Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

06/07/2024, 20:48 መሬትን በካዳስተር ስርዓት መዝግቦ ማስተዳደር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው - የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር

ሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው - የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ

አማርኛ ትግርኛ Afaan Oromoo Af‑Soomaali Qafar Afa English Français ‫عربي‬

ፖለቲካ ማህበራዊ ኢኮኖሚ ስፖርት ሳይንስና ቴክኖሎጂ አካባቢ ጥበቃ ዓለም አቀፍ ዜናዎች መጣጥፍ ቪዲዮዎች ስለ እኛ

መሬትን በካዳስተር ስርዓት መዝግቦ ማስተዳደር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው - የከተማና
መሠረት ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፤የካቲት 2/2016 (ኢዜአ)፡- መሬትን በካዳስተር ስርዓት መዝግቦ ማስተዳደር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን የከተማና መሠረት ልማት
ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፋንታ ደጀን ገለጹ።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በካዳስተር ስራዎችና መልካም ተሞክሮዎች ዙሪያ የከተሞችና የክልሎች የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዳማ
እየተካሄደ ነው።

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_3996505 1/3
06/07/2024, 20:48 መሬትን በካዳስተር ስርዓት መዝግቦ ማስተዳደር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው - የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ

ውስን የተፈጥሮ ሃብት የሆነውን መሬት በአግባቡ ማስተዳደር እና ማልማት እንደሚያስፈልግ በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል።

የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፋንታ ደጀን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የልማት መሰረት የሆነውን የመሬት ሃብት ዜጎች በፍትሃዊነት ሊጠቀሙበት
ይገባል ብለዋል።

ለዚህም መሬትን የመመዝገብ፣ የማልማት እና የማስተዳደር ስራዎች በአግባቡ ሊከናወኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ከተሞች ለካዳስተር ስርዓት ምዝገባ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የመሬት መረጃዎችን ማዘመን እና አገልግሎት አሰጣጡን
ዲጂታላይዝ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለከተሞች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

መሬትን በካዳስተር ስርዓት መመዝገብ ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ፤ከተሞች ዘመናዊ ሆነው እንዲያድጉና እንዲለሙም ወሳኝ መሆኑን
ተናግረዋል።

መሬትን በካዳስተር ስርዓት መመዝገብ የዜጎች የይዞታ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እንደሚጠበቅም ጠቁመው ፤ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት
ለመስጠት እንደሚጠቅምም አስረድተዋል።

ከተሞች መሬትን የካዳስተር ስርዓት መመዝገብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በመረዳት በፍጥነት ወደዚህ ስርዓት እንዲገቡ አሳስበዋል።

ስርዓቱን የጀመሩ ከተሞችም አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የኦሮሚያ ከተሞች የካዳስተር ልማት ትግበራ አፈጻጸም ሂደትና የተገኙ ውጤቶችን ተሞክሮ ያቀረቡት የክልሉ መሬት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ፍቃዱ
ሽፈራው የካዳስተር ስርዓት ለውጤታማነት ያግዛል ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል 42 ከተሞች ላይ መሬት በካዳስተር ስርዓት ለመመዝገብ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው፤ በ37 ከተሞች የመመዝገብ ስራ እና

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_3996505 2/3
06/07/2024, 20:48 መሬትን በካዳስተር ስርዓት መዝግቦ ማስተዳደር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው - የከተማና መሠረት ልማት ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ

© የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት 2015 ዓ.ም

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_3996505 3/3

You might also like