Professional Documents
Culture Documents
የወተት ላም በ2010 ዓ.ም የተሰራ
የወተት ላም በ2010 ዓ.ም የተሰራ
(ሞዴል)
ቀን------------
0
1- የንግድ ስራ ዕቅዱ ማጠቃለያ/ጭብጥ-Excutive Summery:-
ይህ የወተት ከብት እርባታ ፓኬጅ ዕቅድ አምስት አባላትን በመያዝ(ወንድ 3 ሴት 2) በአነስተኛ ንግድ ስራ ኢንርፕራይዝ በፍላጎታቸው
ተመራርጠው በተደራጁ ወጣቶች የተመሰረተ ሲሆን ከአካባቢው ዝሪያ ጋር ተዳቅለው 75% ጄነቲክ-ሜክ-አፕ ያላቸውን አምስት
ዲቃላ የወተት ጊደሮች በመያዝ በምርቱ ተጠቃሚ ለመሆን የተዘጋጀ ዕቅድ ነው፡፡የኢንተርፕራይዙ ባለቤት ወጣቶች ስራውን
በዕውቀትና በክህሎት መምራት የሚያስችላቸውን የንድፈ-ሃሳብና የክህሎት ስልጠና በወተት ከብት አያያዝ የተሰጣቸው በመሆኑ
ስራው በወጣቶቹ ዘንድ አጓጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስራው ዘመናዊ አመራረትን የሚጠይቅ ከመሆኑ የተነሳ በገበያው ላይ ብርቱ ተወዳደሪ
ለመሆን የሚያበቃ የስራ ላይ ስልጠናው በባለሙያዎች በተካታታይ ይሰጣል፤፡፡ በተጨማሪም አካባቢው ለወተት ከብት እርባታ አመቺ
ከመሆኑም ሌላ የአካባቢው ቀበሌ አስተዳደር ለመስሪያ የሚሆን የለማ ተፋሰስ መሬት በድጋፍ የሚያቀርብ ሲሆን ሌሎች የመሠረተ-
ልማት ምቹ ሁኔታዎች ፓኬጁን በአስተማማኝነት አዋጭ ያደርገዋል፡፡
የኢንተርፕራይዙ አባላት ስራውን ለመጀመር በቅድሚያ የመነሻ ካፒታሉን 10% ብር 17,404 እንዲቆጠብና በዋስትና እንዲያዝ ተደርጎ
ተፈላጊውን የብድር መጠን ብር 174,040 ከኦሞ-ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በማግኘት በወተት ከብት እርባታ ተግባር ይሰማራሉ፡፡
በኢንተርፕራይዙ ዕቅድ መሰረት በዓመት 23,870 ሊትር ወተት በመሸጥ በአመት የተጣራ ትርፍ ብር 236,715.3 ለማግኘት
ታቅዷል፡፡ በአመቱ የተገኘው ትርፍ ለእያንዳንዱ ወጣት ሲከፋፈል ደግሞ ለአንድ አባል በአመት ብር 47,343.06 ወይንም በየወሩ ብር
3,945.25 በማግኘት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡በሌላ በኩል በአመቱ ከተገኘው ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ ብር
71,014.59 ተቀንሶ በመጠባበቂያ ካፒታልነት እንዲመደብ በማድረግ የቀጣይ አመት ኢንቬስትመንቱ የበለጠ እንዲሰፋ ይደረጋል፣
በዚህ አጋጣሚ የቁጠባ ባህሉም እየተሸሻለ ኢንተርፕራይዙ በራሱ ካፒታል የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተግቶ ይሰራል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ዕዳውን በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ በመክፈል ትርፋማ ሆኖ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የስራ ፈጠራው ተግባር በሂደት
የወጣቶችን የቁጠባ ባህል ከማሳደጉ ጎን ለጎን ለሌሎች ሰዎች የስራ ዕድል በመፍጠር የገጠር የትራንስፎርሜሽን ሂደትን እውን
ይደረጋል፡፡
1
ከተመረጡ ከአካባቢ ላሞች ጋር ተዳቅለው የተገኙ 75% ጄኔቲክ ሜክ-አፕ ያላቸው 5 የሆሊስቲን ፍሬዥያን የወተት ዝሪያ
ላሞችን በመያዝ ከአንዷ ላም በቀን 14 ሊትር ወተት በዓመት በ 341 ቀናት 4,774 ሊትር ወተት በማግኘት ከ 5 ላሞች
