Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 53

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ቤተክርስቲያን የደብረ ገሊላ አማኑኤል


ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት
ትምህርት ቤት ተከታታይ ትምህርት
ጥናቱ የሚገባው፡ የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል

ሰኔ 2016

አዲስ አበባ ኢትዮጰያ

የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት


ተ.ቁ ስም ፉርማ

1. ኢዮብ ደንድር
2. አብዩ ሰለሞን

አዘጋጅች
3. ቅድስት ታደስ
4. ኢዩኤል ታሪኩ
5. ደርባቸው ታፈሰ
6. ሰላም ሲሳይ
7. ደግፌ አመርጋ
8. ስንታየሁ ክፍሌ
አማካሪ 1. መ/ር ሀብታሙ ይርጋ

የጥናትና ምርምሩ ርእስ የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተጽዕኖ

በቤተ ክርስቲያን ከየት ወደ የት


የጥናትና ምርምር ጊዜ ከመጋቢት - ሰኔ 2016 ዓ.ም
እንደ ደበረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እና አካባቢው
የጥናቱ ቦታ

የጥናትና ምርምሩ ጠቅላላ ወጭ 3500 ብር

ሰንጠርዥ ፩.፩ የአዘጋጆች እና ጠቅላላ መረጃ የያዘ


ምስጋና

በመጀመሪያ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደመኖር ያመጣና የሰው ልጆችን ደግሞ በምድር ከሚኖሩ ሁሉ አብልጦ
መንግሰቱን እንወርስ ዘንድ በክብር ለፈጠረን የመንፈስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ ለዘላለም ሕይወት ያበቃን የዘላለም ሞተን በልጁ
ቤዛነት ያዳነን አምላክ ፍፁም ምስጋና ይግባው፡፡ አትለይምና ጥበቡ የረቀቀብባት እመ ብዘኀን የመዳናችን ምክንያት የሆነችው
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ይግባት። መላዕክት ሰማዕታት ቅዱሳን እንደ ክብራቸው መጠን ክብርና
ምስጋና ይድረሳቸው::

በሁለተኝነት በፀጋ በረድኤት ጠብቃ የዘላለም ሽልማት ለሰጠችን ለኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና
ሶስት አመት ሙሉ የእግዚያብሄርን ማዕድ ዘርግታ ለመገበችን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት እዲሁም ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ላበረከቱልን
ለመምህራኖቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

በሶስተኝነት ይህን ጥናትና ፅሁፍ ስናዘጋጅ በማመከር የጥናትና ምርምሩ ፅሁፍ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ላገዘን ለመምህር
ሃብታሙ ይርጋ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በሰተመጨረሻ ልዩ ምስጋና የሚገባው ለመምህር አንተነ አወቀ የጥናትና
ምረምሩ ፀሁፍ ከመዘጋጀታችን በፊት ቀድመ ቃለመጠይቅ በመሰጠት በጥናትና ምርምሩ ጊዜ ለማኅበራት የሚበተነውን
የፅሁፍ መጠይቅ በመበተን ላይ በማገዝ መረጃ በመሰጠት በሎም እንደ ማኀበራት አንድነት ሃላፊነታቸው እና እንደ ሰንበት
ትምህርት ቤቱ ምክትል ሰብሳቢነት የቃለ መጠይቅ እንደናደርግላቸው የተባበሩን በመሆኑ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ............................................................................................................................................................................... 6
፩. መግቢያ (Introduction)...........................................................................................................................................................6
፩.፩ የጥናትና ምርምሩ ዳራ (Background of the Study)....................................................................................................................6
፩.፪ የችግሩ ምንነት (Statement of the problem)............................................................................................................................8
፩.፫ የጥናትና ምርምሩ ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic research question).......................................................................................................8
፩.፬.፩ ዓብይ ዓላማ (General Objective)........................................................................................................................................8
፩.፬.፪ ንዑስ ዓላማ (Specific Objective)........................................................................................................................................9
፩.፭ የጥናትና ምርምሩ ጠቀሜታ (Significance of the study).............................................................................................................9
፩.፮ ጥናትና ምርምሩ ውስን ያልሆነበት (Delimitation of the study).....................................................................................................9
፩.፯ የጥናትና ምርምሩ ውስንነት (Limitation of the study).................................................................................................................9
፩.፰ የቃላት ትርጉም (Definition of term).....................................................................................................................................10
ምዕራፍ ሁለት............................................................................................................................................................................ 11
የተዛምዶ ጹሑፍ ዳሰሳ (Literature Review)..................................................................................................................................11
ምዕራፍ ሶስት............................................................................................................................................................................. 25
የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴ (Research Design and Methodology)................................................................................................25
፫.፩ የጥናትና ምርምሩ ንድፈ ሃሳብ (Research Design)....................................................................................................................25
፫.፪ በጥናትና ምርምሩ ሽፋን ያገኘው ቦታ (Specific area of the study)................................................................................................25
፫.፫ የጥናቱ የናሙና መጠን (Sample size)......................................................................................................................................25
፫.፬ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ (Sampling Techniques).......................................................................................................................25
፫.፭ ጥናቱ የተጠቀመባቸው የመረጃ አይነቶች (Types of data...............................................................................................................26
፫. ፮ ጥናቱ የሚጠቀመው የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ (Data Collection Method)..........................................................................................26
፫.፲የጥናቱ የመረጃ አተናተን ዘዴ (Data Analysis Method)...............................................................................................................26
፫. የጥናቱ የወረቀት መዋቅር (Organization of the study)................................................................................................................26
ምዕራፍ አራት............................................................................................................................................................................ 27
የመረጃ ትንተና፣ትርጉምና አቀራረብ /Analysis, Interpretation and Presentation of Data/.........................................................................27
ድርሞ/ማጠቃለያ /Summary/.....................................................................................................................................................41
መደምደሚያ /Conclusion/...........................................................................................................................................................43
የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation.............................................................................................................................................44
ማጣቀሻ /Reference...................................................................................................................................................................46
ተቀጽላዎች/አባሪዎች/Appendices/..............................................................................................................................................46

ሰንጠርዥ ማውጫ

፩. ሰንጠርዥ ፩.፩፡ የአዘጋጆች አድራሻ እና ጠቅላላ መረጃ የያዘ....................................................................................2

፪. ሰንጠርዥ ፩.፪፡ ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ..................................................................................28

፫ . ሰንጠርዥ ፩.፫፡ .የባለድረሻ አካላት የሚገኛቸውን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ከሚደረገው ድጋፍ ማሳያ…………………………….………..33
ምዕራፍ አንድ

፩. መግቢያ (Introduction)

፩.፩ የጥናትና ምርምሩ ዳራ (Background of the Study)


ከህገ ኦሪት(ብሉይ ኪዳን) በፊት ማኅበር (ነገድ) የነበረ ሲሆን ሦሰቱ የመላእክት ከተሞች/አኀጉረ መላእክት/ (ሰማየ ኢዮር፣ ሰማየ ራማ
እና ሰማየ ኤረር) ፣ መቶ ነገደ መላእክት ያለቸው እና አስር አለቆች ያለቸው የነበረ ሲሆን አስሩ ነገድ የአጋዕዝት አለቃቸው ሳጥናኤል
ነበረ ፡ (ሳጥናኤል ማለትም ቅሩበ እግዚአብሔር አኃዜ መንጦላዕት ፣አቅራቢ ስብሐት ማለት ነው) በወደቀ ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል
ተደርባል ይህም በመላክትም ማኅበር የነበረ እና ያለ መሆኑን ነው።

በብሉይ ኪዳን በጣም ተደጋጋሚ ጊዜ ሰለ ማኅበረ የተገለፀ ሲሆን በዘፍጥረት 35፥9-11 እግዚአብሔር የአብራሃም የልጅ ልጅ ያእቆብን
ሰሙን እስራኤል ብሎ እደሚጠራው ከነገው በሃላ ‘’ኹሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኀበር በአንተ
ይሆናል ነገስታትም ከጉልበትኽ ይወጣሉ’’ ብሎት የያእቆብ /እስራኤል ልጆች በጠቅላላ “እስራኤል ልጆች ማኅበር” በሚል
በተደጋጋሚ የተገለፀ ሲሆን ከዛ ውጪ የፃድቃን ማኅበር፣ የክፉዎች ማኅበር፣ የቅዱሳን ማኅበር ፣ አማልክት ማኅበር የነበሩና
በመዝሙረ ዳዊት 25-12 “እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና አቤቱ በማኅበር አመሰግናለው” ብሎ የማኀበር ተግባራት በብሉይ እንደነበር
ማየት ይቻላል፡፡

በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሰፊ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ የክርስቲያኖች የመንፈሳዊ ኅብረት ኑሮ የተጀመረውና ጎልቶ የተንጸባረቀው
በአባቶቻችን ሐዋርያት ዘመን ነው። “ በዚህም ወራት ጴጥሮስ መጦ ሃያ በሚያክል በሰዎች መኀበር አብረ በነበሩ በንድሞቹ መካከል
ተነስቶ..” በሚል የማሀበር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠሉን ማየት እንችላል፡፡ ይህ ዘመን ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ፴፮ቱ ቅዱሳት
አንስት፣ ፸፪ቱ ቅዱሳን አርድእት፣ እንዲሁም በእነርሱ ትምህርት ተስበው በክርስቶስ ያመኑ ምእመናን ሁሉ በአንድነት ይኖሩበት የነበረ
ዘመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሁኔታ ሲገልጽ “ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ፣ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው” እንዲል፡፡ (ሐዋ.
፬፥፴፪)

በዚያ ዘመን የነበረው ኅብረት በነፍስም በሥጋም አንድ እስከ መሆን የደረሰና ሁሉም ያለውን ሀብት አንድ ላይ ከማድረጉ የተነሣ
ችግራቸውን በጋራ ይወጡ የነበረበት ዘመን ነው፡፡ የመንፈሳዊ ኅብረት ኑሮ ዋና ጥቅሙም ይህ ነው፤ በሥጋም በነፍስም መረዳዳት
ስለሚንጸባረቅበት።

ከዘመነ ሐዋርያት በኋላ የነበረው ኅብረት (ክርስትና) እየተስፋፋ በመምጣቱ በክርስቲያኖች ላይ የተለያዩ ፈተናዎች ይደርሱባቸው
ነበር፡፡ እንደ ዘመነ ሐዋርያት ባይሆንም በመከራ ውስጥ ሆነውም መንፈሳዊ የአብሮነት ሕይወቱን አስቀጥለዋል፡፡ ይህም በየሀገራቱ
አንድ ዓይነት መልክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ገጽታዎች የሚከናወን ሲሆን በሀገራችንም በተለያዩ መንገዶች ሲሠራበት ቆይቷል።

በሁለተኛው እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተክርስቲያን ዘግናኝና አሰቃቂ የሆነ ስደት ከሮማውያን ነገሥታት ታወጀባት፤፤ በዚህ
ወቅት በእምነት ጽኑዓን የሆነ ምዕመናን በግቡበት ምድር ውስጥ ይማሩ፣ ይጸልዩ፣ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ይፈጽሙ፣ እንደነበረ
የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል፤፤ ለክርስትና እምነት እስከ ዘመናችን ድረስ መዝለቅ የነዚህ የዘመነ ሰማዕታት ማኅበራት አስተዋጽኦ
እጅግ ታላቅ ድርሻ አለው፡፡ ከዚህም በኋላ በየዘመኑና በየሀገሪቱ ብዙ ማኀበራት እንደተነሱ ቢታወቅም ቀደምት አባቶቻችን ያንን
ኅብረት በሰንበቴና በጽዋ ማኅበራት ለማስቀጠል ችለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ፥ መልካም ነው፥
እነሆም፥ ያማረ ነው።” (መዝ. ፩፻፴፫፥፩) በማለት እንደገለጸው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ እነዚህ እየተረሱና እየተተዉ
በመምጣታቸው በኅብረት ከመሆን ይልቅ በተለያዩ ምክንያቶች የተወሰኑ ሰዎች ፍላጎትና ጥቅም ላይ ና ግላዊ አስተሳሰብ ላይ ትኩረት
ማድረግ እየተለመደ መጥቷል።

ጠቅለል ባለ መንገድ ማኅበር አንድነትና ህብረትን የሚያመላክት ነገር ነው፡፡ ቤተክርስትያናችንም ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ፤
አዛውንቶች ደግሞ በሰንበቴ ማኅበራት በመታቀፍ አንድነታቸውን የሚፈጽሙበት ሁኔታ አመቻታላችዋለች ፡፡በዚህም ለብዙ ዓመት
በላይ ስትሰራበት ቆይታለች ነገር ግን ከ 1980 ወዲህ ቤተክርስትያኗ አስቀድማ ካስቀመጠችው አወቃቀር የተለየ በተለየ በ 1990 ዎቹ
መጨረሻ የማበራት ቁጥር እጅግ እየበዛ መጣ በአሁኑ ሰዓት በሺህ የሚቆጠሩ ማኀበራት ይገኛሉ ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በቤተክርስትያን
መዋቅር ውስጥና ህገ ቤተክርስትያንን ዶግማ ቀኖና ትውፊት ጠብቀው የሚሰሩ ማኅበራት እንዳሉ ሁሉ የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው
ግለሰቦች የመሰረቷቸው ማኅበራት ብሎም የንግድና የኑፋቄ ስራን ለመስራት የተቋቋሙ ማኅበራትም መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ለቁጥጥር በማያመች መልኩ በየቦታው በጥቂት ሰዎች ፍቃደኝነት ላይ የሚመሰረቱ ማኅበራ ከጥቅማቸው ይልቅ
ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል ፡፡ ማኀበራት በአግባቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚያደራጃቸው እና መንገዳቸውን የሚከታተል አካል ከሌለ
ከቤተክርስትያኗ በተጨማሪ የሀገርና የህዝብን ሰላም ሊያናጉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን ፤ እንደ ማኀበረ ማርያም የተሀድሶያውያን
ማኅበር በጥቂት ሰዎች መዘውር ውስጥ የገባ ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ላይ የፈጠሩትን ችግር እንደ ማሳያ መውሰድ ይቻላል ፤ እነዚህ
ማኅበራት ጉዳታቸው መናፍቃንን እና ከቤተክርስትያን የታገዱ ሰዎችን በማካተት በማር የተለወሰ ውስጡ መርዝ የሆነ ስብከት
ለምዕመኑ ይዘው መቅረባቸው ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት በነዚህ ማኅበራት አማካኝነት አጥንታቸው በወንጌል ያልጠነከሩ ወገኖቻችንን
በየአዳራሹ እየሰበሰቡ ከመናፍቃን ዘንድ እንዲቀላቀሉ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ፡፡
በመላ ሀገሪቱ ይህን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ማኅበራት ያሉ ሲሆን ለመቆጣጠርና ለመምራት ማጠፊያው እንዳያጥረን ብዙ ጥናቶች
ማድረግ አሰፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በዚህ ጥናት የመንፈሳዊ ማኅበራትን በጥልቀት በማጥናት ለቤተክርስትያን ሚጠቅምና ማኅበራት
ላይ ሚታየውን ችግር መቅረፍ የሚስችል ጥናት በመስራት ብሎም የመፍትሄ ሃሳቦችን መሰጠት ና አቅጣጫዎችን ማመላከት የዚህ
ጥናት ዋንኛ አለማችን ነው፡፡
፩.፪ የችግሩ ምንነት (Statement of the problem)
ማኅበራት ለቤተክርስቲያንና ለሕዝብ፣ የቆሙና ትልቅ ሚና ለዚህች እውነተኛይቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን
ትውፊቷን የሚጠብቁና ለሚመጣው ትውልድ ጭምር የሚሠሩ ብዛት ያላቸው ማኀበራት አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን
የማኅበራት ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ እራሱን በቻለ መልኩ መንፈሳዊና ትውፊታዊ እሴት ያለው ተግባር ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ
መንፈሳዊ ይዘቱን ትውፊታዊ ሕልውናውን እያጣ መምጣቱን ብዙ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጽሑፎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
የሚያነሱት ዓብይ ጉዳይ ከሆነ ውሎ አድሯል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የማኅበራት አሰተዳደር ደንብ ጥቅምት 2015 ዓም በቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ማኅበራት እየተበራከቱ የመጡበት ወቅት በመሆኑ ማኅበራት ለቤተክርስቲያን
የሚያበረክቱት በጎ አስተዋፅኦ ሊኖር ስለሚገባ ¬ በቤተ ክርስቲያን አካላት ክትትል እየተደረገባቸው የሚቋቋሙበት ዓላማ መሠረት
አድርጎ መደበኛ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥራው በማኅበራቱ እየተደገፈ በአግባቡ መወጣት እንዲችል፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እና
መዋቅር ሥር የሚቋቋሙ ማኅበራት የሚያቅፏቸው አባላት፣ የሚሰበስቡት ሀብትና ንብረት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አካላት
ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግበት የሚያስችልን ሥርዓት የሚዘረጋ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ደንብ ያወጣ የነበረ
ቢሆንም መዋቅሩ ወደታች ባለመውረዱ የማህበራት ቁጥር በጅጉ እየጨመረ መጥታል፡፡

የማኅበራት መደራጀት በጎ ሆኖ ሳለ ማኅበራት አሁን ባሉበት ሁኔታ ልቅ ሆነው መንገድ ከሄዱ ቀጣዩን ትውልድ በቤተክርስትያን
ማዕቅፍ ውስጥ ለመምራት እና የቤተክርስትያንን ቀኖና እና ዶግማ ጠንቅቀው እንዲያውቁ ለማድረግ እጅግ ያስቸግራል ፤ ነገ ይህን
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ማኅበር ለመቆጣጠርና ለመምራት እኛም የዚህ ጥናት አጥኚዎች በተጠቀሰው ርዕሰ ጉዳይ ላይ መንፈሳዊ ይዘቱ
ምን እደሚመስል እና ትውፊታዊ ህልውናውን ከማስጠበቅ እና በቂ ግንዛቤን ከመፍጠር አንጻር ነው ። ጥናቱም ፍፃሜውን ካገኘ
በኋላም በአጥኚዎች አስፈላጊና መሠረታዊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡትን የመፍትሔ ሃሳቦች የሚሰጡ ሲሆን እነዚህም በጥናቱ
በሚገኙ ችግሮች ላይ መሠረት ያደረጉ ናቸው

፩.፫ የጥናትና ምርምሩ ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic research question)


1. የዘመናችን የመንፈሳዊ ማኅበራትን ማን እየጀመራቸው ነው? አላማቸውስ ምንድን ነው? በቤተ ክርስቲያን ላይስ ምን አይነት
ተፅዕኖ አድርስዋል?
2. የመንፈሳዊ ማኅበራት አስፈላጊውን አትኩሮት በመዋቅር ደረጃ ካሉት የባለድርሻ አካላት አግኝቶዋል ማለት ይቻላል ?

3. በቤተክርስትያን ስር የሌሉ ማኅበራት በምን ምክንያት ነው? በቤተክርስትያን ስር አለመኖራቸው ጉዳትና ጥቅሙ ምንድን
ነው?
4. የመንፈሳዊ ማኅበራት ቁጥራቸው መዋዠቅ ብሎም እሰከመፈረስ የሚደረሳቸው ችግሮች ምንድን ናቸው?

፩.፬ የጥናትና ምርምሩ ዓላማ

፩.፬.፩ ዓብይ ዓላማ (General Objective)


የዚህ ጥናት መሠረታዊ ሐሳቡ የሚያተኩረው የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በቤተ ክርስቲያን ከየት ወደ የት ብሎም ምን
የመንፈሳዊ ማኅበራት እንቅስቃሴ እንደሚመስል መቃኘት ነው፡፡
፩.፬.፪ ንዑስ ዓላማ (Specific Objective)
1. ምዕመናን ስለ መንፈሳዊ ማኅበር የሚቋቋሙበትን አመሰራረት እና ያለቸውን አፈጻጸም ወይም አተገባበር ና አላማቸው
ግንዛቤ እንዲያገኙና በቤተክርስትያን ላይ በጎ ተዕፅኖ ያለቸው ማኅበራት ላይ ብቻ የሚቋቋሙበትን መንፈሳዊና ሰብዓዊ
ተግባራትን በመፈጸም ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲፈፅሙ ማድረግ
2. የመንፈሳዊ ማኅበራት የባለድርሻ አካላትን አትኩሮት አግኝቶ ሊኖራቸው የሚገባውን የእውቀትና የአፈጻጸም ሒደትን
ማመላከት
3. በቤተክርስትያን ስር የሌሉ ማኅበራት በቤተክርስቲያን ስር እንዳይሆኑ ያደረጋቸውን ችግር በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ
መሰጠት
4. የማኅበራትን የውስጥ ችግር ለቤተክርስቲያና ላይ ያለውን ተፅኖ በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን መስጠት

፩.፭ የጥናትና ምርምሩ ጠቀሜታ (Significance of the study)


 የመንፈሳዊ ማኅበራት ከጥንታዊው የቤተክርስቲያን አስተምህሮት አንጻር ያላቸውን የተቀባይነት መጠን ከማሳየት በዘለለ
የሚያስከትሉትን አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ ከመግለጽ አንጻር ጠቀሜታ አለው፡፡
 የመንፈሳዊ ማኅበራት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በማሳየት ጥናቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው የባለድርሻ አካላት መውሰድ
ስለሚኖርባቸው የመፍትሔ እርምጃዎችን/ድጋፎችን ከመጠቆም አንጻር ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
 ምዕመናን ስለ መንፈሳዊ ማኅበር የሚቋቋሙበትን አመሰራረት እና ያለቸውን አፈጻጸም ወይም አተገባበር ና አላማቸው ግንዛቤ
እንዲያገኙና በቤተክርስትያን ላይ በጎ ተዕፅኖ ያለቸው ማኅበራት ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ከመግለጽ አንጻር ጠቀሜታ አለው፡፡
 ማኅበራት የሚጋጥማቸውን የውስጥ ችግር ሊቀርፉበት የሚችሉ ሃሳቦች፣ አቅጣጫችን ምን መሆን እንዳለበት ከማመላከት
ረገድ ራሱን የቻለ በቁዔት ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
 በጥናቱ የሚገኙ ውጤቶችን በማሳወቅ በቀጣይ በዚህ ርዕሰ ጉዳዩ ላይ ከዚህ ሰፋ ባለ መልኩ ጥናት ለመስራት ለሚነሱ
አጥኚዎች ጉልህ ጠቀሜታ ይኖረዋል በሚል ጽኑ ተስፋ የሚሰራ የጥናትና የምርምር ጹሑፍ ነው፡፡

፩.፮ ጥናትና ምርምሩ ውስን ያልሆነበት (Delimitation of the study)


በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ 230 (እንደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ፌስቡክ ገፅ) በላይ አድባራትና ገዳማት መኖራቸውን
መረጃዎች ያመለክታሉ ሆኖም በሁሉም አድባራትና ገዳማት ዞሮ ጥናት ለማድረግ የገንዘብና የጊዜ እጥረት ከመኖሩም በላይ ባለቸው
ከፈተኛ ተመሳሳይነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን እና አካባቢው
ላይ ብቻ የሚሰራ ሲሆን ብሎም ይህ ጥናት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በተመለከተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና
ሥርዓት መሰረት የተዘጋጁትን መረጃዎችን ብቻ እንደ አጋዥነት የተጠቀመ ነው።

