Professional Documents
Culture Documents
TIMIHRTE HAYIMANOT - 2016-M1 (3)
TIMIHRTE HAYIMANOT - 2016-M1 (3)
ማውጫ
ምዕራፍ አንድ ሃይማኖት ........................................................................ 8
1.1 ሃይማኖት ምንድን ነው? .......................................................................... 8
1.1.1 የሃይማኖት ትርጉም ........................................................................................... 8
1.1.2 የሃይማኖት መገለጫዎች..................................................................................... 8
የቅዱሳን አማላጅነት....................................................................................176
10.6 ቅዱሳን ሥዕላት .................................................................... 181
1 የቅዱሳን ሥዕላት አጠቃላይ ገፅታ ..........................................................182
1.1 በዘመነ ብሉይ ................................................................................................. 182
1.2 በዘመነ ሐዲስ .................................................................................................. 182
2 የመላእክት ባሕርይ................................................................................201
ሀ. የመላእክት አገልግሎት ...........................................................................201
ለ. የመላእክት ስልጣንና ክብር ......................................................................203
ሐ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት .............................................................................204
ዋቢ መጻሕፍት ............................................................................. 210
መግቢያ
ሃይማኖት የሚለው ቃል “ሀይመነ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማመን መታምን ማለት
ነው፡፡ በሀይማኖት የምናምነውም ሆነ የምንታመነው እግዚአብሔርን ነው፡፡
ሃይማኖት ማመን ነው ስንል በአይነ ስጋ አይቶ በስጋ ጆሮ ሰምቶ በልብ አስቦ በስሜት ህዋሳት አድምጦ
ሊመረምሩት የማይቻለውን በርህቀት (ሩቅ በመሆን) እና በርቀት (በረቂቅነት) ያለውን ይሆናል ይደረጋል
ብሎ መቀበል ነው ምክንያቱም ሀይማኖት የሚቀበሉት ነውና፡፡
1. ሀይማኖት የፍጡርና ፈጣሪ የሆነ እግዚአብሔር የሚገናኙበት ረቂቅ መንገድ ነው፡፡ ኤር 6፤16
2. ሀይማኖት ልዑል እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ያደረገው ጉዞ (ፍኖተ እግዚአብሔር) ነው፡፡ ዘፍ 3፤1
ሀይማኖት አምነው የሚቀበሉት እንጂ አውቀው የሚቀበሉት ወይም የሚያምኑት አይደለም፡፡ ከአመኑና
ከተቀበሉ በኃላ ግን ለማወቅና በራሱ ወሰን ለመመርመር ስልጣን መቀበል ይቻላል፡፡
ስሜት በህዋሳት ልናረጋግጠው የምንችለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ መንፈስ ነው (ዮሀ 4፤24) መንፈስን
ደግሞ በስሜት ልንረዳው አንችልምና ለመረዳትም አቅምና እውቀት አይኖረንምና ሀይማኖትን አምነን
እንቀበላልን እንጂ በእውቀት ውስጥ ሆነን አንቀበልም፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 12፤3 ‹‹እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት
እንዳያስብ ከመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ፡፡ አስተምራለሁ፤ እመክራለሁ›› ይህ
ጥቅስ የሚያመለክተው ለአእምሮ ወሰን ሲኖረው ለእግዚአብሔር ግን ወሰን የለውም ስለዚህ ሰው
የማይቻለውን ነገር ሊያደርግ ቢፈልግ አይቻለውምና በእምነት መቀበል ይኖርበታል፡፡
ለ. በተስፋ የሚረዱት ነው
‹‹ተስፋ ለሚያደርጉት ሀይማኖት የተረዳች ናት…..›› ዕብ 11፤1 ሰው ተስፋ ከሌለው አያምንም ካላመነ
ደግሞ ተስፋ አይኖረውም፡፡ ወደፊት ተስፋ የምናደርገውን ዘላለማዊ ህይወትና እግዚአብሔር የሚያወርሰንን
መንግስት የምናረጋግጠው በሀይማኖት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ረድኤትና ፀጋ ፣ ጥበቃና ቸርነትን አምነን
የምንጠቀመው በተስፋ ነው፡፡
በተስፋ የምንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡- ከዘላለማዊ ህይወትና ከመንግስተ ሰማያት በፊት የእግዚአብሔርን
እርዳታ ለስጋዊም ሆነ ለሰማያዊ ህይወታችን ስንፈልግ በፀሎት ጠይቀን የምንጠብቀው በተስፋ ነው፡፡
ሐ. በፍቅር የሚገለጥ ነው
ሀይማኖት የድህነተ ስጋ የድህነተ ነፍስ መንገድ ነው፡፡ የጎሰቆለ ባሪያችንን አድሶ ፣ የተገፈፍነውን ፀጋ
መልሶ ፣ በስጋ በነፍስ ያዳነን ደግሞ በተዋህዶ የከበረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
እርሱም የተገለጠው ከፍቅር የተነሳ ነው፡፡
‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን
እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና›› ዮሐ 3፤16
መ. በስራ የሚተረጎም ነው
አንድ ሰው ይሆናል ይደረጋል ያለውን የሚገልጠው በራሱ ህይወት ወይንም በሌላ ሰው ላይ ነው፡፡ በሌላው
ሰው ላይ የሚያደርገው በፍቅር የሚገለጥ ሲሆን በስራ የሚተረጎመው ብለን የምንገልፀው የመታመን ዋናው
መገለጫ የሆነና በስራ በመጀመር የሚሰራ ነው፡፡
እምነት ዝም ብለን የምንቀበለው በተስፋ የምንረዳው በፍቅር የምንገልጠው እና በስራ የምንተረጉመው ነው፡፡
ይህም በመራቅ ወይም በረቂቅነት በዐይነ ስጋ የማይታዩትን ለማየት ያበቃናል፡፡
ለምሳሌ፡- ለነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስና ለያዕቆብ እግዚአብሔር አምላክ ለእነርሱ ማየት በሚገባቸው መልኩ
ተገልጦ ታይቶአቸዋል፡፡ ኢሳ 6፤6 ዘፍ 20፤13፡፡
ረ. እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ነው
ሀልዎት የግዕዝ ቃል ሲሆን “ሀለወ” ከሚለው ግስ የወጣ ነው ትርጉሙም መኖር ወይም ህልውና ማለት
