Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 52

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

“እናንተ ወንድሞች ሆይ መልካሙን ሥራ ለመሥራት አትታክቱ” 2ኛተሰ 3፣13

መግቢያ
የክርስቲያን ሥነ ምግባር መሠረቱ ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ የተቃኙ ልበ አምላክ
ዳዊት እና ልጁ ሰሎሞን ከእግዚአብሔር በተገለጠላቸው ዕውቀትና ጥበብ መሠረት የሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጋረ
ሊኖራቸው ስለሚገባው መልካም ግንኙነት ሲያስረዱ የዕውቀት መጀመሪያ አድርገው ያስቀመጡት ፈሪሃ
እግዚአብሔርን ነው፡፡
ክርስቲያኖች በሚመሩባቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ባሉባቸው መጻሕፍት ሁሉ በአዎንታ የተገለጹትን አንቀጾች
በአዎንታነታቸው፤ በአሉታ የተገለጹትንም እንደዚያው በአሉታነታቸው መጠበቅና መፈጸም አለባቸው፡፡ ምክንያቱም
ባለጋራችን ሰይጣን በበኩሉ ሥሩ ለሚለው ሕግ አትሥሩ፤ አትሥሩ ለሚለው ሥሩ የሚል የራሱ የሆነ የስሕተት
መንገድ ይዘረጋልናልና፡፡ ክርስቲያን የሆንን ሁሉ ግን የክርስቶስ ተከታይ እንደመሆናችን ሁሉ ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ
የወጣን ነን (ገላ 5፣1)። ስለዚህ ከሰይጣን ግብር ለመራቅ በሕገ-እግዚአብሔር ለመጠበቅ እንችል ዘንድ መንፈሳዊን
ከሥጋዊ ለይቶ ማወቅ ግዴታችን ነው (1ኛጴጥ 5፣8)፡፡
̋ባዶ በርሜል ጩኸት ታበዛለች።˝ ከመንፈሳዊ ዕውቀት፣ ከግብረ ገብነት ጠባይ ባዶ የሆነ ሰው ዕጣ ክፍሉ
እንደ ባዶ በርሜል ነው። ምግባር የሃይማኖታችን መገለጫ በመሆኑ ካመንን ሥራችን ያበራል፤ ታማኝነታችን
ለማግኘት በሕይወታችን መልካም ምግባር እያደረግን ለመጓዝ ይረዳናል (ዮሐ 15፣13)፡፡ ከኃጢአታችን መራቅ ማለት
ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ወዳጅነት መግለጽ ነው፡፡ የክርስቶስን ውለታ አለመርሳት የፍቅራችን መገለጫ ነው፡፡ ሕገ
እግዚአብሔርን ሽረን በኃጢአት ብንመላለስ ግን ይህንን ሁሉ ጸጋ አጣን ማለት ነው፡፡ በሥነ-ምግባር አምሮና ደምቆ
መታየት የክርስቲያን ወጉ ነው፡፡ ይህን ስንል የሥነምግባር መገለጫዎችን በሁለት ትላልቅ ክፍላት ከፍለነው ነው፡፡
እነርሱም፡-
ውጫዊ ሥነ-ምግባር
ለምሳሌ፡- አለባበስ፣ አካሄድ፣ አነጋገር፣ አበላል ወዘተ…
ውስጣዊ ሥነ-ምግባር
ለምሳሌ፡- ትሕትና (ምሳ 15፣33)፣ በጎነት(3ኛ ዮሐ 1፣11)፣ ፍቅር (ማቴ 22፣27)
1.1 የትምህርቱ ዓላማ
 በሃይማኖት ላይ መልካም ፍሬ ለማፍራት /ማቴ 3፡10፣ ያዕ 2፡10/
 ሕጉን፣ ሥርዓቱን፣ አምልኮቱን እንድናውቅ /መዝ 33፡11፣ ምሳ 1፡7/
 እኛ ተለውጠን ኖረንበት ሌሎችን ለመለወጥ /ማቴ 5፡16/
 የመንፈሳዊ ትምህርት ማሰሪያው የምሥጢራት መወሰኛው (መጀመሪያው) በጥሩ ሥነ-ምግባር ራስንና ሌሎችን
ቀርጾ መገኘት በመሆኑ እምነታችንና ምግባራችንን በጥሩ ሥራ መፈጸም አለብን፡፡
1.2 ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ማለት ምን ማለት ነው?
ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው ?
ክርስቲያን የሚለው ቃል፤ ቃል በቃል ሲፈታ ክርስቶሳዊ (የክርስቶስ የሆነ) ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ስለዚሀም
ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ተከታይ፣ ደቀ መዝሙር ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ክርስቲያን የሚለው ቃል
በሚከተሉት ነጥቦች ይተረጎማል፡-
 በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክነት ያመነ የተጠመቀ
 በእግዚአብሔር የባሕርይ አምላክነት አምኖ ሕጉንና ትእዛዙን ጠብቆ የሚኖር ሰው
2

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

 መታመንና ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ

 ለመጀመሪያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ክርስቲያን የሚለውን ሥያሜ ያገኙት በአንጾኪያ ነው፡፡ /ሐዋ 11፡26/
“በርናባስም ሳኦልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ1 ወጣ ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ2 አወጣው፡፡ በቤተክርስቲያንም
አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ ደቀመዛሙርቱም በመጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን
ተባሉ”

ሥን ማለት ምን ማለት ነው ?
“ሥን” የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ሥሩ ወይም መገኛው ‹‹ሠንየ›› የሚለው ግስ ነው፡፡ ትርጉሙም ማማር፣
ውብ መሆን፣ ደመ ግብ መሆን፣ በሥራና በጠባይ መዋብ መጌጥ ማለት ነው፡፡
በሌላም መልኩ ሥነ የሚለው ቃል በብዙ ቃላት ላይ በቅጥያነት እንጠቀምበታለን፡፡ ለምሳሌ፡- ሥነ ፍጥረት፣
ሥነ ልቡና፣ ሥነ ሥርዓት ሥነ ጥበብ ወዘተ በመሆኑም ጥናት ምርምር ትምህርት በመባል ይተረጎማል፡፡
ምግባር ማለት ምን ማለት ነው ?
ምግባር የሚለው የግእዝ ቃል ‹‹ገብረ›› ሠራ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መሥራት ማለት ነው፡፡
አጠቃላይ ድርጊትን በነቢብ፣ በገቢር ወይም በኀልዮ መፈጸምን ያመለክታል፡፡ በነቢብ (በንግግር) እንዲሁም በገቢር
(በተግባር) የሚፈጸሙ ድርጊቶች ውጤታቸው በግልጽ የሚታይ ሲሆን በኀልዮ (በዐሳብ በምኞት) የሚፈጸም ግን
ለመረዳት ብዙ ጊዜ ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን መልካም ለመሥራትም ይሁን ክፋን ለመፈጸም ወሳኙ ያለን ዝንባሌ
እና ፍላጎት ነው እንጂ መፈጸም አለመፈጸምን አይደለም፡፡ ሰው አንድን ኃጢአት በገቢር ከመፈጸሙ በፊት በልቡናው
ያስበዋል ያመላልሰዋል፡፡ ስለዚህም ገና በአሳብ ደረጃ እያለ ካልተቃወመው ከድርጊቱ እኩል አስከፊ ይሆንበታል፡፡
ለዚህም ነው ጌታችን ‹‹ቸ›› (ማቴ5፡27-28፤ማቴ9፡20-21)
 ምግባር በሦስት ነገሮች ሊፈጸም ይችላል፡፡

1 በኀልዮ (በሐሳብ በምኞት)


2 በገቢር (በተግባር)
3 በነቢብ (በንግግር)

ሥነ-ምግባር ማለት ምን ማለት ነው?

“ሥነ-ምግባር” የምለው ቃል እንደየተገለልጋዩ ክፍል የሚሰጠው የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል ተብሎ
ቢገመት ግምቱ ስህተት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥነ-ምግባር በክርስትና ሕይወት ሥነ-ምግባር በሌላ እምነት
ተከታዮች እና የተለያየ አመለካክት ባላቸው የፖለቲካ ሰዎች ዘንድ እንደየእምነታቸውና እንደየግንዛቤያቸው
ሊተረጎም ይችላል፡፡ በአንድ ወገን መልካምና ቅዱስ ተብሎ የሚታመንበት በሌላው ዘንድ ግን የተወገዘና የተበላሸ
ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ በዓለማችን ውስጥ ባሉት የሥራና የትምህርት ዘርፎች ሁሉ የተለያዩ የሥነ-ምግባር ዓይነቶች
አሉ፡፡ ለምሳሌ በህክምናው ዘርፍ ያሉት ባለሙያዎች ሊጠብቁት የሚገባ ከሥራው ጋር ተዛማች የሆነ የሥነ-
ምግባር(Ethics) ሲኖር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንም የሚጠብቁት በውትድርና መስክ ያሉት እንዲሁ
ሊፈጽሙት የሚገባ ሥነ-ሥርዓት (Discipline) ያለ ሲሆን በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ የሙያ ሥነ-ምግባር አለ፡፡
በእምነት አንጻርም ስንመለከተው ሁሉም የሚመራባቸውና ለእምነቱ ተከታዮች የሚያስተምራቸው ግብረ ገብነትና
1
ስለ ጠርሴስ የመጽሐፍ ቅዱስ ከተሞችና ሀገሮች፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ይመልከቱ
2
ዝኒ ከማሁ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የሥነ-ምግባር ዓይነቶች በርካታ ናቸው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምንመለከተው ግን ሥነ-ምግባር በክርስትና ሕይወት
ያለውን ሚና ነው፡፡
“ሥነ-ምግባር” የሚለው ቃል ሠነየ እና ገብረ ከሚለው ከሁለት ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መልካም፣
የተገባ፣ የተፈቀደ፣ የተወደደ፣ ያማረ፣ የሰመረ ምግባር የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡”ሥነ-ምግባር” በማለት ፈንታም
“ሥንዓ-ምግባር” ይላል “ሥንዕው” የተስማማ የተጣጣመ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ “ሥነ-ምግባር” ማለት የተስማማ
ምግባር፤ የተጣጣመ ምግባር ማለት ነው፡፡ ብላታ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስ በሥነ-ምግባር መጽሐፋቸው ላይ
“ሃይማኖትና ሥነ-ምግባር የእግዚአብሔር የወግ ዕቃዎች ናቸው፡፡ ሰዎችም የእግዚአብሔር ወግ ዕቃ ቤቶች
መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ማለት ምን ማለት ነው?
 ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ማለት በክርስቲያናዊ (በመንፈሳዊ) ሥራ ያማረ የተዋበ ማለት ነው፡፡
 የክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር መሠረቱ ፈርሃ እግዚአብሔር ነው፡፡
 አንድ ሰው እምነቱን በሥራ ሊተረጉም ይገባል፡፡ /ያዕ2፡26፣ ራዕ22፡12/

13 የሥነ ምግባር አስፈላጊነት


 ለመንፈሳዊ ሥራ እንድንተጋ ያደርገናል፡፡ ገላ 6፡7
 ከክፋትና ከርኩስት ከኃጢአት ራሳችንን እንድንጠብቅ፡፡ ሮሜ 12፡5
 ክርስቲያናዊ መንፈሳዊ ሥራ ሠርተን የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት፡፡ ማቴ 25፡31
 በመንፈሳዊ ሥነ-ምግባር ታንጸን ለሌሎች አርአያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ማቴ 5፡16
ሕግ
14 የሥነ-ምግባር ሕግጋት አከፋፈል
ሕግ ማለት ምን ማለት ነው
ሕግ ማለት ሐገገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ውሳኔ፣ ሥርዓት፣ ደንብ፣ ለማድረግ
የሚያዝ፣ ከማድረግ የሚከለክል ውሳኔ ሥርዓት ማለት ነው፡፡ “ማንኛውም ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ቅድስናን
አግኝቶ ይኖር ዘንድ የሥነ-ምግባር ሕጎች የትኞቹ እንደሆኑ ለይቶ ዐውቆ መተግበር ይኖርበታል፡፡
የሥነ ምግባር ሕጎች አከፋፈል

የሥነ ምግባር ሕጎች

መንፈሳዊ /አምላካዊ/ ሕግ ዓለማዊ ሕግ

ኢጽሑፋዊ ሕግ ጽሑፋዊ ሕግ የቤተ ክህነት ሕግ የቤተ መንግሥት ሕግ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ሕገ ልቡና

ሕገ ኦሪት ሐዲስ ኪዳን

(ዐሠርቱ ትዕዛዛት) (ስድስቱ ቃላተ ወንጌል)

 መንፈሳዊ (አምላካዊ) ሕግ፡- ለአዳም ፍጥረት ለሆነ ሁሉ ከልዑል እግዚአብሔር በተፈጥሮና በጽሑፍ የተሰጠ
ሲሆን ዘላለማዊ በመሆኑ እና ከእግዚአብሔር በመገኘቱ ወይም በመሰጠቱ መንፈሳዊ (አምላካዊ) ሕግ ይባላል፡፡
“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን መጻሕፍትን
ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት ለጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፡፡” 2ኛ ጢሞ 3፡16
 ሥጋዊ (ዓለማዊ) ሕግ፡- ሃይማኖት ያለውም የሌለውም በእኩልነት የሚመራበት ሕግ ነው፡፡ ሕጉንም
የሚያወጡት በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ስዎች ናቸው፡፡
“ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያረጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን?
መልካሙን አድርግ በእርሱም ዘንድ ምሥጋና ይሆንልሃል፡፡” /ሮሜ13፡1 ፤ 1ኛጴጥ2፡13/
 ኢ-ጽሑፋዊ ሕግ፡- የሰው ልጆች በተፈጥሮ ከልዑል እግዚአብሔር ያገኙት ሕግ ነው፡፡

“ያለ ሕግ ኃጢአትን ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና ሕግም ሳላቸው ኃጢአትን ያደረጉ ሁሉ በሕግ
ይፈረድባቸዋል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉ ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና፡፡
ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ እነዚህ ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ ለራሳቸው ሕግ
ናቸውና እነርሱም ኅሊናቸው ሲመሰክርባቸው አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያማካኝ በልባቸው
የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፡፡” /ሮሜ 2፡12-15/
 ጽሑፋዊ ሕግ፡- ከእግዚአብሔርም ከሰው ልጆችም ለሌሎችና ለእኛ ይጠቅማል ይበጃል ተብለው ተጽፈው
የተበረከቱልን ሕጎች ነው፡፡
 የቤተክህነት ሕግ፡- በሀገራችን ያሉ ቤተክርስቲያኖች የሚመሩበት እንዲሁም በቤተ ክህነት ውስጥ ያሉ የቤተ
ክህነቱ አስተዳዳሪዎች የሚመሩበት የሚተዳደሩበት ሕግ ማለት ነው፡፡
 የቤተ መንግሥት ሕግ፡-በቤተ መንግሥት ውስጥ ያሉ አካላት የሚመሩበት የሚተዳደሩበት ሕግ ነው።
 ሕገ-ልቡና፡- ይህ ሕግ በሰው ልቡና አንድ ጊዜ የተጻፈ በኋላ ሳያረጅ ሳያፈጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ
ያለ የኖረ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ሰው በተባለው ሁሉ በልቡናው ሰሌዳነት ተጽፎ የሚገኝ እያንዳንዱን ሰው ማንም
ሳያስተምረው ክፉና ደግ የሆነውን ሳይነግሩት እንዲያውቅ እንዲረዳ እንዲገነዘብ የሚያደርገው ስለሆነ ሕገ-ልቡና
እየተባለ ይጠራል፡፡ /1ኛቆሮ 6፡12 ፤ 10፡28/ 3“እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሲፈጥር ልቡናውን ንጹሕ ሰሌዳ
አድርጎ ሕጉን ቀርጾ በልቡናው ላይ ሥሎ ነው የፈጠረው፡፡ በዚህ ሕግ ይመሩ የነበሩት ከአዳም እስከ ሙሴ ያሉ
አበው ናቸው፡፡
 የብሉይ ኪዳን ሕግ (10ቱ ትእዛዝ) ፡- እግዚአብሔር አምላክ በቀጥታ በነብዩ ሙሴ አማካኝነት ለጊዜው
ለእሥራኤል ዘሥጋ ፍጻሜው ግን ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠው ነው፡፡ ሕጉም የተሰጠው እሥራኤላውያን
ከግብፅ በወጡ በ3ኛው ወር ፋሲካን ካከበሩ በ3ኛው ቀን በሲና (በኮሬብ) ነው፡፡ /ዘጸ19፡1 ዘጸ 4፡9-10/
 የሐዲስ ኪዳን ሕግ 6ቱ ሕገ-ወንጌል፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ሥጋዌ ሲመላለስ ተናገረው
ያስተማራቸው ሕግጋት ናቸው፡፡ ማቴ 5፡22-48

3
አባ መልከ ጻዲቅ የሦስቱን ሕግጋት አንድነት እንዲ ገልጸዋል (ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር 1983 ገጽ12)

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

1.5 ዐሠርቱ ትእዛዛት


የዐሠርቱ ትእዛዛት አጠቃላይ ገፅታ፡-
ትእዛዛቱ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የተደረጉ ቃል ኪዳኖች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ሙሴ በዘዳ 5፡2-3
ላይ “አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳንን አደረገ፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው
ከእኛ ከሁላችን ጋር እንጂ ከአባቶቻችን ጋር ይህቺን ቃል ኪዳን አላደረገም” ያለው፡፡ ትእዛዛቱ የተጻፉበት ሁለቱ
ጽላቶች “የቃልኪዳኑ ጽላቶች” /ዘዳ 9፡11/ ሲባሉ የተጻፉበት መጽሐፍ ደግሞ “የቃል ኪዳኑ መጽሐፍ” /ዘጸ 24፡7/
ይባላል፡፡
በመሆኑም የእግዚአብሔር ትእዛዛት በጌታና በእኛ መካከል የተደረገ ቃልኪዳን ነው፡፡ ይህንንም ቃልኪዳን
የምንቀበለው በእርሱ ስናምን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቃልኪዳኑን ከእኛ ጋር ሲፈጽም ያለውን ዋጋ እንረዳ ዘንድ
በታላቅ ግርማ እና በሆነ አኳኀን ነው፡፡
1.6 የዐሠርቱ ትእዛዛት ዓላማ
 ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው ውለታውን እንዲያስቡ፡፡
 ወደፊት በአረማውያን መካከል ሲመላለሱ ከኃጢአት እንዲጠበቁ፡፡
 መንፈሳዊ አካሄዳቸው ምን አቅጣጫ መከተል እንዳለበት ለማስተማር ነው፡፡
1.7 የዐሠርቱ ትእዛዛት አከፋፈል
 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን ፍቅር በሁለት ይከፈላል፡፡ ማቴ 22፡34-41
የመጀመሪያው ፍቅረ እግዚአብሔር ሲባል ሁለተኛው ደግሞ ፍቅረ ቢፅ በመባል ይታወቃል፡፡
 ፍቅረ-እግዚአብሔር፡- የምንለው ከትእዛዝ 1 እስከ ትእዛዝ 3 ያለውን ሲሆን የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያመለክት
ነው፡፡እነዚህ ትእዛዛት በቀጥታ እግዚአብሔር አምላክን ስለማክብር እና ስለመውደድ የታዘዙ ትእዛዛት ስለሆኑ
ፍቅረ-እግዚአብሔር ተብለዋል፡፡
 ፍቅረ ቢጽ፡- የምንለው ከትእዛዝ 4 ጀምሮ እስከ ትእዛዝ 10 ያለውን ሲሆን የሰው ልጅ እርስ በእርሱ በፍቅር
እንዲኖር የሚያተጋ ነው፡፡
1.8 ዐሠርቱ ትእዛዛት ለእኛ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው?
ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጪ እንድንሆን፡፡ ሆሴ4፡6
የኃጢአት ሱሰኞች እንዳንሆን፡፡ ሕዝ 18፡32
ከጠላት ዲያቢሎስ እንድንጠበቅ፡፡ ራዕ 2፡10
1.10 ዐሠርቱ ትእዛዛት በቊጥር 10 ስለመሆናቸው
10 ቊጥር
10 ቊጥር የምልአት ምልክት ነው፡፡ ስለዚህ በዐሠርቱ ትእዛዛት ውስጥ ዐሥር ቊጥር ሁሉንም ሕጎች እና
ትእዛዛትን ያመለክታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል በዐሥር ቊጥር በምልአት መመሰሉን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ
ምሳሌዎች እንመለከታለን፡፡
10 ቊጥር በእሥራኤላውያን ዘንድ የሙሉነት መገለጫ ስለሆነ
የ10 ደናግላን ምሳሌ የ5ቱ ሰነፎችና የ5ቱ ልባሞች (ማቴ25፡1) /ማቴ 25-1/ በዚህ ምሳሌ ውስጥ ዐሥር ቊጥር
ሁሉንም ሰዎች ጻድቃንን ሆነ ኃጥእን፤ ዓለምን ሁሉ ይወክላል፡፡
የ10 ባሮች ምሳሌ፡- 10 4ምናን ሰጣቸው እስከመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው፡፡ ሉቃ19፡3

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የ10 ድሪም ምሳሌ ሉቃ15፡8


የዐሥራት በኩራት ምሳሌ ትሚል3፡7-11
ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩ 10 5ደጋግ አባቶች ምሳሌ
እግዚአብሔር በግብፅ ሀገር 610 መቅሠፍቶችን በማዝነብ ፈርኦን እሥራኤልን እንዲለቅ ያደረገው ምሳሌ
ቦኤዝ ለማግባት ባሰበ ጊዜ 10 ምስክሮችን የመጥራቱ ምሳሌ፡፡ ሩት4፡2
ቅዱሳንን ከሕዝቡ መካከል ለማጥፋትና በእሥራኤላውያን ላይ ክፉ ለማድረግ የተማከሩ 710 የአሕዛብ ሀገር
ሕዝቦች ምሳሌ መዝ 62፡6
በብሉይ ኪዳን ታሪክ 8ለምጽ የወጣባቸው የነበሩ 10 ሰዎች ምሳሌ፡፡
1.11 ዐሠርቱ ትእዛዛት በምን ላይ ተሰጠ?
ዐሠርቱ ትእዛዛት በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት በሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች ላይ ተጽፎ አስቀድሞ ለእሥራኤል
ዘሥጋ ፍጻሜው ግን ለሰው ልጆች ሁሉ ተሰጥቷል፡፡ ዘጸ 31፡18
ጽላት ማለት ምን ማለት ነው
ጽላት ማለት ሰሌዳ ማለት ሲሆን ሰሌዳነቱም ለእግዚአብሔር ሕግጋትና ትእዛዛት ነው፡፡ ለነብዩ ሙሴ የሰጠውም
ጽላት ሁለት ነው፡፡
 በመጀመሪያ ጽላት ላይ፡-ፍቅረ እግዚአብሔርን
 በሁለተኛው ጽላት ላይ፡-ፍቅረ ቢጽን ጽፎ ለነብዩ ሙሴ ሰጠው፡፡
እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ ፍቅረ እግዚአብሔርን አስቀድሞ ስጠው
 በፍቅረ ቢጽ(ሰብእ) ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀድማልና፡፡
 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ ጸሎት ባስተማረበት ላይ ከፍቅረ ቢጽ ፍቅረ-
እግዚአብሔር እንደሚበልጥ እንደሚቀድም ነግሮአቸዋል፡፡ ማቴ6፡9-14

አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ
በምድር ትሁን(ፍቅረ እግዚአብሔር) የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችንን ይቅር (ፍቅረ ቢጽን) በለን እኛም
የበደልነውን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባኝ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል
ክብር ምሥጋና ለዘላለሙ አሜን፡፡

4
ምናን ማለት 2000 መክሊት ወቄት (40ድረም ሚዛን) መክሊት ማለት ነጥር፣ ወርቅ፣ እጥፍ ድርብ
5
አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜህ፣ ኖኅ
6
ውኃው ወደ ደም መለወጥ፣ ጓጉንቸር፣ ቅማል፣ ዝንብ፣ ቸነፈር፣ ያሬድ፣ በረዶ፣ አንበጣ፣ ጨለማ፣ የበኩር ልጅ መሞት
7
አዶማውያን፣ እስማኤላውያን፣ ሞአባውያን፣ አጋራውያን፣ ጌባላውያን፣ አሞናውያን፣ አማሌታውያን፣ ፍልስጤማውያን፣
ጢሮሳውያን፣ አሞራውያን
8
ነብዩ ሙሴ አ.ዘዳ4፡6፣ የሙሴ እህት ማርያም ኦ.ዘኁ12፡10፣ ንዕማን 2ኛ ነገ.5፡1-26፣ ግያዝ 2ኛ ነገ.5፡27፣ ዐራቱ የሰማርያ ሀገር
ለምጻሞች 2ነገ 7፡8፣ አዛርያስ 2ኛ ነገ.15፡5፣ ነብዩ ኢሳይያስ ት.ኢሳ.6፡7

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ነብዩ ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እነዚህን ትእዛዛት ተቀብሎ ወደ እሥራኤላውያን ያሉበት ቦታ ስወርድ


እሥራኤላውያን በሌላ ጣኦት እያመለኩ አገኛቸው በዚህ ጊዜ ሙሴ ለእግዚአብሔር ፍቅር ቀንቶ የተሰጠውን
ሁለት ጽላት ወደ ጣኦታቸው ወረወረው ጣኦቱ ደቀቀ ጽላቱ ተሰበረ፡፡
እግዚአብሔርም ነብዩ ሙሴን ጽላቱን ሰርተህ አንጣ እኔም እጽፍበታለው አለው፡፡አዘዳ34፡1-28
በኦሪት ዘመን ታቦት ማለት ማደሪያ መገለጫ ሲሆን ማደሪያነቱ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡
 ለእግዚአብሔር ክብር
 ለጽላቱ
የጽላቱ ማደሪያ እንዲሆን ታቦት ከግራር እንጨት እንዲሰራ ታዟል፡፡ኦዘዳ25፡10-22
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ታቦትና ጽላትን እንደ ብሉይ ኪዳን በመለያየት ሳይሆን በአንድነት ለመስዋዕት እንዲመች
ይቀረጻል፡፡
በብሉይ ኪዳን ታቦትና ጽላት የእንስሳ ደም ይሰዋበት ነበር፡፡ በአዲስ ክዳን ግን ታቦትና ጽላትና የጌታችን
የመድኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ይፈተትበታል ይሰዋበታል ለምእመናን የእግዚአብሔር
ልጅነትና የዘላለም ሕይወት ያሰጣል፡፡ ዮሐ 6፡53

2.1 ትእዛዝ 1
‹‹እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ››
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ
 እግዚአብሔር የሁሉ አስገኚ ፈጣሪ እንደሆነ እንዲሁም፤ የእግዚአብሔር ገዢነት እንዲታወቅ
 እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ሲል በፍጽም ፍቅሩ የሚወደን መሆኑን፣ ፍቅሩን፣ ቸርነቱን ሰው ውለታውን
እያሰበ እንዲያመሰግነው፡፡ ኤር 29፡11
 ከእኔ በቀር ሲል አንድ አምላክ የሁሉ አስገኚ ፈጣሪ፣ መጋቢ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያስገነዝበናል፡፡ ዘፍ 1፡1

በአጠቃላይ ይህ ትእዛዝ አምልኮትን ይመለከታል፡፡ አምልኮት ሲባል እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅርን በእግዚአብሔር
ላይ መጣል ማለት ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ 13፡13
ዐሥርቱ ትእዛዛት የምግባር መመሪያ ብቻ ሳይሆን በይበልጥ የሃይማኖት ሕግ ያለበት ነው፡፡ ከምግባር ደግሞ
ሃይማኖት ስለሚቀድም የዐሥርቱ ቃላት የመጀመሪያ አንቀጽ ሀልወተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔርን መኖር)
የሚገልጽ ነው፡፡ ከእኔ በቀር ብሎ መናገሩ በሰው ልጅ የተጠረቡትንና የተለዘቡትን ሰው ያቆማቸውን የሚታወቁትን
ጣዖት ብቻ ማለት አይደለም፤ በዚሁ አንጻር አንዳንድ ሰዎች ኃይላቸውን፣ ውበታቸውን፣ ዝናቸውን ወዘተ…
ያመልካሉና እነዚህንም ይጨምራል፡፡
ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ እኔ ነኝ ሲል
ለእሥራኤል ሕዝብ ብቻ የተነገረ መስሎን ራሳችንን ማግለል አይገባንም፤ ይህ ቃል እሥራኤል ዘነፍስ
ለተባለች ለቤተክርስቲያን በምሳሌነት ይነገራል፡፡ የጥንት እሥራኤላውያንን ከግዞትና ከባርነት ነጻ ያወጣና ያዳነ
አምላክ በዘመኑ ፍጻሜ ደግሞ በልጁ በኢየሱስ ክርሰቶስ በስሙ የታመኑትን ሁሉ በነፍስም በሥጋም ታድጓቸዋል፡፡
እኛን ክርስቲያኖችን ከዲያቢሎስ ግዛት፣ ከኃጢአት ባርነት ነጻ አድርጎ አድኖናል፤ ከሞት ወደ ሕይወት ከሲዖል ወደ
ገነት አሻግሮናል፡፡ ስለዚህ ቸርነቱንና የማዳን ሥራውን እያሰብን በፍቅርና በምሥጋና ልናመልከውና ልንሰግድለት
ይገባል፡፡ እዚህ ጋር ግን እግዚአብሔር ሕጉንና ትእዛዙን ከመስጠቱ በፊት አስቀድሞ የቸርነቱንና የማዳን ሥራውን
እንደፈጸመልን እናስተውል፣ እሥራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ነጻ ካወጣ በኋላ ነው ይህን ሕግና ትእዛዝ (ቃልኪዳን)
የሰጣቸው፡፡ ዘጸ 19፡20፣ ዘጸ 20፡1
እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