፩.፯ የጥናትና ምርምሩ ውስንነት (Limitation of the study)


በጥናትና ምርምሩ ወቅት ሰለ መንፈሳዊ ማኀበራት የተፃፉ መፀሃፎች እና በርዕሰ ጉዳዩ የተፃፉ ፅሁፎች በጣም አናሳ እና የሉም
ቢመባል ደረጃ መሆኑ
ምንም እንካን ጥናቱ እንዳ ሀገር ከፈተኛ በጀት፣ ንብረት እና ሰው ያህል ተመድቦ ሊሰራ የሚገባው ቢሆንም ባለን አቅም ልንስራ
የምንችለው እንደ ደብራችን እነደ የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስትያንእና አካባቢው መሆኑ የጥናትና ምርምሩ ውስንነት
ነው፡፡

፩.፰ የቃላት ትርጉም (Definition of term)


መንፈሳዊነት በአምላክ መልክ በመፈጠራችን ያገኘነው ችሎታ ነው። (ዘፍጥረት 1:27) መንፈሳዊ ሰው ጠንቃቃ፣ ትሁት ይቅር ባይና
የዋሕ የሆነ፣ በጸሎትና ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት የበረታ ሰው፣ እንቅስቃሴው ሁሉ በመንፈስ የተቃኘ
ነው፡፡https://eotcmk.org/ኦርቶዶክሳዊ-መንፈሳዊነት

ማኀበር ሰዎች ለተመሳሳይ ዓላማ የሚፈጥሩት የሰዎች ትብብርና ስብስብ ነው፡፡

ሁለንተናዊ ተጽዕኖ : በአጠቃላይ በሃይማኖት በታሪክ በኢኮኖሚ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ያለው ጥሩ ወይም ጎጂ ተግባር/ስራ
እና አመለካከት ወይም ዕወቀት

ቤተክርስቲያን:- ቤተክርስቲያን እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥሮ ቤተ ክርስቲያን ማለት “እግዚአብሔር ግዕዛን ካላቸው
ፍጥረታት ጋር ያለው ግንኙነት ነው ይላሉ አንድም ቤተክርስቲያን ማለት የክርስቲያን ወገን ማለት ነው ክርስቲያን የሆነ ሁሉ
(የምእመናን አንድነት ጉባኤ) የሚጠራበት ስም ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ይህም ስብስቡን ብቻ ሳይሆን በዋናነት በመካከላችን ያለውን
ፍቅር ትስስር ህብረት አንድነት ነው የሚመለከተው፡፡ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ራስነት አንድ አካል የሆኑ የምእመናን አንድነት ናት
(https://astemhro.com/).
ምዕራፍ ሁለት

የተዛምዶ ጹሑፍ ዳሰሳ (Literature Review)


የቀለም ቀንዱ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንደተረጎሙት ማኅበር ማለት ‹‹በቁሙ አንድነት ፤ ሸንጎ ፤ ብዙ ሰው ›› ማለት ነው ፡፡
በሌላም አተረጓጎም ‹‹ወገን ፤ ነገድ ፤ ቤተሰብ ፤ ጭፍራ ፤ ሰራዊት›› የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል ፡፡ ማኀበር ሰዎች ለተመሳሳይ ዓላማ
የሚፈጥሩት የሰዎች ትብብርና ስብስብ ነው፡፡ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ - ጀምሮ በዓለማችን ውስጥ ሰዎች በርካታ ማኀበራትን
ፈጥረዋል፤ ስለዚህ ማኅበራት አማካኝነትም ብዙ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡

የማኀበራት አጀማመር

በዚህ ክፍል የቤተ-ክርስትያን ማኅበር አጀማመር ምን እንደሚመሲል የምናይበት እና የምንቃኝበት ሲሆን በ አራት ክፍል የከፈልነውና
ከ ነገደ መላእክት ህብረት ጀምሮ በብሉይ ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳን ኢንዲሁም አሁን በእኛ ዘመን እና ወቅት ማኅበራት አጀማመራቸውና
ማኅበራት ነብሩን? የሚለውን የምንመለከትበት ክፍል ይሆናል።

መንፈሳዊ ኅብረት (የክርስቲያኖች የኅብረት ኑሮ) በክርስቶስ ያመኑ ምእመናን የሚኖራቸው አንድነት ማለት ነው። ይህ አንድነት
በክርስቶስ ያመኑ ክርስቲያኖች በዕለት፣ ዕለት እንቅስቃሴያቸው ሁሉ አብሮ በመሆን መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ሕይወታቸውን
የሚያሳድጉበት፣ ለጽድቅ የሚያበቃቸውን በጎ ተግባራት የሚያከናውኑበት የኑሮአቸው አካል ነው። eotcmk.org/gibi

፪.፩.፪ በነገደ መላእክት ጊዜ

ጥሬ ቃሉን ስንመለከተው መልአክ የሚለው የግእዝ ቃልኹለት ትርጉሞች አሉት፡፡አንደኛው አለቃ፣ ሹም ማለት ነው፡፡ በዮሐንስ ራዕይ
ላይ የምናገኛው ሰባቱ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች መላእክት ተብለው መጠራታቸውም ከዚኽ አንጻር ነው /ራዕ. 2 እና 3/፡፡
ኹለተኛውና ከተነሣንበት ርእስ አንጻር ስናየው ደግሞ መልክእተኛ፣ የተሰደደ፣ የተላከ የሚል ትርጕም አለው /ዕብ.1፡14/፡፡ ይኸውም
የመላእክት ተግባርምን እንደኾነ የሚያስረዳ ቃል ነው፡፡መላእክት ከእግዚአብሔር ወደሰው፥ ከሰውም ወደ እግዚአብሔር የሚላላኩ
መናፍስት ናቸውና፡፡መላእክት በሌላ ስማቸው የሰማይ ሠራዊት ተብለው ይጠራሉ፡፡

መላእክት ኹለት ወገን ናቸው፡፡ብርሃናውያን መላእክትና የጨለማ አበጋዝ የኾነው የዲያብሎስ ሠራዊት የኾኑት እኩያን መላእክት፡፡
ስለዚኽ የእግዚአብሔርን መላእክት ከሌሎቹ መላእክት በአጠራር የምንለያቸው ቅዱስ በሚል ቅጽል ነው፡፡

መላእክት በመጀመሪያው ቀን በእለተ እሁድ በወርኃ መጋቢት 29 ቀን ተፈጥረዋል፡፡ (ኩፋ.2፡7-8) እግዚአብሔር መላእክትን ሲፈጥር
‹‹እምኅበ አልቦ ኅበቦ›› ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጥሮአቸዋል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን በማስመልከት፡-
“በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተፈጠሩ፤ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ” ይላል (መዝ.32፡6)፡፡ አፈጣጠራቸውም
እንደሰው በነቢብ /በመናገር/ ሳይሆን በአርምሞ /በዝምታ/ ተፈጥረዋል፡፡ ሊፈጥራቸው አስቦ ፈጠራቸውም::

ከብሉይ ኪዳን (ከህገ ኦሪት) በፊት ማኅበር (ነገድ) የነበረ ሲሆን ሦሰቱ የመላእክት ከተሞች/አኀጉረ መላእክት/ (ሰማየ ኢዮር፣ ሰማየ
ራማ እና ሰማየ ኤረር) ፣ መቶ ነገደ መላእክት ያለቸው እና አስር አለቆች ያለቸው የነበረ ሲሆን አስሩ ነገድ የአጋዕዝት አለቃቸው
ሳጥናኤል ነበረ ፡ (ሳጥናኤል ማለትም ቅሩበ እግዚአብሔር አኃዜ መንጦላዕት ፣አቅራቢ ስብሐት ማለት ነው) በወደቀ ጊዜ በቅዱስ
ሚካኤል ተደርባል ይህም በመላክትም ማኅበር የነበረ እና ያለ መሆኑን ነው። ለዚህም ጥሩ ማሳይ የሚሆነው በራእይ ዮሐንስ የተጻፈልን
ታሪክ ነው።

“በሰማይም ጦርነት ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም መልሰው ተዋጓቸው፤ ነገር ግን ድል
ተመቱ፤ በሰማይም የነበራቸውን ስፍራ አጡ። ታላቁ ዘንዶ፣ የጥንቱ እባብ ተጣለ፤ እርሱም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ
የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው ነው፤ እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።” ራእይ 12:7-9

፪.፩.፫ በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን በጣም ተደጋጋሚ ጊዜ ሰለ ማኀበረ የተገለፀ ሲሆን በዘፍጥረት 35፥9-11 እግዚአብሔር የአብራሃም የልጅ ልጅ ያእቆብን
ሰሙን እስራኤል ብሎ እደሚጠራው ከነገረው በኋላ ‘’ኹሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኀበር በአንተ
ይሆናል ነገስታትም ከጉልበትኽ ይወጣሉ’’ ብሎት የያእቆብ /እስራኤል ልጆች በጠቅላላ “እስራኤል ልጆች ማኅበር” በሚል
በተደጋጋሚ የተገለፀ ሲሆን ከዛ ውጪ የፃድቃን ማኅበር፣ የክፉዎች ማኅበር፣ የቅዱሳን ማኅበር ፣ አማልክት ማኅበር የነበሩና በመዝሙረ
ዳዊት 25-12 “እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና አቤቱ በማኅበር አመሰግናለው” ብሎ የማኀበር ተግባራት በብሉይ እንደነበር ማየት
ይቻላል፡፡

በብሉይ ኪዳን ወንድም/ባልንጀራ በሥጋ ከአንድ አባት እና እናት የተወለደ፣ በጉርብትና የሚኖር እስራኤላዊን የሚያመለከት ሲሆን
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል በሰጠው ፲ቱ ትእዛዛት ውስጥ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ሲል በጎረቤታሞች መካከል ንጹሕ
ፍቅር እንዲኖር የተሰጠ ትእዛዝ ነው፡፡ (ዘሌ ፲፱፥፲፰) በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሰፊ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ ይህም ወንድም/ባልንጀራ
በክርስቶስ አንድ አካል የሆኑትን የሚያጠቃልል ነው። ለዚህም ነው መንፈሳዊ/ክርስቲያናዊ ኅብረት ማለት በክርስቶስ ያመኑ ምእመናን
የሚኖራቸው አንድነት ነው የተባለው። eotcmk.org/gibi

፪.፩.፬ በሐዲስ ኪዳን

በሐዲስ ኪዳን ስንመለከት የፍቅር አባት የሥርዓት ባለቤት መድኃኔዓለም ክርስቶስ ማኅበራዊነትን በማኅበር ሆኖ አብሮ መብላት
መጠጣት እደሚገባ አስተምሮናል ። አብሮ መስራት መብላት የፍቅር መግለጫ ነውና ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመዋዕለ ስብከቱ ጊዜ የቃሉን ትምህርት ለመማር ፣የእጁን ተዓምራት ለማየት ይከተሉት የነበሩት አምስት እንጀራ እና ሁለት ዓሣ
ለአምስት ሺህ፤ ሰባት እንጀራ እና ጥቂት ዓሣ ለአራት ሺህ ሕዝብ በአንድነት ሰብስቦ ባርኮ መግቧቸዋል ማቴ 14፥14-21, ማቴ
15፥32-39 ።

ሌላው ደግሞ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሰፊ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ የክርስቲያኖች የመንፈሳዊ ኅብረት ኑሮ የተጀመረውና ጎልቶ
የተንጸባረቀው በአባቶቻችን ሐዋርያት ዘመን ነው። “በዚህም ወራት ጴጥሮስ መጦ ሃያ በሚያክል በሰዎች መኀበር አብረ በነበሩ
በንድሞቹ መካከል ተነስቶ…” በሚል የማሀበር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠሉን ማየት እንችላል፡፡ ይህ ዘመን ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት፣
፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት፣ ፸፪ቱ ቅዱሳን አርድእት፣ እንዲሁም በእነርሱ ትምህርት ተስበው በክርስቶስ ያመኑ ምእመናን ሁሉ በአንድነት
ይኖሩበት የነበረ ዘመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሁኔታ ሲገልጽ “ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ፣ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው”
እንዲል፡፡eotcmk.org/gibi

ከዘመነ ሐዋርያት በኋላ የነበረው ኅብረት (ክርስትና) እየተስፋፋ በመምጣቱ በክርስቲያኖች ላይ የተለያዩ ፈተናዎች ይደርሱባቸው
ነበር፡፡ እንደ ዘመነ ሐዋርያት ባይሆንም በመከራ ውስጥ ሆነውም መንፈሳዊ የአብሮነት ሕይወቱን አስቀጥለዋል፡፡ ይህም በየሀገራቱ
አንድ ዓይነት መልክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ገጽታዎች የሚከናወን ሲሆን በሀገራችንም በተለያዩ መንገዶች ሲሠራበት ቆይቷል።
eotcmk.org/gibi

ቀደምት አባቶቻችን ያንን ኅብረት በሰንበቴና በጽዋ ማኅበራት ለማስቀጠል ችለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ
እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።” (መዝ. ፩፻፴፫፥፩) በማለት እንደገለጸው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ እነዚህ እየተረሱና
እየተተዉ በመምጣታቸው በኅብረት ከመሆን ይልቅ በተለያዩ ምክንያቶች ግላዊ ሕይወት ላይ ትኩረት ማድረግ እየተለመደ መጥቷል።
eotcmk.org/gibi

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች ሲጽፍላቸው “ሌሎች ልማድ አድርገው እንደ ያዙት ማኅበራችንን አንተው፤ እርስ
በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ” ባለው መሠረት በኅብረት ለመኖርና ቀጣይነት ላለው
ሕይወት ትኩረት ልንሰጠው ይገባል። (ዕብ. ፲፥፳፭) eotcmk.org/gibi

ማኅበር በኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጽያ ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗን ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰከራል መዝ 67፥311 ። ኢትዮጵያ ሀገራችን በሕገ ልቡና
አምልኮተ እግዚአብሔርን የፈጸመች ፤ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች፤ በሐዲስ ኪዳን ከሁሉ በፊት ያመነች ብጽዕትና ቅድስት ሐገር ናት፡፡
1 ኛ ነገ 1፥1-9,

ማቴ 12፥42, ዮሐ 20፥ 28, ሐዋ 10፥26-39 ። በመሆኗም የአበውን እምነት እና ትውፊት የነብያትን ትንቢት እና ትምህርት
የሐዋርያትን ስብከት ሥርዓት ተቀብላ እነሆ በሥራ ካሠማራች ብዙ ዘመናት ተቆጥሯል ። ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በፍቅር
በአንድነት የኖሩ ሕዝቦች ናቸው። ነቢዩ በውኑ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን ይለውጣልን? ኤር 13፥23 ባለው መሰረት
ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ ባሕላቸውን እምነታቸውን ሥርዓታቸውን የማይለውጡ እና የጸኑ መሆናቸውን እንረዳለን ። ኢትዮጵያውያን
እንግዳ ተቀባይነት ዓለም በሙሉ የሚመሰከረው ነው ። የክርስትና እምነት በመላው ኢትዮጵያ ከተስፋፋበት ጊዜ አንስቶ ያለውን
ስንመለከት

ማኅበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ ያለ ቢሆንም በ 330 ዓ/ም የመጀመርያው ማኅበር መስራች አቡነ ሰላማ ናቸው ። የሰየሙት ማኅበር"
ማኅበረ ጽዮን" የሚል ሲሆን በአክሱም ነበር ። የማኅበር ዓላማ የሐዋርያትን ፈለግ የተከተለ ሲሆን ይኸውም ፍቅርና መግባባት
እንዲሰራበት ትምህርተ ወንጌል እዲስፋፋ ፣ነዳያን እዲረዳበት ፣ በሚል ነው የተቋቋመው። የወንጌል ትምህርት ሲፈጸም አጋፔ ይቀርባል
። በዚህ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት እየበዙ ሲሄዱ "ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊ" በሚል ስያሜ ተለወጠ ። ሰማያውያን የእግዚአብሔር
መንግስት ስለሚያስገቡ ነው ። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር ስለፀናባቸውም በመጨረሻም ስያሜውን "ጽዮን ማርያም
" ብለው ሰየሙት ።የማኅበር መስፋፋት ጀመረ በኢትዮጵያ ።
በ 14 ኛ መ/ክ/ዘመን ሕዝቡን በሃይማኖቱ የበለጠ ለማጽናት ፣ አፄ ዘርዓያዕቆብ በቅዱሳን እና በእመቤታችን ስም ማኅበር እዲጠጣ ህግ
አወጡ ። በዚህን ጊዜ በየደጀሰላሙ ሕዝቡ ማክበር ይጠጣ ነበር ። ካህናቱም እየተገኙ ያስተምራሉ ፣ ይባርካሉ ፣ በዚህ አኳኋን ማኅበር
እየተስፋፋ መጣ ። ውስጥ ውስጡን መታየት የጀመረው የአምልኮ ጣኦት እየጠፋ ሄደ ።

በ 16 ኛ መ/ክ/ዘመን የነበረው በደብረ ንግስት ቁስቋም የሚገኘው የጽዋ ማኅበር "ሰላም መድኃኒዓለም " ይባል ነበር ። በመጀመርያ
ያቋቋሙት አቡነ መብዓ ጽዮን ናቸው ። ማኅበሩም ከእመቤታችን እስከ መድኃኒዓለም ዕለት ድረስ ለሚሰበሰቡ አባላት ወንጌልን
እያስተማሩ, በመካከላቸውም በሽተኞችን ይፈውሳሉ ። ጽዋው ሱቲ ለብሶ አይሰገድለትም ።ሻማም እየበራ በየመንደር አይዞርለትም ።
ጽዋው የማኅበሩ የክብር ዕቃ እደመሆኑ መጠን የማኅበሩ የፍቅር የአንድነት መግባባት መገለጫ ስለሆነ ።ማኅበሩ የሚሰበሰቡበት ቀን
በወር የሚከፍለው ማኅበርተኛ ከፋይ መሆኑን አምኖ የሚመረቅበት እና የሚመራረቁበት ምርጥ እቃ ነው :: ማንም ወደ ቤቱ ይዞት
አይሄድም በቅጽር ቤተ ከርስቲፓን ማኅበሩ የሚጠጣበት ቤት አቃቢቷ ጋር ይቀመጣል ። በዚህም ስነ ስርዓት የቀድሞ ከርስቲያኖች
ሲፈጽሙ ኖሩ ። እስከ እኛ ዘመንም ደርሷል ፡፡

ለሰንበት ት/ቤት መመሰረት (አጀማመር) በኢትዮጵያ ዋንኛ ምክንያቶች በሚዘረርበት ላይ በበዕላት እና በፅዋ ማኅበራት በሰንበቴና
በአብነትትምህረት ቤት ቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ ተሰብስቦ የመማርና የማስተማር ሓዋርያዊ ትውፊት መኖሩ፣ የመናፍቃን ሰውር ደባ
ለመከላከል በዘመናዊ ትምህርት ቤቶች መንፋሰዊ ጉባኤያት መጀመር እና ማተናከር የወጣት ማኅበራት መቋቋም ለሰንበት ትምህርት
ቤቶች መመሰረት ምክንያቶች ነበሩ፡፡(በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ስ/ት/ቤ/ማደራጃ መመተያ ገፅ 281-284)

ሰንበት ትምህርት ቤት ከመመስረቱ በፊት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሚደረጉ የተማሪዎች ጉባኤ እንደነበረ ታሪክ ያስረዳል በ፲፱ 39
ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የዛሬው እንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ይማሩ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የጀመሩት ጉባዬ
እያደገ መጥቶ በ፲፱፵፱ዓ.ም ወደ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም በመዘዋወር እና በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔርን ይማሩ የነበረ
ሲሆን በ፲፱፶የተምሮ ማስተማር ማኅበር ተባለ፡፡ የወጣቶች ማኅበር መስፋፋት እንዲሁ ለሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን መስፋፋት እና
መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቶዋል፡፡የዛሬዎቹ ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን የነሱ ውጤቶች ናቸው፡
(በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ስ/ት/ቤ/ማደራጃ መመተያ ገፅ 281-284)

የነዚህ ማኅበራት መቋቋም በዘመኑ የነበረውን በቤተክርስቲያናችን ላይ የተቃጣውን ፈተና ለመመለስ ታስቦ ነበር፡፡ከላይ ለመግለጽ
እንደተሞከረው በ፲፱፵ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አድባራትና ገዳማት በአጠቃላይ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የተሰባሰቡ ወጣቶች
መንፈሳዊ ማኅበር በማቋቋም ቤተክርስቲያንን ማገልገል ጀመሩ ይኸውም የሆነው የመናፍቃን ወረራ ለመቋቋም ነው በጊዜው ወጣቶቹ
መጽሐፍ ቅዱስ እና ትምህርተ ሃይማኖትን ከመዝሙራት ጋር ያጠኑ ነበር፡፡(በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ስ/ት/ቤ/ማደራጃ መመተያ ገፅ 281-284)

ከዚያም በ፲፱፵፪/፵፫/ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመዞር የወንጌል መልእክተኞች እና የእሑድ ትምህርት ቤት ተመሠረተ፡፡
በዚሁ ዘመንም የአስመራው ማኅበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት ማኅበር ተቋቋመ፡፡ ከዚያም በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ዋናዋና
ከተሞች ላይ የቤተክርስቲያን ልጆች መንፈሳውያን ማኅበራትን ማቋቋም ጀመሩ እነዚህ ማኅበራት በጊዜው ስብከተወንጌል እና
ማስታወቂያ መምሪያ ሥር የወጣቶች መንፈሳውያን ማኅበራት አንድነት ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በሚል በጠቅላይ ቤተክህነት ሥር
ተቋቁሞዋል፡፡ይህ ማእከላዊ የወጣቶች ማኅበር እስከ ፲፱፷፭ በመጠኑም ቢሆን የወጣቶችን መንፈሳዊ ማኅበር ሲያስተባብረው ቈይቶ
በ፲፱፷፭ ወደ ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ አደገ፡፡(በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ስ/ት/ቤ/ማደራጃ መመተያ ገፅ 281-284)

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው አዲስ አበባ ተቋቁሞ የነበረው የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር በ፲፱፷፮ዓ.ም የመንግሥት ለውጡን
ተጠቅመው በራሳቸው አነሳሽነት ስብሰባ በማድረግ በርካታ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡መምሪያውን ያጠናከረው አጠቃላይ ጉባኤ ነበር፡፡
በአጠቃላይ ጉባኤው እና በወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ማኅበራቱ እንደቀድሞው በማኅበርነታቸው ቀጥለው በ፲፱፸ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ
ሕጋዊ አካል ሆነ፡፡ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ በ፲፱፸፬ በደርግ መንግሥት የወጣቶች ማኅበር አኢወማ ጋር በስም ይመሳሰላል ተብሎ
በቤተክርስቲያናችን አባቶች ብልሃት የተሞላው ቀይረዋል፡፡መምሪያውም ከወጣቶች መምሪያ ወደ ሰንበት ማኅበራቱ ወደ ሰንበት
ትምህርት ቤት ስማቸውን ተቀይሮ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምሪያ ስሙ ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተብሎ እስከ ዛሬ
አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡ (በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ስ/ት/ቤ/ማደራጃ መመተያ ገፅ 281-284)

