Apo Harer

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 20

-

እቅበተ እምነት

እንዳለ ተፈራ
ሐረር አማኑኤል

ነ.መለኮት ኮሌጅ
Contents
1. መግቢያ.................................................................................................................................................2

2. ትርጉም.................................................................................................................................................2

3. እምነትእናአመክንዮ.................................................................................................................................3

3.1. በታሪክ ውስጥ.....................................................................................................................................3

3.2. በዘመኑ የነበሩ አሳቢዎች.......................................................................................................................4

4. የክርስትና እውነትነት ለማወቅ..................................................................................................................4

4.1. የመንፈስ ቅዱስ ሚና...........................................................................................................................5

ክርስትና እውነት መሆኑን የምናውቀው እራሱን ራሱን በምስክርነት በገለጠው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።አማኝ
ሲያምን መንፈስ ቅዱስ ውስጡ ያድራል (ገላ 3፡26፣4፡6)፡፡ለማያምነው ደግሞ ክርስትና እውነት ነው የሚል ምስክርነት
ሳይሆነ ወቀሳ ያቀርብበታል (ዮሐ 16፡7-11)፡፡.......................................................................................................5

4.2. አመክንዮ እና ማስረጃ..........................................................................................................................5

4.2.1. ሥነ-አመክንዮ.................................................................................................................................5

5. እቅበት-እምነትእንደመሳርያ.....................................................................................................................5

5.1. ክርስትና እውነት ለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣል..........................................................................................5

5.2. የክርስትና እምነትን ይጠብቃል..............................................................................................................6

6. እቅበት-እምነትስራ ላይ............................................................................................................................6

6.1. ጥቃት መሰንዘር (offensive)................................................................................................................7

6.2. እቅበተ-እምነትምካቴ..........................................................................................................................8

7. የእቅበተ-እምነትአስፈላጊነት....................................................................................................................8

7.1. እቅበተ-እምነት የወንጌል አገልግሎትን ይረዳል.........................................................................................8

7.2. ባህሉን ለክርስትና እንድናስገዛ ይረዳናል..................................................................................................9

7.3. የአማኞችን እምነት ያጠናክራል።..........................................................................................................9

7.4. ልጆቻችንን ዓለምን እንዲገጥሙ እንድናዘጋጅ ይረዳናል..........................................................................10


8. የእቅበተ እምነት አተገባበር መመሪያዎች......................................................................................................10

9. እቅበተ-እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?...................................................................................................11

10. ንፅረተዓለም.....................................................................................................................................13

11. አስተምህሮ......................................................................................................................................14

11.1. ህላዌ እግዚአብሄር.........................................................................................................................14

11.1.1. በእርግጠኝነት አለ..........................................................................................................................14

11.1.2. እግዚአብሄር የለም፡-.......................................................................................................................14

11.1.3. አራቱ ሙግት............................................................................................................................15

የስነኑባሬሙግት............................................................................................................................................15

የኮስሞሎጂ (የፍጥረት)ሙግት........................................................................................................................15

ቴሌሎጂካል (የንድፍ ክርክር)...........................................................................................................................15

የሞራል ሙግት.............................................................................................................................................15

11.1.4. ውስጣዊ መረዳት አምላክን ማወቂያ (inner sense)......................................................................15

11.1.5. እግዚአብሄርን ማወቅ ይቻላል......................................................................................................15

11.2. ትንሳኤ........................................................................................................................................16

11.2.1. እውነታ....................................................................................................................................17

11.3. የመከራ ምንጭ ማነው?.................................................................................................................17

11.3.1. የማያምኑመከራከሪያቸው..........................................................................................................17

11.4. መጸሐፍ ቅዱስ..............................................................................................................................18

11.4.1. ተአማኒነት...............................................................................................................................18

11.4.2. ባለስልጣን................................................................................................................................18
1. መግቢያ
የምናምነውን የምናምነው ለምንድነው? ስለ እግዚአብሄር ስለ ኢየሱስ የክርስትና እምነት እናም እምነታችን በየዕለት
ህይወታችን ላይ የአለውን ፋይዳ ሁሉ ለማስረዳት ይጠበቅብናል፡፡ለሚጠራጠሩን፣በችግር ውስጥ ለአሉ እንዲሁም
ሊያምኑን ለማይፈልጉን ምን አይነት ምላሽ ልንሰጥ ይገባናል፡፡
የማያምኑ ሁሉ ወንጌሉ ለመስማት ፈቃደኞች ቢሆኑ ጥሩ ነበር። እኛ ማድረግ ያለብን ስለ ኢየሱስ ብንነግራቸው ነው፡፡
ወንጌልንም ስንነግራቸው “የምትነግረኝ ነገር ጥሩ ነው እና የቤተ ክርስቲያናችሁ አባል መሆን እፈልጋለሁ ፝ቢሉን እንዴት
መልካም ይሆን ነበር፡፡

በቤተ ክርስቲያናችሁ የአባልነት ቅፅ ላይ መመዝገብ እፈልጋለው ቢሉን መልካም ነበር፡፡ወንጌሉን በምንካፈልበት ጊዜ፣
ብዙውን ጊዜ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ፣ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን መመለስ እና የሌላውን ሰው እምነት እንዴት ትክክል
እንዳልሆነ በእርጋታ ማሳየት አለብን። አጋጣሚ ካገኘን ስለ ኢየሱስ የምሥራች መስበክ ቀላል ነው።

ይህ ዜና እውነት እና ምክንያታዊ መሆኑን ለማሳመን መሞከር ሌላ ታሪክ ነው። ለዚህም ነው እቅበትን ማጥናት
የአለብን። የወንጌል ስርጭት እና እቅበት አብረው የሚሄዱ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ማርክ ሚትልበርግ
እቅበት ላይ የሚሰሩትን “የወንጌል አገልግሎት አገልጋይ”ብሎየጠራቸው።

2. ትርጉም
እቅበት ምንድን ነው? እቅበተ ክርስትና ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ይህ ቃል መጸሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ለምሳሌ
በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ አፖሎጊያ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ተጠቅሶ በአዲስ ኪዳን ላይ ተጠቅሶ እናያለን፡-የሐዋ 22፡1፣
25፡16፣ 1 ቆሮ 9፡3፣ 2 ቆሮ 7፡11፣ፊሊ 1፡7፣ 17 2 ጢሞ 4፡16 1 ጴጥ 3፡15፡፡

ይህ የግሪክኛ ቃል እቅበተ ወንጌልን በፅኑ የሚያረታታው ቁልፍ ቃል በሆነውበ 1 ጴጥሮስ 3:15 ላይ ይገኛል፡“ዳሩ ግን ጌታን
እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት፡፡በእናንት ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር
የተዘጋጃችሁ ሁኑ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት በልባችሁይሁን፟፟።

በበለጠ ምን እንደሆነ ለመረዳት አንዳንድ የስነ-መለኮት ሊቃውንት ትርጓሜን እናነሳለን፡፡ አንዳንድ የእቅበት ትርጓሜዎች
እና ፍቺዎች እናያለን፡፡ አፖሎጂስት እና ፈላስፋው ዳግላስ ግሩቱዊስ የሚከተለውን ፍቺ ይሰጣሉ፡- “ክርስቲያናዊ እቅበት
ተጨባጭ እውነት፣ እና ምክንያታዊ ነው፡፡ አፖሎጄቲክስ የሚለው ቃል የመጣው አፖሎጊያ ከሚለው የግሪክኛ ቃል
ሲሆን‘ መከላከያ’ ወይም‘ መከላከያ’ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ግሮተስ ደግሞ የሰጠው ትርጉም ደግሞ የክርስትና እምነት ተጨባጭ እውነት መሆኑን በማሳየት፣ በአመክንዮ እና ላይ
የተመሰረተ መሆኑን በማሳየት መከላከል መቻል አለብን ይላል።

ግሮተስ ቀጥሎ እቅበተ ወንጌል ከሥነ-መለኮት፣ ፍልስፍና እና ከወንጌል ስርጭት ጋር የተቆራኘ ነው ይለናል። ለወንጌል
ጥብቅና የምንቆም ከሆነ ወይም እውነት መሆኑን የምናሳይ ከሆነ፣ ስለ ነገረመለኮት የጠነከረ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።
እቅበት አንዳንድ የፍልስፍና እውቀትን ይጠይቃል፣ ቢያንስ አንዳንድ የሎጂክ ህጎች እናም ወንጌል ስርጭትን ይደግፋል፡፡
ምክንያቱም የመጨረሻው አላማ አንድን ሰው በኢየሱስ እንዲያምን ክርስትና እውነት እንደሆነ ማሳመን ነው።

ሌላው ፈላስፋ እና አቃቢ-እምነት ዊልያም ሌን ክሬግ ተመሳሳይ ፍቺ ይሰጠናል። “እቅበት ምንድን ነው? አፖሎጄቲክስ
(ከግሪክአፖሎጊያ፡መከላከያ) የክርስቲያን እምነት ምክንያታዊ ማረጋገጫ ለመስጠት የሚጥር ነው።” በሌላ አነጋገር
እቅበት የክርስትና እምነታችን በእውነትና በምክንያት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያሳያል።

ጆንፍሬምእንደተናገረው “እውነታ ሁሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት ስለሚመሰክር ”እውነትና ምክንያት ከእግዚአብሔር


ዘንድ እንደመጣ አክሎ መናገር ይቻላል።
እቅበት እምነታችን የተገነባበትን እውነት ከማግኘት የበለጠ ያሳስበናል። “ከማገልገል በተጨማሪ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ የነገረ
መለኮት ትምህርቶች በአጠቃላይ፣ እግዚአብሔርን በሙሉ አእምሮአችን እንደምንወደው መግለጫ ነው፡፡ እቅበት-ወንጌል
ለማያምኑት የክርስትና እምነትን እውነት ለማሳየት፣ እውነትን ለአማኞች ለማረጋገጥ እና ለመግለጥ ያገለግላል።
በክርስቲያናዊ አስተምህሮ እና በሌሎች እውነቶች መካከል ያለውን ትስስር መመርመርም አስፈላጊ ነው።

እዚህ ላይ፣ ክሬግ እቅበት እግዚአብሔርን በፍጹም አእምሮአችን እንድንወደው፣ እንደሚረዳን፣ ክርስትና እውነት፣
እንደሆነ ለሌሎች እንድናሳይ ይረዳናል ይላል፡፡እምነታችንን ያጠናክራል፣ እና እንዴት ክርስቲያን እንደሆነን እንድንገነዘብ
ይረዳናል፡፡ እቅበት -እምነት በሌሎች የእውቀት ዘርፎች ከሚገኙ እንደ ታሪክ፣ ሳይንስ እና ፍልስፍና ካሉ እውነቶች ጋር
ይዛመዳል።

ጆንፍሬም እቅበት በተመለከተ የበለጠ ሰፊፍቺ ይሰጠናል። እንዲህ ሲል ጽፏል፣ “ክርስቲያኖች ለተስፋቸው ምክንያት
እንዴት መስጠት እንዳለባቸው የሚያስተምር ምካቴ ብለን ልንወስነው እንችላለን።‟ የፍሬምን ፍቺ አደንቃለሁ፣
ምክንያቱም ሌሎች ትርጓሜዎች እቅበት የእምነት መከላከያ ብቻ ነው የሚመስለው።

3. እምነትእናአመክንዮ
ክርስትናችን እውነት ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ መስጠት ይቻላል? በእምነት ነው?በእግዚአብሄር ቃል ባለስልጣንነት ላይ
የተንጠለጠለ ነው?በሌላ አባባል የእግዚአብሄር ይህን ብሏል እና እናምነዋለን ዓይነት ነው?ሃይማኖታዊ ልምምዶች
ናቸው ለዚህ ጉዳይ እንደ ምላሽ ልንሰጣቸው የምንችላቸው?ሌላው ጥያቄ ደግሞ ያለ አመክንዮ ማረጋገጫ ማግኘት
ስለማይቻል እምነታችንን ለማረጋገጥ አመክንዮ መጠቀም አስፈላጊ ነው?

