊና


የተሟላ መረጃ እንሰጣለን

የቡድን ሥራ (Team Work) የኮርፖሬሽኑን ግቦች ለማሳካት በቡድን እንሰራለን

5
ፕሮፌሽናሊዝም (Professionalism) ስራዎቻችንን ግብረገብነት በተሞላውና ጥራትና ስታንዳርድ የጠበቀ እንዲሆን
እናደርጋለን

2.3 ራዕይ
በ 2030 በቤት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ኮርፖሬት ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

2.4 ዕይታዎችና ስትራቴጂክ ግቦች፣

ዕይታ ስትራቴጂክ ግቦች ክብደት


የፋይናንስ ዕይታ 1. ትርፋማነት ማሳደግ 5%

2. የፋይናንስ አስተዳደርን ማሻሻል 5%

የተገልጋይ ዕይታ 4.የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ 20%

የውስጥ አስራር ዕይታ 58.የኮርፖሬት አሰራር ማሻሻል 58%

9.ቅንጅታዊ ስራዎችን ማሻሻል 2%

መማማርና ዕድገት ዕይታ 10.የሰው ሀብት አቅም ግንባታና አስተዳደርን ማሻሻል 8%

11.የቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ 2%

2.5 የአፈጻጸም አቅጣጫዎች

 አገልግሎትን አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ማደረግ፣


 ግዥዎችን በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በወቅቱ በመግዛት ለስራ ማዋል፣
 የንብረት አስተዳደር ስርአቱን ተጠያቂነት ያለው እና ብክንትን በመከላከል እንዲፈጸም ማድረግ፣

6
 በቡድኑ ያለውን የሰው ኃይል በአግባቡ እና ስነምግባራዊ እሴትን በጠበቀ ሁኔታ ስራ ላይ እንዲውል
ማድረግ

7
ክፍል ሶስት
የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም አቅጣጫዎች
3.1 ታሳቢዎች
 ለቅርንጫፉ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብአቶች በወቅቱ ተሟልቶ የሚቀርብ መሆኑ፣
 ሠራተኛው በሙሉ ተነሳሽት እና አቅም የተሰጠውን ተልእኮ የሚፈጽ መሆኑ፣
 የበላይ አመራ እና የዘርፍ አመራር የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚኖር፣
 የኮንስትራክሽን ግብዓት ዋጋ በአንጻራዊ እየተረጋጋ እንደሚሄድ፣
 የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት እንደሚሻሻል
 የጥሬ ዕቃ አቅርቦት በተጠበቀው ልክ ሊሆን እንደሚችል፣
 የፋይናንስ አቅርቦት በተጠበቀው ልክ ሊሆን እንደሚችል፣
 ገበያው እየተረጋጋ እንደሚሄድ፣
 የገበያው የግንባታ ጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት እንደሚሻሻል፣
 የሰው ሀይል አቅርቦት እንደሚጠበቀው እንደሚሆን፣
 IFMIS ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ፣
 ወዘተ.
3.2 ምቹ ሁኔታዎች

 የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ተነሳሽነት እየዳበረ መምጣቱ፣

 የህግ ማእቀፎች ያሉንና በየጊዜው እየተዘጋጁ መሆኑ፣

 ኮርፖሬሽኑ የሚያበረታታ የለውጥ መስመር መያዙ፣

 የኮርፖሬሽኑ ገቢ እየጨመረ መምጣቱ፣

 የስራ አመራር ቦርድ እና የተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የቅርብ ድጋፍና የተቋሙን

ዐቅም ለማሳደግ ቁርጠኝነት መኖሩ፣

 የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ለማሻሻል የሚስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩ

 መንግሥት የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን

በመፍታት የተሳለጠ አገልግሎት አሰጣጥን ለማስፈን ያለው ቁርጠኝነት፣

 በተቋሙ የኢንደስትሪ ሰላም መስፈኑ፣

8
 ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት የተጀመረው ሥራ በተሻለ

.ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑ፣

 የኢንቲግሬትድ ማናጅመንት ኢንፎርሜሽ ሲስተም ሥራ ላይ እንደሚውል፣

3.3 የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ


I. የፋይናንስ ዕይታ (10%)
ስትራቴጂክ ግብ 1፡-ትርፋማነትን ማሳደግ (5%)
I.

ኦፕ.ግብ 1.2.፡- ወጪ ቆጣቢ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ወጪ መቀነሰ (5%)

ተግባር፡-1.2.2. የነዳጅ፣ የስልክ፣ የአሌትሪክ፣ የህትመት፣ የስቴሽነሪና

የትርፍ ሰዓት ወጪን በዕቅድ መምራት፣


ተግባር፡-1.2.3. የሥራ ማስኬጃና አስተዳደራዊ ወጪዎችን መቀነስ
ተግባር፡-.1.2.4. የወጪ ቆጣቢ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ፤

ተግባር፡-1.2.5 የወጪ አጠቃቀምና የሀብት አስተዳደር በተዘረጋው የአሰራር ስርዓትና በኮርፖ

ሬሽኑ መመሪያዎች መሰረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ

ስትራቴጂክ ግብ 3፡- የፋይናንስ አስተዳደርን ማሻሻል (5%)


ኦፕ.ግብ 3.2፡- ተዘጋጅቶ የቀረበ በጀት (3%)

ተግባር፡3.2.1. የቡድኑን ዓመታዊ በጀት ማዘጋጀት፣

ኦፕ.ግብ- 3.5 ኦዲት በተደረጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ላይ የተሰጡ አሉታዊ አስተያየቶችን

በማረም የተሻለ የኦዲት አስተያየት እንዲገኝ ማድረግ (2%)

ተግባር፡-3.51 የተሰጡ የኦዲት አስተያየቶችበዝርዝር በመውሰድ እንዲስተካከል


ማድረግ፣

II.የተገልጋይ ዕይታ(20%)

ስትራቴጂክ ግብ 4፡- የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ (20%)


ኦፕ.ግብ 4.1፣ በውስጥ ደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና የአገልግሎት ጥያቄዎችን በመመሪያውና

በአሠራር ሥርዓቱ በወቅቱ ምላሽ ያገኘና የተፈጠረ የደንበኞች እርካታ ፤ (9%)

9
ተግባር፡-4.1.1 በውስጥ ደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል በወቅቱ ምላሽ መስጠት

ተግባር፡-4.1.2 በውስጥ ደንበኞች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል፣

ተግባር፡-4.1.3 በቡድኑ የውስጥ ከደንበኞች ጋር የተደረጉ ውይይቶችን እና የተወሰዱ እርምጃዎችንና

ማስተካከያዎችን መገምገምና ግብረ መልስ መስጠት፤


ተግባር፡-4.1.4 የተስተናገዱ የውስጥ ደንበኞች 1500

ኦፕ.ግብ 4.2.፣ በዜጎች ቻርተር እና የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ማንዋል ላይ በተቀመጡ


ስታንዳርዶች መሠረት የተሰጠ አገልግሎት፣ (3%)
ተግባር 4.2.1. በቡድኑ የሚሰጡ አገልግሎቶች በቻርተሩ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ፤

ተግባር፡-4.2.2. በስታንዳርዱ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ለሚመለከተው የሥራ ክፍል

መላክ፤

ተግባር፡-4.2.3 በቡድኑ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በቅሬታ አቀራረብና አፈታት ማንዋሉ መሰረት

መሆኑን ማረጋገጥ ፣

ኦፕ.ግብ 4.3. የውስጥ ደንበኞች እርካታን በ 2016 በጀት ዓመት ከ 85% ወደ 93% ማድረስ፤(8%)

ተግባር፡ -4.3.1 በደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል በወቅቱ ምላሽ መስጠት፣