ከ 1980 ወዲህ ቤተክርስትያኗ አስቀድማ ካስቀመጠችው አወቃቀር የተለየ በተለየ በ 1990 ዎቹ መጨረሻ የማበራት ቁጥር እጅግ
እየበዛ መጣ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሺህ የሚቆጠሩ ማኅበራ ይገኛሉ ፤ ባለፉት 20 ዓመታት በሁለት እግሩ የቆመ ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን
አንድ ምሳሌ ነው ፤ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተዋቀረው እና በሰንበት ትምርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር ሆኖ
ቤተክርስትያኗ ያሉባትን ክፍተቶች በተለያዩ ባለሙያዎች በተጠናና በሚጠቅም መልኩ እየሞላ የሚገኝ ማኅበር ነው፡፡ ሌሎች መልካም
ስራ ያላቸው ማኅበራ ቢኖሩም በብዛት በቤተክርስትያኗ መዋቅር ስር አይደሉም ፤ መልካም ስራቸውንም በአደባባይ ማሳየት አልቻሉም
፤ ቅዱስ ሲኖዶስም አያውቃቸውም ፤ ማኅበረ ቅዱሳን የከፍተኛ የትምህር ተቋማት ተማሪዎችን ተገቢ ሊባል በሚችል መጠን
በሚችለው አቅም ያህል አስተምሮ አባል እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ሌሎች ማኅበራት ግን አባላቶቻቸው በምን ያህል መጠን እንደተማሩ
አይታወቅም፡፡

ስለሆነም ከስሜቶቻቸው ጋር የሚጣጣም ማንኛውንም ነገር ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚከለክላቸው ምንም ነገር የለም፡፡ ለምን ቢባል
የቤተክርስትያን አስተምህሮ በአባላቶቹ ዘንድ በጠለቀ መጠኑ ስለማይታወቅ ነው፡፡ ስለሆነም ቤተክርስትያን የወጣቱን መንፈሳዊ
ስሜትን ተረድታ ጉድለታቸውን ሞልታ በበሳል አመራር ለመልካም ነገር ልትጠቀምበት ይገባል ፤ በተለይ የጌታችንና የመድሐኒታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትንና የመስቀል በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተለያዩ ደብሮች የተሰበሰቡ ወጣቶች የላቀ ትኩረት
ያስፈልጋቸዋል፡፡ በብዙ ድካም ልትሰበስባቸው ሲገባ ያለምንም ጥረት በፈቃደ እግዚአብሔር ተሰባስበዋልና ይህን መልካም አጋጣሚ
ተጠቅማና ስሜታቸውን ጠብቃ መሰረታዊውን የሀይማኖት ትምህርት በማስተማር ወደሚፈለገው ደረጃ ልታደርሳቸው ይገባል ፤
የነገይቱን የቤተክርስትያን ተረካቢ መሆናቸውንም ልንዘነጋ አይገባም ፤

የማኅበራት ዓላማ

ማኅበራት ዝርዝር ዓላማቸው በደንባቸው ላይ የተገለጸ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዓላማዎች መሠረት አድርገው ሥራቸውን
ከሚተገብሩበት ሀገረ ስብከት እና ተጠሪ መዋቅር ጋር በመናበብ የተቋቋሙበትን ለማስፈጸም ይቋቋማሉ፡፡ እንደ አትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተ ክስቲያን የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ ማኅበራት እነዚህ አላማ ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል

፩. ትምህርተ ሃይማኖት ለሁሉም እንዲዳረስ ለሚሠሩ ተጠሪ መዋቅራዊ ተቋማት ድጋፍ መስጠት፤

፪. የቤተ ክርስቲያን አካል የሆኑ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተካፋይ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት፣

፫. ምእመናን ቤተ በገንዘባቸውና ክርስቲያንን በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ የማሳወቅና የማስተባበር ሥራ ላይ


ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፣

፬. በቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ታሪክ፣ ትውፊት እና በአብነት ትምህርት ቤቶቿ እንዲሁም ልማታዊ ተግባራት ዙሪያ ጥናትና
ምርምር በማድረግ በሚመለከተው የሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ እንዲጸድቅ ዓደር ደንብ ማድረግ እና ለተግባራዊነቱ ከሚመለከተው
መዋቅራዊ አካል ጋር በጋራ ሆኖ ለውጤት መትጋት ፣
፭. በጎ አድራጊ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በማስተባበር ገዳማትን፤ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ቅርሶችን፤ በተለያየ ጊዜ በሰው ሰራሽ እና
በተፈጥሮ አደጋ ለሚደርሱ ጉዳቶች የመልሶ _ ማቋቋም እና ድጋፍ ከሚሠሩ መዋቅራዊ ተቋማት ጋር በጋራ መሥራት እና አስፈላጊውን
ድጋፍ ማድረግ፤

፮. የቤተ ክርስቲያንን ቅርሶችና ሀብቶች በአግባቡ ለምእመናን እንዲሁም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ዜጎች የማሳወቅ ሥራን
ከሚመለከተው መዋቅራዊ አካል ጋር በጋራ መሥራት እና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፤

፯. በተለያዩ ምክንያቶች የተዘጉ ወይም አገልግሎታቸው ያልተሟላ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ እና አገልግሎት እንዲሰጡ
ከሚመለከተው መዋቅራዊ አካል ጋር በጋራ መሥራት እና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ፤ ፰. ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ሥነ ምግባር
በምእመናን ዘንድ እንዲጎለብት እና እንዲጠናከር ለሚመለከተው መስጠት ድጋፍ መዋቅራዊ ክፍል መሥራት፤ እና በጋራ

፱. ካህናት እና ምእመናን መንፈሳዊ ይዘቱን በጠበቀ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የመረዳዳት ሕይወታቸው እንዲበረቱ የሚያስችሉ
ተግባራትን ከሚመለከተው መዋቅራዊ አካል ጋር በጋራ ማከናወን እና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፤

፲. ሌሎች ከቤተ ክርስቲያን ዓላማ ጋር የማይቃረኑ በጎ መንፈሳዊ ተግባራትን ሥልጣን ካለው ከቤተ ክርስቲያኗ መዋቅራዊ ክፍል ጋር
በመናበብ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት እና ትብብር ማድረግ፡፡ (የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

የማኅበራት ዓይነቶች

፩. “ጠቅላላ ማኅበር” ማለት፡- ቁጥራቸው ፸፻፶/ሰባት መቶ ኀምሳ/ እና ከዚያ በላይ በሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን እምነት ተከታይ፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ ፈቃደኛ በሆኑ ሙሉ ወይም ለመማር የሚቋቋም፣
የተቋቋመበትን መንፈሳዊ አባላት አገልግሎት ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ አህጉረ ስብከት የሚፈጽምና ደር ደንብእና ጠቅላላ ጉባኤው
የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካል የሆነበት ማኅበር ነው፤(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

፪.“የማኅበራት አንድነት ኅብረት” :- በጠቅላላ ማኅበር ቅርጽ የተቋቋሙ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ማኅበራት የጋራ ዓላማቸውን
ለመፈጸም _ ኅብረት በመፍጠር የሚመሠርቱት ሲሆን ቁጥሩም ከ፩/አንድ/ በላይ ሊሆን የማይችል ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር
ደንብ)

፫. “የሙያ ማኅበር” ማለት፡- በተመሳሳይ ሙያ ያሉ/የተመረቁ/ ቁጥራቸው ፲፪/አሥራ ሁለት/ እና ከዚያ በላይ በሆኑ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ ወይም ለመማር ሙሉ
ፈቃደኛ በሆኑ አባላት የሚመሠረት ሲሆን፤ አባላቱ ባላቸው ዕውቀት እና ልምድ መሠረት ቤተ ክርስቲያንን በሚጠቅሙ ልዩ ልዩ
የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን እና የምክር የሚቋቋም፣ አገልግሎቱን ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ አህጉረ ስብከት የሚፈጽም እና ጠቅላላ
ጉባኤው የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካል የሆነበት ማኅበር ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

፬ “የሐዋርያት አገልግሎት ኑሮ አንድነት ለመስጠት ማኅበር” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ፤ የሰበካ
ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ ወይም ለመማር ሙሉ ፈቃደኛ በሆኑ አባላት የሚቋቋም፣ ሕይወት ታንጸው በዓለም
በመንፈሳዊ አባላቱም እየኖሩ በዕውቀታቸው በጉልበታቸው እና በገንዘባቸው ከማናቸውም ገቢ የሚያገኙትን ሀብትና ንብረታቸውን
ለጋራ መንፈሳዊ ዓላማ በማዋል በአንድነት የሐዋርያትን ኑሮ ለመኖር በቁጥር ፲፪/አሥራ ሁለት/ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ስብስብ
ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)
፭. “መንፈሳዊ የአስጎብኚ : ማኅበር” ቁጥራቸው ፲፪/አሥራ ሁለት/ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን እምነት ተከታይ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ እና ጠንቅቀው የሚያውቁ እንዲሁም በቤተ
ክርስቲያን ቅርሶች ላይ በቂ ዕውቀት ባላቸው አባላት የሚቋቋም ሆኖ ዓላማውም የቤተ ክርስቲያንን ቅርስ፣ ሀብት፣ ሥርዓት፣ ታሪክ እና
ትውፊት ለሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ለሚመጡ ጎብኝዎች ታሪክን እና ትውፊትን ሳያፋልሱ በአግባቡ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ እና
የሚያስጎበኙ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

፮. “መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር” ቁጥራቸው በአሥራ ሁለት/ እና ከዚያ በላይ በሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
እምነት ተከታይ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ ወይም ለመማር ሙሉ ፈቃደኛ በሆኑ አባላት የሚቋቋም ሆኖ
እንዲሁም ታሪካዊ እና ትውፊታዊ መንፈሳዊ ቦታዎችን ዓላማውም የተለያዩ ጥንታዊ ገዳማትን እና አድባራትን ለመጎብኘት እና
መንፈሳዊ በረከትን ለማግኘት እናለማስገኘት በማሰብ ለብዙኃን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚቋቋም ማኅበር ነው፡፡(የማኀበራት
አሰተዳደር ደንብ)

፯. “የበጎ አድራጎት ኮሚቴ” ማለት ቁጥራቸው ፭ /አምስት/ ወይም ከዚያ በላይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ እና የሰበካ ጉባኤ አባላት
ክርስቲያን እምነት ተከታይ በሆኑ የኢትዮጵያ በሆኑ ገንዘብ ወይም ሌላ ንብረት ለአንድ የቤተ ክርስቲያን አስቸኳይ የበጎ አድራጎት ዓላማ
ከሕዝብ ለመሰብሰብ ለመርዳት ለመደገፍ ዓላማና ግብ ያላቸው ሰዎች ስብስብ ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

፰. “ሁለ ገብ መንፈሳዊ አገልግሎት ማኅበር” በአንድ ሀገረ ስብከት ቁጥራቸው ከ፪፻፶ሁለት መቶ ኀምሳ/ በላይ በሆኑ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ፤ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና ትምህርተ ሃይማኖትን የተማሩ ወይም ለመማር ሙሉ
ፈቃደኛ በሆኑ አባላት በማኅበሩ መተዳደርያ ደንብ እና መመሥረቻ ጽሑፍ የዓላማ ይዘት እየተመዘነ ውስን ለሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት
ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ፈቃደኛ በሆኑ ምእመናን የሚቋቋም ማኅበር ነው፡፡(የማኀበራት አሰተዳደር ደንብ)

፱. የጽዋ ማኅበር ጽዋዕ ማለት በቁሙ ኩባያ’ዋንጫ’የመጠጥ መሣሪያ የሚል ትርጉም አለው፡፡ በሌላም በኩል በጽዋ ተቀድቶ
የሚሰጥም መጠጥ ጽዋ ይባላል፡፡ ማኅበር ማለት ደግሞ‹‹ኀብረ›› አንድ ሆነ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው፡፡ በአንድ ላይም ጽዋ
ማኅበር ማለት በጽዋ ለመጠጣት የሚሰባሰቡ የምእመናን አንድነት ማለት ነው፡፡ ጽዋ ማኅበር ምእመናን በወር ወር ተራቸውን እየጠበቁ
እየደገሱ የሚያበሉበት እንዲሁም ችግረኞችን የሚረዱበት ሥርዓት ነው፡፡ በጽዋ ማኅበር መሳተፍ በረከትን ያሰጣል (መዝ 3.8′
ምሳ 10.7) እንዲሁም በማቴ 10.42 ላይ እንደተገለጸው ዋጋን አያጠፋም፡፡ https://kidusmichaeltswa.org

የጽዋ ማኅበር አመሰራረት ትውፊታዊ ባህልን የተከተለ ነው፡፡ በዘመነ ሥጋዌ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በአንድነት የፍቅር ማዕድ
/አጋፔ/ ይመገቡ ነበር፡፡ ኋላም ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታ እርገት በኋላ ካመኑና ከተጠመቁ ክርስቲያኖች ጋር በአንድነት ኑሯቸውን
እንዳደረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ሐዋ.ሥራ 2.44-47 https://kidusmichaeltswa.org

በዘመነ ሰማዕታት ግን ይህ ሁኔታ በአብዛኞቹ ክርስቲያኖች ተረስቶ ነበር፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ግን ይህ ትውፊት በአባቶታቻችን
ጸሎት’ብርታት ባህሉ ወጉ ሥርዓቱ ሳይፋለስ ተጠብቆ ለትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን
በኢትዮጲያ የመጀመሪያው የጽዋ ማኅበር መሥራች አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲሆኑ ወቅቱም በ 330 ዓ.ም በአክሱም ነበር፡፡
የማሕበሩ ስም በመጀመሪያ ‹‹ማኅበረ ጽዮን›› ይባል የነበረ ሲሆን ቆይቶ ‹‹ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊ›› ተባለ በመጨረሻም ‹‹ጽዮን
ማርያም›› በመባል ስሙ ሊለወጥ ችሏል፡፡ በ 14 ኛው መ/ክ/ዘ አፄ ዘርዓያዕቆብ ሕዝቡን በሃይማኖቱ የበለጠ ለማጽናት በማሰብ
በቅዱሳንና በእመቤታችን ስም ማኅበር እንዲጠጣ ሕግ አወጡ፡፡ ቀጥሎም በ 16 ኛው መ/ክ/ዘ ማኅበረ ሰላም መድኃኔዓለም የተባለ
በአቡነ መብዓጽዮን የተቋቋመ ማኅበር እንደነበር የቤተክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል፡፡ https://kidusmichaeltswa.org
በቤተክርስትያኒቷ ስር ያሉትን ማኅበራት የሚጀምቸው አካላት እና ከሚያዋቅራቸው አካል

1. ክፍተትን ለመሙላት የተቋቋሙ

እነዚህ ማኅበራት ቤተክርስትያን በነበራት መዋቅር ልትሸፍነው ያልቻለችውን ክፍተት ለመሙላት የተቋቋሙ ማኅበራት ናቸው ፤
ክፍተትን ተረድተው ለመሙላት የሚቋቋሙ ናቸው እነዚህ ማኅበራት የአጭር እኛ የረዥም ጊዜ እቅድ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ
ለምሳሌ ህንጻ ቤተክርስትያን ለማሰራት ፤ እድሳት ለማከናወን ፤ ቤተክርስትያኒቷ የራሷ ተቋም እንዲኖራት የሚሰሩ ፤ የተዘጉ
ቤተክርስትያናትን ለማስከፈት ..እና መሰል አላማን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፡፤ ዛሬ ማኅበራቱ በመሰረቷቸው መልካም ሰዎች
አማካኝነት ጠንካራ ማንነት ቢኖራቸውም እንኳን ነገ እነርሱን የሚተኳው ሰዎች ዓላማቸው ሊለወጥ ስለሚችል የቤተክርስትያን ስጋት
ከመሆን አያልፉም ፤ https://andadirgen.blogspot.com

2. የገጠሪቱን ቤተክርስትያን ለመርዳት በሚል የተዋቀሩ ማኅበራት

በገጠሯ ቤተክርስትያን ያሉ አገልጋዮች ያለባቸው ፈተና በጣም ብዙ ነው፡፡ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኝት ቀን ቀን ከእርሻ ጀምሮ በልዩ
ልዩ ስራዎች ተጠምደው ይውላሉ ፡፡ ማታ ማታ ደግሞ በትግሀ ሌሊት እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ያድራሉ፡፡ በብዙ መዋተት ያገለግላሉ
፤ በዚያ ላይ አልሞላ ብሏቸው ይኖራሉ ፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚቋቋሙ ማኅበራት አሉ፡፡

እነዚህ ማኅበራት የሚያዩትን ችግር አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ለመፍታት ብለው ተመሳሳይ ስሜትና መንፈስ ያላቸውን
ወንድሞችንና እህቶችን በማሰባሰብ በግለሰቦች ቅንነት የተመሰረቱ ማኅበራት ናቸው ፤ አላማቸው እና ምልከታቸው የሚደነቅ ነው ፤
ቤተክርስትያናት በጎደላት ጊዜ ደርሳችሁላታል ፤ ልትመሰገኑ ይገባል ፤ ነገር ግን ሩጫችሁን በድል ለማጠናቀቅ ስለሚቀጥሉት ነገሮች
ተወያይቶ መፍትሄ ማስቀመጥ ያስፈልጋል  ማኅበራቱ የሚዋቀሩት በሰዎች ማንነት ላይ ተመስርተው ነው፡፡ ስለሆነም ግለሰቦች
እንቅፋት በገጠማቸው ጊዜ በርካታ ተከታዮቻቸው የስብስቡን አላማ ከግብ ለማድረስ ሊሳናቸው ይችላል ፡፡ በወንጌል ትምህርት
ያልበሰሉ ከሆኑ ደግሞ ዓላማቸውን በጥቂት መሰሪ ሰዎች ቀይረው መስመራቸውን ሊያስቷቸው ይችላሉ ፤
https://andadirgen.blogspot.com

 ማኅበራ አቅማቸው በፈቀደ መጠን ገንዘብ አሰባስበው ወደ ገጠሯ ቤተክርስትያን በመውሰድ አገልጋዮች ካህናትንና ዲያቆናትን
የተወሰነም ቢባል ደመወዝ በመክፈልና ንዋያተ ቅድሳትን በሟሟላት የተቋረጠውን አገልግሎት እንዲቀጥል የተዘጋችዋን ቤተክርስትያን
እንድትከፈት ፤ የተዳከመው እንዲበረታ በማድረግ ፤ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ጉልህ ድርሻ ጎን ለጎን ግን ስራው
ተጠንቶና ዘላቂነቱ ተረጋግጦ የተጀመረ ባለመሆኑ በየወሩ የሚያወጡት ገንዘብ ከጊዜው የኑሮ ሁኔታ ጋር እየከበዳቸው ይሄዳል ፤
እንቅስቃሴያቸውም በጊዜያት ሂደት እየቀዘቀዘ ይመጣል ፤ በመሆኑም አባላት ወርሐዊ ክፍያቸውን ድንገት ሲያቋርጡ ማኅበራቱ
የሚያቀርቡት ገንዘብ ያጡና የጀመሩት ስራ ይቋረጣል፡፡ ይህን የመሰለ ችግር ወደፊት ለስራቸው እንቅፋት እንደማይሆንባቸው
አውቀውት ቢገቡበት መልካም ነው፡፡ https://andadirgen.blogspot.com

3. ቁጭት የመሰረታቸው ማኅበራት

አህዛባዊ ግብር ባላቸው አካላት በቤተክርስትያን ላይ በደረሰው ጉዳት አንገብግቧቸው በቁጭት የተመሰረቱ ማኅበራትን ይመለከታል ፤
ከአህዛብያውያን አኩይ ግብር የተነሳ አብያተክርስያናት በእሳት እንዲጋዩ ፤ ካህናትና ምዕመናንም በቤተ መቅደሳቸው በሰይፍ ሲታረዱ ፤
ቤተክርስትያን ላይ እሳት ሲሎከስባት ፤ በየቦታው የሚገኙ ክርስትያኖች ላይ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ችግር ሲደርስባቸው ባዩ እና
በሰሙ ጊዜ አዝነው መፍትሄ ለማምጣት ብለው ወጣቶችን በማሰባሰብ የመሰረቸቷው ማኅበራት ናቸው ፡፡ የማኅበሩ አባላት
በቤተክርስትያን ባላቸው ጥልቅ ፍቅርና ተቆርቋሪነት የተሰባሰቡ ናቸው፡፡ ስለ ቤተክርስያን ስርዓት አስተምህሮ ዶግማ እና ቀኖና
ያላቸው እውቀት አናሳ ቢሆንም ፍቅራቸውና መቆርቆራቸው ግን በጣም ጥልቅ ነው፡፡

ቤተክርስያኗ ላይ አንድ ፈተና ቢመጣ እንኳን ከሁላችንም ይልቅ ቀድመው ከፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ እንዲህ አይነት ቅናትና መቆርቆር
ይዞ የመጣን ሰው ደግሞ በአግባቡ ተቀብሎ ማስተናገድ የቤተክርስያኒቱ ተግባርና ሀላፊነት ይመስለናል ፡፡ መንፈሳዊ ከመሆን ጋር
የሚመጣውን ፈተናና የቅዱሳንንም ሕይወት በውል ስለማያውቁ ትከሻቸው መከራንና መገፋትን ለመሸከም አይችልም፡፡ ስለዚህ
በጥሞና እያስረዱ መስመር እንዲገቡ ቅንነታቸውና መቆርቆራቸው ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዳይቀየር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
https://andadirgen.blogspot.com

እንደዚሁም አብዛኛው እንቅስቃሴያቸው ስሜት የተቀላቀለበት ስለሆነ ቀስ በቀስ ጉዳት እንዳያደርስ ቤተክርስትያን ብርቱ ጥንቃቄ
ማድረግ ይጠበቅባታል ፡፡ አንዳንድ ተምረው ምግባረ ብልሹ የሆኑ ግለሰቦች ተቀላቅለው መስመር እንዳያስቷቸው ፤ ቤተክርስትያኗ
ባላት መዋቅር ውስጥ ገብተው እንዲማሩ እና እንዲያገለግሉ በለዘበ ቋንቋ እስከሚገባቸው ድረስ ማስረዳት ይኖርባታል፡፡
https://andadirgen.blogspot.com

ያላቸው ጥልቅ ስሜትና ተቆርቋሩነት ለቤተክርስትያን ስርአት አስተምህሮ ካላቸው እንግድነት ጋር በድምር ተጠቅመው
የቤተክርስትያኒቱን ጉዞ ለማደናቀፍ እንቅልፍ አልባ የሆኑ ቡድኖች ወደ አልሆነ አቅጣጫ እንዳይመራቸው መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
የወቅቱ ስልታቸው እቅዳቸው ይህው መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉና፡፡ https://andadirgen.blogspot.com