3.1. በታሪክ ውስጥ


ቅዱስ አውገስጢኖስ እምነት መሰረቱን መጣል የአለበት በእግዚአብሄር ቃል እና በቤተ ክርስቲያን ስልጣን ላይ ነው፡፡
አመክንዮ መረዳት ለመደገፍ አስፈላጊ ነው የሚል ዕሳቤ አዳብሯል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ስልጣን ካልተገፋፋው በስተቀር በወንጌል ለአምን አልችልም ነበር ብሏል፡፡በትልቅ ባለስልጣንነት ሊያዝ
የሚገባው ቃለ እግዚአብሄር ነው፡፡አንድ ሰው ከማወቁ በፊት ሊያምን ይገባዋል ብሎ ሀሳብ ሰንዝሯል፡፡እዚህ ጋ ባታምኑ
አትረዱም የሚል ቃለ እግዚአብሄር አለ (ኢሳ 7፡9)፡፡

አምላክን ለማመን የትኞቹን ሰዎች እና መጸሐፍ ልናምን እንደሚገባን ልናውቅ ይገባናል፡፡የእግዚአብሄር ስልጣን ማመን
ራሱ መሰረቱን ማድረግ የአለበት ምልክቶች ላይ ሲሆን ያም ተአምራት እና ድንቆች ማለታችን ነው፡፡የአውገስጢኖስ
ስህተት የሚመነጨው ስልጣን ብሎ ሲል የእግዚአብሄር ቃል እና ሁሉንም ትውፊቶችን ማለቱ ነው፡፡

ቅዱስ ቶማስ አኩናስ በእምነት ላይ የተመሰረት እውነትን እና በአመክንዮ ላይ የተመሰረተ እውነትን ነጣጥሎ ለማየት
ሞክሯል፡፡አመክንዮ እርግጠኝ ሊያደርገን የሚችል ነው፡፡ለምሳሌ የእግዚአብሄር ህላዌ ለማረጋገት የምንሞክረው
በአመክንዮ ነው፡፡ሲሆን በአመክንዮ ላይ ያልተመሰረተ እምነት እርግጠኛ አያደርገንም፡፡ለምሳሌ ስላሴን ለማስረዳት
አመክንዮን እንጠቀማለን፡፡

እንደ አውጉስቲን ሁሉቶማስ አኩናስም "እምነት" በስልጣን ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብሎ ያምናል፡፡በመጨረሻ ግን
በአመክንዮ መረጋገጥ አለበት ይህም ማለት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ማስረዳት የምንችል መሆን አለብን ማለት ነው፡፡
ወደ እምነት ለመመራት መንገዱ → የተፈጸሙ ትንቢቶችና ተአምራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የሰጡት
ምሥክርነት →→ክርስቲያናዊ እምነትን ያመጣል ማለት ነው፡፡

ጆን ሎክ ሌላኛው አክራሪ የአመክንዮ ሰው ነው፡፡ሃይማኖታዊ እምነት ማረጋገጫ እንድንስጥ የሚያደርገን መሰረቱን


አመክንዮ ላይ ካሳረፈ ብቻ እና ብቻ ነው ይለናል፡፡እምነት በአመክንዮ መፈተና አለበት ብሎ ያምናል፡፡

ሄንሪ ዶድዎል (1700–1784)፡-በወቅቱ እያደገ የመጣውን ምክንያታዊነት ተቃውሞታል፡፡ይህ ሰው እንደ ካህዲም ይቆጠር
እንጂ ነገር ግን ከዘመኑ የቀደመ አስተሳሰብ ስላለው ብቻ ነው፡፡ይህ ሰው እምነት ምንጩ መሆን የአለበት መንፈስ ቅዱስ
በሰው ውስጥ ስራ ውጤት ነው ብሎ ያምናል፡፡በሌላ ቋንቋ እምነት መነሻ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ በምእመን ልብ
መስራቱን ነው።የዚህ ሰው ዕሳቤ በጆን ዊስሊ ዋይት ፊልድ በመሳሰሉት ሪቫይቫሊስቶች ላይ ታላቅ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

3.2. በዘመኑ የነበሩ አሳቢዎች


-ሁለት ዓይነት አስተሳሰብ ጎልብቶ ወጥቷል፡፡እምነት በምክንያት የሚደገፍ መሆን አለበት የሚል አና አመክንዮ በእምነት
ጉዳይ ምንም የሚጫወተው ሚና የለም የሚል ነው፡፡

ባርዝ እና ቡልትማን፡-ምንም ይሁን ምን በሰው አመክንዮ አቅም ሰው ወደ እግዚአብሄር መቅረብ አይቻለውም የሚል
ምልከታ ነው፡፡እግዚአብሄር በክርስቶስ የገለጠውን ብቻ ማመን ነው የሚገባን ብሎ ያምናል፡፡ምክንያቱም እግዚአብሄር
ምጡቅ ስለሆነ ከሰው አመክንዮ በላይ ነው፡፡በምንም መልክ እግዚአብሄርን ሊያብራራው የሚችል መነጸጸሪያ ማቅረብ
አይቻልም የሚል ምልከታ ነው፡፡

በእምነት መዝለል፡-ባርት ይህን የግል ሐሳብ ጎላ አድርጎ ገልጿል፡፡ያም ሰው ከአምላክ ጋር ለመገናኘት የሚያስፈልገው
መለኮታዊ-አነሳሽነት (sovereign divine initiative) እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ሰው በሃጢያት የጠፋ ስለሆን
እምነትን አፈፍ የሚያደርግበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም፡፡ሰው እንዲያምን ተፅዕኖ ሊያሳርፍ የሚችለው መንፈስ
ቅዱስ ብቻ ነው፡፡

ቮልፍሃርት ፓንነንበርግ፡-ግልጽ በሆነ መንገድ ባቀረበበት ሬቬሌሽን በታሪክ ውስጥ በሚለው መጸሐፉ (1961) መገለጥ
አምላክ በታሪክ ውስጥ ያደረገውን የሚያሳይ ነው እንጂ የሰው ቃላት መሆን የለበትም፡፡ክርስትና በሳይንሳዊ መንገድ
መፈተን አለበት፡፡በክርስትና ውስጥ የአለው ታሪካዊ መሰረቶች ከተናወጡ ተረት ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡

4. የክርስትና እውነትነት ለማወቅ


ክርስትና እውነት መሆኑን በምን እናውቃለን?ምናልባት ይህን ጥያቄ ብዙ ሰው ጠይቆት ሊሆን ይችላል፡፡በእግዚአብሄር
ህላዌ አምናሉ (እግዚአብሄር እንዳለ)፣ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ሕይወት ለዋጭ የሆነ ህይወትን
ተለማምጃለሁ ግን እውነት መሆኑን እንዴት ለማስረዳት እችላለሁ?ክርስትና እውነት መሆኑን ማወቅ እና እውነት
መሆኑን ማሳየት የተለያዩ ናቸው፡፡

4.1. የመንፈስ ቅዱስ ሚና


ክርስትና እውነት መሆኑን የምናውቀው እራሱን ራሱን በምስክርነት በገለጠው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።አማኝ
ሲያምን መንፈስ ቅዱስ ውስጡ ያድራል (ገላ 3፡26፣4፡6)፡፡ለማያምነው ደግሞ ክርስትና እውነት ነው የሚል ምስክርነት
ሳይሆነ ወቀሳ ያቀርብበታል (ዮሐ 16፡7-11)፡፡

4.2. አመክንዮ እና ማስረጃ


በዚህ ውስጥ አደጋ አለ። አንዳንድሰዎች ፈጽሞ አይገባንም ይሉ ይሆናል፡፡ ለእምነት ጥብቅና ለመቆም ጥረት አታድርግ
ብቻ ወንጌልን ስበክ መንፈስ ቅዱስ ይስራ ብለው ይከራከራሉ፡፡

4.2.1. ሥነ-አመክንዮ
ሎጂክ ሎጎስ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው፡፡ለመሆኑ አመክንዩ የሚለው ቃል ምንድነው?የግፅዝ ቃል ሲሆን አመከነየ
ከሚል ግስ የወጣ ነው፡፡አመከነየ ማለትም ምክንያታዊ ባለምክንያት ውይ ምክንያተኛ ሆነ ያም ማንኛውንም ነገር
ምክንያታዊ በመሆን ማየትን መረዳትን ወይም ማስረዳትን ማሳመንን ወይም ማመንንን መመልከትን ስለሚገልፅ
ለሎጂክ ትክክለኛ ምትክ መሆን ይችላል (መሰረታዊ 11)፡፡

ነገር ግን ሎጂክ እንደ ትምህርት ዘርፍም ስለሚያገለግል ስነ-አመክንዮ በማለት እንጠቀማለን፡፡ስነ-አመክንዮ ትክክለኛ
ምክንያት ተጠየቃዊ ፍሰትን የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው፡፡በሌላ አባባል በህግጋት ይመራል፡፡
ሙግት የሚለው ሀሳብ ወደ አንድ ድምዳሜ ለመድረስ የምናቀርበው ምክንያት ማለት ነው፡፡በሎጂክ ሙግት ይበረታታል
እንጂ የሚጣጣል ጉዳይ አይደለም፡፡1

5. እቅበት-እምነትእንደመሳርያ
5.1. ክርስትና እውነት ለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣል
የመጀመሪያው ሀሳብ ክርስትና እውነት ለመሆኑ ማረጋገጫ ወይም ማስረጃ ማቅረብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን
በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግልፅ አስቀምጦታል፡፡

በወንጌሉ መጨረሻ ላይ አካባቢ፣ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች ብዙ
ምልክቶችን በደቀ መዛሙርት ፊት አደረገ። ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥
አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።” ( ዮሐንስ 20፡30-31)።

ዮሐንስ መጽሐፉ ኢየሱስ መሲሕ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እና አምላክ ራሱ መሆኑን ለማሳየት የተጻፈ ነው። ሉቃስ
ወንጌሉን የጻፈው ለተመሳሳይ ዓላማ ነው (ሉቃስ 1፡1-4 ተመልከት)። በተመሳሳይ መልኩ፣ ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ሞትና
ትንሣኤ ሲጽፍ፣ ስለ ትንሣኤው ምስክሮች ብዛት አጽንዖት ሰጥቷል (1 ቆሮ. 15፡3-8)።ጳውሎስ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን
የሚያረጋግጥ ማስረጃ እያቀረበ ነው።

በክርስቶ ስለ ማመን ምክንያታዊ መሠረት የምንሰጥባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።መጽሐፍ ቅዱስ በጥንቱ ዓለም ከነበሩት
በጣም ታማኝ ሰነዶች መካከል መሆኑን ማሳየት እንችላለን። የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊነት (ታሪካዊ ትክክለኛነት) እና
ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን በማቅረብ ሰዎች ስለ አምላክ፣ ስለ ታሪክ፣ ስለሰው ሁኔታ እና ስለ ኢየሱስ
ትክክለኛ መግለጫ አድርገው እንዲያምኑት ልንመራቸው እንችላለን።
(በእምነት፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነ ይገነዘባሉ፣ ምንም እንኳ የማያምን ሰው እንደዚያ
እንዲመለከተው መጠበቁ ምክንያታዊ አይመስለኝም።) የኢየሱስ ትንሣኤ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ማሳየት እንችላለን።
ብዙ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ትንሣኤ እውነተኛና ታሪካዊ ክስተት ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ውስጥ ላሉት
ሌሎች ክስተቶችም የአርኪኦሎጂ ማስረጃዎችን ማቅረብ እንችላለን።