አምላካችን እግዚአብሔር በፍጹም ቸርነቱ የሚወደን መሆኑንና ማንነቱን ጭምር አምላካችሁ እግዚአብሔር
እኔ ነኝና በማለት ገልጦልናል፡፡ ይህ ቃል የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር
ያመለክታል፡፡
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ ተብሎ መነገሩ በሰው ልጅ የተጠረቡትንና ሰው ያቆማቸውን
የሚታወቁትን ጣኦታትን ብቻ ማለት አይደለም በዚሁ አንፃር አንዳንድ ሰዎች ኃይላቸውን ያመልካሉ ውበታቸውን
ዝናቸውን ወዘተ ያመልካሉ፡፡ከዚህ ሌላ ዋና ዋና የተባሉትን የባዕድ አምልኮ ዓይነቶችን በጥቂቱ እንመለከታለን
ገንዘብ፡- ማንም ሰው እግዚአብሔርን አመልካለሁ እያለ ገንዘብን ከተገቢው መጠን በላይ የሚያፈቅር ከሆነ ራሱን
ያሞኛል ገንዘብን ከእግዚአብሔር አብልጦ መውደድ ጣኦትን ማምለክ ነውና ሰው የገዛ ገንዘቡ ጣኦት ሊሆንበት
አይገባም፡፡ማቴ 6፥24’’ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም
ይወዳል ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡’’
ዝናን፡- አንድ አንድ ሰዎች በሚገባ ወይም በማይገባ ነገር ለዝናቸው ወይም ለሚያውቁት ሰው ዝና ሲሟገቱ
ይታያሉ
ዓለምንና የዓለምን ፍላጎት፡-ዓለም ሌላኛዋ ጣዖት ናት ከዓለም ጋር በፍቅር የተሳሰረ ሰው ለእግዚአብሔር ያለውን
ታዛዥነትና በእርሱ ያለውን እምነት ይረሳል፡፡ለዚህ ነው ሐዋርያው ያዕቆብ በመልዕክቱ ’’ዓለምን መውደድ
ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን; እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር
ጠላት ሆኗል’’ያዕ 4፥4
ራስን ማምለክ፡- ከጣዖታት ሁሉ የበለጠውና አደገኛው ጣዖት ራስን ማምለክ ነው፡፡ራሱን የሚያመልክ ሰው
የእርሱን ማንነት እርሱ ብቻ የሚያውቀውና በእርሱ አዕምሮ የተሳለው እርሱነቱ ብቻ ነው ከእርሱ በቀር ሌላው
ሰው ሁሉ ስህተተኛ ነው፡፡እንዲህም ስለሆነ ከዚህ መሰል አምልኮ ጣዖት እንድንጠበቅ ጌታችን ሲመክረን
’’በላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ’’ማር 8፥34
አማልክት ዘበጸጋ
አማልክት ዘበጸጋ ማለት በጸጋ አምላክነትን ያገኙ ማለት ነው፡፡ /ዘጸ 7፡1፣ መዝ 81፡1፣ ዮሐ 10፡34/ ይህ የሚያሳየን
ከአማላጅነት አልፈው የአምላክነትን ሚና ይጫወቱ ዘንድ የጸጋ አምላክ ሆነው መሾማቸውን እንረዳለን፡፡
ለምሳሌ፡-
 እግዚአብሔር በባሕርይው ብርሃን ነው፡፡ ዮሐ 8፡12፣ 1ኛ ጢሞ 1፡17፣ 1ኛ ዮሐ 1፡5 ቅዱሳን ደግሞ በጸጋ
ብርሃንነትን አግኝተዋል፡፡ /ማቴ 5፡14/
 ሁሉን ማድረግ የሚቻለው እግዚአብሔር ነው፤ ኢዮ 42፡2፣ ቅዱሳንም ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ሁሉን
ያደርጋሉ፡፡ ዮሐ 14፡12
 ሁሉን ማወቅ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፤ ቅዱሳንም በጸጋው ሁሉን ማወቅ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 2ኛ ነገ 6፡
8፣ ሐዋ 5፡1፣ 1ኛ ቆሮ 2፡15
የእግዚአብሔርን አክብሮት ለቅዱሳን አንሰጥምና እንድያውም ለእነርሱ የምንሰጠው ክብር እግዚአብሔርን
ማክበር ስለሆነ በብዙ ምሥጋና ለእግዚአብሔር እናቀርባለን፡፡ 2ኛ ቆሮ 9፡13 ስለዚህ ቅዱሳንን ማክበር
ከእግዚአብሔር ውጭ ልዩ አምልኮት አለመሆኑን መገንዘብና ማስገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
የእግዚአብሔር ምክር ለዘላለም ነው፤ እግዚአብሔር የማያደርገውን አይናገርም፣ የተናገረውንም አያስቀርም፣
ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም፣ ዘመናት ይቀየራሉ እግዚአብሔር ግን ያው እግዚአብሔር ነው
አይለወጥም፡፡ (መዝ 32፡11፣ መዝ 101፣25-28፣ ማቴ 4፡35) ስለዚህ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል የማያስቀር
መሆኑን ማመን ይገባናል፡፡ ባለፉት ዘመናት የሠራ እግዚአብሔር ዛሬ እንደማይሠራ በማሰብ የራሳችንን አማራጭ
9

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

መፍጠር የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ያለ ነው፡፡ ዕብ 13፡8 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡
ስለዚህ አይወሰንም ሐዋ 5፣ ዮሐ 20 ይህን ሕግ የሚያፈርሱ ሰዎች ብዙ አይነት በደል ይበድላሉ፡፡ ይኸውም፡-
የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የተባለውን ትእዛዝ ይለውጣሉ፡፡
ከቤተክርስቲያን አንድነት ውጭ ይሆናሉ፡፡
ተስፋ ቢስና ሁሉ የጨለመባቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡
የአምልኮ ስግደት ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም ሊሰጥ አይችልም ደግሞም አይገባም፤ አክብሮት፣ የጸጋ ስግደት፣
ስማቸውን መጥራት ግን ለመላእክት ለቅዱሳን ልናደርግ ይገባል፡፡ በቅዱሳን ስም ምጽዋት ልንሰጥ፣ በጎ አድራጎትን
ልናደርግ፣ በጸሎትም ስማቸውን ልንጠራ የአማላጅነታቸውን ቃልኪዳን እንዲፈጽሙልን ልንለምን እንችላለን፡፡ ማቴ
10፡41-42
የተቀረጸ ምስል
የተቀረጸ ምስል ማለት አንድ ቅርጽ ሠርቶ ይህ አምላክን ይመስላል ወይም አምላክ ነው ብሎ የሚመለክ
ነው፡፡ ይህምእግዚአብሔርን ከማምለክ በቀር የተቀረጸውን ምስል ማምለክ የማይገባና ከጣዖት አማልኮ የሚቆጠር
መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ይህ ትአዛዝ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተሳሉትን የቅዱሳን ሥዕሎችና ለእነዚህ
የቅዱሳን ሥዕሎች የሚሰጠውን ክብር የሚቃረን አይደለም፡፡
በአብያተ ክርስቲያናት ተሰቅለው ሆነ ተለጥፈው የምንመለከታቸው ሥዕሎች የቅዱሳን ዜና ሕይወትና
መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን ጭምር በማሰብና በማስታወስ አብነት እንድናደርጋቸው ለማስቻል ነው፡፡
የምንሳለማቸውም በሥዕሎቹ ለተገለጡት ቅዱሳን ፍቅራችንን ለመግለጥና ስለተጋድሏቸውም ስለምናከብራቸው
እንጂ ስለምናመልካቸው አይደለም፡፡
2.2 ትእዛዝ 2
‹‹የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ››
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ
ለእግዚአብሔር ስም ክብር እንድንሰጥ እንዲሁም በሆነውም ባልሆነውም ቦታና ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም
ማንሳት እንደማይገባ ለማሳሰብ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቅዱስ ስም ንጹሐን መላእክት እንኳን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚጠሩት ክቡር በመሆኑ
የሰው ልጆችም አክብረውት ክብርን እንዲያገኙ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከግብፅ ምድር ስለመውጣታቸው ውለታውን እንዲያስቡ፣ ወደ ፊት በአረማውያን መካከል
ሲመላለሱ ከኃጢአት እንዲጠበቁ፣ መንፈሳዊ አካሔዳቸው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሆን፣ የእግዚአብሔርን ስም
በከንቱ መጥራት እንደሌለብን ክብር መስጠት እንዳለብን ለማሳሰብ ነው፡፡
ስም ምንን ይገልጣል
ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው፡፡ ስም ጠባይን፣ ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ
ሆኖ ሊሰየም ይችላል፡፡
የእግዚአብሔር ስም
የአምላካችን ስም የከበረና ቅዱስ ሲሆን በተራው ነገር ሁሉና በየአጋጣሚው ልንጠራው አይገባም፤ ምክንያቱም
በሆነው ባልሆነው ስሙን በመጥራት ልማድ ወደ ማድረግ ደረጃ ደርሰን ክብሩንና ፍቅሩን እናጣለንና ነው፤ ስለዚህ
ከዚህ ልንጠበቅ ይገባል፡፡

10

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

እግዚአብሔር ባሕርይውን፣ ህልውናውን፣ ግብሩን የሚገልጽ ብዙ ስም አለው፡፡ /ዘጸ 15፡3/ ከብዙዎቹ


የእግዚአብሔር ስሞች ውስጥ፡
 ኤል- ኃይል ማለት ነው፡፡ /ዘፍ 17፡1/
 ኤሎሄ- አምላክ ማለት ነው፡፡ /ማቴ 27፡36/
 ያህዌ- ያለና የሚኖር ማለት ነው፡፡ /ዘፍ 22፡4፣ ዘጸ 3፡13-15/

በሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ወልድ በሥጋ ሲገለጥ በሚከተሉት ስሞች ተጠርቷል፡፡


 አማኑኤል /ኢሳ 7፡14፣ ማቴ 1፡23/
 ኢየሱስ /ማቴ 1፡25፣ ሉቃ 1፡31/
 መሲህ /መምህር/ ዮሐ 1፡42
 መድኃኔዓለም /ዮሐ 4፡42/
የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም፤ ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል፡፡ ማቴ 12፡20 የማይታየው እግዚአብሔር
ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው፡፡ በተለይም ክርሰቶስ በሥጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል፡፡
/ዮሐ 17፡26/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው፡፡ ፊል 2፡9-11 ‹‹እግዚእ መባልን፣ አምላክ መባልን፣ ወልድ መባልን ሰጠው፡፡
››
‹‹ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘለዓለም እንኖራለን፡››
ሚኪ 4፡5 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ስም አክብረን ልንይዘው ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው
አይገባም፡፡
 የእግዚአብሔር ስም ታላቅ፣ ቅዱስ፣ ድንቅ ነው ፡- የልዑል የእግዚአብሔር ስም እንደማንኛውም ስም በልማድ
የምንጠራው አይደለም፤ ምክንያቱም ስሙ ቅዱስ ነውና፡፡ ሉቃ 1፡49 ‹‹ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ነገር አድርጓልና
ስሙም ቅዱስ ነው፡፡››
 የእግዚአብሔር ስም ድንቅ ታምራትን ያደርጋል ፡- ማር 16፡15፣ የሐዋ 3፡6፣ 4፡7፣ 19፡11
 የእግዚአብሔር ስም ለአጋንንት አስፈሪና አስደንጋጭ ነው፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሴቲቱ ያደረውን የጋኔን
መንፈስ ‹‹ከእርሷ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለው አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ›› /የሐዋ 16፡18/
 የእግዚአብሔር ስም በችግር ጊዜ መጠጊያ ነው፡- ‹‹አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኳቸው ፣
መክበቡንስ ከበቡኝ በእግዚአብሔር ስም አሸነፍኳቸው››
መጽሐፍ ቅዱስ ከንቱ የሚላቸው ነገሮች
ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ ፣ የማይገባ ነገር ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ
መጥራት እንደማይገባ ይህ ትእዛዝ ያስተምረናል፡፡ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ከምንጠራባቸው ነገሮች መካከል
እንመለከታለን፡፡
 መሐላ
 በእግዚአብሔር ስም በሐሰት መማል
 ለሥጋ ፈቃድ በከንቱ መማል
 በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል
 በእግዚአብሔር ስም መራገም
መሐላ
የእግዚአብሔር ስም በከንቱ ከሚጠራበት መንገድ አንዱ መሐላ ነው፡፡ መሐላ ማለት አንድን ነገር ለማረጋገጥ ወይም
ተስፋ የተሰጠው ነገር እንዲፈፀም ለማስረዳት እግዚአብሔርን ምስክር ዳኛና ዋስ እንደማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ መሐላ
በማይረባ የሰዎች ጉዳይ ውስጥ ኃያሉን እግዚአብሔርን በምስክርነት መጥራት የእግዚአብሔርን ክብር ማዋረድ

11

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

መሆኑን መረዳት አለብን፤ በእውነተኛ ነገር እንኳ ቢሆን መሐላ አይፈቀድም፤ ……… በብሉይ ጊዜ መሐላ የተፈቀደ
ነበር ምክንያቱም አረማዊነት የበዛ ከመሆኑ የተነሣ አሕዛብ ሁሉ በጣዖታቸው ይምሉ ስለነበር ሕዝበ እግዚአብሔር
ደግሞ ይህን በመስማት ወደ እነርሱ እንዳያዘነብሉ ነገር ግን መመኪያና መጠጊያ የሆነ አምላክ እንዳላቸው
እንዲያምኑ ‹‹እግዚአብሔር አምላክህን ፍራ፣ እርሱንም አምልክ፣ በስሙም ማል፡፡›› የሚል ትእዛዝ ተሰጥቷል /ዘዳ 6፡
13/ ነገር ግን በሐዲስ ኪዳን ፈጽማችሁ አትማሉ የሚል ሥርዓት ስለተላለፈልን ርሱን ይህንን በመከተል
በእግዚአብሔርም ሆነ በቅዱሳኑ እንዲሁም ሌሎች በምንወዳቸው ሰዎች ከቶ መማል የለብንም፡፡ የዘመነ ሐዲስ ሰዎች
እንደመሆናችን መጠን እውነቱን እውነት ሐሰቱንም ሐሰት ማለት ይገባናል፡፡
በእግዚአብሔር ስም በሐሰት መማል
‹‹መሐላችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ እንጂ በሐሰት አትማሉ›› …… ሐሰት የእውነት ተቃራኒ ነው፡፡ የሆነውን አልሆነም፣
ያልሆነውን ሆነ ብሎ አገለባብጦ መናገር ወይም እውነቱን ሐሰት፣ ሐሰቱን እውነት ብሎ በሐሰት መመስከር ነው፡፡
ሐሰት ሳይዘሩት የሚበቅል የጥፋት አረም ሲሆን ከሰናፍጭ ቅንጣት ባነሰ መጠን በሰው ኅሊና ሠርጻ እያደገና ስር
እየሰደደ በመሄድ የበቀለበትን ሰው ሳያጠፋ የማይለቅ ትልቅ ደዌ ነው፡፡ ሐሰትን መናገር ተናጋሪውን ያቀላል፣
አመኔታን ያሳጣል እንዲሁም ከእውነት ሚዛን ያወጣል፡፡ ዘካ 5፡4
ለሥጋ ፈቃድ በከንቱ መማል
‹‹ዓለም ባለማወቅ ለከንቱ ነገር ተገዝቷልና በተስፋ ስለ አስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም›› ሮሜ 8፡20
የእግዚአብሔርን ስም መቼ እንጥራ
1. በሰላምታ ጊዜ ጴጥ 1፣1-2 ሮሜ 1፣7
2. በአምልኮ ጊዜ መዝ 134፣3፣3 ት/ሜል 1፣11፣ፊልጵ 2፣10 ኢዮ 3፣32 ዮሐ 14፣14
3. በቡራኬ ጊዜ ዘኋል 6፣23 2ኛ ቆሮን 13፣13

2.3 ትእዛዝ ሦስት


የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ ዘጸ 20፥8
የትምህርቱ ዓላማ
ከሥጋችን ይልቅ ነፍሳችን የምትበልጥ መሆንዋን እንድናውቅ
ከዚህ ጥላ ዓለም በኃላ የማታልፍ እረፍት መንግስተ-ሰማያት እንዳለን የምንገልፅበት የራሳችን ፈቃድ ያይደለ
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስቀደም እንደሚገባን ለእግዚአብሔርም ተገዢ መሆናችንን የምንገልፅበት ነው፡፡
በመንግስተ-ሰማያት የሚኖረንን ሕይወት የምንገልፅበት ነው፡፡
የሚቀድሰን እግዚአብሔር እንደሆነ የምንገልፅበት ምልክት ናት፡፡ ሕዝ 20፥2
የሰው ባሕርይ ደካማ ነውና ሥጋንም አሳርፎ የነፍስን ሥራ በዚህች ቀን እንዲሰራባት፡፡
ለሰንበት ቀን ክብር እንድንሰጥ ዘጸ 20፥8-11
ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው?
ሰንበት የሚለው ቃል ከዕብራይስጥ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም አቆመ፤ አረፈ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር
ድካም ኖሮበት ሳይሆን ሊፈጥር ያሰበውን ነገር ጨረሰ ለማለት ነው፡፡ ዘፍ2፥2
በተጨማሪም የሰው ልጅ ከጌታ ጋር የሚቀራረብበት መገናኛ መንገድ ነው፡፡ ከማንኛውም ሥጋዊ ተግባር የምንርፍበት
ትርጓሜውም የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናስታውስ የሚደረግበት ቀን ነው፡፡ ይኸውም በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡
ሰንበት የመንግስተ-ሰማያት ምሳሌ ናት፡፡ የሰው ልጅ በዓለም ሰርቶ ወጥቶ ወርዶ በመልካም ሥራው የሚያርፍበት
ቦታ ናት፡፡ ዘዳ5፥14 ማር2፥28

12

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ሰንበትን ከሌሎች ትእዛዛት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?


1. እግዚአብሔር ለህዝቡ የሰጠው ቀዳሚ ትእዛዝ በመሆኑ ዘፍ2፥3፤ ዘጸ16፥23
2. እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈበት በመሆኑ ዘፍ 2፥1-3
3. ከፈጠራቸው ፍጥረታት በሙሉ ከሰው ቀጥሎ የባረከው የቀደሰው ሰንበትን ብቻ በመሆኑ ዘፍ 1
4. ከሰባቱ እለታት ለእረፍት የተመረጠች በመሆኗ
የሰንበት ቀን ሁለት ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡
የሰንበት ቀን የእረፍት ቀን ስለሆነ የሚከተሉት ሁለት ነገሮችን ያሳስበናል፡፡
1. ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት ከአምላኩ ጋር ያለው ግንኙነት የነበረው እረፍት
2. ከጌታችን ከመድኃታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት(ቤዛነት) የተገኘው ዘለዓለማዊ የነፍስ እረፍት ዕብ4፥1-10
ሰንበት በብሉይ ኪዳን
አምላካችን እግዚአብሔር በዘፀ 20፥9 ላይ ለሙሴ በምድረበዳ የሰንበት አከባበሩን ሥርዓቱንም ገልፆል፡፡
˝ አንተ፣ ወንድ ልጅህ ፣ ሴት ልጅህ፣ ሎሌህም፣ ገረድህም ፣ከብትህም በደጆችህ ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ
ምንም ሥራ አትሥሩ፡፡˝ በማለት ሥርዐቱን ሰጥቷል፡፡ በሰንበት ቀን እንስሳቱም ሆነ ሰው ማረፍ አለባቸው፡፡ ነገር ግን
ማረፍ ሲባል ቁጭ ብሎ መዋል ማሳለፍ ሳይሆን ለራስ (ለሥጋ)የሚጠቅሙ ሥራዎችን ትቶ የተለያዩ መልካም የሆኑ
ሥራዎችን መሥራት ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የታመሙትን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጠየቅ፣ የተቸገረ ዘመድ፣
የታመሙ በሽተኞችን መጎብኘትና የመሳሰሉትን መልካም ሥራዎችን መሥራት ነው፡፡ ይህንንም ማድረግ ሲቻል
ማለትም የተቀደሰን ሥራን ስንሰራ ሰንበትን አከበርን ማለት እንችላለን፤ ምክንያቱም ሰንበት የተቀደሰች ቀን ናትና
የምናከብራትም የተቀደሰ ሥራን በመሥራት ነው፤ ይኸም ከነገሮች ሁሉ በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን በማምለክ
እና ለሰው ልጆች ያለውን ፍፁም ፍቅር ስለዚህም ብሎ እንድንድን ያደረገውን በማሰብ ነው፡፡
ነገር ግን እሥራኤላውያን በመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበትን ያከብሩ የነበረው ከላይ ሰንበት መከበር አለበት ባልነው መንገድ
ሳይሆን ከዘረጉ ሳያጥፉ፣ ካጠፉ ሳይዘረጉ ፣ስር ሳይምሱ ቅጠል ሳይበጥሱ፣ የከፈቱትን ሳይዘጉ ነበር፡፡ ትአሞ10፥6
ሕዝ 20፥12 ሌላው ቀርቶ ጦርነት ቢነሳ እንኳን ሰንበት ከሆነ አይንቀሳቀሱም ነበር፡፡
ሰንበት በሐዲስ ኪዳን
በሐዲስ ኪዳን ትእዛዛቶች ሥርዓቶች ባይሽሩም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋ ለብሶ ዐሥርቱን
ትእዛዛቱን ፈፅሞ ሥርዓቱን አስተካክሎ አፅንቶ ወደ መንበሩ መልሶታል፡፡ አዲስ ኪዳንም ማለት አዲስ ውል፣
ስምምነት ማለት ነው፡፡ ለሐዲስ ኪዳን ጥላ መሰረቱ ብሉይ ነው፡፡
ሰንበት በሐዲስ ኪዳን ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ቀዳሚት ሰንበት ሲሆን ሁለተኛው ሰንበት ደግሞ ሰንበተ
ክርስትያን ቅድስት የምትባለው እሁድ ናት፡፡ ሰንበት በሁለቱም ዕለታት እንዲከበሩ ሐዋርያት በሲኖዶስ በፍትሐ-
ነገስት አንቀፅ 19 ላይ ወስነዋል፡፡
ከቅዳሜ ለምን ዕለተ-እሁድ የተለየች ሆኗ ትከበራለች?
የሥነ-ፍጥረት የመጀመሪያ ዕለት በመሆኗ
ዕለተ-ትንሣኤ በመሆኗ ዩሐ20፥1-24
ቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የተላበሱበት የአማናዊቷ ቤተ-ክርስትያን የልደት ቀን በመሆኑ ሐዋ2፥1-41

13

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም የሚመጣበት ለሰው እንደየሥራው ዋጋን የሚሰጥበት የፍርድ ዕለት
በመሆኗ
የመጀመሪያዋ ቤተ-ክርስትያን የተሰራችበት ቀን በመሆኑ
ጌታችን ከትንሳኤ በኃላ ለሴቶችና ለደቀ-መዛሙርት የተገለጠበት እና የታየበት ቀን በመሆኑ
በእግዚአብሔር እና በሕዝብ መካከል ምልክት የታየበት ቀን በመሆኑ ዘፀ31፥7 ሕዝ26፥12
በሰው ዘር ሁሉ የተፈረደውን የሞት ፍርድ በሞቱ ደምስሶ ከሙታን ተለይቶ የተነሳበት ቀን በመሆኑ ማቴ28፥1
መንፈሳዊ ሥራ የሚሰራበት ዕለት ናትና፡፡ 1ኛቆሮ16፥1
ዕለተ ሥጋዌ ናትና፡፡ (ጌታ የተፀነሰበት ቀን ናትና ለክርስትያኖች ልዩ ቀን ናት)
በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ክርስትያኖች የሚሰበሰቡባት ዕለት ስለሆነች ሐዋ20፥7
ታላቁ የቤተ-ክርስትያናችን ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ስለ ሰንበት እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡
˝ ኑ! ከፍ ከፍ እናድርጋት፤ እናክብራት፣ እናወድሳት፡፡ ይህቺውም የበአላት ሁሉ በኩር ሰንበተ-ክርስትያን
ናትና፡፡ ይህቺ ዕለት እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረባት ናትና፡፡ በእርሷ ፈፅሞ ደስ ይበለን፤ ከነብዩ ከአሳፍ ጋር
እናመስግን(እንዘምር)፤ እግዚአብሔር ፍጥረትን ይፈጥር ዘንድ የጀመረባት ይህቺ ዕለት ከሰባቱ ዕለታት የምትቀድም
ናት፡፡ እንደ ቀዳሚት ኃላ የተገኘች አይደለችም፡፡ ለአብርሃም የተገለጠች፣ የጸለየባት ዕለተ-ድህነትን የተመኘባት፣
በመገለጧ ደስ የተሰኘባት፣ ለሙሴ በደብረ ሲና የተገለጠች ከእሥራኤል የተሰወረች፣በነብያት የታወቀች ለእኛ ግን
ፈጽማ ተገለጠች፡፡ በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይበለን፡፡፡ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት፡፡ ˝ ቅ አት ም፡3
እግዚአብሔር አምላክ ያረፈው መቼ ነው?
˝እግዚአብሔር እርሱ አርፎበታልና፤ ሰባተኛውን ቀን ባረከው፡፡˝
 አርፎአል የተባለው ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?
እግዚአብሔር አርፎአል ሲባል የትኛውን አድካሚ ሥራ ሰርቶ ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ ያረፈውስ
ዓለምን በፈጠረ ጊዜ ወይስ ዓለምን ባዳነ ጊዜ?
እግዚአብሔር ዓለምን ለመፍጠር ትእዛዝ ከመስጠትና ከመናገር በቀር ያደረገው አንዳች ነገር እንደሌለ
መጽሐፍት ይናገራሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ˝ እርሱ ተናግሯልና፥ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም፡፡˝ መዝ 33፥9 ˝ብርሃን ይሁን፡፡˝
ባለ ጊዜ ይሆን ነበር፡፡ ˝ከሰማይ በታች ያሉ ውኆች ይሰብሰቡ ˝ ባለ ጊዜ ይሰበሰቡ ነበር፡፡
እነዚህ ከቃል በቀር በእግዚአብሔር ላይ ያስከተሉት ድካም የለም፡፡ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ ስንመረምር
በእርግጥ ድካም እንደነበር እናስተውላለን፡፡ ይህም እግዚአብሔር ሰው ከመሆኑ ከምሥጢረ-ሥጋዌ ሲጀም ነው፡፡
እርሱ ሰውን ለማዳን
 ሰው መሆን ነበረበት፡፡
 መለኮታዊ ልዕልናውን ትቶ ክብሩን በፈቃዱ ዝቅ አድርጎ በትህትና አርአያ ግብርን መንሳት ነበረበት፡፡
 ከኃጢአት በቀር ሰው/ ሥጋ ሚያደርገውን ማድረግ መሆን መሆን ነበረበት፡፡
 መሰደብ
 መመታት
 መሰቀል
 መከራን ሁለ መቀበል

14

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

 መሞት እና
 ከሙታንም መነሳት ይኼ ሁሉ በእርሱ መፈፀም ነበረበት፡፡

እነዚህን ለመፈፀም የሥጋ ድካም መድከም ነበረበት፤ አደረገውም፡፡ በዚህ አድካሚ የማዳን ሥራ ወገኖቹን አዳነ፡፡
ከዚህም በኃላ የእግዚአብሔር እረፍት እውን ሆኗልና ዳግመኛ ድካም የለበትም፡፡
በኃለኛው ዘመን ለዓለም ድህነት የሚያስፈልገውነውን ሁሉ ከፈጸመ እና ሰውን ካዳነ በኃላ ያለው አማናዊ እረፍት
ምሳሌ ነው፡፡ በዚህች ዕለት አርብ የኀጢአትን ሞትን ሞቶ በሞቱ ድል ነስቶ የኀጢአት ደሞዝ የሆነውን ሞት ፈጽሞ
አስወገደ፡፡ ሮሜ6፥23
ሰንበትን አለማክበር ያስቀጣል?
ሰንበትን አለማክበር እስከሞት ድረስ ያስቀጣል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሰንበትን ከሌሎች ትእዛዛት የሚያሳንሱ አሉ፡፡
ለምሳሌ አትግደል ፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ ከሚለው ትእዛዝ ዝቅ የሚያደርጉ አሉ፡፡ እግዚአብሔር ከዐሥርቱ
ትእዛዛት አስቀድሞ የሰጠው ሰንበትን ማክበርን ነው፡፡ ዘጸ 31፥14-15‚35፥2‚ ዘኁ15፥32-36‚ትኤር17፥27
2.4 ትእዛዝ ዐራት
አባትህንና እናትህን አክብር
የትምህርቱ ዓላማ
እናትንና አባትን ማክበርን እነደ ቀላል እንዳናየውና ቅጣቶቹም ከሌሎቹ ትእዛዛት እንደማያንስ ለማስረዳት ዘፀ
21÷15 ዘዳ 21÷18-21
ሌሎቹን ትእዛዛት ከመተላለፍ የምታድን ስለሆነች
ዛሬ ልጅ የሆነ ነገ አባት እናት መሆኑ አይቀርም ዛሬ በልጅነቱ ሳለ ለእናቱ ለአባቱ የሚታዘዝ ከሆነ ነገ ልጆቹ
ይታዘዙለታልና
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ ይህ የቀና ነውና›› ኤፌ 6÷1
ጠቢቡ ሰሎሞንም‹‹ ልጄ ሆይ ያባትህን ትእዛዝ ጠብቅ የናትህንም ሕግ አትተው››ምሳ 6÷20
እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ በሰጠው ሁለት ጽላት መካከል በሁለተኛው ጽላት ላ ከተጻፉት በሰው መካከል ግንኙነት
ከሚመለከቱት ትእዛዛት የመጀመሪው ትእዛዝ ነው፡፡በመጀመሪያ ላይ መቀመጡ ይህንን ትዝዛዝ ከሌሎች ለይተን
እንድናከብረውና አሳንሰን እንዳናየው ነው፡፡
አባትና እናትህን አክብር የሚለው የፍቅረ ቢፅ የመጀመሪያ ሕግ ነው አባትና እናትህን አክብር የሚለው ትእዛዝ
በዘፀአት እንደተጠቀሰው ሁሉ በአዲስ ኪዳንም ከሌሎች ትእዛዛት ጋር ተጠቅሷል፡፡ ማቴ 15÷4፣13÷18 ኤፌ 6÷1
እናትና አባትህን አክብር ሲል በመጀመሪያ የሁሉ አስገኚ የሆነውን ሰማያዊ አባታችንን እግዚአብሔር ሲሆን
በማስከተልም ለሕይወታችን የሚያስፈልገንን ነገር የሚያደርግልን ማለትም የሥጋ አባት እናት እንዲሁም የመንፈስ
አባት እናት በማለት በሦስት ከፍለን እንመለከታለን፡፡
1. የእግዚአብሔር አባትነት

እግዚአብሔር አምላክ የፍጥረት ሁሉ ገዢ እንደመሆኑ መጠን ሁሉ ሥራዎች በእርሱ ሥልጣን የሚተዳደሩ ናቸውና
እርሱንም እግዚአብሔር እንለዋለን ለእኛ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳም ‹‹አባታችን›› እንድንለው ፈቅዶልናል ስለዚህ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጸሎት ባስተማረበት አንቀፅ ‹‹ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ›› እንድንለው
ፈቅዶልናል፡፡

15

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ልዑል እግዚአብሔር አባት ተብሎ መጠራቱ ከጥንት ጀምሮ የነበረና የሚታወቅም ጭምር እንጂ በሐዲስ ኪዳን ብቻ
የተገለጠ አይደለም‹‹ የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶችን ልጆች መልካም እንደሆኑ አየ›› ዘፍ 6÷2 የብሉይ ኪዳን
ነቢያትም ‹‹አቤቱ አንተ አባታችን ነህ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው›› ኢሳ 63÷116 እንግዲህ በዚህ ምንባብ
እግዚአብሔር እራሱን ትሑት አድርጎ በአባትነት ፍቅር የገለጠልንን መሆኑን በሚገባ ተረድተናል ሚል 2 ÷10 ለሁላችን
አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክ የፈጠረን አይደለምን?

