የዘርፉ የሰው ሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም ምክንያት – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

07/07/2024, 17:06 የዘርፉ የሰው ሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም ምክንያት – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

The Ethiopian Herald Bariisaa Bakkalcho ‫العلم‬ ወጋሕታ ዘመን መጽኄት Jobs Tenders Ethiopian Press Agency Search...

መነሻ ዜና  ማህበራዊ  ስፖርት እና መዝናኛ  ርዕሰ አንቀፅ ኢኮኖሚ  ወቅታዊ እና ፖለቲካ  ነፃ ሃሳብ

ወቅታዊ ትንታኔ
ባህልና ቱሪዝም PRESS ONLINE

የዘርፉ የሰው ሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም ምክንያት


ወቅታዊ እንግዳ

በኢትዮጵያ የሩሲያ አ
— July 7, 2024 comments off የዘመን እንግዳ

ጎሜ

ተጠየቅ

ፍረዱኝ RECENT POSTS

ኢትዮጵያን በዓለም
ተናጋሪው ዶሴ
July 7, 2024

ኢትዮጵያ ንግድ ባን
አነሳ
July 7, 2024

‹‹እሳቷ›› ሙናዬ!
July 7, 2024

ከ80 ዓመታት በላይ


የኢትዮጵያ እንግሊዝ
July 7, 2024

የዘርፉ የሰው ሃይል


በኢትዮጵያ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ አበረታች ለውጦች እየተመዘገበ መሆኑን የሚያመላክቱ ተጨባጭ መረጃዎች እያየን ነው። በተለይ በመንግስት በኩል በቱሪዝም
አለመጣጣም ምክን
በመዳረሻ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የዘርፉን መጪ ተስፋ የተሻለ እንደሚያደርጉ ታምኖባቸዋል። የቱሪዝም ዘርፉ ፖሊሲ ማሻሻያ መደረጉና ቱሪዝም ከአምስቱ ዋና ዋና July 7, 2024
የኢኮኖሚ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ተደርጎ መወሰዱ በራሱ መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በሚገባ ያሳየበት አንዱ አስረጂ ነው።

በየደረጃው እየተገነቡ ያሉ የመዳረሻ ልማት ሥራዎች፣ አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ማልማት እንዲሁም በቂ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማስፋፋት የኢትዮጵያ ቱሪዝም Gallery
የሚታይ ለውጥ እንዲያስመዘግብ ጠንካራ መሠረት እንደሚሆኑ ይታመናል።

በሆስፒታሊቲ ዘርፉም ቢሆን በተመሳሳይ በሆቴል፣ ቱር ኦፕሬተርስ እና ሌሎች መሰል ንኡስ አገልግሎት ዘርፎች ላይ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ኢትዮጵያን በጥቂት ዓመታት
ውስጥ በዓለም የቱሪዝም ገበያ ያለውን ድርሻዋን በበቂ ሁኔታ እንድትጋራ መሠረት የሚጥሉ ናቸው።

በሆስፒታሊቲ ዘርፉ ስለተናከናወኑ ተግባሮች ይበልጥ ለማብራራትም ባለኮከብ ሆቴሎች በመላው ሀገሪቱ መስፋፋታቸው፣ በመስህብ ስፍራዎች አገልግሎት ሰጪ ሎጆች፣
ሪዞርቶች እና የቱሪዝም ምርት አቅራቢዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የጎብኚዎችን ፍላጎትና የቱሪዝም ደረጃን የሚያሟሙ
ሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪዎች በመላው ሀገሪቱ እንዲኖሩ ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ እየተገበረ ያለው የምዘናና ቁጥጥር ሥራም እንዲሁ መስመር እየያዘ መምጣቱን
መመልከት ይቻላል። በየጊዜው የኮከብ ደረጃ ምደባዎች መካሄዳቸው የአገልግሎት ጥራትን ለማምጣት ምቹ አጋጣሚን እንደሚፈጥሩም ይጠበቃል።