ነው፡፡ ስለዚህ ሀለዎተ እግዚአብሔር ስንል የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን መኖር
ለማወቅ እና ለመረዳት ቁልፉ እምነት ነው ከእምነት ያልተነሳ ሰው በፍፁም ወደ እግዚአብሔር ሊደርስ
አይቻለውም፡፡ ፈጣሪ እናውቀው ዘንድ የሚያግዙንን ብዙ ነገሮችን ሰጥቶናል እንድናውቀው አጋዥ አድርጎ
ከሰጠን ውስጥ ስነፍጥረት ፣ ህሊና ፣ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ዝንባሌ እና ቃለ እግዚአብሔር ናቸው፡፡
ትውፊት እውነትን የመናገር ብቃት ያለው የእምነት መሰረት ነው ስለዚህ ትውፊት የመጻህፍትና
የእውነትም ምንጭ ስለሆነ መሰረት ሀይማኖት ለመሆን ስልጣን አለው፡፡ ትውፊትን አሁን አግኝተን
መጠቀም የምንችለው ደግሞ ከመምህራንና ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ‹‹በሐዋርያትና በነብያት
መሰረት ላይ ታንፃችኋል የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው›› ኤፌ2፤20፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን
የምታስተምረውን የሚሰማ እና የሚሰራ ሁሉ ታላቅ የእምነት መሰረት አለው፡፡
ለ. ቅዱስ መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስ የእምነት መሰረት ያሰኘው እውነቱን የሚናገርና መለኮታዊ ስልጣን ያለው መጽሀፍ ነው፡፡
ይህንንም ስልጣን የሰጠው ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
ለስጋ
ያለስጋ ነፍስ አትቆምምና መጀመሪያ ለስጋ እንደሚያስፈልጋት እንመለከታለን፡፡ ሀይማኖት ለስጋ ጠቀሜታ
አለው ስንል ለማንኛውም ምድራዊ ህይወታችን ለማለት ነው፡፡ ሰው በሀይማኖት ቢኖር፡-
ሀ. ሰላም ያገኛል
በዚህ አለም የሚኖር ሰው ሁሉ ሰላምን ይሻል፣ ይፈልጋል ሊያገኛት ግን አይችልም ምክንያቱም ሰላምን
እነርሱ የሚፈልጉት በመጠጥ ቤት ፣ በገንዘብ በመሳሰሉት ነውና በእነዚህ ነገሮች ሰላምን የሚመስል
አእምሮን በማታለል ሰላም ሊገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከህሊና ክስ ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሰው በሀይማኖት
ከኖረ ያለፈ በደሉን በንስሐ አስተሰርዮ ከእግዚአብሔር ስለሚያገኝ ፍጹም ሰላም ያገኛል ከእርሱ የምናገኝው
ሰላም ከአለም እንደምናገኝው አይደለም፡፡
ይህን የመሰለ ተረፈ ደዌ የሌለበት ድህነት ስጋ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፡፡ ባለመድሃኒቶች ቢያድኑም
ደዌውን ፈጽመው አያስለቅቁትም ቢያስለቅቁትም ሌላውን የሰውነት ክፍል ጎድተው ነው፡፡ ፍጹም የሆነ
ድህነተ ስጋን ማግኘት የሚቻለው በሀይማኖት ነው፡፡
መ. ከመከራ ስጋ ይጠብቃል
‹‹ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጉዳይ
እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር›› 1ኛ ጴጥ 4፤15
ለነፍስ
ጌታችን በወንጌል ‹‹ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?›› ማቴ 16፤26
እንዳለ ዋናው የሀይማኖት ጥቅም ወይም አስፈላጊነት ለነፍስ ነው፡፡ ይህንንም በሁለት ነጥቦች እንመልከት
ሀ. ድህነተ ነፍስ
ለድህነተ ነፍስ የመጀመሪያው በር ሀይማኖት ነው፡፡ ጌታችን ‹‹እኔ የበጎች በር ነኝ›› ዮሐ 10፤7 ‹‹እኔ
መንገድና እውነት ህይወት ነኝ›› ዮሐ 14፤6 ‹‹በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም ፤ በማያምን ግን በአንዱ
በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል›› ዮሐ 3፤18፡፡ እያለ አስተምሯል፡፡
የሐዋርያትም ትምህርት እንደጌታችን ነበረ ያለ ሀይማኖት ድህነት እንደማይገኝ አስረግረጠው ተናግረዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ሲላስ የእስር ቤቱን ዘበኛ ‹‹በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰቦችህም
ትድናላችሁ›› ሐዋ 16፤31 ያሉት ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ ሰው ለድህነተ ነፍስ በዚህ ምድር በሚያደርገው
ጉዞም በረከተ ነፍስን እያገኘ የሚቆየው በሀይማኖት ነው፡፡
ለ. ክብረ ነፍስ
ሰው በሀይማኖት ከኖረ ክብረ ነፍስን ያስገኛል፡፡ ይህም ከመዳን በኃላ ከተጋድሎ የተነሳ የሚሰጥ ክብር ሲሆን
ክብሩ በምድርም የሚገባቸውን ያህል ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ይህንን ጌታ በዘሪው ምሳሌ ላይ ‹‹አንዱም መቶ
፣ አንዱንም ስልሳ ፣ አንዱም ሰላሳ ያደርጋል (ያፈራል)›› ሲል ማቴ 13፤23፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ቅዱሳን
በክብረ ነፍስ ከብረው በፀጋ በትሩፋት በልፅገው የሚበላለጡ እንደሆነ ሲናገር ‹‹የፀሐይ ክብር አንድ ነው ፣
የጨረቃም ክብር ሌላ ነው ፣ የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው ፣ በክብር አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ ይለያልና››
1ኛ ቆሮ 15፣41 ይህንም ክብራቸውን የምናቀው (የምንገነዘበው) በሚሰጣቸው ፀጋ ነው፡፡ ይህም አንደ
ሀይማኖት ፅናትና እንደ ተጋድሎ የሚሰጥ ነው፡፡
ጌታችን ይህን ሲናገር ‹‹እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ
ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል›› ማቴ 17፤20 ብሎአል፡፡ በዚህ ፀጋ በክብረ ነፍስ የከበሩ
የእግዚአብሔር ወዳጆች ድውያንን ፈውሰዋል ፣ ሙታንንም አስነስተዋል ፣ ብዙ ተአምራትን አድርገዋል፡፡
እነዚህ ፍጥረታት ከሌሎቹ የሚለዩበት ነገሮች ቢኖራቸውም ዋነኞቹ ግን ሁለት ናቸው፡፡ ከእነዚህም
የመጀመሪያውም ግዕዛነ አእምሮ ወይንም እውቀት የተሰጣቸው መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መላዕክት
ፍፁም የማይሞቱ ፣ ሰው ደግሞ የማትሞት ነፍስ ያላቸው መሆናቸው ነው ስለዚህ የዘለአለም ህይወት
ተስፈኞች ናቸውና ከእግዚአብሔር ጋር በመጣላት ወደ ሲኦል ገሀነም እንዳይወርዱ ሀይማኖትና ምግባር
ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሀይማኖት እንዲኖራቸው ያደረገውም ሞት የማያሸንፈው ባህሪ ይዘው መገኘታቸው ነው
የሰው ሞትም የነፍስን ከስጋ መለየት እንጂ የነፍስ መጥፋት አያመለክትም፡፡
ለ. ምርጫ
በነፃ ፈቃድ ይጠቅመናል የምንለውን መርጠን እንድንሰራ መብቱ ተሰጥቶናል ሌላ ቀርቶ ፈጣሪንም
እስከአለማምለክ ቃሉንም እስካለመስማት ድረስ ሰው መምራጥ ይችላል፡፡
ሐ. ኃላፊነት