ተግባር፡- 4.3.2 ከተለያዩ ቅ/ጽ/ቤቶች ተቀምረው የመጡ ተሞክሮዎችን ተግባራዊ

እንዲሆን መከታተልና ተገቢውን ግብዓት መስጠት፡

ተግባር፡- 4.3.3. በቡድኑ የሚሰጡ አገልግሎት እንዲሟሉ ማድረግ፡

ተግባር፡-4.3.4 በየ 6 ወሩ ደንበኞች በተሰጣቸው አገልግሎት ያላቸውን አስተያየት

በመሰብሰ መረጃውን በመተንተን የዕርካታ ደረጃ በመለካት የደንበኞችን


እርካታ ከ 85% ወደ 93% ማድረስ፣

III. የውስጥ አሰራር እይታ(60%)


ስትራቴጂክ ግብ 8፡- የኮርፖሬት አሠራርን ማሻሻል (58%)
ኦፕ.ግብ 8.2 ተግባራዊ የተደረገ የለውጥ አመራር (1%)

10
ተግባር 8.2.1፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን የ 2016 የለውጥና መልካም አስተዳደር ዕቅድ
ማዘጋጀት፣

ተግባር 8.2.2፣ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን የለውጥ መሣሪያዎችን አቀናጅቶ በመተግበር ቀልጣፋና
ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፣

ኦፕ.ግብ 8.7. የሥርዓተ-ፆታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች (1%)

ተግባር 8.7.1 የሥርዓተ-ፆታና ሌሎች የባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን በ በተሟላ ሁኔታ ተፈፃሚ እንዲሆኑ
ማድረግ፣

ተግባር 8.7.2 በኮርፖሬሽኑ የሚወጡ መመሪያዎችና ማንዋሎች የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
በቅርንጫፉ ደረጃ የሴቶችንና ለአካል ጉዳተኞች አውንታዊ ድጋፍ ያካተቱ እንዲሆኑ
በተግባር ማዋል፣

ተግባር 8.7.3 የስርዓተ-ፆታ ማካተቻ ጋይድ ላይን ተግባራዊ ማድረግ

ተግባር 8.7.4 በቅርንጫፉ ይዞታዎች ቢሮዎች እና የመኖሪያ መንደሮች እንዲሁም በተመረጡ የዕፅዋት
ማዕከላት ችግኞችን መትከል፣

ኦፕ.ግብ 8.8፡- ሥራ ላይ የዋለ የተቀናጀ የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ (1.5%)

ተግባር 8.8.1 ፣ ከስነምግባር መከታተያ ጽ/ቤት ታትመው የሚመጡ ብሮሸሮች ለቡድኑ ማሰራጨት፣

ተግባር 8.8.2 በቅርንጫፉ ጽ/ቤት ላይ በውጭ ወይም በውስጥ ኦዲተሮች እርምጃ እንዲወሰድባቸው
ወይም እንዲስተካከሉ ሪፖርት በቀረበባቸው ጉዳዮች ማስተካከያ ማድረግ፣

ተግባር 8.8.3 ከሙስናና ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በመቀበል ማጣራትና ተገቢ
እርምጃ እንዲወሰድ ክትትል ማድረግ፣

ኦፕ.ግብ 8.9፡- የተከናወኑ ፕላኒንግና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራዎች (3.5%)

ተግባር 8.9.1 የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን የ 2015 ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማዘጋጀት
በቡድኑ በማስገምገም ለጽ/ቤት መላክ፤

ተግባር 8.9.2 የቅርንጫፉን የ 2016 በጀት አመት ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፤

ተግባር 8.9.3 የጸደቀውን ዕቅድ ወደ ፈፃሚዎች እንዲወርድ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

11
ተግባር 8.9.4 የቡድኑን የየወሩ፣ የሩብ አመት፣ የስድስት ወር እና የዘጠኝ ወር የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ
አፈፃፀም ሪፖርቶች ማዘጋጀትና እና ማቅረብ፤