ለቱሪዝም ዘርፍ ግን ከላይ ያነሳናቸው አደረጃጀቶች ብቻ በቂ አይደሉም። ቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፉ ኢትዮጵያ ባላት እምቅ ሀብት ልክ ተሻሽሎ ውጤት እንዲያሳይ በዘርፉ
የሠለጠነ የሰው ሃይል በጥራትም ሆነ በብዛት መቅረብ ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ የቱሪዝም ማሠልጠኛ ተቋማት ሃላፊነት ይወስዳሉ። በእርግጥ ከቅርበ ጊዜ ወዲህ በቱሪዝምና
ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ባለሙያዎችን የሚያፈሩ የትምህርት ከፍሎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በብዛት እየተከፈቱ ናቸው፤ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትም እንዲሁ
በስፋት እየተሠራበት ይገኛል። የግል የትምህርት ተቋማትም በዚሁ ሙያ ዘርፍ ሥልጠናዎችን መስጠት ከጀመሩ ቆይተዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ፖሊ ቴክኒኮችና ሌሎች የግልና የመንግሥት ማሠልጠኛዎች የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ባለሙያዎች እየወጡ መሆኑን መረጃዎች
ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ባለሙያዎች ዘርፉ ከሚፈልገው የሰው ሃይል አንፃር በቂ እንዳልሆኑ በቅርቡ የተካሄደ ጥናት ያመለክታል።

https://press.et/?p=131539 1/3
07/07/2024, 17:06 የዘርፉ የሰው ሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም ምክንያት – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
የዘርፉን ፍላጎት የሚያሟላ አቅርቦት ማድረግ እና ጥራት ያላቸው ባለሙያዎችን ማቅረብ ከተቻለ እነዚህም ከመሠረተ ልማት ግንባታ (መዳረሻ ልማት)፣ ከማስተዋወቅና ከገበያ
ልማት እንዲሁም ከፖሊሲ ማሻሻያው ጋር ተደምረው ሚዛኑን የጠበቀ እድገት እንዲመጣ ማድረግ ይቻላል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ ይፋ የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው፤ በቱሪዝም ዘርፍ ካለው የሰው ሃይል ፍላጎት አንፃር አቅርቦቱ የተመጣጠነ እንዳልሆነ ነው። ከዚህ በተጨማሪ
በማሠልጠኛ ተቋማት ውስጥ ተመርቀው ከሚወጡ ባለሙያዎች መካከል የቱሪስት ፍላጎትን እንዲሁም ስታንዳርድን የሚያሟሉት ጥቂቶቹ መሆናቸውንና በዚህ ረገድ ሰፊ
ክፍተት እንደሚታይ ጥናቱ ጠቁሟል።

ሰሞኑን የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባካሄደው ጥናትና ምርምር እንዲሁም በሠለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት ዙሪያ በተካሄዱ
ጥናቶች ላይ በአዳማ ከተማ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በምክክር መድረኩ በተቋሙ በጥናትና ምርምር ዘርፍ እስካሁን የተካሄዱ ሥራዎች፣ ቀጣይ የታቀዱ ሥራዎች
እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎትና አቅርቦት ምን ይመስላል? የሚሉ ጥናቶችም ቀርበውበታል። በዚህ መድረክ ላይ በቱሪዝም ዘርፍ የተሠማራው የሠለጠነ የሰው ሃይል
47 በመቶ ብቻ መሆኑ አንድ ጥናት አመላክቷል።

ሳይንሳዊ መንገዶችን መሠረት ባደረገው በዚህ ጥናት በሥራ ላይ ከተሠማሩት ባለሙያዎች ጥቂት የማይባሉትም ልዩ ልዩ ሙያዊ ክፍተቶች እንዳሉባቸውም አመላክቷል። ይህን
ጥናታዊ ውጤት ይፋ በማድረግ በባለሙያዎች ግምገማና አስተያየት እንዲሰጥበት የተደረገው የዘርፉን የሰው ሃይል አቅርቦትና ፍላጎት በመለየት ቀጣይ ሊወሰዱ ለሚገባቸው
ርምጃዎች መፍትሄ ለማመላከት መሆኑ ተጠቁሟል።

አቶ ፍሬው አበበ የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አሠልጣኝና የጥናቱ አቅራቢ ናቸው። እርሳቸው ጥናታዊ ውጤቱን ይፋ ሲያደርጉ እንደገለጹት፤ በቱሪዝም
የሆስፒታሊቲ ዘርፉ ላይ ባሉ የቱሪስት ስታንዳርዶች ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶችና በአስጎብኚ ድርጅትነት ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱ ቱር ኦፕሬተሮች ውስጥ የሚሠሩ የሠለጠኑ
ባለሙያዎች ቁጥር ከ50 በመቶ በታች ነው። በተጨማሪ በአዳዲስ የሆቴልና ቱሪዝም ምሩቃን ላይ የቋንቋ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት ክፍተት፣ የተግባቦት ችግር እንዲሁም
የሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ይታያል።