የመጨረሻው ደግሞ ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ መርጦ ለወሰነው ውሳኔ ተጠያቂው ወይም ሀላፊነት የሚወስደው
ራሱ ነው፡፡ ሰው ቃለእግዚአብሔርን ላለመስማት ወስኖ በኋላ አልሰማሁምና አይፈረድብኝም የማለት መብት
የለውም፡፡ ቤተ ክርስቶያን የህይወት መንገድ ከፈጣሪ የምታገናኝ የሰማይ ደጅ መሆኗን አምናለሁ እያለ ወደ
ቤተ ክርስቲያን ያልመጣ ሰው እግዚአብሔርን የሸሸ ራሱ ስለሆነ በህይወቱም ችግር ቢደርስበት ራሱ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡ ት.ኤር 31፤34
ሐ. መላዕክት ፍፁም የማይሞቱ ፣ ሰው ደግሞ የማትሞት ነፍስ አላቸው፡፡ ሁለቱም ፍጥረታት የዘላለም
ህይወት ተካፋዮች በመሆናቸው ነው፡፡
የክርስትና ሃይማኖት
የክርስትና እምነት የምንለው በወንጌል ማመን ነው፡፡ ወንጌል ደግሞ የምትናገረው የጌታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ሕይወቱን፣ አኗኗሩን፣ ተአምራቱንና ስራውን ሁሉ ነው፡፡
ለ. ልዩ ነው
1. እምነቱ በአንድ አምላክ ከማመን በላይ ነው በቀድሞው ዘመንም ሆነ በአሁኑ ዘመን የሚኖሩ ብዙ
ፈላስፎች በአንድ አምላክ መኖር ያምናሉ፡፡ የክርስትና ሃይማኖታችንም ከአህዛብ ተለይታ በአንድ አምላክ
የማመኗን ያህል ከአይሁድም ተለይታ በሦስት ገፅ አካላት ታምናለች፡፡ ይህም ‹‹አንድነቱ ሶስትነቱ
የማይከፈለው ፣ ሶስትነቱም አንድነቱን የማይጠቀልለው›› ማለት ነው፡፡
2. ስላሴ በስልጣን ስሩያን ብለን ከማመናችን የተነሳ በተለየ አካሉ ሰው ሆኖ ለተገለጠው አምላክ ማንነት
የምንሰጠው ፍፁም ልዩ ነው፡፡ ‹‹አንተ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ›› ይህም የባህርይ አምላክ ነህ የሚል
ነው፡፡ ይህም የቤተክርስቲያን መሰረት ነው፡፡
ሐ. በር ነው
ወደ ገነት መግቢያው በር ፣ ጽድቅና ድህነትም ማግኛው አንድ ብቻ ነው፡፡ ሰው ሆኖ በተገለጠው በክርስቶስ
ማመን ያለዚህ መንገድ ህግን ቢፈፅሙ ምግባር ትሩፋት ቢሰሩ ሊድኑ አይችሉም፡፡
በክርስቶስ አምኖ ሳይጠመቅ ስጋውን ሳይበላ ደሙን ሳይጠጣ ምስጥራትን ሳይፈፅም ማንም ሊፀድቅ
አይችልም፡፡ ክርስትና ብቸኛና ጠባብ የፅድቅ በር ናት፡፡ ሉቃ 13፤24
1. ቅዱስ፡- እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፡፡ እርሱ ራሱ ‹‹እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› ሲል
ተናግሯል ዘሌ 19፣2 ኢሳ 6፣3፡፡
ዮሐንስ አቡቀለምሲስ (በራዕዩ 16፣7) ‹‹አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህ እውነተኛና
ጽድቅ ነው›› ብሏል
3. አምላከ አማልክት (የአማልክት አምላክ) ፡- እግዚአብሔር አምላክነቱ የባህሪው ነው፡፡ የሰዎች አማልክት
መባል ግን ፀጋ ነው፡፡ የፀጋ አማልክት የሚባሉትም የእግዚአብሔርን ቃል ህዝቡን የሚያስተምሩ መምህራን
ካህናት ናቸው እንጂ ጣኦታት አይደሉም መዝ 81፤6፣ ዮሐ 10፣34
4. የጌቶች ጌታ፡- እግዚአብሔር ጌትነቱ የባህሪው ነው የሰዎች ጌቶች መባል ግን የፀጋ ነው ጌቶች
የሚባሉትም መምህራን ናቸው፡፡ ስለእግዚአብሔር የባህርይ ጌትነት ነብዩ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር እግዚእ
አስተርአየ ለነ›› ይላል መዝ 117፣27፣ ዮሐ 20፣28፡፡
5. ሁሉን ቻይ፡- ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ፈፅሞ የለም ሁሉን ማድረግ ይችላል እግዚአብሔር ራሱ
ለአብርሐም ‹‹ሁሉን ቻይ ነኝ (ኤልሻዳይ)›› ነኝ ብሎ ገልፆለታል፡፡ ዘፍ17፣1 ሉቃ1፣37
6. ሁሉን አዋቂ፡- እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ከመሆኑ በፊት ያውቃል ነገሮች ሁሉ ለመታሰባቸው ፣
ከመሰረታቸው በፊት ያውቃቸው፡፡ መዝ 138፤1-5፣ ዮሐ 2፤5፣ ኤር 17፤10፡፡
7. ዘላለማዊ እግዚአብሔር በዘመናት አይወሰንም፡- ከዘመን በፊት ነበር ፣ ዘመናትንም አሳልፎ ይኖራል፡፡
መዝ 89፤1-2 በጠቅላላ እግዚአብሔር መጀመሪያና መጨረሻ የለውም ራሱ መጀመሪያ መጨረሻ ነውና፡፡
በእርሱ ዘንድ ለውጥ የለም፡፡ ኢሳ 44፤6፡፡
የመለማመጃ ጥያቄዎች
1. ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው)
2. ሃይማኖት በተስፋ የሚረዱት ነው ሲባል ምን ማለት ነው)
3. ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል)
4. የክርስትና ሀይማኖት ልዩ ባህሪያት ምንድን ናቸው)
5. የአማላካችን የልዑል እግዚአብሔር ባሕርያቱ ምን ምን ናቸው)
6. አልፋና ኦሜጋ ምን ማለት ነው)
7. የሃይማኖት አስፈላጊነት ምንድን ነው)
8. የክርስትና ሀይማኖት ልዩ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው)
9. የአምላክ ስሞችን ከነትርጓሜያቸው ዘርዝሩ)
10. የሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ ፣ ምርጫና ኃላፊነት ተሰጥቶታል ስንል ምን ማለታችን ነው)
ልዑል እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን እንዲሁም በእርሱ ውስጥ የሚገኙትን ነገሮች ሁሉ ከምንም ወይም
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣበትን ማለትም የፈጠረበትን ያፈጣጠር ታሪክ በዝርዝር የሚያስረዳ ትምህርት
ሥነ ፍጥረት ይባላል፡፡
በሁለተኛውም ቀን ከበላይና ከበታች ያለውን ውኃ የሚለይ ጠፈርን ፈጠረ ጠፈሩንም ሰማይ ብሎ ጠራው፡፡
በሦስተኛው ቀን ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ተከማችቶ ባሕር እንዲባልና ውሃው አንድ ቦታ ሲከማች
የተገለጸው ደረቅ ቦታ ደግሞ ምድር እዲባል ወስኖ ዘርና ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችና ሳሮችን በምድር ላይ
እንዲበቅሉ አዘዘ፡፡ እንዲሁም ኾነ፡፡
በአራተኛው ቀን ዕለታትን ሳምንታትን ወሮችንና ዓመቶችን እንዲለዩ ተብሎ ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት
ተፈጠሩ፡፡
እንዲሁም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን በላከው መልእክቱም ‹‹ዓለም በእግዚአብሔር አንድ
ቃል እንደተፈጠረ የምናውቀው በእምነት ነው የምናየው ነገር ሁሉ ከምንም እንደተገኘ በእምነት
እናስተውላለን፡፡›› ዕብ 11፤3፡፡
እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሲፈጥር ለእርሱ ምንም የሚያስፈልገው ነገር ኖሮት አይደልም፡፡ በመለኮት ክብሩ
ብቻውን መኖር ሲችል የደግነት ባሕርዩ ኹሉን ፈጠረ፡፡
2.1.1 ትርጉም
ሥነ ፍጥረት ማለት የሁለት ቃላት ጥምር ሲሆን እነርሱም ‹‹ሥነ›› እና ‹‹ፍጥረት›› ናቸው፡፡
‹‹ሥነ›› ማለት ‹‹ሠናይ›› ከሚል የግዕዝ ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ያማረ ማለት ነው፡፡ በዚህም