4. የንግድና የኑፋቄ ስራን ለመስራት የተቋቋሙ ማኅበራት

በዚህ መስመር ያሉ ማኅበራት የሚያንጹና የሚያስተምሩ ሳይሆኑ ስሜት የሚነኩ የተለያዩ ስራዎችን በመስራትና ንግዱ በዚህ መስመር
ያዋጣል ብለው ሲያምኑ የቤተክርስትያኒቱን ሃላፊዎች ሳይቀር ስድብ በመሳደብና በማዋረድ ወደ ሕዝብ የሚገቡ ፤ አላዋጣ ሲላቸው
ደግሞ እያወቁ ያዋጣናል ብለው የገቡበትን መስመር ጥለው ያለ ጥቂት ሀፍረት እንደ እባባ አቅጣጫ ቀይረው የሚጠመዘዙ ናቸው፡፡
https://andadirgen.blogspot.com

በኑፋቄ ተልእኮታቸውና ስሜት የሚነኩና ልቅ የሆኑ ትምህርቶቻቸውና መዝሙሮቻቸው ምዕመናን ለቤተክርስያኗ ስርአት የነበራቸው
ጥብቀት እንዲላላ ፤ ተቆርቆሪነታቸውም ደረጃ በደረጃ እየተሸረሸረ እንዲሄድ የሚሰሩ ተቋማት ናቸው ፡፡ በትኩረት ከተመለከትነው
የዘወትር ስራቸው ምእመናን ቤተክርስትያኒቷን እንዲከተሉ ፤ ቅዱሳንን እንዲወዱ ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር እንዲኖራቸው ፤
እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና ለጽድቅ የሚያበቃ ስራ እንዲሰሩ ሳይሆን የእነሱ ደጋፊዎችና የንግድ አጋሮቻቸው እንዲሆኑ ማድረግ
ተቀዳሚ አላማቸው ነው ፡፡ አንድ ጊዜ አውደምህረት ላይ አንዱ አሁን ከአውደ ምህረት የታገደ ሰው ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ ህዝቡን
እስኪ አንድ ጊዜ እጃችሁን ወደ ላይ አለ ፤ ምዕመኑም እጁን ወደ ላይ በማውጣት ተባበረው ፤ ከዚያ ቃል ግቡልኝ ካለ በኋላ
‹‹በማርያም ይህን ካሴት አንድ አንድ ግዙኝ›› ብሎ አረፈው …ይህ ሰው መጀመሪያም የመጣው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ
ሳይሆን ካሴት ለመሸጥ ነው፡፡ https://andadirgen.blogspot.com

እነዚህ ማኅበራት ምዕመናን ወደ ቤተክርስትያን የእግዚአብሔር ጉባኤ ሳይሆን የእገሌ ጉባኤ አለ ብለው እንዲመጡ በማድረገስ
ስራዎችን በሰፊው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለእነዚህ አይነት ቡድኖች ማኅበራት ቤተክርስትያን ልዩ አይን ሊኖራት ይገባል፡፡ ሲመች የሚሰሩ
ሳይመች ምድር ቀደው የሚገቡ ቢሆኑም ቤተክርስትን ያላት ህጋዊ መብት ተጠቅማ ቢያንስ ይፋዊ እንቅስቃሴያቸውን መግታት
ይኖርባታል፡፡

የስብከተወንጌል ሰራተኞችና ሰ/ት/ቤቶች ምዕመኑ እገሌን ብሎ ሳይሆን እግዚአብሔርን ብሎ ወደ ቤተክርስትያን እንዲመጣ ተግተው
መስራት ይኖርባቸዋል፡፡‹‹ሀጥያተኛ በሃጥያቱ ይጠፋል ደሙን ግን ካንተ እሻለሁ›› ያለ አምላክ እግዚአብሔር እንድታገለግሉ
በሰጣቸው እድል መጠን ይጠይቃችዋል፡፡ በየትኛውም ደረጃ ላይ የምታገለግሉ የቤተክርስትያኒቷ መሪዎች በሚያልፍ ዘመናችሁ
የማያልፍ መከራ አስቀምጣችሁባት እንዳትሄዱ ልትጠነቀቁ ያስፈልጋል፡፡ https://andadirgen.blogspot.com

5. የስነ ምግባር ያለባቸው ግለሰቦች የመሰረቷቸው ማኅበራት

በመጨረሻ ደረጃ የምናያቸው ማኅራት በተለያዩ ስነ ምግባር ችግሮች ከሰ/ት/ቤት ወይም በድምሩ ከቤተክርሰትያን አገልግሎት የታገዱና
ለቤተክርስትያኗ አስተዳር ከላይ እስከ ታች ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ግለሰቦች የሚያቋቁማቸው ማኅበራት ናቸው፡፡

እነዚህ ማኅበራት በቁጥር እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ስራቸውም በተጨባጭ ይሁን በተፈጠረ ምክንያት ምዕመናን የቤተክርስትያን አስተዳደር
በጥቅሉ እንዲጠሉ ማድረግና ቤተክርስትያን ውስጥ ቢሆኑ ልናገኝ እንችል ነበር ብለው የሚያስቡትን ማኛውንም ጥቅማ ጥቅም
የማስጠበቅ ዓላማን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ግለሰቦች ከቤተክርስትያን አገልግሎት የታገዱት በፈጠሩት የስነ ምግባር ችግር
አማካኝነት መሆኑን ማሰብ አይፈልጉም፡፡(እነዚህ በሌላ ጊዜ ሰፋ ባለ ዘገባ ልመለስባቸው ፤ ለዛሬ ይብቃ )
https://andadirgen.blogspot.com

እኛ ምዕመናን ስለ ማኅበራት ያለንን አመለካከት አሁን እናስተካክል ፤ እኛው ተሰናክለን ሌላውን አናሰናክል ፤ ሳናውቅ ለቤተክርስትያን
የእግር እሳት አንሁንባት ፤ ይህን የማኅበራት ችግር አሁን መፍታት ካልቻልን ነገ ከዚህ የባሰ ነገር ስለሚፈጠር መጀመሪያ ራሳችን
የቆምንበትንና ያለንበትን ማኅበር እንመርምር ፤ እንደ በግ ከመነዳት ራሳችንን እንጠብቅ ፤ ለቤተክርስትያን እሾህ የሆናትን ከመቃወም
ወደ ኋላ አንልም ፤ ለቤተክርስትያን በማይጠቅማት መንገድ የቆመን አይተን የምናልፍበት አይን የለንም ፤ ሰምተንም ከናንተ
የምንደብቀው ሚስጥር የለም ፤ የምንፈራው እውነትም የለም ፤ https://andadirgen.blogspot.com

የመንፈሳዊ ማኀበራት ከሚጠቀሱት ጥቅሞች

ማኀበራት በታላቁ በቅዱስ መጽሐፋችን ሕዝቦችን፤ ምዕመናንን ቤተሰብን በአንድነት በብዙ ቦታ አብረው መኖር እንዳለባቸው
ያስረዳል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ "ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው" መዝ 68፡9 ይለናል፡፡
በዘመናችን የማኅበራት መሰባሰብ አብዛኛው በጥናቱ የተካተተ ችግሮቻቸው ቢሆንም በስፋት ለመልካም ነገር የተሰበሰበና ማኅበር
የመሠረቱ መልካም ምግባርና እውቀት ስለሃይማኖታቸው የሚቆረቆሩ ማኅበራት አሉ፡፡ እነዚህ ማኅበራት ለአገር፣ ለሕዝብ፣
ለቤተክርስቲያን፣ የቆሙና ትልቅ ሚና ለዚህች እውነተኛይቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን ትውፊቷን
የሚጠብቁና ለሚመጣው ትውልድ ጭምር የሚሠሩ ብዛት ያላቸው ማኀበራት አሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ማኀበራት
መሰባሰባቸው ለአንድ ዓላማ ብቻ አይደለም፡፡ ይህም ማለት አጠቃላይ ማኀበርተኛ የራሱ የሆነ ድርሻና ኃላፊነት አለበት፡፡ ይህም
ለምሳሌ ቤተክርስቲያን ችግር ቢደርስባት ከውጪም ሆነ ከውስጥ የሚነሱ ጠላቶችን እንደየአንዳንችን የቤተክርስቲያን ምዕመናንነት
የራሳቸውን ድርሻ ይወጣሉ፡፡ ማኅበራቱ እጅግ ብዙ ሚና ስላላቸው ነገር ግን እኔ እንዳጠናኋቸው ዋና ዋና የሚባሉትን ጥቅሞቻቸውን
በዝርዝር እናያቸዋለን፡፡ (መንግሥቱ ጌታቸው 2004)

1. ቤተክርስቲያንን ስለማነጽና ስለመርዳት


በማድረግ ማኀበራት እጅጉን ድርሻቸው የሚሆነው ቤ/ክን በሌለበት ቦታዎች ማነጽ ቅዱስ ዳዊት "የቤትህ ቅናት በላኝ" አይደል ያለው
እነዚህ ማኅበራትም እጅጉን ድርሻቸው በዘመናችን በአባላት መዋጮ ለማኅበሩ ገቢ በማሰባሰብ የመጀመሪያ ድርሻቸው የሚሆነው
ቤተክርስቲያን በሌለባቸው ቦታዎች ሕዝቡን ወይም ምዕመኑን አምልኮተ እግዚአብሔር እንዲያመልክ ማድረግ ነው፡፡ ባላቸው መጠን
ቤተክርስቲያንን ያንጻሉ፡፡ ሌላው በተወሰኑ ማኀበራት ላይ የተከታተልኩትና ያጠናሁት ደግሞ የተ ዘጉ ቤተ ክርስቲያኖችን የሚያስ
ፈልገውን ጥገ ናና እድሳት የተዘጉት በማስከፈት አገልግሎት እንዲሰጥበት ማድረግ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን እንዲመለክ ማድረግ
የዘወትር ሥራቸው ነው፡፡ ትሐ በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለመ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን" ሐጌ 1፡4 ይህ
እግዚአብሔር በነቢዩ ላይ አድሮ ያስተማራቸው ማኀበራት በዚህች ምድር ላይ የተቻላቸውን ሲወጡ ለዚህች ቤተክርስቲያን
የተቻላቸውንና አቅማቸው የፈቀደውን እንደሚያደርጉ እያየናቸው ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በገጠሪቱ፡ ቤተክርስቲያን ላይ ስለሚያደርጉት
በጎ ሥራቸው ደግሞ በጥቂቱ እንይ፡፡ ይህንን በአገልጋይ እጥረት አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለካህናት፣ ለዲያቆናት፣ በወር በወር ደመወዝ
በመክፈል አገልግሎት እንዲከናወን እግዚአብሔር በቦታው እንዲመስገንና ምዕመነና አገልጋዩ ወደተለያዩ ቦታ እንዳይዘዋወሩ
ከሚሠሯቸው ሥራዎች አንዱ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቁሳቁሶችን በመላክ ለምሳሌ አገልጋይ ኖሮ ለአገልግሎት ማከናወኛ
የሚቸገሩባቸው የገጠሪቷን ቤተክርስቲያን፣ በጧፍ፣ በእጣን፣ በዘቢብ፣ በካህናት በዲያቆናት ልብሶች፣ በምሥጢር እቃዎች፣ በመግዛት
ይልኩላቸዋል፡፡ ማኀበራቱ በቤተክርስቲያን ላይ እጅጉን ይሠራሉ፡፡ ይቺን ቤተክርስቲያን በማንኛውም በኩል ችግር እንዳይነካት
የእያንዳንቸው የየዕለት ሥራቸው ይሆናል፡፡(መንግሥቱ ጌታቸው 2004)

2. የተቸገሩ ሰዎችን ስለመርዳት

በኢ/ኦ/ተዋሕዶ እምነት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ላለ ባስተማራቸው መሠረት ሁለት ልብስ ያላችሁ አንድ
ለሌለው ስጡ ብሎ ባስተማረው ማኀበራት ውስጥ ሲፈጸም እናያለን፡፡ እያየንም ነው፡፡ ይህም በመዝሙር 140፡1 "ለችግረኛ ለምስኪን
የሚያስብ ምስጉን ነው" ይላል፡፡ ማኀበራትም ችግረኞችን ወይም ነዳያንን በተለያየ ቦታ፣ወቅት፣ ሲረዷቸው እያየን ነው፡፡ እነዚህ ነዳያን
በቦታቸው በመሰብሰብ፣ ለምሳሌ ጾምን በማስያዝ፣ የቤት ኪራይ በመክፈል፣ ልጆቻቸውን ሲፈታም በማስፈታት፣ ልብሶችን በማልበስ፣
በማስተማር፣ በሽተኛ የሆነት በማሳከም፣ አጋዥ ረዳት የሌላቸውን በመርዳት፣ በበዓላት ወቅት በመሰብሰብና እግዚአብሔር በሚወደው
መልኩ አብረዋቸው በዓሉን በማሳለፍ እያንዳንዱ ማኀበርተኛ በነፍስ ወከፍ አንድ የችግረኛ ልጆችን በየቤታቸው በመውሰድ ለማሳደግ፣
በማስተማር፣ በማልበስ፣ ከልጆቻቸው እኩል በማኖር የሚኖሩ ማኀበራት በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ወቅት የተዋወቅኳቸውና የጎበኘኋቸው
ማኀበራት እንዳሉ አይቻለሁ፡፡ ሌላው ከሥጋ በዘለለ ለነፍሳቸው እንዲኖሩ በመንፈስ ትምህርት በማስተማር በምግባርና በትሩፋት
እንዲኖሩ አምላካቸውን እንዲያመሰግነ ራሳቸውን እንዲያተርፉ እያደረጓቸው ነው፡፡ ከዚህም አልፎ በአንድ ማኅበር በተዘጋጀ ማኀበር
ላይ ተጠርቼ ያየሁት በጣም ያስደሰተኝን በማኅበራቱ ጉዞ በማዘጋጀት በመዋጮ ከተለያዩ ሰዎች እርዳታ በመሰብሰብ ነዳያንን ወደ 8
የሚሆኑ በጎዳና የሚኖሩ ሲሆን ቤት ተከራይተው ትምህርት በማስተማር ከነዳያኑ በመጣ ፍቃድ ወደተከበረው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር
ደሙ እንዲበቁ አድርገዋቸዋል፡፡ ከማኀበራቱ ያየሁት ትልቅ ሥራ ሌሎች ማኀበራትን ይህን በጎ ሥራ እንደሚሠሩ ሰምቻለሁ፡፡ እነዚህ
ማኀበራት መልካም የሚባሉ ሥራቸው በየዓመቱ እንደሚቀጥሉ የማኀበሩ ተጠሪ ባነጋገርኩት ወቅት ጠቅሶልኛል፡፡ 63 ማኅበራት እርስ
በእርስ የመረዳዳት(መንግሥቱ ጌታቸው 2004)

3. የማኀበር ጸሎት በማድረግ


ለቤተክርስቲያናችን ትምህርት መሠረት የማኀበር ጸሎት እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህም በማኀበር ጸሎት ወቅት እግዚአብሔር አምላክ
በመካከላችን ስላለ አንድ ንጹህ ሰው ሲል የራሳችንን ጸሎት ይቀበለናል የሚል እምነት አለን እናምናለንም፡፡ ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ
ለአንድ ሰው ትልቁ መሠረት እንደሆነ ያሳውቀናል፡፡ ይህም ምንድን ነው አምላካችንን፣ ፈጣሪያችንን፤ የምናናግርበት፣ የምንፈልገውን
የምንመኘው፤ የምንጠይቅበት ትልቁ መሣሪያ ጸሎት ሲሆን በማኀበር ደግሞ እጅጉን ብዙ ድርሻዎች አሉት፡፡ የሐዋ ሥራ 1፡14
ሐዋርያት በመሰብሰብ በመካከላቸው ወላዲተ አምላክን ድንግል እመቤታችንን በማድረግ ይጸልዩ ነበር፡፡ ይለናል ስለዚህ ማኀበራት
አብዛኛውን ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ወቅቶች በተወሰነ ጊዜ ስለቤተክርስቲያን ይጸልያሉ። ማኅበራቱ የሚጸልዩት
ስለአንድነታቸው፣ ስለሃገራችን፣ ስለህዝባቸው፣ ስለችግረኞች፣ ስለበሽተኞች፣ ስለየቤተሰቦቻቸው፣ ሁሌም ላይሰለቹ ፈጣሪያቸውን
በህብረት ሆነው ይለምናሉ፡፡ በጸሎት አምላካቸውን እንደሚረዳቸው ስለሚያውቁ ስለሚሠሩትም ሥራ እግዚአብሔር አምላክ
እንዲረዳቸው ተግተው ጸሎታቸውን ይጸልያሉ፡፡ ማኅበራቱ በተከታተሉባቸው ወቅት አብዛኞቹ ማኀበርተኛ ለጸሎት : እጅጉን :
ለሚሰጧቸው ጊዜዎች ዋነኛው ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ሥራ ከመሥራቱ በፊት፣ ለመሥራት ሲያስብ፥ እግዚአብሔር : አምላክን
ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ እንዳለበት : ስለሚያምነ ማኅበራቱን ይህን ሥራ ሲሰሩ እናያለን፤፤(መንግሥቱ ጌታቸው
2004)

4. ማኅበርተኞችን ለንስሐ ስለማብቃት

የሰው ልጅ በምድር ላይ የሠራቸውን ሥራዎች በሰማይ ቤት እንደሚያከማች ሁሉ በዚህ መልካም ሥራ ወደሚሆነው ወደዘላለማዊ
ሰማያዊት ቤቱ እንዲገባ የሚያደርገው ንስሐ በመግባት ማኅበራቱ አብዛኛው የንስሐ አባት የሌሌው የንስሐ አባት በማስያዝ ንስሐ
ያልገባውን ንስሐ እንዲገባ ማድረግ ያደርጓቸዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ራሳቸው ንስሐ በመግባት ነው፡፡ በመጨረሻም ማኅበራት
አባላቱን የመጨረሻ ግባቸው በዚህች ምድር የሠሯቸውን በጎ ሥራዎች ከሰማይ አባታቸው በመቀበል ቅዱስ ጳውሎስ
"ወደእግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መጋደል እንገባለን እንዳለ ኤፌ 6፡12 ማኅበራቱ በዚህች ምድር የሠሯቸውን ትሩፋቶች
ለመቀበል በመልካም የተመሠረቱ ማኀበራትን በምድር ላይ የቱንም ዓይነት በጎ ሥራ ቢሠሩ አምላካቸው እንደተናገረው ሥጋዬና ደሜን
ያልበላ የዘለዓለም ሕይወት አይወርስም እንዳለው ማኀበራቱ ለሥራቸው በነሯቸው በሕይወታቸው ሲሉ ይሆን በማሰብ : አባላቱ
ቤተሰቦቻቸውን ከገቡ መውጣት፣ ካገኙ ማጣት፤ የሌለባትን መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ የበቁና የተዘጋጁ ይሆኑ ዘንድ ማኀበራት
የሚ ታዩአቸው መልካም ስዎች ይህን ቅዱ ስ ሥ ጋውን ክቡር ደሙን እንዲቀበሉ ማድረግ ነው። ማኀበራት በጣም ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች
ቢኖሯቸውም ግን እንደነዚህ ያሉ ጥቅሞች የሚታዩባቸው : ማኀበራት በስፋት እንዲኖሩ - ማድረግ የሚለው ከላይ ችግሮቻቸውን
ባየንበት ነጥቦች ራሳቸውን መፈተሽ አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እውነተኞቹን ማኀበራት ይጠብቅልን፡፡(መንግሥቱ ጌታቸው
2004)

5. ሌሎች የማኅበራት ጥቅሞች

የአንድማኅበርን ስራዎች በመዘርዘር ሌሎች ማኅበራትን ጥቅም ማየት እንድንችል


 ቃለ ወንጌል በማስፋፋት ረገድ በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶችን በማስተማር ቤተክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና በሥነ ምግባር
እንዲታነጹ አድርስል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ብዛት ያላቸው መዓት ለሥጋ ወደሙ የበቁ ሲሆን፣ ከያላነሱ ደግሞ በሥርዓተ ተክሊል
በቅዱስ ቁርባን ጋብቻቸውን ፈጽመዋል፡፡ ❖ በተለያዩ ጊዜያት ከአዲስ አበባ መምህራን ይዞ በመሄድ በሩን ክፍል የያ ሁለት ወር
የክረምት ኮርስ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔያትን በማዘጋጀት ኅብረተሰቡ በተኩላ እንዳይነጠቅ ጉልህ
 እንቅስቃሴ አድርገዋል፡
 ለገጠር አብያተክርስቲያናት : ካህናት : በመቅጠር የአካባቢው ምእመናን እንዲገለግል አድርገዋል፡፡
 በዕለተ ሰንበትና በታላላቅ ጉባዔያት ምዕመናን የቤተከርስ ቲያን ሥርዓት እንዲጠብቁ የማስተባበር፤ የማስተናገድ ሥራአከናውነዋል
!
 በሠርግ፣ በልቅሶ፤ በምረቃ ጊዜ በስብከት፣ በመዝሙር ትምህርት አስተላልፈዋል።
 በየአካባቢያቸው ሕፃናትን በማስተማር እስከ ዲቁና የደረሱ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በልዩ ልዩ በዓላት ነዲንን ምግበ ሥጋ ምግበ
ነፍስም መግበዋል !
 በየሳምንቱ እሑድ ጠዋት በቅጽረ ግቢ ውስጥ የሚገኙትኾ ከግቢው ውጪ ያሉትን ነዲን የቁርስ መርሐ ግብር በማኅ ጋጀት
መግበዋል! በመመገብም ላይ ይገኛሉ፡
 የገቢ ውስጥ የሚገኙ ነዳያን የውኃ እጥረት እንዳይኖርባቸው ሮቶ ውኃ ማጠራቀሚያ እንዲገባላቸው አድርገዋል፤
 በተለያዩ ጊዜያት ኢልባሳት እና ፍራሽ በመግባት ለነዲን አድለዋል፡፡
 የተቸገሩና የአይምሮ ህመም ያለባቸውን : ልብሳቸውንና ገላቸውን : በማጠብ ንጽሕናቸውን
 ጠብቀዋል በመጠበቅ ላይም ይገኛሉ።
 ማኀበራትን በማሰባሰብ አንድ ሰንበት ት/ቤት ድንግል ማርያም ምልጃ ይህንን ያህል ደረጃ መድረስ ከቻለሁ ሁሉም ማኅበራት
ቤት ቢተባበር ምን ሊሠራ እንደሚችል መገመት አያቅትምና በመተባበር እንስራ
በጥቅምት 2015 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት አስተዳደር ደንብ ቁጥር፫/፳፻፲፭ ዳሰሳ