አንድን ወደ እግዚአብሔር የሚያመለክቱ ብዙ ክርክሮችም አሉ። አጽናፈ ሰማይ ስላለ፣ የአጽናፈ ሰማይ መንስኤ መኖር
አለበት፣ ምክንያቱ ደግሞ እግዚአብሔር ነው ብለን ልንከራከር እንችላለን። ሥነምግባር ስላለ የዚያ ሥነ ምግባር
ተጨባጭ እና ሥልጣናዊ ምንጭ መኖር አለበት እና ያምንጭ እግዚአብሄር መሆኑን ማሳየት እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር
የአመክንዮ እና የምክንያት ምንጭ ነው ብለን መከራከር እንችላለን። ለሰው ልጅ ሕልውና የተስተካከለ ሥርዓት ያለው
አጽናፈ ዓለም እንዲኖር ያደረገው እርሱ ነው ብለን መከራከር እንችላለን።

5.2. የክርስትና እምነትን ይጠብቃል


ሁለተኛው እቅበት-እምነት ጉዳይ የክርስትና እምነት መከላከል ነው። ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን “በወንጌል
ጥበቃና” (ፊልጵስዩስ 1፡7, 16) ስለቆሙ አመስግኗቸዋል። ፍሬም እንደተናገረው፣ “በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉት
አብዛኛው የጳውሎ ስጽሑፎች በዚህ መልኩ እቅበተ-ወንጌልን ስራ የሚጠይቁ ናቸው።

ለጢሞቴዎስ ትምህርቱን እንዲጠብቅና ከሐሰት ትምህርት እንዲጠነቀቅ ነግሮታል። እንደ አለመታደል ሆኖ፣
ክርስቲያኖች ሁል ጊዜ ተቃውሞዎችን መመለስ እና እውነተኛውን እምነት በሐሰት አስተማሪዎች እንዳይዛባ መከላከል
አለባቸው።

1Geisler, Norman L. ; Brooks, Ronald M.: Come, Let Us Reason : An Introduction to Logical Thinking. Grand Rapids,
Mich. : Baker Book House, 1990, S. 21
ይሁዳ የጻፈውን ተመልከት፡- ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለመዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ጓጉቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን
አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ
በሥጋ ነፍስ ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ክደዋል። ( ይሁዳ 3-4 )“አንዳንድ ሰዎች
”ሾልከው ወደ ጉባኤው ስለሚገቡ ይሁዳ“ ለእምነት እንዲታገሉ” አበረታቷቸዋል።

በዚህ ክፍል ላይ አስተያየት ሲሰጥ ማይክል ግሪን እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “ይሁዳ የዚህ እምነት መከላከያ ቀጣይነት ያለው፣
ብዙ ዋጋ ያለው እና የሚያሰቃይ መሆኑን ለማጉላት ኢፓጎኒዚስታይ የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ቅጥይ መሆን
የሚያስከፍለውን ዋጋ፣ በዚያ ዘመን ለነበረው ሰው ሊረዳው በሚችል መንገድ መግለጽ የሚያስከትል ሥቃይ ነው። እንደ
ወታደር ወንጌልን መከላከል ነበረባቸው ወይም እንደ አትሌቶች በአደባባይ እንደሚወዳደሩት ይታገሉ ዘንድ የቀረበ ጥሪ
ነው፡፡።

6. እቅበት-እምነትስራ ላይ
ሁለት ዓይነት እቅበተ-እምነት እንዳለ ምሁራን ይናገራሉ፡፡እነዚያም አጥቂነት (አውንታዊ) እና ምካቴ (አሉታዊ) ናቸው፡፡
አውንታዊ የምንለው ለክርስትና እምነት ማስረጃ በማቅረብ የሚሞግት ነው፡፡አሉታዊ ያልነው ደግሞ እነዚያን የክርስትና
እውነቶችን ለመከላከል የሚደረግ ጥረት ነው፡፡

6.1. ጥቃት መሰንዘር (offensive)


እቅበት-ወንጌልን ለጥቃት ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ይህ ማለት ግን ሰዎችን ለማናደድ አስበናል ማለት አይደለም።
ይልቁንም የሌሎች (በአምላክ የለሽም ሆነ የሌላ እምነት ተከታዮች) እምነት እውነት አለመሆኑን ለማሳየት እውነትን
እና አሳማኝ ምክንያቶችን ማቅረብ እንችላለን።

“እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚጠራው የማያምኑትን ተቃውሞ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ በሐሰት ላይ ጥቃት


እንዲሰነዝርም ጭምር ነው። “ክርክርን” ስንል እንጣላለን ወይም እንነታረካለን ማለት አይደለም። ሙግት አንድን ነጥብ
የሚያረጋግጡ ተከታታይ ምክንያቶች፣ ማስረጃዎች እና/ ወይም እውነታዎች ናቸው። መሟገት ማለት አንድን አቋም
ለመውሰድ ምክንያትን ማሳየት ነው።

ብዙውን ጊዜ፣ የሌሎች ንፅረተ-ዓለምን በሙግት ሂደት ወጥነት ይጎድለዋል፡፡እግዚአብሔርን የማናምንበት ምንም
ምሁራዊ ምክንያት እንደሌለለ ለሌሎች ስናሳይ - በእርግጥም እግዚአብሔርን አለማመን በመጨረሻ ፀረ-ምሁራዊ
መሆኑን ቁልጭ ብሎ መታየት ይጀምራል፡፡መጽሐፍቅዱሳዊ እውነትን ወደ ብርሃን እናመጣለን፡- “ሰነፍ በልቡ አምላክ
የለም ይላል” (መዝ. 14:1፣ 53:1)።

ቲም ቼስተር እና እስቲቭ ቲሚስ እንደሚሉት፣ “በምክንያት ላይ የተመሰረተ እቅበተ-ወንጌል ሚና አለማመን


ከጭንቅላት ችግር ይልቅ የልብ ችግር መሆኑን ማሳየትነው። ሰዎች እንቅፋት እንደሆኑ ሊናገሩ ይችላሉ።

ለእምነት እንቅፋት የሚሆነው በምድር ላይ የሚከሰት ስቃይን ማብራራት አለመቻል ወይም ተአምራት አሉ ብሎ
ማስረዳት አለመቻል ወይም የሌሎች ሃይማኖቶች መኖር ነው ብለው አንዳንዶች ይናገራሉ። የእቅበተ-እምነት ሚና
እነዚህ እውነተኛ አለማመን መንስኤዎች እንዳልሆኑ ማሳየት ነው። ሰበቦችን ለመንቀል እና ዓመፀኛ ልቦችን ማጋለጥ
አስፈላጊ ነው። ”ግሩቱዊስ እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “እቅበተ-እምነት ሰዎች ክርስቶስን እንደ ጌታ እንዳይቀበሉ
የሚከለክሉትን ምሁራዊ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ስለዚህ እንደ ቅድመ-
ስብከተ ወንጌል ያገለግላል።

የእቅበተ-እምነት ጨካኔ ሊመስል ይችላሉ፣ ነገር ግን ለዚህ መጸሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ አለ። ጳውሎስ ስለቆሮንቶስ
ክርስቲያኖች በጻፈው ጊዜ ድካሙንና ትሕትናውን ተናግሯል። ሆኖም፣ ውሸትን ለማጥቃት እንደማይፈራም ጠቁሟል።
በሥጋ ብንመላለስም እንደ ሥጋ ፈቃድ አንዋጋም።የጦር ዕቃችን የሥጋ አይደለምና፥ ምሽግን ለማፍረስ በእግዚአብሄር
ፊት ብርቱ ነው፡፡ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ክርክርና ከፍ ያለውን አሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፥
ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፤ መታዘዛችሁ በተፈጸመ ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀለው
ተዘጋጅተናል።( 2 ቆሮ. 10:3-6 )

በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሱ ክርክሮች እና አስተያየቶች ምንድንናቸው? ዴቪድ ጋርላንድ ሲናገር “ስለዚህ
እነዚህ ምሽጎች ሰዎች የወንጌልን እውነት ለመከልከል ሲሉ የሚገነቡትን ምሁራዊ ክርክሮች ሊያመለክቱ ይችላሉ።

ጳውሎስ እነዚህን አስተሳሰቦች ለማፍረስ ብቻ ሳይሆን ይህን የሚይዙትንም ሰዎች ከቤተክርስቲያን ለማስወገድ
ተዘጋጅቷል። ("አለመታዘዝን ሁሉ ቅጡ" ማለት ይህ ነው።)
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከወንጌል እውነት ጋር የሚቃረኑ አመለካከቶችን የሚይዙ ሰዎች እንደሌሉን ተስፋ
አደርጋለሁ። እነርሱን ለክርስቶስ ልናሸንፋቸው ከፈለግን ወንጌልን ከመቀበላቸው በፊት የአስተሳሰባቸውን ድክመቶች
እና የእውነት እጦት መግለጥ ያስፈልገን ይሆናል።

እቅበተ-እምነት እንደ ማጥቃት ከወሰድነው በሁለት ይከፈላል፡፡ያም የተፈጥሮ ሥነ መለኮት (natural theology)ና
በክርስቲያናዊ ማስረጃዎች ይከፋፈላሉ። የተፈጥሮ ስነ-መለኮት (natural theology) በስሩ ስነ-ኑባሬ (ontological)
አፅናፈ-ዓለም (cosmological) የንድፍ ክርክር (teleological) እና የስነ ምግባር ክርክር፡፡የክርስትና ማስረጃ የምንለው
ደግሞ የተፈፀሙ ትንቢቶች፣የወንጌላት-ታሪኮች ተአማኒነት፡፡
6.2. እቅበተ-እምነትምካቴ
እቅበተ እምነት ን ዑስ ክፍልም አለው።ከተፈጥሮ ሥነመለኮት ጋር በሚመሳሰል ክፍል ውስጥ ይቅርታ መጠየቅ በቲኦሎጂ
ላይ የሚነሳውን ተቃውሞ ያስወግዳሉ። እዚህ ላይ ዋነኛው አከራካሪ ጉዳይ የአምላክን ጽንሰ ሐሳብና የክፋት ችግር
አለማጣጠሙ ነው። ከክርስቲያናዊ ማስረጃዎች ጋር መመሳሰል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩ ትንቢቶችን
ከመቃወም ይከላከላል።

7. የእቅበተ-እምነትአስፈላጊነት
በዚህ ክፍል መጀመሪያ ላይ እንደገለጽኩት፣ ሁሉም ሰው ወንጌልን ለመስማት እና ለማመን ዝግጁ ቢሆን ጥሩ ነበር። ግን
ይህ ስላልሆነ ለእምነት መከላከል አለብን። “መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ስለሚል (ይህ የሚሰራው ለአማኝ ብቻ ይሆን)
”የሚሉበት ጊዜ አልፏል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው ካላመኑ ወይም በአምላክ የማያምኑ
ከሆነ, እንዲህ ያለው መግለጫ ምንም ተጽእኖ አያመጣም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተጨባጭ እውነት እና ሥልጣናዊ ነው፣
እናም ከመጽሐፍ ቅዱስ ለሰዎች ስንናገር እውነትን እንናገራለን፣ ያለምክንያት መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስን
እውነት ለማሳየት ይችላል። ነገር ግን መንፈሱ የእኛን“ ለእምነት መሟገት”ሊጠቀምበት ይችላል።

ክርስቲያኖች በዚህች አገር ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው የሚለውን እውነታ ልንይዘው
ይገባል።ክርስቲያን ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት የላቸውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለምን እንደ ሥልጣን
መቆጠር እንዳለበት አንዳንድ ማስረጃዎችን ሳናቀርብ በቀላሉ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መማረክ አስቸጋሪ ነው።

የምንኖረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በብዙ ሰዎች፣ ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች ሳይቀር የተተወበት ጊዜ ስለሆነ
መጽሐፍ ቅዱስ እምነት የሚጣልበት ለምን እንደሆነ ማስረጃዎችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆን አለብን። እንዲሁም ሰዎች
በክርስትና እንዲያምኑ ለማሳመን የተለያዩ አመለካከቶችን እና ክርክሮችን ለመጠቀም ዝግጁ መሆን አለብን።

