የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለችግሮች መፍትሔ አመንጪ እየሆነ መጥቷል – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 2

07/07/2024, 15:35 የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለችግሮች መፍትሔ አመንጪ እየሆነ መጥቷል – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

The
መነሻEthiopian HeraldማህበራዊBariisaa
ዜና   ስፖርት እናBakkalcho
መዝናኛ  ርዕሰ‫العلم‬
አንቀፅ ወጋሕታ
ኢኮኖሚ  ዘመን እና ፖለቲካJobs
መጽኄት
ወቅታዊ  Tenders
ነፃ ሃሳብ Ethiopian Press Agency Search...

FEATURED PRESS ONLINE

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለችግሮች መፍትሔ አመንጪ እየሆነ መጥቷል


በኢትዮጵያ የሩሲያ አ
— July 7, 2024 comments off

RECENT POSTS

ኢትዮጵያን በዓለም
July 7, 2024

ኢትዮጵያ ንግድ ባን
አነሳ
July 7, 2024

‹‹እሳቷ›› ሙናዬ!
July 7, 2024

ከ80 ዓመታት በላይ


የኢትዮጵያ እንግሊዝ
July 7, 2024

የዘርፉ የሰው ሃይል


አዲስ አበባ፡– የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ በሀገሪቱ ላሉ ችግሮች መፍትሔ አመንጪ እየሆነ መምጣቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
አለመጣጣም ምክን
July 7, 2024
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ሁለት ሺህ 100 ሰልጣኞች በትናንትናው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የክብር እንግዳ የነበሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንደገለጹት፤ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ በሀገሪቱ ላሉ ችግሮች መፍትሔ Gallery
አመንጪ እየሆነ ለሀገር እድገት ትልቅ ፋይዳ እያኖረ መጥቷል።

ሚኒስትሯ፤ ባለፉት ዓመታት በኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የለውጥ ሃሳቦች ተለይተው እየተተገበሩ መምጣቱን የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም በተወሰኑ የፈጠራ ውጤቶች ፍሬውን ማየት
ተጀምሯል ብለዋል።

በኢንስቲትዩቱ እስካሁን እስከ ደረጃ ሰባት ያሉ ስልጠናዎች እየተሰጠ የነበረ ሲሆን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ደረጃ ስምንት እንዲካተት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ
እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ መሳተፍ እራስን ብሎም ሀገርን ከችግር ማስፈንጠር ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ በዘርፉ ውስጥ መሳተፍ የቻሉ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንክቲትዩት ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ሀገርን ለማሳደግ እንዲሁም ራስን ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ
ይገኛል ብለዋል።

ተቋሙ በዘንድሮው ዓመት የስልጠና ሥርዓቱን ሲያዘምን እንዲሁም የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ሲያስፋፋ መቆየቱን ገልጸው፤ በቀጣይ ደግሞ ገበያ ተኮር የሆኑ አዳዲስ
የስልጠና መስኮችን ለመክፈት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኢንስቲትቱ አንዱ ተልዕኮ የሆነው ጥናትና ምርምሮችን በጥራት የመስራት ተልዕኮ ተግባራዊ በማደረግ በበጀት ዓመቱ 55 ጥናቶች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህም መፍትሄ
አመላካች የሆኑ ፖሊሲዎችን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያግዙ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡

https://press.et/?p=131508 1/2
07/07/2024, 15:35 የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለችግሮች መፍትሔ አመንጪ እየሆነ መጥቷል – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
ኢንስቲትዩቱ ከበርካታ ኢንዱስተሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ሰልጣኞች የተግባርኢኮኖሚ
ልምምድ እንዲያገኙ፣ የቴክኖሎጂ ልምድ ላይ እውቀት እንዲኖራቸውና
መነሻ ዜና  ማህበራዊ 
ስፖርት እና መዝናኛ 
ርዕሰ አንቀፅ ወቅታዊ እና ፖለቲካ 
ነፃ ሃሳብ
በሚሰማሩበት ሥራ መስክ ጥራት እንዲኖራቸው በትኩረት መሠራቱን ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ብሩክ፣ የቴክኖሎጂ ልማት ሥራን ለማጠናከር በተደረገ እንቅስቃሴም ከመላው ሀገሪቱ በተወጣጡ ቴክኖሎጂስቶች 75 የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማውጣት መቻሉን
ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በዛሬው ዕለት ሁለት ሺህ 100 ተማሪዎችን ማስመረቁን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ከተመራቂዎች ውስጥም የደቡብ ሱዳንና የሶማሌላንድ ተማሪዎች መኖራቸውን
ተናግረዋል።

መስከረም ሰይፉ

አዲስ ዘመን ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You

የፖለቲካ እሳቤ ያልከፋፈለው ሕዝባዊ ንባብ ያለፈውን፣ የአሁኑንና የነገን መንግሥት መሠረታዊ ስብራቶችን ተመራቂዎች የቀሰሙትን ዕውቀት
ተሳትፎ በአረንጓዴ አሻራ ተጨባጭ ትውልድ የሚያገናኝ መሳሪያ ነው በመጠገን ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ በመጠቀም መላውን ሕዝብ በቅንነት
ውጤት አምጥቷል ለመገንባት እየሠራ ነው ማገልገል አለባቸው

© 2024 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

https://press.et/?p=131508 2/2

You might also like