Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 1

7/10/24, 11:01 AM ተጠያቂነት ሥልጣንን መነሻ ያድረግ -

Wednesday, July 10, 2024   

Home / Uncategorized / ተጠያቂነት ሥልጣንን መነሻ ያድረግ 

ተጠያቂነት ሥልጣንን መነሻ ያድረግ


ኢትዮጵያ ፌደራላዊ የመንግስት ሥርአት የምትከተል ሃገር ነች። ፌደራላዊ መንግስት በሁለት እርከን የተከፈለ የመንግስት ሥልጣንና ተግባር ያለው የሃገር አስተዳደር ሥርአት ነው። አንደኛው የስልጣን እርከን የፌደራሉ መንግስት ሲሆን ሌላኛው
የስልጣን እርከን የፌደራሉ አባላት የሆኑ ግዛቶች/ክልሎች መንግስታት ነው። እንደየሃገሩ ነባራዊ ሁኔታ የግዛት መንግስታቱ ሁለትና ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሥርአት በ1987 ዓ/ም በጸደቀ ህገመንግስት
የተመሰረተ ሲሆን ስያሜውም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) ነው።
የኢፌዴሪ መንግስት ዘጠኝ አባላት አሉት። እነዚህም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፤ የኢትዮጵያ ሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ
መንግስት፤ የቤኒሻንጉል/ጉምዝ ብሄራዊ ክልል፤ የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት፤ የጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት፤ የሃረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ናቸው። የኢፌዴሪ መንግስትና ክልላዊ መንግስታት በህገመንግስት
የጸና የየራሳቸው የስልጣን ገደብ አላቸው።
የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 51 የፌደራል መንግስትን ስልጣንና ተግባር ይዘረዝራል። አንቀጽ 52 ደግሞ የክልል መንግስታትን ስልጣን ይዘረዝራል። በህገመንግስቱ አንቀጽ 52 ንኡስ አንቀጽ 1፣ በህገመንግስቱ ለፌደራል መንግስት በተለይ
ለፌደራል መንግስቱና ለክልሎች በጋራ በግልጽ ያልተሰጠ ስልጣን የክልል ስልጣን የሆናል ይላል። በህገመንግስቱ መሰረት የፌደራል መንግስት የራሱን የስልጣንና ተግባር ገደብ አልፎ በክልል መንግስታ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ የመግባት ስልጣን
አይኖረውም። የክልል መንግስታትም በፌደራል መንግስቱ ስልጣን ውስጥ ጣልቃ አይገቡም። ክለሎች ደግሞ በፌደራል መንግስት ውስጥ በውክልና ደረጃ ካላቸው የስልጣን ድርሻ ውጭ አንዱ በሌላው ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንዲገቡ ማድረግ
የሚያስችላቸው አንዳችም ህገመንግስታዊ አግባብ የለም። የሁሉም ክልሎች ስልጣን በክልላቸው ውስጥ የተገደበ ነው።
ህገመንግስቱ በአንቀጽ 50 የሥልጣን አካላት አወቃቀር በሚል ርዕስ ስር በተራ ቁጥር 8 ላይ፣ የፌደራሉ መንግስትና የክልሎች ሥልጣን በዚህ ህገመንግስት ተወስኗል። ለፌደራል መንግስት የተሰጠው ስልጣን በክልሎች መከበር አለበት።
ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በፌደራል መንግስት መከበር አለበት ይላል።
እርግጥ በክልሎች መሃከል በተለይ በተዋሳኝ ክልሎች መሃከል ያለመግባባት ሊፈጠር ይችላል። እንደችግሩ አያያዝ ሁኔታ ይህ አለመግባባት ወደግጭት ሊያመራ የሚችልበት ሁኔታም አለ። ከዚህ በተጨማሪ ክልል ተሻጋሪ የሆኑ ሁለትና ከዚያ
በላይ የሆኑ ክልሎች የሚጋራቸው ወንዞች ሊኖሩ ይችላሉ። ከክልል ተሻጋሪ ወንዞች የውሃ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ በክለሎች መሃከል የይገባኛል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። በዚህ አይነት በክልሎች መሃከል የሚፈጠሩ አለመገባባቶችንና የተፈጥሮ
