መልክዐ_አቡነ_አቢብ_እና_ማሕልየ_መሓልይ_ማሳያ_የሚሆን_

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 19

መልክዐ አቡነ አቢብ (ዘአኅተሞ ገብረ ሥላሴ)

መልክዐ አቡነ አቢብ-ግዕዝ የአቡነ አቢብ መልክዕ በአማርኛ

፩. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ 1. ባሕርይው ተመርምሮ ፈጽሞ የማይታወቅ በአካል


አሐዱ አምላክ ሠለስቱ፤ ዘባሕርይክሙ ሦስት በመለኮት አንድ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ
ዋሕድ ዘኢይጤየቅ ጥንተ ኵነቱ፤ ጽልመተ ቅዱስ ስም አባታችንና ወዳጃችን የሆነ የአቢብን
አርምሞ ጽፉቀ እምልሳንየ ያእትቱ፤ ለአቢብ ተኣምሩን እመሰክርና እገዛለት ዘንድ የከበደ የዝምታ
አበ ኵልነ ወለፍቁርነ ውእቱ፤ ከመ ዜናሁ ጨለማን ከአንደበቴ ያስወግድ፡፡
እትናገር ወእትቀነይ ሎቱ፡፡
2. ለዝክረ ስምከ፡- በወሬ ለአልተገኘ ለጥቁር ጠጒርህ
፪. ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘያስተፌሥሕ ኅሊና፤ እና ኅሊናን ለሚያስደስት ለስምህ መታሰቢያ ሰላምታ
ወለሥዕርትከ ጸሊም ዘኢተረክበ በዜና፤ ይገባል፤ የማስተዋልና የጥበብ ሰው አብርሃም አቢብ
አቢብ አብርሃም ብእሴ ጥበብ ወልቡና፤ ሆይ! አምላክን በሲና በቃል ያደነቀው የዮና ልጅ
ያስተበጽዐከ ልሳነ ጴጥሮስ ዘዮና፤ እንተ የጴጥሮስ አንደበት ያደንቅሃል፡፡
አስተብጽዖ በቃል ለአምላክ በሲና፡፡
3. ለርእስከ፡- ንጹሕ የሃይማኖት መጐናጸፊያን
፫. ሰላም ለርእስከ ወለገጽከ ብሩህ፤ ዘወትር ለተጐናጸፈ ለሚያበራ ፊትህና ለራስህ
ዘይትቈጸል ዘልፈ ቀጸላ ሃይማኖት ንጹሕ፤ ሰላምታ ይገባል፤ የየዋህ በግ ማኅተም ይሥሐቅ
አቢብ ይሥሐቅ ማኅተመ በግዕ የዋህ፤ አቢብ ሆይ! ከአውሬ ዘወትር ትጠብቀኝ ዘንድ በበዛ
ተማሕፀንኩ በጸሎትከ ወበጾምከ ብዙኅ፤ ከመ ጸሎትህና ጾምህ ተማፀንሁ፡፡
ትዕቀበኒ ዘልፈ እምአርዌ ቀይሕ፡፡
4. ለቀራንብቲከ፡- የሦስቱ ብርሃናት ምሳሌ ለሆኑ
፬. ሰላም ለቀራንብቲከ ዘኢቀነዮን ድቃስ፤ ዐይኖችህ እና እንቅልፍ ለአልገዛቸው ቅንድቦችህ
ወለአዕይንቲከ ሰላም አርአያ ብርሃናት ሠላስ፤ ሰላምታ ይገባል፤ ክርስቶስ የመረጠህ ያዕቆብ አቢብ
አቢብ ያዕቆብ ዘኀረየከ ክርስቶስ፤ ታዕድወኒ ሆይ! ነፍስ ከከበበው ደዌ ባሕር ወደ ረድኤትህ ዳርቻ
እስእለከ በረድኤትከ አድማስ፤ እምባሕረ ደዌ ታሻግረኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡
ዘዐውዱ ነፋስ፡፡
5. ለአእዛኒከ፡- ዕንባን ለታገሠ ጒንጭህ እና
፭. ሰላም ለአእዛኒከ ትእዛዘ አምላክ ዘሰምዐ፤ የአምላክን ትእዛዝ ለሰማ ጆሮህ ሰላምታ ይገባል፤
ወለመላትሒከ ሰላም ዘተዐገሠ አንብዐ፤ ሥርዐትህ የተደነቀ መልከ ጼዴቅ አቢብ ሆይ! የበደል
መልከ ጼዴቅ አቢብ ዘሥርዐትከ ተበጽዐ፤ ሰው ጠላቴ በእኔ ላይ በተነሣ ጊዜ ለማዳን ወደ እኔ
ፀርየ ብእሴ ዐመፃ አመ ላዕሌየ ተንሥአ፤ ና፡፡
ለአድኅኖትየ መንገሌየ ነዐ፡፡
6. ለአእናፊከ፡- ከማርያም እንቦሳ ጋር መልካም
፮. ሰላም ለአእናፊከ አፈዋተ ዓለም መዐዛን ያሸትቱ ዘንድ የዓለምን መዐዛ ለአላሸተቱ
ኢያጼነዋ፤ ከመ ያጼንዋ አፈዋተ ምስለ አፍንጫዎችህ ሰላምታ ይገባል፤ ሙሴ የተባልህ
ማርያም ጣዕዋ፤ አቢብ ሙሴ አስተበቍዐከ አቢብ ሆይ! ከሞት ማሰሪያና ከጠላት ሰይጣን

1
ነዋ፤ እማእሰረ ሞት ለሕይወትየ ታሕይዋ፤ ወጥመድ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እነሆ እማልድሃለሁ፡
ወእመሥገርቱ ለሰይጣን እድዋ፡፡ ፡

፯. ሰላም ለከናፍሪከ ኅብረ ቀይሕ ሮማን፤ 7. ለከናፍሪከ፡- የመድኅን ክርስቶስ ኢየሱስን


ወለአፉከ ነባቢ ትምህርተ ኢየሱስ መድኅን፤ ትምህርት ለተናገረ አፍህ እና ቀይ ሮማንን ለመሰለ
አቢብ አሮን ምክሐ ቤተ ሌዊ ካህን፤ ይሰወጥ ከንፈርህ ሰላምታ ይገባል፤ የካህን ሌዊ ወገን
ውስተ ልብየ ቃለ ፍሥሓከ ወይን፤ መመኪያ አሮን አቢብ ሆይ! ገዥ ኀዘን እንዳይገዛኝ
ኢይኰንነኒ መኰንን ኀዘን፡፡ የደስታህ ቃል ወይን በልቤ ውስጥ ይጨመር፡፡

፰. ሰላም ለአስናኒከ ዘኅበሪሆን ጽዕድው፤ 8. ለአስናኒከ፡- በክርስቶስ ትምህርት ጨው ለጣፈጠ


ወለልሳንከ ቅሱም በትምህርተ ክርስቶስ አንደበትህና መልካቸው ለነጣ ጥርሶችህ ሰላምታ
ጼው፤ አቢብ ኤልያስ ሥርግወ ድንጋሌ ይገባል፤ የአመረ ድንግልናን የተዋብህ ኤልያስ አቢብ
ቅድው፤ ይሰወጥ ለለጽባሑ ውስተ ልብየ ሆይ! ይኸውም ሽቱ የሆነ የደስታህ ቃል በየቀኑ ወደ
ማኅው፤ ቃለ ፍሥሐከ ዘውእቱ አፈው፡፡ ልቤ ብርሌ ይጨመር፡፡

፱. ሰላም ለቃልከ ድምፀ መንፈስ ቅዱስ 9. ለቃልከ፡- የጥበብ በር በሩ ለሆነ እስትንፋስህ እና


ድምፁ፤ ወለእስትንፋስከ ሰላም ዘአንቀጸ የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ድምፁ ለሆነ ቃልህ ሰላምታ
ጥበብ አንቀጹ፤ አቢብ ብፁዕ ለኤልሳዕ ቢጹ፤ ይገባል፤ የኤልያስ ወዳጅ ብፁዕ አቢብ ሆይ! በፍቅርህ
በመዐዛ ፍቅርከ እስመ ሕዋሳትየ ሮጹ፤ መዐዛ ሕዋሳቶቼ ሩጠዋልና ፊቱ ከሚያስፈራ ጠላቴ
ዕቀበኒ እምፀርየ ዘመፍርህ ገጹ፡፡ ጠብቀኝ፡፡

፲. ሰላም ለጕርዔከ ወይነ መንፈስ ቅዱስ 10. ለጕርዔከ፡- ከትከሻ ላይ ለተቈረጠ አንገትህ እና
ዘአጥለለ፤ ወለክሣድከ ሰላም ዘዲበ በመንፈስ ቅዱስ ወይን ለለመለመ ጒሮሮህ ሰላምታ
መታክፍት ተከለለ፤ አቢብ ሳሙኤል አምጣነ ይገባል፤ ሳሙኤል የተባልህ አቢብ ሆይ! ኀይልን
ለበስከ ኀይለ፤ ለጻሕቀ ልብየ እስእለከ ለብሰሃልና ምሕረትንና ይቅርታን ለእኔ ትለምን
ስኢለ፤ ከመ ትስአል ሊተ ምሕረተ ወሣህለ፡፡ ዘንድ በልቤ ትጋት መለመንን እለምንሃለሁ፡፡

፲፩. ሰላም ለመታክፍቲከ አርዑተ መስቀል 11. ለመታክፍቲከ፡- ከኪሩቤል ጀርባ ይልቅ
እለ ፆራ፤ ወለዘባንከ ሰላም እምዘባነ ኪሩብ ለምናከብራት ጀርባህ እና የመስቀል ቀንበርን
ዘናከብራ፤ አቢብ ኤርምያስ ወነቢየ ጽድቅ ለተሸከሙ ትከሻዎችህ ሰላምታ ይገባል፤ የእውነት
ዕዝራ፤ በፍኖተ ጽድቅ አእጋርየ ይሑራ፤ ነቢይ ዕዝራና ኤርምያስ አቢብ ሆይ! በእውነት ጎዳና
ዕቀበኒ ዘልፈ እምብዙኅ መከራ፡፡ እግሮቼ ይጓዙ ዘንድ ዘወትር ከብዙ መከራ ጠብቀኝ፡፡

፲፪. ሰላም ለእንግድዓከ ምርፋቀ ኢየሱስ 12. ለእንግድዓከ፡- የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለሆነ
ክርስቶስ፤ ወለሕንፅከ ሰላም ማኅደረ መንፈስ ጭንህ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ማረፊያ ለሆነ ደረትህ
ቅዱስ፤ አቢብ ሰላማ ዘግዕዝከ ውዱስ፤ ሰላምታ ይገባል፤ ማንነትህ የተመሰገነ ሰላማ አቢብ
ለዳዊት ሰብዕናየ ኢይዳደቆ እንኩስ፤ ሆይ! ዳዊት ሰውነቴን እንኩስ እንዳይጣለው በዐዲስ
አስተበቍዐከ አነ በልሳን ሐዲስ፡፡ አንደበት እማልድሃለሁ፡፡