ኦፕ.ግብ 8.10 ፡- በ 2016 በቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት የሚካሄዱ የዕቃ፣ የአገልግሎት፣ የጥገናና ሌሎች የካፒታል
ዕቃዎች ግዥዎች፣(21%)

ተግባር 8.10.1 በቅርንጫፉ ስቶሮች በሙሉ ያሉትን እና በስቶክ የተመዘገቡ ንብረቶችን ከቡድኖች መረጃ
ማሰባሰብ እና ማደራጀት፣

ተግባር 8.10.2 ከቡድኖች ከተሰበሰቡ እና ከስቶክ በተገኙ መረጃዎች መሰረት የ 2016 ን የቅርንጫፉን
ዓመታዊ የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ማቅረብ፣

ተግባር 8.10.3 በቅርንጫፉ ግዥ ሲከናወን የገበያ ጥናት በሚያስፈልጋቸው ግዥዎች ላይ ጥናት ማከናወንና
ለግዥው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ፣

ተግባር 8.10.4 ከግዥ ጠያቂ ቡድኖች የግዢ ፍላጎት መግለጫ ዝርዝር (Specification) እንዲዘጋጅ
ማድረግና የግዥ ማስፈጸሚ ሰነድ ማዘጋጀት፣

ተግባር 8.10.5 በተለያየ አማራጭ ግዥዎች ለማስፈጸም የሚያስችሉ ኮሚቴዎችን ማደራጀት እና


ግምገማ እንዲያከናውኑ ማድረግ እና በግዥ አጽዳቂዎች እንዲጸድቅ ማድረግ፣

ተግባር 8.10.6 በቅርንጫፉ በግዥ እቅዱ መሰረት በተለያዩ የግዥ አማራጮች ሂደቱን እና የሚፈለግበትን
ወቅት የጠበቀ የብር 6 ሚሊዮን የአቃዎች፣ የጥገና የማማከር እና ሌሎች ግዥዎችን
ፈጽሞ ስራ ላይ ማዋል፡፡

ኦፕ ግብ 8.11 የቅርንጫፉን ንብረት ቆጠራ ማከናወን እና 100% የተሟላ መረጃ መያዝ፣(28%)


ተግባር 8.11.1 በቅርንጫፉ የሚገኙ አላቂ እና ቋሚ ንብረት መረጃ ቆጠራ ለማከናወን የሚያስችል
የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን፣ የንብረት ቆጠራ ማከናወን እና የቆጠራውን
መረጃ ማጠናቀር እና ማቅረብ፤

ተግባር 8.11.2 በሚወጣው ሪፖርት መሰረት በንብረት ቆጠራ ወቅት በጉድለት የተለዩ ንብረቶች ካሉ
በወቅቱ አስፈላጊውን የማስተካከያ ስራ መስራት፣

ተግባር 8.11.3 ግዥዎች ከመፈጸማቸው በፊት አስፈላጊ መረጃዎችን ከሁሉም ግምጃ ቤቶች
በማሰባሰብ ለግዥው ግብአት እንዲውል ለግዥ ፈጻሚ ክፍል ማስተላለፍ፣

12
ተግባር 8.11.4 በቅርንጫፉ በተፈቀደው ግዢ መሠረት በተለያዩ የግዥ ዘዴዎች በሮፍርማ፣
በማእቀፍ እና በፒቲ ካሽ እቃዎችን በመግዛት በባለሙያ እየተረጋገጠ
ንብረቶች በአግባቡ ወደ ንብረት ክፍል እንዲገቡ ማድረግ፣
ተግባር 8.11.5 በዋናው መ/ቤት በተለያዩ የግዥ ዘዴዎች ተገዝተው የሚመጡ ንብረቶችን
በእስፔስፍኬሽኑ መሰረት ትክክለኛ መሆኑን በባለሙያ ከተረጋገጡ በኋላ
የገቢ ሰነድ በማዘጋጀት ገቢ ማድረግ ፤ ቢን ካርድና እስቶክ ካርድ ላይ
በመመዝገብ
ተግባር 8.11.6 በበጀት አመቱ የተፈጸሙ የቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን ግዥ በስፔሲፊኬሽኑ መሰረት
መሆኑን በማረጋገጥ መረከብ እና መዝግቦ መያዝ እና በወቅቱ ማሰራጨት