ሃብት አጠቃቀምን በተመለከተ የመዳኘትና ስርአት የማስያዝ ስልጣን የፌደራል መንግስት ነው።
የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጥ 48፣ የአከላለል ለውጦች በሚል ርዕሰ ስር፤ በንኡስ አንቀጽ 1 ላይ፣ የክልሎችን ወሰን በሚመለከት ጥያቄ የተነሳ እንደሆነ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች ስምምነት ይፈጠራል። የሚመለከታቸው ክልሎች
መሰማማት ካልቻሉ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት የህዝብ አሰፋፈርና ፍላጎት መሰረት በማድረግ ይወሰናል ይላል።
የፌደራል መንግስትን ስልጣን በተመለከተ በአንቀጽ 51 “የፌደራል መንግስት ሥልጣንና ተግባር” በሚል ርዕስ ስር የፌደራል መንግስቱ ከክልሎች ጋር በተገናኘ ያለውን ስልጣን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ሰፍረዋል። እነዚህም በንኡስ አንቀጽ 12፣
13 እና 14 ላይ የሰፈሩ ናቸው።
ንኡስ አንቀጽ 12፤ የፌደራል መንግስት በክልሎች መሃከል የሚደረግን የንግድ ግንኙነትና የውጭ ንግድን ይመራል፤ ይቆጣጣራል ይላል። ንኡስ አንቀጽ 13፤ በፌደራል መንግስት ገንዘብ የተቋቋሙ ከአንድ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚሸፍኑ
የአገልግሎት ተቋማትን ያስተዳድራል፤ ይመራል ይላል። ንኡስ አንቀጽ 14፤ ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሰረት የሃገሪቱ የመከላከያ ሃይል ይሰማራል ይላል።
ከዚህ በተጨማሪ የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር በሚወስነው አንቀጽ 62 ንኡስ አንቀጽ 3፣ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብትን በተመለከተ በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በህገመንግስቱ
መሰረት ይወሰናል ይላል። የዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 6 ደግሞ በክልሎች መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ ይፈልጋል ይላል።
በኢፌዴሪ ህገመንግስት መሰረት በፌደራል መንግስቱና በክልል መንግስታት መሃከል ያለው ግንኙነት ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረት የተወሰነ ነው። ከዚህ ባሻገር በሥልጣን ደረጃ አንዱ ክልል በሌላ ክልል ወይም በሌሎች ክልሎች ጉዳይ
ጣልቃ መግባት የሚያስችለው አንዳችም ህገመንግስታዊ ድንጋጌ የለም። ሃገሪቱ በኢፌዴሪ ህገመንግስት መሰረት በፌደራላዊ ሥርአት በተዳደርባቸው ያለፉ ሃያ ሶስት ዓመታት ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በክልሎች መሃከል በተለይ
ከወሰን ጋር በተያያዘ አለመግባባት ሲፈጠር፣ ከክልሎች የሰላም አስከባሪ ሃይል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ችግር ሲያጋጥም በክልሎቹ ጥያቄ ካልሆነ በስተቀር የክልል መንግስታት ክልላቸውን ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሲያስተዳድሩ
ቆይተዋል።
በዚህ ረገድ ችግር አለ ቢባል እንኳን፣ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይሆን የፌደራሉን መንግስት ጣልቃ ገብነት በሚሹ በሁለት ክልሎች የወሰን አለመግባባትና መሰል ችግሮች ላይ የፌደራል መንግስቱ ሃላፊነቱን በአግባቡ ያለመወጣት
ችግር ነው የተስተዋለው። ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል መንግስት ክልል አቋራጭ የሆኑ ወንዞች ውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ እስካሁን በህገመንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ግልጽ ፖሊሲ አላዘጋጀም። ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በየዓመቱ