መሰረት ሥነ ፍጥረት ማለት የተዋበ ያማረ ፍጥረት ማለት ነው፡፡
‹‹ሥነ›› ማለት ‹‹ተንስአ›› ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተስማማ ማለት ነው፡፡ በዚህም
መሰረት ሥነ ፍጥረት ማለት የተስማማ የተግባባ ፍጥረት ማለት ነው፡፡ ስያሜው ሊሰጥ የቻለው አራቱ
ባሕርያተ ሥጋ እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ሲሆኑ በእግዚአብሔር ጥበብና ኃይል ተስማምተው
መኖራቸውን ለማመልከት ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ይህን ዓለም የፈጠረበት ዓላማ ፍጥረታትም የተፈጠሩበት እንደዚህ ነው፡፡ ከሀያ ሁለቱ
ፍጥረታት መካከል ሁለቱ ሕያዋን ሲሆኑ ሀያዎቹ ግን አላፊዎች ናቸው ሁለቱ ሰው እና መላእክት ናቸው፡፡
የእነርሱ የመፈጠር ዓላማ ስሙን ቀድሰው ክብሩን እንዲወርሱ ሲሆን ሌሎቹ ፍጥረታት ግን ልንበላቸው
ልንጠጣቸው ልንሰራባቸው ልንማርባቸው ተፈጥረዋል፡፡
1. እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ
እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ እንደፈጠረ በዕብራውያን 11 ቁ 3 ‹‹ዓለሞች በእግዚአብሔር
ቃል እንደ ተዘጋጀ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን›› በሌላም ስፍራ
‹‹የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራ›› ሮሜ 4 ቁ 17 ተብሏል፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ‹‹የሚታየው ነገር
ከሚታዩት እንዳልሆነ›› እና ‹‹የሌለውን እንዳለ›› የሚሉት ቃላት እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ መፍጠሩን ያስረዳሉ፡፡
እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ በሌላ ስሙ ‹‹ጥንተ ተፈጥሮ›› ይባላል፡፡
2. ግብር እም ግብር
ከተፈጠረ ነገር የተፈጠሩ ከሚባሉት ውስጥ ለምሳሌ የሰው ሥጋ ከአፈር የአዕዋፍ ደግሞ ከውኃ
መፈጠራቸው ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘፍ 1፤20 ዘፍ 2፤7፡፡
የፍጥረታት አገኛኛታቸው
1. በአርምሞ (በዝምታ) ልዑል እግዚአብሔር በአርምሞ (በዝምታ) የፈጠራቸው ፍጥረታት በዕለተ እሁድ
የተፈጠሩ መሬት ፣ ውሃ ፣ ነፋስ ፣ እሳት ፣ ጨለማ ፣ ሰባቱ ሰማያት እና መላዕክት ናቸው፡፡
2. በነቢብ (በመናገር) ልዑል እግዚአብሔር በነቢብ (በመናገር) የፈጠራቸው ፍጥረታት ከእለተ እሁድ
ስምንተኛ ፍጥረት ብርሃን አንስቶ እስከ ዓርብ ሦስተኛ ፍጥረት ድረስ ያሉትን ፍጥረታት በመናገር
ፈጠራቸው፡፡ ለምሳሌ ብርሃን ጠፈር ዕፅዋት እንስሳት … ወዘተ
3. በገቢር (በመስራት) ልዑል እግዚአብሔር በገቢር (በመስራት) የፈጠራቸው ፍጥረታት ብዛት አንድ ነው
እርሱም የሰው ልጅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት እንደ ሰው የከበረ ፍጡር የለም ከዙፋኑ
ወርዶ ከመሬት ጭቃ የሰውን ልጅ በእጁ ፈጥሮታልና፡፡ ዘፍ 1፤26፡፡
ዳግመኛም የሰው ባህርይ መራብ መጠማት ስለሆነ የሚባለው የሚጠጣው ነገርን ይሻል፡፡ እርሱ ግን ይህን
ሁሉ አይሻም፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ይህንን ዓለም የፈጠረው በስድስት ቀናት ነው፡፡ በዘመነ ዮሐንስ በወርሃ መጋቢት 29
ቀን ልዑል እግዚአብሔር 22ቱን ፍጥረታት መፍጠር ጀመረ፡፡ በሚያዝያ 5 ቀን ፍጥረታትን መፍጠር
አቆመ፡፡ ይህ ቀን እንዴት ሊታወቅ ይቻላል ቢሉ በባህረ ሃሳብ ስሌት መሰረት ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ከእለተ እሁድ እስከ እለተ ዓርብ ድረስ የፈጠራቸው ፍጥረታት እያንዳንዱ ቢቆጠሩ
ፍጡር ተናግሮ አይፈጽመውም ነበር ነገር ግን ብዙውን አንድ ወገን እያደረጉ ቢቆጥሩ 22 ይሆናል፡፡ ይህም
ምሳሌነቱ የሀያ ሁለቱ አርስተ አበው ነው፡፡ እነርሱም፡- አዳም ፣ ሴት ፣ ሄኖስ ፣ ቃይና ፣ መላልኤል ፣
ያሬድ ፣ ማቱሳላ ፣ ላሜህ ፣ ኖህ ፣ ሴም ፣ አርፋክሳድ ፣ ሳላ ፣ ኤቦር ፣ ፋሌቅ ፣ ረግው ፣ ሴሩሕ ፣
ናኮር ፣ ታራ ፣ አብርሃም ፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ ናቸው፡፡
እነዚህ ከላይ ልዑል እግዚአብሔር ከእሁድ አንስቶ እስከ አርብ ድረስ የፈጠራቸው ፍጥረታት ናቸው፡፡
ከእነዚህ ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ አሉ ልዑል እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር የማይንቀሳቀሱም አሉ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ በመጀመርያው ቀን እሑድ ስምንት ፍጥረትን ፈጥሮአል፡፡ እነርሱም ነፋስ ፣ እሳት ፣
ውኃ ፣ መሬት ፣ ጨለማ ፣ መላእክት ፣ ብሩህ ሰማይና ብርሃን ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል እያንዳንዱን
ፍጥረታት በዝርዝር እንመለከታልን፡፡
1 አራቱ ባሕርያተ ሥጋ
እግዚአብሔር እሑድ ቀን በመጀመርያው ሰዓት ሌሊት አራቱ ባሕርያተ ሥጋን ፈጠረ፡፡ አራቱ ባህርያተ
ሥጋ የሚባሉት ነፋስ ፣ እሳት ፣ ውኃና መሬት ናቸው፡፡ አራቱ ባህርያተ ሥጋ ሦስት ግብር (ጠባይ)
እንዲኖራቸው አድርጎ ነው የፈጠራቸው፡፡ ይኸውም በባሕርዬ አንድነት ሦስትነት እንዳለ እወቁ ማለቱ ነው፡፡
አራቱ ባሕርያተ ሥጋ አራት የሆኑበት ምክንያት በባሕርዩ አራት ነገሮች እንዳሉት ለማመልከት ነው እኒህም
ባለጠግነት ርኀሩህነት ከሃሊነት እና ፈታሒነት ናቸው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ባለጠጋ ነኝ ሲል መሬትን ፈጠረ ሀብት ሁሉ ከመሬት ይገኛልና ሌላው ደግሞ መሬት
ሁሉን ቻይ ናት የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ችላ ትኖራለች እንደዚሁም ሁሉ ልዑል እግዚዘብሔር ሁሉን
ችሎ ታግሶ ለሁሉ ሀብቱን ሰጥቶ ይኖራል፡፡
ከሃሊነት ማለት ቻይነት ማለት ነው፡፡ እሳት በተነሳ ጊዜ ገደልና ባሕር ካልከለከለው በስተቀር ሁሉን
ማጥፋት ይቻለዋል፡፡ እግዚአብሔርም ቸርነቱ ካልከለከለው በቀር ሁሉን ማጥፋት ይቻለዋል፡፡
‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም›› ሉቃ 1፤37፡፡
ፈታሒነቱ (ፍርዱ) በነፋስ መመሰሉ ገበሬ አዝመራውን አጭዶ ከአውድማው ላይ ወቅቶ በመንሽ ባነሳው
ጊዜ በነፋስ ኃይል ፍሬ ከገለባው ገለባውም ከፍሬ ይለያል፡፡ ልዑል እግዚአብሔርም በፍርዱ ጻድቃንን ከኃጣን
ኃጣንን ከጻድቃን ይለያል፡፡ ‹‹መንሹም በእጁ ነው አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል ስንዴውንም በጎተራ
ይከታል ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል›› ሉቃ 3፤17