2
፲፫. ሰላም ለአእዳዊከ ፈውሰ ሕሙማን 13. ለአእዳዊከ፡- የተለዩትን ለገዛ መከንጃህና
ዘጵሩጳጥቄ፤ ለመዛርዒከ ሰላም እንተ ኰነኑ የይቅርታ ቤት የሕመምተኞች ፈውስ ለሆኑ እጆችህ
ፈራቄ፤ አቢብ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላምታ ይገባል፤ የተሰሎንቄ ሐዋርያ ጳውሎስና
ዘተሰሎንቄ፤ ባልሐኒ በረድኤትከ እምከርሠ ጴጥሮስ የተባልህ አቢብ ሆይ! ማንነቱ ጥርጥር ልብሱ
ሰይጣን አንቄ፤ ዘልብሱ ዕበድ ወግዕዙ ኑፋቄ፡ ስንፍና ከሆነ ከጠላት ሰይጣን ሆድ በረድኤትህ
፡ አድነኝ፡፡

፲፬. ሰላም ለኰርናዕከ ኵርናዓ ያኖስ ክቡድ፤ 14. ለኰርናዕከ፡- የተወደደውን ትእዛዝ ለምትለካ
ወለእመትከ ሰላም መሥፈርተ ትእዛዝ ክንድህ እና እንደ ያኖስ ክርን ለከበደ ክርንህ ሰላምታ
መፍቅድ፤ አቢብ እንድርያስ ዕብነ ሕይወት ይገባል፤ እንድርያስ የተባልህ የሕይወት ድንጋይ
መረግድ፤ ኅብአኒ ወሠውረኒ በረድኤትከ ዕንቊ አቢብ ሆይ! የግፍ የመከራ ነፋስ በዐደባባይ
ማኅፈድ፤ ነፋሰ መከራ ጽኑዕ ሶበ ይነፍሕ በነፈሰ ጊዜ በረድኤትህ አዳራሽ ሠውረህ ሸሽገኝ፡፡
በዐውድ፡፡
15. ለእራኅከ፡- በብራና ውስጥ ትእዛዝን ለጻፉ
፲፭. ሰላም ለእራኅከ ለወይነ ምሕረት ጣቶችህ እና ለምሕረት ወገን አውድማ ለሆነ መሐል
ምክያዳ፤ ወለአጻብዒከ ሰላም ጸሐፌ ትእዛዝ እጅህ ሰላምታ ይገባል፤ የስንፍናን ጨለማ
ውስተ ሰሌዳ፤ አቢብ ፊልጶስ ለጽልመተ የምታስወግድ ፊልጶስ አቢብ ሆይ! በደለኛ ይሁዳን
ዕበድ ዘትሰድዳ፤ አሰስል እምላዕሌየ ዘልብሰ ያለበሰችው የመርገምን ልብስ ከእኔ አርቅልኝ፡፡
መርገም አነዳ፤ ዘከደነቶ ለጊጒያ ይሁዳ፡፡
16. ለአጽፋረ እዴከ፡- የቀና ሃይማኖትን ለተጐናጸፈ
፲፮. ሰላም ለአጽፋረ እዴከ ፍቅደ ሳድስ ጐንህ እና በቊጥር ዐሥር ለሆኑ ለእጅህ ጥፍሮች
ወርብዕ፤ ወለገቦከ ሰላም ዑጹፈ ሃይማኖት ሰላምታ ይገባል፤ ሰማዕትነትንና መከራን የታገሥህ
ርቱዕ፤ አቢብ ያዕቆብ ዕጉሠ ገድል ወስምዕ፤ ያዕቆብ አቢብ ሆይ! ከአንበሳ ረኀብና ከተኵላ ጥማት
ኢይምስጡኒ እስእለከ ለጽሙድከ በግዕ፤ የተነሳ እኔ በግ አገልጋይህን እንዳይነጥቁኝ
አንበሳ ርኁብ ወተኵላ ጽሙዕ፡፡ እለምንሃለሁ፡፡

፲፯. ሰላም ለከርሥከ ኀይለ ረኀብ ዘኢቀነዮ፤ 17. ለከርሥከ፡- የበቀልን ፊት ለአላየ ልብህ እና
ወለልብከ ሰላም ለገጸ በቀል ዘኢርእዮ፤ ካህነ የረኀብ ኀይል ለአልገዛው ሆድህ ሰላምታ ይገባል፤
አምላክ አቢብ ዘሥርጋዌከ ሎግዮ፤ ለኅጡአ ሽልማትህ ግምጃ የሆነ የአምላክ አገልጋይ አቢብ
ጽድቅ ወልድከ ከመ ታስተስሪ ጌጋዮ፤ ሆይ! ጽድቅን ያጣ ልጅህ በደሉን ታስተሰርይለት
መንገለ ዚኣከ ያወትር ጸልዮ፡፡ ዘንድ ወደ አንተ መለመን ያዘወትራል፡፡

፲፰. ሰላም ለኵልያቲከ በአሥራወ ኂሩት 18. ለኵልያቲከ፡- በጠለቀ የጸሎት ባሕር እነርሱ
ዘተላጸቃ፤ ወተሰምያ እሎን ለባሕረ ጸልዮ የተሰየሙና በቸርነት ጅማት ለተጣበቁ ኵላሊቶችህ
እመቃ፤ ፍቁረ እግዚእ አቢብ ለፀሐየ ጥበብ ሰላምታ ይገባል፤ የጥበብ ፀሐይ መውጫ የጌታ ወዳጅ
ምሥራቃ፤ እስእለከ ኢትኅድገኒ ማዕከለ አቢብ ሆይ! ንስር የወለደችውን ልጇን እንደማትተው
ጽልመት ወጣቃ፤ ከመ ኢትኀድግ ንስር በከባድ ጨለማ መካከል እንዳትተወኝ እለምንሃለሁ፡፡
ዘወለደት ደቂቃ፡፡

3
፲፱. ሰላም ለኅሊናከ ዘይኄሊ ሠናየ፤ 19. ለኅሊናከ፡- በቸርነት እሳት ለነደደ አንጀትህ እና
ወለአማዑቲከ ሰላም በእሳተ ርኅራኄ ዘውዕየ፤ በጐ ነገርን ለሚያስብ ኅሊናህ ሰላምታ ይገባል፤ በጸጋ
አቢብ በጸጋ ዘረሰይኩከ አቡየ፤ ውስተ ጽርሐ አባቴ ያደረግሁህ አቢብ ሆይ! በይቅርታህ አዳራሽ
ሣህልከ ከመ ትትፈጋዕ ልብየ (ነፍስየ)፤ ውስጥ ነፍሴ ትደሰት ዘንድ ነባቢት ነፍሴ
ታስተበቍዐከ ነባቢት ነፍስየ፡፡ ትማልድሃለች፡፡

፳. ሰላም ለንዋየ ውስጥከ ምዕላደ ትእዛዛት 20. ለንዋየ ውስጥከ፡- የመልኩ ደም ግባት ለተለየ
ዐሥር፤ ወለኅንብርትከ ሰላም ዘሥነ ርእየቱ እምብርትህ እና የዐሥሩ ትእዛዛት መገኛ ለሆነ ሆድ
መንክር፤ በርተሎሜዎስ አቢብ ብእሴ ጥበብ ዕቃህ ሰላምታ ይገባል፤ የምክርና የጥበብ ሰው
ወምክር፤ ታዕድወኒ እስእለከ በረድኤትከ በርተሎሜዎስ አቢብ ሆይ! ጣዕሙ መራር ከሆነ
ሐመር፤ እምባሕረ ኀዘን ዕሙቅ ወጣዕሙ ከጥልቅ የኀዘን ባሕር በረድኤትህ መርከብ ታሻግረኝ
መሪር፡፡ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡

፳፩. ሰላም ለሐቌከ ኤፉደ ሃይማኖት ዘቀነተ፤ 21. ለሐቌከ፡- ምስጋናን ለተሸለሙ ጭኖችህ እና
ወለአቍያጺከ ሰላም ዘተረሰያ ስብሐተ፤ የሃይማኖት መታጠቂያን ለታጠቀ ወገብህ ሰላምታ
አቢብ ቶማስ ምስማከ ርእስየ አንተ፤ በጻሕቀ ይገባል፤ ቶማስ የተባልህ አቢብ ሆይ! የራሴ መጠሪያ
ልብየ እስእለከ ስእለተ፤ ከመ ትምርሐኒ አንተ ነህ፤ ወደ ቀና መንገድ ትመራኝ ዘንድ በልቤ
ርቱዐ ፍኖተ፡፡ ትጋት መለመንን እለምንሃለሁ፡፡

፳፪. ሰላም ለአብራኪከ መክሊተ ስግደታት 22. ለአብራኪከ፡- የስብከት አውራጃዎችን ለዞሩ
ዘአፈድፈዳ፤ ወለአእጋሪከ ሰላም አድያማተ እግሮችህ እና የስግደት ገንዘብን ለአበዙ ጒልበቶችህ
ስብከት ዘዖዳ፤ አቢብ ማቴዎስ መምህረ ሰላምታ ይገባል፤ የይሁዳና የብንያም መምህር
ብንያም ወይሁዳ፤ ቅድመ ዕበይከ ተውላጠ ማቴዎስ የተባልህ አቢብ ሆይ! በገናናነትህ ፊት ስለ
ብሩር ጸዐዳ፤ አቀርብ ለከ አምኀ ወጋዳ፡፡ ነጭ ብር ለውጥ እጅ መንሻንና ስጦታን ለአንተ
አቀርባለሁ፡፡
፳፫. ሰላም ለሰኳንዊከ በድካመ ዕበድ
ዘኢድኅፃ፤ ወለመከየድከ ሰላም መርኅበ 23. ለሰኳንዊከ፡- በመከራ የአሸዋ ሜዳ ለተራመደ
ሥቃያት ዘኆፃ፤ አቢብ ታዴዎስ ለሀገረ መረገጫህ እና በስንፍና ድካም ለአልተሰነካከሉ
ጥበብ አንቀጻ፤ ክልለኒ በረድኤትከ ተረከዞችህ ሰላምታ ይገባል፤ የጥበብ ሀገር በር
ኢይንድፉኒ አሕጻ፤ እስመ ለፍቅርከ ሐወፀኒ ታዴዎስ አቢብ ሆይ! የፍቅርህ ድምፅ ጐብኝቶኛልና
ድምፃ፡፡ ጦር እንዳይወጋኝ በረድኤትህ ጋርደኝ፡፡

፳፬. ሰላም ለአእጋሪከ ዘአርአያሆን አዳም፤ 24. ለአእጋሪከ፡- ዳግመኛ ለጥፍሮችህ እና መልካቸው
ዓዲ ፈድፋደ ለአጽፋሪከ ሰላም፤ አቢብ ለአማረ እግሮችህ በእጅጉ ሰላምታ ይገባል፤ መኖሪያህ
ዮሐንስ ዘንብረትከ ገዳም፤ ተማሕፀንኩ በረሓ የሆነ ዮሐንስ አቢብ ሆይ! የሚያስፈራ ነበልባል
በጸሎትከ ወበዘዚኣከ ጾም፤ ከመ ኢያውአየኒ እኔን እንዳያቃጥለኝ በጾምህና በጸሎትህ ተማፀንሁ፡፡
ሊተ ነበልባል ግሩም፡፡

4
፳፭. ሰላም ለቆምከ ከመ ቆመ በቀልት 25. ለቆምከ፡- የከበረ የአብ ልጅ ምሳሌ ለሆነ
ሥሙር፤ ወለመልክዕከ ሰላም አርአያ ወልደ መልክህ እና እንደ ሰሌን ቁመት ለአማረ ቁመትህ
አብ ክቡር፤ ናትናኤል አቢብ ርኡሰ አሐቲ ሰላምታ ይገባል፤ የአንዲት ማኅበር አለቃ ናትናኤል
ማኅበር፤ ሰይጣን መልአከ ሞት ኢይሰደኒ አቢብ ሆይ! መልአከ ሞት ሰይጣን በግድ
በግብር አስተበቍዐከ አቡየ ማእምር፡፡ እንዳይወስደኝ ዐዋቂ አባቴ ሆይ! እማልድሃለሁ፡፡