7.1. እቅበተ-እምነት የወንጌል አገልግሎትን ይረዳል


ቀደም ሲል እንደተገለፀው እቅበተ-እምነት የስብከተ ወንጌል አገልጋይ ነች።ሁለቱም ሰዎች በኢየሱስ ወደ እምነት
በማምጣት እግዚአብሔርን የማክበር የመጨረሻ ግብ አላቸው።ወንጌልን ስንካፈል ሰዎች ለምን እንዲያምኑበት
ምክንያት ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለብን።
እንደ እኔ ከሆናችሁ፣ ከዚህ በፊት ወንጌልን ማካፈል ተስኖሃል ምክንያቱም የማያምን ሰው የሚጠይቃቸውን ከባድ
ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንደምትችል ስለማታውቅ ነው።እነዚህ ጥያቄዎች ስለ ሳይንስ እና ስለ አጽናፈ ሰማይ
አመጣጥ ወይም እግዚአብሔር መልካም ከሆነ በዓለም ላይ ለምን ክፋት እንደሚኖር ላይ ሊሆኑ ይችላሉ።ክርስቲያን
ያልሆነ ሰው በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ አንዳንድ አሳፋሪ ነገሮችን ማሰረዳት ሊጠበቅበት ይጋል፡፡

ዊልያም ሌ ንክሬግ እንደዚያ ነው ብሎ ያምናል።ብዙ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ለማያምኑት በፍርሃት ብቻ


አይካፈሉም።ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች አንድ ጥያቄ እንዳይጠይቃቸው ፍራቻ አላቸው፡፡ “መጽሐፍ ቅዱሳዊ የዓለም
እይታ በሰው ሕይወት ላይ ሥር ነቀል ተጽዕኖ አለው”የሚል ፍራቻ አላቸው፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ-የዓለም እይታ-በሰው-
ሕይወት-ላይ-አክራሪ-ተፅእኖ-አለው? ከፍራቻ የተነሳ ዝምታን ምርጫ ያደርጋሉ፡፡እናም ብርሃናቸውን ከእንቅብ በታች
ያውላሉ፡፡
ምክንያቱም አንድ ሰው ላመነበት ነገር በቂ ምክንያት እንዳለው እና የማያምን ሰው ሊያነሳው ለሚችለው ዓይነተኛ
ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ጥሩ መልስ እንዳለው ከማወቅ በላይ በራስ መተማመንን እና ድፍረትን ያነሳሳል።በእቅበተ-
እምነት ላይ የሚሰጥ ጥሩ ስልጠና ከፍርሃት የለሽ የወንጌል ስርጭት ቁልፍ አንዱ ነው።በዚህ እና በሌሎች በርካታ
መንገዶች እቅበተ-እምነት እያንዳንዱ አማኞችን በማጠናከር የክርስቶስን አካል ለመገንባት ይረዳል።

እቅበተ-እምነት ወንጌልን በማስረጃ ስለሚደግፍ ለወንጌል አገልግሎት እንደሚረዳ አምናለሁ። ነገር ግን በጣም ጥሩዎቹ
ክርክሮች ብቻ ሰዎችን ወደ ክርስትና መለወጥ አይችሉም። አንድን ሰው ክርስቲያን ሊያደርግ የሚችለው መንፈስ ቅዱስ
ብቻ ነው። አንድን ሰው ወደ እምነት ለማምጣት እቅበተ-እምነት ሊመርጥ ይችላል፣ ነገር ግን ጥሩ ምክንያት እና ብዙ
ማስረጃ ብቻ አንድንሰው አያድኑም። ነገር ግን፣ እግዚአብሔር አንድን ሰው ለማዳን ክርክራችንን እና የወንጌል
አቀራረባችንን ለመጠቀም ከመረጠ፣ ይህን ማድረግ ይችላል።

ከስብከተ ወንጌል ጋር የተያያዘ አንድ ተጨማሪ ነጥብ፡- ክርስትና በማኅበረሰባችን ውስጥ ያለው ተጽእኖ አነስተኛ
ስለሆነ፣ ሰዎች በምንም መልኩ እንዲሰሙን የክርስትናን እምነት ምክንያታዊነት ለማቅረብ ጠንክረን መሥራት
ያስፈልገናል። ብዙ ሰዎች ክርስትናን እንደ ሞኝነት ስለሚቆጥሩት፣ በምክንያታዊነት ወጥነት ያለው መሆኑን ማሳየት
አለብን። በአገራችን ቀደም ባሉት ጊዜያት ክርስትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አማራጭ መሆኑን ለማሳየት ጠንክረን
መሥራት አይጠበቅብንም, አሁን ግን እናደርጋለን. ክሬግ እንዳስቀመጠው፣ “ሁኔታው ወደ ፊት እንዳይበላሽ ከተፈለገ፣
ክርስትና ጨካኝ እና እሴቶችን የማሰብ የቀጥታ አማራጭ ሆኖ እንዲቆይ የሀገራችንን የአእምሯዊ ሁኔታ መቀረፅ የግድ
ነው።

7.2. ባህሉን ለክርስትና እንድናስገዛ ይረዳናል


ወንጌልን በትክክል እና በፍቅር ማካፈል እንችላለን እናም ሰዎች ላያምኑ ይችላሉ። ወንጌልን መከላከል እና ለምን እውነት
እንደሆነ ብዙ ምክንያቶችን መስጠት እንችላለን፣ እና አሁንም ሰዎች በኢየሱስ ወደ እምነት ለመምጣት አሻፈረኝ ሊሉ
ይችላሉ። ሆኖም፣ ክርስቲያኖች አሁንም ዓለምን በክርስቲያናዊ እሴቶች እና በክርስቲያናዊ የዓለም አተያይ እንዲለወጡ
ጥረት ማድረግ እንችላለን፡፡ በአለም ላይ ከሆንን ፅንስ ማስወረድ ለምን ህገ-ወጥ እንደሆነ እየተከራከርን ከሆነ ለምሳሌ
ከሥነምግባር አኳያ ስህተት መሆኑን ለማሳየት ምክንያታዊ ክርክር ሊኖረን ይገባል። በሕዝብ አደባባይ ለሚነሱ ሌሎች
በርካታ ጉዳዮችም እንዲሁ።

7.3. የአማኞችን እምነት ያጠናክራል።


እቅበተ-እምነት ተመሳሳይ ጥቅም ሊሰጠን ይችላል።እምነታችን እግዚአብሔር የሰጠን ነው (ኤፌ. 2፡8-9፤ ፊልጵ. 1፡
29)። በእግዚአብሄር ማመን ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገር ነው፡፡ በዚህም እግዚአብሔር በእርሱ እንድናምን ልባችንን
መክፈት አለበት። ከተፈጥሮ በላይ በሆነ እምነት በእግዚአብሔር ብናምንም፣ አሁንም ለዚያ እምነት አመክንዮአዊ፣
ምክንያታዊ፣ ግልጽ መሠረት አለ። እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን ፈጠረ፣ በእውነት ሰው ሆነ፣ በመስቀል ላይ ሞተ፣
በእውነት ከመቃብር ተነስቷል፣ የሚሉት እነዚህ ተጨባጭ እውነቶች የክርስትናን እምነት ያጠብቃሉ፡፡

እንዲያውም ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች የሚለየው አንዱ በእውነተኛ ታሪካዊ እውነታዎች ላይ የተመሰረተ
ተጨባጭ መሆኑ ነው፡፡ስለዚህ ክርስተና በስሜት ላይ የተመሰረተ መንፈሳዊነት የለም፡፡

ጆንፍሬም እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ “እቅበተ-እምነት ለአማኝ የቅዱሳት መጻሕፍትን ምክንያታዊነት የሚያሳይ ነው፡፡ ያ
ምክንያታዊነት ለአማኙ ምሁራዊ መሰረት፣ ይሰጣል፡፡ እምነትና በሕይወታችን ውስጥ ጥበብ ያለበት ውሳኔ ለማድረግ
የሚያስችል መሠረት ነው።”
የክርስትና እምነት በጭፍን እምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም። አእምሮን የሚያሳትፍ፣ ምክንያታዊ የሆነ እና ንቁ የሆነ
የእውቀት ህይወትን የሚያበረታታ እምነት ነው።እቅበተ-እምነት ስንማር፣ በማዕበል የምንገፋበ በትምህርትም ነፋስ
ሁሉ ወዲያ እና ወዲህ የማንል፣ በሰው ተንኰል፣ ተንኰለኛም ሽንገላ የማንታለል እንሆናለን” (ኤፌ. 4፡14)፡፡ በእውነት
ላይ ስንመሠርት፣ “እንደ ክርስቶስ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ ትምህርት የአለ ፍልስፍና አያጠፋንም
(ቆላ. 8)፡፡

7.4. ልጆቻችንን ዓለምን እንዲገጥሙ እንድናዘጋጅ ይረዳናል


ዓለማችን በሴኩላሪዝም የተመራች ናት፡፡ ፍልስፍናዋ እግዚአብሔርን በጠረጴዛ ላይ የሚክድ ነው። የሕዝብ ትምህርት
ቤቶቻችን ከክርስትና ውጪ ማንኛውንም ፍልስፍና ወይም እምነት ከሞላ ጎደል እንዲማሩ ያስችላቸዋል። ሳይንስ
የመጨረሻው የእውነት ምንጭ ነው፡፡ የሚለው አመለካከት አምላክ የለም ብሎ ማመን ነው። ማንኛውም ፍልስፍና
በመጨረሻ በእምነት ግምቶች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ማንም ሰው በተጨባጭ ሊያረጋግጥ በማይችለው ሀሳቦች ላይ ነው.
የምንኖረው፡፡ በክርስትና ላይ ጥላቻ እየጨመረ በመጣበት ወቅት ላይ ነን። በአለማመናቸው ለሚጠፉት መስቀል ሞኝነት
ብቻ ሳይሆን በደል ነው።

ልጆቻችንን ማለትም የሕዝብ ትምህርት ቤት፣ የቤት ትምህርት ቤት፣ የክርስቲያን ትምህርት ቤትን እንዴት
ብናስተምርም፡፡በ ሆነ በአንድ ወቅት፣ በኮሌጅ ወይም በሥራ ቦታ ወደ ዓለማዊ አካባቢ ይገባሉ። በእምነታቸው ላይ
የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመቋቋም ዝግጁ ካልሆኑ, አስቸጋሪ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ “የተቃረቡ ክርስቲያኖች” በመሆን
እምነታቸውን ይደብቃሉ ወይም ከዓለም ተለይተው ወንጌላዊ መሆን አይችሉም።
ክሬግ በተለይ የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ለሚገቡ ክርስቲያን ልጆች ይፈራል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ኮሌጅ ውስጥ ክርስቲያን ታዳጊ ወጣቶች ከክርስቲያናዊ ያልሆኑ የዓለም እይታዎች
ጋር በአእምሮ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ ወላጆች በእውቀት ከእምነታቸው ጋር ካልተሳተፉ እና ለክርስቲያናዊ ሥነ-
መለኮታዊ ጽንሰ-ሀሳብ ትክክለኛ ክርክር እና ለልጆቻቸው ጥያቄዎች ጥሩ መልስ ከሌላቸው ወጣትነታችንን የማጣት
እውነተኛ አደጋ ላይ ነን። ልጆቻችንን የመጽሐፍ ቅዱስ መደብሮችን ማስተማር በቂ አይደለም፡፡ ትምህርት እና እቅበተ-
እምነት ይፈልጋሉ። እውነቱን ለመናገር፣ ዛሬ ሰዎች እቅበተ-እምነት ሳያጠኑ ወላጅነትን እንዴት አደጋ ላይ ሊጥሉ
እንደሚችሉ ለመረዳት ይከብደኛል። በመቀጠልም “ልጆቻችንን ለጦርነት ማሰልጠን አለብን” ሲል አክሎ ተናግሯል።
እቅበተ-እምነት ወሳኝ የሚሆንበት ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በግሌ፣ እምነቴን የሚያጠናክር እና
ወንጌልን እንዳካፍል እምነት የሚሰጠኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እውነት ሁሉ ከአምላክ የመጣና ከመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት
ጋር የሚስማማ መሆኑን ስመለከት በአእምሮዬ አርኪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