የደንቡ አሰፈላጊነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ማኅበራት እየተበራከቱ የመጡበት ወቅት በመሆኑ ማኅበራት ለቤተክርስቲያን
የሚያበረክቱት በጎ አስተዋፅኦ ሊኖር ስለሚገባ ¬ በቤተ ክርስቲያን አካላት ክትትል እየተደረገባቸው የሚቋቋሙበት ዓላማ መሠረት
አድርጎ መደበኛ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥራው በማኅበራቱ እየተደገፈ በአግባቡ መወጣት እንዲችል፣ በቤተ ክርስቲያን ስም እና
መዋቅር ሥር የሚቋቋሙ ማኅበራት የሚያቅፏቸው አባላት፣ የሚሰበስቡት ሀብትና ንብረት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አካላት
ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግበት የሚያስችልን ሥርዓት የሚዘረጋ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፣ ማኅበራት ለቤተክርስቲያን
አገልግሎት፣የበጎ አድራጎትና የልማት ሥራ ያላቸው አስተዋፅኦ እንዲጎለብት፣ አመሠራረታቸው፣ አሠራራቸውና አገልግሎታቸው
በታወቀ የቤተ ክርስቲያን ሕግ እንዲመራ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ የማኅበራት አስተዳደር ሥራን ለሚያስፈጽሙ የቤተ ክርስቲያን
አካላት ግልጽ ተግባርና ሐላፊነት የሚሰጥ እና ማኅበራትን የሚመዘግቡበት፣ የሚቆጣጠሩበትና የማስተካከያ ውሳኔ የሚሰጡበት ሥነ
የሚደነግግ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፣ በቤተ ክርስቲያን ሥር የሚቋቋሙ ማኅበራት ለተመሠረቱበት ዓላማ ብቻ እንዲሠሩ
የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ደንቡ ሊወጣ ችላል፡፡(የማኅበራት አሰተዳደር ደንብ/2015)

ማኅበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ ተግባርና ሐላፊነት

የማኅበራት ምዝገባ፣ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ የሚከተሉት ተግባርና ሐላፊነት ይኖረዋል፡-

፩. በዚህ ደንብ መሠረት ማኅበራትን መመዝገብ ፣ መደገፍ፣ ማስተባበር፣ ማድረግ፣

፪. ማኅበራት ሥራቸውን በሕግ አግባብ ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር

፫. የማኅበራትን ዓመታዊ የሥራና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት መመርመር፤
፬. የማኅበራቱ ማናቸውም ገንዘብ እና ንብረት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሞዴላ ሞዴል እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ ደረሰኞችንም በአግባቡ
ያሰራጫል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣

፭. ማኅበራት ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የውስጥ አስተዳደር እና የራስ አስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን
ድጋፍ መስጠትና ተፈጻሚነቱን መከታተል፤

፮. ከሚመለከታቸው የሀገረ ስብከት የሥራ ክፍሎች ጋር በመተባበር በቤተ ክርስቲያን ሥር የሚንቀሳቀሱ ማኅበራትን ቁጥር፣

ስብከትና የተሰማሩባቸውን አህጉረ የአገልግሎት ዘርፎች፣ የተጠቃሚዎቻቸውን እና የአባሎቻቸውን ብዛት እና መሰል መረጃዎች
የሚይዝ የመረጃ ማእከል ማቋቋም፤መረጃዎችንም በመተንተን ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት፤

፯. ማኅበራትን በሚመለከት ከአህጉረ ስብከት የሥራ ክፍሎች ጋር እንዲሁም ከማኅበራቱ ጋር ቋሚ የምክክር መድረኮችን ማዘጋጀት፤

፰. ማኅበራት ቤተ ክርስቲያን ለምታወጣቸው ሕጎችና መመሪያዎች ተገዢ እንዲሆኑ መሥራት፣

፱. ማኅበራትየሚያከናውኑት የልማት ሥራና የሚፈጽሙት አገልግሎት ቤተ ክርስቲያን ከምታወጣቸው የልማትና መንፈሳዊ


የአገልግሎት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ መሥራት፤

፲. የማኅበራትን መተዳደሪያ ደንቦችና ማሻሻያዎቻቸውን ማረጋገጥና መመዝገብ፤

፲፩. በዚሕ ደንብ መሠረት የምዝገባና የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ክፍያ፤የፈቃድ እድሳት ክፍያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን
ከማኅበራት በበጀት እና ሒሳብ መምሪያ በኩል እንዲሰበሰብ ማድረግ፤ ፲፪. ማኅበራት በሕግ አግባብ ፈቃዳቸው ሲሠረዝ ወይም
መፍረሳቸው ሲረጋገጥ በሒሳብ አጣሪነት የሚያገለግሉ ባለሙያዎችን መመደብ እና ሥራቸውን በአግባባቡ ማከናወናቸውን
መቆጣጠር፤ ፲፫. ማኅበራት ከዚህ ሕግ ድንጋጌ ውጭ ሲሆኑ በዚህ ሕግ መሠረት ማገድ እና እንደአስፈላጊነቱ ጥፋት መፈጸማቸው
ያለማስተባበያ በበቂ ሁኔታ እና ማስረጃ ሲረጋገጥ ፈቃዳቸውን መሠረዝ፤

፲፬. የማኅበራት የምዝገባ፤የፈቃድ አሰጣጥ የፈቃድ እድሳት፣ የሰነድ ማረጋገጥ፤ የአገልግሎት ክፍያ እና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ
በማውጣት በሚመለከተው አካል እንዲጸድቅ ማድረግ፤

፲፩. ማንኛውም ማኅበር አባላቱ ትምህርተ ሃማኖትን የተማሩ ወይም ለመማር ዝግጁ የሆኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡

ማኅበራት ለምን በቅዱሳን ስም ይጠራሉ/ይሰበሰባሉ

ቅዱስ ማለት በቁም ሲተረጐም ፦ የተቀደሰ ፥ ክቡር ፥ ምስጉን ፥ ልዩ ፥ ምርጥ ፥ ንጹሕ ፥ ጽሩይ ማለት ነው። ለብዙ ሲሆን ቅዱሳን
ይባላል። በአጠቃላይ « ነገረ ቅዱሳን » የሚለው ሲተረጐም፦ የቅዱሳንን ነገር መናገር ፥ መስበክ ፥ ማስተማር ፥ ማብሠር ፥ መጻፍ
ይሆናል።https://nohamin.blogspot.com/2016/04/part-1-14.html

፪፡- ቅዱስ ማነው?ከሁሉ በላይ ቅዱስ የሚባለው እግዚአብሔር ነው። ጥንትም ፥ ዛሬም ፥ ለዘላለምም (ቅድመ ዓለም ፥ ማዕከለ ዓለም
፥ ድኅረ ዓለም) ቅዱስ ነው። በቅድስናም የሚመስለው ማለትም የሚተካከለው የለም፡፡ ነቢዩ አሳይያስ « እንግዲህ እተካከለው ዘንድ
በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ ፤ » በማለት የነገረን ይኽንን ነው ። ኢሳ ፵ ፥ ፳፭
፡፡https://nohamin.blogspot.com/2016/04/part-1-14.html
ስለምን ማኀበራት በቅዱሳን ስም ተሰየሙ ለሚለው ጥያቄ ለመመለስ የነቢዩ የኢሳያስን ቃል መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡“እግዚአብሔር
ሰንበቴን ለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኝንም ነገር ለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላል በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ
ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ የሚበልጥ (መታሰቢያ ስምን) ለዘለዓለም እሰጣቸዋለሁ” ይላል ኢሳ 56÷4::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት በማድረግ በቅዱሳን ስም አብያተ
ክርስትያናትን ፣ታቦታት፣ እና ማኅበራትን አንደ መታሰቢያቸውን ታደርጋለች፡፡ ነገር ግን በማናቸውም ቅዱሳን ስም አምልኮ
አትፈጽምም!!! ለምሳሌ በጻድቁ አቡነ ተክለ- ሃይማኖት ስም ማኅበር ቢቃቃም ተክለ-ሃይማኖትን ለማምለክ አይደለም እግዚአብሔርን
እንጂ !!! ስለዚህ የትም ቤተክርስቲያን ብንሄድ የማኅበር ፀሎት ብናደርግ የምናመልከው እግዚአብሐየርን እንጂ መታሰቢያ
የተደረገለትን ቅዱስ አይደለም፡፡

መታሰቢያቸውንም የምታደርገው ቅዱሳን የተወለዱበትን ፣ ያረፉበትን እና ተአምራት ያደረጉበትን ቀናት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
በቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ እንተማመናለን!!! ጸሎታቸው ድውይን ይፈውሳል!!! ቃልኪዳናቸው መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳሷል!!!
ቅዱሳንን እንድናከብርና እንድናስባቸው ለረዳን ለቅዱሳን አምላክ ክብርና ምስጋና ይሁን አሜን፡፡

በዚህ ዘመን አንድነታችንን መጠበቅ ከመንፈሳዊ ፋይዳው በተጨማሪ ለህልውናችንም በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ከበፊቱ ይልቅ አጥብቀን
ልንይዘው ይገባል። eotcmk.org/gibi

ምዕራፍ ሶስት

የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴ (Research Design and Methodology)

፫.፩ የጥናትና ምርምሩ ንድፈ ሃሳብ (Research Design)


ይህ ጥናትና ምርምር የሚከተለው የጥናት ንድፈ ሃሳብ (Research design) አይነት ገላጭ የጥናትና ምርምር ንድፈ ሃሳብ
(Descriptive research design) የሚባለውን ሲሆን ይህም የተመረጠበት ምክንያት ንድፈ ሃሳቡ የአንድን ሁኔታ ትክክለኛ ገጽታ
ለማወቅ ወይም በትክክል ለመግለጽ ሲባል መረጃዎችን ከርዕቱ ምንጭ (primary source) እና ኢ-ርዕቱ ምንጭ (secondary
source) በማጠናቀር ትንተና በማድረግ የሚያጠና በመሆኑ ነው፡፡

፫.፪ በጥናትና ምርምሩ ሽፋን ያገኘው ቦታ (Specific area of the study)


በዚህ የጥናትና ምርምር ሥራ ውስጥ መረጃዎች ከደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ውስጥና ዉጪ ካሉ ማኅበራት
የሚሰበሰብ የጽሁፍ መጠይቅ ሲሆን በቤተክርስቲያና ስር ያልሆኑ መንፈሳዊ ማኅበራት ማለትም በማኅበራት አንድነት ማደራጃና
መከታተል ውሰጥ ከማይሳተፉ ማኅበራት እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት አደረጃጀቶች ውጪ አንድ የማኅበራት አንድነት ሃለፊን በቃለ
መጠይቅ የሚሳትፍ ነው፡፡
፫.፫ የጥናቱ የናሙና መጠን (Sample size)
ናሙና ከአጠቃላይ የህዝብ ስብጥር (ስብስብ) (Target Population) ውስጥ ስብስቡን ለመወከል በሚመች መልክ ለጥናታዊ
ምርምር የሚወሰድ የመረጃ ማግኛ ክፍል ነው፡፡ጥናቱ የሚነካቸው ማኀበራት ከሁኔታዎች ፣ ከጊዜ፣ ከገንዘብና ከሰው ኃይል አንጻር
አንድ ላይ ለማጥናት ሰለማይቻል ግምት የማይሰጥ (Non-Probability Sampling) ነው፡፡

በዚህ መሰረት 30 በ ቤተክርስቲያና ስር ያሉ መንፈሳዊ ማኅበራት ማለትም በማኅበራት አንድነት ማደራጃና መከታተል ውሰጥ
ከሚሳተፉ ማኅበራት (አብዛኛው ማለትም ከ 30 ው ማኅበራት 27 ቱ ማኅበር የገጠር አብያተ ቤተክርስትያናትን መሰረት አድርገው
የተቃቃሙ) 10 እንዲሁም 10 የሚሆኑት ደግሞ ከማይሳተፉ( ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ) አካላትን በማሳተፍ ጥናቱን
ከአጠቃላይ ስብጥር ማለትም 20 ከሚሆኑ መኀበራት ተገቢውን መረጃ ማግኘት እንችላለን ብለን በአጥኚዎቹ ዘንድ ተመራጭ እና
ምክንያታዊ ሆኖ አግባብነት እንዳለው ታስባል፡፡

፫.፬ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ (Sampling Techniques)


ጥናቱ የሚጠቀመው የናሙና አወሳሰድ ዘዴን ስንመለከት ግምት በማይሰጥ የናሙና አወሳሰድ (non probability sampling)
ከሚባሉት ውስጥ የታለመ ናሙና የሚባለውን (Purposive sampling) ዘዴን የሚጠቀም ነው፡፡ ምክንያቱም ጥናቱ ያቅፋቸዋል
ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ወይም ሁኔታዎች መካከል በይበልጥ ለተመረጠው ርዕስ ይስማማሉ ብሎ የሚገምታቸውን ለይቶ
በመውሰድ እና ከቤተክርስትያን ውጪ ያሉትን ማህበራትም ቁጥራቸው የማይታወቅና በአካባቢው ያሉትን ትልልቅ ማኅበራትን
የሚሳትፍ የሚጠቀምበት የናሙና አመራረጥ ስልት በመሆኑ በአጥኚዎቹ የተመረጠ ነው፡፡

፫.፭ ጥናቱ የተጠቀመባቸው የመረጃ አይነቶች (Types of data


ጥናቱ በመረጃ ምንጭነት የሚጠቀመው ሁለቱንም የመረጃ ምንጮችን ሲሆን እነርሱም ርቱዕ ምንጭ / Primary source/ ኢርቱዕ
ምንጭ /Secondary source/ በመባል የሚታወቁትን ነው፡፡ ርቱዕ የመረጃ ምንጭ / primary source/ ለጥናትና ምርምር ሥራ
ተፈላጊ የሆነ ጥሬ መረጃ በጽሁፍ መጠይቅ፣ በቃል መጠይቅ፣ አማካኝነት በቀጥታ የሚገኝ ነው፡፡ ኢርቱዕ የመረጃ ምንጭ
(Socondary Source) ደግሞ አንዳንድ መጽሐፍት፣ መጽሔቶችና ኢንተርኔት ሶሻል ሚዲያዎች በሎገሮች የመሳሰሉት በጽሑፍ
መልክ የሚገኙ ዶክመንቶች ከኢርቱዕ የመረጃ ምንጮች የሚመደቡበት ነው፡፡ እነዚህ ምንጮች የብዙ ምሁራንና የምርምር
ባለሙያዎችን ጥናታዊ ሪፖርቶች ፍሬ ነገር በማሰባሰብና በመጭመቅ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለጥናትና ምርምር ሥራ ከፍተኛ እገዛ
ያደርጋሉ ብሎ በማመን ነው፡፡

፫. ፮ ጥናቱ የሚጠቀመው የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ (Data Collection Method)


መረጃን ለመሰብሰብ ከምንጠቀምባቸው መንገዶች መሐከል ይህ ጥናት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ውስጥ የመጀመሪያው የጹሑፍ
መጠይቅ (Questionnaire) ሲሆን ይህም ክፍት እና ዝግ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎችን የሚጠቀም ሲሆን በሁለተኛ ደረጃም ጥናቱ
የቃል መጠይቅ (Oral Interview እንደ መረጃ አሰባሰብ ስልት የሚጠቀመዉ ነው፡፡
፫.፲የጥናቱ የመረጃ አተናተን ዘዴ (Data Analysis Method)
በዚህ ጥናት ውስጥ በጥናቱ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኙትን መረጃዎች ገላጭ (ግልጥ) በሆነ መልኩ ለማቅረብ የሚሞከርበት ከመሆኑ
በተጨማሪ መረጃዎችን ለመተንተን የምንጠቀምበት መንገድ የቃላትና የቁጥር ድቅል (Both Qualitative and Quantitative
Method) የሚባለውን ሲሆን እያንዳንዱ የተገኘውን መረጃ ለመተንተን ከተሞከረ በኋላ የመረጃዎቹ አቀራረብ ቀጥሎ የሚሰራ ወይም
የሚተገበር ይሆናል፡፡ በተጨማሪም መረጃዎችንም ለማቅረብ የሚሞከረው የተለያዩ የመረጃ አቀራረብ ዘዴዎችን በመጠቀም ሲሆን
ይህም ሰንጠረዦችን፣ አማካይ ውጤቶችን(Percentages) እንዲሁም የተለያዩ የግራፍ አይነቶችን በመጠቀም ይሆናል፡፡

፫. የጥናቱ የወረቀት መዋቅር (Organization of the study)


ይህ ጥናትና የምርምር ተግባር የሚከናወነው በአምስት ምዕራፎች ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ በውስጡ የያዛቸው ርዕሰ ጉዳዮች
የጥናትና ምርምሩ ዳራ፣ የችግሩ ምንነት፣ የጥናቱ ቁልፍ ጥያቄዎች፣ የጥናቱ ዓላማ፣ የጥናቱ ጠቀሜታ፣ የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ ታሳቢ
ክፍተቶች እንዲሁም የርዕሰ ጉዳዩ የቃላት ትርጉም ናቸው፡፡
በምዕራፍ ሁለት ደግሞ የተዛምዶ ጹሑፍ ዳሰሳ የሚካሄድበት ሲሆን ይህም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ናቸው፡፡
በምዕራፍ ሦስትም የጥናትና ምርምሩ ሥነ - ዘዴ እና አካሄድ የሚገለጽበት ሲሆን በዉስጡም የጥናቱ ግልጻዊ የቦታ ሽፋን፣ የጥናቱ
ንድፈ ሃሳብ (Research Design)፣ የጥናቱ አጠቃላይ የሕዝብ ስብጥር፣ የጥናቱ የናሙና መጠን፣ የጥናቱ የናሙና አወሳሰድ ስልት፣
ጥናቱ የሚጠቀምባቸው የመረጃ አይነቶች፣ ጥናቱ የሚጠቀመዉ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ እና የጥናቱ የመረጃ አተናተን ዘዴ የሚካተቱበት
ሲሆን
በምዕራፍ አራትም የመረጃ አተናተን እና አቀራረብ ዘዴ የሚቀርብበት ሲሆን በውስጡም ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ
እንዲሁም በጥናቱ የተገኙ አበይት ውጤቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡
በመጨረሻም የማጠቃለያ፣ የመደምደሚያ እና የመፍትሔ ሐሳቦችን በምዕራፍ አምስት የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡

ምዕራፍ አራት

የመረጃ ትንተና፣ትርጉምና አቀራረብ /Analysis, Interpretation and Presentation of Data/


የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተፅዕኖ በቤተክርስቲያን ከየት ወደየት በሚል ለምናዘጋጃው ጥናታዊ ፅሁፍ የሚረዳ 20 የጥሁፍ መጠይቅ ያዘጋጀን ሲሆን
ጥናታችን የቁጥር ትንታኔ መሠረት በጥናትና ምርምሩ ከተሳተፈት ማኅበራት በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ በማኅበራት አንድነት ውስጥ የሚሳተፉ

10 ማኅበራት 50% እና ከቤተክርስትያን ውጪ ተደራጀተው ካሉ ማኅበራት 10 ማኅበራት ማለትም 50 % መሆኑንን ጥናቱ ያመለክታል፡፡
➔ ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ በተመለከተ

ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ በተመለከተ ላስቀመጥናቸው አምስት ጥያቄዎች


ፆታ፡-ከተሳታፊዎች ማኀበራት መካከል በዚህ የፅሁፍ መጠይቅ የተሳተፉ 15 ወይም 75% ወንድ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 5 ወይም
25% ሴቶች ናቸው በብዛት በማኅበር አመራርነት ያሉት ወንድ ሲሆኑ ይህም በፀሎት ለማሰጀመር ጉባዬዎችን ለመምራት እና
ለመሳሰሉት ተግባራት ጥሩ ነው፡፡
በዚህ መጠይቅ ላይ የተሳተፉትን የማኅበራት አመራር በእድሜ ስንመለከት አብዛኛው ማለትም 12 ወይም 60% የሚሆኑት

ከለ 21-30 ኣመት ሲሆኑ 5 ወይም 25% ቱ ከ 30 እስከ 40 እድሜ ክልል ውስጥ ናቸው የተቀሩት 3 ወይም 15%
ከ 15 እስከ 20 አመት ላይ መሆናቸውን ተገንዘበናል፡፡

የትምህርት ደረጃ ሰንመለከት ከ 9 ኛ ክፍል እስከ 12 ኛ ክፍል 7 ወይም 35% ዲፕሎማ 7 ወይም 35% ሲሆኑ ቀሪዎቹ

6 ወይም 30% የዲግሪ ትምህርት ያጠናቀቁ ናቸው፡፡


ማኅበራትን እየመሩ ያሉ አመራሮች ያላቸውን መንፋሰዊ ማዕረግ ለማወቅ በጠየቅነው ጥያቄ 14 ወይም 70% ሚሆኑት

ምዕመን ሲሆኑ 5 ወይም 25% የሚሆኑት ዲያቆን ናቸው፡፡ ቀሪው 1 ዌም 5% ማኅበር የመምህርነት የመንፈሳዊ ማዕረግ
እንዳለቸው መረዳት ችለናል፡፡
ለናሙና የተመረጡ ማኅበራትነን ከሚመሩ አመራሮች በማኅበሩ ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት ለመረዳት በጠየቅነው ጥያቄ

የማኅበሩ ሰብሳቢ (ሙሴ) 7 ወይም 35%፣ የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ 5 ወይም 25% የማኅበሩ ሂሳብ ክፍል 1 ወይም 5%፣
የማኅበሩ ኅዝብ ግንኙነት 2 ወይም 10% ቀሪዎቹ 5 ወይም 25% ሌላ መንፈሳዊ ማዕረግ በሚል መለሱ ሲሆን ያም ማለት
መዘሙር ክፍልና ትምህርት ክፍል ናቸው፡፡

ተ.ቁ. መጠይቆች ምርጫ የመረጡ ከመቶ በ %


ማኅበራት
በቁጥር
፩ ጾታ? ፩.ወንዴ 15 75
፪.ሴት 5 25
፪ እዴሜ? ፩.ከ 15 - 20 3 15
፪.ከ 21 - 30 12 60
፫.ከ 30 – 40 5 25
፬. ከ 40 በላይ - -
፩.ከ 1- 8
፪.ከ 9 - 12 7 35
የትምህርት ደረጃ ፫.ዲፕሎማ 7 35
፫ ፬.ዲግሪ 6 30

፭.. ማስተርስና ከዚያ በላይ - -


፩.መምኅር 1 5
፬ መንፈሳዊ ማዕረግ
፪.ዲያቆን 5 25
፫.ቄስ - -
፬. ምዕመን 14 70
፭.ሌላ መንፈሳዊ ማዕረግ

፩.የማኅበሩ ሰብሳቢ (ሙሴ) 7 35


በማኅበሩ ውስጥ ያለዎት ኃላፊነት
፪.የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ 5 25
፭.
፫.የማኅበሩ ሂሳብ ክፍል 1 5
፬. የማኅበሩ ኅዝብ ግንኙነት 2 10
፭.ሌላ መንፈሳዊ ማዕረግ 5 25

ሰንጠርዥ ፩.፪፡ ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ

➔ የማኅበሩ ዓላማ ፤ አጀማመራቸውና በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው ተፅዕኖ በተመለከተ