፳፮. ሰላም ለጸአተ ነፍስከ ከመ ጸአተ ነፍስ 26. ለጸአተ ነፍስከ፡- እግዚአብሔርን እያመሰገነች
አኮ፤ ዳዕሙ ወፅአት ለእግዚአብሔር እንዘ ወጣች እንጂ እንደ ነፍስ መውጣት ላይደለ ለነፋስህ
ትባርኮ፤ አቢብ ኅሩይ ለማትያስ ዘተባየጽኮ፤ መውጣት ሰላምታ ይገባል፤ ማትያስን የተወዳጀኸው
ማዕበል በላዕሌየ አመ ተሐውከ ተሐውኮ፤ የተመረጥህ አቢብ ሆይ! ማዕበል በእኔ መታወክን
የሐድፈኒ ዘለከ ተልእኮ፡፡ ቢታወክ የአንተ አገልግሎት ያሻግረኝ፡፡

፳፯. ሰላም ለበድነ ሥጋከ ዘኢለከፎ ርስሐት፤ 27. ለበድነ ሥጋከ፡- በልዑላን ኀይላት እጅ
ወለግንዘትከ ሰላም በእደ ልዑላን ኀይላት፤ ለመገነዝህ እና መተዳደፍ ለአልነካው ለሥጋህ በድን
ወልደ እልፍዮስ አቢብ ሰባኬ ሐዲስ ሰላምታ ይገባል፤ ዐዲስ ትምህርትን የምታስተምር
ትምህርት፤ ዕቀበኒ ወሠውረኒ እመሥገርተ የእልፍዮስ ልጅ አቢብ ሆይ! ከሞት መርዝ ወጥመድ
ኅምዙ ለሞት፤ ወያስተፍሥሐኒ ዘዚኣከ ሰውረህ ጠብቀኝ፤ ደስታህም ያስደስተኝ፡፡
ትፍሥሕት፡፡
28. ለመቃብሪከ፡- ሁልጊዜ እንሽቀዳደምና በኋላው
፳፰. ሰላም ለመቃብሪከ ዘመዓዛ አፈው እንሮጥ ዘንድ የሽቱ መዐዛ መዐዛው ለሆነ መቃብርህ
መዐዛሁ፤ ንትባደር ዘልፈ ወንረውጽ ሰላምታ ይገባል፤ ብፁዕ አቢብ ሆይ! የፍቅርህ ዜና
በድኅሬሁ፤ አቢብ ብፁዕ ታስተበቍዐከ ናሁ፤ ተሰምቷልና የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ጽርሑ፤ እነሆ ትማልድሃለች፡፡
እስመ ለፍቅርከ ተሰምዐ ዜናሁ፡፡
29. ለቆብዐ ርእስከ፡- የከበረ የመላእክት አስኬማ
፳፱. ሰላም ለቆብዐ ርእስከ ዘኢለከፎ ጌጋይ፤ ለሆነ አስኬማህ እና በደል ለአላገኘው ለራስህ ቆብ
ወለአስኬማከ ሰላም አስኬማ መላእክት ሰላምታ ይገባል፤ የታላቅ ጉባኤ አለቃ ማርቆስ አቢብ
ጽሩይ፤ አቢብ ማርቆስ ርእሰ ጉባዔ ዐባይ፤ ሆይ! በቤቱ ምግብ የለውምና ድኻ ልጅህ
ያስተበቍዐከ ወልድከ ነዳይ፤ እስመ በቤቱ ይማልድሃል፡፡
አልቦቱ ሲሳይ፡፡

ተረፈ መልክዕ
ተረፈ መልክዕ
፴. ሶበ መስቀለ ትዜከር ለለአፈ ኵሉ ጽባሕ፤
እንበለ ምሒክ ትወድቅ መልዕልተ ሰይፍ 30. ሶበ ትዜከር፡- በየጠዋቱ መስቀልን በአሰብህ ጊዜ
በሊሕ፤ አቢብ ሉቃስ ሥርግወ ሃይማኖት በተሳለ ሰይፍ ላይ ያለመራራት ትወድቃለህ፤
ወንጽሕ፤ ኢያስጥመኒ ተማሕፀንኩ በጸሎትከ በሃይማኖትና በንጽሕና የተዋብህ ሉቃስ አቢብ ሆይ!
ብዙኅ፤ ባሕረ ኵነኔ ግሩም ወጥቀ መፍርህ፡፡ እጅግ ፈጽሞ የሚያስፈራ የመከራ ባሕር
እንዳያሰጥመኝ በበዛ ጸሎትህ ተማፀንሁ፡፡

5
፴፩. አርእየኒ ገጸከ ወአስምዐኒ ቃለከ፤ 31. አርእየኒ ገጸከ፡- በትጉህ ኅሊና ልጅህ አንተን
በጻሕቀ ኅሊና ወልድከ ተአሚንየ ኪያከ፤ አምኜ በአቅሜ በጥቂቱ ዜናህን ጨርሻለሁና በምሽት
እስመ በአቅምየ ሕቀ አምጣነ ፈጸምኩ ዋጋውን ይሰጡት ዘንድ የብርቱ ሰው የብርታቱ ልክ
ዜናከ፤ ለጽኑዕ ብእሲ እስመ አቅመ ኀይሉ ወደ እኔ ተልኳልና ፊትህን አሳየኝ፤ ቃልህንም
ተልዕከ፤ ዐስበ ዚኣሁ የሀብዎ ሠርከ፡፡ አሰማኝ፡፡

፴፪. ሰላም ለከ እምአልባበ ኵሉ ልሳን፤ 32. ሰላም ለከ፡- ሰማዕትና ጻድቅ የብዙዎች አባት
አቢብ አንተ አበ ብዙኀን፤ ሰማዕት አቢብ ሆይ! ከኹሉ አንደበት ልብ ማስተዋል የተነሣ
ወጻድቃን፡፡ ሰላምታ ለአንተ ይገባል፡፡

፴፫. ሰላም ለከ አቢብ ሰማዕት ፍቁረ ኢየሱስ 33. ሰላም ለከ፡- የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጅ አቢብ
ክርስቶስ፤ ሥቃየ መከራ ጽኑዕ እንዘ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤ የጸና የመከራ ሥቃይን
ትትዔገሥ፤ ኢፈራኅከ አንተ ገጸ ንጉሥ፡፡ እየታገሥህ አንተ የንጉሥን መከራ አልፈራህም፡፡

፴፬. ሰላም ለከ ጸዋሬ መስቀል አቢብ 34. ሰላም ለከ፡- ስለ ክርስቶስ ስም ያለ ልክ


መትልወ ሰማዕታት ኵሎሙ፤ እንተ የታገሥህ ሰማዕታትን ኹሉ የተከተልህ መስቀልን
ተዐገሥከ እንበለ ዐቅሙ፤ ለክርስቶስ በእንተ የተሸከምህ አቢብ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡
ስሙ፡፡
35. ሰላም ለከ፡- የጽድቅን ሥራ በበረሓና
፴፭. ሰላም ለአቢብ ዘአስተጋብዖ አሐተኔ፤ የሰማዕትነትን ሥራ በዐደባባይ ውስጥ በአንድነት
ምግባረ ጽድቅ በገዳም ወምግባረ ሰማዕት ያስተባበርህ አቢብ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤
ውስተ ኵርጓኔ፤ እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ በሚያሳዝን የምስጋና ቃል ለብቻህ የአምላክህን
አኰቴት ማኅዘኔ፤ ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ምሥጢር ፈጸምህን! በገድል ሥራም ሥጋህን
ዘአምላክከ ቅኔ፤ ታጻሙ ሥጋከ በዘገድል ታደክማለህ፡፡
ኵነኔ፡፡
36. ሰላም ዕብል፡- ለሦስት ሺህ አርባ ሦስት
፴፮. ሰላም ዕብል ዐሠርተ ወምዕተ ዓምዓተ፤ ወንዶችና ለሦስት መቶ ሠላሳ ሴቶች ሰላም እላለሁ፤
አርብዓ ወሠለስተ ተባዕተ፤ ሠለስተ ምዕተ እነርሱም የብፁዕ አቢብን መጨከን በዐደባባይ ውስጥ
ወሠላሳ አንስተ፤ ወሶበ ርእዩ በውስተ ዐውድ በተመለከቱ ጊዜ የተጋደሉ ሰማዕት ሆኑ፡፡37. ሰላም
ዘአቢብ ጥብዓተ፤ እለ ተጋደሉ ወኮኑ ዕብል፡- በመጠንቀቅ ለብፁዕ አቢብ ሰላም እላለሁ፤
ሰማዕተ፡፡ የወንጌልን አበባ የታጠቀ በጠለቀ የጸሎቱ ስም
እየጸለይሁ፤ ሕያው ሰው በተጠራጠረ ጊዜ በእውነት
፴፯. ሰላም ዕብል ለአቢብ ጥንቁቀ፤ ጽጌያተ በቃል ኪዳኑ በማመን የቃል ኪዳኑን ክብር የሞተው
ወንጌል ዕጡቀ፤ እንዘ እጼሊ በስመ ጸሎቱ በተረዳ ነገር ተናገረ፡፡
ዕሙቀ፤ ብእሲ ሕያው ሶበ ናፈቀ፤ አሚነ
ኪዳኑ ጽዱቀ፤ ክብረ ኪዳኑ ዜነወ ምውት
ጥዩቀ፡፡
38. ኦ አምላከ አቢብ፡- ‹አቤቱ የአቢብ አምላክ ጌታ
፴፰. ኦ አምላከ አቢብ ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ኀጢአቴን አስተስርይልኝ›

6
እግዚእየ፤ ስረይ ኀጢአትየ፤ እንዘ ይብል እያለ ኃጥእ ሰው በጸለየ ጊዜ ጌታም ‹በስሜና
ብእሲ በጊዜ ጸለየ፤ ይቤ እግዚእ በስምየ፤ በባሪያዬ በአቢብ ስም የሠራውን ኀጢአት
ወበስመ አቢብ ገብርየ፤ አኃድግ ሎቱ ዘገብረ እተውለታለሁ› አለ፡፡
ጌጋየ፡፡
39. ተዘኪረከ ክርስቶስ፡- አምላካችን ክርስቶስ ሆይ!
፴፱. ተዘኪረከ ክርስቶስ ሥቃያተ አቢብ የበዛውን የአቡነ አቢብን መከራ አስበህ በነፍሱ
ብዙኀ፤ ወርኅ ጸአተ ነፍሱ ፍሉሃ፤ ኢታጽንዕ መውጣት ወር ርኅሩኅ ልብህን አታጽናብኝ፤ ለሰው
ብየ ልበከ ርኅሩኀ፤ እስከ እትመየጥ ከሞቱ በኋላ ንስሓ የለውምና ወደ አንተ እስክመለስ
መንገሌከ ጽንሐኒ ጸኒሐ፤ እስመ ድኅረ ሞቱ ድረስ ጠብቀኝ፡፡
ለሰብእ አልቦቱ ንስሓ፡፡
አቤቱ የአቡነ አቢብ አምላክ ሆይ! እኔን ባሪያህን.....
ኦ አምላከ አቡነ አቢብ ዕቀበኒ ወአድኅነኒ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ዘወትር በየጊዜውና
እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለገብርከ….. በየሰዓቱ አድነኝ፤ ጠብቀኝም፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ወትረ በኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት ለዓለመ
ዓለም አሜን፡፡ አባታችን ሆይ…