ልዑል እግዚአብሔር እነዚህን አራቱ ባህርያተ ሥጋን በአንዴ በሙላት (በብዛት) አልፈጠራቸውም ጥቂት
እሳት ጥቂት መሬት ጥቂት ነፋስ ጥቂት ውሃ ፈጥሮ ብዙ ተባዙ ብሎ በቃሉ ቢያዛቸው በዝተው ተባዝተው
ህሊና እግዚአብሔር የመጠነላቸው ድረስ ደርሰው ቆመዋል፡፡ በከሃሊነቱ ፀንተው ራሳቸውን ያዙ፡፡
እግዚአብሔር ካዘዘው ቅንጣት ታክል አልጨመሩም አልቀነሱም፡፡
አምላካችን እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩት ግብር ይዘው የፈጠራቸው ፍጥረታት አንዱ ከአንዱ ጋር ቢጣሉ
ያስታርቃቸዋል በእነዚህ ባሕርያቸው
እሳት በውዕየቱ (በማቃጠሉ) (በሙቀቱ) ከነፋስ በብሩህነቱ (በብርሃናዊነቱ) ከውሃ በይቡስነቱ ከመሬት
አዋህዶ አስማምቶ ትቶታል፡፡
ውሃን በብሩህነቱ (በብርሃናዊነቱ) ከእሳት በቆሪርነቱ (በቀዝቃዛነቱ) ከነፋስ በርጡቡነቱ (በርጥብነቱ)
ከመሬት አስማምቶታል፡፡
መሬትም በይቡስነቱ (በደረቅነቱ) ከእሳት በጽሉምነቱ (በጨለማነቱ) ከነፋስ በርጡቡነቱ (በርጥበቱ) ከውሃ
እንዲህ አድርጎ አስማምቶታል፡፡
በተጨማሪም እነዚህ አራቱ ባህርያተ ሥጋ እርስ በእርሳቸው እንዲሸናነፉ አድርጎ ነው የፈጠራቸው ይህም
እንዲህ ነው እሳት ውሃን ያጠፋዋል ውሃ ደግሞ እሳትን ያጠፋዋል፡፡ እንዲሁም ነፋስ መሬትን ይበትነዋል
መሬት ደግሞ ነፋስን ይገድበዋል፡፡
1 ጨለማ
ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሁድ ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል ጨለማ በአምስተኛ ደረጃ የተፈጠረ
ነው የተፈጠረውም በዝምታ ነው ስለምን በዝምታ ፈጠረ ቢሉ የሚሰማ በሌለበት መናገር አይረባምና ሲል
ነው፡፡ ሌላው የሚሰሙ መላዕክት አልፈጠረም እና በዝምታ ጨለማን ፈጠረ፡፡ ይህ ጨለማ በዚህ ዘመን
ካለው ጨለማ ጋር የሚወዳደር አይደለም ይህ ጨለማ በውስጡ ምንም አይነት ብርሃን የለውም ድቅድቅ
ጨለማ ነበር ታዲያ አሁን ያ ጨለማ የት ሄደ ያሉ እንደሆነ አስቀድሞ ዲያቢሎስ በበደለ ጊዜ ተጠቅልሎ
ወደ ሲኦል ወርዶበታል፡፡ ስለምን ጨለማን ፈጠረ ያሉ እንደሆነ ባትፈልጉኝ ባትመረምሩኝ አልገኝም ሲል
ጨለማን ፈጠረ፡፡
2 ሰባቱ ሰማያት
ሰባቱ ሰማያት በሌላ አጠራር ብሩህ ሰማይ በመባል ይታወቃል፡፡ አጠራሩ ቀና ብለን ከምንመለከተው ሰማይ
(ጠፈር) የተለዩ ሰባቱ ሰማያትን ለማመልከት ያገለግላል፡፡ ሰማያት ሰባት ስለመሆናቸው ‹‹የሰማይ ምጥቀቱ
ሳይታይ ሰባቱ ሰማያት ሳይቆጠሩ›› ዕዝ 4፤4
በግዕዝ በዕብራይስጥ
ሀ. ጽርሐ አርያም
ከሰማያት ሁሉ በላይ ናት፡፡ ከእርሷ በላይ ሌላ ሰማይ የለም፡፡ ዳርዋና መጨረሻዋን የሚያውቅ እግዚአብሔር
ብቻ ነው፡፡ ጽርሐ አርያም በመንበረ ስብሐት ላይ እንደ ጠፈር ሆና ተፈጥራለች፡፡
መንበረ መንግሥት መንበረ ብርሃን ፣ መንበረ ስብሐት እና መንበረ ጸባዖት የተባሉ ሌሎች ስሞች አላት፡፡
አሰራሯም እንደ ቤተ መቅደስ ነው፡፡ በዚህች ሰማይ ላይ ሥላሴ ለጻድቃን ለሰማዕታት እና ለመላእክት
በዘፈቀደ ሁነው ይታዩበታል፡፡
በዘፈቀደ ሁነው ይታዩበታል ሲባል ለምሳሌ ለነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር በአዳራሽ እንደተቀመጠ ንጉስ
ሆኖ ተገልጦለታል፡፡ ‹‹ንጉስ ኦዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔር በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ተቀምጦ
አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር›› ኢሳ 6፤1
ሐ. ሰማይ ውዱድ
ሰማይ ውዱድ በኪሩቤል ጀርባ ላይ የተዘረጋ ሆኖ ለመንበረ መንግስት እንደ አዳራሽ ወለል ነው፡፡በሌላ
አገላለጽ መንበረ መንግስት እንደ ዙፋን የተዘረጋበት ሰማይ ነው፡፡ ‹‹ከእንስሶች (ኪሩቤል) ራስ በላይ
የሚያስፈራ በረዶ የሚመስል የጠፍር አምሳያ በራሳቸው ላይ ተዘርግቶ ነበር›› ሕዝ ምዕ 1 ቁ 22፡፡
መ. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አሠራሯ እንደ ቤተ መቅደስ ያለ ነው፡፡ አስራ ሁለት ደጆች አሏት፡፡ ብርሃኗ ከሌሎች
ሰማያት ልዩና የተዋበ ነው፡፡ አዕማዶቿ የብርሃን ክዳኗ የብርሃን መርገፏ የብርሃን የሆነላት ሰማይ ናት፡፡
በሰባት የእሳት መጋረጃና በሰባት የእሳት አጥር የታጠረች ናት፡፡
በጉኖቿም የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም በመድረኳም የአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ስም በምሶሶዋ
የጻድቃንና የሰማዕታት ስም ተጽፎበታል፡፡
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጧ ቁመቷም ወርዷም እኩል የሆነ ከብርሃን ተሰራች ‹‹ታቦር ዘዶር›› የምትባል
የእመቤታችን ምሳሌ የሆነች ታቦት የተቀመጠባት ሰማይ ናት፡፡ ‹‹ታቦት ዘዶር እንተ ይእቲ እግዝትነ
ማርያም›› እንዲል አባ ሕርያቆስ
ከዚህ በታች የተቀሩት ሦስቱ ከተሞች ዓለመ መላእክት (የመላእክት ከተሞች) ይባላሉ፡፡
ሠ. ኢዮር
ረ. ራማ
ሰ. ኤረር ናቸው፡፡
እነዚህን ሦስት የመላእክት ከተሞች ሲፈጥር ከላይ ከሰማይ ውዱድ አስከ ጽርሐ አርያም ድረስ እርሱ ባወቀ
ዘግቶታል እነዚህን ግን ሲሰራ ውስጥ ለውስጥ እንዲገናኙ ግን ወደ ላይ ከሰማይ ውዱድ እስከ ጽርሐ
አርያም ያለውን የሚያሳይ ምንም መስኮት አልሰራላቸውም ብቻ ወጥ ድፍን አርጎ ሰርቷቸዋል ስለምን ቢባል
በቀጣይነት የሚፈጥራቸው ፍጥረታት በነዚህ ሰማያት ያሉ መላእክት ምሥጢሩን እንዳያዩ ነው፡፡ ሌላው
እርሱ ሲሰራ አግዘነዋል ብለው እንዳይስቱ ነው፡፡
3 መላእክት
አፈጣጠራቸው
መላእክት በእለተ ዕሁድ የተፈጠሩ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መላእክትን በመቶ ነገድ በአስር አለቃ በአስር ከተማ
በሦስቱ ሰማያት ፈጥሮ አስፍሮአቸዋል፡፡ መላእክት ከምንም ነገር የተፈጠሩ ሲሆን አንዳድ ወገኖች የዳዊት
መዝሙርን በመጥቀስ መዝ 10፤3 ከእሳት እና ከነፋስ ተፈጠሩ ይላሉ፡፡ ዳዊት ያለው ተልዕኳቸውን
ለማመልከት ነው፡፡ ነፋስ ፈጣን ነው መላእክትም በተልዕኳቸው ፈጣኖች ናቸው፡፡ እሳት ረቂቅ ነው
መላእክትም ረቂቃን ናቸው፡፡ ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል›› መዝ
103፤4
አሰፋፈራቸው
እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ በሦስቱ የመላእክት ከተሞች በኢዮር በራማና በኤረር በከተማ
አሥር በነገድ መቶ አድርጉ አስፍሯቸዋል፡፡
4 ብርሃን
ብርሃን በዕለተ እሁድ በስተመጨረሻ በስምንተኛነት የፈጠረው ፍጥረት ነው፡፡ ብርሃን የተፈጠረው በመናገር
ነው፡፡ በዚህም በዕለቱ ብቸኛው በነቢብ የተፈጠረ ፍጥረት ነው፡፡ ብርሃን በነቢብ (በመናገር) ከተፈጠረበት
ምክንያት አንዱ የሚሰሙ (ሰማዕያን) መላእክት የተፈጠሩ ስለሆነ ብርሃንን በመናገር ፈጠረው፡፡
ታሪኩም እንዲህ ነው እግዚአብሔር አምላክ መላእክትን ከፈጠረ በኋላ ተሰወራቸው ከዚህም በኋላ መላእክት