፩. ማኅበራቹ የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ ወይም ሊሰራ የተነሳው (ያሰበው) ምን አገልግሎት ነው ብለን ለጠየቅነው ክፍት ጥያቄ
አብዛኛው የመለሱልን መልስ ተመሳሳይ ቢሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
 የገጠሩ አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን በመናፍቃን አሉታዊ ተፅዕኖ እና በነዋያተ ቅድሳት ምክንያት አገልግሎታቸው
እንዳያቋርጡ ማገዝ።

 ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሱ ወጣቶች እምነታቸውን እንዳይቀይሩ እንዲፀኑ

 ቤተክርስትያናትን በተለይ ገዳማትን መደገፍ

 የእመቤታችን እና የቅዱሳንን ዝክር ለመዘከር

 በተመሳሳይ እድሜ የሚገኙ ወጣቶችን ከልዩ ልዩ እድሜ ተኮር አይጋዎች ማዳን

 የንስሀ ሕይወት ለማለማመድ

 ማኅበሩ ላይ ላሉ ሰዎች ቃለ እግዚያብሔር እንዲያውቁ ማድረግ

 የተቸገሩ ነዳያንን መርዳት

 የአባቶችን አደራ ለመጠበቅ

 ወንጌልን ለማስፋፋት
 እርስ በርስ ለመደጋገፍና ለመረዳዳት

 ነዋየ ቅድሳት መግዛትና በጉልበት ድጋፍ ማድረግ

 የቅድስት ቤተክርስትያን አስተምሮ በኪነ ጥበብ ለመግለጽ

 በጥምቀት በዓል ምክንያት የተሰበሰቡ ወጣቶች ከበአሉ በኋላ እንዳይበተኑ ለማድረግ

፪. ማኅበራቹ መቼ እና በማን ተመሰረተ ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ 20 ማኅበራት የመለሱት መልስ የተለያየ ቢሆንም እንደኛ ጥናት
1983 ዓ.ም እሰከ 2014 ዓ.ም ሲሆን ከ 33 ዓመት እሰከ 2 ዓመት የቆዩ ማኅበራት በጥያቄው መሳተፋቸውን መረዳት እንችላለን፡፡
የሚሰረቱት አብዛኛው በአካባቢ ወጣቶች እና በጉደኛሞች ሲሆን በንስሐ አባት እና በሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን
የሚጀመሩ አሉ

፫. በቤተክርስቲያን ስርዓት (ዶግማ ፤ ቀኖና ፤ ትውፊት) በሚያፋልስ መልኩ ስራዎች ይከናወናሉ ? ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ በጣም
እስማማለው ያሉት 20 ሲሆኑ
በጥናታችን መሠረት በቤተክርስቲያን ስርዓት (ዶግማ ፤ ቀኖና ፤ ትውፊት) በሚያፋልስ መልኩ ስራዎች ይከናወናሉ ? ብለን ለጠየቅነው
ጥያቄ ባስቀመጥነው መሠረት ከተጠየቁት (20) ማኅበራት ውስጥ 13 ወይም 65% የሚሆኑት አልስማማም ያሉ ሲሆን 5 ወይም 25
% በከፊል እስማማለው 3 ማኅበራት ወይም 15% ደግሞ በጣም እስማማለው በሚል የመለሱ በመሆኑ ጥቂት የማይባሉ ማኅበራት
ላይ ከዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ጥሰት የሚከናውንበት መሆኑ ጥናታችን አመላካች ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ስርዓት (ዶግማ ፤ ቀኖና ፤ ትውፊት) በሚያፋልስ መልኩ

13

በጣም እስማማለው በከፊል እስማማለው አልስማማም

፬ .ቤተክርስቲያን ስም የተቋቋሙ ማኅበራት ሆነው ለቤተክርስትያን ጥቅም ከመስራት ይልቅ በማኅብራት ስም የራሳቸውን
ሀብት ጥቅም የሚያካብቱ አሉለሚለው በዚህ ጥያቄ የተሰጠው ግብረ መለስ አብዛኛውም ማለትም 8 ወይም 40 %
ማኅበራት የለም ሲሉ 4 ወይም 20% ማኅበራት በብዛት አሉ 5 ወይም 25% ቁጥራቸው አናሳም ቢሆን አሉ የሚል ምላሽ
የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቸሁ 3 ወይም 15% ማሀበራት ደግሞ መረጃው የለኝም ምላሽ የሰጡ ናቸው ናቸው፡
9
8
8

6
5
5
4
4
3
3

0
በብዛት አሉ ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም አሉ የሉም መረጃው የለኝም

➔ በመዋቅር ደረጃ ካሉ የባለድርሻ አካላት አስፈላጊው አትኩሮት እና ድጋፍ በተመለከተ

፩ .ማኅበራቹ በማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ወይም በሰንበት ት / ቤት ስር ተመዝግቧል


በለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ 10 ወይም 50% ማኅበራት አዎ ተመዘገበናል ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ወይም 50% አይ
አልተመዘገብንም ያሉ ሲሆን ምክንያታቸውን ሲሰቀምጡ
 በቂ የሆነ አደረጃጀት እና እንዲሁም ጠንካራ አመራር ስለሌለው
 ማኅበራችን የጠየቀውን ጥያቄ መለስ በማጣቱ ምክንያት ከማኅበሩ አንድነት ተወካዮች ቅሬታ ስላለው
 እንቅስቃሴው በተወሰነ መልኩ እንዳሰብነው እና እንዳለምነው መጠን አለመስራታችን
 መመዝገብ እንዳለብን መረጃው ስለሌለን
 በበቂ ሁኔታ ባለመደራጀታችን እና ማድረግ ያለብንን ነገር ባለማድረጋችን
 ሰንበት ት/ቤቱ ጋር በግልጽ መግባባት አንችልም ይህ ስንል ሰንበት ት/ቤቱ ብዙ የቁጥጥር ስርአት ያበዛል እና
ለምናስበው ስራ በፍጥነት የሚካሄዱ ነገሮች ባለመኖራቸው ስራችንን ስለሚያጏትቱት አልተመዘገብንም የሚሉ
ምክንያቶችን አሰቀምጠዋል።
100%
90%
80%
70%
60%
10
50% 10
40%
30%
20%
10%
0%
አዎ

አይ

50% 50%2

፪ .ማኅበራቹ ከባለድርሻ አካላት ( ማኅበራትን ከሚከታተል ፤ ከሚቆጣጠር እና ከሚደገፍ መዋቅራዊ ተቋማት ጋር በጋራ
ይሰራል ?

በለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ 10 ወይም 50% ማኅበራት አዎ ይሰራል ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ወይም 50% አይ አይሰራም
ያሉ ሲሆን ምክንያታቸውን ሲሰቀምጡ
 የሚደግፉት ባለድርሻ አካላት በወረቀት ላይ ( በቃል ) ብቻ ላይ ያለ ነው በተግባር ድጋፍ ማድረግ ላይ ክፍተት ይታያል

 ከሌላ ተቋማት ጋር ተግባቦት ስለሌለው

 አላሰብንበትም እስካሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረግንም

 ግንኙነት ስሌለን በጋራ መስራት አልቻልንም

 ባለድርሻ አካላት ቀርበው ስላላናገሩን እኛም ወደ እነርሱ ስላልሄድን

 ግንዛቤ ስለሌለን ወደ ፊት ብንታቀፍ ደስተኛ ነን ።



10
10 10
9
8
7
6
5
4
3
2
1
0
አዎ

አይ

Series 1 Series 2

፫ .ከባለድረሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያገኛችሁ ነው ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ 8 ወይም 40% የሚሆኑ
ማኀበራት አይ ድጋፍ አናገኝም ያሉ ሲሆን 7 ወይም 35% የሚሆኑት ማኅበራት ደግሞ አዎ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 5
ይም 25% ማኅበራት በከፊል ድጋፍ እናገኛለን ብለዋል ፡፡

Chart Title

8 7 8
7
6
5
4 5
3
2
1
0
አዎ
አይ
በከፊል

Column1 Column2 Column3


.ከባለድረሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ጋር በተያያዘ አይ ብለው መልስ የሰጡማኅበራት ምክንያት በሚያስቀምጡበት ጊዜ እነዚህን ምክንየቶች አንስተዋል
 በሰንበት ት/ቤት ስንታቀፍ አስፈላጊውን አትኩሮት አላገኝንም
 ፍላጐት ቢኖረንም ግንዛቤ ስላልነበረን አገልግሎቶችን አልተጠቀምንም
 ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለን ቅርበት (ግንኙነት) አናሳ ስለሆነ።
 ከማንም ድጋፍ ባለማግኘታን በራሳችን ወርሀዊ መዋጮ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመግዛት እና በመደጋገፍ እየሰራንነው።

ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት ስለሌለን እና ድጋፍ ባለመጠይቃችን

.ከባለድረሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል መልሶ አዎ ከሆነ የሚገኛቸውን ድጋፍ 1 እጅግ በጣም ጥሩ 2 በጣም ጥሩ 3 መካከለኛ 4 ደካማ 5 በጣም ደካማ በሚል የሚደረገውን
ድጋፍ ይግለፁልን ባልነው መሰረት አዎ እና በከፊል ብለው ከመለሱ 13 ማኅበራት ውስጥ እያንዳንዱን ድጋፍ በመተንንተን
የመረጡት የማኅበራት ብዛት
የሚደረገውን ድጋፍ 1 እጅግ በጣም ጥሩ 2 በጣም ጥሩ 3 መካከለኛ 4 ደካማ 5 በጣም ደካማ
በቁጥር ከመቶ በ በቁጥር ከመቶ በ በቁጥር ከመቶ በ በቁጥር ከመቶ በ በቁጥር ከመቶ በ %
% % % %

ያላችሁን አባላት ወደ መንፈሳዊ ተግባራት (ሰራዎች) በመንፈሳዊ ኅይወታቸው 1 7.69 1 7.69 8 2 15.4 1 7.69
ኅይወታቸው ለውጥ እንዲያመጡ መምህራንን በመመደብ የንስሃ አባትና ጊዜያትን
በማመቻቸት ያግዛችሁል?
መኅበራቹ አመታዊ እቅድ ማዘጋጀት፣ የአመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት የሒሳብ መዘገብ 2 15.4 5 38.4 3 23.1 3 -
አያያዝ እና ሌሎች የመያዊ ሰልጠናዎችን ይሰጣል?
ማኅበራት ከሌሎች ማኅበራት ጋር ልምድ ልውውጥ(ተሞክሮ) እንዲወሰድ ያመቻቻል 1 7.69 2 15.4 7 1 7.39 2 15.4

ለማኅበራቹ የግኑኝነት ጊዜ (ለፀሎት ፣ለመማማር እና ሌሎች ስራዎችን ለመስራት) 5 38.4 1 7.39 - 3 23.1 4
መሰብሰቢ ቦታዎችን የዘጋጃል/ያመቻቻል?
ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት እና ነዋየ ቀድስን እቃዎችን ያቀርባል 8 61.5 2 15.4 1 7.69 1 7.69 1 7.69

ሰንጠርዥ ፩.፫፡ .የባለድረሻ አካላት የሚገኛቸውን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ከሚደረገው ድጋፍ ማሳያ
Chart Title

20 1
18

16 7

14
8

12
2 3 1
10 1
3
2
8 5
1
6
8
1 5 3
4
2
2
2 1 1

0
እጅግ በጣም ጥሩ በጣም ጥሩ መካከለኛ ደካማ

መምህራንን በመመደብ የንስሃ አባትና ጊዜያትን በማመቻቸት የመያዊ ሰልጠናዎችን መሰብሰቢ ቦታዎችን የዘጋጃል/ያመቻቻል
ልምድ ልውውጥ(ተሞክሮ) ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት
፬ . አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ( ዋና ዋና ክንዋኔ የሚያሳይ ፤ የገቢና የወጪ የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ አካል
ያቀርባል ለሚለው ጥያቄ 10 ወይም 50% የሚሆኑ ማኅበራት ሪፖርት እናቀርባለን ያሉ ሲሆን 5 ወይም 25% በተወሰነ መልኩ
እናቀርባለን ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 5 ወይም 25% ሚሆኑት ማኅበራት አናቀርብም ያሉ ሲሆን ምክንያት ተብለው ለተጠየቁት

 ሀሳብም አልመጣልንም እናም ጥያቄ አላቀረብንም

 ሁላችንም እርስ በእርስ እንሰራለን እንጂ ሪፖርት እና እቅድ የለንም።

 የሚቀርብለት የበላይ አካል የለንም እርስ በእርስ እናወራበታለን

 ገና እየተቋቋመ ስለሆነ ጊዜ ይጠብቃል።

አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት

10

አዎ ያቀርባል በተወሰነ መልኩ ያቀርባል አያቀርብም


በቤተክርስቲያን
ስር የሌሉ ማኅበራትን በተመለከተ
፩ በቤተክርስትያን ስር ያለሆኑ ( ያልተመዘገቡ ወይም በሰንበት ትምኅርት ቤት ያልታቀፉ ) ማኅበራት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው
በለን ለጠየቅነው ክፍት ጠያቄ ማኅበራቱ ከጠቀሳቸው ምክንያት ውስጥ
 በግንዛቤ ማነስ እንዲሁም በትክክል ማኅበራቱ ባለመደራጀት

 ማኅበራቱ በቤተ-ክርስቲያን ስር የቦታ ማጣት

 በሠንበት ት/ቤቱ ዘንድ የቁጥጥር ስርዓተ መብዛቱ እንደልብ መስራት ስለማይቻል

 ስርዓትና የአሠራር ሂደት ያለማወቅ ችግርና መልካም ያልሆነ ግንኙነት ከቤተክርስቲያን አስተዳደር አካላት ጋር መኖሩ

 የአመራር ብቃት ማነስ የተጠየቁትንም በአግባቡ ማነስና ተገቢውን ምላሽ አለማግኘት

 በማኅበራቱ ዘንድ በመንፈሳዊ ህይወት አለመዳበር እና ለማወቅም ፍላጎት አናሳ መሆን

 ማኅበራት በሠንበት ት/ቤት ለመመዝገብ ምን እንደሚመስል አላማወቃቸው ከተጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ ዋንኛዎቹ ናቸው፡
፪. በማኅበራትና በሰንበት ትምኅርት ቤት መካከል እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ፣ ግጭት ዉስጥ የሚገቡ ማኅበረት
እንዳሉ ይነገራል በሚል ያለቸውን አመለካከት አብዛኛው ማለትም 11 ወይም 55% በጣም እስማማለሁ ያሉ ሲሆን 7 ወይም
35% በከፊል የሚስማሙ ሲሆን 1 ወይም 5 ማኅብር ብቻ ነው አንስማማምያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 1 ወይም 5% መረጃው የለኝም
ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ፍክክርና ግጭት እንዳለ መታዘብ ይቻላል፡፡

እበልጥ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ፣ ግጭት ዉስጥ የሚገቡ ማኅበረት

1
1

7 11

በጣም እስማማለው በከፊል እስማማለው አልስማማም መረጃው የለኝም

፫. በቤተክርስቲያን ውጪ በተለያዩ አዳራሾች ፤ የግለስብ ቤቶች ፤ እንዲሁም በሌላ ቦታ የሚደረጉ ጉባኤዎችና


ስብሰባዎች በቤተክርስቲያን ላይ ምን ተፅዕኖ አላቸው
አሉታዊ ተፅዕኖ :-
 ለመናፍቃን አስተምሮ ይጋለጣሉ

 ሠንበት ት/ቤት የቤተክርስቲያን በቅርበት ለመከታተል ይከብደዋል ይህም ማኅበሩ ከህግ እና ደንብ ውጪ እንዲሆን
ያደርገዋል።

 በቤተ ክርስቲያን ቀኖና - ትውፊት - ዳግማ ሊፍለስ ይችላል። በዚህ ምክንያት የሐሰት ት/ት ሊስፋፋ ይችላል፡፡

 ከቤተክርስቲያን መራቅን ያስከትላል

 ከቤተክርስቲያን ስርዓት ውጪ የሆነ ስርዓት ቢፈፅም ለመቆጣጠር አዳጋች ይሆናል።

 የማኅበራዊ መንፈሳዊነት ለመሸርሸር ቅርብ ይሆናል

 አላስፈላጊ የሆነ ደግስ እና ስካር እንዲሁም የቃል ልውውጦች ሊከሠት ይችላል። በነፃነት መከናወኑ የማኅበሩን
ዓላማ ሊያስት ይችላል
አወንታዊ ተፅዕኖ :-

 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቦታ እጥረት ስላላ ከእርሱ አንፃር ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡

 ከሠየት መባከን ምክንያት እንደመፍትሄ ሊሆን ይችላል

 ለግለሰብ ቤት አቅራቢያቸው በመሆኑ አመቺ ሊሆን ይችላል

 በቦታ ምክንያት በቤተክርስቲያን ስር ከሚገኙ አካላት ጋር ጭቅጭቅ እና አለመግባባት እንዳይፈጠር ይረዳል

 ነፃነት እና የመነቃቃት ሀሳብ እንዲኖራቸው በወጣት ምእመኑ ዘንድ ይፈጥራል

 ከስራ ሒደት ቅርበት አንፃር መልካም ነገር ይፈጥራል

➔ ከማኅበራት ቁጥር መዋዥቅና ( መፈረስ)ችግሮች በተመለከተ ( አአንድ በላይ ምላሽ መስጠትይችላሉ! )


፩. ለማኅበራት መፍረስ ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው ብለን ለመነሣ እንዲሆን ያሰቀመጥንለቸውን መልስ አሰጣጥ ላይ ከአንድ በላይ
መልስ መሰጠት እንደሚችሉ ያሰቀመጥንላቸው ሲሆን በዚህም አብላጫ ማለትም 17 ማኅበራት የአባላት ተነሳሽነት እያነሰ
መምጣት ያሉ ሲሆን በውስጥ የማስተባበር የመምራት ችግር ደግሞ 9 ማኅበራት በምክንያትነት አሰቀምጠውትታል ሌሎች 6
ማኅበራት ደግሞ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ አናሳ መሆን ነው ምክንያቱ ያሉ ሲሆን 3 ማኅበራት ሌላ ምክንያት አለ በሚል
በተቀመጠው ባዶ ቦታ ላይ የማኅበራት የማኅበራት ምዕመን አናሳ መሆን፣ በስራ ፣ በትዳር ፣ በቦታ ርቀት ማሳበብ እና በቂ የሆኑ
ትምህርት አለማግኘት

Chart Title

17 3
6
ሌላ ምክንያት
20 1
15 9
የመተዳደሪያ ገንዘብ አለማግኘት
10
5
0 በውስጥ የማስተባበርና የመምራት ችግር
በውስጥ የአባላት የመተዳደሪያ የባለድርሻ ሌላ ምክንያት
የማስተባበርና ተነሳሽነት ገንዘብ ድጋፍ አናሳ
የመምራት እያነሰ አለማግኘት መሆኑ
ችግር መምጣት

በውስጥ የማስተባበርና የመምራት ችግር የአባላት ተነሳሽነት እያነሰ መምጣት የመተዳደሪያ ገንዘብ አለማግኘት
የባለድርሻ ድጋፍ አናሳ መሆኑ ሌላ ምክንያት

፪. ማኅበራት ላይ ቤተክርስትያን ካስቀመጠቻቸው ወይም ከመደበቻቸው አካላት ወጪ ተፅዕኖ የሚያሳድሩአካላት አሉ ወይ ብልን


ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች አብዛኛው ማኅበር ማለትም 15 ወይም 75% የሚሆኑት ማኅበራት የሌሎች ጣልቃ ገብነት የለም ያሉ
ሲሆን ቀሪዎቹ 5 ወይም 25 %ማኅበራት አዎ ያሉ ሲሆን እነማን ናቸው ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች

 ማናቸው ያልተለየ አካላት አሉ

 መናፍቃን ተፅዕኖ ያሳድራሉ

 አማኝ መሳይ ነጋዴዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ያምፃሉ

 ግለሰብ በተለይም የጥበቃ አካላት

 በሠንበት ተማሪዎች እንዲሁም የንዑሳን ክፍላት ተጠሪዎች ምክንያት ጣልቃ ገብነት አለ ሲሉ አንሰተዋል

ቤተክርስትያን ካስቀመጠቻቸው ወይም ከመደበቻቸው


አካላት ወጪ ተፅዕኖ የሚያሳድሩአካላት አሉ

5
አይ አዎ
15

ከደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ እና የማኅበራት አንድነት ኃላፊ ጋር የተደረገ ቃለ
መጠይቅ

1. ስም እና በቤተክርስትያን ሃላፊነትዎን ቢገልፁልን? መምህር አንተነህ አወቀ ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ እና የማኅበራት
አንድነት ኃላፊ መንፈሳዊ ማዕረጎን ቢገልፁልን? መምህር
2. ማኅበራት አጀማመራቸው ምን ይመስላል?

ማኅበራት አጀማመራቸውን ስናነሳ ቀደምት ከሆኑት ማኅበራት ስንመለከትና እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ማኅበር የኮሌጅ
ተማሪዎች ከብላቴ ጀምሮ የጀመሩትን ሂደት አቡነ ጎርጎርዮስ ዘኑሲ ዘወይ ትምህርት ቤት ነበር የመጀመሪያው አቡነ ጎርጎርዮስ ማለት
እሳቸው በነበሩ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳንን ሰብስበው ያስተምሩ ነበር የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ተሰብስቦ የማኅበረ ቅዱሳንን መስርተዋል
ተብሎ የሚነገረው ይህ ነው።

ከእነርሱ በፊት ደግሞ ሃይማኖታ አበው የሚባል ማኅበር ነበር የተማሪዎች ማሀበር ነበር በስልሳዎቹ የነበረ ማኅበር ነበር በኋላ
ላይ ግን አካሄዱ ከመስመር ላይ እየሳተ እየወጣ ስለሄደ የማኅበር የመናፍቃን መሰብሰቢያ ስለነበር በቤተ ክህነት ደረጃ እንዲቋረጥ
ተደረገ አቡነ ጳውሎስ ከመጡ በኋላ እንደገና ሃይማኖተ አበው በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቦታ ተሰጥቷቸው የቀደመው
ሃይማኖት አበው ማኅበር በሚል ተሰባስበው ሂደቱን ቀጥለዋል።

እንደ አጠቃላይ ግን ማኅበራት የበዙት ከ ከተሃድሶ እንቅስቃሴ በኋላ ነው የጽዋ ማኅበራት የግቢ ሌሎች ማኅበራት ሁሉ
ለራሳቸው መጠቀሚያ እያደረጓቸው በመጡ ጊዜ በየቦታው ማኅበራት የመሰብሰብ ሂደት እንዲፈጥሩ ተደረገና የበለጠ በተሻለ
ማኅበራት እንዲሰሩ የተደረገው በዚያን ወቅት ነበር ከእነርሱ ቀጥሉ ደግሞ በ 2000 ዓ.ም ላይ መጥምቃውያን በተለምዶ የሚባሉት
ጥምቀት ላይ ምንጣፍ በማንጠፍ በማገልገል የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት እየተደራጁ በየአጥቢያቸው በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን የእገሌ
ማኅበር እየተባለ መቋቋም ተጀምሯል።

3. ማኅበራት በቤተክርስቲያን ላይ ያላቸው ተፅኖ የሚያሳዩ ወይም የሚገልፁ ማኅበራትን ቢጠቅሱልን?