አቡነ ዘበሰማያት… 



ማሕልየ መሓልይ ዝ ውእቱ ዘሰሎሞን


መመመ (በዚህ ከለር የተቀመጡት ከተለመደው የመሓልይ ጸሎት የተለዩና ከብራናው ላይ ተወስደው
የተጨመሩ ናቸው)

ማሕልየ መሓልይ ዝ ውእቱ ዘሰሎሞን ከምስጋና የሚበልጥ ምስጋና ይኸውም ሰሎሞን


የተናገረው ነው፡፡

መሓልይ ፩ መሓልይ 1
ይስዕመኒ በስዕመተ አፉሁ፡፡ በአፉ መሳም ይስመኛል፡፡

አዳም አጥባትኪ እምወይን፡፡ ከወይን ይልቅ ጡትሽ (ኹለቱ ጽላቶች) የአማረ ነው፡፡

ወመዐዛ ዕፍረትኪ እምኵሉ አፈው፡፡ የሽቱሽም መዐዛ ከሽቱ ኹሉ የአማረ ነው፡፡

ወአልባስኪ ከመ ኅብረ አፌዝ፤ ልብሶችሽ ወርቃማ መልክ ናቸው፡፡

ዕፍረት ዘተሠውጠ ስምከ፡፡ ስምህ ሽቱ የተቀላቀለበት ነው፡፡

በእንተ ዝ ደናግል አፍቀራከ፡፡ ስለዚኽም ደናግል (ቈነጃጅት) ወደዱህ፡፡

7
ወሰሐባከ ድኅሬከ፡፡ ከወደኋላህም ሳቡህ፡፡
በመዐዛ ዕፍረትከ ንረውጽ፡፡ በሽቱህ መዐዛ እንሮጣለን፡፡
አብአኒ ንጉሥ ውስተ ጽርሑ፡፡ ንጉሡ ወደ አዳራሹ (ቤተ መቅደስ) አገባኝ፡፡
ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ብኪ፡፡ በአንቺ ፈጽሞ ደስ ይለናል፡፡
ናፍቅር አጥባተኪ እምወይን፡፡ ከወይን ይልቅ ጡትሽን (ጽላቶችሽን) እንወዳለን፡፡
ወርቱዕ አፍቅሮትኪ፡፡ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው፡፡
ጸላም አነ ወሠናይት እምአዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡ ከኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ይልቅ የአማርኩ ስሆን እኔ
ጥቁር ነኝ፡፡

ከመ ምጽላላተ ቄዳር ወኀይመታተ ሰሎሞን፡፡ በመከራ እንደ ዘላን ጐጆ እንደ ሰሎሞን ድንኳኖች፤

ቄዳር ወምንስንጉን ኢይበውዕዎን ትቤ አቅሌስያ፡ አቅሌስያ ‹ዘላንና ያልተገረዙ አይገቡባቸውም› ትላለች፡፡

ኢትርአያኒ እስመ አነ ጸላም፡፡ እኔ ጥቁር ነኝና አትዩኝ፡፡

እስመ ኢርእየኒ ፀሐይ፡፡ ፀሐይ አላየኝምና (ረድኤቱ)፡፡

እስከ ይከውን ፍና ጎሕ ወይሠርቅ ብርሃን በላዕሌየ ብርሃን ጎሕ ቀድዶ በላዬ እስከሚያርፍ ድረስ፤

ዘይወርድ እምአርያም ወይሠርቅ በላዕሌየ፡፡ ከአርያም ወርዶ በላዬ የሚያድር፤

ደቂቀ እምየ ተባአሱ በእንቲኣየ፡፡ የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፡፡

አንበሩኒ ዐቃቢተ ዐጸደ ወይን፡፡ የወይን ቦታ ጠባቂ ብለው አኖሩኝ፡፡

ዐጸደ ወይን ዘዚኣየ ኢዐቀብኩ፡፡ እኔ ግን የወይን ቦታዬን አልጠበቅሁም፡፡

ንግረኒ ዘአፍቀረት ነፍስየ፡፡ ሰውነቴ የወደደችውን ንገረኝ፡፡

ንግረኒ በአይቴ ትረክቦ ለፍቁርየ፡፡ ወዳጄን የት እንድታገኘው ንገረኝ፡፡

አይቴ ትሬዒ ወአይቴ ትሰክብ ጊዜ ቀትር፡፡ ወዴት ትሠማራለህ በቀትር ጊዜስ ወዴት ትተኛለህ ፤
(ትሰቀላለህ)፡፡
ከመ ኢይኩን እንዘ አንጌጊ ውስተ መራዕየ
ካልኣኒከ፡፡ ከባልንጀሮችህ መንጋዎች ስቅበዘበዝ እንዳልገኝ፡፡

እመ ኢያእመርኪ ርእሰኪ ሠናይት እምአንስት፡፡ ራስሽን (እግዚአብሔርን) ካላወቅሽ ከሴቶች ይልቅ


አምረሽ የነበርሽ፡፡
ፃኢ አንቲ ውስተ ሰኰናሆሙ ለመርዔት፡፡
የመንጋዎችን ፍለጋ ተከትለሽ ውጪ፡፡
ወረዐዪ መሐስዐ አጣሊኪ፡፡
የፍየሎችሽንም ግልገሎች ጠብቂ፡፡
ውስተ አዕጻዳቲሆሙ ለኖሎት፡፡
በእረኞች ቦታዎች፡፡
ለፈረስየ ወለሠረገላተ ፈርዖን፡፡
በፈረሴና በፈርዖን ሠረገላዎች፡፡
እብለኪ፤
እልሻለሁ፤
ብፁዓን እለ ይሬእዩኪ ይዴመሙ፡፡
የሚያዩሽ ንዑዳን ክቡራን ይደነቃሉ፡፡
አስተማሰልኩኪ እንተ ኀቤየ፡፡
በእኔ በኩል መሰልሁሽ፡፡
ነየ እንቲኣየ ሠናይት ርግብየ፡፡
እነሆኝ የእኔ መልካሚቱ ርግብ፤
ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ፡፡
ፊትሽ እንደ ዋኖስ እጅግ የአማረ ነው፡፡
ወክሣድኪ ከመ አርማስቆስ፡፡
አንገትሽም እንደ ብር ዘንግ ነው፡፡
አምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ዘብሩር፡፡
በወርቅ አምሳል የብር ዝንጉርጉር ይሥሩልሽ፡፡

8
እስከ ሶበ ንጉሥ ያሰምክ ቦቱ፡፡ ንጉሥ እስኪጠጋት ድረስ፤
ናርዶስ ወሀበ መዐዛሁ፡፡ ናርዶስ መዐዛውን ሰጠ፡፡
ዕቍረ ማየ ልብን ዘወልድ እኁየ ሊተ፡፡ የወልድ ወንድሜ የተቋጠረ ልባንጃ ሽቱ ለእኔ ነው፡፡
ማእከለ አጥባትየ የዐርፍ፡፡ በጡቶቼ መካከል ያርፋል (በኹለቱ ጽላት)፡፡
አስካል ዘጸገየ ዘወልድ እኁየ ሊተ፡፡ የአበበ የወልድ ወንድሜ ፍሬ ለእኔ ነው፡፡
ውስተ ዐጸደ ወይን ዘበጋዲ፡፡ በጋዲ ባለ በወይን ቦታ፤
ነያ ሠናይት እንተ ኀቤየ፤ ነያ ሠናይት፡፡ በእኔ ዘንድ እነሆ የአማርሽ ነሽ፤ የአማርሽ ነሽ፡፡
አዕይንትኪ ዘርግብ፡፡ ዐይኖችሽ የርግብ ዐይኖች ይመስላሉ፡፡
ወዕፍረትኪ ከመ ፍዛ፡፡ ሽቱሽ እንደ ጠብታ ነው፡፡
ናሁ ሠናይ አንተ ወልድ እኁየ፡፡ እነሆ አንተ ወልድ ወንድሜ የአማርህ ነህ፡፡
አዳም በውስተ ምስካቢነ ዘበሕቊ፡፡ ዞጲ በሚሆን መኝታችን የአማርን ነን፡፡
ወመዋጽሕተ ቤትነ ዘአርዝ፡፡ የቤታችን መዋቅርም የዝግባ ዛፍ ነው፡፡
ወመሥዕርቲነ ዘሕቊ፡፡ ትራሳችንም የዞጲ ነው፡፡
አነ ጽጌ ገዳም፡፡ እኔ የምድረ በዳ አበባ ነኝ፡፡
ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቈላት፡፡ በቈላ ያለ የሱፍ አበባ፡፡
ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ፡፡ በእሾኽ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፡፡
ከማሁ አንቲኒ እንተ ኀቤየ በማእከለ አዋልድ፡፡ አንቺም በልጃገረዶች መካከል በእኔ ዘንድ እንደዚሁ ነሽ፡
ወከመ ኮል ዘውስተ ዕፀወ ገዳም፡፡ በምድረ በዳ ዛፎች መካከል አንዳለ እንኮይ ነሽ፡፡
ኮልኪ ዘሠናየ ይጸጊ ወቀይሐ ይፈሪ፡፡ እንኮይሽ መልካሙን አብቦ ቀይ ፍሬን ያፈራል፡፡
ከማሁ ዘአፈቅር በማእከለ አኀው፡፡ የምወደው በወንድሞቹ መካከል እንደዚያ ነው፡፡
ታሕተ ጽላሎቱ ፈተውኩ ወነበርኩ፡፡ ከጥላው በታች መኖርን ወደድሁ፡፡
ወፍሬሁኒ ጥዑም ለጒርዔየ፡፡ ፍሬውም ለጕሮሮዬ የጣፈጠ ነው፡፡
አስራጥዮን የዐጽር፡፡ በገንዳም የተጠመቀ ነው፡፡
አብኡኒ ቤተ ወይን፡፡ ወደ ወይኑም ቤት አገቡኝ፡፡
ገብሩ ላዕሌየ ፍቅረ፡፡ በእኔ ላይ ፍቅርን አደረጉ፡፡
አጽንዑኒ በዕፍረት፡፡ ሽቱ ቀቡኝ፡፡
ሰደቁኒ በአክዋል፡፡ በእንኮዮች ኰሉኝ፡፡
እስመ ተነደፍኩ በፍቅሩ፡፡ በፍቅሩ ፍላፃ ተወግቻለሁና፡፡
የማኑ ተሐቅፈኒ ወጸጋሙ ታሕተ ርእስየ፡፡ ቀኙ ታቅፈኛለች ግራውም ታንተርሰኛለች፡፡
(ቀኙ ወንጌል ግራው ኦሪት ያጸኑኛል)፡፡
አመሐልኩክን አዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ሆይ! አማፅኛችኋላሁ፡፡
በኀይሉ ወበጽንዑ ለገዳም፡፡ በከኻሊነቱ በምድረ በዳ በአደረገው ተኣምራቱ፡፡
አመ ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታነ፡፡ ከሙታን ተነሥቶ ሙታንን በአስነሣ ጊዜ፡፡
አፈቅሮ እስከ አመ ፈቀደ፡፡ እስከወደደኝ ድረስ እወደዋለሁ፡፡