ተግባር 8.11.7 ከየስራ ክፍሉ የሚመጡ የንብረት ጥያቄዎች ትክክለኛ መሆናቸውን በማረጋ
ገጥ በወቅቱ የወጪ ሰነድ በማዘጋጀት በወቅቱ ማሰራጨት እና እስቶክ እና
ቢን ካርድ ላይ ማቀናነስ፤ ወጪና ገቢ የተደረጉባቸውን ሰነዶችን በመመዝገብ
ማጠቃለያ ሪፖርት በመስራት ለፋይናንስና ገቢ አሰባሰብ ቡድን መላክ ፣

ተግባር 8.11.8 አገልግሎት ሰጥተው ከተለያዩ ስራ ክፍሎች እና ከጥገና ተመላሽ የሚደረጉ


እቃዎችን ገቢ ማድረግ፣

ተግባር 8.11.9 ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም የማይሰጡ ንብረቶችን በተለያየ ዘዴ ማስወገድ እና የተ


ወገዱ ንብረቶችን ዝርዝር መረጃ በመያዝ ከመደበኛ ንብረት ዝርዝር ጋር
ማስታረቅ፤

ኦፕ.ግብ 8.13፡- ፡-የተሻሻለ የማህደር አደረጃጀትና የመረጃ አያያዝ (2%)


ተግባር 8.11.1 የቡድኑን መረጃ በዘመናዊ መንገድ አደራጅቶ መያዝ፣

ተግባር 8.11.2 ገቢና ወጪ ደብዳቤዎችን በአግባቡ ለሚመለከታቸዉ ማድረስ፡፡

ስትራቴጂክ ግብ 9፡- ቅንጅታዊ አሰራርን ማሻሻል፤ (2%)

ኦፕ.ግብ 9.1- ከሌሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ስራ ክፍሎች መቀናጀት መስራት (1%)


ተግባር፡-9.1.1 ከሌሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ስራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ስራዎችን ማከናወን፣

13
ተግባር፡-9.1.2 ከሌሎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ስራ ክፍሎች ጋርሥራዎችን ለማከናወን የጋራ ዕቅድ
በማዘጋጀት መፈፀም፡

ተግባር፡-9.1.3 ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረሰው የጋራ ስምምነት መሰረት ስራዎችን ማከናወን፣

ኦፕ.ግብ 9.2፡- ከውስጥ የስራ ከክፍሎች ጋር የግንኙነት መድረክና የዳበረ በቅንጅት የመስራት ባህል (1%)
ተግባር፡-9.2.1 ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች እና በቡድኖች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነት እና የትስስር
ስምምነት ሰነድ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፤

ተግባር፡-9.2.2 ከውስጥ የሥራ ክፍሎች ጋር በየሩብ ዓመቱ በጋራ መድረክ በመገናኘት ሥራዎችን
በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ፣

IV. የመማማርና እድገት ዕይታ (10%)

ስትራቴጂክ ግብ 10፡- የሰው ሀብት አቅም ግንባታና አስተዳደርን ማሻሻል፤/የመፈጸም ዐቅም ማሳደግ፣

ኦፐሬሽናል ግብ 10.2፣ በቡድኑ የአመራርና ሠራተኞችን ብቃት የሚያሳድጉ የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎች


እንዲያገኙ ክትትል ማድረግ፣(2%)
ተግባር 10.2.1፣ የልሥጠና ፍላጎት በመለየት ለሚመለከተው የሥራ ክፍል ማስተላለፍ፣

ተግባር 10.2.2፣ በዕቅዱ መሠረት ሥልጠናውን እንዲያኙ ክትትል ማድረግ ፣

ም ተግባር 10.2.3፣ የሰራተኞች ዘና የአፈፃፀም ውጤቶችን መስት ባደረገ መልኩ መለካት ፣

ኦፐሬሽናል ግብ 10.4፣ የቡድኑን የሠራተኞች ዕርካታን 90% ማድረስ፣(6%)


ተግባር 10.4.1፣ሠራኛውን በቡድኑ ዕቅድ ዝግጅትና ግምገማ መድረኮች ማሳተፍ፣

ተግባር 10.4.2፣ ከሠራኞች የሚቀርበውን ቅሬታ በወቅቱ መፍታት፣

ተግባር 10.4.3፣ የሥራ አካባቢዎች ለሠራተኛው አመቺ እንዲሆኑ ማደረግ፣

ተግባር 10.4.4፣ የሠራተኞች ምዘና የአፈጻጸም ውጤትን መሠረት ባደረገ መልኩ መለካት፣

ተግባር 10.4.5 ፣የሥራ መሪና ሠራተኛን ቆየታ/Retenetion Rate/ማሳደግ፣

ስትራቴጂክ ግብ 11፡-የቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ (2%)

ኦፐሬሽናል ግብ 11.1 ፣ የለሙ ሶፍትዌሮችን ወደ ትግበራ ማስገባት

14
ተግባር 11.1.1 የተቀናጀ የማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምን ትግበራ ስልጠናዎችን መከታተል

ተግባር 11.1.2 ከስራ ክፍሎች በ IMIS ሲስተም አተገባበር ወቅት የሚመጡ ጥያቄዎችን በመቀበል
ማሻሻዎችን ማድረግ እና መከታተል

ተግባር 11.1.3 ልዩ ልዩ ችግር ፈቺና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ መተግበሪያዎችን ሲለሙ ወደ አገልግሎት


እንዲገቡ ማድረግ፣

ክፍል አራት
የቡድኑ የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች፣

o የግዥና ንብረት አገልግሎትን ጥራት ለማሻሻል የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድን መጠቀም፣


o አገልግሎትን አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ማደረግ፣

ክፍል አምስት

ለ 2016 የግዥ ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልግ በጀት

በቡድኑ የታቀደ በጀት


5.1 የወጪ በጀት፣
 ለ 2016 ለቡድኑ ስራ ማስፈጸሚያ ብር 2,136,434.00 በጀት ተጠይቋል፡፡ ከዚህ ውስጥ

የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን


የ 2016 በጀት ዓመት የበጀት እቅድ ማጠቃለያ
ተ.ቁ የእቃው ዓይነት የገንዘብ መጠን ምርመራ
1 የጽህፈት እቃዎች 466,990.00
2 የጽዳት እቃዎች 112,350.00
3 ቋሚ እቃዎች 877,094.00
ለ 2015 በጀት አመት ቆጠራ ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች እና
4 የትርፍ ሰዓት ክፍያ 200,000.00
ደራሽ ስራዎች ለማሰራት
በእቃ ግምጃ ቤት በረዳትነት ለሚሰሩ ጉልበት ሠራተኞች
ደመወዝ፣ በንብረት ቆጠራ ለሚሰሩ ጉልበት ሠራተኞች፣ ሲሚንቶ፣በሎኬት
የመሳሰሉ እቃዎች ሲገዙ
5 የጉልበት ሠራተኛ 350,000.00 የሚያወርዱና የሚደረድሩ በተጨማሪም ተከራዮች በተለ
ያዩ ምክንያት እቃቸውን ሳያወጡ የሚሄዱትን እቃ ወደ
መጋዘን ለማስገባት የሚጭኑና የሚያወርዱና የሚደረድሩ
ጉልበት ሠራተኞች ክፍያ ፡፡