8. የእቅበተ እምነት አተገባበር መመሪያዎች


8.1. ፀሎት፡-እኛ ሳንሆን የሰውል ልብ የሚከፍት ጌታ ራሱ ነው (የሐዋ. 16፡14)፡፡ክርክርን መርታት ሳይሆን ልብን መማረክ
ይገባል፡፡ታዲያ የእኛ የተራቀቀ መከራከሪያ ነጥብ እና ምሁራዊ አቀራረብ ያለ እግዚአብሄር እርዳታ ይህን መፈጸም
አይችልም፡፡ምሪትን (ዮሐ. 14፡14) በጸሎት ጠይቅ መረዳትን እንዲጨምር (ያዕቆብ. 1፡5) እናም ንግግርን እንዲባርክ
(ቆላ. 4፡6)፡፡
8.2. ቃሉን፡-አንድ አንድ ጥቅሶችን በቃል መያዝ ይገባናል (መዝ. 119፡11፣ 2 ጢሞ. 3፡16)፡፡የእግዚአብሄር ቃል የሚሰራ
እንዲሁም ሀይለኛ ነው (ዕብ. 4፡12)፡፡የእግዚአብሄር ቃል ጥቅስን በአውድ ውስጥ መጥቀስ አስፈላጊ ነው፡፡
8.3. መረጃ ይኑርህ፡-ማንኛውም ከአምልኮት ጋር የአሉ ፅሁፎችን፣ዓለማዊ ፍልስፍና እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን
ይያዙ፡፡የመከራከሪያ ነጥቡን ጠንካራ ደካማ ጉን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ሁሉን ማወቅ ባይቻልም ጥቂት ሀሳቦችን መያዝ
(ሞርሞን፣ዝግመተ ለውጥ ፍልስፍና) ያስፈልጋል፡፡
8.4. ማድመጥ፡-የሚነገርህን በትክክል ማድመጥ እና ምላሽ መስጠት፡፡በማድመጥ ሂደት ውስጥ ነው ምን እንደምንመለስ
ልናውቅ የምንችለው፡፡ስህተቱን፣መከራከሪያውን፣መነሻ ሀሳቡን በመስማት ውስጥ መረዳት ይቻላል፡፡
8.5. ጠይቅ፡-የሚያምኑትን እንዲያብራሩልህ ጥያቄ አቅርብ፡፡ጠለቅ ብለው ወደ ጉዳዩ ሲገቡ ጉዳያቸው በግምት ላይ
የተመሰረተ እንጂ ጠንከር የአለ እንዳልሆነ ይገባቸዋል፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው መጸሐፍ ቅዱስ በስህተት የተሞላ ነው ብሎ
ቢናገር ወሳኝ የሆኑ እንደ ዕብ.9፡27፣ ዮሐ. 3፡16 የአሉ ጥቅሶች ስህተታቸው ምን እንደሆ እንዲያብራራልን ልንጠይቅ
እንችላለን፡፡

8.6. አታቋርጥ፡-ይህ ሰናይ ምግባርም ነው፡፡ምላሽ አለህ ማለት ወዲያው እንድትሰማ ግድ መሆን አለበት ማለት
አይደለም፡፡ማቋረጥ እንደ ልማድ ከተወሰደ መማማር አሸቀንጥረን እንጥለዋለን፡፡
8.7. አተካራ አትግጠም፡-ሰውን የሚተናኮስ ነገር ትክክል አይደለም፡፡ሰዎችን የሚያምኑትን የማመን መብት አላቸው፡፡
ምንም እንኳን የከፋ ስህተት ቢሆንም፡፡የሚናገሩት ነገር የማይገጥም ቢሆንም በሰዎች ላይ ማሾ አግባብ አይደለም፡፡
የሚናገረውን ነገር በቁም ነገር የማንወስድ ካልሆነ ሊያደምጠን ፈቃደኛ አይሆንም፡፡እናንተ ላይ ቢያሾፉባችሁ ምን
ይሰማችኃል?
8.8. አጥና፡-የማታውቀውን ነገር አጥና፡፡ስህተት ብንሰራ ልንደናገጥ አይገባም፡፡የተማርከውን መጸፍ አትርሳ፡፡የቱንም ያክል
ትንሽ ብትሆን እያሻሻልክ ትሄዳለህ፡፡
8.9. ዕድል ተጠቀም፡-ለመናገር እና እምነትህን ለመመከት አትፍራ፡፡ይህን ለማድረግ መሸምደድ መልስ ማዘጋጀትን
መለማመድን አትርሳ፡፡

9. እቅበተ-እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?


እስከዚህ ነጥብ ድረስ አንብበው ከሆነ, የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ መሆን አለበት፡፡እቅበተ-እምነት ከሚደግፉ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሆኑ ትጥቅሶች መካከል አንዳንዶቹ 1 ጴጥሮስ 3: 15; ይሁዳ 3; ፊልጵስዩስ 1:6, 17; 2
ቆሮንቶስ 10:3-6; እና ቆላስይስ 4:6 ሲሆኑ የሚያበረታቱ ግን እነዚህ አንቀጾች ብቻ አይደሉም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ እግዚአብሔር እቅበተ-እምነትን ሚና ሲወጣ ይታያል ያም “እኔ አምላክ ነኝ፣ ስለዚህ በእኔ
እመኑ!” ብቻ አይልም። ቃላቱን በተአምራዊ ተግባራት ያጅባል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክነቱን የሚያረጋግጠው
በብዙ ተአምራዊ ኃይል ሲሆን እነዚህም ብዙውን ጊዜ “ምልክቶችና ድንቆች” ይባላሉ። ኢየሱስ አምላክነቱን
በተአምራት ያሳየ ሲሆን ከእነዚህም ሁሉ የሚበልጠው ትንሣኤ ነው። እግዚአብሔር ስለራሱ ብቻ አይደለም
የሚናገረው; በተግባሩ ያረጋግጣቸዋል። `
ኢየሱስ ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያንና ጸሐፍት ሊፈትኑት ሲሞክሩ ራሱን መከላከል ችሏል። ለምሳሌ ማቴዎስ 16፡1-4
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ኢየሱስን ከሰማይ ምልክት እንዲሰጠው በመጠየቅ ሊፈትኑት ሲመጡ ተመልከቶ።
ፈሪሳውያን “በቃሉ እንዴት እንደሚይዙት” ሲያሴሩ ማቴዎስ 22:15 ን ተመልከት። ኢየሱስ ግብር ስለመክፈል አስደናቂ
መልስ ሰጣቸው፣ ይህም ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነት ቄሳርን ጨምሮ በሁሉም ኃይሎች ላይ ስላለው ታላቅ እውነት
የሚያስተምር ነው (ማቴ. 22፡16-23)።ወዲያው በሚከተለው ምንባብ፣ ኢየሱስ ሰዱቃውያን ስለጋብቻ ያቀረቡትን
ጥያቄ በሚያስገርም ሁኔታ መለሰላቸው (ማቴ. 22፡23-33)።

ጳውሎስም እቃቢ እምነት ነበር። ከሐዋርያት ሥራ የቀረቡትን አንቀጾች ተመልከት፡፡ ጳውሎስም እንደልማዱ ገባ
በሦስት ሰንበትም ቀን ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር፡፡ እያስረዳቸውም ክርስቶስ መከራ ይቀበል ዘንድ
ከሙታንም ይነሣ ዘንድ እንዲገባው አስረዳቸው።ይህ እኔ የምነግራችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው እያለ ሊያሳምናቸው
ሲታትር ይታያል፡፡ ከእነርሱም አንዳንዶቹ አምነው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ እንዲሁም ከግሪክ ሰዎች ብዙዎች
ከሽማግሌዎች ጥቂቶች ያይደሉ ነበሩ።
( የሐዋርያትሥራ 17:2-4 )፡፡
ጳውሎስ በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ ከተማይቱ በጣዖታት መሞላቷን አይቶ መንፈሱ ተበሳጨ። 17 በምኵራብም
ከአይሁድና እግዚአብሔርን ከሚያምኑ ሰዎች ጋር በየቀኑም በገበያ ስፍራ በዚያ ካሉት ጋር ይነጋገር ነበር። (
የሐዋርያትሥራ 17:16-17 )፡፡

በየሰንበቱም ሁሉ በምኵራብ ይነጋገር ነበር፥አይሁድንና የግሪክ ሰዎችንም ያስባብ ነበር። ( ሥራ 18:4 ) ወደ ኤፌሶንም
መጡ በዚያም ትቷቸው ሄደ፤ እርሱ ግን ወደ ምኵራብ ገብቶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር ( የሐዋርያትሥራ 18:19 )፡፡
ወደ ምኵራብም ገባ፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸውና እያሳመናቸው ለሦስት ወራት ያህል በግልጥ
ይናገር ነበር። አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በማኅበሩ ፊት መንገዱን ሲሳደቡ፥ ከእነርሱም ፈቀቅ ብሎ
ደቀመዛሙርቱን ይዞ በጢራኖስ አዳራሽ ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር። በእስያም የሚኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም
የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲሆን ( የሐዋርያትሥራ 19:8-10 )፡፡ እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን
ስለመግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ ሲናገር ፊልክስ ፈርቶ፡—ለአሁኑ ሂድ፡ አለ። እድል ሳገኝ እጠራሃለሁ አለው (
የሐዋርያትሥራ 24:25 ) ይለናል፡፡
ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ሲያብራራ፣ አብዛኛውን ጊዜ ይህን ያደረገው ከሌሎች አይሁዳውያን ጋር ነበር።
የዕውቀታቸው መሠረት ብሉይ ኪዳን ስለሆነ፣ ጳውሎስ እየጠበቁት የነበረው መሲሕ፣ የዳዊት ልጅ እና የሰው ልጅ
እንደሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት ገልጿል።በአቴንስ ግን ጳውሎስ ከግሪኮች ጋር በተለየ መንገድ ማመዛዘን ነበረበት።
አሕዛብንና ነዋሪዎቻቸውን ጨምሮ ሁሉን ስለሠራው እውነተኛው አምላክ ከመናገሩ በፊት “የማይታወቀው አምላክ”
ለተባለው ጣዖት መሠዊያ ተጠቀመ። ከዚያም ጳውሎስ አንዳንድ የግሪክ ባለቅኔዎችን ጠቅሶ፣ እውነት ሁሉ
የእግዚአብሔር እውነት እንደሆነ፣ ምንም እንኳን ከማይመስሉ ምንጮች ቢመጣም (የሐዋርያትሥራ 17፡28)
ለማስረዳት ሞክሯል። ከዚያም ያንን እውነት ተጠቀመ (የሰው ልጆች በሙሉ በሰፊው አነጋገር።

“የእግዚአብሔርዘር”) እውነተኛው አምላክ ግላዊ መሆን እንዳለበት ለማሳየት እንጂ በሰው የተሠራ የወርቅ ወይም
የብር ወይም የድንጋይ ክምር መሆን የለበትም (ሐዋ. 27፡29)።
ጳውሎስ ይህንን መረጃ የተከተለው “የድንቁርና ጊዜ ”አሁን አብቅቷል እና እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ ንስሐ ይጠራቸዋል
ምክንያቱም አንድ ቀን ከሙታን በተነሣው በኢየሱስ በኩል በዓለም ላይ ይፈርዳል (ሐዋ. 17፡30-31)። ) በማለት ነው፡፡