9
መሓልይ ፩-መዝሙረ ክርስቶስ መሓልይ 1-መዝሙረ ክርስቶስ
በመሓልይሁ ሰሎሞን ይቤለከ ቅድመ፤ ነቢይ ሰሎሞን አስቀድሞ በመዝሙረ መሓልዩ፤
ደናግለ ዓለም ኵሉ አፍቀራከ ፍጹመ፤ ‹ዓለምን በፍቅር የመላህ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ሆይ!
ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዘአስተሳለምከ ዓለመ፤ ዓለም ኹሉ ፈጽሞ ወደደህ፤
ማሕየዊ መስቀልከ አመ በእንተ ሰብእ ቆመ፤ በአዳኝ መስቀልህ ስለ ሰው ፍቅር በተሰቀልህ ጊዜ፤
እምነ ሰብእ ሰዐረ መርገመ፡፡ ከሰው መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስን አጥፈተኻልና›
አለህ፡፡

መሓልየከ ነገረ ሰሎሞን ጸዋሬ አክሊል፤ ዘውድን የተቀዳጀ ነቢይ ሰሎሞን አስቀድሞ ዕሥራኤል
ዕሥራኤልሀ ሕዝበከ እንዘ መርዓተከ ይብል፤ ሕዝብህን ሙሽራይቱ ብሎ ምስጋናህን ተናገረ፤
መርዓዊ ክርስቶስ አመ ትመጽእ በኀይል፤ ሙሽራ ክርስቶስ ሆይ! ለመፍረድ በመጣህ ጊዜ፤
ኢትፍልጠነ ለአግብርቲከ እምዘዚኣከ አካል፤ አንተ ራስ እኛም አካል ነንና፤
እስመ አንተ ርእስ ወንሕነ አባል፡፡ አቤቱ አገልጋየችህን ከአንተ አትለየን፡፡

መሓልይ ፩-መዝሙረ ድንግል መሓልይ ፩-መዝሙረ ድንግል


መሓልየ መሓልይ ዝ ውእቱ ዘሰሎሞን፤ ከመዝሙረ ዳዊትና ከአገልጋዩ ከነቢይ ሙሴ ምስጋና
እመዝሙረ ዳዊት ዘይተሉ ወእምስብሐተ ሙሴ የሚከተል፤
ካህን፤ የነቢይ ሰሎሞን መሓልየ መሓልይ ይኽ ነው፤
አዳም ይቤ ዚኣኪ እምወይን፤ ለመሥዋዕት ከተዘጋጀም የሽቱ ቅመምና፤
ማርያም ጥዕምተ ስም እምነ ዕቊረ ማይ ዘልብን፤ ከሽቱ ፈሳሽ መዐዛ ይልቅ ስምሽ የሚጣፍጥ ድንግል
ወእምነ ፀበል ዘስኂን ለመሥዋዕት እዩን፡፡ ማርያም ሆይ!
ከወይን ይልቅ የአንቺ ፍቅር የአማረ ነው፡፡

መሓልይ ፪ መሓልይ 2
ዘይዜኑ ርደተ ወልድ ወተሠግዎቶ እምድንግል፡፡ የወልድን መውረድና ከድንግል ሥጋን መንሣቱን
የሚናገር

ቃል ወልድ እኁየ ናሁ ውእቱ መጽአ፡፡


ቃል ወልድ ወንድሜ እነሆ መጣ፡፡
እንዘ ይቀንጽ ማእከለ አድባር፡፡
በተራራዎች መካከል ላይ እየዘለለ (መጣ)፡፡
ወያንበሰብስ ዲበ አውግር፡፡
በኰረብቶች ላይም እየተመላለሰ፡፡
እገሪሁ ቀሊል ከመ ነፋስ፡፡
እግሮቹ እንደ ነፋስ ፈጣን ናቸው፡፡
ይመስል ወልድ እኁየ ከመ ወይጠል፡፡
ወልድ ወንድሜ እንደ ፈጣን ፌቆ ይመስላል፡፡
በገዳመ ሲሎኖዶሮስ፡፡
በሲሎኖዶሮስ በረሓ፤
ወከመ ወሬዛ ሀየል ውስተ አድባረ ቤቴል፡፡
በቤቴል ተራራ የተሠማራ የዋልያ ወይፈንን ይመስላል፡፡
በአንጻረ ሙሓዛተ ማያት ዘምጥማቃት፡፡
በማጥመቂያዎቹ የውኆች መፍሰሻዎች በኩል፤
ወይሠርቅ ብርሃን እምኤማሁስ፡፡
ብርሃን ከኤማሁስ ይወጣል፡፡
ወይትዐጸፍ ርትዐ ውስተ ገቦሁ፡፡
በጐኑም ቅንነትን ይጐናጸፋል፡፡
ናሁ ውእቱ ይቀውም ድኅረ አረፍት፡፡
እነሆ እርሱ ከቅጽር በኋላ ይቆማል፡፡

10
ወይሔውጽ እንተ መሳክው፡፡ ወደ መስኮቱም ይመለከታል፡፡
ወከመ ቴገን ይትረአይ፡፡ እንደ ዓላማ ይታያል፡፡
ወይደንን እንተ ተድባብ፡፡ ወደ መዛነቢያውም ያዘነብላል፡፡
ያወሥእ ወልድ እኁየ ወይብለኒ፡፡ ወልድ ወንድሜ ይመልስልኛል፤ እንዲህም ይለኛል፡-
ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ እንቲኣየ ሠናይት ‹አቅራቢያዬ የእኔ መልካሟ ርግቤ ተነሥተሽ ነዪ፡፡›
ርግብየ፡፡
እስመ አፈቅሮ አፈቅረኪ፡፡ እወደዋለሁና እወድሻለሁ፡፡
ወእስዕመኪ በስዕመተ መንፈስ ቅዱስ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅርም እሳለምሻለሁ፡፡
እስመ ናሁ ክረምት ኀለፈ፡፡ እነሆ ክረምት አልፏልና፡፡
ወዝናም ገብአ ለሊሁ (ድኅሬሁ)፡፡ ዝናሙ ወደ ኋላው ተመልሷልና፡፡
ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ፡፡ በምድራችን አበባው ታየ፡፡
ጊዜ ገሚድ በጽሐ፡፡ የወይኑን ዘለላ የሚቈረጥበት ጊዜ ደረሰ፡፡
ቃለ ማዕነቅ ተሰምዐ በምድርነ፡፡ የዋኖስ ድምፅም በምድራችን ተሰማ፡፡
በለስ አውፅአ ሠርጸ፡፡ በለስም ቡቃያውን አወጣ፡፡
አውያን ጸገዩ፤ ወወሀቡ መዐዛ፡፡ ወይኖች አበቡ መዐዛንም ሰጡ፡፡
ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ አቅራቢያዬ ተነሥተሽ ነዪ፡፡
እንቲኣየ ሠናይት ርግብየ፡፡ የእኔ መልካሟ ርግቤ፡፡
ውስተ ጽላሎተ ኰኵሕ ቅሩበ ጥቅም፡፡ በቅጥሩ አጠገብ ወደ አለ ዋሻ ጥላ ነዪ፡፡
ወኑባሊስዕ እምንፍታሌም ይትዓደዎ፡፡ ኑባሊስዕም ከንፍታሌም ይሻገረዋል፡፡
አርእየኒ ገጸከ ወአስምዐኒ ቃለከ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ቃልህንም አሰማኝ፡፡
እስመ ቃልከ አዳም ወገጽከ ላሕይ (ልሑይ)፡፡ ቃልህ የአማረ ፊትህም ውብ ነውና፡፡
አሥግሩ ለነ ቈናጽለ ንኡሳነ እለ ያማስኑ ዐጸደ የወይን ቦታችንን የሚያጠፉ ቃናናሾች ቀበሮችን
ወይንነ፡፡ አጥምዳችሁ ያዙልን፡፡
ዐጸደ ወይንነ ይጽጊ፡፡ የወይን ቦታችን ያብብ፡፡
ፍሕሦራስ ይጸጊ ምስቈላርምራር ወተምራር፡፡ ቀይ አበባና ጽጌ ረዳ ቴምርም፤
ያስተርእዩ በውስተ አርእስተ አድባር፡፡ በተራሮች ጫፍ ላይ ይበቅላሉ፡፡
ቲሳኢ ያንጸበርቅ ዲበ ምድር፡፡ የዐይን ብሌን በምድር ላይ ያንፀባርቃል፡፡
እንዘ ይትረአይ ውስተ ጽጌያት፡፡ በአበቦች ውስጥ ሲታይ፤
አነ ለወልድ እኁየ፡፡ እኔ ለወንድሜ ወልድ፤
ወልድ እኁየ ሊተ፤ ወአነ ሎቱ፡፡ ወልድ ወንድሜ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፡፡
መኑ ይትዐደዎ ለወልድ እኁየ፡፡ ለወልድ ወንድሜ የሚተላለፈው ማን ነው?
እስመ ልዑል መዝራዕተ የማኑ፡፡ የማናዊ ክንዱ (ሥልጣኑ) ከፍ ያለ ነውና፡፡
ዘይትረዐይ ውስተ ጽጌያት፡፡ ወደ አበባዎች የሚሠማራ፤
እስከ ሶበ ያስተነፍስ ዕለት ወያንቀለቅል ጽላሎት፡ ቀኑ እስኪመሽ ጥላውም እስኪመለስ ድረስ፤
ተመየጥ አንተ ወልድ እኁየ፤ ወተመሰላ አንተ ወልድ ወንድሜ ተመለስ፤ ፌቆንም ምሰላት፡፡

11
ለወይጠል፡
ወይርአያከ አዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶችም ይዩህ፡፡
ወንበር ዲበ ሳሬል፡፡ በኪሩቤል ላይ ተቀመጥ፡፡
ወዲበ አርባዕቱ አርባብ፡፡ በአራቱ ሱራፌል ላይም፡፡
ወከመ ወሬዛ ሀየል ውስተ አድባረ ድኁኃን፡፡ በጸኑ ተራራዎች የተሠማራ የዋልያ ወይፈን፤
ቅንጽ አንተ ወልድ እኁየ ከመ ወይጠል፡፡ አንተ ወልድ ወንድሜ እንደ ፌቆ መር ብለህ ዝለል፡፡
በዐራትየ ወበለያልይየ፡፡ ሌሊት በአልጋዬ ሳለሁ፤
እኅሥሥ ዘአፍቀረት ነፍስየ፡፡ ሰውነቴ የወደደችውን እፈልግ ዘንድ፤
ኀሠሥክዎ ወኢረከብክዎ፡፡ ፈለግሁት፤ አላገኘሁትም፡፡
ጸዋዕክዎ ወኢተሠጥወኒ፡፡ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም፡፡
እትነሣእ ወአዐውድ ሀገረ፡፡ ተነሥቼ ሀገር ለሀገር እዞራለሁ፡፡
ውስተ ምሥያጣት ወውስተ መራሕብት፡፡ ወደ ገበያ ወደ አደባባዮችም፡፡
እኀሥሥ ዘአፍቀረት ነፍስየ፡፡ ሰውነቴ የወደደችውን እፈልግ ዘንድ፤
ኀሠሥክዎ ወኢረከብክዎ፡፡ ፈለግሁት፤ አላገኘሁትም፡፡
ጸዋዕክዎ ወኢተሠጥወኒ፡፡ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም፡፡
ረከቡኒ መዓቅብት እለ የዐቅቡ ሀገረ፡፡ ሀገርን የሚጠብቁ ዘበኞች አገኙኝ፡፡
ርኢክሙኑ ዘአፍቀረት ነፍስየ፡፡ ሰውነቴ የወደደችውን አያችሁን?
ንስቲተ ኀሊፍየ እምኔሆሙ፡፡ ከእነርሱ ጥቂት እልፍ ብዬ፡፡
ይእተ ጊዜ ረከብኩ ዘአፍቀረት ነፍስየ፡፡ ያንጊዜ ሰውነቴ የወደደችውን አገኘሁ፡፡
አኀዝክዎ ወኢየኀድጎ፡፡ ያዝሁት አልተወውም፡፡
እስከ ሶበ አባእክዎ ውስተ ቤተ እምየ፡፡ ወደ እናቴ ቤት አስካገባው ድረስ፡፡
ወውስተ ውሳጥያቲሃ ለእንተ ሐፀነተኒ፡፡ ወደ አሳደገችኝ ወደ እልፍኝዋ፡፡
አመሐልኩክን አዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ሆይ! አማጽኛችኋላሁ፡፡
በኀይሉ ወበጽንዑ ለገዳም፡፡ በከሃሊነቱ በምድረ በዳ በአደረገው ተኣምራቱ፡፡
አመ ተንሥአ ወአንሥአ ኵሎ ሙታነ፡፡ ከሙታን ተነሥቶ ሙታንን ባስነሣ ጊዜ፡፡
አፈቅሮ እስከ አመ ፈቀደ፡፡ እስከወደደኝ ድረስ እወደዋለሁ፡፡