2. የሥጋ አባት እናት


ሀ ወላጆቻችን ዕብ 12÷9 ዘፍ 2÷24
ለ የትውልድ አባት ዮሐ 4÷12
ሐ የአንድ አይነት የኑሮ ወገን አባት ዘፍ 4÷20
መ አሳዳጊ (ሞግዚት) 1ኛ ቆሮ 4÷15
ሠ በወላጆቻችን እድሜ የሚገኙ ዘሌ 19÷23 1ኛ ጴጥ 1 ÷ 2
ረ የቀለም አባቶች
ሰ የሀገሯ መሪዎች ሮሜ 3÷7 1ኛ ጴጥ 2÷17
ሸ ሽማግሌዎች ዘሌ 19÷32 1ኛ ጴጥ 1÷2
ቀ የጡት አባት ፡- በእናትም በአባትም በኩል ዝምድና ሳይኖረው ልጁን እንደወለደው ሆኖ
የሚየሳድግ/የምታሳድግ
በ የእንጀራ አባት ፡-ከአንዱ ወገን የተወለደ
ለወንዱ፡ የእንጀራ አባት
ለሴቷ ፡ የእንጀራ እናት
3. የመንፈስ አባት እናት
ሀ የንስሐ አባት
ለ ካሕናት
ሐ የወንጌል ሰባኪ 1ኛ ቆሮ 4÷14 1ኛ ጢሞ 5÷17 1ኛ ተሰ 5÷12
መ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ፡ትዳን 7÷27
ሠ የክርስትና አባትና እናት

የወላጆች ድርሻ
በመጀመሪያ እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረው በኋላ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ረዳት እንፍጠርለት
በማለት ሔዋንን ከግራ ጎኑ ፈጠረለት ዘፍ1÷21-22 እንዲሁም ልጆችን በመውለድ ምድርን ይሞሏት ዘንድ ባረካቸው፡፡
ዘፍ 1÷21-22 ዘፍ 9÷1-7
16

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

እግዚአብሔር በመጀመሪያ አዳምንና ሐየዋንን በፈጠረ ጊዜም ሆነ በኋላ የሰው ልጅ ፈጣሪውን በድሎ በማየ
ሲያጠፋው ኖህንና ቤተሰቡን ካስቀረ በኋላ የተናገረው ቃል አንድ ነበር ፡፡››ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት፡፡ይሁን እንጂ
ልጅ ሳንወልድ ስለ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ግድ የማይለን ከሆነና በሚገባ ላናሳድጋቸው ዝም ብለን የምንወልድ ብቻ
ኮነ በልጆች ደም ተጠያቂ እንደምንሆን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኤሊ ልጆቹን ከወለደ በኋላ እግዚአብሔርን እንዳስቀየሙት እያየ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ምን እንደሰሩና
ሕይወታቸው ፈፅሞ ከእግዚአብሔር መራቁን እያወቀ ችላ ስላለ ተቀጣ 1ኛ ሳሙ 4÷18 የእርሱ ቸልተኝነት ለራሱም ሆነ
ለልጆቹ አልጠቀማቸውም፡፡ከእግዚአብሔር የተሰጡንን ልጆች በክርስቲያናዊ አስተዳደግ አሳድገን የመንግስቱ ወራሽ
የማይሆኑ ከሆነ ይልቁንም እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ከሆነ ባንወልዳቸው ይሻላል፡፡›› ሲራ 16÷1-4
ነገር ግን ክርስቲያን የሚወልዳቸውን ልጆች ከእግዚአብሔር አደራ የተሰጡት መሆናቸውን በማሰብ በቃለ
እግዚአብሔር እየኮተኮትን እግዚአብሔርንም ቤተሰብንም የሚያስደስቱ እንዲሆኑ መጣር አለበት፡፡ መዝ 127÷3-4
ክርቲያን ልጅ ባይኖረው እንኳን አያዝንም ምክንያቱም የደረቀ እንጨት የሚያለመልም አምላ መካን የነበራትንና
በእርጅናቸው ወራት ልጅ የሰጣቸውን ሣራና ኤልሳቤጥን እንዲሁም መካን ሆና ከቆየች በኋላ ስድስት ልጅ
የወለደችውን ሐና እመ ሳሙኤል በማሰብ በእምነት በመሆንና በመጽናት ሁሉን ማድረግ ወደሚችል አምላክ
በመጮኽ ያገኛል፡፡ልጆችን የምንቀበለው አድሎ ከሌለበት ለምነውት ከማይጨክን ከአባታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ
ነውና ከዚያ ባለፈ ወደ እግዚአብሔር አመልክቶ የማያገኝ ቢኖር ለምነን የማናገኘው ነገር እርሱ ባወቀ መሆኑን
ተገንዘበን ለሁሉም ነገር የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብሎ ለአኮቴት ለመቀበል ራስን ማዘጋጀት ይገባል፡፡ 2ኛ ቆሮ 12÷7-9
‹‹ እነሆ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው›› መዝ 126÷3-4
‹‹እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች›› ኢሳ 8÷18
‹‹መካኒቱን በቤት የሚያኖራት ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት………›› መዝ 112÷9
‹‹መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፡፡››1ኛ ሳሙ 1÷5-13፤ 2÷5
ስለዚህ ልጆች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰውንም የሚያከብሩ እንዲሆኑ በምን ዓይነት ሁኔታ ማደግ አለባቸው
የሚለው ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ ቀጥሎ እንመለከታለን ወላጆች ልጆችን በምን አይነት መንገድ ማሳደግ አለባቸው
1. የጸሎት ሕይወት ለምደው ኢዮብ 1÷5
2. በሃይማኖት መሰረት ላይ ታንጸው ሲራ 16÷1-3 ዕብ 11÷24-28 ዘዳ 4÷40 ምሳ 9÷10
3. ከቤተክርስቲያን ሳይርቁ በውስጧ ሆነው ምሳ 8÷34 መዝ 1÷1-3
4. ከመጥፎ ጠባያት ዝንባሌ ርቀን ምሳ 16÷25

የልጆች ድርሻ
በቤታችን ውስጥ ያሉ ታላላቅ እና ታናናሽ ልጆች እየተያዩና እየተማሩ የሚያድጉ የቤተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
የታላላቆች አነጋገር አለባበስ፣አካሄድ ፣መንፈሳዊ ሕይወት፣አመለካከትና የመሳሰሉት ሁሉ በታናናሾቹ ልጆች ላይ
ሲደገም ይስተዋላል ይህም አብሮ ከመኖርና ከመላመድ የሚመጣ ነው፡፡
ፍትሐ ነገስት‹‹በኩር ሆኖ የተወለደ ልጅ እናት አባቱን ከእናትና አባቱ ቀጥሎ ወንድሞቹን እህቶቹን መርዳት ይገባዋል፡
፡››በማለት ይናገራል፡፡ፍትነገ ገጽ 190 አንቀጽ 11 ቊጥር 458
በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ለሕጻናት አስተዳደግ ከወላጆቹ ያልተናነሰ ትልቅ ድርሻ ያላቸው የሕፃናቱ ታላላቅ
ወንድሞችና እህቶች ናቸው፡፡ትንንሽ እህቶችና ወንድሞችም ከመታዘዝና በመፈቃቀድ ቤተሰቡን ሰላማዊ ለማድረግ
17

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የአቅማቸውን ጥረት ማድረግን መማር ይኖርባቸዋል፡፡በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ልጆቻችን በሚገባቸው ሁሉ


አድገው ለቁም ነገር እንዲበቁ እርስ በርሳቸው ሊኖራቸው ከሚገቡት አስፈላጊ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ
ቀጥለን እንመለከታለን፡፡ወላጆችም ‹‹ልጆቼ እንዲዋደዱ እፈልጋለሁ›› ማለት ብቻ ሳይሆን እነዚህ ነጥቦች በርግጥም
በልጆቻችን መካከል መኖራቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል፡፡
1. እግዚአብሔርን መውደድ እርስ በርሳቸውም መዋደድ አለባቸው፡፡ 1ኛ ዮሐ 3÷10 1ኛ ዮሐ 4÷20 ዘፍ 43÷30 ዘፍ
45÷14
2. መጣላትን ከመካከላቸው ማስወገድ አለባቸው ዘፍ 13÷8
3. መቀናናትን ማስወገድ አለባቸው ዘፍ 3
4. ይቅርታ መጠየቅና ይቅርታ መቀበልን መልመድ ይኖርባቸዋል ማቴ 26÷28 ዘፍ 37 ዘፍ 50÷15-21
5. ወላጆችን በሥራ ማገዝ ይኖርባቸዋል ሲራ 3÷7፣12

የመንፈስ አባት እና እናት ድርሻ


የመንፈሳዊ አባት እና እናት ድርሻ የኃጢአት እስረኛ የሆነውን ሰው በተሰጣቸው መነንፈሳዊ አደራ ከታሰረበት
የኃጢአት እሥራት ነጻ ማውጣት መንፈሳዊ ግዴታቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ በኃጢአት ምክንያት ተስፋ የቆረጡ
ቢኖሩ እንኳን‹‹አጽናኑ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ፡፡›› ኢሳ 40÷1 እንደተባለ ማፅናናት ተስፋቸው
እንዳልተሟጠጠ በመግለፅ በንስሐ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ ማስተማር የአባቶች የእናቶች ትልቁ አደራ ነው፡፡
ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው መለኮታዊ አደራም ይኸው ነው‹‹ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ
ትወደኛለህን? አለው›› ዮሐ 21÷15 ጌታችን በመጀመሪያ ቅ/ጴጥሮስን በትክክል እንደሚወደው ማረጋገጥ ስለነበረበት
‹‹ትወደኛለህን›› የሚል ከባድ ጥያቄ አቅርቦለታል፡፡‹‹አዎ ጌታ ሆይ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ ›› የቅዱስ ጴጥሮስ
መልስ ይህን ይመስል ነበር ጠቦቶቼን ተብቅ በጎቼን አሰማራ (ቁ17) እንደሚወደው ‹‹አዎን ጌታ ሆይ›› በማለት
ካረጋገጠለት በኃላ የተሰጠው አደራ ጠቦቶቹንና በጎቹን እንዲጠብቅ ነው፡፡በጎች የጠባሉት ምዕመና ጠቦቶች የተባሉት
ደግሞ የበግ ግልገሎች ወይንም ከልጅ እስከ ወጣ ያሉት ክርስቲያኖች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ጥበቃውም ከሀሰተኛ
መምህራን ሲሆን በቃሉ በኩል ነፍሰን ከዘላለም ሞት መታደግ ከሥጋ ሥራ ተላቀው መንፈሳዊ ፍሬ እንዲኖራቸው
በማድረግ ነው፡፡ጌታችን መምህር ተብሎ መምህራን ሊቀ ካህናት ተብሎ ካህናት እረኛ ተብሎ እረኞች የመባል እድል
(መመረጥ) ያገኙ አባቶች ካናት ናቸው፡፡
የሦሥት ሺህ ዓመታት የታሪክ ባለቤት መሆኗ የምትታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካንበት ዘመን ለመድረስ
በታሪካዋ ክፉም ደግም እየተፈራረቁባት በሃይማኖት አባቶችና እናቶች መንፈሳዊ ትምህርት እገዛ ጭምር መሆኑ ግልጽ
ነው፡፡ ዛሬም ሀገሩንና ታሪኩን ሃይማኖቱን የሚጠብቅ በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት የሃይማኖት
አባቶችና እናቶች ኃላፊነት ግንባር ቀደም ሊሆን ይገባል፡፡
ትውልድ ሀገሩንና ሀይማኖቱን አፍቃሪ ብሎም ተቆርቋሪና ታማኝ ሆኖ እንዲያድግ የአባቶች እና የእናቶች ሚና በሁሉ
ረገድ ወሳኝ ነው፡፡‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ
መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ›› ኤፌ 6÷16
አባትና እናትን አለማክበር ያስቀጣል
በብሉይ ኪዳን አባቱንና እናቱን የማያከብር ሰው በሞት ይቀጣ ነበር፡፡‹‹አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይገደል
አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል፡፡›› ዘፀ 21÷15-17 ዘፀ 20÷9
በአዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ሲገስፅ
‹‹ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዝጅግ ንቃችኃልና ሙሴ አባትህንና እናትህን አክብር ደግሞ
አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሏልና እናንተ ግን ሰው ለእናቱና ለአባቱ ምንም እንኳን ሊያደርግ
ወደፊት አትፈቅዱለትም ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡››

18

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

2.5 ትእዛዝ 5
አትግደል ዘጸ 20፤13
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ
እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው አድርጎ እንደፈጠረውየሚያስገነዝብ ነው
በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረውን ሰውን ሁሉ መውደድ (ፍቅር መስጠት) እንደሚገባን ያሳየናል
ለሰው ሁሉ በበጎ ብቻ አብነት መሆን እንደሚገባን ያስተምራል፡፡
የሰው ልጅ ሕይወት በአጋጣሚ፣ በልማድ የምትገኝ አይደለችም፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በዕውቀቱና በጥበቡ
ያስገኛት የእግዚአብሔር የእጅ ሥራ ገንዘቡ ናት፡፡ ስለሆነም በዚህ ሕይወታችን ላይ መግደልም ሆነ ማዳን የሚቻለው
እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን እንድናውቅ ይህ ትእዛዝ ተሰጥቶናል፡፡ ዘዳ 32፤39/ 1ኛ ሳሙ 2፤6
መግደል ሊመለስ (ሊካስ) የማይችል ኃጢኣት ነው፤ የገደለውን ሰው ነፍስ ሊመልስ አይቻለውምና፡፡ መግደል እጅግ
አስከፊ የሚሆነው ደግሞ የሞተው ሰው ኃጥእ የሆነ እንደሆነና ንስሓ ሳይገባ የሞተ እንደሆነ ነው፤ ይህ ለሰማያዊው
ሕይወት ለመዘጋጀት ያለውን ዕድል ያሳጣዋልና፡፡
የተገደለው ሰው ጻድቅ (ንጹሕ) ሰው የሆነ እንደሆነ እርሱን በማጣት የሚገኙት መልካም ነገሮች ሁሉ አብረው
ስለሚጠፉ የተገደለው ሰው ጠቃሚ በሆነ ቊጥር ገዳዩ ያለበት ተጠያቂነት እየጨመረ ይሔዳል፡፡
ጻድቅንም ሆነ ኃጥእን መግደል ታላቅ ኃጢኣት ነው፤ ነገር ግን ጻድቃንን መግደል የበለጠ ያስጠይቃል፤ እነርሱን
ለመግደል ምንም ምክንያት የለምና፡፡
እግዚብሔር ደግሞ ስለ ጻድቃን ነፍስ እንደሚጠይቅ በመጽሐፍቅዱስ ተገልጧል፡፡ ማቴ 23፤35 ዘፍ 4፤10
እግዚአብሔር ገዳዮችን ስላጠፉት ነፍስ ይበቀላል፡፡ ዘፍ 4፤14-151ኛ ቆሮ22፤8 በቀል የእኔ ነው፤ ብድራትን
እመልሳለሁ ብሎ ጌታ ስለተናገረ ሰዎች ችግር እንኳ ቢደርስባቸው በቁጣ ተነሥተን ራሳችን እንድንበቀል
አልተፈቀደም፡፡
በአጠቃላይ ነፍስ መግደል ከፍተኛ ኃጢኣት ነው የተባለው ስለሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
 የእግዚአብሔርን ሕንፃ ማፍረስ ነውና፡፡ አንድ ሰው ያልሠራውን ማፍረስ፣ የሰው ንብረት የሆነውን ማጥፋት
እንደማይገባው፣ ይህን ሁሉ ፈጽሞ ከተገኘ የሚያስቀጣ ከሆነ የእግዚአብሔር ሕንፃ የሆነውን ሰውን ያህል ፍጥረት፣
እግዚአብሔር በአርኣያውና በአምሳሉ የፈጠረውን ሰውን መግደል ከወንጀል ሁሉ የሚበልጥ ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡
 ነፍስን የማዳንም ሁነ የማጥፋት ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ሲሆን፣ እግዚአብሔር ይኖር ዘንድ የወሰነለትን
ሕይወት ማጥፋት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡
 በዚህ ዓለም የመኖርን ዕድል እግዚአብሔር ከሰጠው በኋላ ሰው ሲያጠፋው መልሶ ሊያገኘው የማይችለውን
የሰውን ፣ብት በምድር እንዳጠፋ የእርሱንም የሰማያዊ ሕይወት ዕድልን ይነሣዋልና፡፡
 አንድ ሰው በዚህ ዓለም ሊሠራውና ሊፈጽመው የተሰጠውን ሳይሠራ ሕይወቱ እንዲያልፍ በማድረጉ በእርሱም
በራሱ በዚያኛው በደል ይጠየቃልና፡፡
ወደ መግደል የሚያደእርሱ ነገሮች
ወደ መግደል የሚያደእርሱ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም ቅንዓት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ጥላቻ፣ ቁጣ… ጥቂቶቹ
ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ቁጣን ብንመለከት በሁለት ሰዎች መካከል የሚነሳውን ጠብ የሚያባብስ ዋነኛ ምክንያት
ነው፡፡ በእርግጥ የሚገባ ቁጣ አለ፤ ይህንንም ሲያስረዳ “ተቆጡ፤ ነገር ግን ኃጢኣትን አታድርጉ፡፡” መዝ 4፤4

19

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

“ተቆጡ፤ አትበድሉም፤ ፀሐይ ሳትጠልቅም ቁጣችሁን አብርዱ፡፡” ኤፌ 4፤26 ጌታችንም “አትግደል”የሚለውን ሕግ


ለመፈጸም ወደ መግደል የሚያደርሰውን ቁጣን ማስወገድ እንዲገባ ሲገልጽ “በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ
ይገባዋል፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ ማቴ 5፤21-22 ከስድብም ስድብ ይበልጣል፡፡ ጨርቅ ለባሽ ሲል ሰውዬውን ብቻ
የሚመለከት ነው፡፡ ደንቆሮ ሲል ግን ሰውየውንና ፈጣሪውን የሚመለከት ነው፡፡ ደንቆሮ ሲል ግን ሰውዬውን
ፈጣሪውን የሚመለከት በመሆኑ በደሉም ከፍ ያለ ነው፤ በገሃነመ እሳት ያስቀጣል፡፡ የሰውዬውን ተፈጥሮ እያዩ
መሳደብ ይቆጠራልና፡፡ ስለዚህ የአእምሮና የአካል ጉድለት ያለበትን ሰው ከመርዳትና ከማፍቀር በስተቀር ሁኔታውና
አይቶ መናቅና ማቃለል ወይም መቀለድና ማሾፍ ትልቅ በደል መፈጸም መሆኑን አንርሳ፡፡ በንግግር ለሚፈጸሙት
ስሕተቶች ተጠንቅቀን ሳንቆጣና ሳንሳደብ መናገር ብልህነት ነው፡፡ “ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ሰው ሁሉ
ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገርም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቁጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና፡፡” በማለት ቅዱስ
ያዕቆብ ይመክረናል (ያዕ 1፤19-20)፡፡
አትግደል ሲባል ምንን ያመለክታል
 በአጠቃላይ አትግደል ሲል፡-
1. ደመነፍስን መግደል
2. ሕያዊት ነፍስን መግደል
3. በቊጥር አንድና ሁለት የተዛመደ ሆኖ ነገር ግን በራስ ላይ የሚፈጸመው ራስን መግደል ናቸው፡፡
የሚገባ መግደል
እግዚአብሔር ምንም እንኳ አትግደል የሚል ሕግን ቢሰጠን በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን መግደልን ፈቅዷል፡፡
መፍቀድም ብቻ ሳይሆን እንደውም መግደል አስፈላጊ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እንዳሉም ጭምር አዝዟል፡፡ ይህንን
እውነት ከሚያስረዱን ተጨባጭ መረጃዎች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
 ዘሌ 20፤10-16 “ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና
አመንዝራዪቱ ፈጽመው ይገደሉ፡፡”
 ዘፀ 21፤12 “ሰው ሰውን ቢመታ፣ ቢሞትም፣ የመታው ፈጽሞ ይገደል፡፡”

 ዘፀ 21፤16 “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ፡፡”

 ዘፀ 21፤17 “ከእሥራኤል ልጆች አንዱን የሰረቀ ወይም ግፍ የፈጸመበት፣ ወይም አሳልፎ ቢሰጠው፣ ወይም በእርሱ
ዘንድ ቢገኝ፣ እርሱ ይገደል፡፡”
 ዘፀ 31፤14 “ለእናንተ በእግዚአብሔር የተቀደሰች ናትና ሰንበቴን ጠብቁ፤ የሚያረክሳትም ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፡
፡”
 ዘሌ 24፤16 “የእግዚአብሔርንም ስም ጠርቶ የሚሰድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፡፡” 1ኛ ነገ 24፤13 ማቴ 26፤65

 ዘፀ 22፤20 “ከእግዚአብሔር ብቻ በቀር ለአማልክት የሚሰዋ ፈጽሞ ይጥፋ፡፡” 1ኛ ነገ 18፤40 ዘዳ 13፤5፣16

 ዘዳ 13፤5-7 “አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም
ሕልም አላሚ ይገደል፡፡” በተዘዋዋሪም መንገድ የገደለም ይገደል ነበር፤
 ዘፀ 21፤19 “በሬው ግን ትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፣ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባያስወግደውም፣
ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፣ በሬው ይወገር፤ ባለቤቱም ደግሞ ይገደል፡፡”

20

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

እነዚህን ሁሉ ጥፋተኞች በሞት መቅጣት እንደ ኃጢኣት አይቆጠርም፤ በስድስተኛው ትእዛዝም ሥር


አልተካተተም፡፡ ይልቁንም ሕግ ተላላፊዎቹን ባለመግደል ትእዛዝን አለመፈጸም እግዚአብሔርን የሚያሳዝን መጥፎ
ድርጊት ነው፡፡
እግዚብሔር ሕግ ተላላፊዎችንና ጣኦት አምላኪዎችን እንዲገደሉ ያዘዘው ሃይማኖትን ለመጠበቅ በማለት ነው፡፡
በጦርነትም ወቅት መግደልን ፈቅዷል፤ ይህ የሚሆነው ግን እርሱ የፈቀደው ጦርነት ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ጦርነት
የሚካሔደው ራስን ለመከላከል ወይም የሕብረተሰብን ደኅንነት ለመጠበቅ ከሆነ እግዚአብሔር አይቃወመውም፡፡
ሆነ ብሎ ሌላውን ተተናኩሎ ወደ ጦርነት መግባት ግን በዚህ ሕግ መሠረት ያስቀጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወታደሮች
የተማረከን ሰው ይገድሉ ዘንድ አልተፈቀደላቸውም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ጦርነት ቢያካሂዱ
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተቃወሙ ማለት ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ እግዚአብሔር የነፍሳችን እውነተኛ ባለቤት መሆኑ
ነው፡፡ የሰውን ሕይወት በማንኛውም መንገድ የማቆም መብት (ሥልጣን) አለውና፡፡
ከላይ ያየናቸው በሙሉ አስቀድሞ ሥጋዊ ምግብና በነበረበት በኦሪት የታዘዙ ነበሩ፡፡ አሁንም ቢሆን ለሥጋዊ
ገዢዎች በእግዚአብሔር የተሾሙ (አገልጋዮች) ናቸውና እንደ አግባቡ መርምረው ያጠፋን ሰው ሊቀጡ ይችላሉ፡፡
ቤተክርስቲያን ይህን በዓለም ያለ የሞት ቅጣት አትደግፈውምም፤ አትቃወመውምም፡፡ ሮሜ 13፤1-5 ነገር ግን ዛሬ
በሐዲስ ኪዳን መንፈሳዊ ዳኞች ይህን አይፈጽሙም፤ የመንፈሳዊ ምግብና ጊዜ ስለሆነ ቀድሞ በመግደል ይፈጸም
የነበረ ዛሬ አውግዞ በመለየት ተተክቷል፤ ቀድሞ በመግረፍ የነበረ ዛሬ በጾም፣ በስግደት፣ በምጽዋት በመቅጣት
ተተክቷል፡፡
 ሌላው የሚገባ መግደል፣ ኅሊናን ከክፉ ምኞት መግደል፤ ምድራዊ ሰውነታችንን ከዝሙት ከርኵሰት መግደል ቆላ
3፤5
 እንስሳትን እና ጥቃቅን ነፍሳትን መግደል፡- ስድስተኛው ትእዛዝ ስለ ሰው ልጅ ነፍስ ስለ ተሰጠ እነዚህን
አያጠቃልልም፡፡ የሰው ልጅ በሥነ ፍጥረት ላይ ያዝባቸው ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታልና ያሻውን ሊያደርጋቸው
ይችላል፡፡ አንዳንድ ለሕይወት እና ለጤና ጎጂ የሆኑ እንስሳትንና ነፍሳትንም ማጥፋት ይጠበቅበታል፡፡ ለምሳሌ፡-
የወባ ትንኝ፣ አንበጣ… ነገር ግን ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ምንም ጉዳት የማያደእርሱበትን የእግዚአብሔር ፍጥረታት
የሆኑ እንስሳትን መግደል ርኅራኄ አልባነትን ከማሳየቱም በተጨማሪ ለእንስሳቱ ፍቅርና እንክብከቤን ካልለገሰ ከጎኑ
ላለው ባልንጀራው ያንን የፍቅርና የይቅርታ ጠባይ ሊያሳይ እንደማይችል ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔርም እንስሳትን
እንድንንከባከብ አዝዞናል፡፡ (ምሳ 12፤10 ዘዳ 22፤10 25፤4 ዘፍ 33፤13) ቅዱሳን ከሰው አልፈው ለእንስሳት እጅግ
ከመራራታቸው የተነሣ ለተራቡ እንስሳት ሥጋቸውን እየቆረሱ አስከመስጠት ደርሰዋል፡፡
የአገዳደል ዓይነቶች
ደመነፍስን (ሥጋን) መግደል
መግደል ከሰው ውስጥ የሚወጡ ሰውንም የሚያረክሱ ብሎ ጌታችን ከዘረዘራቸው ክፉ ሥራዎች አንዱ ነው፡፡ (ማቴ
15፤19፣ ማር 7፤22) ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ መልዕክቱ ላይ ከዘረዘራቸው 16 የሥጋ ሥራዎች አንዱ ነው፡፡ (ገላ 5፤
2) ይህም በተለያዩ መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡
1. በተለያየ መሣሪያ ሕይወቱን ማጥፋት፣ ደብድቦም መግደል፡፡
2. በአሳብ መግደል፡- ለመግደል ማሰብ በራሱ ኃጢኣት ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን እንዴት እንደሚገድል ወይም
ሌሎች እንዴት እንዲገሉት እንደሚያደርግ ሊያሰላስል ይችላል፡፡ አልያም ያ ሰው በፊት ለፊቱ እንደሞተ ሆኖ
እየታየው በዚህ ሊደሰትና ሊረካ ይችላል፡፡ ይህ ሰው መንፈሳዊ ተጠያቂነት አለበት፡፡ ሰውን በአሳቡ ባይገድል እንኳ
እንዲሞት መመኘት ሌላው የመግደል ዓይነት ነው፡፡
3. ፅንስን ማስወረድ፡- ይህ ገና ያልተወለደ ግን ነፍስ ያለውን የእግዚአብሔርን ፍጥረት መግደል ነው፡፡በፍላጎትና
ያለፍላጎት ሊፈጸም ይችላል፡፡ በፍላጎት ከሆነ የሚፈጽውም ሐኪም በተወሰነ መልኩ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሌሎች

21

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

መንገዶችን ከተጠቀሙ ደግሞ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ እናቶቹ ላይ ያርፋል፡፡ ውርጃው የተፈጸመበት ምክንያት
የኃላፊነቱን ክበደት ይወስነዋል፤ ምክንያቱም ሌላ ወንጀልን ለመሸፈን የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላልና ነው፡፡
ያለፍላጎት የሚፈጸመው ደግሞ እናትየው ራሷን በከባድ ሥራ ጠምዳ ለራሷ ተገቢውን እንክብካቤ ከማድረግ ቸል
ስትል ነው፡፡ እርጉዝ ሴቶችን በማሠራት በሥራው ከሚመጣው መዳከም ልጆቻውን እንዲያጡ የሚያደርግ አሠሪ
አትግደል የሚለውን ትእዛዝ ስለተላለፈ ይጠየቃል፡፡ ባልም በእርግዝና ወቅት ለሚስቱ ጤንነት ተገቢውን አንክብካቤ
ባያደርግ እና ልጁ ቢጨናገፍ ተጠያቂ ነው፡፡
በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን ውርጃን ስለሚከተሉት ምክንያቶች ትከለክላለች፡-
ሀ የእግዚአብሔርን ሥራ ማቋረጥ ስለሆነ፤ ኢዮ 10፤10፣ ቅዳሴ አትናቴዎስ 113፤115
ለ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ያለውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚቃወም ስለሆነ፤
ሐ የሰውን በዚህ ምድር ላይ የመኖርን መብት የሚጋፋ ስለሆነ፤
መ ኃጢኣትን ለመሸፈን የሚደረግ ግብር ስለሆነ
ከዚሁ ጋር የሚመሳሰለው ፅንስን እንዳይፈጠር በተለያዩ የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶች ተጠቅሞ (የሴት ማኅፀንን
በማዘጋት፣ የወንድ የመራቢያ ዘርን በማስወገድ፣ የተለያዩ መድኃቶችን በመጠቀም) መከላከል ነው፡፡ ይህ ተግባር
ሊወለድ ያለውን ዘር አለአግባብ ወደ ውጭ እንዲፈስስና እንዲጠፋ ስለሚያደርግ ይህም ነፍስን የማጥፋት ወንጀል
ነው፡፡ እንዲህ ያለው ተግባር ግብረ አውናንም ይባላል፡፡ ዘፍ 38፤10 ቅጣቱም እንደ አውናን ተቀስፎ መሞት ነው፡፡
4. በከፊል መግደል፡- በዚህ ሥር በሰውነት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ መደብደብ፣ማሳመም፣ ማሰቃየት ይጠቃለላሉ፡፡
ሰውን በመምታት የአካል ክፍሉን ልንጎዳበት እንችላለን፣ ይህም በከፊል ገደልነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህን አንድ ሰው
በንግግርም ይሁን በመምታት ጉዳት ማድረስ የመግደል ኃጢኣት አንዱ መገለጫ ነው፡፡
5. በተዘዋዋሪ መንገድ መግደል፡-
 በተለያዩ ሁኔታ (በቃላትና በመጠቆም) አጥፊውን በመርዳት ማቴ 26፤17
 የሰው ሕይወት ሊድን የሚችልበትን መረጃ በመከልከል፡፡
 ሞራልን መግደል፡- የሰውን ስም፣ ክብር የሚያጠፋ ሥራ በመሥራት፣ በሰዎች መካከልም በማዋረድ በአካል
በይሆንም ሰው በሞራል ይገደላል፡፡ ሰውን ያለጥፋቱ መክሰስ፣ ደካማ ተሪትመንት፣ ማዳከም፣ ማንቋሸሽ፣ ሰው
ለምንም እንደማይጠቅም፣ በሁሉም በኩል ደግሞ የማይሳካለት አድርጎ መቁጠር ሰውን በሞራል መግደል ነው፡፡
በሀብቱ በመብቱ ገብቶ ሰውየው እንዲዋረድ እንዲያዝን በዚህም እንዲሞት ማድረግ
 ማናደድ፡- ሰው ላይ በማሾፍ፣ ኅሊናውን እስኪያጣ በማበሳጨት ፈጽሞ እንዲናደድ፣ እንዲታመም ኋላም
እንዲሞት ምክንያት መሆን የመግደል ኃጢኣት ውስጥ ይካተታል፡፡ ኤር 9፤8 መዝ 55፤21
 በተቀጣሪዎች ላይ የሚፈጸም በደል፡- ሀብታም ቀጣሪዎች ለተቀጣሪዎቻው ብዙ ሰዓት እያሠሩ ለኑሯቸው
የማይበቃ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ ክፍያ ቢከፍሏቸው በዚህ ምክንያት ለሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ እንዲሁም
ሞት ተጠያቂ ናቸው፡፡ ያዕ 5፤4 ዘሌ 19፤13 ዘዳ 24፤14-15 ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ማባረር፣ሥራ ሊቀጠሩ
የሚመጡትንም መንፈግ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ፍላጎት ማቆም፣ እነርሱንም ስርቆትን ወደመሰሉ
ኃጢኣቶች መጨመር ስለሆነ በነፍስም በሥጋም መግደል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሽታና ድካምን ሌላም ችግርን
ሲያዩ ለሞት የሚያደርስ ሥራ ማሠራት የመግደል ዓይነት ነው፡፡
 ሀብቱን ንብረቱን ወስዶ የሚበላውን የሚጠጣውን አጥቶ እንዲሞት ማድረግ
 ብድር፣ አራጣና ማስያዣ፡- ሰው የሚያስፈልገውን ነገር መከልከል ዘጸ 22፤25 ዘዳ24፤17፣6
22

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

 ርዳታን ከመስጠት መከልከል፡- ሰው ሊሞት እንደሆነ እያየን የቻልነውን ርዳታ ካለገስነው እንደ ገደልነው
ይቆጠራል፡፡ ምሳ21፤13 ያዕ 4፤17
 የረሃብተኞችንና የሕመምተኞችን ድምፅ ቸል በማለት እስኪሞቱ መመልከት ግልጽ የሆነ የመግደል ዓይነት ነው፡፡
ሉቃ16፤19-22 ችግረኛውን ሳይረዳው፣ ሳይደግፈው እንዲሁ የሰው ልጅ እንዲሞት ማድረግ 1ኛ ዮሐ 3፤7 ዕብ 2፤15
ሲራ 31፤25
 በቸልተኝነት መግደል፡- ዘጸ 21፤28-29፣ 33-34፣ ዘዳ 22፤8 በአሁኑ ጊዜም መኪናን በአግባቡ ባማስተካከል፣
የሥራ ቦታን ምቹ ባለማድረግ ለሚመጡ ጉዳቶችና የሞት አደጋዎች ሁሉ ሰዎች ተጠያቂ ናቸው፡፡
 ባልና ሚስትን ነገር ሠርቶ ማጣላት፡፡ ሲራ 31፤26
 ጌታችን በሐዲስ ኪዳን አትግደል የሚለውን ሕግ በማጥበቅ ወደ መግደል የሚያደርሰንን ስድብና ቁጣ
እንዳንፈጽም ከልክሏል፡፡ ማቴ 5፤21
ሕያዊት ነፍስን መግደል
1. ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ባዶ መሆኑን አይቶ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ፣ ቃሉን ተምሮ ሙሉ እንዲሆን
አለማድረግ፤ ሆሴ 4፤6 በዚህም ከእግዚአብሔር እንዲለይና ወደ ሲኦል እንዲጣል ማድረግ ምሳ 7፤26፡፡ በዚህ ረገድ
ሰይጣን ዋነኛ ነፍሰ ገዳይ ነው (ዮሐ 8፤44)
2. ለመጥፎ ነገር አርአያ በመሆን ሰውን ማሰናከል፡፡ ማር 9፤42፣ ማቴ31፤41-42 እንቅፋት (መሰናክል) መሆን፣
ሌሎች ኃጢኣትን እንዲሠሩ ማበረታታት፣ ለእነርሱም መሰናከያ መሆን ነፍሳቸውን መግደል ነው፡፡ ማቴ 18፤6-7
1ኛቆሮ 8፤10-13 ያዕ 1፤15 ለአብነትም የኃጢኣት ምክንያት የሆነው በለአምን (ራእ 2፤14)እና በቤቱ ጥፋትን ያመጣ
ኢዮርብኣምን (1ኛ ነገ 13፤34) መመልከት ይቻላል፡፡
3. ጥላቻ የመግደል ዓይነት ነው፡፡ 1ኛ ዮሐ 3፤15 “ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡” ማቴ 5፤21-22
4. እረኞች የተባሉ ካህናት ልጆቻቸውን በሚገባ አለመጠበቃቸው፡፡ ሕዝ 3፤ 16-21፣ 1ኛጴጥ 5፤1-5 ሕዝ 3፤17-19
ካህናት መልካም የሚጠበቅባቸው መሆን ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ነፍሳትን ማዳን ጭምር ነው እንጂ፡፡ የካህኑ
ተጠያቂነት በዙሪያው በመናፍቃን፣ ሰዎችን በሚያስቱ ፈላስፎች ምእመኑንም ከቀጥተኛይቱ የእምነት መንገድ
በሚያስወጡ ሰዎች የተከበበ ከሆነ ይጨምራል፡፡ ሆሴ 4፤6 1ኛሳሙ 2፤29-34
5. ፍትሐዊ ያልሆነ ውግዘት፡- ያለበቂ (አጥጋቢ) ምክንያት አንድን የቤተክርስቲያን አባል አውግዞ መለየት
የምእመኑን ነፍስ መግደል ነው፤ ከቤተክርስቲያን ምስጢራት ይለያልና፡፡ አንድ ሰው ተወግዞ የተለየ እንደሆነ እንኳ
ይመለስ ዘንድ ከቤተክርስቲያኒቷ ውጪም እየሄዱ መጎብኘት ይገባል፡፡
6. ልጆችን በቸልተኝነት ማሳደግ፡- ሕዝ 3፤18 እናትና አባት የእግዚአብሔር ስጦታዎች የሆኑትን ልጆቻቸውን
በተገቢው መንገድ ቀርጾ የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ “እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፡፡” ኢያ24፤15
እንዲል ሃይማኖት የግል ጉዳይ ሳይሆን የቤተሰብመ ጭምር ነው፤ ቤተሰብ አንድ የሕይወት አካል ነውና፡፡ አንዳንድ
ባሎች ለሚስቶቻቸው ከልክ ያለፈ ትኩረት ከመስጠታቸው የተነሣ ስለልጆቻው ያላቸውን ኃላፊነት ይዘነጋሉ፡፡ ትዳር
ግን ቤተሰብ ልጆችን አፍርቶ ለእግዚአብሔር እና ለቤተክርስቲያን የሚሰጥበት መንፈሳዊ ተቋም ነው፡፡ በትንሣኤ
ዘጉባኤ እያንዳንዱ ወላጅ ስላፈራው ልጅ ይጠየቃል፤መጥፎም ከሆነ ይህንን ሁሉ ዓመት ከእርሱ ጋር ሲኖር ስለምን
በመልካም ሥነምግባር እንዳላሳደገው ይጠየቃል፤ ይቀጣበታልም፡፡ ወላጆች መልካም ያልሆነ ምሳሌ በማስቀመጥ
ልጆቻቸውን ሊገድሏቸው ይችላሉ፡፡ ልጆች ጭቅጭቅ፣ ስድብ፣ መጥፎ ቃላት ባለበት ያድጉና ይህንኑ ተከትለው
ይጓዛሉ፤ አልያም ይህንን ጠልተው ከቤት በመውጣት ለጎዳና ሕይወት ይዳረጋሉ፡፡
7. ሃይማኖታዊ ፍስፍናዎችና ምንፍቅናዎች፡- ምሳ 22፤28 አዳዲስ አሳቦችን ወደ ሃይማኖት መጨመር ጀግንነት
አይደለም፡፡ ይልቁንም ቀናይቱን ከአባቶቻችን የወረስነውን ሃይማኖት ጠብቆ፣ ከምስጢራት እየተካፈሉ መኖር
23

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ብልህነት ነው፡፡ አለበለዚያ ግን ይህን ተከትሎ የሚመጣው ምንፍቅና ውጤቱ በነፍስ መሞት፣ በሲኦልም መቃጠል
ነው፡፡ፊደል ይገድላል ሲባልም የነፍስ ሞት ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ 3፤6
ራስን መግደል
ራስን መግደል ልክ ሌሎችን እንደመግደል ሁሉ ያስቀጣል፡፡ ይህም በቀጥታ (ወዲያው) ሕይወትን ማጥፋት ወይም
ቀስ በቀስ በጊዜ ሒደት የሚፈጸም ራስን ጥፋት ሊሆን ይችላል፡፡
ሰው ነፍሱ የእርሱ አይደለችምና ያሻውን ሊፈጽምባት አይችልም፡፡ ነፍሳችን የክርስቶስ ናት፤ እርሱ አስቀድሞ
ካለምንም ፈጥሯት፣ ኋላም በመስቀል ባፈሰሰው ደሙ በዋጋ ገዝቷታልና፡፡ ይህ ሕግ ግን ለአእምሮ ሕመምተኞች
አይሠራም፤ እነርሱ በዚህ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ኃጢኣቶችም አይጠየቁም፡፡
ሰው በገመድ ታንቆ፣ ከባሕር ጠልቆ፣ ከገደል ራሱን ጥሎ፣ መርዝ ጠጥቶ ራሱን ይገድላል፡፡ ሰው ራሱን ማጥፋቱ
ተስፋ መቁረጡን ያመለክታል፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ ላይ ተስፋ ማድረግ አለመቻሉ በራሱ ደግሞ
ኃጢኣት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ መከራን መቋቋም አለመቻልን ያሳያል፡፡ ራሱን የሚያጠፋ ሰው ሞት ለሁሉም ችግሮቹ
ማብቂያ መንገድ ነው ብሎ ያስባል፡፡ ይህ ግን ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ የሚያምን ከሆነ ፍጹም የተሳሳተ ነው፤
ራስን መግደል ለማያልቀው ለሲኦል እሳት አሳልፎ ይሰጣልና፡፡ ስለዚህ ራስን ማጥፋት ለችግሮች መንፈሳዊም ሆነ
ተግባራዊ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡
ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ወዳጅነት፣ ፍቅር ያፈረሱ፣ ራሳቸውን የወደዱ ስለሆኑ
በቤተክርስቲያን ሥርዓት ጸሎት አይደረግላቸውም፤ የክርስቲያን ማዕረግ አይሰጣቸውም፡፡
ቀስ በቀስ የሚደረግ ራስን ማጥፋት፡- ከመግደል ወንጀል እንደሚቆጠሩ የማይታወቁ ብዙ ራስን የማጥፊያ መንገዶች
አሉ፡፡ የራስን ጤና በአግባቡ አለመጠበቅ አንዱ ራስን የመግደያ መንገድ ነው፡፡ ሰውነታችን የእግዚአብሔር ስጦታ
ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውንም መንፈሳዊ ተግባር ያለምንም ችግር መፈጸም እንችል ዘንድ ጤንነታችንን ልንጠብቅ
ይገባናል፡፡ ክርስትና ሰውነትን መግደልን አያዝም፤ ይልቁንም የሥጋን ፍትወትና ምኞት ባሉት ምስጢራት ድል
ማድረግን ነው እንጂ፡፡ ሰውነታችንን ሳይሆን ፍትወታትን እንገድላለን፡፡ (ኤፌ 5፤29) እግዚአብሔርም ለሰውነታችን
እረፍት ይሆነን ዘንድ ሰንበትን ሰጥቶናል፡፡ ደካማና ጤናማ ያልሆነ ሰውነት በአግባቡ መጾም፣ መጸለይ፣ ሌሎች
መንፈሳዊ ተግባራትንም ማከናወን ያዳግተዋል፡፡
ሰውነታችንን የሚጎዱ ብዙ ልማዶች አሉ፡፡ አብዝቶ መብላት፣ ቶሎ ቶሎ መመገብ እንዲሁም በየጣልቃው መብላት
ሰውነትን ያደክማል፣ ለልዩ ልዩ በሽታዎችም ይዳርጋል፡፡
የዝሙት ኃጢኣት ሌላው ሰውነትን የሚጎዳ ነገር ነው፡፡ ሰውነታችን ከሚችለው አቅም በላይ ማሠራት እና ለድካም
መዳረግም የሰውነታችንን ጤና በእጅጉ ይጎዳዋል፡፡ ለሕመምና ለድንገተኛ ሞትም ሊዳረገን ይችላል፡፡
ሌሎች በጊዜ ሒደት ራሳችንን ለማጥፋት ምክንያት የሆኑት ደግሞ ማጤስ፣ መጠጥ መጠጣትና የአደገኛ ዕፅ ሱሰኝነት
ናቸው፡፡ እነዚህ በእጅጉ የሰው ልጅን አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አደገኛ ነገሮች ናቸው፡፡
ምሳ 23፤31-32፣ ምሳ 20፤1 1ኛ ቆሮ 6፤9-10፣ 5፤11
ራሳቸውን በነዚህ ነገሮች የሚገድሉ ሰዎች የሚወልዷቸው ልጆች ደካማ (ያለጠነከሩ)ና ጤናማ ያልሆኑ ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሱስ የተያዙ ሰዎች ጎጂነቱን እንዲሁም ደግሞ ራሳቸውም መላቀቅ እንዳልቻሉ ቢያዉቁትም
ሌሎችን ወደዚህ ተግባር እንዲገቡ ስለሚገፋፉ ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይገድላሉ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ ራስን ማጥፋት፡- የመጀመርያው የገዛ ነፍስን የሚያጠፋው ነገር ኃጢኣት ነው፣ ኃጢኣት ራሱ ሞት ነውና፡፡
(ኤፌ 2፤5፣ሮሜ 6፤23፣ ሮሜ 8፤6) ሰው ኃጢኣትን በመሥራት ከእግዚአብሔር ነፍሱን ይለያል፣ ወደ ሲኦልም
ይጣላል፡፡ ከመንፈሳዊ ተግባራት መራቅም ሌላው የነፍስ ሞት ነው፡፡ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ተመስጦን፣ መንፈሳዊ
ንባባትን፣ ንስሓን፣ ሥጋና ደሙን መቀበልን እንዲሁም ሌሎች ጸጋን የሚያሰጡ ሥራዎችን ማቆም ነፍስን
ያደክማታል፣ እየሸረሸረም ያጠፋታል፡፡ ለሥጋዊ ምኞቶቹ ያደረ፣ በዓለም ምኞትም የሚቃጠል ስድስተኛውን ሕግ
አፍርሷል ማለት ነው፡፡
24

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

 የመግደል ውጤቶች
የሰውን ሕይወት ያበላሻል፤ ዕድሜን ያሳጥራል፤ ሕልውናን ያጠፋል፡፡ የገዳይንም ሕይወት ለኀዘን፣ ለትካዜ፣
ለሥጋት፣ ለጭንቀት፣ ለፍርሃት፣ ለፀፀት፣ ለሽሽት፣ ለብቸኝነት በመጨረሻም ለፍትሕ ያጋልጣል፡፡
በሰማይም በምድርም፣ በነፍስም በሥጋም ያዋርዳል፡፡
የሁለት ዓለም ስደተኛ ያደርጋል፡፡
 ይህንን የጭካኔ ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ሰው ባይኖር እንኳ በሚከተሉት ነገሮች ይወቀሳሉ፣ ይከሰሳሉ፡፡
የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር፡- ለይቅርታ የማይመች አሰቃቂ ኃጢኣት በመሆኑ እግዚአብሔር ይጸየፈዋል፡፡
2ኛነገ 24፤3-4 ዘዳ 32፤39 ዘፍ 9፤5
የራሱ የአጥፊው ኅሊና፡- ዘፍ 4፤14
በደሉ የሚፈጸምበት ሰው ደም (ነፍስ)፡- ዘፍ 4
በዙሪያው የሚኖሩ ሥነ ፍጥረቶች፡- ዘዳ 32፤1 ኢዮ 20፤27
2.6 ትእዛዝ 6
‹‹ኢትዝሙ (አትዘሙት)›› ዘፀ 20፡14
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ፡
1 ስለማንኛውም ሰው ክብር፣ ንጽሕና፣ ቅድስና ሕይወት ሲባል
2 የእግዚአብሔር ሕዝብ ከሌላው አረማዊ ሕዝብ የተለየ ወይም ቅዱስ መሆን ስለሚገባው በፆታዊ ሕይወቱ ላይ
ሥርዓትና ሕግ እንዲኖረው ለማድረግ
3 የፆታ ሕይወት በተቀደሰ ጋብቻ ተጠብቆ በጥንቃቄ እንዲኖር ለማስቻል ነው፡፡
የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ትእዛዝ አታመንዝር በማለት ይገልጸዋል፡፡ ይህ ግን የዝሙት አንድ ገጽታ እንጂ
ሙሉውን ስለማይወክል አትዘሙት በሚል ቢገለጽ የተሻለ ይሆናል፡፡ ዝሙት ማለት ፍቅረ ተራክቦ ማለት ነው፤
ዝሙት አንድ የኃጢአት ግብር ሆኖ ሳለ በተለያዩ ሦስት መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡ እነዚህም አመንዝራነት፣
ሴሰኝነትና ጋለሞታነት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ እንደ መላእክት ባለ ንጽሕና ይኖር ዘንድ ተፈጥሮ ሳለ በዝሙት ምክንያት
እንስሳዊ ባሕርዩ እየጎላ በሔደ ቊጥር እግዚአብሔርን ያሳዝናል፡፡
ከዚህ በታች ዝሙት የሚፈጸምባቸውን የተለያዩ መንገዶች እንመለከታለን፡፡
1 አመንዝራነት፡ አመንዝራነት የሚለው የቃሉ ፍቺ መንዛሪ ማለት ሲሆን በትዳር ውስጥ ያለውን አንድነት
የሚመነዝር (የሚያበዛ) የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ሚስት ከባሏ ባልም ከሚስቱ ውጪ ሲሄዱ አመንዛሪ
የሚባሉ ሲሆን እግዚአብሔር የሰጣቸውን አንድነት ወደ ብዙ ቊጥር በመቀየራቸው፣ በማፍረሳቸው ስያሜ ነው፡፡
በሌላ በኩል በማቴዎስ ወንጌል ላይ ተጽፎ እንደምናነበው ማቴ 5፡32 ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ ያለ ዝሙት ምክንያት
ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል›› የሚለውን ኃይለ ቃል ስንመለከተው ሚስት ከሌላ ሔዳ ካላመነዘረች
በስተቀር የሚፈታት ከሆነ በትዳራቸው ውስጥ ያለውን አንድነት ይመነዝረዋል፡፡ ሚስቱ እንደምታመነዝር ካወቀ ግን
አንድነታቸውን ያፈረሰቸው እርሷ ናትና መፍታት ይገባዋል፡፡ እርሷም ይህንን ድርጊት ከፈፀመች በኋላ ምንም እንኳን
በንስሐ ብትመለስ ያላት ብቸኛ አማራጭ መመንኮስ ብቻ ነው፡፡

25

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ከዚህ በተጨማሪ በወንጌል ‹‹ሴትን ያያት የተመኛትም በልቡ አመነዘረ፡፡›› ማቴ 5፡28 እንደተባለው ይህች ትንሽ
የልብ ምኞት ናትና አድጋ ወደ ተግባር የምትቀየረው ከእርሷ ጋር በልቡ አመንዝሯል ያሰኛል፡፡
2 ሴሰኝነት፡ የቃሉ ፍቺ ሱሰኛ ማለት ሲሆን ራሱን መግዛት ካለመቻሉ የተነሣ በበዓላት፣ በአጽዋማት፣ ጊዜና ቦታ
ሳይመርጥ አብዝቶ ሩካቤ የሚፈጽም ሰውን ይመለከታል፡፡ በሌላ በኩል ሴሰኝነት ስስታም ተብሎም ሊተረጎም
ይችላል፤ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በጋብቻ ተወስኖ ቤተሰብ ማፍራት የማይፈልግ ራስ ወዳድነት፣
ስግብግብነት የሚያጠቃው ሰው ይህ ስያሜ ሊሰጠው ይችላል፡፡
3 ጋለሞታነት፡ ገንዘብን ለማግኘት ሰውነታቸውን ለዝሙት የሚያስገዙ ዝሙትን እንደ ሥራ ዘርፍ ወይም የገቢ
ምንጭ አድርገው የሚኖሩ ሰዎች ጋለሞታ በመባል ይጠራሉ፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው ሦስቱ ዝሙት ሊፈጸምባቸው ከሚችሉት መንገዶች በተጨማሪ እጅግ አስከፊና ከባድ
የሆነው ኃጢአት ግብረሰዶም ነው፡፡ ይህ የዝሙት ዓይነት በበለጠ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር የሚደረግ ሲሆን እጅግ
የረከሰና እንስሶች እንኳን የማይሠሩት አስጸያፊ ሥራ በመሆኑ ቅጣቱ ከባድና የእግዚአብሔርን እርግማን የሚያመጣ
ነው፡፡ ስለዚህ በልዩ ልዩ በደልና ክፋት የተቀጡትን በተለይም በዓመፅ ሥራና በዝሙት ኃጢአት ብዛት ከምድረ ገጽ
የጠፉትን የኖኅ ዘመን ሰዎችን (ሰብአ ትካትን) ፣ በአብርሃም ዘመን የነበሩትን ሰዶምና ገሞራን እያሰብን ራሳችንን
እንዲህ ካለው ኃጢአት መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
የአመንዝራነት መንስኤዎች
መንስኤ ማለት የአንድ ነገር መነሻው መሠረቱ ሲሆን የአመንዝራነት መንስኤዎች በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ከእነርሱም
ውስጥ ጥቂት ብንመለከት፡
1 ተገቢ ያልሆነ አለባበስ፡ የልብስ አስፈላጊነቱ ሰውነትን ለመሸፈን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል፡፡ በኦሪት
ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈው ‹‹የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ፤ የበለስንም
ቅጠሎች ከፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ፡፡›› ዘፍ 3፡7 ከዚህ ወረድ ብሎ ዘፍ 3፡21 ‹‹እግዚአብሔር
አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፣ አለበሳቸውም›› ይላል፤ ይህ የሚያሳየን መሸፈን ያለበት
ሀፍረት ብቻ ሳይሆን ሰውነታችንም ጭምር መሆኑን ነው፡፡
ሌላው የሰው ገላ የሚሸፈንበት ምክንያት ከልብስ መራቆት ሰውን ለማሰናከል ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ እናት ሔዋን ከአዳም ግራ ጎን መገኘቷ መሸፈን እንዳለባት ያጠይቃል፡፡ ማንም ሰው ጎኑን በእጁ
አውቆም ይሁን ሳያውቅ ይሸፍናል፡፡ ተፈጥሮ እንኳን ይህንን ስለሚያስተምረን የምዕራባውያንን ዘመን አመጣሽ ርካሽ
ባሕላቸውን በመተው ባሕላችንን የጠበቀና አግባብነት ያለው ልብስ መልበስ ይጠበቅብናል፡፡
2 አብዝቶ መብላትና መጠጣት፡ የመብል አስፈላጊነት ለቁመተ ሥጋችን ጽናት ነው፡፡ ነገር ግን ሐዋርያው ቅዱስ
ጴጥሮስ እንዳስተማረን ሁሉ በአግባቡና በሥርዓት መሆን ስላለበት አብዝተን ማንኛውንም ነገር ማድረግ የለብንም፡፡
1ኛ ጴጥ 5፡8፣ ሕዝ 16፡49 ሥጋ የነፍስ ፈረስ ነው፤ካልተገራና ልጓም ካልተበጀለት ገዢው ተገዢ መሆኑ አይቀርም፡፡
አንድ ሰው አብዝቶ በበላ ቊጥር ደማዊት ነፍሱ እየሞላች ትሄድና ሕያዊት ነፍስ ዕውቀቷን መሳያ ቦታ ታጣለች፡፡
በመሆኑም ሰው በኅሊናው ማሰብ ያቆምና እንደ እንስሳት በደመነፍሱ ማሰብ ይጀምራል፡፡ ያን ጊዜ ጾር እንኳን
ቢመጣበት የመጣበትን ጾር በስግደት ለመከላከል ያዳግተዋል፡፡ በመሆኑም በቀላሉ በዝሙት ኃጢአት ይወድቃል፡፡
ስለዚህ ሐዋርያው እንዳስተማረን ሁሉን በአግባቡና በልክ እየተጠቀምን ፈቃደ ሥጋችንን ለፈቃደ ነፍሳችን ማስገዛት
ይበጀናል፡፡
አብዝቶ መጠጣት ከመብል ጋር ተመሳሳይ ውጤት የሚያስከትል ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሰው ልጅ አስተሳሰብን
ከጤናማ አሠራር ውጪ ስለሚያደርገው እጅግ አስከፊ የሆነ ጉዳት በራስና በሌላው ሕብረተሰብ ላይ ያስከትላል፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ ምሳሌ ላይ እንዳሰፈረልን አብዝቶ የጠጣ ሰው ራሱን እንደሚያውቅ እንረዳለን፡፡ ምሳ
23፡31-38 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ሰካራም አውቆ አበድ ነው በማለት አብዝቶ የመጠጣትን አስከፊነት
ገልፆልናል፡፡

26

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

3 ምኞት፡ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ‹‹ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፡፡››
ምኞትም ከጸነሰች በኋላ ኃጢአትን ትወልዳታለች፤ ኃጢአትም ከተፈፀመች ሞትን ትወልዳታለች፡፡ ያዕ 1፡14-15
እንዳለ ምኞት የበደል ሁሉ ምንጭ ናት፡፡ በሰው ልጅ የታሰበችው ትንሽዋ… ምኞት ወደ ኃጢአት ታመራና ፍጻሜዋ
ሞት ይሆናል፡፡
4 ተገቢ /ጤናማ/ ያልሆነ የተቃራኒ ፆታ ቅርርብ፡ ተገቢ ያልሆነ ነገር ውጤቱ አስከፊና አሳዛኝ መሆኑ እሙን ነው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም በመልዕክቱ ጴጥ 5፡8 ላይ ‹‹ሁሉ በአግባቡና በስርዓት እንዲሆን አዝዞናል፡፡›› ይህን ትእዛዝ ጥሰን
አግባብነት በሌለው መልኩ ከተቃራኒ ፆታ ጋር በመቀራረብ በዝሙት ኃጢአት ለመውደቅ መንስኤ ስለሚሆን ሕዝብ
በበዛበት ስውር ባልሆነ ቦታ በመገናኘት ሲገናኙም ለዝሙት የሚጋብዙ ነገሮችን ባለማውራትና ባለማድረግ
ራሳችንን እንዲህ ካለው ኃጢአት መጠበቅ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡
5 ተገቢ ያልሆኑ ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን እንዲሁም ሥዕላትን ማየት፣ መስማትና ማንበብ፡
የዓመፅና የኃጢአት ሁሉ በተለይም የዝሙት መቀስቀሻው በአብዛኛው ጊዜ በማየትና በመስማት በመሆኑ ክፉውን
ከደጉ እየለየን መጠቀምና ማወቅ ይበጀናል፡፡ የመገናኛ ብዙኃንን አጠቃቀም በጥበብና በማስተዋል ብናደርገው
ይበጀናል፡፡ አላስፈላጊና አልባሌ የሆኑ ነገሮችን ማየት ጤናማ የሆነውን አእምሯችንን ይበክላል፤ ቀስ በቀስም
የሀልዮ/የማሰብ/ በደል ወደ መናገር ብሎም ወደ መፈጸም ይደርሳልና ነገሮች እዚህ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት
ምክርን ሰምቶ ለሚፈጽማት ሁሉ መልካም ይሆንለታልና ራሳችንን መጠበቅ ያሻል፡፡
6 ዘፈን፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንደሚባል ዘፈንም ስንሰማ ሥጋችንን ደስ እያሰኘና ወደ ዝሙት እየገፋፋ
ሰውን በኃጢአት አዘቅት ውስጥ በመጣል ከእግዚአብሔር ከአምላኩ ያለያየዋልና ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ዘፈንን
ከመስማት፣ ከማዳመጥ፣ አብሮም ከመዝፈን ሊቆጠብ ይስፈልጋል፡፡
7 ሥራ ፈትነት፡ የሰው ልጅ በሥራ ሲጠመድ ኃጢአትን ማሰብ ይቀንሳል፤ ያልታሰበ ኃጢአት ደግሞ ፍጻሜ
አይኖረውምና መሥራት በዝሙት ከመውደቅ ይጠብቃል፡፡ ‹‹ሥራ ፈት አዕምሮ የዲያቢሎስ ቤተ ሙከራ ነው››
እንደሚባል ሰው የሚሠራው ሲያጣ ሰይጣን በልቡ ይገባና ያልሆነ ሐሳብ እያሳሰበ ሰውን በኃጢአት ይጥለዋል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም ክርስቲያን ራሱን በሥራ መጥመድ ይገባዋል፡፡ ‹‹ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀድዶ ይሰፋል፡፡››
የሚባለውም እንዲሁ ተረትና ምሳሌ ሳይሆን መነኮሳት አዕምሯቸውን ሥራ ላለማስፈታትና ራሳቸውን ከኃጢአት
ለመጠበቅ ሥራ ቢያጡ እንኳን ቆባቸውን ቀደው እንደሚሰፉ ለመግለጥ ነው፡፡
የአመንዝራነት መገለጫዎቹ ምንድን ናቸው
የአመንዛራነት ውጤቱ
አመንዝራነት በመንፈሳዊ ገጽታው
ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው ማመንዘር ማለት አንድ የሆነውን ነገር ማብዛት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በመሆኑም
ከላይ ከተመለከትናቸው ገጽታው በተጨማሪ አመንዝራነት በመንፈሳዊ ገጽታው ስንመለከተው፡
1 እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖት ማምለክ አመንዝራነት እንደሆነ ነቢዩ ኤርምያስ በትንቢቱ ኤር 3፡8-10 ‹‹ ከዳተኛይቱ
እሥራኤል እንዳመነዘረች አየሁ፤ የፍችዋንም ደብዳቤ በእጅዋ ሰጥቼ ሰደድኋት፣ ጎስቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ
አልፈራችም፤ እርሷም ደግማ ሔዳ አመነዘረች፡፡ ዝሙቷም ከንቱ ሆነ፤ እርሷም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች፡፡
›› በማለት ጣዖት አምልኮ አመንዝራነት መሆኑን አስረድቶናል፡፡
2 በሌላ በኩል ሃይማኖትን መለዋወጥ ማመንዘር ነው፡፡ ሃይማኖት አንዲት እንደሆነች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ለኤፌሶን ምዕመናን በላከው መልዕክቱ ገልጾልናል፡፡ ኤፌ 4፡4 ‹‹ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› በመሆኑም
ይህችን ሃይማኖትን ማብዛትና መመንዘር ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ››
ኤፌ 4፡3 እንደተባልንና እንደታዘዝን አንዲቷን ሃይማኖት በፍጹም ቁርጠኝነት ልንጠብቃትና በእርሷም ልንጸና
ያስፈልጋል፡፡