እቅበተ-እምነት ስንወያይ ጳውሎስ ከሰዎች ጋር የተጠቀመባቸውን ሁለት መንገዶች (ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲሁም
የተለያዩ ማስረጃዎችንና ክርክሮችን በመጠቀም) እንደሆነ እንመለከታለን። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን አቃቢ እምነት
እንዲሆን ሲጠይቀው “የጌታ አገልጋይ”“ ማስተማር፣ በትዕግሥት ክፋትን እየታገሠ፣ ተቃዋሚዎቹን በየዋህነት ማረም
መቻል” እንዳለበት ነገረው። እግዚአብሔር እውነትን ወደ ማወቅ የሚያደርሰውን ንስሐ ሊሰጣቸው ይችላል ወደ
አእምሮአቸውም ተመልሰው ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ ከዲያብሎስ ወጥመድ ያመልጣሉ።” ( 2 ጢሞ. 2:24-26 )፡፡ እቅበተ-
እምነትምን እንደሆነ እና ለምን ማጥናት እንዳለብን ካወቅን በውስጣችን ያለውን ተስፋ ለሰዎች ለመስጠት የተለያዩ
ዘዴዎችን መመልከት እንጀምራለን።

10. ንፅረተዓለም
ፓናንቲዝም (panentheim)
ፓንኤንቲይዝም አጽኖት የሚሰጠው በእግዚአብሔርና በተፈጥሮ መካከል ባለው መስተጋብራዊ ግንኙነት ላይ ነው፡፡ በዚህ
አመለካከት ነፍስ በስጋዊ አካል ውስጥ እንዳለች እንዲሁ እግዚአብሔርም በዓለም ውስጥ አለ፡፡ ዓለም እግዚአብሔር
ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከዓለም ይልቃል፡፡ በዚህ ነገረ መለኮት ዓለም እራሱ የተገኘው/ የመነጨው ከእግዚአብሔር
ማንነት ውስጥ እንጂ ከባዶ ኢክስ ኒሂሎ አልተፈጠረም፡፡ አንዳንድ ሃሳባዊ ፈላስፎች (ለምሳሌ፡- ጆርጅ ባርክሌይ) ዓለም
በእግዚአብሔር አእምሮ ውስጥ ያለ ሃሳብ ነው ይላሉ፤የእግዚአብሔር ሃሰብ ስለሆነ ከእግዚአብሔር ሊለይ አይችልም፡፡
ፓንቲይዝም (pantheism)
ፓንቲይዝም ፓን እና ቲኦስ ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሁሉም አምላክ ነው፤ አምላክ ሁሉም
ነው የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ የፓንቲይዝም ስነ ኑባራዊ መሠረት ሁለት ሲሆኑ እነርሱም፡- የሁሉም እውነታ አንድነትና
የዚያ አንድነት መለኮታዊነትን ያረጋግጣል፡፡ በፓንቲይዝም አመለካከት ያለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ያ አንድ ነገር
እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉም ነው፤ ሁሉም እግዚአብሔር ነው፡፡ ፓንቲይዝም እውነታ አንድ ብቻ ነው
በሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ከተፈጥሮአዊነት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን በሁለተኛው ነጥብ ደግሞ ከቲኢዝም ጋር
ይመሳሰላሉ፡፡ ሁለቱም ይህ ዓለም በእግዚአብሔር ላይ እንደተደገፈ ይገነዘባሉ፡፡ ከቴኢዝም የሚለየው እንደ ቴኢዝም
የእግዚአብሔር ህልውና ከዚህ ዓለም ህልውና ይለያል የሚለውን ሃሳብ አይቀበልም፡፡

ተፈጥሮአዊነት (naturalism)
በተፈጥሮአዊያን አመለካከት እግዚአብሔር የሚባል ነገር ዬለም፡፡ ያለው ቁሳዊ ዓለም ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል
ተፈጥሮአዊነት በሌላ አባባል የአምላክ ክህደት (ኤትይዝም) ነው፡፡ ክህደት ደግሞ ወደ ባዶነት ያመራል፡፡ በሰው አእምሮ
ውስጥ የተተከው የአምላክ ህልውናን መካድ ለጥፋት ያጋልጣል፡፡

ዴይዝም ከአስራ ሰባተኛ መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለብዙ ጊዜ የዘለቀ ትውፊታዊ እምነትን በአምክንዮኣዊ ሐይማኖት
ለመቀየር የሚፈልግ ፕሮግራም ነው፡፡ አምላክ ሩቅና በዓለም ጣልቃ የማይገባ ሲሆን ፍጥረተ ዓለምን በማሽን መልክ
በራሱ ሥርዓትና ህግ እንዲመራ ፈጠረ፡፡ እርሱ ምጡቅ እንጂ ቅሩብ አይደለም፤ በዓለም ጣልቃ አይገባም ብሎ ያምናል፡፡
በዴይዝም አስተሳሰብ እግዚአብሔር ሠዓትን ከፈጠረ ሰው ጋር ይመሳሰላል፡፡ ሰዓትን የፈጠረው ሰው ሠዓት እንዲሰራ
ሥርዓትና ህግ ፈጥሮለት ሠዓትን ከፈጠረ በኋለ ሰዓቱ ዬት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡ ሠዓት በተስተካከለለት ህግና
ሥርዓት ይሠራል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ዓለም የፈጠረው ሲሆኑ ዓለሙ ግን በተሰራለት ህግ የሚሰራ እንጂ አምላክ
በዓለም ውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡ ዴይዝም መለኮታዊነት ሲቀነስ ቅሩብነት ልንለው እንችላለን፡፡

ቴኢዝም/መለኮታዊነት
በቴኢዝም አስተሳሰብ መለኮታዊ አምላክ ህግ/ሥርዓት ሳይሆን ሰብአዊ፣ ምጡቅ፣ ቅሩብና ከሁሉ በላይ ነው፡፡ ያለ ና
የሚኖር አምላክ ነው፡፡ ምንም እንኳን ምጡቅ ቢሆንና ባይደረስበትም ሰብአዊ አምላክ (personal God) ነው፡፡ በምጥቀቱ
ከጽንፈ አለም ይልቃል፤ በቅርቡነቱ ደግሞ በዓለም ውስጥ ይሳተፋል፡፡ እግዚአብሔር በታላቅነቱ መጀመሪያም
መጨረሻም ፣ አልፋም ኦሜጋ፤ ያለና የሚኖር ደግሞም የሚመጣ ነው (ራዕይ 1፡8)፡፡በዚህ አመለካከት ፈጣሪ አምላክ
በማንነቱ ከፍጡሩ ይለያል (God is ontologically different from the creation). ፈጣሪ ፍጡር አይደለም፤ ፍጡርም
ፈጣሪ አይደለም፡፡ ፈጣሪና ፍጡር ልዩነታቸው ማንነታቸው ነው፡፡ በሌላ አባል ፈጣሪነቱና ፍጥርነታቸው ነው፡፡

11. አስተምህሮ
11.1. ህላዌ እግዚአብሄር
በዚህ ስፍራ አምላክ ብለን ስንል የክርስቲያን አምላክ ማለታችን እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡ያም ሁሉን ቻይ፣ መልካም
አምላክ፣ዘለዓለማዊ ፈጣሪ እና ተቆጣጣሪ እንዲሁም የአጥናፈ ዓለሙ አምላክ አለ ማለታችን ነው፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ
የተያዘው አቋም አከራካሪ ነው፡-አንዳንዶች በእርግጠኝነት አለ ሲሉ፣ ጭራሽ የለም የሚል አቋም የያዙ አሉ፣መኖር
አለመኖሩን በጭራሽ አናውቅም የሚል አቋም አሉ፣ሌሎች ነገሮችን ዝም ብለው ሀሳብ መስጠት ወደዋል፣በመጨረሻም
አለ ግን በአመክንዮ ማስረዳት አይቻልም የሚሉ አሉ፡፡
11.1.1. በእርግጠኝነት አለ
በዚህ ላይ ሁለት ዓይነት አቋም ያላቸው አሉ፡፡አንዱ በመንስኤ እና ውጤት መኖሩን ማወቅ ይቻላል (posteriori) የሚሉ
እና ከእግዚአብሄር ሀሳብ አንጻር (priori)ለመከራከር ጥረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የመንስኤ እና ውጤት ሙግት፡-አንዱ
ከሀሳብ ተነስቶ የሚከራከር ሲሆን (ስለዚህ ለማይለወጡ እውነቶችን መሰረት የሆነ ወሰን የለሽ የማይለወጥ አህምሮ
(ያም እግዚአብሄር) ያስፈልጋል፡፡) ሌላው ደግሞ ለመኖር የመደገፍ ሙግት (contingent-የሚደግፍ አካል የሚደገፍ አካል
አይሆንም (contingent being is not contingent) ነገር ግን አስፈላጊ (የምንደገፍበት ወይም መንስኤ የሆነ) አለ፡፡
በማለት የእግዚአብሄርን መኖር በመንስኤ እና ውጤት ለማሳየት ሞክሯል፡፡) ነው፡፡
11.1.2. እግዚአብሄር የለም፡-
ከእኩይ አንጻር የቀረበ ትችት፡-ክፉ እስከ አሁን አለና ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት አምላክ የለም፡፡ለዚህ ምላሽ የሚሆነው
አንደኛ. ነጻ ፈቃድ በአለበት (ሳይጠፋ) ክፉን ነገር ማጥፋት አይቻለም (አውገስጢኖስ ትልቁ ችግር የሰው ነጻ ፈቃድ ነው
እንዳለው)፡፡እግዚአብሄር የለም ብለው የሚክዱ ሰዎች የክፉ መጥፋትን ጊዜ የወሰኑ ይመስላል፡፡እግዚአብሄር እስከ አሁን
ክፋትን ካላጠፋ ከዚህ በኃላ አያጠፋም የሚል አቋም ነው፡፡አማኞች ይህን ለማወቅ ሁሉን አዋቂ መሆን ይጠይቃል የሚል
ሙግት ያቀርባሉ፡፡
ራሱን አኗሪ ማንነት ሊኖር አይችልም፡-እግዚአብሄር ለመገኘቱ ምክንያት ከሌለ በራሱ የሚገኝ ማንም የለም የሚል
ሙግት ነው፡፡የተሰጠው ምላሽ እግዚአብሄር ራሱን ያስገኘ (self-caused Being) ሳይሆን ያለ ምንም የመገኛ ምንጭ
የተገኘ (uncaused Being)ነው የሚል ነው፡፡አማኞች ሁሉም ነገር ለመገኘታቸው ምክንያት አላቸው አይሉም ይልቅ
ለመኖር በሌላው ላይ የሚደገፉ ብቻ ምክንያት አላቸው (contingent things)፡፡አስፈላጊ ማንነት (Necessary Being)
ምክንያት አያስፈልገውም፡፡
እግዚብሄር የማይመስል ባህሪያት አሉት፡-እግዚአብሄር ሁሉን ይችላል ከአለን ራሱ የማያነሳውን ድንጋይ ሊፈጥር ይችላል
ብለው ይላሉ፡፡ስለዚህ ሁሉን ቻይ የሚባለው ባህሪ አይሄድም፡፡ለዚህ ምላሽ የሚሆነው እግዚአብሄር የማይችለውን
አይሰራም፡፡የማይቻል በእርሱ ዘንድ የለም፡፡

11.1.3. አራቱ ሙግት


የስነኑባሬሙግት
መሰረቱን የሚያደርገው ስለ እግዚአብሄር ከአለ ሀሳብ ተነስቶ ነው፡፡አንድ ሰው ከሚያስበው በላይ የአለ ማንነት አለ ብሎ
ነው፡፡ታዲያ ህልውና ከዚህ ኑባሬ ጋር የተያያዘ ነው፡፡2 ለመኖር አስፈላጊ ኑባሬም እንበለው ብቻ አለ ማለት ነው፡፡
የኮስሞሎጂ (የፍጥረት)ሙግት
በዘህ በሚታየው አጥናፈ ዓለም ውስጥ የአለ ማንኛውም ነገር ለመገኘቱ ምክንያት አለው፡፡ራሱ አጥናፈ ዓለሙም
ያስገኛው ምክንያት አለ ለዚህ ትልቅ ዓለም መገኘት ምክንያቱ ደግሞ አምላክ (እግዚአብሄር) ብቻ ነው፡፡3
ቴሌሎጂካል (የንድፍ ክርክር)
ትኩረት የሚያደርገው መጣጣም (harmony)፣ስርዓት (order) እና ንድፍ (design) ላይ ነው፡፡ዋናው መከራከሪያ ነጥብ
የዚህ ዓለም ንድፍ (design) ታላቅ ዓላማ ከጀርባው እንዳለው አመላካች ነው፡፡አጥናፈ ዓለም በሚገርም ንድፍ
ስለተፈጠረ በዓላማ ተፈጥሯል ይህም ትልቅ ዓላማ የአለው አዋቂ አምላክ አለ ብለን ማለት እንችላለን፡፡4
የሞራል ሙግት
ሰው ትክክል እና ስህተት ብሎ የህሊና ዳኝነት እንዲሰጥ የሚያደርገው ስሜት ነው፡፡ፍትህ እንዲበየን የመፈለግ ከፍተኛ
ፍላጎት፡፡ከዚህ ተነስቶ ትክክል እና ስህተት ብለን ብያኔ እንድንሰጥ የሚያደርግ የፍተህ ምንጭ መኖር አለበት ያም
እግዚአብሄር ነው፡፡5