መሓልይ ፪-መዝሙረ ክርስቶስ መሓልይ 2-መዝሙረ ክርስቶስ


ዓዲ ይነግር በመሓልየ ካልእ ክፍል፤ ዳግመኛም በኹለተኛው የመዝሙረ መሓልይ ክፍል፤
ርደተከ ክቡረ እምጽርሐ አርያም ልዑል፤ ከልዑል ጽርሐ አርያም መውረድህን ይናገራል፤
ጽጌ ተሠግዎ ክርስቶስ ዘመዐዛከ ወንጌል፤ መዐዛህ ወንጌል የኾነ ጽጌ ተሠግዎ ክርስቶስ ሆይ!
ወትብለከ ቤተ ክርስቲያን በዘኢይማስን ቃል፤ ቤተ ክርስቲያን በማይጠፋ ቃል፤
ወልድ እኁየ ተመየጥ በኀይል፡፡ ‹ወልድ ወንድሜ ሆይ! በኀይል ተገለጥ› ትልኻለች፡፡

የአብ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ሆይ! ቀድሞ በተራሮችና


አስተርአይከ ቅድመ ማእከለ አድባር ወአውግር፤ በኮረብቶች፤
እንዘ ደኃራዊ በሥጋ ክርስቶስ በኵር፤ ኋላም ሥጋን ተዋህደህ ተገለጥህ፤

12
እስመ ወራሲ ለሊከ ወተወራሲ ሀገር፤ አንተ ፈጣሪ ዓለሙም ኹሉ ፍጡር ነውና፤
ይቤለከ በእንተ ዝ ቄርሎስ ክቡር፤ ስለዚኽም የከበረ አባ ቄርሎስ፤
እግዚእ ከመ አቡከ ወከማነ ገብር፡፡ ‹እንደ አባትህ ጌታ፤ እንደ እኛም ፍጹም ሰው ኾንህ›
አለ፡

መሓልይ ፪-መዝሙረ ድንግል መሓልይ ፪-መዝሙረ ድንግል


ቃል ወልድ እኊየ ማዕከለ አድባር ቀነጸ፤ መለኮቱን ከሥጋሽ ጋራ አንድ ያደርግ ዘንድ፤
እንተ ተድባብ ደነነ ወእንተ መሳክው ሐወጸ፤ ከተድባበ ሰማይ ዝቅ ብሎ መተላለፊያዎችን በጐበኘ
ውስተ ሥጋኪ ይደምር ርስነ መለኮቱ ብቊጸ፤ ጊዜ፤
ማርያም በእንተ ዝንቱ ረኪበነ ገጸ፤ ቃል ወልድ ወንድሜ በተራሮች መካከል ዘለለ፤
መፆረ እሳት ሰመይናኪ ዕፀ፡፡ ስለዚኽም ድንግል ሆይ! ምሕረቱን አግኝተናልና፤
‹እሳት የተዋሐዳት ዕፅ› ብለን ሰየምንሽ፡፡
መሓልይ 3
መሓልይ ፫
ከምድረ በዳ የምትወጣ ይኽች ማን ናት?
መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ተዐርግ እምገዳም፡፡
ጠፈር በሚባል ሰማይ እንዳለ ደመና፡፡
ከመ ደመና ዘጠፈረ ሰማይ፡፡
የዕጥነቷ አወጣጥ እንደ ጢስ የሆነ፡፡
ወከመ ሠርጸ ጢስ ዕጥነታ (አዳም)፡፡
ኹለቱ ጡቶችሽ (ጽላቶች) ወተትን ያፈሳሉ፡፡
ክልኤ አጥባትኪ ያውሕዛ ሐሊበ፡፡
ከርቤ ስኂን የሚባሉ ሹቱዎች ከሽቱ ቅመሞች ኹሉ ጋራ
ከርቤ ወስኂን እምኵሉ ጸበለ አፈው (ኤፌኔዎስ)፡፡
አሉሽ፡፡
እነሆ የሰሎሞን አልጋ፤
ናሁ ዐራቱ ለሰሎሞን፡፡
ከዕሥራኤል ኀይለኞች የተመረጡ ስድሳ ኀያላን ከበዋት
ስሳ ኀያላን ዐውዳ እምኀያላነ ዕሥራኤል፡፡ ይቆማሉ፡፡
ኵሎሙ እኁዛነ አስይፍት ወምሁራነ ቀትል፡፡ ኹሉም ሰይፍ የያዙ ሰልፍም የተማሩ ናቸው፡፡
ብእሲ ብእሲ ሰይፉ ዲበ መንቅዕቱ፡፡ አንዱም አንዱም ሰው ሰይፉ በብብቱ ነው፡፡
ይትሜሰሉ በድንጋፄ ሌሊት፡፡ በሌሊት አስደንጋጭ ነገር ይመስላሉ፡፡
መጾረ ገብረ ለርእሱ ንጉሥ ሰሎሞን እምዕፀወ ንጉሡ ሰሎሞን ከደጋ ዕንጨቶች ለራሱ አልጋ ሠራ፡፡
ሊባኖስ፡፡
ሸንኰሩንም የብር አደረገ፡፡
አዕማዲሁ ገብረ ዘብሩር፤ ሰርዲኖስ ምስለ
ሰርዲኖስ ከሚባል ዕንቍና ተርሴስ ከሚባል ዕንቍ ጋራ፡፡
ተርሴስ፡፡
ኢዮጶሎግዮስ ከሚባል ዕንቊና ሶፎር ከሚባል ዕንቍ ጋራ
ኢዮጶሎግዮስ ዘምስለ ሶፎር፡፡
አደረገበት፡፡
መጠጊያውን የወርቅ አደረገ፡፡
ምስማኩ ዘወርቅ፤ አቊላፊሁ ወአቊፋሊሁ
ፍልፍሉ መጠምጠሚያው ኢያሴሜር የሚባል ዕንቊ ነው፡
ኢያሴሜር፡፡
መቀመጫው ሐምራዊ ግምጃ የቢረሌ የሚሆን መገናኛው
መንበሩ ዘሜላት፤ ኅንብርቱ ዘቢረሌ ዘምስለ
ኢያሰጲድ ከሚባል ዕንቍ ጋራ በዕንቈ ባሕርይ
ኢያሰጲድ በባሕርይ ክዱን፡፡
ተለብጧል፡፡
ውስጡ ንጹፍ በእብነ ሰንፔር፡፡
ውስጡ በዕንቈ ሰንፔር ተለብጧል፡፡
ኣፈቅሮ ፈድፋደ እምአዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡
ከኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ይልቅ እወደዋለሁ፡፡
ፃኣ ትርአያ አዋልደ ጽዮን፡፡
የጽዮን ልጃገረዶች ታዩ ዘንድ ውጡ፡፡
ለንጉሥ ሰሎሞን፡፡
ንጉሥ ሰሎሞንን፤

13
በአክሊል ዘአስተቀጸለቶ እሙ፡፡ እናቱ ያቀዳጀችውን ዘውድ፤
በአክሊል ዘአስተቀጸልዎ አዝማደ ለእሙ፡፡ ለእናቱ ዘመዶች የኾኑ በአቀዳጁት ዘውድ፤
አመ ዕለተ መርዓሁ፡፡ በሠርጉ (በነገሠበት) ቀን፤
ወአመ ዕለተ ፍሥሓ ልቡ፡፡ ልቡ ደስ ባለበት ቀን፤
አመ ዕለተ ሕማሙ ወአመ ዕለተ ስቅለቱ፡፡ መከራ በተቀበለበት ቀንና በተሰቀለበት ቀን፤
ወአመ ዕለተ ሞቱ፡፡ በሞተበትም ቀን፤
ዕፁበ ረከቦ እምአዝማደ እሙ፡፡ ከእናቱ ዘመዶች ችግር አገኘው፡፡
ስማዕ ሰማይ ወአጽምዒ ምድር፡፡ ሰማይ ስማ፤፡ ምድርም አድምጪ፡፡
ሐራውያ ገዳም እንዘ ይንዕዎ ለአንበሳ፡፡ የዱር አሳማዎች አንበሳን ሲያድኑት፤
ዘመደ ብርሃናት ኀብኡ ጸዳሎሙ፡፡ የብርሃናት ወገኖች ብርሃናቸውን ሸሸጉ፡፡
ጽልመተ ሌሊት ተመየነ፡፡ የሌሊት ጨለማ ተመጻደቀ፤
በምሴተ ዐርብ ሠረቀ ፀሐይ፡፡ በዐርብ ፀሐይ ወጣ፡፡
ተፈትሑ ሙቁሐን እለ እምትካት ተአስሩ፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ የታሰሩ እስረኞች ተፈቱ፡፡
ይትፌሥሐኒ ልብየ በአምላኪየ፡፡ ልቤ በአምላኬ ደስ ይለዋል፡፡
አመ ዕለተ መርዓሁ፡፡ በደስታ ቀኑ ጊዜ፤
ገዳም ጸገየት ወፈረየት ብዙኅ፡፡ ገዳም አብባ እጅግ አፈራች፡፡
ተፈሥሒ ወተሐሠዪ ጎልጎታ፡፡ ጎልጎታ ፈጽሞ ደስ ይበልሽ፡፡
ንጉሥኪ ተንሥአ ብርሃነ ለቢሶ፡፡ ንጉሥሸ ብርሃን ለብሶ ተነሥቷል፡፡
ነያ ሠናይት እንተ ኀቤየ ነያ ሠናይት፡፡ በእኔ ዘንድ እነሆ የአማርሽ ነሽ፤ የአማርሽ ነሽ፡፡
አዕይንትኪ ዘርግብ፡፡ ዐይኖችሽ የርግብ ዐይኖች ናቸው፡፡
ወሥዕርትኪ ከመ መርዔተ አጣሊ፡፡ ጠጕርሽም እንደ ፍየል መንጋ ነው፡፡
እለ ተከሥታ እምአድባረ ገለዓድ፡፡ በገለዓድ ተራራ እንደተሠማሩ፤
ስነንኪ ከመ መራእይ እለ ተቀርፃ፡፡ ጥርሶችሽም እንደተሸለቱ መንጋዎች፤
ወእለ ወፅአ እምሕጻብ፡፡ ከመታጠቢያ እንደወጡ፤
ኵሎን እለ ይመነትዋ፡፡ ኹሉም መንታ መንታ እንደሚወልዱ፤
ሰብዓ ወሰብዓተ እለ ይወልዳ፡፡ ሰባ ሰባትም እንደሚወልዱ ናቸው፡፡
ወአልቦ እምኔሆን መካን፡፡ ከእነርሱም የማይወልድ መኻን የለም፡፡
እልፈ ወአእላፈ እለ ይፈርያ አፈዋተ፡፡ የብዙ ብዙ ሽቱዎችን የሚያፈሩ፤
ኰሳኵሰ ወጸዓድዒደ ይወልዳ፡፡ ዥንጒርጒርና ነጫጮችን ይወልዳሉ፡፡
ወጸሊመ ልብሰ ይከድንዎን፡፡ ጥቁር ልብስን ያለብሷቸዋል፡፡
እምወርቀ ኦፌር ይፀድል፡፡ ከኦፌር ወርቅ ይልቅ ያበራል፡፡
ወይን ይትከየድ ውስተ መርህቦን፡፡ ወይን በሜዳቸው ውስጥ ይረገጣል፡፡
ብዙኃን ይዴመሩ ውስተ ማኅበሮን፡፡ ብዙዎች በማኅበራቸው ውስጥ ይደመራሉ፡፡
እምነ ጽዮን በሐ፡፡ እናታችን ጽዮን ሰላምታ ይገባሻል፡፡