ተመራማሪው በሰው ሃይል ፍላጎትና አቅርቦት ላይ ባቀረቡት በዚህ ጥናት ከተዳሰሱት 401 ሆቴሎች መካከል 47 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በሠለጠኑና የብቃት ምዘናን ባሟሉ
ባለሙያዎች እየሠሩ መሆኑን አመልክተዋል። ብቁ ባልሆነ የሰው ሃይል የሚያሠሩ አካላትም ከትርፍ ይልቅ ባልተሟላ አገልግሎታቸው ምክንያት ደንበኛ ሲሸሻቸው መታየቱን
ተመራማሪው ጠቁመዋል። በዘርፉ የተመረቁትም ቢሆኑ የክህሎት ክፍተት እንደሚታይባቸው አመልክተዋል።

‹‹እየተስፋፋ ካለው የቱሪዝም መሠረተ ልማት እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ አንጻር የሰው ሃይል አቅርቦቱ ተመጣጣኝ አይደለም›› የሚሉት ጥናት አቅራቢው፤ በ80 በመቶ ሆቴሎች፣
74 በመቶ በሚሆኑ ሬስቶራንቶችና 50 በመቶ በሚሆኑ አስጎብኚ ድርጅቶች ከሰው ሃይል ገበያው ላይ ብቃት ያለው የሠለጠነ የሰው ሃይል ማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው
ያገኙትን ሳይንሳዊ መረጃ በመተንተን ያመለክታሉ። ለዚህ ምክንያቱ ከፍተኛ የሆነ የሠለጠነና ብቁ ባለሙያ እንዲሁም አሠልጣኝ እጥረት መኖሩ መሆኑንም ይገልፃሉ። በዚህ
ምክንያት ቀጣሪዎችም ሙያዊ ሥልጠና ያልወሰዱ ሠራተኞችን ለመቅጠር እንደሚገደዱና ይህም በጥራት አገልግሎት መስጠት ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር ይገልፃሉ።

ይህ ጥናት ሆቴሎችና የቱሪዝም መዳረሻዎች ክፍተቶቻቸውን በመጠቆም ብቃት ባለው ሰው ሃይል ልማት ላይ አተኩረው እንዲሠሩ አጋዥ ይሆናል የሚሉት አቶ ፍሬም፤
በተደረገው ዳሰሳ መሠረት መፍትሄ የሚሆኑ ምክረ ሃሳቦችም እንደተቀመጡም ይገልፃሉ።

በዋናነትም አሁን እየታየ ያለውን የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን ለመሙላት የሥልጠና መርሃ ግብሮችን ማስፋት፣ ባለሙያዎች ወደ ዘርፉ ሙያ እንዲገቡ በመገናኛ ብዙሃን
ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ፕሮግራሞችን መሥራት፣ ለሥልጠና ተቋማትና አሠልጣኞች የአቅም ግንባት ሥራ ማከናወን ያስፈልጋል። በባለሙያዎች ላይ የሚታየውን የክህሎት፣
የሥነ ምግባር እንዲሁም የተግባቦት ችግር ለመፍታት ከኢንዱስትሪው አንቀሳቃሾች ጋር በትብብር መሥራት ያስፈልጋል።

በመድረኩ የተገኙት የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ ሥልጠና በመስጠት፣ የጥናትና ምርምር
እንዲሁም የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። የጥናት እና ምርምር ውጤቶቹንም ያሠራጫል። በበጀት
ዓመቱም ካካሄዳቸው ጥናትና ምርምሮች መካከል ይሄ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ የሰው ሀብት ፍላጎትና አቅርቦት የሚያመለክተው ጥናት አንዱ ነው።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት በቱሪዝም መዳረሻዎችና የቱሪስት አገልግሎት ደረጃ ያሟሉ ሆቴሎች በሰው ሃይል ፍላጎትና አቅርቦት በኩል
ያላቸውን ገጽታ ለማሳየት በቀረበ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ መምከር ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በጥናት ለተዳሰሱት ችግሮች መፍትሄ አመላካች
አቅጣጫዎችን ለፖሊሲ አውጪዎችና ለባለድርሻ አካላት ለመጠቆም እንዲያስችል ነው።