23,870 ሊትር የወተት ምርት ማግኘት፡፡
ለሥራው የመነሻ ካፒታል 100% ከመንግስት ብድር የተመቻቸ ሲሆን እንቴርፕራይዙ ከኦሞ-ማይክሮ ፋይናንስ
ተቋም ብድሩን ለማግኘት 10% በተቋሙ አካውንት ቆጥቧል፤ይህን መነሻ ካፒታል በመጠቀም ከኢንቨስትመንቱ
የሚገኘውን ገቢ በማሳደግ በቀጣይ ኢንተርፕራይዙ በራሱ ካፒታል የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
አባላቱም በየአመቱ ከእንቴርፕራይዙ የሚያገኙት ገቢ አስተማማኝ ስለሚሆን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው
የጎላ ነው፡፡ በተጨማሪ ስራው እየሰፋ ስለሚሄድ በአካባቢው ላሉ ሰዎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለድህነት
ቅነሳው የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፤
ፓኬጁ በአካባቢው የወተት ከብት ዝሪያዎች ከገበያ በሚገኝበት ተጠንቶ በወጣቶቹ ምርጫ መሠረት ስለሚተገበር
በግብኣት በአቅርቦቱ ላይ የሚፈጠር ችግር የለም፡፡ከክልሉ የመንግስት እርባታ ጣቢያዎችም ሲገኝ ቀድሚያ
ለወጣቶች ይሰጣል፡
በወተት ከብት እርባታ የኢንተርፕራዙ አባላት በቅድሚያ በሥራ አጥ መመልመያ መስፈርት መሰረት የመሥራት አቅምና የሥራ
ፍላጎታቸው ያላቸው ብቻ ተለይተው እንዲደራጁበት የተደረገ በመሆኑ ወጣቶቹ በስራ ፈጠራ የቁርጠኝነት መንፈስ ያላአው ሲሆን
ራሳቸውን ለመለወጥ በሚያደርጉትም ጥረት ለስራው አጋዥ የሚሆኑ ተጨማሪ የአቅም ግንባታ ስልጠና በእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት
ቢሮ በኩል የሚገኝበት-ሁኔታ አስተማማኝ ነው፤በተጨማሪም በአካባቢው በመልካም ተሞክሮነት የተቀመሩ ተግባራትን በልምድ
ልውውጥ በማግኘት ስራው እንዲጠናከር ይደረጋል፡፡ ከዚህ ባሻገር የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚረዳ በሁሉም አባላት የጸደቀ
2
ጠንካራ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቷል፤ በተጨማሪም አዳዲስ የአሰራር ስልትና የአመለካከት ለውጥ በማድረግ በየጊዜው የህብረት
ስራውን የሚያጎለብቱ ምክክሮችና የስራ ግማገማዎች ይደረጋሉ፤
የቢዝነሱን አዋጭነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ በርካታ የአሰራር ስልቶች የሚቀየሱ ሲሆን በተለይ በየጊዜው ተፈላጊ የሆነውን
ጥራት ያለው ንጹህ ወተት ማምረት እንዲቻል ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የቴክኒክ ይዘቱ በክህሎት
የሚታገዝና በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀርብ የሚደረግ ሲሆን ለስራው የሚያስፈልጉትን ወጪዎች በፋይናንስ ስታንዳርድ
ዕውቀት፣መሰረትእንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የገቢና ወጪ ማነጻጸሪያዎችን ተከታትሎ በአግባቡ በመስራት የትርፍ ምጣኔው
ታንዳርዱን በጠበቀ ሁኔታ (ከ 30% በላይ) እንዲሆን ይደረጋል፤
በአካባቢው የሚገኙ የገጠርና የከተማ ማህበረሰብ ክፍሎችን የገበያ ደንበኛ አድርጎ በመነሳት እንደ ተጠቃሚዎቹ ፍላጎት ወተት
እንዲመረትና እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