27

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

3 በየጊዜው ጓደኛን መቀያየር፣ ወረተኝነት፣ በአንድ አለመወሰን፣ ከአንዱ ጋር ስንሆን አንዱን ማማት፣ በእጮኝነት
ጊዜ ሀብትን፣ ጤንነትን መሠረት ማድረግ በክርስቶስ ወገኖች መካከል ያለውንና ሊኖር የሚገባውን አንድነት
ይመነዝረዋል (ያበዛዋልና) አመንዝራነት ያሰኛል፡፡
የዝሙት አስከፊነት
ዝሙት ልዩ ልዩ በሽታዎችን ያስከትላል፡፡ ለሥጋችን የማይፈወስ ደዌን፣ ለልቡናችን የማያቋርጥ ጭንቀትን፣
ለቤተሰብም ጉዳትና ሥጋትን እንደሚያመጣብን አውቀን ራሳችንን በጥብቅ እየተቆጣጠርን መሸሽ ይጠበቅብናል፡፡
ብዙ ምዕመናን ራሳቸውን በመቆጣጠር በክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር በመኖራቸው ከደዌ ነጻ ሆነው በሰላምና በጤና
እንደሚኖሩ ቅድስት ቤተክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡
የዝሙት፣ የርኩሰት ሥራ ሁሉ እንስሳዊ ባሕርይያችንን ስለሚያሆላ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረችንው ነፍስን በጣም
ይጎዳታል፡፡ በሥጋም በነፍስም ጥፋትን ያስከትልባታል፡፡ የክርስቶስ አባል፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነው
ሰውነታችን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልዕክቱ ላይ ገልጾልናል፤
የሚከተለውንም ምክርና መመሪያ ሰጥቶናል ‹‹ከዝሙት ሽሹ፣ ሰው የሚሰራው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጪ ነው፤
ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል፡፡›› 1ኛ ቆሮ 6፡12-20
ልቡናቸው በሐፀ ዝሙት የተወጋ ሁሉ በተለይም ልጆችና ወጣቶች መጨረሻቸው ጥፋት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ
ያደጉ ሁሉ አመንዝራና ክፉ ትውልድ ስለሚሆኑ ለቤተሰባቸውና ለሕብረተሰቡም የማይጠቅሙ ለሀገርና ለወገን ጤና
የማይሰጡ፣ በሥራ ተሠማርተው መልካም ውጤት የማያስገኙ ሞራለ ብልሹዎችና ወኔ ቢሶች በመሆን ራሳቸውን
ሌሎችንም ጭምር ይጎዳሉ፡፡
የዝሙት አፈጻጸም ዓይነቶች
የዝሙት ኃጢአት የሚፈጸመው በሥራ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መንገዶች ጭምር ነው፡፡
ሀ በስሜት የሚፈጸም ዝሙት፡
ለ በማሰብ የሚፈጸም ዝሙት፡ ሰው በመንፈሱ፣ በሥጋው፣ በነፍሱ፣ በኅሊናው በሁለንተናው ንጹሕ ሆኖ ሊኖር
ይገባዋል፡፡ ሐሳብ በእናታችን በሔዋን ውስጥ ሲጀምር ተራ ጥያቄ ስለ ነበር ከእርሷ ይልቅ ደካማ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ
እርሷ ይህን ሐሳብ ልታፈርሰው ትችል ነበር፤ ይሁን እንጂ ሔዋን በኃጢአት ከተሞላ ሐሳብ ጋር ስትደራደር
ላልተቋረጡ ውትወታዎችና ለማባበሉ ስለተጋለጠጭ ልትደክም ጀመረች፡፡ በውስጧ የነበረው ሐሳብ ወደ ጥርጥር
በመጨረሻም ወደ ምኞት ስለተለወጠ እጇን ዘርግታ ፍሬውን በመቁረጥ በላች፡፡ የዝሙት ሐሳብም በኅሊናችን
ከተፀነሰ ጊዜ ጀምሮ የሰውን ቅዱስ መንፈስ ያሸሸና በምትኩ በመንገሥ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነው ሰውነታችንን
ያረክሰዋል፡፡ ይህም ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ፍጻሜ ላይ በመድረስ የኃጢአት አዘቅት ውስጥ ይጥለናል፡፡ በመሆኑም
በትጋት፣ በጸሎትና እግዚአብሔርን በመለመን የሐሳብን ኃጢአት አጥብቀን ልንዋጋው ያሻል፡፡
ሐ በልብ ምኞት የሚፈጸም ዝሙት፡ በልብ ምኞት ስለሚፈጸመው ዝሙት ጌታቸን አምላክችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በወንጌል እንደሚከተለው አስተምሮናል፡፡ ‹‹አታመንዝር እንደተባለ ሰምታችኋል፣ እኔ ግን እላችኋለው ወደ
ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል፡፡›› ማቴ 5፡ 27-30 ስለዚህ ድርጊት አልባ
የሆነውን ምኞት ከማመንዘር ተቆጥሯል፡፡
መ በመናገር (በጸሑፍ) የሚፈጸም ዝሙት፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹‹ሰዎች
ስለሚናገሩስት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል›› ማቴ 12፡36 በማለት አስተምሮናል፡፡ በዚሁ
ወንጌል ትንሽ ወረድ ብሎ ምዕራፍ 15፡11 ላይ ‹‹ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው
ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው…›› ብሏል፡፡ ይሄ ደግሞ የአንደበት ኃጢአቶች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ
ይገልጽልናል፡፡ አንደበት ከሚወድቅባቸው ኃጢአቶች መካከል አንዱ የዝሙት ኃጢአት ሲሆን እነዚህ ቃላት በመጥፎ
ታሪኮች፣ በጋጠወጥ ቀልዶች፣ በአሳፋሪ ዘፈኖች፣ በዝሙት በሚፈታተኑ ቃላት፣ ትሕትና በጎደለው ጠባይ ውስጥ

28

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የሚገለጡ ማንኛውንም ………… ቃላት ናቸው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ክርስቲያን ራሱን ከእንደነዚህ ያሉ አሳፋሪ
ተግባር ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡
አንድ ክርስቲያን በዝሙት ኃጢአት ቢወድቅ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
አንድ ሰው አውቆም ይሁን ሳያውቅ በአጋጣሚ ምክንያት ባልጠበቀው ሰዓትና ሁናቴ በዝሙት ኃጢአት ተስፋ ቆርጦ
እንዳይቀር በክርስቶስ የመዳን ዋስትና እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት እንደማይለየው አውቆና አምኖ
ከወደቀበት ተነሥቶ ንስሐ ገብቶ መንፈሳዊ ተጋድሎውን መቀጠል አለበት፡፡ ምክንያቱም ንስሐ የማይሽረው ኃጢአት
የለምና፡፡ የሐዋርያውን የቅዱስ ዮሐንስን መልእክት ትምህርትና ምክር በትክክል መረዳት ይኖርበታል እንጂ ተስፋ
መቁረጥ የለበትም፡፡ ሐዋርያው ‹‹ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለው›› ብሎ ቋሚ ትእዛዛትን
ከሰጠን በኋላ ይቀጥልና ምናልባት በኃጢአት የወደቀ ቢኖር በዚያው ተስፋ ቆርጦ እንዳይቀር አስቦ ‹‹ማንም
ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ የኃጢአታችን
ማስተስረያ ነው፤ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ ›› ብሎናል፡፡ 1ኛ ዮሐ 2፡12
ስለዚህ ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ነጻ ሊያወጣን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡››
1ኛ ዮሐ 1፡7-9 ትልቁ ሞት ተስፋ መቁረጥ ነውና በእግዚአብሔር ምሕረት እንተማመን! ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና
ተስፋ አንቁረጥ (መዝ 117፡1) ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ሰባት ጊዜም ይነሳል የተባለውን እያስታወስን በልዩ ልዩ
ፈተና በመግባት በሀልዩ፣ በነቢብ፣ በገቢር በማወቅ ባለማወቅ በሠራነው ኃጢአት በወደቅን ጊዜ እንደ ወደቅን
ሳንቆይና ሳንቀር ወዲያውኑ ተነሥተን በመንፈስ ቅዱስ ተጽናንተን በንስሐ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን መልሶ
ማጠናከር ይገባናል (ምሳ 24፡16) እንግዲህ በክርስቶስ ያለን ሁሉ ኩነኔ እንደሌለብን አውቀንና አምነን (ሮሜ 8፡1-4)
ድካማችንን በሚያውቅልንና በሚያግዘን በመንፈስ ቅዱስ እየተመራን እንደ ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈቃድ
እየተመላለስን ወደ እግዚአብሔር አባታችን በመጸለይ በተለይም የንጽሕ ተጋድሏችንን መፈጸም ግዴታችን ነው (ሮሜ
8፡12-13) ‹‹ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም›› የሚባለው አባባል ትክክለኛና ተስፋችን እግዚአብሔር መሆኑን አምነን
በንስሐ በመመለስ ሕይወታችንን ልንመራ ያስፈልጋል፡፡
በክርስትና ተቀባይነት የሌላቸው ግንኙነቶች
እንደ ቅደስት ቤተክርስቲያናችን አስተምሮ የጋብቻ ዓላማዎች ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም ዘር ለመተካት፣ ለመረዳዳትና
ከዝሙት ለመጠበቅ ናቸው ፡፡ ነገር ግን በክርስትና ተቀባይነት የሌላቸውን ጋብቻ መመሥረት የጋብቻን ዓላማ አስቶ
ወደ ኃጢአት ያመራል ፡፡ በመሆኑም አንድ ክርስቲያን ከእነዚህ የተሳሳቱ መንገዶች ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
እነዚህ ምንድናቻ ቢሉ፡
1 ከሕገ ወጥ ፍቺ በኋላ የተመሠረተ ጋብቻ፡ አመንዝራነትን ከሚያስፋፉት ነገሮች አንዱ የጋብቻ መፍረስ፣ የባልና
ሚስ መፋታት ነው፡፡ መፋታት በወንጌል የተከለከለ ነው፤ ‹‹ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ያመነዝራል››
ማቴ 5፡32 የተባለውም ሊዚሁ ነው፡፡ እንዲህ ካለ ሕገ ወጥ ፍቺ በኋላ ዳግም ጋብቻን መመሥረት ከበፊቱ ከፍ ያለ
ቅጣትን ያስከትላል፡፡
2 የተፈታችውን (የተፈታውን) ማግባት፡ ‹‹…የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፡፡›› ማቴ 5፡32 ብሎ
ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ እነደጻፈልን ይህንን ማድረግ አግባብነት እንደሌለው እንመለከታለን፡፡
3 ዘመድ ማግባት፡ እግዚአብሔር አምላክ አዳምና ሔዋንን ከፈጠራቸው በኋላ ልጆችን እንደሰጣቸው ቅዱሳት
መጻሕፍት ይመሰክራሉ፤ ልጅንም በወለዱ ጊዜ በመጀመርያ ቃየልና ሉድን (መንታ ሆነው) ሁለተኛ ደግሞ አቤልንና
መንትያው አቅሌማን ያገኛሉ፡፡ አባት አዳም እነዚህ ወጣቶች በደረሱ ጊዜ ዝምድናን ለማራራቅ ብሎ የአቤልን
መንትያ ለቃየል፣ የቃየልን መንትያ ለአቤል መዳሩን መጻሕፍት ተባብረውበታል፡፡ አባታችን አዳም እንዲህ ያደረገው
ዝምድናን ለማራራቅ ብሎ ከሆነ ታዲያ በዚህ ዘመን የሰው ዘር በበዛበት ጊዜ ዘመድን ከዘመድ ጋር ማጋባት እጅግ
አሳፋሪና አስጸያፊ ሥራ በመሆኑ በክርስትና ተቀባይነት የለውም፡፡
4 ከአንድ በላይ ማግባት፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በተዓቅቦ መኖር፣ አንድ ወንድ በአንዲት ሴት አንዲት ሴትም
በአንድ ወንድ ጸንታ እንድትኖር ታስተምራለች፡፡ ምክንያቱም ከዝሙት ኃጢአት ለመሸሽ ይህ የሚያዋጣና እውነተኛ

29

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

መንገድ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ በትዳር ውስጥ ያለውን አንድነት የሚያበዛና የሚመነዘር በመሆኑ ተቀባይነት
እንደሌለው አስረግጣ ትናገራለች፡፡ ይህ ግን ባል ወይም ሚስት የሞቱባቸውን ሰዎች አያካትትም፡፡
የዝሙትን ጾር እንዴት እንቋቋም?
ክርስቲያን የዝሙትን ጾር ሊቋቋም የሚችለው ፈቃደ ሥጋውን ለፈቃደ ነፍሱ ማስገዛት ሲችል ነው፡፡ ይህንንም
ለማድረግ የሚከተሉትን ነገሮች መተግበር ይኖርበታል፡፡
1 ዝሙትን ከማሰብ መሸሽ፡ አንድን ነገር እንድናስበው በቅድሚያ ማወቅ ይጠበቅብናል፤ የምናውቀውም በማየት
ነው፡፡ እንግዲህ የዝሙት ኃጢአት መነሻዋና መሠረቷ ምኞት ሲሆን የምኞት ቀስቃሽዋ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ
ክፉውን በማየት እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ የማይገባውን ነገር ማየት በተለይም ክፉውን አይቶ
መመኘትን ለመቆጣጠር ያልተቆጠበ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ የሥጋ ምኞትንና የዓይን አምሮትን በመንፈስ ኃይል ዘወትር
በመጠን እየኖርን በጾም በጸሎት ሆነን በጸጋው አጋዥነት መታገል አማራጭ የሌለው ብቸኛ መፍትሔ ነው፡፡ እንዲህ
ያለው የዝሙት ምኞት ቆይቶ ወደ ድርጊት ስለሚያመራ በቅድሚያ እሱን መቆጣጠር የመጀመርያው ሥራችን መሆን
ይገባዋል፡፡
2 ከዝሙት ማዕበል ጋር ከመጋፈጥ መሸሽ፡ በአሁኑ ዘመን በየቤቱ፣ በየመንገዱና በየቦታው ከሰዎች ዘመን አመጣሽ
አለባበስ በተለይም ገመናን ከሚያጋልጥ አለባበስና አካሄድ ጀምሮ እስከ ዝሙት ማስታወቂያዎች ከዚያም አልፎ እስከ
መጠጥና ዳንኪራ ቤቶች የበዙበት ሁናቴ ስለተፈጠረ ከመቼውም ይበልጥ ወጣቶች በሚያዩት ነገር እየተታለሉ
ሲሰነካከሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ከመጋፈጥ መሸሽና በሩቁ በመከላከል ሕገ-ወንጌልን እንድንፈጽም መታገል
ይኖርብናል፡፡ ይህንንም ብናደርግ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ዋጋችንን በሰማይ ይከፍለናል፡፡
3 ከሥራ ፈትነት መሸሽ፡ ሥራ መፍታት በተለያዩ የኃጢአት ወጥመዶች ተጠምደን እንድንውል መንገድ ስለሚከፍት
ከሥራ መቦዘንን ማስወገድ ይጠበቅብናል፡፡
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው ራሳችንን ለመግዛትና ፈተናን ለመቋቋም እግዚአብሔር ከሚያደርግልን ረድኤል
ጋር እኛ በበኩላችን ልንፈጽማቸው የሚያስፈልጉ ነገሮችን ተመልክተናል፡፡ ጤናማው ክርስቲያናዊ ሕይወት
በንጽሕናና በቅድስና ተጠናክሮ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደርሳል፡፡ ይህም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለሆነ በመንፈስ ኃይል
ፈቃደ ሥጋንና ምግባረ ሥጋን እየተዋጋን ክርስቶስን በመምሰል የዘለዓለም ሕይወትን ለመውረስ የሚያበቃንን ፍሬ
እንድናፈራ ስጦታው (ጸጋው) ያስችለናል፡፡ እንደ ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈቃድ ከኖርን የመንፈስን ፍሬ
እናፈራለን፣ ራስን መግዛት እንማራለን፣ ንጽሕናንም ገንዘብ እናደርጋለን ፡፡ አምላከ ቅዱሳን ትእዘዛቱን ጠብቀን
የመንግሥቱ ወራሽ እንድንሆን በረድኤት አይለየን! አሜን፡፡
2.7 ትእዛዝ 7
‹‹አትስረቅ›› ዘጸ 20፡15
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ፡
 ማንም ሰው በሀብቱና በንብረቱ ላይ ያለውን ባለቤትነት፣ መብትና ነጻነት ለማሳወቅ፤ በሌላው ሰው
እንዳይሰረቅና እንዳይቀማ ለማድረግ፣ ሕግን ለማስከበር፣ ወንጀልን ለመከላከል
 አንድ ሰው በጉልበቱ ደክሞ አሊያም በስጦታ አግኝቶ የራሱ ገንዘብ ሊያደርግ ይገባል እንጂ በኃይሉ ተጠቅሞ
መቀማት፣ በጥበቡ ተጠቅሞ ማታለል፣ የእርሱ ያልሆነውን ለማግኘት መጣር እንደሌለበት ለማስገንዘብ
 ሰው ሁሉ ‹‹ጥረህ ግረህ ብላ›› የተባለውን ትእዛዝ በመፈጸም ሠርቶ እንዲጠቀም፣ አንዱ በሌላው ጉልበት
እንዳይኖር፣ ጉልበተኛ ደካማውን እንዳያጠቃ፣ ሁሉም ተስማምቶ እንዲኖር ስለ ሰው ልጆች ንብረት መጠበቅ ይህ
ሕግ ተሰጠ፡፡

ሌብነት ምንድን ነው

30

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ስርቆት ሰረቀ ከሚለው የግእዝ ግስ የመጣ ሲሆን ወሰደ የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ይህም ያለባለቤቱ ፈቃድ
(ሳያይ ተደብቆ) የሌላውን ንብረት መውሰድ መጠቀምና ለራስ ማድረግን ያመለክታል፡፡
የተሰረቀው ከማን ነው
የድሀውን ወይም የእለማውታን ወይም የመበለቲቱን ልጅ ገንዘብ ወይም ንብረት መስረቅ እጅግ የከፋ
ኃጢአት ነው፡፡ በቅዱስ መጽሐፍም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ’’እናንተ ጻፎችና
ፈሪሳውያን…የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ…’’በማለት መናገሩ ከድሀውና ከመበለቲቱ መቀማት የከፋ
ኃጢአት መሆኑን የሚመለክት ነው፡፡ ማቴ 23-14
የዕለት ጉርስን ማግኘት ከማይችለው ችግረኛ አራጣ መጤቅም የሰውየውና የልጆቹን የዕለት ጉርስ እንደመስረቅ
ቆጠራል፡፡’’ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለወገኔ ለድሀው ገንዘብ ብታበድረው እንደባለ አራጣ አትሁን አራጣ
አትጫንበት ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱም ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ ነገር ግን አምላክን
ፍራ’’ዘጸ22፥25-26 ዘሌ 25፥ 35-37
ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከእግዚአብሔር ሚሰርቅ ሰው ነው ይህም ዐሥራት በኩራትና ቀዳሚያትን
በታዘዘው መሰረት ባለማውጣት የሚፈጸም ነው፡፡ይህን በተመለከተ ነብዩ ሚልክያስ ’’ወደኔ ተመለሱ እኔም ወደ
እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡እናንተ ግን የምንመለሰው በምንድር ነው ብላችል ሰው
እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችል፡፡እናንተም የሰረቅንህ በምንድር ነው ብላችል፡፡በዐሥራት
እና በበኩራት ነው ፤በቤት ውስጥ መብል እንዲሆን ዐሥራትን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤…በረከትንም አትረፍርፌ
ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ’’
ወደ ስርቆት የሚያደእርሱ ነገሮች

ሰውን እንዲሰርቀ የሚገፋፉት ነገሮች በርካታ ሲሆኑ ከዚህ በመቀጠል የተወሰኑትን እንመለከታለን፡፡

1 አለማመን፡ አለማመን ወደ ስርቆት ሊያደእርሱ ከሚችሉት ነገሮች አንዱ ሲሆን የተወሰኑትን እንመለከታለን፡፡
ሃይማኖት የለሽ መሆን፡ እንኳንስና ክርስትና ማንኛውም ቤተ እምነት ስርቆትን አይደግፍም፡፡ አንድ ሰው
በሃይማኖት ጥላ ሥር ሆኖ ኑሮውን መምራት ካልቻለ ነገሮችን በግድ የለሽነትና ከጤናማው የሕብረተሰብ ክፍል
አስተሳሰብ ለይት ባለ መልኩ የሚያይ በመሆኑ ስርቆትን እንደቀላል ነገር ሊመለከተውና ሊሰርቅ ይችላል፡፡
የእምነት ጎዶሎነት፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መጀመሪያ በጻፈው መልእክት እንዳሰፈረልን 1 ጴጥ 5፡7
‹‹እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት›› ተብለናል፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ምን
እንበላለን፣ ምን እንጠጣለን፣ ምን እንለብሳለን፣ በምንስ እንኖራለን በማለት ዛሬ ላይ ሆነው ስለ ነገ አለአግባብና
ከመጠን በላይ በማሰብ ብሎም በመጨነቅ አእምሯቸውን ዕረፍት ከነሡ በኋላ ከሚመጣላቸው መፍትሔዎች ውስጥ
አንዱ ስርቆት ሲሆን ብዙ ነገሮችንም ማሟላት ስለማይጠይቅ በቀላሉ ወደዚህ ዓለም ይቀላቀላሉ፡፡
2 እግዚአብሔርን አለመፍራት፡ አንድን ነገር ማክበራችንንና መፍራታችንን ከምንገልጽባቸው መንገዶች አንዱ
ትእዛዝን ማክበርና መፈጸም ሲሆን ሌቦች እግዚአብሔርን ባለመፍራት በድፍረት ዐይነ ልቡናቸው በመታወሩ
ምክንያት አትስረቅ የሚለውን ትእዛዝ አፍርሰው ይህን በደል ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
3 ፍቅረ ንዋይ (ገንዘብን መውደድ)፡ ይህ በአቋራጭ ለመክበር በአንዴ ባለጸጋ ለመሆን መመኘት፣ ያለኝ ይበቃኛል
አለማለትን ያመለክታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀመዝሙሩ ለሆነው ለቅዱስ ጢሞቴዎስ በላከው የመጀመርያ
መልእክቱ 1 ጢሞ 6፡8 ‹‹ምግባችንንና ልብሳችንን ካገኘን ይበቃናል›› በማለት አስተምሮናል፡፡ ታዲያ ይህንን ቃል
በመዘንጋት በስርቆትና በማጭበርበር በአንዴ ሀብትና ንብረት ማካበት የሚፈልጉ ሰዎች ጥቂት አይባሉም፡፡
በመሆኑም ፍቅረ ንዋይ ለመስረቅ ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ምክንያቶች አንዱ በመሆን ሊጠቅስ ይችላል፡፡
4 በሰይጣን ግፊት፡ የዲያቢሎስ ዋና ዓላማው የሰው ልጆች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወእርሱ ማድረግ
ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ሌቦች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወእርሱም›› 1ኛ ቆሮ 6፡10 በማለት ኢየሩሳሌም

31

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ሰማያዊትን ላለመውረስ ከሚያበቁን ምክንያቶች አንዱ ሌብነት እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ሰይጣንም ይህንን ስለሚያውቅ
ዓላማውን ለማሳካት አንድ ሰው ቢሰርቅ በቀላሉ ሀብታም፣ ደስተኛ፣ ከሁሉ በላይና ኑሮ የተደላደለ እንደሚሆን
በማመላከት ያስጎመጀዋል፣ ይፈታተነውማል፤ በዚህም ተነሳስቶ ሊሰርቅ ይችላል፡፡
5 በተንኮልና በምቀኝነት፡ ይህ የስርቆት ዓይነት አጥተው፣ ሰስተው፣… ወዘተ ሳይሆን የሚዘርፉትን ግለሰብና ቤተሰብ
ለመጉዳት፣ ለማናደድ ሆን ብለው የሚያሴሩት ሴራ ነው፤ የሚፈጽሙትም በተንኮልና በምቀኝነት በመነሳሳት ነው፡፡
6 በልማድ፡ ሕፃናት ያዩትንና የሰሙትን ነገር ለመቀበል አእምሯቸው ፈጣን እንደሆነና ነጭ ወረቀትን ይመስል
የሰጥዋቸውን እንደሚቀበሉ ይታወቃል፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የእጅ አመል ያለበት ሰው ካለና ስርቆትን በሕፃናቱ ፊት
የሚያዘወትር ከሆነ ስርቆትን እንደ ትምህርት ሊወስዱት ይችላሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር አንድ ሕፃን የሰውን ዕቃ
ሳያስፈቅድ በድብቅ ቢወስድና ባገኙት ጊዜ ካልቀጡት ያደረገው ነገር ትክክል እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ ይህን ችላ ማለት
ሕፃኑን ከልጅነቱ ጀምሮ የስርቆትን መጥፎ ገጽታ አለማሳየትና እንደ ጥሩ ልማድ እንዲቆጥረው ሊያደርገው ይችላል፡፡
ይህም እያደር አብሮት ያድግና ኋላ ለኑሮው የሚያስፈልገውን በቂ ንብረት ቢያፈራ እንኳን ሱስ ስለሚሆንበት ሊሰርቅ
ይገደዳል፡፡
7 በድኅነት፡ ከደረሰባቸው ችግር የረሀብ ጽናት፣ የስቃይና የእንግልት ኑሮ ለመላቀቅ ስርቆት አማራጭ መንገድ
መስሏቸው በተሳሳተ አስተሳሰብ ወደዚህ ሕይወት የሚገቡ ሰዎች አያሌ ናቸው፡፡
8 በስንፍና፡ አንዳንድ ሰዎች ስንፍና አብሯቸው ከማደጉ የተነሳ በራሳቸው ጥረት በገዛ ወዛቸው ንብረት ለማፍራት
በመስነፋቸው በሰው ላብ ለመኖር ዝርፊያን ያካሂዳሉ፡፡
ስርቆት የሚፈጸምባቸው መንገዶች
ስርቆት ሊፈጸምባቸው የሚችሉበት መንገዶች በርካታ ሲሆኑ ከተሰራቂው አካል ማንነት አንጻር በሁለት ዐበይት
ክፍል ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡
1 ሰውን መስረቅ፡ ከስሙ እንደምንረዳው ይህ የስርቆት ዓይነት የሚፈጸመው በሰው ላይ ነው፡፡ በተለያዩ መንገዶችም
ሊፈጸም ይችላል፤ ከዚህ በመቀጠል ከሰው ልንሰርቅባቸው ከምንችላቸው መንገዶች የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
ባለቤቱ ሳያውቅ (በስውር) በድብቅ በመውሰድ፡ ተሰራቂውም አካል ሆነ ሌላ ምስክር ሊሆን የሚችል አካል አየኝ
አላየኝ እየተባለ የሚፈጸም የስርቆት ዓይነት ነው፡፡
ጨለማን ተገን በማድረግ፡ ይህንን በሁለት ወገን ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ የመጀመርያው ወገን ጨለማን
ለብሰው፣ ጨለማን ተጎናጽፈው፣ አጥር ቅጥር አፍርሰው ሀብት ንብረትን የሚወስዱትን ሲወክል ሁለተኛው ደግሞ
በኃይል፣ በጉልበት፣ በመሣሪያ በማስፈራራት የሚነጥቁት የሰውንም ሕይወት እስከማጥፋት የሚደእርሱት ሽፍቶችን
ይይዛል፡፡
በማታለል (በማጭበርበር)፣ ስፍር በማጉደል፣ ሚዛን በማቃለል፡ ከሃይማኖታዊና ከሰብዓዊ የግብረ ገብ (የሥነ
ምግባር) ሕጎች ውጪ በሚዛንና በሥፍር፣ በልውውጥና በግብይት የሚፈጸመውን የተዛነፈ አሠራርና ስርቆትን
ይወክላል፡፡ የሌላውን ሕይወትና ኑሮ የሚጎዱ መጥፎ ነገሮችን መልካም አስመስሎ ቀይጦና የማይፈለጉ ዕቃዎችን
አመሳስሎ በመሸጥ በማይገባ ሁናቴ ለመክበር የሚደረገውን ከንቱ ጥረትና የተሳሳተ ቅድድምን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
የሠራተኞቸን ዋጋ ቀንሶ ማስቀረት፡ ይህንን ማድረግ ወይንም አሳንሶ መክፈል የሰውን የጉልበት ዋጋ መቀማት
እንደመሆኑ መጠን ከስርቆት ዓይነት ይመደባል፡፡
እጅ መንሻን መቀበል፡ ሥራውን በትክክል መፈጸም ሲገባው ግዴታውም ሲሆን ያን በማድረግ ፈንታ ከሰው
ጉቦን፣ መተያያን ገንዘብ ይቀበላልና ስርቆት ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ በመሆን ሊጠቀስ ይችላል፡፡
የሥራ ሰዓትን አለማክበር፡ በሥራ ሰዓት በአግባቡ ባለመገኘትና ያልሠሩበትንና ያልደከሙበትን ሰዓት አለአግባብ
ገንዘብ መቀበል ስርቆት ነው፡፡
የተበደሩትን አለመመለስ፣ በመያዣ የተቀበሉትን ሀብት ንብረት መካድ፡ ብድር (ውሶ) ስጦታ እንዳለመሆኑ
መጠን በተገቢው ጊዜ መመለስ ይገባናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሰው ብድር ተበድሮን በጊዜው ከመለሰልን በኋላ
በማስያዣነት የተቀበልነውን ንብረት አለመመለስ፣ መንጠቅና ማስቀረት ስርቆት ነው፡፡