11.1.4. ውስጣዊ መረዳት አምላክን ማወቂያ (inner sense)


አምላክ እንዳለ፣እነርሱም የእርሱ ፍጥረታት እንደሆኑ እና እርሱም ፈጣሪያቸው እንደሆነ ሰዎች ሁሉ መረዳት አላቸው፡፡
እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም እንጂ አህዛብ እንኳን ይህ ዓይነት መረዳት እንዳላቸው ጳውሎስ ተናግሯል (ሮሜ. 1፡21-
25)፡፡ይህ ማለት ሰው ፈቅዶ ገሸሽ ወይም ወዲያ እንደሚያደርገው ያሳያል፡፡ስለ እግዚአብሄር ያአለ እውቀት ግልፅ ነው፡፡
ይህን የእውነት እውቀት በኀጢያት በመጋረድ እና ሆን ብለው ክደውታል (ሮሜ. 1፡18)፡፡

2Grudem, Wayne A.: Systematic Theology : An Introduction to Biblical Doctrine. Leicester, England;
Grand Rapids, Mich. : Inter-Varsity Press; Zondervan Pub. House, 1994, S. 143
3Grudem, Wayne A.: Systematic Theology : An Introduction to Biblical Doctrine. Leicester, England;
Grand Rapids, Mich. : Inter-Varsity Press; Zondervan Pub. House, 1994, S. 143
4Grudem, Wayne A.: Systematic Theology : An Introduction to Biblical Doctrine. Leicester, England;
Grand Rapids, Mich. : Inter-Varsity Press; Zondervan Pub. House, 1994, S. 143
5Grudem, Wayne A.: Systematic Theology : An Introduction to Biblical Doctrine. Leicester, England;
Grand Rapids, Mich. : Inter-Varsity Press; Zondervan Pub. House, 1994, S. 143
6

11.1.5. እግዚአብሄርን ማወቅ ይቻላል


እግዚአብሔርን የማወቂያው መንገድ የዕብራዊያን አቀራረብና የግሪካዊያን አቀራረብ በሚል ለሁለት ይከፈላል፡፡
በእብራዊያን አቀራረብ እግዚአብሔርን የማወቂያው ብቸኛ መንገድ መገለጥ ሲሆን በግሪካዊያን አቀራረብ ደግሞ
አመክንዮአዊ ፍለጋ ነው፡፡ በመጀመሪያው አቀራረብ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሲገለጥ ይታወቃል የሚል ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ ሰው በራሱ አመክንዮአዊ ችሎታ እግዚአብሔርን ፈልጎ ያገኘዋል የሚል ነው፡፡

እግዚአብሔርን የምናውቀው በቃሉና በተግባሩ ነው፡፡


በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር እራሱን በቃሉና በተግባሩ ገልጧል፡፡ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ልናውቀው አንችልም፤
አናውቀውምም፡፡ መጽህፍ እንደ ሚል እግዝአብሔርን ማንም አላየውም፤ እርሱ ብቻ የማይሞትነው፤ ማንም
ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል(1 ጢሞቲዮስ 6፡16)፡፡ ነገር ግን ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል
ፊቴን ማየት አይችልም (ዘጸአት 33፡20)፡፡

ምንም እንኳን እግዚአብሔር በቀጥታ ባይታወቅም በተዘዋዋሪ መልኩ በስራውና በቃሉ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ዕውቀት
ስለ ነፋስ ካለን ዕውቀት ጋር ልናመሳስለው እንችላለን፡፡ ነፋስ መኖሩ የሚታወቀው በውጤቱ እንጂ በራሱ አይታይም፡፡
አቅጣጫውን፣ ጥንካሬውንና ቅለቱን በነገሮች ላይ ባለው የግፊት መጠንና አቅጣጫ ነው የምናውቅ፡፡እንዲሁም
የእግዚአብሔርን መኖር የምናውቀው ከነገሮች በስተጀርባ ባለው ምኩናዊነትና በቃሉ በተጻፈው ተግባር ነው፡፡
ለምሳሌጆን ካልቪን እግዚአብሄርን የምናውቀው በስነኑባሪያዊ ምርምር (metaphysical investigation) ሳይሆን
በሰራው ብቻ ነው›› ይላል፡፡

ዕውቀት ባለቤታዊ እውቀት (ሰብጄክቲቭ ኖሌጅ)ና የነገራዊ ዕውቀት (ኦብጄክቲቭ ኖሌጅ) በመባል ለሁለት ይከፈላል፡፡
ባለቤታዊ ዕውቀት አንዳንድ ጊዜ ህሊናዊ ዕውቀት ይባላል፡፡ ይህንን ትምህርት ለማብራራት ሲባል ግን ባለቤታዊ ዕውቀት
በሚል ስያሜ እንጠቀማለን፡፡ ባለቤታዊ እውቀት የሚባለው አዋቂው ብቻ ሳይሆን ታዋቂውም ባለቤት በሚሆንበት ጊዜ
ስለ ሁለተኛው ባለቤት የምታወቅ ዕውቀት ነው፡፡ ነገራዊ ዕውቀት የምንለው ግን አዋቂው ባለቤት ሆኖ ታዋቂው ግን ነገር
በሚሆንበት ጊዜ አዋቂ ባለቤት ታዋቂውን ነገር የሚያውቅበት የዕውቀት ዓይነት ነው፡፡ ነገራዊ እውቀት በሳይንሳዊ
መንገድ ተመዝኖ፣ ተለክቶ፣ ተፍታቶና ተተንትኖ ሙሉ ለሙሉ ሊታወቅ የሚችል የነገር ዕውቀት ነው፡፡ባለቤታዊ ዕውቀት
ግንከነገራዊ እውቀት በተለየ መልኩ ታዋቂው ባለቤት እራሱን በገለጠለት ልክ ብቻ የሚታወቅ ነው፡፡

አንድን ሰው የማውቅበትና አንድን ወንበር የማውቅበት ዕውቀት ይለያያል፡፡ ሰውን የምናውቅበት ዕውቀት ባለቤታዊ
ዕውቀት ሲሆን ወንበርን የምናውቅበት ዕውቀት ነገራዊ ዕውቀት ነው፡፡ ስለ ወንበር ቁመት፣ ክብደት፣ ቴክስቸር ለማወቅ
ወንበሩ እራሱን ሊገልጽልኝ አያስፈልገውም፡፡ ስለ ሌላው ሰው ለማወቅ ግን የሚቻለው ሰውዬው እራሱን ሊገልጥልኝ
በፈቀደና በቻለ ልክ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔርም ዕውቀት እንደዚሁ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልናውቅ የምንችለው
እግዚአብሔር እራሱን በገለጸልን ልክ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት ዘፍ 12፡1-3፣ 15፣ 17፣ 22 እግዚአብሔር ለያዕቆብ ተገለጠለት ዘፍ 28
እግዚአብሔር ለነቢያት ተገለጠላቸው ኤርሚ. 1. ኢሳ. 6 ኢየሱስ ለሐዋሪያቶቹ ተገለጠ፣ በመጨረሻም ለጳውሎስ
ተገለጠ ሐዋ. 9፣ 22፣ 26 በእብራዊያን አስተሳሰብ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በመገለጥ አማካይነት ነው፡፡
እግዚአብሔር እራሱን ሲገልጽልን ብቻ በዚያ ልክ እናውቀዋለን፡፡ እኛ ፈልገን የምናገኘው ሳይሆን እርሱ ሲገለጥልን
በእምነት የምንመልሰው ነው፡፡በዕብራዊያን ምልከታ መሠረት አምላክ/እግዚአብሔር የሚታወቀው በመገለጥ ብቻ ነው፡፡

6Grudem, Wayne A.: Systematic Theology : An Introduction to Biblical Doctrine. Leicester, England;
Grand Rapids, Mich. : Inter-Varsity Press; Zondervan Pub. House, 1994, S. 141
11.2. ትንሳኤ
መንደርደሪያ 1 የክርስቶስን ሞት እና ትንሳኤ በተመለከት ሊነሳ የሚችለው ነገር ምንድነው ብለን ብንጠይቅ
እንደሚከተለው ማቅረብ ይቻላል፡፡በዮሴፍ አርማቲያስ ቀብሩ መከናወኑ፣ባዶ መቃብር፣ከሞቱ በኃላ በትነሳኤ
መታየቱ፣ደቀ-መዛሙርት በትንሳኤ ማመናቸው፡፡

መንደርደሪያ 2 ይህ ከላይ የተጠቀሰውን ጉዳይ ለመተንተን እግዚአብሄር የናዝሬቱ ኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል የሚለው
እሳቤ መልካም የሆነ እና ሊታመን የሚችል መሆኑን ልባ ማለት ይቻላል፡፡

መንደርደሪያ 3 እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል ማለት እግዚአብሄር አለ ማለት ነው፡፡ማጠቃለያ 4 ስለዚህ
እግዚአብሄር አለ

11.2.1. እውነታ
እውነታ 1 ከስቅለቱ በኃላ የአርማቲያው ዮሴፍ ኢየሱስን ቀብሮታል፡፡ይህ ደግሞ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ምክንያቱም
አይሁድም ሆነ ደቀ-መዛሙርት የቀብሩ ቦታ የት እንደሆነ አውቀውታል፡፡በሌላ አባባል ቀብሩ የት እንደነበር ማወቅ
ተችሏል ማለት ነው፡፡

የኢየሱስ መቀበር ዘግየት ብለው ከተጠቀሱት እንደ ጳውሎስ ከአሉ ምንባባት (ለምሳሌ የቆሮንቶስ መጸሐፍ) እስከ
መጀመሪያ ዶክምነት እስከሆነው የማርቆስ መጸሐፍ ዘግበውታል፡፡የአርማቲያው ዮሴፍ ኢየሱስ ላይ የፈረደበት የአይሁድ
ሸንጎ አባል ስለነበር ዮሴፍ አርማቲያው ቀብሮታል እና መቃብሩን ያውቀዋል የሚለው ሀሳብ በምንም አይነት የክርስቲያን
ፈጠራ ሊሆን አይችልም (እኛ አይተነዋል አላሉም)፡፡ስለዚህ መቀበሩ በምንም አይነት አፈ ታሪክ ሊሆን አይችልም፡፡
ሌላው ደግሞ በጥንት ጊዜ እንዲህ ዓይነት ተነጻጻሪ ታሪክ የለም፡፡

እውነታ 2 ከስቅለቱ እና ከቀብሩ በኃላ እሁድ መቃብሩ ባዶ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ይህም ጳውሎስ ተቀበረ እና ተነሳ ብሎ
ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡በማርቆስ ቆየት በአለው ሰንዱም ይህን የባዶ መቃብር ዜና ተናግሯል፡፡ታሪኩ አፈ-ታሪክ
የማይመስል እና አሳማኝ ነው፡፡በሴቶች መገኘቱ ምናልባት የሴት ምስክር በአይሁድ ማህበረሰብ አናሳ ቢሆንም ሃዋርያት
የሰጡት የትንሳኤ ምስከርነት ስለ ባዶ መቃብሩ ጥሩ ትንተና ሊሆን ይችላል፡፡

እውነት 3 በተለያየ ጊዜ እና ቦታ የተለያዩ ሰዎች የኢሱስን ትንሳኤ ተመልክተዋል፡፡ከነዚህም መካክል ኬፋ፣አስራ ሁለቱ፣
ከ 500 የሚበዙት ያዕቆብ እና ጳውሎስ ራሱ፡፡

እውነታ 4 ደቀ-መዛሙርቱ በድንገት እና በየወሃነት የኢሱስን ትንሳኤ አመኑ፡፡እና ለዚህም እውነት ለመሞት ቆረጡ
አብዛኞቹም ይህንኑ ሲሰብኩ ሞተዋል፡፡እንዴት ለውሸት በዚህ ደረጃ ልትሞት ትችላለህ፡፡

መደምደሚያ አልሞተም ወይም ደቀመዛሙርቱ ሰርቀውታል ቢባል ለታሪኩ ተፈጥሯዊ ማብራሪያ አይደለም፡፡

11.3. የመከራ ምንጭ ማነው?