በተፈጥሮአቸው ፈጣሪያቸውን መመርመር ጀመሩ አንዱ የአንዱን ትንፋሽ በተሰማሙ ጊዜ ከየት መጣህ
ማን ፈጠረህ በማለት እርስ በእርሳቸው መጠያየቅ ጀመሩ ፤ ማን ፈጠረን በማለት መመራመር ጀመሩ፡፡ ያን
ጊዜ ሳጥናኤል ከሁሉ በላይ ነበርና ቀና ብሎ ቢያይ ሁሉ ከሱ በታች ናቸው ከዚያም እኔ ፈጠርኳችሁ አለ
ያን ጊዜ መላእክቱ አንተማ አልፈጠርከንም አንተ አኛን ከፈጠርክ እኛ ደግሞ ከኛ በታች ያሉትን ፈጥረናል
ማለት ነው አሉት፡፡ ያን ጊዜ እግዚአብሔር በዙፋኑ ሆኖ ቢገለጥ ሰባቱ ሰማያት ተናወጠ መላእክቱ እጅግ
ተረበሹ ተንቀጠቀጡ ያን ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ንቁም በበሕላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› የፈጠረን እራሱ
እስኪገለጥ ባለንበት እንጽና ብሎ መላእክትን አረጋጋ ያን ጊዜ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሁሉን መላእክት
እያቀፈ ይጠይቃቸው ጀመር ማን ፈጠራችሁ ይህ ሁሉ ሰማይ የኔ ቤት ነው ማን እዚህ አስገባችሁ ብሎ
ጠየቃቸው እነርሱም ይህን ሁሉ አንተ ታውቅ እንደሆነ እኛ አናውቅም አሉት ያን ጊዜ ብርሃን ይሁን ብሎ
አዘዘ ወድያው በስተምስራቅ ተፈጥሮ የነበረ እንደ ምንጭ እየፈሰሰ እየጎረፈ ሁሉ ዓለማትን አጥለቀለቀ፡፡
በዚህ ዕለት አምላካችን እነዚህን ስምንት ፍጥረታት ፈጥሮአል እሁድ ማለት አሃደ ከሚል የግእዝ ግስ
የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረገ ማለት ነው፡፡ ሥነ ፍጥረት አንድ ተብሎ የጀመረው በዚህ ቀን
ስለሆነ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሰኞ ዕለት እሁድ የፈጠረውን ውኃ ለሦስት ከፍሎ አንዱን እጅ ውኃ ከኤረር በታች አሰፈረው፡፡
ስሙንም ሐኖስ አለው፡፡ ይህንን ብጥብጥ ውኃ ባቢል በሚባል ነፋስ ተሸካሚነት ከጠፍር በላይ አሰፈረው፡፡
ሁለተኛውን እጅ ከሐኖስ በታች አሰፈረው ስሙንም ጠፈር አለው፡፡ ይህም የረጋ ውሃ ነው፡፡ ሦስተኛውን
እጅ ደግሞ በዚህ በምድር አሰፈረው ስሙንም ውቅያኖስ አለው፡፡ ሌላው እግዚአብሔር ጠፈርን የፈጠረው
የሰው ልጅ ጠፈርን እያየ ሰማያዊ ርስት እንዳለው እዲያውቅ እና ተስፋ እንዲያደርግ እንዲሁም በዕለተ
ረቡዕ ለሚፈጥራቸው ለፀሐይ ለጨረቃ ለከዋክብት ማህደር መመላለሻ እንዲሆኑ ነው፡፡
እግዚአብሔር በዕለተ ሰኞ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ካዘጋጀ በኋላ በመቀጠል ምድር የተበጠበጠ እርጎ
መስላ ነበር፡፡ እናም ያንን ማስታካከል ጀመረ መሬትን ለያት ውሃውን ወደታች መሬትን ወደ ላይ አወጣት
እንደ አይብና እንደ አጓት ለይቶአቸዋል ከዚያም ለውሃው ውስጥ መንገድ ሰርቶ ትቶታል፡፡ ምድር ግን
ተራራውን ኮረብታውን የምትወልድ አስክትሆን ድረስ አግዝፎ አወፍሮ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን
እስከ ደቡብ ጎዝጉዞ ዘርግቶ አንጥፎ ከውሃ በላይ እንደ መርከብ አጽንቶታል፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር
ምድርን ዙርያዋን ሁለት እጅ አድርጎ ከፈላት የወዲያኛውን አንዱን እጅ ናጌብ አለው፡፡ የወዲያኛውን
ሁለተኛውን እጅ አድማስ አለው፡፡ በናጌብ እና በአድማስ መካከል ያለውን ጉድጓድ ውሃ ሞልቶበት ውቅያኖስ
አለው፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ታላቁን ተራራ በታላላቁ ሚዛን ታናናሹ ተራራ በታናናሹ ሚዛን
ይመዘን ብሎ አዘዘው ያን ጊዜ ሁሉም በሚዛኑ ተመዝኖ ደጋው ያደላድል ቆላው ይጉደል ወንዙ ይከፈል
ብሎ አዘዘው ከዚያም እግዚአብሔር ከዚህ ከመሬት በታች ያሉትን ፍጥረታት ለእሳት ለነፋስ ለበርባኖስ
ለጨለማ ስድስት በምስራቅ ስድስት በምዕራብ ስድስት በሰሜን ስድስት በደቡብ በአጠቃላይ ሀያ አራት
መስኮት አወጣላቸው በእነዚህም በእነዚህም ሁለት ሁለት መላእክት ሰይፍ እያስያዘ ጠባቂ አቁሞአል፡፡
በመቀጠልም እግዚአብሔር ከእሳት በታች ያሉትን ነፋሳት አስራ ሁለት አለቆች አደረገላቸው ፤ አራቱን
አለቆች ነፋሳተ ምሕረት ስምንቱ አለቆች ነፋሳተ መዓት ናቸው፡፡ በሁለቱ ነፋሳተ መዓት መሐከል አንድ
አንድ ነፋሳተ ምህረት እያደረገ ሰርቶአቸዋል፡፡ በመቀጠልም አስራ ሁለቱን የእሳት አለቆች ከአስራ ሁለቱ
መስኮቶች አስራ ሁለቱን የነፋሳት አለቆች ከአስራ ሁለቱ መስኮቶች ወጥተው ምድር እንዲያደርቋት አዘዘ ያን
ጊዜ እነዚህ የእሳት እና የነፋሳት አለቆች ከየመስኮታቸው ወጥተው ምድርን የምስራቁ ወደ ምዕራቡ የሰሜኑ
ወደ ደቡቡ ወዲያ ወዲህ ቢመላለሱ ተራራው ኮረብታው ረጋ ፀና ዲንጋዩ በብረት የሚቆፈር ሆነ ምድር ግን
ገና በእግዚአብሔር ቃል ዘር የሚወድቅባት ናትና እጅግም በጣም አልደረቀችም በጣምም አልረጠበችም፡፡
ውሃ ምጥጥ አድርጋ ነበር ልክ እንደ ግንቦት እንደ ሰኔ ማሳ ያማረች የለሰለሰች ሆነች፡፡ ሌላው ደግሞ
ከምድር ጋር ተቀላቅሎ የነበረውን ውሃ በሦስት እጅ ከፍሎ አንዱን እጅ ከውቅያኖስ ቀላቀለው ሁለተኛውን
እጅ ከምድር በታች አደረገው ሦስተኛውን ደግሞ በምድር ላይ ባሕር ወንዝ ሐይቅ ኩሬ አደረገው፡፡ ለምድር
ሦስት ስም አላት ከውሃ ሳትለይ ፀብር (ጭቃ) ደርቃ ስትፍታታ መሬት ከውሃ ከተለየች በኃላ አፈር ትቢያ
ትባላለች፡፡
የዕለተ ሰኞ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰኞ (ሰኑይ) ማለት ሁለት ማለት ነው፡፡ እንግዲህ በሁለተኛው ቀን
ዘጠኝ ፍጥረታት ደርሰዋል፡፡ ሰኞ ማለት ለፍጥረታት ሁለተኛ ለቀመር ሰባተኛ ለፀሐይ ስድስተኛ ማለት
ነው፡፡
እግዚአብሔር በዕለተ ማክሰኞ (ስሉስ) የፈጠራቸው ፍጥረታት ብዛት ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ገነትን በምስራቅ አቅጣጫ ዘፍ 2፤8 ብሔረ ሕያዋንን በሰሜን አቅጣጫ ብሔረ
ብጹአንን በደቡብ አቅጣጫ መሬትን በመሐል ሲዖልን በምዕራብ አቅጣጫ እነዚህን አምስት አለማት አዘጋጀ፡፡
ምድርም ከተደላደለች በኋላ ጉበት መስላ ቢያያት ‹‹ምድር ዘር የሚሰጥ ሣርና ቡቃያ ውጣ›› ብሎ ከላይ
የዘረዘርናቸውን የዕለቱን ሦስት ፍጥረታት ፈጥሯል፡፡ በመቀጠልም እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ብዙ ዕፆችን
አበቀለ ከእነሱም መካከል ዕፀ ሕይወትን በመሐል ገነት አበቀለ ይህች ዕፀ ሕይወት በጣም ረጅም ቁመት
ፍሬዋ ደግሞ እንደ ሮማን ፍሬ ተነባብሮ ከታች እስከ ላይ ድረስ የሞት ነበረች፡፡ ከዚችም ከዕፀ ሕይወት ስር
ማየ ሕይወት አወጣ ማየ ሕይወት ከወተት ሰባት እጥፍ ትነጻለች ከማር ከስኳር ሰባት እጥፍ ትጣፍጣለች፡፡
በዚህች ዕፀ ሕይወት በአራቱም መአዘን አራቱን ዓብይ ዕፅዋት አኖረ፡፡ ከዚያም አራቱን ዓብይ አፍላጋት
(ወንዞች) አወጣ የነዚህም ስማቸው ግዮን ፣ ኤፍራጥስ ፣ ኤፌሶንና ጤግሮስ ይባላሉ፡፡ እነዚህም ገነትን
ወዲያ እና ወዲህ እንደ መስቀል ተመላልሰው ያጠጥዋታል፡፡ ይህች እለት በእመቤታችን ትመሰላለች፡፡ ያለ
ዘር ስላፈራች እነዚህን ሁሉ ፍጥረት ስላስገኘች፡፡
የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረታት እነዚህ ናቸው፡፡ ማክሰኞ (ስሉስ) ማለት ለፍጥረታት ሦስተኛ ለቀመር አንደኛ
ለፀሐይ ሰባተኛ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ፍጥረታት አስራ ሁለት ደርሰዋል፡፡
እግዚአብሔር በዕለተ ረቡዕ የፈጠረው ፍጥረት ብዛት ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት
ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ፍጥረታት ከምን ፈጠራቸው ቢሉ ፀሐይን ከእሳት እና ከነፋስ አደረገ ይህም
ይታወቅ ዘንድ በእሳትነቷ ትሞቃለች በነፋስነቷ ትሔዳለች፡፡ የተቀሩትን ደግሞ ከውሃና ከነፋስ ፈጥሯቿል
ይህም ይታወቅ ዘንድ በውሃነታቸው ይቀዘቅዛሉ በነፋስነታቸው ይሔዳሉ፡፡
ከዚህም ሌላ እግዚአብሔር በዕለተ ሰኞ በሰራው ጠፍር ላይ በሦስት ኬክሮስ በሦስት መዓረግ ዝቅ አድርጎ
በምስራቅ በኩል ጨረቃን በምዕራብ በኩል ፀሐይን ፈጥሯል፡፡ ለፀሐይ መዓልቱን (ቀኑን) ለጨረቃ ሌሊቱን
አስገዛ፡፡ ይህን ማድረጉ ለፍጥረቱ አስቦ ነው ሀያ አራቱንም ሰዓት ፀሐይ ብትገዛ ፍጥረት በሙቀት ብዛት
በቀለጠ ነበር እንደገና ሀያ አራቱንም ሰዓት ለጨረቃ ቢያስገዛት ፍጥረት በቅዝቃዜ በውርጭ ባለቀ ነበር ፤
ሁሉም ተቻችለው እንዲኖሩ አደረጋቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ ቀንና ሌሊቱን ካስከዛ ለከዋክብትስ ምንን አስገዛ
ቢሉ አራቱን ወቅቶች ነው፡፡ እነዚህም ክረም በጋ ፀደይ መፀው ናቸው፡፡ መዝ 135፤8-9 ከዋክብት አራት
አለቆች አሏቸው እነዚህም፡-
1. ምልክኤል
2. ሕልሜልሜሊክ
3. ምልኤል
4. ናርኤል ናቸው፡፡
1. መፀው (ናርኤል)
ከመስከረም 26 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ያለው ወቅት መፀው ይባላል፡፡ በመፀው ሰልጥኖ የነበረው ቁር
ወረታች ተቀብሮ የከረመው ሙቀት ወደ ላይ ሲል ከታች ሙቀት ከላይ ዝናብ ሲመታው አዝዕርት አትክልት
ዕፅዋት ያድጋሉ ይገዝፋሉ ያብባሉ በዚህ ወቅት ደግሞ ናርኤል ይመግበዋል (ይገዛዋል)፡፡
2. ሀጋይ (ምልኤል
ከታህሳስ 26 እስከ መጋቢት 25 ድረስ ያለው ወቅት ሀጋይ ይባላል፡፡ በሀጋይ ሰልጥኖ የነበረው ብርድ ፈጽሞ
ሲጠፋ ተቀብሮ የነበረው ሙቀት ሲወጣ ከሙቀቱ ፅናት የተነሳ አዝዕርት አትክልት ይደርቃሉ ታጭደው
ተወቅተው በጎተራ ይገባሉ በዚህ ወቅት ምልኤል ይመግበዋል (ይገዛዋል)፡፡
3. ፀደይ (ምልክኤል)
ከመጋቢት 26 እስከ ሰኔ 25 ድረስ ያለው ወቅት ፀደይ ይባላል፡፡ በፀደይ ሰልጥኖ የነበረው ሙቀት ወደ ታች
ተቀብሮ የነበረው ብርድ ወደ ላይ ሲወጣ ከላይ ሙቀቱ ከታች ቅዝቃዜ ሲመታው ምድር ትረሰርሳለች፡፡
በዚህ ወቅት ደግሞ ምልክኤል ይመግበዋል (ይገዛዋል)፡፡
4. ክረምት (ህልሜልሜሌክ)
ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ ያለው ወቅት ክረምት ይባላል፡፡ በክረምት የፀሐዩ ሙቀት ይጠፋል
ከውሃው ብዛት ከምንጩ ጽናት የተነሳ ምድር ፈረስ ፈረስ ናድ ናድ ትላለች፡፡ በዚህ ወቅት ህልሜልሜሌክ
ይመግበዋል (ይገዛዋል)፡፡
እነዚህ የከዋክብት አለቆች እነዚህን ወቅቶች እንደዚህ እያደረጉ ይመግባሉ (ይገዛሉ) ግን የቀን አገዛዛቸው
እያንዳንዱን ስንቆጥር ዘጠና ቀን ነው፡፡ ከጳጉሜ አምስቱን ቀን አንድ አንድ ሲጨመርላቸው ዘጠና አንድ ቀን
ይመጣል፡፡
እነዚህ የዕለተ ረቡዕ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ረቡዕ ማለት ለፍጥረት አራተኛ ለቀመር ሁለተኛ ለፀሐይ አንደኛ
ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር በዕለተ ሐሙስ ምን ፍጥረት ፈጠረ ቢሉ በዕለተ ሐሙስ ባህር ሕያውን (ሕይወት ያላቸው)
ፍጥረታትን (እንስሳትን) ታስገኝ ብሎ አዘዘ በዛን ጊዜ ሦስት ፍጥረታትን ባሕር አስገኘች፡፡ እነዚህም፡-
1) በእግር የሚሽከረከሩ
2) በክንፍ የሚበሩ
3) በደረት የሚሳቡ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ፍጥረታት በባሕር (በውቅያኖስ) ተወስነው የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ
ፍጥረታት ናቸው፡፡ አፈጣጠራቸውም ከአራት ባሕያርተ ሥጋ ነው፡፡ በሐሙስ ፍጥረት ደመ ነፍስ የሌላት
ባህር በደመ ነፍስ ሕያዋን ሆኑ ፍጥረታት ማስገኘቷ ጌታም ፍትወት እንስሳዊት ከሌለባት ከእመቤታችን
የመገኘቱ ምሳሌ ነው፡፡
የዕለተ ሐሙስ ፍጥረታት እነዚህ ሲሆኑ ሐሙስ ማለት አምስተኛ ዕለት ማለት ነው፡፡ ለፍጥረታት
አምስተኛ ለቀመር ሦስተኛ ለፀሐይ ሁለተኛ ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር በዕለተ አርብ የፈጠራቸው ፍጥረታት አራት ናቸው፡፡ በዕለተ ሐሙስ ባህርን እንዳዘዘ ሁሉ
በዕለተ አርብ ደግሞ መሬት(የብስን) ሕያዋን(ሕይወት ያላቸውን) ፍጥረታ በየወገኑ ታወጣ ዘንድ አዘዛት
መሬትም ሦስቱን ፍጥረታት በየወገኑ አስገኘች፡፡ እነርሱም፡-
1. በእግር የሚሽከረከሩ
2. በክንፍ የሚበሩ
3. በደረት የሚሳቡና
4. ሰው ናቸው፡፡
በዚህ ዕለት በስተመጨረሻ በአራተኝነት እግዚአብሔር እንዲህ አለ ‹‹ኑ እንውረድ ሰውን እንደ መልካችን
እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ፡፡›› ዘፍ 1፤25 ሥላሴ እስካሁን ድረስ ያሉትን ፍጥረት የፈጠሩት በዝምታ
በመናገር ነበር አሁን ግን ከሰማይ ወርደው በእጃቸው አክብረው አዳምን ፈጠሩት፡፡ አዳም የተፈጠረው
ከአራቱ ባህርያተ ሥጋ እና ከሦስቱ ባህርያተ ነፍስ ነው፡፡
2.2.8 የሰው ልጅ
ሰው ማለት ሰብ ከሚል የግዕዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም ሰባት ማለት ነው፡፡ ሰባት የተባለበት
ምክንያት ሰው ከሰባት ነገሮች የተፈጠረ ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህም ባህርያት ከአራቱ ባህርያተ ሥጋ ከሦስቱ
ባህርያተ ነፍስ ናቸው፡፡
አራቱ ባህርያተ ሥጋ
መሬት
እሳት
ነፋስ
ውሃ ናቸው፡፡
ሕያዊት
ልባዊት
ነባቢት
አዳም እና ሔዋን
አዳም ማለት እጅግ የልረዘመ እጅግም ያላጠረ መካከለኛ ይህ ቀረ የማይባል መልከመልካም ማለት ነው፡፡
ሔዋን አዳም ስም ሲያወጣላት አጥንትሽ ካጥንቴ ስጋሽ ከስጋዮ ይቼ ከወንድ ተገኝታለች ስም ሴት ትባል
አላት ቆይቶ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሔዋን ትባል አላት፡፡
የሰው አፈጣጠር ከእሱ ቀደም ብለው ከተፈጠሩት ፍጥረታት ይለያል ይከብራል፡፡ ዘፍ 1፤25 ‹‹ኑ እንውረድ
ሰውን እንደመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር›› ብለው ሥላሴ ተናግረው ሰውን በመልካቸው እንደ
ምሳሌያቸው ፈጠሩ ፤ ሰው መልኩ ሥላሴን ይመስላል፡፡ በሚያዚያ 5 ቀን በዕለተ አርብ በ4 ሰዓት አዳም
ተፈጠረ፡፡ አዳም የተፈጠረበት ቦታ ኤልዳ በምትባል በማዕከላዊ ምድር ተፈጠረ፡፡ ከተፈጠረ በኋላ በአርባኛው