‹‹የቱሪዝም ዘርፉን የኢኮኖሚ ፍሰት ለማረጋገጥ የሠለጠነና ብቃቱ የተመዘነ ባለሙያ ማሰማራት ወሳኝ ነው›› ነው ሲሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው ነጋሽ፤ እንደ ሀገር ለቱሪዝም
ዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት መነሻ በማድረግ ነባሮቹን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማደስ እና አዳዲሶችንም በስፋት ለመገንባት የሰው ሃይል ላይ መሥራት ተገቢ ሆኖ መገኘቱን
አስታውቀዋል። ይህንንም በጥናት በተደገፈ መልኩ ለ ማከናወን ማስፈለጉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ችግር ፈቺ ጥናቶችን ወደ ተግባር በመቀየር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን የውጭ ምንዛሬ የሚጨምሩ አሠራሮችን በመከተል ዘርፉን የማሻሻል ሥራ
እንደሚከናወን ዋና ዳይሬተሩ አስታውቀዋል። ለተፈጻሚነቱ የቱሪዝምና ሆቴል ማሠልጠኛዎች የተሟላ ሥልጠና በመስጠት ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራትና በዘርፉ በማሠማራት
በኩል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በመወጣት የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሠለጠነ የሰው ሃይል በብዛት ለማሠማራትም ደረጃቸውን የጠበቁ የማሠልጠኛ ተቋማትን ማስፋፋትና የባለድርሻ አካላት ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
ይህም ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ከማረጋገጥ በተጨማሪ የባለሙያ ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በሀገር ገጽታ ግንባታ ላይ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ
አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

እንደ መውጫ

https://press.et/?p=131539 2/3
07/07/2024, 17:06 የዘርፉ የሰው ሃይል ፍላጎት እና አቅርቦት አለመጣጣም ምክንያት – የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
በጥናታዊ ውጤቱ ላይ ተመሥርተን አሁን ያሉትን የዘርፉን ችግሮች ለመረዳት ስንሞክር ሁለት ነገሮችን እንገነዘባለን። አንደኛው የቱሪዝም ዘርፉ ከሚፈልገው በተቃራኒ የሰው
ሃይል አቅርቦቱ አናሳ መሆኑ ሲሆን፣ በሁለተኛው ደግሞ ከጥራት አንፃር ጉድለቶች መኖራቸውን ነው። በመሆኑም በጥናቱ ከተለዩ መፍትሄዎች ጎን ለጎን የሚከተሉት ርምጃች
ቢወሰዱ መልካም ይሆናል የሚል እምነት አለን።

እንደሚታወቀው ባለ ኮከብ ሆቴሎች ላይ የሚገኙ የሠለጠኑ ባለሙያዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው፤ ወደ ታች ወረድ እያልን ስንሄድ ግን አሃዙ አነስተኛ ይሆናል። ከዚህ አንጻር
የባለሙያ አቅርቦትና ጥራት ከላይ ጀምሮ ወጥ እንዲሆን ስትራቴጂ ቀርፆ መሥራት ተገቢ ነው። የተሻሻሉ ሥልጠናዎችን መስጠት በሚቻልበት መንገድ ላይ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር
በመተባበር ስርዓተ ትምህርቱን ከመከለስ ጀምሮ ሌሎች ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድም ያስፈልጋል።

በተለይ ክህሎት ከማዳበር አንጻር እንደ ሀገር አንድ የልህቀት ተቋም መገንባት ይገባል። ለዚህ ርምጃ እንደ ቱሪዝም ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት አይነት ተቋማትን ማጠናከር ላይ
መሠራት ይኖርበታል። እስካሁን መሰል የልህቀት ማእከላት ባለመኖራቸው ምክንያት ትልልቅ ሆቴሎች፣ የቱር ኩባንያዎች እና ኢንተርናሽናል ሆቴሎችን ለቦታው የሚመጥኑ
ባለሙያዎችን ለማግኘት ሲያዳግታቸው ተመልክተናል። በመሆኑም በዚህ በኩል የሥራና ከህሎት ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴርና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ የበኩላቸውን ድርሻ
መወጣት ይኖርባቸዋል።

ዳግም ከበደ

አዲስ ዘመን ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You

ለኮንስትራክሽን ዘርፉ የሥራ ላይ የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንትን የገበያ ድርሻው እያደገ የመጣው የሀገር
የጤና መኮንኑ አርሶ አደር
ደህንነትና ጤንነት ያነቃቃው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርት

© 2024 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

https://press.et/?p=131539 3/3

You might also like