14
ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍርኪ፡፡ ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፡፡
ንባብኪ አዳም፡፡ ንግግርሽ የአማረ ነው፡፡
ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሕኪ እንበለ ከዝምታሽ በቀር ጕንጭሽ እንደ ሮማን ቅርፊት ነው፡፡
አርምሞትኪ፡፡
ወከመ ማኅፈደ ዳዊት ክሣድኪ፡፡ አንገትሽም እንደ ዳዊት ግንብ ነው፡፡
እለ ተሐንጻ ዲበ ተልፍዮስ፡፡ ተልፍዮስ በሚባል ተራራ እንደ ተሠሩ፡፡
ዐሠርቱ ምእት ንዋየ ሐቅል ስቁል ውስቴቱ፡፡ በውስጡ ሺሕ የሜዳ ጸብት (የጦር ዕቃ) እንደተሰቀለበት፡
ኀበ ኢይሬእዮ ሰብእ ወኢይበጽሖ ፀሐይ፡፡ ሰው ከማያየው ፀሐይም ከማይደርስበት፤
ወኵሉ መዋጽፍተ ቤቱ ኀያላን ወጽኑዓን፡፡ በምድር ነገድ የቤቱ ዙርያ ኹሉ ኀያላንና ጽኑዓን፤
ወኀያላን እለ የዐቅብዎ ሠለስቱ እደው፡፡ የሚጠብቁት ሦስት አርበኞች ወንዶች ናቸው፡፡
፪ኤ አጥባትኪ ከመ ፪ኤ ዕጒለ መንታ ዘወይጠል፡ ኹለቱ ጡቶችሽ መንታነት እንዳላቸው እንደ ኹለቱ ፌቆ
፡ ገላግልት ናቸው፡፡
ዘይትረዐይ ውስተ ጽጌያት፡፡ በሱፍ አበባዎች መካከል የሚሠማራ፤
እስከ ሶበ ያስተነፍስ ዕለት ወይትሐወስ ጽላሎት፡፡ ቀኑ እስኪነፍስ ጥላውም እስኪመለስ ድረስ፤
አሐውር ለልየ ኀበ ደብረ ከርቤ፡፡ እኔ ከርቤ ወዳለበት ተራራ እሔዳለሁ፡፡
ወውስተ አውግረ ስኂን ምዑዝ፡፡ ምዑዝ የሚሆን ነጭ ዕጣን ወዳለበት ኮረብታም
ወይትቀባዕ እመዐዛሁ አውልዐ ገዳም፡፡ እሔዳለሁ፡፡
የምድረ በዳ ወይራም ከመዐዛው ይቀባል፡፡
ወይበልዓሁ አዕዋፈ ቈላት ወኢይመውታ፡፡ በቈላ ያሉ ወፎችም ይበሉታል፤ አይሞቱም፡፡
እስመ ይሔድሳ ውርዙቶን፡፡ ሕፃንነታቸውን ያድሳሉና፡፡
ንዒ እኅትየ እንቲኣየ ሠናይት ርግብየ፡፡ መልካሚቱ ርግብ እኅቴ ሆይ! ነዪ፡፡
ኵለንታኪ ሠናይት እንተ ኀቤየ፡፡ በእኔ ዘንድ ሁለንተናሽ የአማረ ነው፡፡
አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፡፡ በአንቺ ላይ ምንም ምን ነውር የለብሽም፡፡
ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡፡ መርዓት ሆይ! ከደጋ ነዪ ከደጋ ነዪ፡፡
ንዒ ወትወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት፡፡ ሃይማኖትሽን ደጀን አድርገሽ ትወጪያለሽ፡፡
ወታስተርእዪ ውስተ አድባረ ጽባሕ፡፡ በምሥራቅ ተራራ ትታያለሽ፡፡
እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን እንዘ ትሰቀዪ ጠለ፡፡ ከሳኔርና ከኤርሞን ተራራ ራስ ጠለ ረድኤትን
እየተመገብሽ፤
ከአንበሶች ጒድጓድና ከነብሮችም ጒድጓድ (ወጣሽ)፡፡
እምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት፡፡
ዮርዳኖስና ቤቴል ወደ ኤርሞን ይቀርባሉ፡፡
ዮርዳኖስ ወቤቴል ይቀርባ ኀበ ኤርሞን፡፡
እኅቴ መርዓት አሳዘንሽኝ፡፡
እራኅራኅክኒ እኅትየ መርዓት፡፡
አንድ ጊዜ በዐይኖችሽ ባለማየትሽ አሳዘንሽኝ፡፡
አራኅራኀክኒ ምዕረ በአዕይንትኪ፡፡
በአንገትሽ ቀና ባለማለትሽ፤
በአሐቲ ንብረተ ክሣድኪ፡፡
ጵጥጳሮስና አርስቢኖስ የልብስሽ መዐዛ ናቸው ፡፡
ጵጥጳሮስ ወአርስቢኖስ መዐዛ ልብስኪ፡፡
መጐናጸፊያዎችሽ እንደ ፓፓራስ እና እንደ እራሶርክ
ፓፓራስ ወእራሶርክ መዋጥሕኪ ይጼኑ፡፡

15
ሽቱዎች ይሸታሉ፡፡
ሚ አዳም አጥባትኪ እኅትየ መርዓት፡፡ እኅቴ መርዓት ሆይ! ጡቶችሽ ምን ያምሩ!
ወሐሊቦን ይጥዕም እመዓር ወሶከር፡፡ ወተታቸውም ከሸንኮርና ከመዓር ይጣፍጣል፡፡
ወእምተምር ዘውስተ ገነት፡፡ በገነት መካከል ካለ ተምርም ይልቅ፡፡
ጥቀ አዳም አጥባትኪ እምወይን፡፡ ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ እጅግ ያማሩ ናቸው፡፡
ወመዐዛ ዕፍረትኪ እምኵሉ አፈው፡፡ ሽቱሽም ከሽቱ ኹሉ ይልቅ መዐዛው የአማረ ነው፡፡
ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍርኪ፡፡ ከከንፈሮችሽም የማር ወለላ ይፈስሳል፡፡
ሐሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፡፡ ከአንደበትሽም በታች ወተትና ማር፤
ወጼና አልባስኪ ከመ ጼና ስኂን፡፡ የልብስሽም መዐዛ እንደ ነጭ ዕጣን መዐዛ ነው፡፡
ገነት ዕጹት እኅትየ መርዓት፡፡ እኅቴ መርዓት የታጠረች ተክል ናት፡፡
ገነት ዕጹት ዐዘቅት ኅትምት ፍናወ ዚኣኪ፡፡ መንገድሽ የታጠረች ተክል የታተመች ጕድጓድ ናት፡፡
ኀበ ኢይሬእዮ ኬንያ ወኢይከርዮ ሰራቂ፡፡ ብልሃተኛ ከማያየው ሌባም ከማይቈፍረው፤
ገነት ምስለ ፍሬ አቅማሕ፡፡ ከሽቱ ቅመም ጋራ ሽቱ አለሽ፡፡
ሰንድሮስ ምስለ ጵርስቅላ፡፡ ሰንድሮስ ጵርስቅላ ከሚባል ሽቱ ጋራ፤
ቆዕ ምስለ ናርዶስ፡፡ ቆዕ የሚባል ሽቱ ከናርዶስ ጋራ፤
ናርዶስ ዘምስለ መጽርይ፡፡ ናርዶስ ከቀጋ ጋራ፤
ቀጺመታት ወቀናንሞስ፡፡ ቀጺመታትና ቀናንሞስ ከሚባሉ ሽቶች፤
ምስለ ኵሉ ዕፀወ ሊባኖስ፡፡ ከደጋ ዕፀዋት ኹሉ ጋራ፤
ከርቤ ወዐልው ምስለ ኵሉ መቅድመ ዕፍረታት፡፡ ከርቤና ዐልው የሚባሉ ሽቱዎች ከነዚሁ ሽቱዎች ጋራ
አሉሽ፡፡

ነቅዐ ገነት ዐዘቅተ ማየ ሕይወት፡፡ የሕይወት ውኃ ጕድጓድ የገነት ምንጭ፤

ዘይውሕዝ እምሊባኖስ፡፡ ከደጋ የሚፈስስ፤

ተንሥእ ሰሜን ወነዐ ደቡብ፡፡ ሰሜናዊ ነፋስ ተነሥ፤ ደቡባዊ ነፋስም ና፡፡

ንፋህ ሠርቀ ንፋሕ ገነትየ፡፡ በማለዳ ጊዜ በጓሮዬ ተመላለስ (በተክሌ ላይ ንፈስ፡፡)