15
6 ለተለያዩ እቃዎች ማስጠገኛ 100,000.00
ለ 2015 በጀት ዓመት ንብረት ቆጠራ
7 ለሚሰሩ ሰራተኞች የምሳ አበል 30,000.00
ክፍያ

አጠቃላይ ድምር 2,136,434.00

ክፍል ስድስት

ስጋቶችና የሚወሰዱ እርምጃዎች

ሥጋቶችና ስጋቶቹን ለመካላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች/ለምሳሌ የቀረበ/


ስጋቶች የሚከናወኑ ተግባራት የስጋቱ የጊዜ ሠሌዳ የስጋቱ ባለቤት
ተ.ቁ ደረጃ 1ኛ 2ኛ 3ኛ 3ኛ
ሩብ ሩብ ሩብ ሩብ
ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
1 የጥገና እቃ የአገልግሎት ግዥ እቃዎችን ለጊዜው በፒቲ ከፍተኛ     የቤቶች አስተዳደር
ዋጋ በየጊዜው መጨመርና ካሽ በመግዛት ዘርፍ እና ቅርንጫፉ
ፕሮፎርማ በተፈለገው መጠን ፕሪፎርማውን
አለማገኘት፤ በመከታተል ችግሩን
ለመፍታት የሚቻልበት
መንገድ መፍጠር፤

ክፍል ሰባት

ከቅርንጫፉ እና ከሌሎች ስራ ክፍሎች ድጋፍ የሚጠይቁ ጉዳዮች

6.1 ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱና ከስራ ክፍሎች ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች

 በቅርንጫፉ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ሲኖሩ ፈጣን ውሳኔ መስጠት

 ለቅርንጫፉ የሚያገለግሉ የተሸከርካሪ አቅርቦት ባለው አቅም እዲሟላ ማድረግ፣

 ከማእከል የሚያስፈልጉ ግብአቶች በወቅቱ እንዲቀርቡ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ፣

 ለቅርንጫፉ ሥራ በቂ የሆነ በጀት እንዲመደብ እና በወቅቱ እንዲላክ ማድረግ፣

16
ክፍል ስምንት

የክትትልና ግምገማ ዕቅድ

8.1. የቡድኑ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ዓላማ

የቡድኑ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ዓላማ የዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ተከታታይና
ወቅታዊ የሆኑ የክትትልና ግምገማ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣ በመተንተንና ለውሳኔ አሰጣጥ
ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሻሸል በማድረግ ተልዕኮውና
ራዕዩ እውን እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡
ይህንን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉትን የክትትል ዘዴዎች በመጠቀም የክትትልና ድጋፍ
ተግባራት ይከናወናሉ፡፡

8.2. የክትትል ሪፖርት


የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የክትትልና ግምገማ ዕቅድ ዋና ትኩረት በክትትል አግባብ ለዘመኑ ዕቅድ ትግበራ
አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች/የሰው ኃይል፣ሥልጠና፣ የፋይናንስ፣ የማቴሪያል፣ ወዘተ./ በታቀደው ልክ የቀረቡ
መሆኑን፣ በማረጋገጥ የታቀዱ ሥራዎችን በመተግበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ውጤታማ ለማድረግ በወጪ፣በጊዜና
ጥራት የሚመዘን እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