አንድም ጥያቄ የሚጭረው መከራ በምድር ላይ ለምን ይከሰታል የሚል ጥያቄ ነው፡፡ለዚህ የሚሰጠው የተለያየ ምክንያት
ቢሆን ዋናው ነገር ግን የዋህ ለምን ስቃያል የሚለው አብይ ጥያቄ ነው፡፡

11.3.1. የማያምኑመከራከሪያቸው
የወጥነት ጥያቄ (Logically Impossible) ሁሉን የሚችል አምላክ አለ እና መንደርደሪያ 2 ደግሞ መከራ አለ የሚለው
መከራከሪያ የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ሁሉን ቻይ አምላክ ከአለ የፈለገውን አለም መፍጠር ይችል ነበር፡፡አፍቃሪ ከሆነ
መከራን ያጠፋ ነበር የሚል ነው፡፡

ነገር ግን ነጻ ፈቃድ አለ የሚል መከራከሪያ ብናነሳ፡፡በሌላ አባባል እግዚአብሄር የሚፈልገውን ዓለም ያልፈጠረው ለሰው ነጻ
ፈቃድ ስለሰጠው ነው የሚል ነው፡፡ሌላው ደግሞ ብትመለከቱት ለበለጠው መልካም ሲባል መከራን እንፈቅዳለን ለምሳሌ
ልጃችንን ወደ ህክምና ልንወስደው እንችላለን፡፡

ማስረጃ አልባነት (Evidential Version) እግዚአብሄር መከራን የሚፈቅድበት ምንም አይነት ምክንያት የለውም ወይም
ማስረጃ ሊኖረው የሚችል አይመስለም የሚል ምልከታ ነው፡፡
ሰው ግን ውስን ነው፡፡እግዚአብሄር የዓለምን ክስተት የሚረዳ አምላክ ነው፡በጊዜ በቦታ የተለየ አምላክ ነው፡፡እግዚአብሄር
የለም የሚለው መከራከሪያ ነጥብ መከራን የምንጠቅስ ከሆነ ክፉን እና ደግን እንድትለይ ባደረገህ የሞራል ባለበት ሆነሀል
እና እግዚአብሄር አለ፡፡
የእግዚአብሄር ዋናው ሀሳብ እርሱን እንድናውቅ እንጂ በዚህ ምድር ደስታ እንድንሸምት ብቻ አይደለም፡፡የሰው ልጅ
በማያቋርጥ አመፅ ውስጥ አለ፡፡የሰው ልጅ በዚህ ምድር ጉዳዩ የሚያበቃ አይደለም ይልቅ ዘለአለም የሚባል አለም አለ፡፡
መከራው ከመከራው አይመጣጠንም ያንንም እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡

11.4. መጸሐፍ ቅዱስ

ሰዎች ጥያቄ የሚያነሱት መጸሐፍ ቅዱስ በስሀተት እና በተቃርኖ የተሞላ ነው፡፡የእግዚአብሄር ቃል አይደለም ይልቅ በሆኑ
ሰዎች የተጻፈ ነው፡፡በታሪክ የተሞላ ነው፡፡የመጀመሪያዎቹ የዘፍጥረት 11 ምዕራፍ አፈታሪክ ነው፡፡መጸሐፍ ቅዱስ
የመጀመሪያ ቅጂዎች የሉንም ስለዚህ ሊታመኑ አይችሉም፡፡ለመሆኑ ለምን 66 መጸሐፍ ብቻ፡፡

11.4.1. ተአማኒነት
ወደ 5586 የግሪክ ቅጂዎች በእጃችን ላይ ይገኛሉ፡፡ወደ 20 ሺህ ቀደምት ትርጉሞችን ጨምሮ፡፡ በእጃችን የአለው ፅሁፍ
የመጀመሪያው ከተጻፈ ከ 100 ዓመታት በኃላ የተጻፈ ነው፡፡የፅሁፍ ጊዜን የሚወስኑ የፅሁፉን ማቴሪያል፣የደብዳቤ
ቅርፅ፣የቀለም ዓይነት ሁሉ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡

የቁጥር ግጭት የሚመስሉ ሀሳቦች ይታያሉ፡፡ለምሳሌ በጌርጌሲኖን ማቴዎስ 8፡28-34 ሁለት አጋንንት ያደሩባቸው ነበሩ
ሲል ሉቃስ 8፡26-39 አንድ ብሎ ይናገራል፡፡ሉቃስ አንድ ብቻ ነው አላለም (ብቻ ቢል ግጭት ይፈጥራል)፡፡ይህ ዓይነት
አገላለፅ በተለምዶ የምንናገረው ነው (ሰው አብሮኝ አለ ስትመጣ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡ምናልባት አንዱ አጋንንት
ያደሩበት የተገለጠ ሊሆን ይችላል፡፡

11.4.2. ባለስልጣን
መጸሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጸሐፍ የሚለየው ምንድነው?ወጥነቱ ለየት ያደርገዋል፡፡1500 ዓመታት ውስጥ 40
በሚያክሉ የተለያዩ ሰዎች (እረኛ፣ንጉስ፣ካህን፣ቀረጥ ሰብሳቢ፣የቀን ሰራተኛ) በተለያየ ሁኔታ ውስጥ (ጦርነት፣ሰላም እና
ስደት) መጸፉ፡፡በተለያየ ቋንቋዎች ተፅፎ አንድ ጭብጥ፡፡ በትምህርቱም ለየት ይላል፡፡ትንቢት፡-የኢየሱስ መወለደ
(ጊዜውን በተመለከተ ዳን.9 ከተማ ሚኪ 5፡2 ሁኔታ ኢሳ. 7፡14)፡፡

11.4.3. ጠባብ ቀኖና


ለምንድነው ጠባብ ቀኖና ወንጌላውያን አማኞች የተቀበሉት? ዋናው ነገር ቤተ ክርስቲያን እነዚህን መጸሐፍት
ስለማካተት ብይን አልሰጠችም ይልቅ እውቅና ሰጥታለች፡፡በሐዋርያት ወይም ከሐዋርያት በቅርብ ሰው ተፅፏል ወይ?
(ምስክርነት ለመስጠት ይችላል ወይ ለምሳሌ ከትንሳኤው አንጻር)፣ ያንጻል ወይ (ሕይወትን የመለወጥ ሀይል አላቸው
ወይ ለምሳሌ ቅዱስ አውገስጢኖስ ወይም ሉተር ሮሜን ሲያነብ እንደተለወጡ ዓይነት) እና የመሳሰሉትን በማዘጋጀት
እውቅና ቸራቸዋለች፡፡መጀመሪያ ለ 66 መጸሐፍት እውቅና የሰጠው ቅዱስ አውገስጢኖስ ሲሆን ከዚያ በካርቴጅ በ 367
ዓ.ም አዲስ ኪዳን እንዲሁም በ 150 ዓ.ዓ አካባቢ ለብሉይ ኪዳን መጸሐፍት እውቅና ተሰጥቷል (ኢየሱስ ከሀግ፣ከነቢያት
እና ከታሪክ እየጠቀሰ ያስተምር ነበር-ሉቃ.24፡44 11፡51)፡፡
11.5. ኢየሱስ ላይ

ኢየሱስ ላይ ከሚነሱ ትችቶች መካከል ኢየሱስ ነቢይ፣መምህር እና መልካም ስነ-ምግባር የነበረው ጥሩ ሰው ነበር እንጂ
ራሱን አምላክ ብሎ አልጠራም፡፡የኢየሱስ ማንነት የክርስትና ቁልፍ ሀሳብ ነው፡፡ይህን ቁልፍ እውነት አለመገንዘብ
ከድነታችን ጋር ቀጥታ ተያያዥነት አለው፡፡

ድነታችን ሙሉ ለሙሉ ከዚህ እውነታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ኢየሱስ ስለኀጢያታችን እንደሞተ እንደተነሳ ማመን
ለመዳናችን ዋስትና የሚሰጠን ያ ብቻ ነው፡፡ለምን እግዚአብሄር ይህን ከባድ መንገድ መረጠ? ፍትህን እና ፍቅርን ለመበየን
ነው (ሮሜ 3፡23፣ 6፡23)፡፡

ኢየሱስ በታሪክ የነበረ ሰው ነበር? መጸሐፍ ቅዱስ የውልደቱን ጊዜ (ሉቃ. 2፡1-7) አስተምህሮውን እንዲሁም ለአገልግሎ
ሲለይ የ 30 ዓመት ሰው እንደነበር (ሉቃ. 3፡23)፣ የነበረበት ጊዜ የመቅደሱ ስራ ወደ 46 ዓመታት ጊዜ ፈጅቷል (26
ዓ.ም)፡፡

ለመኖሩ ታሪክ ዘጋቢዎች (Secular historians) የዘገቡተን ብናይ የምስራቁን ሜዴትራኒያንን ከትሮጃን ጦርነት እስከ
52 ዓ.ም የዘገበው ታሉስ በአንድ ከሰዓት ታላቅ ጨለማ ወድቆ ነበር ያ ወቅት መሉ ጨረቃ የነበረችበት ወቅት ስለነበር
የፀሐይ ግርዶሽ አይታሰብም ነበር፡፡የሮም ታሪክ ዘጋቢ ኮርነሌስ ታክትየስ (55-120 ዓ.ም) ክርስትና በሮም እንደነበረ ይህን
ከክርስቶስ ሞት ጋር ይያያዝ እንደነበር ዘግቧል፡፡የአይሁድ ታሪክ ዘጋቢ ጆሴፈስም (37-100 ዓ.ም) ቤተሰቡን፣ትምህርቱን
መሰቀሉን ዘግቧል፡፡

ኢየሱስ አምላክ ነውን ወይስ አምላክ ነኝ ብሏልን? ወንጌላት ያን ዘግበውታል ማርቆስ 14፡61-64፣ዮሐ 8፡24 ፣58፣ 10፡30
አይሁድ ያንን ተገንዝበው ሊገድሉት ነበር፡፡ ለምሳሌ ዮሐ 10፡33 ከዮሐ 8፡24 58 ከዘፀአት 3፡14 ጋር አያይዘን እንየው፡፡
ሌላው ኀጢያትን አስተሰርዟል (ማር. 2፡5-7)፣ ሕይወት እንደሆነ ቆጥሯል (ዮሐ. 14፡6) በዓለሙ እንደሚፈርድ (ዮሐ. 5፡
26-27) እንዲመለክ ፈቅዷል (ማቴ. 14፡33 ከሐዋ. 10፡25-26 እንዲሁም ራዕይ. 19፡10 ጋር አወዳድር)፡፡

የአዲስ ኪዳን ፀሐፍት አምላክነቱን ዘግበዋል እግዚአብሄር (ሉቃ. 3፡22) ጴጥሮስ (ማቴ. 16፡15-18፣የሐዋ. 2፡36 2 ጴጥ.
1፡1 ጳውሎስ. ሮሜ. 9፡5 ፊሊ. 2፡6) ቶማስ (ዮሐ. 20፡28) ማር 1፡1

You might also like