32

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

አራጣ ማስከፈል፡ አራጣ ማስከፈል ተገቢ አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያስረዳናል፣ ያዘናልም ‹‹›ከአንተ
ጋር ለተቀመጠው ለድሃው ወገንህ ብር ብታበድረው አታስጨንቀው፣ አራጣም አታስከፍለው› ዘጸ 22፡25 ‹‹ወንድምህ
ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፣ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ
እግዚአብሔር ነኝና›› ዘሌ 25፡36 በማለት አራጣ ከእኛ ያልሆነውን ያልሰጠነውን ትርፍ ነገር መሆኑን በመናገር አራጣ
ማስከፈል የሰውን ንብረት መሻት በአጠቃላይ ሌብነት መሆኑን ይገልጻል፡፡
የሌላውን አሳብ እንደራስ አድርጎ ማቅረብ፡ አድናቆትንና ተወዳጅነትን ለማትረፍ ከመሻት የሚመጣ ሲሆን ከራስ
ያልሆነውን የሰውን አሳብና የፈጠራ ሥራ ሰርቆ የራስ አስመስሎ ማቅረብ ትልቅ ስርቆት ነው፡፡
በእግዚብሔር ስምና ቃል እየሰበኩ የምዕመናን ንብረት ለግል ጥቅም ማዋል፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ ለሚገኙት
ምዕመናን በላከው መልእክቱ ‹‹እንግዲህ ሌላውን የምታስተምር ራስህን እንዴት አታስተምርም ? አትስረቁ ትላለህ፣
ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰርቃለህ ›› ሮሜ 2፡21 በማለት መምህራኑን ሲገስጻቸው እንመለከታለን፡፡ ይህንን ማድረግ
የጻፎችና የፈሪሳውያን ግብር (ሥራ) ነው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ‹‹የመበለቶችን ገንዘብ የሚበሉ፣
ለምክንያት ጸሎትንም የሚያስረዝሙ እነዚህ ታላቅ ፍርድን ይቀበላሉ›› በማለት እንደገለጸልን ጸሐፍት ፈሪሳውያንም
በጸሎት ርዝመት እያመካኙ የመበለቶችን ቤት ይበዘብዙ እንደነበር ተተርኳል፡፡ ይህ ስርቆት ሊፈጸምባቸው
ከሚችሉት መንገዶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይሁዳም ከጌታችን ጋርና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር እየኖረ ክርስቲያን
በመምሰል ሙዳየ ምጽዋት ውስጥ ይገባ የነበረውን ገንዘብ ይሰርቅ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በዚህም
ምክንያት በእግዚአብሔር ስም የምዕመናንን ንብረት ለሚዘርፉ ሁሉ አብነት ይሆናል፡፡
2 እግዚብሔርን መስረቅ፡ ሰው እግዚአብሔርን በተለያዩ መንገዶች ሊሰርቅ ብችልም ከዚህ በታች የተወሰኑትን
በመመልከት እንሞክራለን፡፡
በቤተክርስቲያን የሚገኙ ለአምልኮ የምንጠቀምባቸውን ንዋያተ ቅድሳት መስረቅ፡ እነዚህ ዕቃዎች ለእግዚአብሔር
አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የተለዩና የተቀደሱ በመሆናቸው እነዚህን ዘርፎ ለግል ጥቅም ማዋል ትልቅ ኃጢአትና
ድፍረት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ንጉሥ ብልጣሶር የደረሰበትን ቅስፈት እስከመቀበል የሚያደርስ ቅጣት ሊያስቀጣ
ይችላል፡፡ ይህ እግዚአብሔርን ከምንሰርቅበት መንገዶች አንዱና ዋናው ነው፡፡
ለእርሱ የሚገባውን ጊዜና ቦታ አለመስጠት፡ ጊዜን ለእግዚአብሔር መስጠት መገዛታችንን የምንገልጽበት አንድ
መንገድ ሆና ሳለ ጊዜያችንን ለሥጋ ፈቃድ ብቻ በማዋል በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር አለመገናኘት፣ በጉባኤ ላይ
አለመገኘት ተገኝቶም ትኩረትን ሰጥቶ አለማዳመጥ እግዚአብሔርን መስረቅ ነው፡፡
ዐሥራት በኩራትን አለማውጣት፡ ለእግዚአብሔር ሊሰጥ የሚገባውን ከዐሥር አንድ እጅ፣ ቀዳሚያቱንና የበኩር
የሆነውን ማስቀረት ስርቆት ነው፡፡
ዐሥራት፡ አንድ ሰው ከሚያገኘው ከተጣራ ገንዘብ ላይ ዘጠኝ እጁን ለራሱ በመውሰድ አንድ እጁን ለእግዚአብሔር
መስጠር ዐሥራት ማውጣት ይባላል፡፡ እዚህ ላይ ግን እያንዳንዳችን ልናውቅ የሚገባን ነገር ቢኖር የምጽዋትና
የዐሥራት በኩራት ልዩነት ነው፡፡ ምጽዋት ‹‹ከፈቃድ ገንዘቤ እሰዋልሃለሁ›› መዝ 53፡8 እንደተባለው ዐሥራት
በኩራት ቀዳሚያት ወጥቶለት ከቀረው ገንዘብ በፈቃድ በመምህረ ንስሐ አማካይነት ወይም በስውር ለድሆች የሚሰጥ
ገንዘብ ነው፡፡ በወንጌልም ጌታችን ‹‹የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር›› ብሎ እንደተናገረው ዐሥራትን
ለነዳያን መመጽወት አይገባም፡፡ ዐሥራት አለማውጣትም እግዚአብሔርን መስረቅ ነው፤ በእግዚአብሔር ገንዘብ ላይ
የሚያዝ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ዐሥራትን ሰርቆ ለድሆች መመጽወት የተከለከለ ነው፡፡ ዐሥራት
የሚሰጠው ለምንጠቀምበት፣ ለምንገለገልበት፣ ንስሐ አባታችን ላሉበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ነው፡፡
ስዕለት አለመፈጸም፡ አንድ ሰው ስዕለት ተስሎ ቃል የገባውን ነገር ካስቀረ
እግዚአብሔርን ለማታለል በመሞከሩ ሌባ ያሰኘዋል፤ ይህም ስርቆት ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡
የስርቆት አስከፊነት
ስርቆት በሥጋችንም ሆነ በነፍሳችን ልዩ ልዩ መከራንና ቅጣትን ስለሚያስከትልብን እጅግ ትልቅና አስከፊ የሆነ
ኃጢአት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ ከዚህ በመቀጠል በመስረቃችን ሊያገኙን የሚችሉትን ቅጣቶች በሁለት ከፍለን
እንመለከታቸዋለን፡፡
1 የሥጋ (የምድር ቅጣት)

33

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ሀ በሕገ መንግሥቱ፡ አንድ ሀገር የምትመራበት ሕገ መንግሥት ስርቆት ወንጀል እንደሆነና ቅጣት እንደሚያስከትል
እንደሚያውጅ እሙን ነው፤ በመሆኑም ሌቦች ተይዘው ራሳቸውን ለእስር ቤተሰባቸውን ለሰቀቀን ይጋልጣሉ፡፡
በዚህም በሥጋቸው ላይ ብዙ መከራን ይቀበላሉ፡፡
በዘመነ ኦሪት በነበረው ሕግም ‹‹የእሥራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ሀገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ
አካን፣ እርሱም የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ … እሥራኤልም ሁሉ በድንጋይ
ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት… በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ›› ኢያ 7፡1-28 በማለት
ስርቆትን የፈጸመ ሰው በሥጋው ታላቅ መከራ እንደሚደርስበት መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል፡፡
ለ በሰዎች መገለል፡ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ምግባር በመሆኑ ስማችን በአካባቢው መጥፎ ገጽታ
ስለሚኖር ከሕብረተሰብ ጋር ተስማምተን መኖር ካለመቻላችን የተነሳ በሰቀቀን፣ ጭንቀት እንሰቃያለን፡፡
2 ሰማያዊ (የነፍስ) ቅጣት፡ ሌቦች መንግሥተ እግዚአብሔርን አይወእርሱም ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈ
ስርቆት ትሉ ከማያንቀላፋት፣ ጨለማው ከሚዳሰስበት እሳቱ ከማይጠፋበት የሲዖል አዘቅት ውስጥ ይጨምረናል፡፡
ከዚህ ሁሉ ለመዳን መፍትሔው ምንድን ነው?
 ስላጠፋነው /ስለሰረቅነው/ ፈንታ መክፈል፡ በሉቃስ ወንጌል ታሪኩ ተመዝግቦ የሚገኘው ዘኬዎስ ለጌታችን
በደሉን ሲናዘዝ ‹‹… ጌታዬ ሆይ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፈንታ
አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ…›› ሉቃ 19፡8 በማለት ስላጠፉት ፈንታ ካሳ መመለስ ተገቢ እንደሆነ አስተምሮናል፡፡
 ከአቅም በላይ አለማሰብ (እምነት አለማጣት)፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንዳስተማረን ስለ ነገ
ከአቅም በላይ መጨነቅ እንደሌለብን፣ ብንጨነቅም ምንም መፍትሔ የሚሆን ነገር እንደማናመጣና የሰማይ ወፎችን
ሳይደክሙ የሚመግብ አምላክ በአርአያና በአምሳሉ የፈጠረውንና ከፍጥረቱ ሁሉ አልቆ የሚወደውን የሰው ልጅ
ከእርሱ በላይ እንደሚያስብለት በመግቦቱና በጠብቆቱ ከእርሱ እንደማይለይ ገልጾልናል፡፡ በመሆኑም ሰው ሁሉ
እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ ጥሎ ወደዚህ የኃጢአት ግብር /ሥራ/ እንዳይገባ ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
 በሰዎች ልቡና ውስጥ የታማኝነት ፍቅር መትከል፡ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን መፍራት ሰውንም ማፈር
እንደሚገባው ቅድስት ቤተክርስቲያን ታስተምራለች፡፡ በመሆኑም ሌብነት በሕብረተሰቡ ዘንድ የተጠላ ተግባር
መሆኑን በመረዳትና ሰውን በማፈር ‹‹መልካም ስም ከመልካም ሽቱ›› ይበልጣል እንደሚባለው በታማኝነት
ተቀባይነት ያለውን ሥራ መሥራት ይገባናል፡፡ በዚህም ምግባራችን በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ መልካም ስም
እናተርፋለን፡፡
 ከሕጋዊ ውጪ የሚመጣን ገንዘብ ለራስ አለማድረግ፡ ይህንን በማድረጋችን ብዙ በረከት እናገኛለን ከብዙ
ውድመትም እንጠበቃለን፡፡ ምክንያቱም ሕጋዊ ከሆነ አሠራር ውጪ የሚመጣ ገንዘብ በሕጋዊ ያገኘነውን ሀብት
ንብረት በሙሉ ይዞ በመጥፋት በረከታችንን ያሳጠናል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ድርጊት ራስን መጠበቅ ይገባል፡፡
 ዳግም አለመስረቅ፡ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት በዚህ የኃጢአት ግብር ውስጥ የምንኖር ቢሆንም በንስሐ
ከተመለስን በኋላ ዳግም ወደ መጥፎ ሥራችን መመለስ የለብንም፡፡ ምክንያቱም ንስሐ ማለት ኃጢአትን መጥላት
ስለሆነ የቀደመ በደላችንን ፈጽመን ልናስወግደው ይገባናል፡፡
 የግል ድርሻን ማፍራት፡ ሰው የግል ድርሻ ከሌለው ሕይወቱ ለስርቆት ይጋበዛል፡፡ የግል ድርሻ ባይኖር ኖሮ ዓለም
ውጥንቅጡ የጠፋ ሕይወት በኖረው ነበር፡፡ ምክንያቱም ራሱን የሚያስተዳድርበት ንብረት በማጣት ያልሆነ ሕይወት
ውስጥ እንዲገባ ይገደዳል፡፡ ስለዚህ ሰው የራሱ ንብረት ሊኖረው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ 7ኛው ትእዛዝ የሚያስተምረን አንድ ሰው የራሱ ሀብት ያልሆነውን መውሰድ መቀማት በሆነም ባልሆነም
መንገድ መንጠቅ ተገቢ አለመሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሠርቶ ወጥቶና ወርዶ በአገኘው እውነተኛ ገንዘቡ መኖር
መተዳደር ይገባዋል፡፡ አትስረቅ የሚለው ቃል ሰዎች እንዳይሰርቁ ብቻ ሳይሆን የሚሰርቁም ስርቆታቸውን አቁመው
እንዲመለሱ ይጋብዛል፡፡ ‹‹የሰረቁ አይስረቁ›› ተብሎ እንደተጻፈው ኤፌ 4፡28 በክርስቶስ ስም የተጠራ ክርስቲያን
ሀብቱን ንብረቱን ለሌላው ይሰጣል፣ ያካፍላል፣ በሕይወቱም እንኳን ተላልፎ እስከ መሞት ሌሎችን ይረዳል፣
ይታደጋል እንጂ አይሰርቅም፣ አይቀማም የማይገባውንም አያደርግም፡፡ በመሆኑም ክርስቲያኖች ‹‹እኔ ቅዱስ ነኛና
እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› ብሎ ባዘዘን አምላካዊ ቃል መሠረት ከርኩሰት ሥራ ርቀን ሰውነታችንን ልንቀድስ
ያስፈልጋል፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ትእዛዛቱን ፈጽመን የሕይወትን ቃል እንድንሰማ ያብቃን፡፡ አሜን!
34

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

2.8 ትእዛዝ 8
‹‹በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር››
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ፡
በሕብረተሰቡ ውስጥ እውነትና ሐቅ ጠፍቶ፣ ፍርድ ጎድሎ፣ ድሀ ተበድሎ ሰዎች ሁሉ ጊዜያቸውን ፣ ኃይላቸውን
እንዲሁም ገንዘባቸውን በክርክርና በጠብ እንዳያጠፉ፣ ሰላማቸውን እንዳያጡ፣ በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል
ሰዎች በሐሰት በመመስከር ንጹሕ ደምን አሳልፎ በመስጠት እንዳይጎዱ ለመርዳትና ለመጠበቅ
ስለ ሰው ልጆች ስም፣ ክብር፣ ሕይወትና መብት መጠበቅ ይህ ሕግ ተሰጠ፡፡
ከላይ ከርዕሱ እንደምንመለከተው ስምንተኛው ትእዛዝ የሚነግረን በባልንፈራችን ላይ በሐሰት እንዳይመሰክር ነው፡፡
ከሁሉ በፊት ግን ባልንጀራ፣ ሐሰት፣ ምስክርነት የሚሉትን አሳቦች ለየብቻ መመልከት ያስፈልጋል፡፡
ባልንጀራ ማለት ትርጉሙ
ባልንጀራ፡ ባልንጀራ ማለት ዘር፣ ጎሳ ሳይለይ በአርአያና በአምሳለ ሥላሴ የተፈጠረውን የሰውን ልጅ ሁሉ
ያመለክታል፡፡
ሐሰት፡ ሐሰት ከነባራዊው እውነታ የወጣ፣ ወይም ልብ ያወቀውን አእምሮ ያወጣ ያወረደውን እውነት ለውጦ መናገር
በተግባር መለወጥ ማለት ነው፡፡
ምስክር ማለት ትርጉሙ
ምስክርነት፡ ምስክርነት ማለት ስለ ሥነ ሥርዓትና ስለ እውነት ጉዳይ በተሰየመ ጉባኤ ፊት የቀረበውን ሙግትና
ክርክር አዳምጦ በትክክል ለመፍረድና ለመወሰን የሚረዳ የቃል ማረጋገጫና ሌሎች መረጃዎችን የሚያመለክት ነው፡፡
ሦስቱን ቃላቶች በዚህ መልኩ ከተረዳናቸው በሐሰት መመስከር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት አያዳግተንም፡
፡ ያላዩትንና ያልሰሙትን ጨርሶ የማያውቁትንና ያላጣሩትን ነገር በትክክል እንደሚያውቁት አድርጎ በማቅረብ
ለፈራጅ የተሳሳተ መረጃ መስጠት በሐሰት መመስከር ይሰኛል፡፡ ሐሰተኞች ነቢያትም በሐሰት ከሚመሰክሩ ኃጥኦች
ወገን ናቸው፡፡
የምስክር ዓይነት
የሐሰት ምስክርነት የሚሰጥባቸው መንገዶች
1 በምላስ፡ ይህ የሚፈጸመው ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ በአካል ሳይገኙም ሆነ ተገኝተው የነበረውን እውነታ
በመለወጥ የሐሰት ማስረጃን በማቀበል ነው፡፡
2 በጽሑፍ፡ የሐሰት መረጃዎችን ሰነዶችንና መዝገቦችን በማጭበርበርና በማዘዋወር እውነት አስመስሎ በማቅረብ
ይፈጸማል፡፡ ለምሳሌ፡ በአንድ የሥራ መስክ በቂ ችሎታና ዕውቀት ሳይኖረው እንደ ዐዋቂና ብቁ ባለሙያ አስመስሎ
መረጃ በሐሰት በማሠራት ሥራ እንዲያገኝ መጣር
3 በፊርማ፡ አስመስሎ በመፈረምና በተሰረቁ ማኅተሞች በመጠቀም ሐሰተኛ የሆነ ነገርን የያዘውን ወረቀት ማጽደቅ
4 በዝምታ፡ ፍርድ እንዳይዛባ ጠቃሚና ትክክለኛ መረጃ ይዘን ሳለ ባለመመስከራችን መሰጠት የሚገባውን ፍርድ
እናዘንፋለንና ዝምታችንም ምንም እንደማናውቅ ይገልጣል፤ በዚህ መልኩ የሐሰት ምስክርነት ሊፈጸም ይችላል፡፡
ሰዎች እንዴት በሐሰት ይመሰክራሉ

35

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

1 በልማድ፡ አንድ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ ከሠራው ጥፋትና በዚያም ከሚደርስበት ጥፋት ለማምለጥ በሚዋሽ ጊዜ
አብሮት ያድግና ሐሰት መናገር ሱስ ይሆንበታል፡፡ በመሆኑም ራሱንም ሆነ ባልንጀራውን ከሚደርስባቸው ቅጣት
ለመታደግ መዋሸት ለእርሱ ቀላል ይሆንለታል፡፡
2 በዘረኝነት፡ የኔ የሆነውን ሰው እውነት ተናግሬ ከምጎዳ በሐሰት ብመሰክር ይሻላል በማለት ስምንተኛውን ሕግ
ሰዎች በብዛት ይጥላሉ፡፡
3 በምቀኝነት፡ በሐሰት የሚመሰክሩበትን ሰው ሆነ ብሎ ለመጉዳት የራሳቸውን ሐሳብ ጨምረውበት፤ መደምደሚያ
አበጅተውለት የራሳቸውን ፍላጎት እንዲያስተላልፍ አድርገው በማመቻቸት ንጽሕ ሰውን ይጎዳሉ፡፡
4 በጥቅም፡ ራስንና ባልንጀራን አላግባብ ለመጥቀም እንዲሁም በሐሰት ከሚመሰከርለት ሰው ገንዘብ ለማግኘት ሰው
በሐሰት ይመሰክራል፡፡
5 በይሉኝታ፡ አጥፊው ግለሰብ ከዚህ በፊት ያደረገለትን ውለታ በማሰብ በእርሱ ላይ እውነቱን ተናግሮ ከማስፈረድ
በሐሰት በነጻ እንዲሰናበት ማድረግ ይሻላል፣ ምንስ ይለኛል? በማለት ሐሰቱን መናገር
6 ምሥጋናን (ውዳሴ ከንቱን) በመፈለግ፡ ወዳጅን ለማጎላመስ ሌላውን ለማኮሰስ በወዳጁም የማይገባውን ምሥጋና
ለመመስገን በመሻት የሚፈጸም የሐሰት ምስክርነት ነው፡፡
7 ከፍርሀት የተነሳ፡ አንዳንድ ሰዎች ስለ አንድ ነገር የሚጠይቃቸው ሰው ከሚያደርስባቸው ጫና የተነሳ ሊዋሹ
ይችላሉ፡፡
የሐሰት ምስክርነት አስከፊነት?
1 ሰው በሐሰት በመመስከሩ ራሱን ይጎዳል፡ በኦሪት ዘዳግም ‹‹በዐመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር
ቢቆም፤ ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ ፈራጆችም
አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፣ በወንድሙ ላይ
ክፋትን ያደርግ ዘንድ እንደወደደ በእርሱ ላይ ታደርጉበታላችሁ፤ እንዲሁም ከእናንተ መካከል ክፉውን
ታስወግዳላችሁ ›› ዘዳ 19፡16-20 በማለት የሐሰት ምስክር የሚደርስበትን ቅጣት ተናግሯል፡፡
በሌላም መልኩ ለውሸታም ሰው ክብር ስለሌለ በየጊዜው በሚናገረው ውሸት ሲቀል ይኖራል ‹‹ውሸታም ሰውና ስንቅ
እያደር ይቀላል›› እንደሚባል እንዲሁም ዕድሜም ብዙ አይኖረውም በሐሰቱ ብዙ አደጋ ሊያገኘው ይችላልና፡፡
ይህንም ስለመሰለው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የሚከተለውን ምክር ይሰጠናል ‹‹ተጽፏልና ሕይወትን ይወድ ዘንድ
መልካምንም ዘመን ያይ ዘንድ የሚሻ ምላሱን ከክፉ ይከልክል፣ ከንፈሮቹም ሽንገላን እንዳይናገሩ›› በማለት ብዙ
ዕድሜ ለመኖር ውሸት እንደማይበጅ አስጠንቅቋል፡፡
2 በሐሰት የተመሰከረበትን ሰው ይጎዳል፡ የሐሰት ንግግር ሰውን ከሞት፣ ንብረትን ከመበዝበዝ ከመባከን ያደርሳል፡፡
በዚህን ጊዜ የሀብቱ ባለቤት በችግር ወይም በብስጭት ምክንያት ካልሆነ በሽታ ወድቆ ሕይወቱ ሊጠፋ ይችላል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስም በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ላይ ታሪኩ ተጽፎ እንደምናነበው ‹‹ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን
ሰድቧል›› በማለት ያልሰሙትን መስክረው በሐሰት በግፍ በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል ሆኗል፡፡ ከዚህም
እንደምንረዳው በሐሰት የምንመሰክርበትን ሰው ምን ያህል እንደምንጎዳው ነው፡፡ (1ኛ ነገ 20፡1-26)
3 የሚመሰክሩለትን ሰው ይጎዳል፡ ከላይ በተገለጸው ታሪክ ውስጥ ንግሥት ኤልዛቤል ናቡቴ ላይ በፈጸመችው በደል
ፍርዱን የማያስቀረው አምላክ እርሷንም ከፎቅ ቤት ላይ ሰዎች ገፍትረው እንዲትሏትና ተፈጥፍጣ እንድትሞት
አድርጓል፡፡ ነቢዩ ኤልያስም እንደተነበየው ሥጋዋን ውሾች በልተውታል (1ኛ ነገ 20፡22-23) ፡፡ እርሷን
እንጠቅማለነው ብለው በሐሰት የመሰከሩላት በተዘዋዋሪ ጎድተዋታል፡፡ ዛሬም ቢሆን የንጽሑን የናቡቴን ደም
የተበቀለ አምላክ ሁልጊዜ ይፈርዳል፡፡

36

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

4 የሚመሰከርበትን ሰው ቤተሰብ ይጎዳል፡ ሰውን በሐሰት ከመወንጀል የተነሳ የግለሰቡ ቤት ሊፈታ፣ ቤተሰቡም
ሊበተን ይችላል፡፡ በዚህም ልጆችን ከጎዳና በማስወጣት ማለቂያ የሌለው ግፍ ሲፈጽም ይኖራል፡፡
በቅዱሳን ላይ በሐሰት መመስከር

የመዋሸት ምክንያትና መንስኤው


አንዳንድ ሰዎች መዋሸት ከፈጸሙት ጥፋት የሚያድናቸው እየመሰላቸው የሠሩትን ኃጢአት ለመደበቅ ይዋሻሉ፡፡
ይሁን እንጂ የሐሰት መንገድ አጭር እና የትም የማያደርስ ብዙ ጊዜም መገለጡም የማይቀር መሆኑን ሰዎች ከሐሰት
ይልቅ የሚያድናቸውን እውነተኛና ተገቢ መንገድ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ከመበሳጨት ወይም ከመፍራት ወይም ስለአንድ ነገር የሚጠይቃቸው ሰው ከሚያሳድርባቸው
ጫና የተነሳ ሊዋሹ ይችላሉ፡፡ከመዋሸት ይልቅ በእንደዚህ ያለ ጊዜ ዝምታ መልካም መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡
ዋሽቶ ማስታረቅ ይቻላል
ዋሽቶ ማስታረቅ እንዲሁ ከላይ ከላይ ስናየው ጥሩ ነገር ቢመስልም ነገር ግን ኋላ ኋላ ብዙ መዘዝ ሊያስከትል
የሚችል ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው ሰውን ይቅር ሊለው የሚገባው ከልቡ አምኖበት የሠራውን በደል ይቅር ማለት
እፈልጋለሁ ሲል ሲሆን ዋሽቶ ማስታረቅ ግን አጥፊው የሠራውን ሥራ አልሠራም በማለት የሚደረግ ሲሆን በተበዳዩ
ላይ ድጋሚ ሌላ በደል መጨመር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተበዳዩ ይህንን ሥራ ባወቀ ሰዓት ከአጥፊውም
ከአስታራቂውም ጋር ይጣላልና፡፡
የሐሰት ምስክሮች የሚደርስባቸው ቅጣት
ይህንን ትእዛዝ ባለመፈጸም ከእውነት ይልቅ ሐሰትን የሚወዱ በክፉ ሥራዎቻቸውም የሚጸኑ ግን መጨረሻቸው
ከሐዲዎችና ከነፍስ ገዳዮች ጋር በእሳት መቃጠል እንደሆነ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
‹‹የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍስ ገዳዮችም የሴሰኞችም የነፍስ ገዳዮችም ጣዖትን የሚያመልኩ የሐሰተኞች
ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው›› ራእ 21፡8፣ ኤፌ 4፡25፣ ቆላ 3፡9 በምድርም
ሐሰታቸው እስከታወቀ ድረስ በእሥራትና በእንግልት ሥጋቸውን ያሰቃያሉ፡፡
ሳያጣሩ መፍረድስ ተገቢ ነውን?
የአንድ ሰው ማንነቱ ሳይታወቅ ማስረጃ ሳይኖር እንደዚሁ በግምታዊነት በሰውየው ላይ ውሳኔ ማስተላለፍ ባላወቁት
ነገር ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም፡፡ ይህን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ኃጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ የሚፈርድ፣
ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፡፡›› ምሳ 17፡15 የሚል ተጽፎ እናገኛለን፡፡ በመሆኑም ሳናጣራ
በመፍረዳችን ‹‹አትፍረዱ ይፈረድባችኋል›› ማቴ 7፡1-5 እንደተባለ ከእግዚአብሔር ፍርድ አናመልጥም፡፡ በመሆኑም
በባልንጀራችን ላይ የምንሰጠው አስተያየት በማስረጃ የተደገፈ በማስተዋል የተመጠነ መሆን ይኖርበታል፡፡
በሐሰት በመመስከር ከሚደርስበን ቅጣት ለመዳን ምን ማድረግ ይጠበቅብናል
በሐሰት የምንመሰክረውም ሆንን የምንመሰክርለትን ግለሰብ የማንጠቅም መሆኑን ተረድተን በንግግራችን መካከል
እውነተኛ ሆኖ በመገኘት፣ በሥራችን ሰዎችን ለማሳመን በመጣር፣ በሐሰት ካልመሰከርን ጉዳት የሚደርስብን ቢሆን
እንኳን እውነቱንም ሐሰቱንም አለመናገር ይበጃልና በዝምታ፣ የንግግር አቅጣጫ በመቀየርም ቢሆን መልስ
ላለመስጠትም ይቅርታ በመጠየቅም ቢሆን በተቻለ መጠን ራሳችንን ከሐሰት መስካሪነት መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
በንግግራችን እውነተኛ ሆኖ መገኘት ስላለብን ምስጢር ሁሉ ይፋ ይውጣ ማለታችን አይደለም፡፡ ለምሳሌ፡
የቤተክርስቲያን ምስጢራት ለሰው የማይነገሩ እንደ ኑዛዜ ያሉ፣ የሀገር ምስጢራትና ይህንን የመሳሰሉት በስውር
37