 በመሆኑም የአፈጻጸም ሪፖርት ትኩረቶች የዕቅድ ክንውንን ከዒላማ ጋር በማነጻጸር የአፈጻጸም ደረጃን
በመቶኛ ማሳየት፣ አፈጻጸሙ በማነስ ወይም በመብለጥ ከሆነ ምክንያቶቹን ማቅረብ፣ ምክንያቶቹ
ከፈጻሚ አካል የመፈጸም ጉድለት ጋር የተያያዘ ከሆነ በድክመትነት እንዲመዘገብ በማድረግ የማሻሻያ
እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ማሳየት፣ ከፈጻሚው አካል ቁጥጥር ውጭ ከሆነ ደግሞ ያጋጠመ ፈታኝ
ሁኔታ ተደርጎ እንዲወሰድና በሚመለከተው የበላይ አካል ውሳኔ እንዲሰጥበት ከውሳኔ ሃሳብ ጋር
ማስተላለፍን ያካትታል፡፡
 የዕቅዱን አፈጻጸም የሚመለከት ወርሃዊ፣ የሩብ አመት፣ የግማሽ ዓመት የዘጠኝ ወራትና ዓመታዊ የተሟላ
የጽሑፍ ሪፖርት ፈፃሚዎች ለቡድኑ ቡድኖች ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡
 የቡድኑ ሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ አኳያ የተገመገሙ ወርሀዊ ሪፖርቶች ወሩ በተጠናቀቀ በ 1 ካሌንደር
ቀናት፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ኣመትና የ 9 ወራት ሪፖርቶች የሪፖርቱ ዓመታዊ ሪፖርት የበጀት አመቱ
በተጠናቀቀ በኋላ በ 2 ካሌንደር ቀናት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡

8.3. ሱፐርቪዥንና ድጋፍ አሰጣጥ

17
ሱፐርቪዥን በየደረጃው ያሉ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ኣና ሱፐርቫይዘሮች በጽሑፍ የቀረቡ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችንና
ሥራዎችን በአካል በመገኘት የሚከታተሉበት/የሚያረጋግጡበትና ድጋፍ የሚሰጡበት የክትትል ዘዴ ነው፡፡
 የሱፐርቪዥን ትኩረቶች፣ የታቀዱ ሥራዎች በታቀደው ጊዜ፣ ወጪና ጥራት መሠረት እየተከናወኑ መሆኑን
በመስክ ዕይታ ማረጋገጥ፣ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን ቦታው ላይ ሆኖ ለሥራ ማነቆ ለሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ
ማፈላለግና ውሳኔ መስጠት ናቸው፡፡ በሱፐርቪዥን ወቅት መረጃዎች የሚሰባሰበው ከመስክ ከተለያየ መረጃ
ማግኛ ይሆናል፡፡

 የቢሮ ስራዎችን አፈጻጸም ለመከታተል በቡድን መሪዎች፣ በቅርንጫፍ ኃላፊ በፕሮግራምና ድንገተኛ
የሱፐርቪዥን ስራዎች ይከናወናሉ፤
8.4. የክትትልና ግምገማ መድረኮች፣
 ቡድኖች በየወሩ የሰራተኞቻቸውን የዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም መረጃዎችን አደራጅተው
ያስቀምጣሉ፤

 ሥራ አፈጻጸም መገምገሚያና ሪፖርት ማድረጊያ ስታንዳርድ ቼክሊስት/ፎርማት ተዘጋጅቶ በየወቅቱ


እየተከለሰ ሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል፤
 ቡድኑ በየወሩ የሰራተኞቻቸውን አፈጻጸም በመገምገም መረጃዎችን አደራጅተው ያስቀምጣሉ፤
 ቡድን መሪ ፈፃሚዎች የሚሳተፉበት የአፈጻጸም ግምገማ የሚካሄድበት እና በየደረጃው የሚያጋጥሙ
ችግሮች የሚፈቱበት የ 1 ወር ቋሚ መድረክ ይኖራል፣
 በየ 6 ወሩ በሚዘጋጀው የግምገማ ሥርዓት መሰረት ሁሉም ሠራተኛ ተገምግሞ ደረጃ እንዲሰጠው
ይደረጋል፣
 የሠራተኛው የጭማሪና የጥቅማ ጥቅም ተጠቃሚነቱ በበጀት ዓመቱ በሚመዘገበዉ ውጤት ላይ
የተመሰረተ እንዲሆን ይደረጋል፤

6.3 ግብረ መልስ፣

ቡድኑ ለፈጻሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የቃል ወይም የጽሁፍ ግብረ መልሶችን ይሰጣል፤

18
19
20

You might also like