ኢንቴርፕራይዙ፣የገጠር፣ግብርና፣ትንስፎርሜሽንን፣ማዕከል፣ያደረገ፣እንቬስትመንት፣ከመሆኑም፣በተጨማሪ ስራ አጥ ወጣቶችን ስራ
ፈጣሪ ለማድረግ ተግባሩ በመንግስት በኩል፣ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በቢሊዬን የሚቆጠር ፈንድ ተመድቧል፡፡በመሆኑም ወጣቶቹ፣አቅደው
ለሚያከናውኑት ተግባር በፌደራልና በክልል ደረጃ ከተቀረጹት ፖሊሲዎች፤ ስትራቴጅዎች፤ አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በእጅጉ
የሚጣጣም ነው፤
ኢንተርፕራይዙ አምስት አባላትን በማቀፍ ህጋዊነት ያለው አደረጃጀት ሲሆን መዋቅራዊ ድርጅቱም በተለያዩ ተመራጭ
ኮሚቴዎች የሚመራ ነው፡፡ በመዋቅሩ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በመባል በሚታወቀው የጠቅላላ አባላት የጋራ ውሳኔ መሰረት
መተዳደሪያ ደንቡን በማዘጋጀት የኢንተርፕራይዙ ድርጅታዊ መዋቅር በህግ ማዕቀፍ እንዲታገዝ ተደርጓል፡፡ በመሆኑ በህገ-ደንቡ
መሰረት የኢንተርፕራይዙ መዋቅር ስራ እፈጻሚ ኮሚቴ(ከ 3-5 አባላት ማለትም ሰብሳቢ፤ፀሃፊና ሂሳብ ሹም እና ገንዘብ
ያዥ)፤ቁጥጥር ኮሚቴና እንደአስፈላጊነቱ ጥቂት የቅጥር ሰራተኞች እንደሚኖሩት ተደርጎ ሥራው በአመራሩና በአብዛኛው
በአባላቱ ዕውቀትና ጉልበት ይከናወናል፡፡የእያንዳንዱ ተመራጭ አባልና ቅጥር ሰራተኛ የስራ ሃላፊነት በህገ ደንቡ ላይ
እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
ጠቅላላ አባላት(5)
ጠቅላላ አባላት(5)
ቁጥጥር ኮሚቴ(2)
ሥራ ኣፈጻሚ ኮሚቴ(3)
ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተው የድርጊት መረሃ-ግብር የሚያመለክት ሲሆን የድርጊት መረሃ-ግበሩ የየአካካቢውን
ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት በማድረግ መተግበር ይኖርበታል፡፡
4
ለጽ/ቤት ቋሚ ዕቃዎች የሚያስፈልግ ወጪ
የምርት/የአገልግሎት ጥሬ ዕቃዎች ግዥ
êU
2 ( ( ( ( ( (
ጠቅላላ ዋጋ 110,000
1 በጥቅል - - 100
የጽህፈት መሣሪያ
ድምር 1,150
2 የማምረቻወጪዎች 149,200
3 ተዛማጅ ወጪዎች 1150
ጠቅላላ የሚያስፈልግ ካፒታል 174,040 ወለድና ዕርጅና አልተደመረም፤ ብድር
ስለማይጠየቅበት
t.q$ êU MRm‰
7
ተ.ቁ ጠቅላላ ሐብት/ንብረት- ጠ/ዕዳና ካፒታል
1 ጊዚያዊ ንብረት - 3 የዕዳ መጠን
1.1.1 ጥሬ ገንዘብ በእጅ 1,000 3.1 የተዘዋዋሪ ብድር ተከፋይ ዕዳ 174,040
1.1.2 ጥሬ ገንዘብ በባንክ 432,140 3.2 ለመንግስትየሚከፈል የገቢ ግብር 26,301.7
1.1.3 ጥሬ ገንዘብ በሰነድ 3.3 ለአባላትየሚከፋፈል ትርፍ(70%) 165,701
የጠ/ዕዳ ድምር 366,042.41
1.1.4 በመጋዘንያለ ምርት/ያልተሸጠ ካፒታል
1.1.5 ያልተሰበሰበ ገንዘብ 4.1 የአባላት መዋጮ/ዕጣ 17,404
1.1.6 የጊዚያዊ ንብረት ድምር 4.2 በስጦታ የተገኘ ንብረት 0
2 ቋሚ ንብረት 4.3 ከትርፍ መጠባበቂያ ካፒታል 71,014.8
2.1 የንብረት ዋጋ 23,690 -
2.2 ሲቀነስ የእርጅና ታናሸ 2,369 - -
2.1 የዘመኑየተጣራ የንብረት ዋጋ 21,321 4.4 የካፒታል ድምር 84,418.59
2.2 ጠቅላላ የንብረት ዋጋ ድምር 454,461 5 ጠ/የዕዳና የካፒታል ድምር 454,461