እያደገ ከመጣው የመስኖ እርሻ ጋር ተያይዞ ያለመግባባት መንስኤ መሆኑ አይቀሬ ነው። በአዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ላይቀሰቅስ የሚችልበት ምክንያትም የለም።
በአጠቃላይ የኤፌዴሪ ሥርአት እውነታ ከላይ የተገለጸውን ይመስላል። የፌደራልና የክልል ሥልጣን በህገመንግስቱ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ ሁለቱም የሥልጣን አካላት ተጠያቂ የሚሆኑት በሥልጣናቸው ገደብ ውስጥ ብቻ ነው። የክልል
መንግስታት በህገመንግስቱ የተሰጣቸውን እንዲሁም በክልላዊ ህገመንግስታቸው ላይ የተሰጣቸውን ሥልጣን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ለሚፈጠር ችግር የፌደራል መንግሰት ተጠያቂ ሊሆን ይችልም።
ይሁን እንጂ በዚህ ዙሪያ መደበላለቆች ይታያሉ። አንዳንንድ ችግሮች ከክልላዊ መንግስታት አፈጻጸም ችግር የመነጩ ሆነው ሳለ፣ የፌደራል መንግሰቱ የሚወቀስበት ሁኔታ ይታያል። እርግጥ ከላይ እንደተገለጸው በተለይ በክልሎች መሃከል
ከተፈጠረ አለመግባባት ጋር በተያያዘ የፌደራል መንግስት ሃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ክፍተቶች የታዩበት መሆኑ ባይካድም፣ የፌደራል መንግስቱ በህገመንግስት ለክልሎች በተሰጠ የስልጣን ገደብ ውስጥ ጣልቃ የገባባት ሁኔታ የለም።
ይህ ብቻ አይደለም፤ በአንዳንድ አጋጣሚዎች በአንድ ክልል ውስጥ ለሚፈጠር ችግር ሌላ ክልልን ተጠያቂ ለማድረግ የመሞከር ሁኔታም ይታያል። ለምሳሌ አማራ ክልል ወይም ኦሮሚያ ውስጥ ለሚፈጠር ችግር የትግራይ ክልልን ለማስተዳደር
በትግራይ ህዝብ የተወከለውን ህወሃት የመውቀስ ሁኔታ የተለመደ ነው። ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልሎች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚሰሙት የትግራይ ህዝብ ይበጀኛል ብሎ የመረጠውን ህወሃት ላይ የሚሰማውን ወያኔ ይውረድ የሚል የተለመደ
መፈክር ለዚህ አስረጂነት መጥቀስ ይቻላል። ይህ ተገቢ ያልሆነ ደርግ ተክሎት የሄደው በሽታ ነው። ሞኝና ወረቀት የያዘውን አይለቅም እንዲሉ አንዳንድ የዋሆች፣ ነገሮች ተለዋውጠው ባለበት ሁኔታም ያንኑ የደርግ ዘፈን ሲያዜሙ ይሰማሉ።
እርግጥ የብሄር ጥላቻ ለመቀስቀስ ሆን በለው ይህን የሚያደጉ ቡድኖች መኖራቸው ይታወቃል። የአብዛኛው ግን ካለማወቅ የመነጨ ነው። በመሰረቱ እንኳን የትግራይ ክልላዊ መንግስት የፌደራል መንግስቱም ቢሆን በህገመንግስት ከተሰጠው
ስልጣን ውጭ በክልል መንግስታት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት አይችልም። እስካሁን ይህ የሆነበት ተጨባጭ ሁኔታም የለም።
ይህ በክልሎች ውስጥ፣ ከክልላዊ መንግስቱ ስልጣንና ተግባር አፈጻጸም ለሚፈጠር ችግር የፌደራል መንግስቱን ወይም ሌላ በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ ሊገባ የሚችልበት ምንም ሥልጣን የሌለውን አካል ተጠያቂ የማድረግ አካሄድ ለችግሮች
መፍትሄ ማምጣት አይችልም። ከዚሀ በተጨማሪ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ህገመንግስታዊ ሥርአቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁከት ለመቀስቀስ ውዥንብር መንዛት ለሚፈልጉ ቡድኖች አመቺ እድል ይፈጥራል። እናም ተጠያቂነት በህገመንግስቱ በተሰጡ
ሥልጣኖችና ተግባሮች ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል።

https://waltainfo.com/am/48816/ 1/1

You might also like