በበጎ የሚገለፁ ማኅበራት ብዙዎች ክፍለሀገር ደረጃ የሚንቀሳቀሱት ናቸው ለምሳሌ ደጆችሽ አይዘጉ ላይ ያለውን ከአቡነ
እስጢፋኖስ ጋር እየተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን እያስከፈቱ ያሉ ናቸው እንደነሱ ያሉ በጣም ከፍተኛ ስራ እየሰሩ የሚገኙ አሉ በዚህ
ደብር የታቀፉትን ስንወስድ ገጠር ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት መነሻ የትውልድ ቦታቸው የሆኑትን ቤተ ክርስቲያን በማሳነስ ስብከተ
ወንጌል በማስፋፋት ለካህናት ደሞዝ በመክፈል ለቤተክርስቲያኒቱ ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖራት ችግኝ በማፍላት ወፍጮ ቤት
በመትከል ብዙ የተለያዩ ነገሮችን በመስራት ለቤተ ክርስቲያኑ ተመልሶ ገቢ የሚሆንበትን ነገር ከመስራት በጎ ተፅእኖ አላቸው።

4. ማኅበራት በቤተክርስቲያን ያላቸው ጥሩ ያልሆነ ምግባራት ያስተዋሉትን ቢገልፁልን?

ማኅበራት በዋናነት በስርዓት ደረጃ ክፍተት ይታይባቸዋል። ማኅበራት የፈለጉትን ነገር በፈለጉት ጊዜ ያደርጋሉ ለምን በሰንበት
ትምህርት ቤት የታቀፉት እንደዚህ አይነት ነገር በእነርሱ ዘንድ በብዛት አይተዋሉም በሰንበት ትምህርት ስር ያልሆኑት በውጭ ያሉት
ግን ጉዞ ያዘጋጃሉ የሚገኘው ገቢ ለማን እንደሆነ አይታወቅም ስርዓትን የመጣ እንዲሁ ከቤተክርስትያን አባቶችን ባለማክበር ምንም
ስህተት ቢፈጠር በአግባቡ መጠየቅ እየተቻለ ከስርዓት መውጣትና ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳትን በገንዘብ መግዛትና እንዲመቻቸው እንዲሆኑ
የማድረግ ጥሩ ያልሆነው ድርጊቶች ይስተዋላሉ።

5. በ 2015 ዓ.ም ማኅበራትን የመመዝገብ አዋጅ በወጣው ላይ በሰንበት ትምህርት ቤቶች የታቀፉ ማበራትን በቤተክርስቲያን ብቻ
ሳይሆን በዚህም አዲሱ ማኅበራት ማደራጃ ላይ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሙከራ ምን ይመስላል?

ማኅበራቱ በሰንበት ትምህርት ቤቱ እየታቀፉ ስለሆነ በዚያ አንድነት ማደራጃ እንዲታቀፉ አላስፈለገም ምክንያቱም
ማኅበራትን እንደ አባል ሰንበት ትምህርት ቤቱ አቀፎ ስለያዘ ሰንበት ትምህርት ቤትም በየ 15 ቀኑ የአንድነት ጉባኤ አዘጋጅቶ
እንዲገናኙ ያደርጋል ወደ ገጠር ሲሄዱ ዩኒፎርም እየሰጣቸው አገልግሎት አድርገው እንዲመለሱ ያደርጋል ከእነርሱም ዘንድ ወደዚያ
ለመታቀፍ የጠየቀንም ማኅበር የለም።

6. ማኅበራትን ከአመታዊ ሪፖርት አመታዊ ወጪ ገቢ ማቅረብ እና ሙያዊ ድጋፍ ከመስጠት አንጻር ያለበት የሰንበት ትምህርት ቤቱ
ማኅበራት አንድነት እንዴት ነው?

ገቢና ወጪ የማንንም ማኅበራት አንቆጣጠርም ምክንያቱም ብዙዎች ማኅበራት ወደ አንድነት ለመምጣት የሚከብዳቸውም
ይህ የሚጠይቅ ስለሚመስላቸው ነው፡፡ ነገር ግን ምን ሰርተዋል የሚለውን እንጠይቃለን ገጠር ላለው ቤተ ክርስቲያን ቋሚ
ፕሮጀክቶችን መቅረጽ አባላታችን ንሰሃ እንዲገቡ ኮርስ እንዲማሩ ስጋው ደሞ ለመቀበል እንዲበቁ ያደረጉትን ለመከታተል ፎርም
እንሰጣቸዋለን እነርሱ በእቅዳዳቸው መሰረት እንዲሰሩ ክትትል እናደርጋለን።

7. በማኅበራት መካከል እኔ በሚልፉ ክርክር ይነሳል ለዚህ ምክንያቱና መፍትሄው ምንድነው?

በመጀመሪያ ማኅበራትና ሰንበት ትምህርት ቤት አይገናኝም ሰንበት ትምህርት ቤት በቃ ከ 13 ቱ ክፍሎች አንዱ ሆነ ያለነው
የብቻ አይደለም ሰበካ ጉባኤ ሲቋቋም ከሰንበት ትምህርት ቤት ከካህናት ከምዕመ ከማኅበር የሚል የለም ስለዚህ ማኅበራት ይህንን
ማለት አይችሉም ምክንያቱም እነርሱ ከመዋቅር ውጪ ናቸው ነገር ግን ማኅበራት አያስፈልጉም ማለቴ አይደለም ጥሩ ምሳሌ
ለመስጠት ማበረ እስጢፋኖስ ውስጥ የነበረ መለሰ ታቦር የሚባል ከማኅበራት ወጥቶ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሊቀመንበር ሆኖ
እስከማገልገል ደርሷል። እንዲሁ ሌላ ማስረጃ ካስፈለገ ማስረሻ ካሳ የሚባል በምክትል ሊቀመንበርነት ከማኅበራት ወቶ የሰንበት
ትምህርት ቤቱ መከተል ሊቀመንበር ሆኖ እስከማገልገል ደርሷል ይህንን ስል ማኅበራት ውስጥ ማኅበረ አባል መሆናቸውን ሳይታ
እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ሆኖ ሁለቱንም ሳይተው በማገልገላቸው ነው።

8. ማኅበራት ከመፍረስ አንፃር እንዲሁም ማኅበራት በሰንበት ትምህርት ቤቱ ማበራት አንድ ዘንድ በቂ ምላሽ አናገኝም ይላሉ ለዚህ
ጥያቄ ምን ይመልሱልናል?

ይህን የሚሉ ማኅበራት ምን አሉ ለምሳሌ ምን ከእኛ ዘንድ መጥተው ጠየቁ እኛ በምንፈልገው መጠን አያስተናግዱንም ሲባል
ቤተ ክርስቲያን ስርአት አላት በፊት ማበራትን በየመጠያው ቦታ እየሰጠን እናስተናግድ ነበር ነገር ግን እነዚህ አንዱ ማኅበር መዝሙር
ሲያጠና ከአንዱ ዘንድ ደግሞ ትምህርት ሲማር እርስ በርስ አጠገብ ያለ መጠሪያ በመሆኑ ተቸገሩ ስለዚህ ሁሉንም ማኅበራት
ለማስተናገድ ስለማይቻል በየአስራ አምስት ቀኑ በአንድ ጊዜ በአንድነት የሚገናኙበት ርዓት አመቻች በዚያ መሠረት እያስተናገድን
መጣን በግልጽ ለመንገድ ያክል ማኅበራት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ሲመጡ በግልጽ የሚጠየቁት ነገር አለ ወራዊ ክፍያ 50 ብር
እንዲከፍሉ በማኅበር ደረጃ እናደርጋለን 50 አባል ወይም ደግሞ መቶ አባል ያለው ሊኖር ይችላል ብቻ እንደ ማኅበር ሆኖ ሀምሳ ብር
ይጠየቃሉ ሌላ ሁለተኛ የሚጠይቁት የተወካዮች የስብሰባ በወር አንድ ጊዜ ይደረጋል በዚያ የማኅበሩ ተወካይ መከተል ሰብሳቢው እና
ፀሐፊው ሦስቱ እንዲገኙ ይደረጋል።

9 ባለድርሻ አካላት አስፈላጊ ያደርጉ ለሚጠይቁት ጥያቄም ተገቢ ምላሽ አይሰጡም ይባላል ይህ እንዴት ይታያል?

ቤተ ክርስቲያን ርአት አላት ከዚህ ቀደም ማኅበራትም በሰንበት ትምህርት ቤት አቀፈ አንዱም በአንድ መጠሪያ ሲዘምር አንዱ
በሌላኛው ትምህርት ይማር ነበር በዚህ የመጋጨት ነገር እየተፈጠረ ሲሄድ በፈረቃ ሆነ አንዱ ሌላኛው በመጨረሻው ወደ አንድነት
ወደ አንድነት እንዲመጡ በ 15 ቀን አንዴ በቤተክርስቲያን ውስጥ ጉባኤ ተዘግቶላቸዋል እንደሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ መማር
ጀመሩ ሌላው አመታዊ በአል ማክበር ይፈልጋሉ ግን ሰንበት ትምህርት ቤት አንድ አዳራሽ ነው ያለው ያን ለብዙ ማኅበራት ማዳም
አይቻልም የአቅሙ ስንነስ ስላለ ነው አስፈላጊ ገዛም የሚባለው በዚህ ምክንያት ጉባኤ አዘጋጅተናል ሌላው ገዛ እንዲደረግላቸው
የሚጠይቁትን ነገር ማሟላት አለባቸው ለምሳሌ ዋና ዋና የሚባሉት በ 15 ቀን አንዴ መገኘት እንደ ማኅበር በወር ሃምሳ እንደ ማኅበር
በወር 50 እንዲሁም የተወካዮች ስብሰባ በወር አንድ ጊዜ መገኘት ያስፈልጋል ሰንበት ትምህርት ቤቱ የማኅበሩ መብት ያከብራል

10. ብዙ ማኅበራት ማኅበራት በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ መታከፉ እንደሚቻል ግንዛቤንም ይላሉ አንጻር ምን እየተሰራ ስራ
አለ?

ሰንበት ትምህርት ቤቱ መተው እንዲመዘገቡ ቅስቀሳ ያደርግም ራሳቸው በፍላጎታቸው መጥተው ነው የሚመዘገቡት
ምክንያቱም ህጉ አይፈቅድምም አስገድደን እንዲመዘገቡ ማድረግ አንችልም የሚመጡ ካሉ በመመሪያ መሠረት መመሪያውን አንበቦ
ከተስማሙ ስም ዝርዝር ከፊርማ ጋር በማምጣት ውስጥ ይቀላቀላሉ

11. በመጨረሻ ማጠቃለያ የእርሱን ሐሳብ ስለማኅበራት የተሻለ መፍትሄ ይህ ነው ይህ ይህ ቢሆን የሚሉትን ይንገሩን?
ማኅበራት ሁሉንም በየራሳቸው መስመር እየሄዱ የሚመጡ ከሆነ ከስርአቱ የሆነ እድላቸው እጅግ ሰፊ ነው። በቤተክርስቲያን
ስር በመሆን በመግባባት እና በመነጋገር ከሰንበት ትምህርት ቤተሰብ በመሆን ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀን እና የተሻለውን ሁሉ
ለማድረግ መስራት ተገቢ ነው።

ምዕራፍ አምስት

ድርሞ/ማጠቃለያ /Summary/
በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በቤተ ክርስቲያን ከየት ወደ የት በሚል ዕርስ ትናታችንን ያዘጋጀን ሲሆን
የማኀበራት ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ አጀማመር በነገደ መላዕክት ህብረት ፣በ ሕገ ኦሪት እና በአዲስኪዳን ብሎም በዘመነ ሰማዕታት መንፈሳዊ
ማኅበራት ምን ይመሰል እንደነበር ለመንሳት የሞከርን ሲሆን እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መነፈሳዊ ማኅበራት ምን አይነት ታሪካዊ እንቅስቃሴ
እንደነበራቸው አሁን እሰካሉበት ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማኅበራት የማኅበራት ዓላማ፣ የማኅበራት
ዓይነቶች፣በቤተክርስትያኒቷ ስር ያሉትን ማኅበራት የሚጀምቸው አካላት እና ከሚያዋቅራቸው አካል፣ የመንፈሳዊ ማኀበራት ከሚጠቀሱት
ጥቅሞች በማየት በ 2015 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ በማኅበራት አሰተዳደር ደንብ ላይ የደንቡን መውጣት ምክንያትና የባለድሻ
አካላት ሃለፊነትን ለመዳሰስ ሞክረን በመጨረሻም ማኅበራት ለምን በቅዱሳን ስም ይጠራሉ/ይሰበሰባሉ ሚለውን ከዳሰሰን በሃላ ከጥናታችን ወንኛ
አላማ በመነሳት ቁልፍ ጥያቄዎችን የመረጥንን ሲሆን በዚያም የፅሁፍና የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት ለ 20 መንፈሳዊ ማኅበራት በመበተን
እነዚህን ማጠቃላያዎቸ ከጥናቱ አግኝተናል፡፡

በዚህ ጥናት ላይ መንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተዕኖ ምን ይመስላል ብለን ስንመለከት በአስተዳደር ደረጃ የሚገኙት ማለትም ከ 75% በላይ
የሆኑ በወንዶች ስር ነው ያለው ይህ አሉታዊ ተጽዕኖ ባይሆንም ወንዶች ለክህነት እንዲሁም ለአገልግሎት በቅድሚያ የሚያስፈልጉ ከመሆናቸው
አንፃር መልካም ነው ሌላው እነዚህ ማኅበራት ሲቋቋሙ ከ 85% በላይ የሚሆኑት 21 እስከ 40 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው ይህ ደሞ
በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ መሆናቸው ዘመኑ ለመዋጀትና ወደሱስና ወደ መናፍቃን ዘንድ እንዳይሆኑ በጓደኞቻቸው ግፊት ወደ ቤተ
ክርስቲያን እንዲቀርቡ ይረዳል የህ ብቻ ሳይሆን 65% የሚሆኑትን ስንመለከት በዲግሪ እና ዲፕሎማ ደረጃ የትምህርት ዕውቀት ያካበቱ ናቸው
ይህም አለማዊ ዕውቀትን ከመንፈሳዊ እውቀት ጋር ያደበሩ መሆኑን እንመለከታለን መንፈሳዌ ማዕረጋቸውን ስንመለከት ግን 70% የያክሉ
በማኅበራት አስተዳደር ላይ የሚገኙት ምዕመናን ናቸው ይህ ደግሞ በምእመናን ዘንድ የሚመሩ ማበራት እንደሚበዙ ያሳያል ቀሪው 30% ብቻ
የድቁና እንዲሁም የመምህርነት መንፈሳዊ ማድረግን ባላቸው አስተዳደራት ይመራሉ

ማኅበራት የሚቋቋሙበትን ዋነኛ የሚባሉ አላማዎቻቸውን ስንመለከት አብዛኞቹ ተመሳሳይ የሆኑ ዓላማን ያነገቡ ናቸው ይህም የገጠሪቱ አብያተ
ክርስቲያናትንና ምዕመናን ላይ የተኮረ ነው ይህ ሲባል በገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያናት የሚያስፈልገውን የንዋየ ቅዱሳት በመግዛት ለካህናት ደሞዝ
በመክፈል ወንጌልን በማስፋፋት በጉልበት ድጋፍ በማድረግ ለተክርስቲያኒቱ ቋሚ የገንዘብ ምንጭ እንድታገኝ ለማድረግ የሚቋቋሙ ናቸው ከዚህ
ባለፈ ግን ወጣ ያለ ዓላማ ያነገቡ ማለትም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በኪነ ጥበብ ለመግለጽ ዝክር ለመዘከር በጥምቀትም ሆነ በተለያዩ
በዓላት የሚሰበሰቡ ወጣቶችን እንዳይበተኑ ለማድረግ በሚል ዓላማ ማኅበራት ይቋቋማሉ

ማኅበራት ይበልጡን ተቋቁመው እና ተመስረተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ያለፉት 10 እና 15 አመታት ውስጥ ናቸው ከእነርሱ መሃል በእድሜ ጠገበ
እንዲሁም ገና በጥቂት እድሜ ውስጥ የተመሠረቱ ማኅበራት ሲገኙ አመሰራረታቸው በአካባቢው ወጣቶችና በጓደኛሞች ሲሆን አልፎ አልፎ ደግሞ
በንስሃ አባት እና በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዘንድ በህብረት በመሆን ይመሠረታሉ በጥናታችን መሰረት 60% ማኅበራት በቤተ ክርስቲያን
ስርዓት (ዶግማ ቀኖና ትውፊት) መሰረት ማበራት እየተንቀሳቀሱ ያልሆኑ ማኅበራቶች እንዳሉ ያምናሉ ቀሪዎቹ ማኅበራት ደግሞ ይህንን በከፊል
የሚስማሙና በጭራሽ የሉም ብለው የሚያምኑ ማኅበራት ናቸው ይህ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ስም የተቋቋሙ ማኅበራት የራሳቸውን ሀብት
የሚያካብቱ ናቸው ብለው የሚያምኑ 45% የሚሆኑ ማኅበራት አሉ ሌሎች ማኅበራት ደግሞ ማለትም 55% የሚሆኑት አይ የግል ሀብት
የሚያካብቱ አይደለም የሚል ሀሳብ የሌላቸው እና ጭራሹን መረጃው የሌላቸው ማኅበራት ናቸው

ማኅበራት በምዝገባ እና ክትትል ስር ወይም በሰንበት ትምህርት ቤት ስር የተመዘገቡ ማኅበራቶችን አግኝተናል ይህም መልካም የሚባል ሲሆን
በተመሳሳይ መልኩ ያልተመዘገቡ ማኅበራትም ይገኛሉ ታዲያ የእነዚህ ማኅበራት ዋና ዋና ምክንያትን ብለው የሚጠቅሱት በራሳቸው ማኅበር
ውስንነት በቂ የሆነ አደረጃጀት እና ጠንካራ አመራር የለንም የሚሉ እንዳሉ አውቀናል በዚህ ብቻ አይደለም ማኅበራቸው በቂ አደረጃጀት
ቢኖረውም ከማኅበራት አንድነት የሚመራው ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር መግባባት አንችልም ወይም ሰንበት ትምህርት ቤቱ የቁጥጥር ስርዓት
ያበዛብናል ይህ ደግሞ ለምንሰራው ስራ እንቅፋት ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ ተገንዝበናል። በተጨማሪ ግን ከዚህ ወጣ ያለ ሀሳብ ያላቸው
ማኅበራት አሉ እነዚህም ጭራሹን በሰንበት ትምህርት ቤት ማበራት አንድነት የሚባል እንዳለና መመዝገብ አለብን ወይም የለብንም የሚል ጉዳይ
አውርተው እንደማያውቁና የግንዛቤ ችግር እንዳለ ተመልክተናል ይህ ደግሞ ከቤተክርስትያን ጋር ከመስራት አንጻር ክፍተት እንደሚስተዋል
ማሳያዎች ናቸው ከቤተክርስትያን ዘንድ ድጋፎችን ስንመለከት ማኅበራት ያላቸው ምላሽ ቃል ብቻ እንጂ ተግባራዊ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው
ማኅበራት ይናገራሉ ይህ ከቤተክርስትያን ወገን ይሁን እንጂ ማኅበራትም በራሱ ቀርበው ድጋፍ የሚጠይቁ እንዳልሆኑም ተመልክተናል

የድጋፍና ክትትል ጠንካራ ጎኖች ብለው ማኅበራት ከሚያነሱት ውስጥ መምህራንን በመመደብ የንስሐ አባት እና ጊዜያትም በማመቻቸት ድጋፍ
እንደሚደረግላቸው አብዛኞቹ ማኅበራት ዘንድ ተመልከታናል ከዚህ ተቃራኒ ቦታ አድርገው ወይም ድክመት ብለው በአብዛኞቹ ማኅበራት ዘንድ
ደግሞ ለማኅበራቸው የግንኙነት ጊዜ ወይም ለፀሎት ለመማር እና ሌሎች ስራዎችን ለመስራት መሰብሰቢያ ቦታዎችን የማጣት ችግር እንዳለ በግልጽ
ነግረውናል

በቤተክርስቲያን ስር የሌሉ ማኅበራት ለምን በቤተ ክርስቲያን ስር እንዳልታቀፉ ባደረግነው ጥናት መሠረት የግንዛቤ ማነስ በማኅበራት ዘንድ
የስሚተዋል መሆኑ እና ማኅበራት በቤተክርስትያን ቦታ የማግኘት እጥረት ስላለ እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤት ማበራት አንድነት ስር ቢታቀፉ
የቁጥጥር ስርዓት በመኖሩ እንደልብ መስራት እንደማይችሉ እና ስርአት እና የአሠራር ሂደት የዓለምወቅ በማኅበራቱም ዘንድ መንፈሳዊ ህወታቸው
አለመዳበር እና ለማወቅም እንዲሁ ፍላጎታቸው አናሳ መሆኑ ዋና ብለው የሚያስቀምጡት ምክንያታቸው ነው በማኅበራት ዘንድም እኔ እበልጣኔ
እበልጥ የሚል ግጭት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጋር እንዳለ ከ 55% በላይ የሆኑት ይስማማሉ ቀሪዎቹ ከፊል የሆነ ስምምነት እና መረጃውም
የሌላቸው ማኅበራት ናቸው ከቤተክርስትያን ውጪ የሚደረጉ የማኅበራት መሰብሰቢያ ቦታዎችም በተመለከተ ደግሞ ማኅበራት እንደ አሉታዊ
ተዕኖ የሚያዩት ነገር ለመናፍቃን አስተምህሮ እንደሚጋለጡ ከቤተክርስትያንም ቀኖና ትውፊት ዶግማ ውጪ የመሆን እድሉ ሰፊ እንደሆነና
የማኅበራት መንፈሳዊነት ለመሸርሸር ቅርብ መሆኑን ይስማማሉ እንደ አዎንታዊ ጎን ከሚያነሱት ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የቦታ እጥረት
ከመፍታት እና ከሰዓት መባክ እንዲሁም ከስራ ሂደት ቅርበት አንፃር መልካም ነገር እንደሚፈጥር ይስማማሉ