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የሚያዙ የሚጠበቁ ምስጢሮች በመኖራቸው አላውቅም አልሰማሁም በማለት ልናሳልፍ ይገባናል፡፡ ይህን
በማድረጋችን ሐሰት እንደተናገርን አይቆጠርብንም እንዲያውም ምስጢር በመጠበቃችን ምክንያት ዋጋ የሚገባን
ይሆናል እንጂ፡፡ እነዚህን አሳልፎ መስጠት ግን በቤተክርስቲያንም በመንግሥትም ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡
የሐሰት መገኛዋ የሰው ሁሉ ጠላት ዲያቢሎስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ያልሆነ ሁሉ የሰይጣንን ሥራ ይሠራል፤
የሰይጣንን ሥራ የሚሠራም የሰይጣን (የዲያቢሎስ) የግብር ልጁ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር የሚገኘውን ትምህርት
ያልተማሩ የእውነት ተቃራኒ በሆነ መንገድ ለሞት ለመከራ አሳልፈው ለመስጠት የንጹሕ ሰውን ሕይወት የሚፈልጉ
ሁሉ ሐሰትን ከራሱ አንቅቶ የሚናገር የሐሰት አባቷ ፈጣሪዋ የሆነ የሰይጣን ልጆች ናቸው፡፡ ይህንንም በዮሐንስ
ወንጌል ዮሐ 8፡41-45 ድረስ ራሱ ገልጦ ተናግሮታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ የሐንስ እንዳስተማረው የእግዚአብሔርና
የሰይጣን ልጆች የሚለዩት በግብራቸው (በሥራቸው) ነው፡፡ ‹‹ከእግዚአብሔር የተወለደ፣ ከእግዚአብሔር የተማረ፣
ኃጢአትን አይሠራም፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነውና፤ በእርሱ አምኖ ጸንቶ ይኖራልና፣ መበደል አይቻለውም፣…በዚህም
የእግዚአብሔርና የጋኔን ልጆች የተለዩ ናቸው፡፡›› 1ኛ ዮሐ 3፡8-10 እንዲል፡፡ በሐዋርያው መልእክት አገላለጥ ከአባት
ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ውርስ ከሰይጣን የሚወረስ ክፉ ሥራ የሐሰት ምስክር መሆን ነው፡፡
ሐሰት ማለቂያ የሌለው ኃጢአት ነው፡፡ ሐሰት ተናጋሪው በሐሰት ደግሞ ይምላል፤ በዚህን ጊዜ የአምላኩን
የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ይጠራል እንዲሁም በሐሰት መስክሮና ምሎ ግለሰቡን እንዲገደል እንዲታሠር ሀብት
ንብረቱ እንዲዘረፍ በማድረጉ አትግደል የሚለውን ትእዛዝም ያፈርሳል፤ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥልና ሌሎችንም
ሕግጋት ሁሉ ወደ መሻር ያደርሳል፡፡
ዕለታዊ ጥቅምን በመፈለግ ማንም በሐሰት እንዳይመሰክር እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት እንድንል በሐሰት
አትመስክር በማለት አምላካዊ ሕግ ያዛል፡፡ ሌላው ይቅርና ሰማሁ በማለት እንኳን መመስከር ትክክል ሊሆን
አይችልም፡፡ ሐሰትን የሚመሰክሩ ሰዎች ከእምነት ከአውነትና ከቁም ነገር የተራቆቱ ናቸው፡፡
ክርስቲያን እውነትን መመስከር አለበት እንጂ የሐሰት ባሪያ መሆን የለበትም፡፡ የሐሰት መንገድ አጭርና የትም
የማያደርስ መሆኑን ተገንዝበን መገለጡም የማይቀር በመሆኑ የሚያድነንን የእውነት መንገድ መጠቀም ይኖርብናል፡፡
ሐሰት በተገለጠ ጊዜ የሚያሳፍርና ማኅበራዊ ከበሬታውና መንፈሳዊ ተአማኒነትን የሚያሳጣ በመሆኑ ከምንም በላይ
ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ለሁሉም የሚበጀው ልቡናን ከክፋት አእምሮን ከሐሰት አፅድቶ ነጻ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር
መኖር ነው፡፡ አምላካችን ይህንን ትእዛዝ ፈጽመን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን ይፍቀድልን፡፡
2.9 ትእዛዝ ዘጠኝ

የባልንጀራህን ቤት አትመኝ

የሰው ልጅ ንጽሕና በውጪ ብቻ ሳይሆን በውስጥም መሆን አለበት፡፡ አትመኝ ሲባል መመኘት ብቻ ሳይሆን
አታስበው አትፈልገው ሲል ነው፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ሕወት ከልቡ በመነጨ ግዴታ ብቻ ሳይሆን
ከኅሊና ከመነጨ ፍቃድ እንዲጠብቁለት ይፈልጋል፡፡ ሰው ሕግን እንዲፈራ ብቻ ሳይሆን እንዲያመዛዝን
እንዲያገናዝበውም ጭምር ነው፡፡ ‹‹ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች›› ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች››

የባልንጀራህን ቤት

የባልንጀራህን ቤት ሲባል ቤቱን ብቻ ሳይሆን በቤቱ ውስጥ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ይህንንም
በሶስት ክፍል ማየት ይቻላል ዘፀ 20÷17
1. የባልንጀራ ሚስት
2. ሌላውን ገረዱን(አገልጋዩንም)
3. አህያውን፣ በሬውን (እንስሳቱንም) እነዚህን መመኘት እንደማይገባ ይህ ትእዛዝ ያስገነዝበናል፡፡ምኞት ከፍ ባለ
ስሜት አንድን ነገር መሻትና መፈለግ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለማየት ቢመኝ የቃሉን ወተት
ሲመኝ ሰላም ፍቅርን ሕብረትን ሊመኝ ተገቢ ነው፡፡

38

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ምኞት ምንድን ነው
ምኞት፡- የሰው ልጅ በዓይናቸው ያዩትን በእጃቸው የዳሰሱትን በጆሮአቸው የሰሙትን ልባቸው የወደደውን
የፈቀደውን ለማግኘት በህሊናቸው ሰሌዳ ላይ የሚቀረፅ መሻት (ፍላጎት) ነው፡፡
ይህ ፍላጎት በ3 ይከፈላል
1. መንፈሳዊ ምኞት
2. ሥጋዊ ምኞት
3. ሰይጣናዊ ምኞት
መንፈሳዊ ምኞት፡- ቀደምት ቅዱሳን አበው የተጋደሉትን መንፈሳዊ ተጋድሎ ከገድላቸው ተረድቶ የእነርሱን አሰረ
ፍኖት በመከተልና እነርሱ ያገኙትን ጸጋ ለማግኘት (እንደእነርሱ ለመሆን) በልብ ጽላት ላይ ተቀርጾ መከራውን
ፈተናውን ሁሉ በትዕግስት እንዲቀበሉ የሚገፋፋ ኃይል መንፈሳዊ ምኞት ይባላል፡፡
ሥጋዊ ምኞት፡- የዐይን አምሮተ የሥጋ ፍላጎትን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ጉዳትም ጥቅምም አለው፡፡ለምሰሌ ጥቅም
ሌሎች የደረሱበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ዶክተር የሆኑትን አይቶ ዶክተር ለመሆን፣ፕሮፌሰር የሆኑትን አይቶ ፕሮፌሰር
ለመሆን፣ኢንጂነር የሆኑትን ኤቶ ኢንጂነር……………… አስቀድሞ ውስጣዊ መሻት በልቡና መቅረፅ አለበት፡፡ይህም
ተማሪውን ተክቶ እንዲያጠና ሰራተኛው ጠንክሮ እንዲሰራ ይገፋፋዋል ለሥጋዊ ሕይወት ይህ አይነት ምኞት
ያስፈልገዋል በክርስትና ትምህርትም ይሕ አይወገዝም፡፡
ሰይጣናዊ ምኞት፡- የበጎ ነገር ሁሉ ተጻራሪ ርኩስ መንፈስ በረቂቅ መንገድ በህሊናችን የሚያሳድረው መጥፎ ምኞት
ሰይጣናዊ ምኞት ይባላል፡፡
ሰው ከምኞት ጋራ በተፋጠጠ ጊዜ ከምኞት ከመታል ይልቅ የሚበጀው ከመመኘት መሸሽ ነው ምክንቱም ምኞትን
ከማሸነፍ አስቀድሞ ሊሸነፍና ልቡናውም በምኞት ጦር ተወግቶ በምኞት መርዝ የተነደፈ ሊሆን ይችላልና ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ ‹‹ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሹ፡፡›› 2ኛ ጢሞ 2÷22
ለምኞት የሚዳርጉ ምክንያቶች
ሀ ያለኝ ይበቃኛል አለማለት፡ ሰው ውስጣዊ ፍላጎቱን ‹‹ያለኝ ይበቃኛል›› በሚል መንፈሳዊ መርህ ካልለጎመው
በስተቀር የሰው ፍላጎት ሁሉ የሚያየውን ሁሉ እንዲመኝ ያደርገዋል፡፡ስለዚሀ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ያለኝ
ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁ›› እንድንል እምነታችን ያዘናል፡፡
ለ ስንፍና፡ ሰው ሆይ ለፍትህ ጥረህ ግረህ በላብህ ወዝ ብላ ለሚለው አምላካዊ ትእዛዝ ጀርባቸውን የሰጡ ሰነፎች
ሌላው ወጥቶ ወርዶ ያፈራውን ንብረት እያዩ ‹‹ምነው ይህን ለእኔ ባደረገው እንዲህ አይነት ቤት ቢኖረኝ አቤት የእገሌ
ሀብት ለእኔ ቢያደርገው፡፡›› እያሉ የሌላውን ንብረት የእነርሱ እንዲደርገው ሌት ተቀን ሲያልሙ ይኖራሉ፡፡
ሐ ራስን ከሌሎች ጋር ማነጻፀር ፡ ሰው እንደራሱ እንጂ እንደጎረቤቱ አይኖርም ይባላል፡፡ አንድ ሰው ሕይወቱን ሊመራ
የሚገባው ከራሱ አቅም አንጻር መሆን ይኖርበታል ዳሩ ግን የራሱን ሕይወት ከሌሎች ጋር ማወዳደር ከጀመረ በምኞት
ባህር ውስጥ ጠልቆ መዳከር ይመጣል፡፡
2.10 ትእዛዝ 10
‹‹ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ›› ዘሌ 19፣18
ይህ ትእዛዝ የተሰጠበት ዓላማ፡
ይህ ትእዛዝ እንደ ሌሎቹ 9ኝ መሰሎቹ ትእዛዛት በኦሪት ዘጸዓት ተጽፎ አናገኘውም፤ ለብቻው በኦሪት ዘሌዋውያን
እንጂ፡፡ ይህም አቀማመጡ በሐዲስ ኪዳን በማቴዎስ ወንጌል ላይ ተጽፈው የምናነባቸውን 9 የብፁዓን አንጾችና

39

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

10ኛው ተለይቶ በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተጻፈውን አንቀጸ ብፁዓን ይመስላል፡፡ ዘጠኙን አንድ ቦታ ዐሥረኛውን
ደግሞ ነጥሎ ሌላ ቦታ ማምጣቱ ስለምንድን ነው ቢሉ? አባታችን አዳም እንደ መላእክት በ10ኛ ተፈጥሮ በ10ኛ
ማዕረግ ከብሮ ሳለ በኃጢኣት ምክንያት አጥቶት ነበር፡፡ ጌታም ካሣ ከፍሎበት በሳጥናኤል ፈንታ ያኖረው ስለሆነ፤
ከሰው ወገን የሆነ አዳም ከመላእክት ማኅበር መደመሩን የሚገልጥ ነው፡፡
‹‹ባልንጀራ›› ተብሎ የተቀመጠው ቃል በጣም ቅርብ የሆነ የቤተሰብ አባል /ዘመድ/፣ በወዳጅነትና በግል ጓደኝነነት
ቀለበት ውስጥ ያለ፣ የመደብ፣ የአካባቢ ይህንም በመሰለው ሁሉ የተዘምዶ ቋንቋ የሚቀርበው ብቻ ሳይሆን፣ አልፎ
ሂያጅ፣ መንገደኛ፣ ለአንድ ሀገር እንግዳ፣ ለሰው ባዕድና ፍጹም ባይተዋር የሆነ በዚህ የሕይወት ገጠመኝ የፍርሃት፣
የጭንቅና የችግር ጨለማ ውስጥ የገባ ማንኛውም የእኛ ድጋፍና ርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ነው፡፡
ፍቅር ማለት ደግሞ መውደድ፣ መዋደድ፣ ማክበር፣ ማስከበር፣ መከበር፣ ባለሟል መሆን፣ ይቅርታ ዕርቅ፣ ሰላም፣
የኅሊና ነጻነት፣ የልብ አንድነት፣ ስምምነት፣ ረቂቅ የልብ መጣበቅ፣ የአሳብና የአእምሮ ሙጫ ማለት መሆኑ
በሊቃውንት ተረጋግጧል፡፡
አፈቀረ ብሎ ወደደ፣ ተቀበለ፣ ተስማማ፣ አከበረ፣ አስወደደ ያሰኛል፡፡ በዚህ መሠረት ፍቅር ተፋቅሮ /መፋቀር/፣
መዋደድ፣ መከባበር፣ በአንድ አሳብ መስማማት፣ መተሳሰብ፣ መግባባት የሚሉ የትርጉም ጽንሰ አሳቦችን ያጠቃልላል፡

ስለ ፍቅር ከላይ የተዘረዘረው ትርጉም እንዳለ ሆኖ ፍቅርን በትክክል ለመግለጽ ግን እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ ይህ
የሆነበት ምክንያትም ፍቅርን በሰው ልጆች ቋንቋ መግለጽ ከማንኛውም ነገር በላይ እጅግ ጥልቅ ስለሆነ ነው፡፡ ፍቅር
በማንኛውም ድርጊት ውስጥ /በግልጽም ሆነ በድብቅ/ ስለሚንጸባረቅና የሕይወት መንገድ ስለሆነ እርሱን ተራ በሆነ
ስሜቶች መተርጎም አስቸጋሪ ነው፡፡ ፍቅር ለማንኛውምና ለእያንዳንዱ ነገር መግበያ ነው ማለት ይቻላል፡፡
የፍቅር መገኛውና ምንጭ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ
ጳውሎስም ‹‹የትእዛዝ ሁሉ ፍጻሜ ግን በንጹሕ ልብ በመልካም ጠባዕይ ጥርጥር በሌለበት ሃይማኖት መዋደድ ነው፡፡
›› ብሎናል፡፡ ፍቅር በሰው ልጆች ሕይወት ያለ ገደብ ሊኖር የሚገባው ግዴታ ነው፡፡
ባልንጀራችንን ምን ያህል ነው መውደድ እንደሚገባን መለኪያው ‹‹እንደ ራስህ ውደድ›› የተባለው ሐረግ ነው፡፡
እንደራስ መውደድ የተባለውም አንቀጽ ያለበቂ ምክንያት አልተጠቀሰም፡፡ ምንም ራስን መውደድ የታዘዘም ባይሆን
በውስጠ ታዋቂ ያለና የነበረ ነገር ነው፡፡ ሰው ራሱን ይወዳል፤ ባልንጀራን የመውደድ ተግባራዊ መለኪያው ልክ ራስን
ከመውደድ ጠባይ አንጻር ተመልክቶ የተቀመጠ ነው፡፡ ይህም ደግሞ ከማናቸውም ነገር መለኪያና መስፈሪያ በላይ
ክብደት ያለው ነው፡፡ በምናስበውና በምንናገረው፣ በሚሰማንና በምናየው፣ በምናደርገውና በምንተወው ምርጫችን
ሁሉ ተፈጥሯችን ራስን ወደ መከላከል፣ ራስን ከፍ ከፍ ወደ ማድረግና ግላዊ ሕይወትን ወደ ማበልጸግ ያመዝናል፡፡
ሌላው መስፈርት ወርቃማው ሕግ ተብሎ በሚጠራው በወንጌል ቃል ተገልጧል፡፡ ‹‹እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ
የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና›› የሚለው ነው፡፡/ማቴ 7፣12/
እኛ ከሌሎች እንዲረግልን የምፈልገውን ያህል ሌሎችም ከእኔ እንደሚፈልጉ በተፈጥሮ የተሰጠን የአእምሮ ሚዛን
ይነግረናል፡፡ ይህም ባልንጀራችንን ራሳችንን የምንወደውን ያህል መውደድ እንደሚገባን ያጠይቃል፡፡
‹‹ባልንጀራህን አንደራስህ ውደድ›› ሲል ምን ማለት ነው? የሚለውን ስንመለከት በሕገ ኦሪት ባልንጀራ ሲባል
ወገናዊነት ያለው ነው፤ በቤተስብ በጎሳ የተሣሠረ እሥራኤላዊ ዜጋ የሆነውን ብቻ ማፍቀር እንደሚገባ ያመለክታል፡፡
ከቤተ እሥራኤል ውጭ የሆነው ሁሉ የተጠላና የተጣለ ነው እንጂ የተወደደና የተከበረ አይደለም፡፡ በሕገ ወንጌል
ግን የሰው ዘር የሆነው ሁሉ ባልንጀራችን መሆኑንና እንደራሳችንም እንድንወደውና እንድንረዳው ታዝዟል፡፡ በሕገ
ኦሪት የጸና አንድ የሕግ ዐዋቂ ባልንጀራዬ ማነው? ብሎ ሲጠይቅ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የደጉ ሳምራዊን የፍቅር ሥራና በጎ አድራጎት በመተረክ መልሶለታል፡፡ ደጉ ሳምራዊ በመንገድ ወድቆ የነበረውን
ቁስለኛ አንሥቶ እንደረዳው አንተም እንደዚሁ አድርግ ብሎታል፡፡ /ሉቃ 10፣25-37/ በዚህ ታሪክ ውስጥ
የምንማረው ለወደቀው ቁስለኛ ባልንጀራ የሆነው ወገኑ ዜጋው ያልሆነው ሳምራዊው ሰው እንደነበርና እኛም
ባልንጀራችን የሰው ዘር በሙሉ መሆኑን ነው፡፡

40

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

የገዛ ሰውነቱን የሚጠላ የለም፡፡ /ኤፌ 5፣30/ እኛ ሁላችን የክርስቶስ አካል እንደሆንንና እያንዳንዳችንም ብልቶች
እንደሆንን በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል፡፡ /1ቆሮ 12፣27/ ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኝም ሊለው አይችልም፤
የራሱ ብልት ነውና፡፡ ከሰውነታችን ክፍል ስስ የሆነው ዓይናችን ነው፤ ዓይናችን በታመመ ጊዜ ይህ ስስ ብልት
አያሰፈልግም ብለው እንደ እጅና የመሣሠሉት ብልቶች ዝም አይሉም፡፡ ደግፈው አስታመው እንዲያገግም የበለጠ
ትኩረት በመስጠት ተንከባከበው ይፈውሱታል እንጂ፡፡ ምክንያቱም ምንም ስስ ቢሆን እጅግ አስፈላጊ ነውና፤
ያለእርሱም መኖር ይከብዳልና ነው፡፡ እኛም የክርስቶስ ብልቶች በመሆናችን ርስ በርሳችን ልንደጋገፍ ይገባናል፡፡
አንዳችን ያለአንዳችን መኖር አይቻለንምና፡፡ ቅዱሳን እኛ ደካሞችና ኃጢኣተኞች የሆንነውን ብልቶቻቸውን በጸሎት
በምልጃ ከእግዚአብሔር በማስታረቅ በበረከት በረድኤት በመጠበቅ በችግራችን ጊዜ በመራዳት የሚፈውሱን አንድ
አካል በመሆናችንና እኛን በማፍቀራቸው ነው፡፡ እኛም የሃይማኖትን ነገር የነገሩንን ዋኖቻችን የሆኑትን እያሰብን
በኑሯቸውና በመልካም ፍሬያቸው እነርሱን እየመሰልን ሌላው ቢቸገር ቢታመም ቢደሰት የኛም እንደሆነ አስበን ልክ
እንደራሳችን ልንረዳው ይገባል፡፡ ክርስቲያኖች ሰዎችን ሁሉ መውደድ እንደሚገባቸው ተምረናል፡፡ ጌታችን
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጆቻችንን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻችንንም ጭምር እንድናፈቅራቸው
በሕገ ወንጌል አዝዞናል፡፡ ‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ ፣
በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግሟችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሏችሁም
መልካም አድርጉ፣ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፣ በጻድቃንና
በኃጢኣተኞችም ላይ ዝናብን ያዘንባልና፡፡ የሚወዷችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ
የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን
እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ›› /ማቴ 5፣43-48/ በማለት ያስተማረን የሰው
ዘርን በሙሉ እንድንወድ ነው፡፡
ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ ተፈጥረዋል፡፡ ሁሉም ከአዳምና ከሔዋን ዘር የተገኙ ናቸው፡፡ እንዲህ
ከሆነ ለሁሉም እኩል የሆነ አንድ ዓይነት ፍቅር ሊኖረን ይገባል፡፡ ሁላችንም ግብዝነት በሌለው እውነተኛ ፍቅር
ከልባችን አጥብቀን ልንዋደድ ይገባል፡፡ /ሮሜ 12፣9 1ጴጥ 1፣22/ የክርስቲያን ፍቅር ከጠባያዊ ፍቅር የተለየ መሆን
አለበት፡፡ ማንኛውም ጠባያዊ ፍቅር መነሻው ምንጩ ጥቅም ሊኖረው ይችላል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በተግባር እውነተኛ ፍቅርን አሳይቶናል፤ ምሳሌም ሆኖናል፡፡ /ማቴ 5፣43-48 1ጴጥ 2፣23 ሉቃ 23፣
24/ ጠላትን ይቅር ብንል ምንም መነሻ አይኖረንም፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ከወደደን እኛ
ደግሞ ዘመድን ባዕድን የቅርቡንም የሩቁንም ወዳጅንም ጠላትንም ቢሆን በአንድ ፍቅር መውደድ ይገባናል፡፡ /ዮሐ
3፣16 ሮሜ 5፣10/
ሌላው ባልንጀራን መውደድ ማለት በስሜት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን በተግባር የሚፈጸም ነው፡፡ ቃልና ተግባር
የተለያዩ ናቸው፡፡ በልብ የሚታሰበውን በኅሊና የሚመላለሰውን፣ በአንደበት የሚነገረውንና በብዕር ተቀርጾ በጽሕፈት
የሚነበበውን ቃል የሚተረጎመው ተግባር፣ ድርጊት ነው፡፡ ጌታ ያስተማረው የቃልን ፍቅር፣ የልብን ምኞት አይደለም፡
፡ በድርጊት የሚታይ፣ በሥራ የሚተረጎመውን ፍቅር ነው፡፡ ከጌታችን የተማርነው ፍቅር በቃል ተነግሮ በሥራ
የተገለጠ፣ እስከሞት ያደረሰ ፍቅር ነው፡፡ የመውደድ መለኪያው የማፍቀር መሥፈርቱ ድርጊት ነው፡፡
ሰውን መውደድ የሚለው ቃል አጠቃላይና ዓለም አቀፍ ነው፡፡ በሚሊዮን አኀዝ የሚቆጠረውን የሰው ዘር በሙሉ
እወዳለሁ እያሉ በቃል ብቻ በጥቅል ከመናገር ይልቅ በቅርብ የሚገኘውን ሰው በመርዳት ፍቅረ ቢጽን በተግባር
መግለጥ ይበልጣል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስፋት ያለውን ፍቅረ ቢጽ ቀረቤታ ባለው መልኩ መላውን የሰው ዘር
በጥቅሉ ሳይሆን በቅርብ ወደሚገኙት አብረናቸው ወደ ምንኖራቸው ሰዎች ማተኮርና በተግባር መተርጎም
ወደሚያስችለው መስክ አቅጣጫን ማዞር ያስፈልጋል፡፡ ተጨባጩና እውነተኛ ፍቅረ ቢጽ አብሮን ከሚኖረው ሰው
ጋር በምንችለው ድጋፍ የምንገልጠው ነው፡፡ ይህንንም ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ
ያለው ወንድሙንም የሚያስፈልገውን ሲያጣ ዐይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት
ይኖራል? ልጆች ሆይ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ፡፡›› /1 ዮሐ 3፣14-18/ በማለት በቅርብ ያለ
ባልንጀራችንን በተግባር መውደድ እንደሚገባን አስተምሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ለሰው
ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ›› ይላል፡፡ /ገላ 6፣10/ ይኸውም ባልንጀራችንን በሥጋና
በመንፈሳዊ ሕይወት በመርዳት ይገለጣል፡፡

41

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

በሥጋዊ ሕይወት
ለኑሮ የሚያስፈልገውን ነገር እንዲያገኝ በመርዳት
መብቱ እንዲጠበቅለት በማድረግ
ጉዳት እንዳይደርስበት በመጠንቀቅና በመከላከል
በመንፈሳዊ ሕይወት
በጸሎት በማሰብ /2ጢሞ 1፣3/
በጥሩ ተምሳሌትነት ወደ ቤተእግዚአብሔር ማቅረብ /ማቴ 5፣16 1ጴጥ 5፣3/
በመንፈሳዊ ምክር በማነጽ /ሮሜ 12፣8/
ከራስ አልፎ /ልክ እንደራስ/ ለሌሎች ማሰብና ማድረግ /ማቴ 7፣12/ ደካማነት፣ ሞኝነት፣ መበለጥ፣ መዋረድ፣ በራስ
መተማመንም ማጣት ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የምንኖር መሆናችንን
የሚያሳይ የሥነምግባር ሠሌዳ ነው፡፡ ሌሎችም ዐይተው ይማሩበታልና፡፡/ሮሜ 14፣7/ ‹‹መልካሙን ሥራችሁን
ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩት ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› የተባለው አምላካዊ ቃል
የሚተረጉመው ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ፍቅርና ስለፍቅር ያለን ዕውቀት ተግባራዊ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ነው፡፡
/ማቴ 5፣16/
በቅዱስ ዮሐንስ የተሰጠው የፍቅር መለኪያ ደግሞ ክርስቶስ እኛን እስከሞት እንወደደን እኛም ወንድማችንን
እንደዚሁ መውደድ አለብን በሚለው ንጽጽር ላይ ተመሥርቷል፡፡ ይህም የሚገለጸው በቃልና በስሜት ብቻ ሳይሆን
በእውነትና በርኅራኄ ሥራ ነው፡፡ ክርስቶስ ስለእኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶናልና በዚህ ፍቅርን ዐውቀናል፤ እኛም
ስለወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል፡፡ በመሆኑም ፍቅር በዚህ ብቻ ሳይወሰን ለሌላው ራስን
አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ የፍቅር የመጨረሻው ደረጃ ይህ ነው፡፡ ጌታችን ነፍሱን ስለወዳጆቹ
ከማኖር ፍቅር የሚበልጥ ፍቅር ለምንም የለውም ብሏል፡፡ /ዮሐ 15፣13/እኛም ስለወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን
እስከ መስጠት ድረስ ልንወዳቸው ይገባናል፡፡
እውነተኛ ፍቅር ይህ ጠላት፣ ያ ወዳጅ አያሰኝም፡፡ ‹‹ወንድሙን የሚጠላ በሞት ጥላ ውስጥ ይኖራል፡፡ ወንድሙን
የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፣ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ›› በማለት
አገናዝቦ እንዳስረዳ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ /ማቴ 22፣35-40/ እውነተኛ ፍቅር ያንዱን ሥራ ከሌላው
አያመዛዝንም፣ ስጦታና መጣቀምንም አይሻም፡፡ አንድ ነገር ይደረግልኛል በሚል ጠባብ አስተሳሰብ ከራስ ምኞትና
ጥቅም አንጻር ሌላውን መውደድና አይታይበትም፡፡
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ትምርት ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል፤ ፍቅር ከሌለን ‹‹እንደሚጮህ ናስ ወይም እደሚንሸዋሸው
ጸናጽል›› መሆናችን ነው፡፡ ሁሉም ነገር ኖሮን ፍቅር ግን ከሌለን ከንቱ መሆናችንን እንማራለን ፡፡ ፍቅር ካለን የጽድቅ
ሥራዎችን እንሠራለን ከክፉ ሥራዎች እንታቀባለን፡፡ ‹‹ፍቅር ይታገሣል፤ ፍቅር ያስተዛዝናል፤ ፍቅር አያቀናናም፤
ፍቅር አያስመካም፤ ፍቅር ልቡናን አያስታብይም፤ ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም፤ አያበሳጭም፤ ክፉ ነገርንም
አያሳስብም፤ ጽድቅንም በመሥራት ደስ ይሰኛል እንጂ ግፍን በመሥራት ደስ አያሰኝም፡፡ በሁሉም ይቻላል፤ በሁሉም
ያስተማምናል፤ በሁሉም ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉም ያስታግሣል፡፡ ፍቅር ለዘወትር አይጥልም፤ ትንቢት የሚናገርም
ያልፋል ይሻራልም፤ በልዩ ለልዩ ቋንቋ የሚናገርም ያልፋል፤ ይሻራልም፤ እንዲህም ከሆነ እምነት ተስፋ ፍቅር
እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው›› /1ቆሮ 13፣1-13/
ቤት በመሠረት ይጀመራል፤ በጉልላት ይፈጸማል በጥንቱ የሀገራችን ቤት አሠራር ልማድና ትውፊት በሣር ክፍክፋት
/ክዳን/ ይሠሩ የነበሩ ቤቶች ከጉልላታቸው በላይ ‹‹ሞገስ›› በመባል የሚታወቅ፣ እንደዘወድ እንደ አክሊል ያለ
ይቀመጣል፡፡ ለቤቱ የመጨረሻ ውበት የሚሰጥ ስለሆነ ይህ ስም ሞገስ የሚለውን አግኝቷል፡፡ ለሰው ልጆች
የሕይወት መመሪያ ሕግን የሠራ እግዚአብሔርም ‹‹ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አይኑርህ›› መሠረት አድርጎ እንደ ሞገስ
ያስቀመጠው ‹‹ወንድምህን /ባልንጀራህን/ እንደራስህ ውደድ›› የሚለውን ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ትእዛዛት ለሰው ልጆች
ሰላማዊ ሕይወት መሠረትና ጉልላት ናቸው፡፡ የሕይወት መሠረት ‹‹እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም

42

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ነፍስ፣ በፍጹም ኃይል፤ በፍጹም አሳብ መውደድ›› ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ላይ የጸና ጉልላቱ /ሞገሱ/ ‹‹ባልንጀራህን
እንደ ራስህ ውደድ›› የሚለው ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ትእዛዛት የማይነጣጠሉ፤ አንዱ ከሌላው ተለይቶ የማይታይ፣
እንደ አንድ ሣንቲም ሁለት ገጽ ወይም ሁለት ጫፎች እንዳሉት አንድ ሰንሰለት የተያያዙ ናቸው፡፡ ትልቁ
የክርስቲያኖች የሥነ ምግባር ትምርት የሚነሣው ከዚህ ነው፡፡ ባልንጀራችንን መውደድ እግዚአብሔርን ከመውደድ
ተለይቶ የሚሄድ አለመሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ያስረዳናል፡፡ እንዲያውም አንድ ክርስቲያን ፍቅረ
እግዚአብሔር እንዳለው ወይም እንደሌለው ማወቂያው ባልነጀራውን መውደድ አለመውደዱን በማየት ይሆናል፡፡
‹‹ማንም፡- እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን
እግዚአብሔርን እንዴት ሊወድ ይችላል? እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ
ከእርሱ አለችን? /1 ዮሐ 4፣20-21/ በማለት ገልጾታል፡፡ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር
ፍቅር ነውና፡፡ /1ዮሐ 4፣7/
የፍቅር ሕግ ሁሉ መፈጸሚያ መሆኑን የተገነዘቡ አበው ሊቃውንት ‹‹ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ›› የሚለውን
ከኦሪት ዘሌዋውያን (19፣18) ጠቅሰው የዐሠርቱ ቃላት መደምደሚያ ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን የትእዛዛት ሁሉ
ማጠቃለያ መሆኑን ያብራራሉ፡፡ /ሮሜ 13፣8-10 ገላ 5፣13-14/ በክርስቲያን ሃይማኖት ፍቅር ከፍተኛ ቦታ አለው፡፡
ሃይማኖቱም ምግባሩም በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ነውና የተመሠረተው፡፡ ደኅንነታችንን ያገኘነው እስከ ሞት ድረስ
በወደደን በክርስቶስ ፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ በዝርዝር እስካሁን የተመለከትናቸውን ትእዛዛት ሁሉ በአንድ ቃል
በሕገ ተፋቅሮ ይፈጸማሉ፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው
በሁለት ትእዛዛት ሕግም ሁሉ ነቢያትም ተጠቅልለዋል፡፡ /ማቴ 19፣ 17-19 ማቴ 22፣34-40/
የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ የጋራ አካፋያቸው ራስ ወዳድነትን ጨክኖ መቋቋም /መተው/ እና ለሌላው
መሥዋዕት የመሆን ፈቃደኝነት ነው፡፡ ሕይወታችንን በዚህ መመሪያ በማሠልጠን ለራሳችን ብቻ መኖር የሌለብን
መሆናችንን ስንገነዘብ ያን ጊዜ ለእግዚአብሔርና እግዚአብሔር እኛን እንደሚወደን ለምንወደው ባልንጀራችን
የተመቸን እንሆናለን፡፡ ከሁሉ በፊት ርስ በርሳችሁ አጥብቃች ተዋደዱ፡፡ /1ጴጥ 4፣8/ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ
ጴጥሮስ አዝዞናልና ትእዛዙን ለመፈጸም ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ይርዳን!
እንደ ራስ መውደድ
ባልንጀራህን እንደ ራስ አድርገህ ውደድ ሲባል አንተ ላይ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን እዚያ ሰው ላይ አለማድረግ፣
አንተም ሌሎች እንዲያደርጉልህ የምትሻውን ለሌላው በማድረግ የሚገለጽ ነው፡፡
ስድስቱ ሕግጋተ ወንጌል/ትእዛዛት/
የቤተ ክርስቲያን መምህራን ስለ ሕገ ወንገጌል የተለያየ አመለካከት አላቸው፡፡
1ኛ ማቴ 5÷22-45 የተዘረዘሩትን ሕገ-ወንጌል ናቸው በማለት የሚያስተምሩ
2ኛ ማቴ 25÷25-36 የተዘረዘሩትን ሕገ ወንጌል ናቸው በማለት የሚያስተምሩ
3ኛ ሕግጋተ ወንጌልንና ቃላተ ወንጌልን በመለየት ፡ በማቴ 5 ያሉትን ሕግጋተ ወንጌል በማቴ 25 ሉት ቃላተ ወንጌል
ናቸው የሚል አመለካከት ያላቸው ናቸው፡፡
ሕግ ሲባል ለማድረግ የማይዘገይ ከማድረግ የመከልከል ባሕር አለው፡፡ በማቴ 5 ያሉት የሕግ ባሕርይ ያላቸው
በመሆኑ ሕግጋተ ወንጌል ሊባሉ ይችላሉ፡፡በማቴ 25 የተዘረዘሩት ከላ የተጠቀሱት የሕግ ባሕር አይታይባቸውም፡፡
በዕለተ ምፅአት ክርስቶስ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት በይባቤ መላእክ በተገለጠና በፍርድ ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ
ኃጥአንን ጻድቃን በግራና በቀኝ ቆመው እንዲመልሱ የሚያቀርብላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቃላተ
ወንጌል ይባላሉ፡፡
በማቴ 5 ያሉትን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕግጋተ ኦሪትን እያስታወሰና እየተቀሰ መሆኑ ከሕግ ወገን
ሕግጋት ለመሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡

43

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

1. በወንድምህ ላይ በከንቱ አትቆጣ


ቁጣ፡- የሚቆጣውንም ሰው ቁጣውን የሚወረውርበትንም ሰው ይጎዳል፡፡
 ቁጡ ሰው ሕይወቱን ለጉስቁልና ያጋልጣል
 ቁጣ ዕድሜውን ለእርጅና ያጋልጣል
 ቁጣ የጽድቅን ሥራ አያሰራም
‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ በከንቱ የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ወንድሙን ጨርቅ ለባሽ የሚለው በሸንጎ
ደንቆሮ የሚለው ግን በገሀነም ይፈረድበታል፡፡››ማቴ 5÷22
 ሕንጻውን መንቀፍ አናጢውን መንቀፍ ነው፡፡

2. ወደሴት አትመልከት በልብህ አታመንዝር


በሐዲስ ኪዳን የተሰጠ ሕግ ነው፡፡አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን አታመንዝር የተባለውን የሚያጠናክርና ግልጥ በሆነ
መልኩ የሚያስረዳ ነው፡፡ ‹‹አታመንዝር እንደተባለ ሰምታችኋል እኔ ግን እላችኋለሁ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም
ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሯል››ማቴ 5÷27-28
ለማናቸውም ኃጢአት መነሻው ማየትና መመኘት ስለሆነ አይኖቻችንን ከክፉ ነገር ጾመኛ ማድረግ ይበጃል፡፡በጆሮ
የሰሙትን ምኞት በተግባር የሚያስፈፅም የማየት ፈተና ነው፡፡ሔዋን ከጠላት ሰማች ፍሬዋን አይኗ ባየች ጊዜ
የምታስጎመጅ ሆና ተገኘች በልታም ተጎዳችበት፡፡የማየት አገልግሎት የሚሰጠው ዓይን ለስህተት ምክንያት ከሆነ ማቴ
5÷29
‹‹ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ካንተ ጣላት ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንዱ
ቢጠፋ ይሻልሀልና፡፡››
3. ሚስትህን ያለዝሙት ምክንያት በሌላ ነውር አትፍታ
ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረና ያለ በቂ ምክንያት ሊፈታ የማይገባው ጽኑ ሕግ መሆኑን የሚገልጥ ነው፡፡‹‹ሰው
አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ……………እግዚአብሔር አንድ
ያደረገውን ሰው አይለየውም፡፡››
 ሴት ከባሏ ሰውነት ከባሏ ሕይወት የተገኘች ሕይወቱ ሰውነቱ መሆኗን የሚገልጥ ሀይለ ቃል ነው፡፡
 ሰው ሚስቱን ሲፈታ አንዱን አካል/ስውነት/ ከሁለት እንደመክፈል የሚታይ ነው፡፡
 በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መፍታት እንደሌለብ በወንጌሉ አዟል፡፡
 ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ ያለ ዝሙት ምንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እርሱ አመንዝራ አደረጋት የተፈታችውንም
ያገባ አመነዘረ፡፡››ማቴ 5÷32

4. ፈጽመህ አትማል
የታዘዝነው እውነትን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ብለን እንድንናገር እንድንመሰክር ነው፡፡
‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ ከቶ አትማሉ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና በምድርም አይሆንም የእግሩ
መረገጫ ነውና በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉስ ከተማ ነውና በራስህም አትማል አንዲቱ ጠጉር ነጭ ወይም
ጥቁር ልታደርግ አትችልምና ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን አይደለም አይደለም ይሁን ከነዚህም የወጣ ከክው ነው፡፡
››ማቴ 5÷34-37
የአምላን ስም ከንቱ ማድረግ ሕይወትን ከአጥር ውጪ ማውጣት ነው፡፡የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ
የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ በማለት መሀላን ፈጽሞ ከልክሏል፡፡
44

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

5. ክፉን በክፉ አትመልስ


የዚህ ሕግ ዋና መልዕክት ትዕግስት ነው፡፡ይህ ሕግ በቀልን የሚቃወም ነው፡፡
‹‹ አትበቀሉ…… በቀል የእኔ ነው ይላል እኔም ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ››
ክፉን በክፉ አለመቃወም ማለት
 ክፉውን ነገር በክፉ ድል ለመንሳት አለመዘጋጀት
 ክፉውን ግብር በክፉ ግብር አለመቃወም በአጠቃላይ አለመቃወም ማለት ነው፡፡
‹‹ እኔ ግን እላችኋለሁ ክፉውን አትቃወሙ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥ ለሚመታህ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት
እንዲከስህም እጀጠባብህን እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ
ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ ለሚለምንህ ስጥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ
አትበል፡፡›› ማቴ 5÷ 39-42
ቅዱስ ጳውሎስ
‹‹ለማንም ስለ ክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ ቢቻላችሁስ ከእናንተ በኩል
ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ ለቁጣው ፈንታ ስጡ እንጂ››ሮሜ 12÷17-19
‹‹ክፉውን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አታሸንፉ›› ክርስቲያን ክፍዎችን ሰዎችን መቃወም ሳይሆን ለእነዚህ
የሚፀልይ ነው፡፡
6. ጠላቶችህን ውደድ
የዚህ ሕግ ዋናው መልዕክት ፍቅር ነው፡፡
ክርስቶስ ጠላቶቹን እንደወደደ እኛም እንንወድ ይህ ሕግ ተሰጥቶናል፡፡ክርስቶስ ሀሉንም በመውደድ በፍጹም ፍቅር
እንደተገለጠ እኛ ክርስቲያኖች ሁሉን መውደዳችን ፍጹም ያደርገናል፡፡
‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ በሰማይ ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን የሚረግሙአችሁን መርቁ
ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሀይን ያወጣልና
በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናብን ያዘንባልና የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ ቀራጮችስ ያንኑ
ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሱ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?
እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ››ማቴ 5 ÷44-48
ቅዱስ ጳውሎስ
‹‹ ጠላትህ ቢራብ አብላው ቢጠማ አጠጣው››ሮሜ 12÷20
የክርስቲያኖች እውነተኛ ፍቅር የሚታወቀው ጠላትን በመውደድ ነው፡፡
ማርይስሐቅ
‹‹ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር አትጋት ባገኘኸውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው አክብረው ወደህ እየው ከበጎ
ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ነገር ትስብዋለህና ነፍስህ
ከለመደችው አንድም አንተ ነፍስህን ካለመድካት ባልንጀራህን ከመውደድህ የተነሳ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ
ይቀረጻል ፍጹም ትህትናን ገንዘብ ታደራጋለህ ሳትጠራ ብዙ ሥራ ትሰራለህ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ
አይደለም ነውር ያለበትንም ቢሆን አክብረው እንጂ ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት ጥበብ
የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘንና መራራት ነው››ማር ይስ አንቀጽ
6ቱ ቃላተ ወንጌል

45

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

1. ተርቤ አብልታችሁኛልና ማቴ 25÷35


2. ተጠምቼ አጠትታችሁኛልና ማቴ 25÷35
3. እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና ማቴ 25÷35
4. ታዜ አልብሳችሁኛልና ማቴ 25÷36
5. ታምሜ ጠይቃችሁኛልና ማቴ25÷36
6. ታስሬ ወደ እኔ መጠታችኋልና ማቴ 25÷36
1. ‹‹ተርቤ አብልታችሁኛልና ተጠምቼ አጠትታችሁኛልና……››
ክርስቲያኖች የተራቡትን የማብላትና የማጠጣት መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው›› በጾም ወቅትም
‹‹እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን?እንጀራህንስ ለተራበ ትቆርስ ዘንድ…… አይደለምን›› ኢሳ 58÷7
አንድ ሰው ጻዲቅ መሆን ቢፈልግ ማድረግ ያለበት
ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ
በተራራ ላይ ባይበላ
ኤኖቹን ወደ ቤተ እሥራኤል ጣኦት ባያነሳ
የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ
አደፋም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ
ሰውንም ባስጨንቅ
ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ
ፈጽሞም ባይቀማ
ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ
የተራቆተውንም በልብስ ቢያለብስ
በአራጣ ባያበድር
በትእዛዜም ቢሄድ
እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ እርሱ ጻዲቅ ነው›› ትሕዝ 18÷5-9
ቅዱስ ያዕቆብም ለተራበ ማብላት እንዳለብን ሲናገር ‹‹ወንድም ወይም እህት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም
ቢያጡ ከእናንተም አንዱ ሂዱ እሳት ሙቁ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት የሚያስፈልጉትን ባትሰጠአቸው ምን
ይጠቅማቸዋል? >> ያዕ2÷15
ግብዣ ስናደርግ መጥራት ያለብን
‹‹ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባትም እንዳይጠሩህ ብድራትንም እንዳይመልሱልህ
ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህም ባለጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና
ጉንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ በጻድቃን ትንሳኤ
ይመልስልሀልና››ሉቃ 14÷12
2. ለተጠማ ማጠጣት እናዳለብን ሲነግረን
‹‹ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም፡፡››ማቴ 10÷42
የድሆችን ጩኸት የማይሰማ ሰው የእርሱንም ጩኸት እንደማይሰማው
‹‹የደኻውን ጩኸት እንዳሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም፡፡››ምሳ 21÷13
ሰው በእግዚአብሔርም ቃል መኖር እንዳለበት
46

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

‹‹ ማንም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት


እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ አሥራበህም አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ››
ዘዳ 8÷3
‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኤኖርም›› ማቴ 4÷4
3. ‹‹እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና……››
እንግዳ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነውን ሰው እግዚአብሔር በእንግድነት ሊቀበለው ኤችልም፡፡
እንግዳ በመቀበልና በማስተናገድ አባታችን አብርሀምና ጻዲቁ እዮብ
አብርሃም አንግዳን በመቀበሉ ስላሴን በድንኳኑ ተቀብሏል ዘፍ 18÷1-5
ሎጥም እንግዳን በመቀበሉ መላእክትን በእንግድነት ተቀብሏል ዘፍ 19÷1-3
ጻዲቁ እዮብም እንግዳን ይቀበል ስለነበር መከራ በገጠመው ወቅት እንዲህ ብሎ ተናግሯል ‹‹መጻተኛው ግን በሜዳ
አያድርም ነበር ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፤………››ኢዮብ 31÷32
ቅዱስ ጳውሎስ እንግዳን ስለመቀበል ሲነግረን ‹‹እንግዳን መቀበል አትእርሱ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን
በእንግድነት ተቀብዋልና››ዕብ 13÷2
እንግዶችን ለመቀበል መትጋት እንደሚገባ አበክሮ ሲነግረን‹‹…… እንግዶችን ለመቀበል ትጉ፡፡››ሮሙ 12÷13
ስደተኞችን መቀበል ለክርስቲያን ወጉና ክብሩ ነው፡፡ለሀገር እንግዳ ለሰው ባዳ ናቸውና
4. ታርዤ አልብሳችሁኛልና………››
መታረዝ ማለት ከልብስ መራቆት ማት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል………›› ሉቃ 3÷11
ነብዩ ኢሳያስ ሰዎች በጾም ወቅት ማድረግ ስለሚገባቸው ነገሮች ኢሳ 58÷7
‹‹የተራቆተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሸግ አይደለምን?>>
ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በመጓዝ ላይ እያለ በወንበዴዎች እጅ የወደቀው ሰው ካህኑ፣ሌዋዊው፤ሳምራዊው
ሉቃ10÷29-37
እግዚአብሔር አምላክ በፈቀደ ሁለት እጀ ጠባብ ያለው አንዱን ለሌለው እንዲሰት ያስተምረናል፡፤

 ሰው ካለበሰ ከእንስሳ ያንሳልና


 ፀጋውም ክብሩም ይረክሳልና
 ለታረዘ ማልበስ ፀጋን ማጎናፀፍ ነውና
አዳም በኃጢአቱ ከፀጋው ታረዘ እኛ በኃጢአታችን መታረዝ እንዳይኖርብን ከቅድስት ቤተክርስቲን አባቶች የንስሐ
ልብስ በወንጌል ተምረን እንልበስ እናልብስ
ከቃሉ የታረዝን ብዙ ነንና እርቃናችንን እየቷግዝን የሰው መሳቅያ ሆነናል፡፡ሥነ ምግባርን ልብስ አድርገን መልበስ
አለብን፡፡
5. ‹‹ታምሜ ጠይቃችሁኛል…………››

47

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

በሽታ ወይም ደሜ በተለያዩ ምክንያት ሊመጣ ወይም ሊከሰት ይችላል፡፡


1. በኃጢአት ምክንያት
ኢሳ 1÷5-6
‹‹ራስ ሁሉ ለሕመም ልብም ሁሉ ለድካም ሆኖአል ከእግር ጫማ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም
ቁስልኛ እብጠት የሚመግልም ነው አልፈረጠም አልጠገነም በዜትም አለዘበም፡፡››
2. የእግዚአብሔር ክብር በሰዎች ላይ ይገለጥ ዘንድ
ለምሳሌ ጻዲቁን ኢዮብን፤የአይን ቅርፅ እንኳን የሌለው ዮሐ11
ሕመምተኛውን መጠየቅ እንዳለብን ሲነግረን ፡ የጴጥሮስ አማችን ሉቃ 4÷38-39 ፤ የመቶ አለቃውን ልጅ
ዮሐ 4÷46
ቅዱሳንም ይታመማሉ ፡ ቅዱስ ጳውሎስ ጢሞቲዎስ በታመመ ጊዜ ‹‹ ስከ ሆድህና ስለ በሽታ ብዛት ጥቂት የወይን
ጠጅ ጠጣ እንጂ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ›› 1ኛ ጢሞ 5÷23
ሰው የተባለ ሁሉ ለታመመ ወንድሙ በጎ አድራጎትን መፈጸም አለበት፡፡
6. ‹‹ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና………››
የታሰሩት ሁሉ ወንጀለኞች ናው፡፡ጥፋተኞች ናቸው ማለት አይቻለም፡፡
ሐዋርያት የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ስለሰበኩ በተለያየ ጊዜያት ታስረዋልና፡፡
 መጥምቁ ዮሐንስ ማቴ11÷2
 ሐዋርያት ሐዋ 5÷18
 ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋ 12÷7
 ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ሲላስ ሐዋ 16÷23-40
ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ ጊዜ እንደታሰረና መጠየቅ እንዳለብን ሲናገር ‹‹ከእርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ እስረኞችን
አስቡ………››ዕብ 13÷3
አስቧቸው ማለቱ እየሄዳችሁ ጠይቋቸው ልታደርጉላቸው የምትችሉትን ሁሉ አድርጉላቸው ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ለእስረኞች ማዘንና መራራት እንዳለብን ሲነግረን ‹‹የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማ
ራሳችሁ እንዳለ አውቃችሁ በእሥራቴ ራሩልኝ››ዕብ 10÷34
እስረኞቸን መጠየቅና ለእነርሱ መራራት በሰማይ የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ ማከማቸት ነው፡፡
እስረኞችን ለመጠየቅ እንትጋ ይህን ለማድረግ የምንተጋ ከሆነ ክርስቶስ በፍርድ ቀን ‹‹……እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ፤…››
ማቴ25÷34
በመጨረሻም የክፉ ሰዎች ጠባያትን በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቲዎስ እንዲህ ብሏል፡፡
17ቱ የክፉ ሰው ጠባያት
‹‹ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመታ ይህን እወቁ
1. ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና
2. ገንዘብን የሚወዱ
3. ትምክህተኞች
4. ትዕቢተኞች
5. ተሳዳቢዎች
6. ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ
48

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

7. የማያመሰግኑ
8. ቅድስና የሌላቸው
9. ፍቅር የሌላቸው
10. ዕርቅን የማሰሙ
11. ሐሰተኞች
12. ራሳቸውን የማይገዙ
13. ጨካኞች
14. መልካም የሆነውን የማይወዱ
15. ከዳተኞች
16. ችኩሎች
ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ………›› 2ኛ ጢሞ 3÷1-4
6ቱ ቃላት ወንጌል በአንድምታ
ማቴ 25÷35 ‹‹ብራብ አብልታችሁኛል››
ኢሳ 58÷7 ‹‹እንጀራህን ለተራበ ትቆርስ ዘንድ››
ማቴ 25÷35 ‹‹ብጠማ አጠትታችሁኛልና››
ማቴ 25÷35 ‹‹እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁኛልና››
ማቴ 25÷36 ‹‹ብታመም ጠይቃችሁኛልና››
ማቴ 25÷36 ‹‹ብታሰር ወደ እኔ መጥታቸሁ ጠይቃችሁኛልና፡፡››
ሐተታ
የመንግስተ ሰማያት ዋጋ አይሆንምና አጠገባችሁኝ አኖራችሁኝ አዳናችሁኝ አስፈታችሁኝ አላለም
ይህም ሦስቱ የባለጠጎች ሦስቱ የነዳያን ነው
አንድም
ለመምህራን፡ በክህደት ምክንያት ብራብ ብጠማ አስተምራችሁናልና፡፡
 በክህደት እንግዳ ብሆን በትምህርት ተቀብላችሁኛልና
 በክህደት ምክንያት ልጅነት ባይሰጠኝ በሃይማኖት እንዲሰተኝ አድርጋችኋልና
 በክህደት ብታመም በትምህርት ጠይቃችሁናልና
 በማዕሰረ ክህደት ብታሰር በትምህርት አስፈትታችሁኛልና
አንድም
 ለቀሳውስት፡ በኃጢአት ከስጋው ወደሙ ብከለከል በንስሐ ስጋውን ደሙን ሰጥታችሁኛልና
 በኃጢአት እንግዳ ብሆን በንስሐ ተቀብላችሁናልና
 ልጅነት በኃጢአት ቢነሳኝ በንስሐ እንዲመለስልኝ አድርጋችኋልና፡፡

ሕገ ወንጌል በአንድምታ
1. ማቴ 5÷22
እኔ ግን ወንድሙን በከንቱ ያሳዘነ ሁሉ ኃጥእ ተብሎ ይፈረድበታል ብዬ እነግራችኋለሁ
49

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ሐተታ
ኦሪትንስ የሠራው እሱ አይደለም?
ወንጌልንስ
 እኔ ግን ማለቱ ስለምን ቢሉ፡ ኦሪትን በሙሴ፣ በኢያሱ አድሮ ሰርቶታል

ወንጌልን ግን እርሱ ራሱ ሰው ሆኖ ሰርቶታልና


አንድም
 ለቀደሙት ሰዎች እንዲህ ብሎ ነበር ዛሬ ግን እንደአልኩ
አንድም
 ያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ነበር ዛሬም እንዲህ አልኩ
በከንቱ አለ የሚገባ ቁጣ አለና
የሚገባ ቁጣ
 ሕጻናት ያልተማሩ እንዲማሩ
 የተማሩት እንዳገድፉ
 መናፍቃን እንዳሰለጥኑ
 ሃይማኖት እንዳይጠፋ
 ክህደት እንዳይስፋፋ
አንድም
በከንቱ ያለውን መፍቃርያነ መንት የጨመሩት ነው ትሐጌ 2÷8
‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ከክብሩ በኃላ በዘበዜአችሁ አህዛብ ልኮኛል የሚነካችሁ የዐይኑ ብሌን
የሚነካ ነውና፡፡››
ወንድሙን ጨርቅ ለባሽ አባቱን ታናሽ ብሎ የሰደበ በደለ በአደባባይ ይፈረድበታል፡፡
ወንድሙን ዲዳ ደንቆሮ ያለው እሱ በደለ በእሳተ ገሀነም ይፈረድበታል፡፡
ሐተታ
ወንድሙን ጨርቅ ለባሽ አባቱን ታናሽ ቢለው ባደባባይ ደንቆሮ ቢለው በገሃነም ይፈረድበታል አለ ምነው ቢሉ
ከተፈጥሮተ ሥጋ ተፈጥሮተ ነፍስ እንዲበልጥ ከስድብም ስድብ ይበልጣልና ከፍዳውም ፍዳውን አበለጠ፡፡
አንድም
በዓውድ ገሃነም በገሃነም ዓውድ ያለ ነው፡፡

መጽሐፉን አይቶ መንቀፍ ጸሐፊውን


ሕንፃውን ኤቶ መንቀፍ አናፂውን እንደመንቀፍ ነው፡፡
ፍጥረቱንም አይቶ መንቀፍ እግዚአብሔርን
50

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

2. ማቴ 5÷27-28
 ለቀደሙት ሰዎች አትሳሳት የሚለውን ሰምታችኋል እኔ ግን ሴትን ያየ ሁሉ ፈጽሞ በደለ ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
 ራእይን መከልከሉ ነው ቢሉ
አዎን አርቆ ማጤን ነው፡፡
አንድም
ፈተው ያለውን ይሻል ኤቶ ባገኛት ቢል
3. ማቴ 5÷32
እኔ ግን ሳትሰስንበት ሰነፈች ደረቀች ብሎ ሚስቱን የፈታ ሰው ሁሉ ዘማዊት አሰኛት ብዬ እነግራችኋለሁ ፡፡
በነውር የተፈታቸውንም ያገባ በደለ፡
በምን ያውቀዋል ቢሉ
አቡን እጨጌ ይፍቱን ባለማለቱ
ኃላ እንደምን ትሁን ቢሉ
የፍርድ መፅሐፍ በጉጉ ብሎ ወስዶታል፡፡
ንስሐ መግባቷን መምህረ ንስሐዋ ጎረቤቶቿ መስክረውላት ታግባ ብሏል፡፡
አንድም
 ኦሪትን የሚተው ሰው ሁሉ ወንጌልን ተክቶ የተው የወንጌልን ሥራ ሳይሰራ ግን ኦሪትን የጠወ ሰው ወንጌልን
ኃላፊት ሕግ አደረጋት፡፡ከተዋት በኃላ ወደ ኦሪት ቢመለስ በደለ ኃጥእ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡

4. ማቴ 5÷34-37
እኔ ግን ፈጽሞ አትማሉ እላችኋለሁ፡፡
በሰማይም ሆኖ ከሰማይ የመጣ መቅሰፍት አይሳተን ሰማይ ተንዶ ይጫነን እያሉ ይምላሉና
የደጉ ንጉሥ የእግዚአብሔር የመመለኪያው ሀገር ናትና
በራሳቸሁም አትማሉ እንዲህ ያድርገን እያሉ ይምላሉና፡
በራሳቸው ፀጉር አትማሉ እንደራሳችን ፀጉር ያጥቁረን
የራሳችንን ፀጉር አሞራ መጥቶ ይብላን እያሉ ይምላሉ፡፡ከራሳቸው ፀጉር አንዱን ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ ማድረግ
አይቻላችሁምና››
ያዕ 5÷12
‹‹ከሁሉም በፊት ወንድሞቼ ሆይ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሓላ ቢሆን በምንም አትማሉ ነገር ግን
ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ይሁን አይደለም ቢሆን አይደለም ይሁን፡፡››
 ነገራችሁ እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ይሁን እንጂ
ሐተታ
51

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ


ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

እውነት ቢለው ያምንለታልን ቢሉ ይመንለት ወንጌል መሰራቷ ለሁሉ ነው፡፡እንጂ ላንድ ብቻ ነውን ይላሉ
ባያምንለትስ ቢሉ
 መሐላውን በገንዘብ ያስቀረው፡ ገንዘብ ባይኖረውስ ቢሉ ያማል
 ዕዳው ባማዩው ይሆናል እንጂ በማዩ አይሆንምማ እንደምነው አይጠላም ቢሉ
 አይጣላም ሐዋርያ የርትዑን ጌታ የትሩፋቱን ተናገራ
አንድም
ሁሉም ርትእ ነው ሐዋርያ ዳኛ ፈርዶባችሁባላጋራ አውርዶላችሁ ማሉ ሲል ነው፡፡ ጌታ ዳኛ ሳይፈርድባችሁ
አትማሉ ሲል ነውና
አንድም
 ኢ በሰማይ ብለህ መልስ በመለኮት አትማሉ ባሕርዩ ነውና
 ወ ኢበምድር በትስብእት አትማሉ ባሕርዩ ነው
 ወኢበኢየሩሳሌም በሥጋው በደሙ አትማሉ ባሕርዩ ነውና
 ወኢበርስክሙ በክርስቶስ አትማሉ
 ከጻድቃን ከሰማዕታት አንዱን ኃጥዕ ጻድቅ ጻዲቁን ኃጥዕ ማድረግ አየቻላችሁምና፡፡

5. ማቴ 5 ÷39-42
እኔ ግን ክፉውን ሰው በክፉ ነገር ድል አትንሱት ክፉውን ግብር አታጥፋት እላችኋለሁ፡፡
ቀኝ ፊትህን ቢመታህ ግራ ፊትህን አዙረህ ስጠው ፍቃደ ሥጋህን ተው ቢልህ ፈቃደ ነፍስህን ተውለት
መጎናጸፊያህን ሊቀማ ቢወድ ቀሚስህን ደርብለት
ታሪክ
አንዳንድ ባሕታዊ ወንበዴዎች እንግዶች መስለው መጡ እግራቸውን አጥቦ አብልቶ አጠጥቶ አሳደራቸው ለሊት
ተነስተው እሱን አስረው መብራት አብርተው ያለ ገንዘቡን ይዘው ሄዱ ከሄዱ በኋላ መብራት አብርቶ ቢያይ
ሁለት ድሪም የምታወጣ ደምር አገኘ ይቺም ላንድ ጉዳ ትሆናችኋለች ብሎ ተከትሎ ወስዶ ሰጣቸው፡፡ይህ ሰው
እንዲህ በማድረጉ ከዚህ የበለጠ ዋጋ እንዳለ ቢያውቅ እንጂ ነው፡፡ብለው ተመልሰው ንስሐ ገብተው የሚኖሩ
ሆነዋል፡፡
አንድም
 አፍአዊ ግብርህን ሊስተውህ ቢወድ ውሳጣዊ ግብርህን ተውለት
 ትብትብ አሸክሞ አንድ ምዕራፍ ቢወስድህ ይህማ የግድ አይሆንምን ብለህ የፈቃድ ሁለት ምዕራፍ ተሸክመህ
ውሰድለት፡፡
 መምህረ ንስሐ አንድ ሱባኤ ቀኖና ቢሰጡህ ይህ ተስማምቶኛል ጨምርልኝ ብለህ ከሱ አስፈቅደህ ሁለት
ሱባኤ ጹም፡፡

52

የ/ደ/ይ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ

You might also like