ቀን ወደ ኤዶም ገነት ገባ፡፡ አዳም ከተፈጠረ ከስምንት ቀን በኋላ ሔዋን ጎኑ ተፈጠረች፡፡ እግዚአብሔር
ሔዋንን ሲፈጥራት በአዳም ላይ እንቅልፍ ጥሎበት ከግራ ጎኑ አንድ አጥንት ወስዶ ነው፡፡ ሐዋን በተፈጠረች
በሰማንያኛው ቀን ወደ ኤዶም ገነት ገባች፡፡ አዳም የተፈጠረው የ30 አመት ጎልማሣ ሲሆን ሔዋን ደግሞ
ስትፈጠር የ15 አመት ቆንጆ ነበረች፡፡ አዳምና ሔዋን በኤዶም ገነት ውስጥ የኖሩት ለ7 አመት ከ3 ወር
ነው፡፡
አዳምና ሔዋን ወደ ገነት የገቡት አዳም በተፈጠ በ40 ቀን በመላእክት አጃቢነት ሔዋንም በተፈጠረች በ80
ቀን እንዲሁም መላእክት አጃቢነት ወደ ኤዶም ገነት ገብተው ይኖሩ ነበር፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በኤዶም
ገነት 3 ዕፆችን አስቀምጦ ነበር፡፡ አንዱን ብላ ፣ አንዱን አትብላ ብሎት አንዱን ደግሞ ሰውሮት (ብላም
አትብላም አላለውም) ነበር፡፡ ብላ ያለው በኤደን ገነት ያሉትን ዕፅዋት ሁላ ሲሆን ፤ አትብላ ያለው ደግሞ
ዕፀ በለስን ነው ፤ ሦስተኛው ልዑል እግዚአብሔር የሰወረው ዕፀ ሕይወትን ነው አዳም አትብላ ያለውን ዕፅ
ሳይበላ ትዕዛዙን ጠብቆ ቢሆን ኖሮ ከዕፀ ሕይወት በልቶ ታድሶ ኢየሩሳሌም በገባ ነበር፡፡ ልዑል እግዚአብሔር
አዳምን ዕፀ በለስን አትብላ ያለው የእርሱን ገዢነት የነርሱን ተገዢነት ለማሳወቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ አዳምን የአራዊት ሁሉ ጌታ አድርጎ ሹሞት ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ተሳስበው ከአዳም
ዘንድ እየመጡ ይባረኩ ነበር፡፡ እርሱም ለእያንዳንዳቸ ስም ያወጣላቸው ነበር፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እንስሳት አራዊት ሁሉ እንደልማዳቸው ተሰብስበው ሔደው አርደህ ብላን አልበህ ጠጣን
አሉት ፤ እርሱም ምን አጥቼ ጌታዬ ሁሉን ብላ ሁሉን ጠጣ ብሎ ሰጥቶኛል ካንድ ዕፅ በስተቀር የከለከለኝ
የለም፡፡ እናንተስ ባላችሁበት ያብዛችሁ ያርባችሁ ብሎ አሰናበታቸው፡፡ ዲያብሎስም ከመንገድ ጠብቆ
የትደርሠው እንደመጡ ጠየቃቸው እነርሱም ከጌታቸው ከአዳም ዘንድ እንደ ሆነ ነገሩት፡፡ እርሱም እንዴት
ነው አላቸው እነርሱም ነገሩት፡፡ እግዚአብሔር በገነት ያሉትን ነገሮች እንዲመገብ እፀ በለስን እንዳይበላና
እርሱን ከበላ የሞት ሞትን እንደሚሞት ነግሮታል አሉት፡፡ ዲያቢሎስ ይህን ሲሠማ አዳምን የሚያስትበትን
መንገድ መፈለግ ጀመረ ያን ጊዜ እባብ እየተቻኮለች መጣች እርሱ ባለበት መንገድም ስታልፍ ዲያቢሎስ
ወዴት እንደምትሄድ ጠየቃት እርሷም ጌታዬ አዳም ዘንድ ነው የምሄደው አለችው፡፡ ዲያቢሎስም እባብን
አብሬሽ ልሂድ አላት በዛን ጊዜ እባብ ፈቀደችለት አብረውም ሲሄዱ ዲያቢሎስ እንዲህ አላት ‹‹እባብን እስከ
ገነት ተራራ ድረስ ልዘልሽ አንቺ ደግሞ ከዚያ በኋላ ታዝይኛለሽ›› ብሎ አዘላት በዛን ጊዜ ዲያቢሎስ እባብን
አዝላ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ከገነት ተራራ ከታች ሲደርሱ በይ በተራሽ እዘይኝ ብሎ ከገነት በር ሲደርሱ ውረድ ባለች
ጊዜ እንደ ቅቤ ቀልጦ በሰውነቷ ተዋሃዳት፡፡
ተዋሃዳት የሚለው
ዲያቢሎስ ቀደም ብሎ እባብን ሲያናግራ አልተስማሙም ነበር እርሷ መልከመልካም አቋም እንደ ግመል
አይነት ነበረች እርሱ ደግሞ መልከ ጥፉ ነበር፡፡ በተነጋገሩ ሰዓት ምን ይላት ነበር እዘይኝ እና እርሱ ዘንድ
ስንቀርብን የኔ ንግግር ያንቺ ደግሞ መልክ ይሻላል ሲላት ነበር ፤ ያን ነውን በስተመጨረሻ ተግባራዊ
ያደረገው፡፡
ከዚያም በኋላ ዲያቢሎስ ከእባብ ተዋህዶ ወደ አዳም ቀረቡ፡፡ አዳምንም አዳም ሆይ የሠማይ የምድር ገዢ
ባለው ጊዜ አዳም ተቆጣው እኔ የምድር እንጂ የሠማይ ገዢ አይደለሁም አለው፡፡ ያን ጊዜ ዲያቢሎስ አዳም
ነገሩን አዳም እንዳልተቀበለው ባወቀ ጊዜ ዲያቢሎስ አዳምን ጠየቀው አጋርህ ሔዋን ወዴት ናት አለው፡፡ እዛ
አለችልህ ብሎ አሳየው ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ወደ ሔዋን ሲሄድ ሔዋን ሆይ የሰማይና የምድር ንግስት አላት
ያን ጊዜ ሔዋን በሐሴት ተዋጠች ፤ ነገሩን እንደተቀበለችው አውቆ ለይቼ የጠየቅኋት እንደሆነ
ታውቅብኛለች ብሎ በገነት ካለው ዕፅ ሁሉ አትብሉ ያላችሁ ለምን ነው አላት፡፡ እሷም አረ በገነት ያሉትን
ሁሉ ዕፅ እንበላለን ነገር ግን ዕፀ በለስን እንዳንበላ አዞናል አለችው፡፡ ያን ጊዜ ዲያቢሎስ እንዴት አላት፡፡
እርሱን በበላችሁ ጊዜ የሞት ሞት ትሞታላችሁ ብሎናል አለችው፡፡ ዲያቢሎስም እናንተ ሞኝ ምግብ ከመቼ
እባብንም፡- አንቺ በደረትሽ የምትሣቢ ሁኚ ፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል ፀብን አደርጋለሁ፡፡ ከእርሷ
የሚወለደው አንተን አናት አናትህን ይበልህ ፤ አንተም ሽኮና ሽኮናውን ትላለህ አለው፡፡ ዘፍ 3፤15
በሔዋን ላይ፡- አንቺ በለሲቱን እንዳደማሽ ያንቺም ደም ይፈሳል ከባልሽ በታች ሁኝ ባልሽ ይግዛሽ፡፡ ዛሬ
በየወሩ ሴቶች የሚፈሳቸው የወር አበባ ኋላም አርግዘው በጭንቀት ወልደው እንደገና ህመማቸውን ረስተው
ወደ ቦታቸው መመለሳቸው ከዚያ የተነሳ ነው፡፡ ዘፍ 3፤16
አዳም፡- አንተ ሚስትህን እንደሰማህ ዘወትር ከእርሷ ትዕዛዝ አትውጣ ምድር እሾህ አሜኬላ ታብቅል ብሎ
ረገመው፡፡ የሞት ሞትን ትቀምሳለህ አለው፡፡ ዘፍ 3፤17
ከዚያም በኋላ ልዑል እግዚአብሔር አዳም እና ሔዋንን የቆዳ ልብስ አልብሶ ከገነት አስወጣቸው፡፡ ገነትንም
በኪሩቤል መላዕክ ጠባቂ አስቆመለት፡፡ አዳምንም ከገነት በስተምስራቅ በደብረ ቅዱስ በተባለ ተራራ
አስቀመጠው፡፡ ከዚያም አዳምንም አምላኩ ይቅር ይለው ዘንድ ሱባኤ ያዘ የዚያን ጊዜ የያዘው ሱባኤ 41 ቀን
ነበር በ38ኛ ቀን ዲያቢሎስ በመላዕክት ተመስሎ አዳምን ፀሎትህ ተሰምቶአልና ተከትለኸኝ ወደ ገነት
ትገባለህ አለው፡፡ አዳም የሱባኤው ቀን ስላልተገባደደ ተጠራጠረው ያን ጊዜ ዲያቢሎስ እንዳወቀ ገብቶ
አዳምን ደሞ አንተ አትሰማም ብሎ ወደ ሔዋን ሄደ ሔዋን ጸሎታችሁ ተሠምቷል ኑ እንሒድ ባላት ሰዓት
ከሱባኤው ወጣች ያን ጊዜ አዳም በጣም አዘነ መላዕኩ ገብርኤል ከዚህ በፊት እንዳትለያት ብሎት ነበርና
ዲያብሎስን ተከትለው ወደ ገነት ጉዞ ጀመሩ ያን ጊዜ ገነት በር ላይ በደረሱ ጊዜ ዲያቢሎስ ማንነቱን
ገለጠላቸው ወዲያው ድንጋይ አንስቶ አዳምን ፈነከተው አዳምም አለቀሰ ከዚያም በኋላ ዕለት ዕለት
የሚመገበው በገነት ያሉ አዋፋት የሚያመጡለት ፍራፍሬ ነበር፡፡ ያንን ፍራፍሬ ተፈንክቶ ከፈሰሰው ደም
ጋር ለወሰ መስዋትንም አቀረበ፡፡ ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ለአዳም ቃል ኪዳን ገባለት ከአምስት ቀን
በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለው አለው፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ያንተን ደም መስዋዕት አድርገህ አታቅርብ
እንሠሣትን በመስዋትነት እንዲያቀርብ ነገረው፡፡
የመለማመጃ ጥያቄዎች