በተጨማሪም ይህ ህጥናት የማኅበራት ቁጥር መዋዥቅን ምክንያት ስንመለከት ዋና ዋና ምክንያቶቹ ማኅበራት የአባላታቸው ተነሳሽነት እያነሳ
መምጣቱ እና በውስጥ የመተባበር የመምራት ችግር ዝቅተኛ መሆኑን ያመለክተናል ሌላው ግን እስከመፍረስ የሚያደርሳቸው ምክንያት ምን
እንደሆነ ስንመለከት ከቤተክርስትያን ውጭ የሚገኙ አካላት ተዕኖ እንደማያሳድሩባቸው 75% ማኅበራት ያምናሉ ይህም ደግም ከውጭ ካለው
ተዕኖ ይበልጥ በውስጥ የአባላት ተነሳሽነት በማነሱና የመተባበር ችግር መኖሩ ለዚህ እንደሚዳርጋቻው የሚያመላክት ነው ይህ እንዳለ ሆኖ አባላት
ምንድነው ተነሳሽነት ያሳጣቸው ምንስ ጉዳይ ነው የያዛቸው ብለን ለመመልከት ስንሞክር የስራ የትዳር እንዲሁም የቦታ ርቀት ማሳሰብ እና በቂ
የሆኑ ትምህርቶችን ዓለማግኘታቸው እንደ ዋና ምክንያትነት ይገልፃሉ
መደምደሚያ /Conclusion/
በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በቤተ ክርስቲያን ከየት ወደ የት በሚል ዕርስ በሰራናው ጥናት
እነዚህን ዋና ዋና መደምደሚያዎች ይዘናል፡፡

የዘመናችን የመንፈሳዊ ማኅበራትን በአብዛኛው በአካባቢ ወይም በተወላጅ ወጣቶች የአካባቢያቸውን በተለይም የገጠሩ አብያተ
ክርስቲያናትና ምዕመናን በመናፍቃን አሉታዊ ተፅዕኖ እና በነዋያተ ቅድሳት ምክንያት አገልግሎታቸው እንዳያቋርጡ ማገዝ
ቤተክርስትያን ለማሰራት አላማ አድርግው ሚንቀሳቀሱ ማሀበራት ቢበዙም ከዚህ ጎን ለጎን በየአካባቢው ለመንፈሳዊ ጉዞ ዝክር
ለመዘከር የእርዳታ ተግባር ለማከናወን እና ቁጭ ብለው መመራት የማይፈልጉ በቤተክርስቲያና በተለያዩ ቦታዎች ሲገለግሉ
የነበሩግለሰቦችም የመሰረታቸው ማኅበራት መኖራቸውን ጥናቱን ያሳያል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይስ ያለቸው ተፅዕኖ በአብዛኛው
በጎ/ ጥሩ ተፅዕኖ ሲሆን የቤተክርስቲያንን ስርዓት( ዶግማ ፣ ቀኖና፣ ትዉፊት ) በሚያፋልስ መልኩ ስራዎች የሚሰሩ ማኀበራት እና
ለቤተክርስትያን ጥቅም ከመስራት ይልቅ በማኅበራት ስም የራሳቸውን ሀብትና ጥቅም እናዳሉ ከጥናታችን መረዳት ችለናል፡፡

የመንፈሳዊ ማኅበራት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናናን ስብስብ እንደመሆናቸው ብሎም ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንደመሰባሰባቸው
/እንደመቋቋማቸው አስፈላጊውን አትኩሮት በመዋቅር ደረጃ ካሉት የባለድርሻ አካላት ማለትም የማኅበራት ምዘገባ ክትትል እና
ቁጥጥር ከሚከናወን አካል ተገቢውን ድጋፍ አጊንተዋል ማለት አይቻልም ፡፡ ድጋፎቹም ቢሆን በሰንበት ትምህርት ቤት እና አባቶች
እንጂ ወጥነት የሌለው ሲሆን ከሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚገኘው ድጋፍ ብዙ ክፍተቶች ያሉበት ነው ።ለማሳያ ያህልያላችሁን አባላት
ወደ መንፈሳዊ ተግባራት (ሰራዎች) በመንፈሳዊ ኅይወታቸው ለውጥ እንዲያመጡ መምህራንን በመመደብ የንስሃ አባትና ጊዜያትን
በማመቻቸት ላይ እና ለማኅበራት የግኑኝነት ጊዜ (ለፀሎት ፣ለመማር እና ሌሎች ስራዎችን ለመስራት) መሰብሰቢ ቦታዎችን
ማመቻቸት ላይ ክፍተት እንዳለበት ጥናቱ ሊሰየን ችላል፡፡ እንዲሁም የማኀበራትን አመታዊ የስራና የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርት
በአግባቡ አይቀርብም በዚህ ምክንያት አንዳንድ ማህበራት የሚገኘውን ገቢ ለቤተክርስትያን ከማዋል ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም እና
አላስፈላጊ ነገር እየተደረገበት ይገኛል፡፡

የማኅበራት አሰተዳደር ደንብ የወጣ ቢሆኑም በሚፈለገው መንገድ ማኅበራት እየተመዘገቡ ያልሆነበት በቤተክርስትያን ስር ያሉ
ማኅበራት እንኳን የምንለው በሰንበት ትምህርት ቤት የታቀፉ እንጂ በ 2015 ዓ.ም በወጣው ደንብ መሰረት ማኅበራትን በሚመዘገብ
አካል አለመሆኑ ከጥናታችንን ልናሰተውል ችለናል፡፡ በአንዳንድ ማኅበራት እና በሰንበት ትምህርት ቤትም ላይ ያለው የተቀናቃኝነት
መንፈስ (ጥሩ ያልሆነ) ፈክክር እነዳለ ማየት ችለናል፡፡
የመንፈሳዊ ማኅበራት ቁጥራቸው መዋዠቅ ብሎም እሰከመፈረስ የሚደረሳቸው ችግሮች ብዙ ባለድረሻ አካል የሚነካ ችግር መሆኑን
እና ለመፈረስ ምክንያት ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡትን ችግሮች መቅረፍ በጣም አሰፈላጊ ሲሆን ማኅበራትን ሊመዘገብ ሊከታተልና
ሊቆጣጠር ከተመደቡ አካለት ውጪ ተገቢ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ጥናቱ አሳይታል

የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation


በዚህ ጥናት ውስጥ መፍትሔ ነው ተብለው የተቀመጡ ሐሳቦች በየደረጃው ተቀምጧል ።

ሰንበት ት/ቤት

 በሰንበት ተማሪዎች እና የሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች በማኀበራት የሚሳተፉበት ጊዜ ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና ግንዛቤ
መሰጠት እና እንዲሳተፉ ማድረግ
 ከማኅበራት ጋር ለሚከሰቱ ችግሮች ችግሮችን ባለመፈጠር ለሚፈጠሩ ችግሮችን በቤተሰባዊነት እና የቤተክርስትያንን ጥቅም
ባሰቀደመ መልኩ ለችግሮቹ መፍትሄ መፈለግ ቢቻል

ምዕመናን

 ማኅበራት ዘርፈ ብዙ ትቅም ያለቸው ቢሆኑም ለሚደግፉት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ተገቢውን ደረሰኝ ወይም የድጋፉን
መድረሻ ቢያጣሩ
 ምእመናን ማህበራትን በሚያቋቁሙበት ወይም ደግሞ በሚጀምሩበት ወቅት ከማዕከላቸው መንፈሳዊ ማድረጉ የተሻለ
በድቁና ወይም ደግሞ በትህትነት አሊያም በመምህርነት ደረጃ እንኳን የሚገኝ አድርገው አካተው ቢጀምሩ መልካም ነው

ማኅበራት

 ማኀበራት በማኀበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ቢታቀፉ አልያም በአብየተ ክርስቲያናት ውስጥ ባሉ ሰንበት
ትምህርት ቤት ውስጥ በጊዜያዊነት ቢታቀፉ
 አንዳንድ ማኅበራት ለቤተክርስትያን በማለት የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ያውላሉ እንዲሁም ጉዞ በማዘጋጀት
የሚገኘውን ገቢ ለሊላ ጥቅም ይውለል፡፡ ሰለዚህ እነዚህ ማኅበራት ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ እየሰሩ ሰለሆነ
ከድርጊታቸው ቢቆጠቡ ጥሩ ነው ፡፡

በቤተክርስትያን አሰተዳደር
ማህበራት በውጪ የሚደረጉ ጉባዬች በተለያዩ ቦታዎች ሲከናወኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሰለሚያመጡ ውጢ የሚከራዩት አዳራሾችና
የግለሰብ ቤቶች በዋጋም ውድ ሰለሆነ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለቤተክርስትያን የሚሰገኝ በመሆኑ ማህበራት ሌሎች ነገሮችን
በማይረብሽ መልኩ ቦታዎችን በኪራይ ማመቻቸት ቢቻል

ከካህናት እና መምህራን

ማህበራት ከቤተክርስቲን ውጪ ሆነው በሚሰበሰቡበት እና በጉባዬ ወቅት ከቤተክርስትያን ስርዓት ውጪ ሆኑ ነገሮች እየተደረጉ
ሰለሆነ ለምሳሌ መጠጥ፣ ግጭት የመሳሰሉት ይከሰታሉ፡፡ እንዲሁም በሃሰት ትምህርት ውስጥ ወድቀው ወደ ሌላ ዕምነት ይሄዳሉና
ተገቢ የሆነ ማስተማርና እገዛ ቢያደርጉ፡፡

የማኀበራተ ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ማኅበራት እየተበራከቱ የመጡበት ወቅት በመሆኑ ማኅበራት ለቤተክርስቲያን
የሚያበረክቱት በጎ አስተዋፅኦ ሊኖር ስለሚገባ ሰላለም¬ በቤተ ክርስቲያን አካላት ክትትል እየተደረገባቸው የሚቋቋሙበት ዓላማ
መሠረት አድርጎ መደበኛ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥራው በማኅበራቱ እየተደገፈ በአግባቡ መወጣት እንዲችል፣ በቤተ ክርስቲያን
ስም እና መዋቅር ሥር የሚቋቋሙ ማኅበራት የሚያቅፏቸው አባላት፣ የሚሰበስቡት ሀብትና ንብረት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
አካላት ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግበት የሚያስችልን ሥርዓት የሚዘረጋ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፣ እና በሌሎች
ምክንያት የማኅበራት አሰተዳደር ደንብ የወጣ ቢሆኑም ደንቡ እላይ ተንጠለጠለ ማኅበራትም ግንዛቤ የሌላቸው ሰለሆነ የግንዛቤ
ማሰጨበጫ ስራዎች መስራት፡፡ በአሰተዳደር ደንቡ ላይ በግልፅ የተሰጠውን ስልጣን ከሌሎች የቤተክርስትያን አሰተዳደር መዋቅር
ጋር በመሆን ለመፈፀም ስራዎችን መስራት ቢችል ተሻለ ነው፡፡

የሚገኘውን ገቢ ለቤተክርስትያን ከማዋል ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም እና አላስፈላጊ ነገር ላይ የሚያደርጉ ማህበራትን በአግባቡ
መመርመርና ገንዘቡ አግባብ ላለው ነገር ላይ እንዲውል ቢያደርጉ፡፡

በዚህ ጥናት የተገነዘብናቸውን ልዩ ልዩ ችግርን በ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት አስተዳደር ደንብ
ቁጥር፫/፳፻፲፭ የፀደቀውን ደንብ ተግባራዊ አድርጎ በአዲስ መዋቅር ቢያንስ በክፍለተማ ደረጃ እንዲኖር ቢደረግና ማኀበራትን
ቢያስተዳድር ችግሮቹ ይቀረፋሉ የሚል እምነት አለን፡፡

በሰተመጨረሻ ዛሬ በቤተክርስትያን ላይ የሚረባረበው ሁሉ ይመስላል በውጪ አካላት ትፈተናለቸ በጎጠኛ በራሳ ልጆች ትፈተናለች
ይህ እንደጎርፍ የመጣ ፈተና በመሆኑ ከቤተክርስትያን ጋር አብሮ መስራት የጎርፉ ማምለጫ በቸኛ መሳሪያ ሁሉም ምዕመን፣ ሰንበት
ት/ቤት፣ ማኅበራት፣ በቤተክርስትያን አሰተዳደር፣ ከካህናት እና መምህራን የማኀበራተ ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያ አብሮ
መስራት ነው፡፡

እናመሰግና
ማጣቀሻ /Reference
 ሰማኒያ ሓዱ መፀሃፍ ቅዱስ፣ ብራና ሰላም ማተሚ ቤት 1987
 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የማኅበራት አሰተዳደር ደንብ ጥቅምት 2015
 የሰንበት ት/ቤቶች የማሰተማሪያ መፀሐፈትና የመምህራን መመረ ከቁጥር 1-12፣ 2011 ዓ.ም አዲሳ አበባ ኢትዮጵያ
 ዲያቆን ዓብይ ሙሉቀን ሐመር መፅሄት 27 ኛ ዓመት ቁጥር 7 ህዳር 2012 ዓ.ም
 ማየ ሕይወት 10 ኛ ዓመት ጥር 2012 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት
ትምህርት ቤት ቁጥር 5 መንፈሳዊ መፅሔት
 አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ፌስቡክ ገፅ MEDIA OF ADDIS ABABA DIOCESE
 https://andadirgen.blogspot.com/2012/04/blog-post
 https://eotcmk.org/gibi-a ዲ/ን ግርማ ተከተለው
 https://nohamin.blogspot.com/2016/04/part-1-14.html
 https://kidusmichaeltswa.org/index.php/resources/abouttswa/
 መንግሥቱ ጌታቸው 2004 ለደ/ኃ/ቅ/ራጉኤል ቤ/ክ/አ/ብ/ሰ/ት/ቤት መመረቂያ ጥናታዊ ጽሑፍ
ተቀጽላዎች/አባሪዎች/Appendices/

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሐሃዱ አምላክ አሜን በኢትዮጽያ


ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ
የፅሁፍ መጠየቅ

ይኅ የፅሁፍ መጠየቅ የመንፈሳዊ ማኅበራት ሁለንተናዊ ተፅዕኖ በቤተክርስቲያን ከየት ወደየት በሚል
ለምናዘጋጃው ጥናታዊ ፅሁፍ የሚረዳ በመሆኑ ይህ መጠይቅ ከመመረቂያ ፅሁፍ ባለፈ የቤተክርስትያንን
ችግሮች ለመቅረፍ ብሎም ለመማሪያነት ለማዋል እንጂ የትኛውንም ማኅበር የማይጎዳ በመሆኑ ለጥያቄዎቹ
እውነተኛ መልስ ለመስጠት ስለተባበሩን በቅዱስ አማኑኤል ስም ከልብ እናመስግናለን።
በተቀመጡት ምርጫዎች ፊት ባለው ሳጥን ላይ ምላሾን በ ( √ ) ምልክት ይግለፁ!

 ለናሙና የተመረጡ አካላት ግላዊ መረጃ

፩. ፆታ ወንድ ሴት
፪. እድሜ

ከ 15 - 20 ከ 21 - 30 ከ 30 – 40 ከ 40 በላይ

፫. የትምኅርት ደረጃ

ከ 1- 8 ከ 9 - 12

ዲፕሎማ ዲግሪ ማስተርስና ከዚያ በላይ

፬. መንፈሳዊ ማዕረግ
መምኅር

ዲያቆን ቄስ ምዕመን
ሌላ የማኅበሩ
፭. በማኅበሩ ውስጥ ያለዎት ኃላፊነት
የማኅበሩ ሰብሳቢ (ሙሴ) የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ

የማኅበሩ ሂሳብ ክፍል የማኅበሩ ኅዝብ ግንኙነት

ሌላ የማኅበሩ
 የማኅበሩ ዓላማ ፤ አጀማመራቸውና በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው ተፅዕኖ በተመለከተ

፩. ማኅበራቹ የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ ወይም ሊሰራ የተነሳው (ያሰበው) ምን አገልግሎት ነው ?

፪. ማኅበራቹ መቼ እና በማን ተመሰረተ ?

፫. በቤተክርስቲያን ስርዓት (ዶግማ ፤ ቀኖና ፤ ትውፊት) በሚያፋልስ መልኩ ስራዎች ይከናወናሉ ?

በጣም እስማማለው በከፊል እስማማለው አልስማማም

፬ .ቤተክርስቲያን ስም የተቋቋሙ ማኅበራት ሆነው ለቤተክርስትያን ጥቅም ከመስራት ይልቅ በማኅብራት


ስም የራሳቸውን ሀብት ጥቅም የሚያካብቱ አሉ?
በብዛት አሉ ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም አሉ

የሉም መረጃው የለኝም

 በመዋቅር ደረጃ ካሉ የባለድርሻ አካላት አስፈላጊው አትኩሮት እና ድጋፍ በተመለከተ

፩ .ማኅበራቹ በማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ወይም በሰንበት ት / ቤት ስር ተመዝግቧል?

አዎ አይ

መልሶ አይ ከሆነ ለምን ?

፪ .ማኅበራቹ ከባለድርሻ አካላት ( ማኅበራትን ከሚከታተል ፤ ከሚቆጣጠር እና ከሚደገፍ መዋቅራዊ


ተቋማት ጋር በጋራ ይሰራል ?
አዎ አይ

መልሶ አይ ከሆነ ለምን ?


፫ .ከባለድረሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያገኛችሁ ነው ?

አዎ በከፊል አይ

መልሶ አይ ከሆነ ለምን ?

መልሶ አዎ ወይም በከፊል ከሆነ የሚገኛቸውን ድጋፍ 1 እጅግ በጣም ጥሩ 2 በጣም ጥሩ 3 መካከለኛ 4 ደካማ
5 በጣም ደካማ በሚል የሚደረገውን ድጋፍ ይግለፁልን?
የሚደረገውን ድጋፍ 1 2 3 4 5
ያላችሁን አባላት ወደ መንፈሳዊ ተግባራት (ሰራዎች) በመንፈሳዊ ኅይወታቸው
ኅይወታቸው ለውጥ እንዲያመጡ መምህራንን በመመደብ የንስሃ አባትና
ጊዜያትን በማመቻቸት ያግዛችሁል?

መኅበራቹ አመታዊ እቅድ ማዘጋጀት፣ የአመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት የሒሳብ


መዘገብ አያያዝ እና ሌሎች የመያዊ ሰልጠናዎችን ይሰጣል?

ማኅበራት ከሌሎች ማኅበራት ጋር ልምድ ልውውጥ(ተሞክሮ) እንዲወሰድ


ያመቻቻል

ለማኅበራቹ የግኑኝነት ጊዜ (ለፀሎት ፣ለመማማር እና ሌሎች ስራዎችን ለመስራት)


መሰብሰቢ ቦታዎችን የዘጋጃል/ያመቻቻል?

ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚውሉ አልባሳት እና ነዋየ ቀድስን እቃዎችን ያቀርባል

ሌሎች የሚደረጉ ድጋፎች ወይም ሌላ ሃሳብ ካሉ

፬ . አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ( ዋና ዋና ክንዋኔ የሚያሳይ ፤ የገቢና የወጪ የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ
ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል ? )
አዎ ያቀርባል በተወሰነ መልኩ ያቀርባል አያቀርብም

መልሶ ኢያቀርብም ከሆነ ለምን ?


 በቤተክርስቲያን ስር የሌሉ ማኅበራትን በተመለከተ

፩ በቤተክርስትያን ስር ያለሆኑ ( ያልተመዘገቡ ወይም በሰንበት ትምኅርት ቤት ያልታቀፉ ) ማኅበራት ዋነኛ


ምክንያት ምንድን ነው

፪. በማኅበራትና በሰንበት ትምኅርት ቤት መካከል እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ፣ ግጭት ዉስጥ
የሚገቡ ማኅበረት እንዳሉ ይነገራል።
በጣም እስማማለው አልስማማም

በከፊል እስማማለው መረጃው የለኝም


፫. በቤተክርስቲያን ውጪ በተለያዩ አዳራሾች ፤ የግለስብ ቤቶች ፤ እንዲሁም በሌላ ቦታ የሚደረጉ
ጉባኤዎችና ስብሰባዎች በቤተክርስቲያን ላይ ምን ተፅዕኖ አላቸው
አሉታዊ ተፅዕኖ :-

አወንታዊ ተፅዕኖ :-

 ከማኅበራት ቁጥር መዋዥቅና ( መፈረስ)ችግሮች በተመለከተ ( አአንድ በላይ ምላሽ መስጠትይችላሉ! )

፩. ለማኅበራት መፍረስ ዋነኛ ምክንያት

በውስጥ የማስተባበርና የመምራት ችግር የአባላት ተነሳሽነት እያነሰ መምጣት


የመተዳደሪያ ገንዘብ አለማግኘት የባለድርሻ ድጋፍ አናሳ መሆኑ
የመናፍቃን ተፅኖ

ሌላ ሀሳብ ካለዎት :-

፪. ማኅበራት ላይ ቤተክርስትያን ካስቀመጠቻቸው ወይም ከመደበቻቸው አካላት ወጪ ተፅዕኖ የሚያሳድሩአካላት


አሉ

አዎ አይ
መልሶ አዎ ከሆነ ለምን እነማ?

ቃለ መጠይቅ
1. ስም እና በቤተክርስትያን ሃላፊነትዎን ቢገልፁልን? መንፈሳዊ ማዕረጎን ቢገልፁልን?

2. ማኅበራት አጀማመራቸው ምን ይመስላል?

3. ማኅበራት በቤተክርስቲያን ላይ ያላቸው ተፅኖ የሚያሳዩ ወይም የሚገልፁ ማኅበራትን ቢጠቅሱልን?

4. ማኅበራት በቤተክርስቲያን ያላቸው ጥሩ ያልሆነ ምግባራት ያስተዋሉትን ቢገልፁልን?

5. በ 2015 ዓ.ም ማኅበራትን የመመዝገብ አዋጅ በወጣው ላይ በሰንበት ትምህርት ቤቶች የታቀፉ ማበራትን በቤተክርስቲያን ብቻ
ሳይሆን በዚህም አዲሱ ማኅበራት ማደራጃ ላይ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሙከራ ምን ይመስላል?

6. ማኅበራትን ከአመታዊ ሪፖርት አመታዊ ወጪ ገቢ ማቅረብ እና ሙያዊ ድጋፍ ከመስጠት አንጻር ያለበት የሰንበት ትምህርት ቤቱ
ማኅበራት አንድነት እንዴት ነው?

7. በማኅበራት መካከል እኔ በሚልፉ ክርክር ይነሳል ለዚህ ምክንያቱና መፍትሄው ምንድነው?

8. ማኅበራት ከመፍረስ አንፃር እንዲሁም ማኅበራት በሰንበት ትምህርት ቤቱ ማበራት አንድ ዘንድ በቂ ምላሽ አናገኝም ይላሉ ለዚህ
ጥያቄ ምን ይመልሱልናል?

9. ባለድርሻ አካላት አስፈላጊ ያደርጉ ለሚጠይቁት ጥያቄም ተገቢ ምላሽ አይሰጡም ይባላል ይህ እንዴት ይታያል?

10 ብዙ ማኅበራት ማኅበራት በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ መታከፉ እንደሚቻል ግንዛቤንም ይላሉ አንጻር ምን እየተሰራ ስራ አለ?

11. በመጨረሻ ማጠቃለያ የእርሱን ሐሳብ ስለማኅበራት የተሻለ መፍትሄ ይህ ነው ይህ ይህ ቢሆን የሚሉትን ይንገሩን?

You might also like