Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

06/07/2024, 20:24 የከተሞችን ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ሊዘጋጅ ነው - ኢዜአ አማርኛ

አማርኛ ትግርኛ Afaan Oromoo Af‑Soomaali Qafar Afa English Français ‫عربي‬

ፖለቲካ ማህበራዊ ኢኮኖሚ ስፖርት ሳይንስና ቴክኖሎጂ አካባቢ ጥበቃ ዓለም አቀፍ ዜናዎች መጣጥፍ ቪዲዮዎች ስለ እኛ

የከተሞችን ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ሊዘጋጅ
ነው

አዳማ (ኢዜአ) ነሐሴ 25/2014--የሀገሪቷን ከተሞች ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ለማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዘርፉ ለተካሄደ የፖሊሲ ጥናት ረቂቅ ሰነድ ግብአት ለማሰባሰብ ያዘጋጀው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚነስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደገለጹት፣ ነባሩ የከተሞች መሰረተ ልማትና የቤቶች ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ እስከዛሬ
ሲሰራበት ቆይቷል።

https://www.ena.et/web/amh/w/am_182961 1/3
06/07/2024, 20:24 የከተሞችን ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ሊዘጋጅ ነው - ኢዜአ አማርኛ

ይሁንና የሀገሪቷን ከተሞች ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ማስፈለጉን ገልጸዋል።

ለእዚህም የህዝብን የልማት ፍላጎት ያገናዘበ የተቀናጀ የከተሞች መሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ በአዲስ መልክ ለማዘጋጀት የሚያስችል የፖሊሲ ጥናት መከናወኑን
ጠቁመዋል።

"በአሁኑ ወቅት ነባሩን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና የከተሞች ልማት ፕሮግራሞች ክለሳና አዲስ ማዘጋጀት አስፈልጓል" ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ አዲስ የሚዘጋጀው ፖሊሲ
በነባሩ ላይ ያሉትን ጉድለቶች ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የሚችሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የተካተቱበት መሆኑን ጠቁመዋል።

ጥናቱ በተለይ በተቀናጀ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ ጥራትና ደረጃ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶች ልማት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ ዘመናዊ የከተማ መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ላይ በጥልቀት እንደተካሄደ ገልጸዋል።

የፖሊሲ ጥናቱ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሀገሪቷ ያሉ 20 ዋና ዋና ከተሞችን እንደሚሸፍን ያመለከቱት ኢንጂነር ወንድሙ፤ "የቻይና፣ ኮሪያ፣ ኬንያ እና ካሜሩን
ከተሞች ልማትና ዕድገት ፖሊስ ተሞክሮ በጥናቱ ተካቷል" ብለዋል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ በፖሊሲው ለከተሞች ዘመናዊ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ በመኖሪያ ቤት የፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ችግሮችን ለመፍታት
ትኩረት ተደርጓል።

በተጨማሪም የከተማ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓቱን ለማዘመን እና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ጭምር ይዘጋጃሉ
ብለዋል።

የመድረኩ ዓላማ ጥናቱን በግብዓት ለማዳበር መሆኑን የገለጹት ደግሞ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ናቸው።

"በተካሄደ ጥናት በግኝት ከተለዩት መካከል የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት እጥረትና ዋጋ መናር፣ የቤት አቅርቦት ቅንጅት መጓደል፣ መካከለኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች
የቤት አቅርቦት አማራጭ አለመኖር ይጠቀሳሉ" ብለዋል።

ፕሮፌሰር በየነ እንዳሉት የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃ፣ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች የተቀናጁና የተናበቡ አለመሆናቸውን በጥናቱ ግኝት
ተረጋግጧል።

https://www.ena.et/web/amh/w/am_182961 2/3
06/07/2024, 20:24 የከተሞችን ቀጣይ ልማትና እድገት ያገናዘበ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፖሊስና ስትራቴጂ ሊዘጋጅ ነው - ኢዜአ አማርኛ

© የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት 2015 ዓ.ም

https://www.ena.et/web/amh/w/am_182961 3/3

You might also like