ለየሐዝ አፈዋተ ዚኣየ፡፡ ሽቱዬ ይፍሰስ፡፡

ለይረድ ወልድ እኁየ ውስተ ገነቱ፡፡ ወልድ ወንድሜ ወደ ተክል ቦታው ይውረድ፡፡

ወይብላዕ እምፍሬ አቅማሒሁ፡፡ ከሽቱም ቅመም ፍሬ ይብላ፡፡

ቦእኩ ውስተ ገነትየ እኅትየ መርዓት፡፡ እኅቴ መርዓት ሆይ! ወደ ተክል ቦታዬ ገባሁ፡፡

አረርኩ ከርቤ ምስለ አፈዋትየ፡፡ ከሽቱዬ ጋራ ከርቤን ለቀምኹ፡፡

በላዕኩ ኅብስትየ ምስለ መዓርየ፡፡ እንጀራዬንም ከማሬ ጋራ በላሁ፡፡

ሰተይኩ ወይንየ ምስለ ሐሊብየ፡፡ ወይኔንም ከወተቴ ጋራ ጠጣሁ፡፡

በልዑ ካልኣንየ ወጸግቡ፡፡ ወዳጆቼ በልተው ጠገቡ፡፡

ሰትዩ ውሉደ አኀውየ ወሰክሩ፡፡ የወንድሞቼ ልጆች ጠጥተው ሰከሩ፡፡

እስመ ዕንቡዛን እሙንቱ፡፡ እነርሱ አእምሯቸውን ያጡ ናቸውና፡፡

16
ወትእኅዞሙ ቅንአት ከመ ሰልብልያኖስ፡፡ እንደ ዲያብሎስ ቅንአት ትይዛቸዋለች፡፡
ሐረገ ወይን ኮነ መድኀኒትየ፡፡ የወይን ሐረግ መድኀኒት ሆነኝ፡፡
ዘእምኀሢሦን ይትገዘም ወበጎልጎታ ይተከል፡፡ ከኀሢሦን ተቈርጦ በጎልጎታ ይተከላል፡፡
ቃል ወልድ እኁየ መጽአ እንዘ ይጐደጕድ ወልድ ወንድሜ ደጃፍ እየመታ መጣ፡፡
ኆኅተ፡
አነ ንዉም ወልብየ ንቅህት፡፡ እኔ ተኝቼ ነበር፤ ልቡናዬ ግን ነቅታ ነበር፡፡
ቃል ወልድ እኁየ መጽአ እንዘ ይጐደጕድ ወልድ ወንድሜ ደጃፍ እየመታ መጣ፡፡
ኆኅተ፡
ቃለ እግዚአብሔር ይከብር እምአእላፍ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ከአእላፍ ይበልጣል/ይከብራል፡፡
አርኅውኒ እኅትየ ካልእትየ፡፡
እኅቴ ወዳጄ ደጃፉን ክፈችልኝ፡፡
ርግብየ ፍጽምትየ፡፡
ፍጽምት የምትሆኝ ርግቤ፡፡
ከመ ፋጻ ቀጢን ቃሉ ወከመ መሰንቆ ሐዋዝ
ያስተፌሥሐኒ በሰሚዖቱ፡፡ ቃሉን በሰማሁ ጊዜ እንደ ረቂቅ ፉጨት እንደ አማረ
መሰንቆ ልቡናዬን ደስ ያሰኘኛል፡፡
እስመ ርእስየኒ ምሉዕ ጠለ፡፡
ራሴ ጠልን የተመላ ነውና፡፡
ወድምድማየኒ ነፍኒፈ ሌሊት፡፡
ጒተናዬም የሌሊት ካፊያን ተመልቷል፡፡
አውፃእኩ አልባስየ እፎኑ እለብሶን፡፡
ልብሶቼን አውልቄአለሁ እንደምን አድርጌ እለብሳቸዋለሁ
ኀፀብኩ እገርየ እፎኑ እጌምኖን፡፡
እግሬን ታጥቤዋለሁ፤ እንደምን አሳድፈዋለሁ?
እስመ ተኀፀብኩ አነ በስኂን ወበአቅራህዮን፡፡
እኔ ስኂንና አቅራህዮ በሚባል ሽቱ ታጥቤዋለሁና፡፡
ወልድ እኁየ ፈነወ እዴሁ እንተ ስቊረት፡፡
ወልድ ወንድሜ እጁን ወደ መስኮት ሰደደ፡፡
ሶቤሃ ገሠሠ ርስኒ መለኮት፡፡
ያን ጊዜ የመለኮትን ኀይል ዳሠሠ፡፡
እስመ በሊኅ ልቡ እምኲናት፡፡
ከጦር ይልቅ ልቡናው ፈጣን ነውና፡፡
ከርሥየ ደንገፀት ቦቱ፡፡
ሆዴ በእርሱ ደነገጠች፡፡
ተንሣእኩ አነ አርኅዎ ለወልድ እኁየ፡፡
እኔ ለወልድ ወንድሜ ደጃፉን እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፡
እደውየ ያውሕዛ ከርቤ፡፡
እጆቼ ሽቱን ያፈስሳሉ፡፡
ወአጻብዕየ ከርቤ ምሉዓት፡፡
ጣቶቼም ሽቱን የተመሉ ናቸው፡፡
ውስተ እደ መንሠግ ተንሣእኩ አነ አርኅዎ
ለወልድ እኁየ፡፡ እኔ ለወልድ ወንድሜ እከፍትለት ዘንድ ወደ ቊልፉ
ለመሔድ ተነሣሁ፡፡
ወልድ እኁየ ኀለፈ፡፡
ወልድ ወንድሜ ሔደ፡፡
ነፍስየ ደንገፀት እምቃሉ፡፡
ሰውነቴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፡፡
ኀሠሥክዎ ወኢረከብክዎ፡፡
ፈለግሁት፤ አላገኘሁትም፡፡
ጸዋዕክዎ ወኢተሠጥወኒ፡፡
ጠራሁት፤ አልመለሰልኝም፡፡
ረከቡኒ መዓቅብት እለ የዐቅቡ ሀገረ፡፡
ሀገርን የሚጠብቁ ዘበኞች አገኙኝ፡፡
ዘበጡኒ ወፈቅዑኒ፡፡
ደበደቡኝ፤ ገመሱኝም፡፡
ነሥኡ ግልባቤየ እምላዕለ ርእስየ እለ የዐቅቡ
ቅጽረ፡፡ አምባ የሚጠብቁ ዘበኞች ክንንቤን ከራሴ ላይ አውርደው
ወሰዱብኝ፡፡

17
አምሐልኩክን አዋልደ ኢየሩሳሌም፡፡ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ሆይ! አማጽኛችኋለሁ፡፡
በኀይሉ ወበጽንዑ ለገዳም፡፡ በከሃሊነቱ በምድረ በዳ በአደረገው ተኣምራቱ፤
እመ ረከብካሁ ለወልድ እኁየ ከመ ታይድዓሁ፡፡ ወልድ ወንድሜን ያገኛችሁት እንደሆነ እንድትነግሩት፤
እስመ ንድፍት አነ በፍቅሩ፡፡ እኔ በፍቅሩ ፍላፃ ተወግቼ አለሁና፡፡

መሓልይ ፫-መዝሙረ ክርስቶስ መሓልይ 3-መዝሙረ ክርስቶስ


ወሣልስ ይነግር ዕርገተ ምድራዊ ትስብእት፤ ትርጒሙና ስሙ ሕይወት የኾነ፤
ምስለ ህላዌከ ልዑል እምነ ልዑላን ኀይላት፤ የመሪር ሞት ዘውድን በፈቃድህ የተቀዳጀህ፤
ወሀቤ ጸጋ ክርስቶስ በጊዜ መንግሥት፤ ለነገሥታት ሞገሰ ጸጋን የምታጐናጽፍ ክርስቶስ ሆይ!
እንተ ተቀጸልከ አክሊለ መሪር ሞት፤ ሦስተኛውም ከከበረ መለኮት ጋራ በተዋሕዶ፤
ዘፍካሬሁ ወስሙ ሕይወት፡፡ የዐረገ የምድራዊ ሰውነትን ዕርገት ይናገራል፡፡

በረድኤትከ መርዓት እምገዳመ ንዴት ወመከራ፤ በረድኤትህ ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን ከመከራ በረሓ፤
እንተ ዐርገት ብከ ኀበ ዘቀዳሚ ሀገራ፤ ወደ ቀደመ ሀገረ ክብሯ ከፍ ከፍ የአለችብህ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቀ ዳንኤል ወዕዝራ፤ የነቢያቱ የእነ ዳንኤልና ዕዝራ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ
ነፍስየ ዘትቤለከ ኢትርሳዕ ነገራ፤ ሆይ!
ውስተ ማኅደርከ ትረሲ ማኅደራ፡፡ ማደሪያዋን በማደሪያህ ውስጥ ታደርግ ዘንድ፤
ነፍሴ የምትለምንህን ልመናዋን አትርሳ፡፡

መሓልይ ፫-መዝሙረ ድንግል መሓልይ ፫-መዝሙረ ድንግል


መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ተዓርግ እምገዳም፤ ድንግል ማርያም ሆይ! ነቢይ ሰሎሞን
ከመ ሠርፀ ጢስ ዕጥነታ አዳም፤ ‹መዐዛዋ እንደ መልካም ጢሰ ዕጣን የሚጣፍጥ፤
ሰሎሞን ይቤ በእንቲኣኪ ማርያም፤ ከገዳም የምታበራ ይኽቺ ማን ናት!› አለ፤
ወሶበ ተጠብጠበ ብዝኀ ክብርኪ በክርታስ የክብርሽ ብዛት በክርታስና በቀለም ቢጻፍ፤
ወበቀለም፤ የዓለም መጽሐፍ በአልቻለውም ነበር፡፡
እምኢያግመሮ መጽሐፉ ለዓለም፡፡

መሓልይ ፬
መሓልይ 4
ምንት ውእቱ ወልድ እኁኪ እምውሉደ አኀው፡፡
ወልድ ወንድምሽ ከወንድማማች ልጆች ማንን ይመስላል?
ሠናይት እምአንስት፡፡
ከሴቶች ይልቅ የአማርሽ፤
ወምንት ውእቱ ወልድ እኍኪ እምውሉደ አኀው፡፡
ወልድ ወንድምሽ ከወንድማማች ልጆች ማንን ይመስላል?
ዘከመዝ መሐላ አምሐልክነ፡፡
ይኽን ያህል መሐላ ያማልሽን፤
በፀሐይኑ ወበያሮስ ወበከማንዮስ፡፡
በጨረቃና በፀሐይ በአስታርቦ ሸሽ ኮከብ ትመስዪዋለሽን?
ወልድ እኁየ ጸዐዳ ወቀይሕ፡፡
ወልድ ወንድሜ ነጭና ቀይ ነው፡፡
ምስለ ኵሉ ኅብረ ቤቱ፡፡
ከኹሉ የቤቱ ሽልማት ጋራ፤
ምንት ይሤኒ እምሊባኖስ እስቦን ወቀንሞስ፡፡
እስቦንና ቀንሞስ እንጂ ከሊባኖስ ምን ደስ ያሰኛል!
ይጸጊ መርህቦ፡፡
በሜዳው ያብባሉ፤
ወየዐውድዎ እልፍ ወትእልፊተ አእላፋት፡፡
እልፍ ወትእልፊተ አእላፋት መላእክት ይከብቡታል፡፡
ውሉድ እምአእላፍ፡፡

18
ርእሱ ወርቀ ቄፋዝ፡፡ ከአእላፍም የተመረጠ ነው፡፡
ድምድማሁ ድሉል ወጸሊም ከመ ቋዕ፡፡ ራሱ የቄፋዝ ወርቅ ነው፡፡
አዕይንቲሁ ከመ ርግብ ውስተ ምሉዕ ምዕቃለ ጐተናው የተሸራሸ እንደ ቍራም የጨቈረ ነው፡፡
ማያት፡፡ ዐይኖቹ በሞላ ኩሬ ውኃ እንዳሉ ርግቦች ናቸው፡፡
….
…. …..
…. …..
…..
ተፈጸመ ማሕልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ወልዱ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን የአመሰገነው ምስጋና
ለዳዊት፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡ በዚኹ ተፈጸመ፡፡ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና
ይግባው አሜን፡፡
አቡነ ዘበሰማያት…
አባታችን ሆይ…



19

You might also like