Professional Documents
Culture Documents
አዲስ ጅማሮ (New beginnings) Regions & Zones
አዲስ ጅማሮ (New beginnings) Regions & Zones
A Preferred Operator
2020/21 ANNUAL BUSINESS PERFORMANCE REVIEW, BRIDGE
STRATEGY (2021-2024) & 2021/22 ANNUAL BUSINESS PLAN
7,152
PARTICIPANTS
MANAGED
WITHIN
4 DAYS
22
SESSIONS
August 3-6,2021
የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸምና ስትራቴጂ ውይይት በዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች (1/3)
የኩባንያችን ዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች ከዚህ በፊት በኮርፖሬት ዋና የሥራ ክፍሎች ደረጃ የተካሄደውን በ2013 በጀት
ዓመት አፈጻጸም፣ በቀጣይ ሦስት ዓመታት (2014-2016) ስትራቴጂ እንዲሁም በ2014 በጀት ዓመት ዕቅዶች ላይ
ያተኮረ “NEW BEGINNINGS—Stay Strong, Move Forward with Positive Attitude & Embrace a New
Perspective!” በሚል መርህ ከሐምሌ 27-30/2013 ዓ.ም ድረስ በ22 መርሃ-ግብሮች በየዞን እና ሪጅን ጽ/ቤጾች
ደረጃ የአንድ ቀን ውይይት ተካሂዷል፡፡
ሁሉም የዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች በተዘጋጀላቸው የስብሰባ ጊዜ ሠሌዳ መሠረት ሠራተኞቻቸውና ሁሉም
የማኔጅመንት አባላት የተሳተፉበት ውይይት ያደረጉ ሲሆን ውይይቶቹ በኦፕሬሽን ዳይሬክተሮች መሪነት
እንዲሁም ከዋናው መ/ቤት የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂደዋል፡፡ ስብሰባዎቹ ሲካሄዱ የኔትወርክ
እና ለደንበኞቻችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ሳይስተጓጎሉ እንዲከናወኑ መላው ሠራተኛ እና የሥራ ኃላፊዎች
ያደረጉት አስተዋጽኦ የሚመሰገን ነው፡፡
በውይይቱ ላይ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ በሁሉም ቦታዎች ሰፋ ያለ ተሳትፎ እና የሐሳብ መንሸራሸር የነበረ ሲሆን
የነበረውን አጠቃላይ የውይይት መንፈስ የሚያሳይ ሪፖርት ሁሉም ዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች ስብሰባውን ለመታደም
ከዋናው መ/ቤት በተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት ለዋና ሥራ አስፈጻሚ አቅርበዋል፡፡ ከተሳታፊዎች
የቀረቡት ሐሳቦች በአብዛኛው በመርኃ-ግብሩ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ላይ፣ ኩባንያችን በአስቸጋሪ ወቅትም ቢሆን
በ2013 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ውጤት እንዲሁም የተሻሻለው ስትራቴጂ የተቀመረበት መንገድ ሳይንሳዊ
መሆን ላይ ያተኮሩ አዎንታዊ ግብዓቶች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኩባንያው ባለፉት ሦስት ዓመታት ተከታታይነት
ያለው ለውጥ እንዲያመጣ፣ እድገት እንዲያስመዘግብ እንዲሁም ራሱን ለውድድር ዝግጁ እንዲያደርግ ከፍተኛ
አመራሩ የሰጠው አመራርም በበጎነት ተነስቷል፡፡
የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸምና ስትራቴጂ ውይይት በዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች (2/3)
የ2013 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና ስትራቴጂን የተመለከቱ ሊሻሻሉ የሚገባቸው፣ በተለየ መልኩ መታየት
ያለባቸው እና ግልጽነት የሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ላይ በኦፕሬሽን ዳይሮክተሮችና በከፍተኛ አመራሮች ማብራሪያና
አቅጣጫ በመስጠት በሁሉም ዘንድ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ ተችሏል፡፡ በተሳታፊዎች ቀጣዩን የሶስት
ዓመታት ስትራቴጂና የ2014 በጀት ዓመት ቢዝነስ ዕቅድ ከመተግበርና የኩባንያችንን ተወዳዳሪነት ከማረጋገጥ አኳያ
ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ተብለው በዋናነት ከተለዩት ውስጥ የቴሌብር አገልግሎትን ተደራሽነትና ተጠቃሚነት
ለማስፋፋት አገልግሎቱን በጥሩ ሁኔታ ማስተዋወቅ እንዲሁም ከደንበኞች ምዝገባ ጀምሮ እስከ አጠቃቀም ድረስ
ባሉት ሂደቶች የሚያጋጥሙትን የሲስተም ውስንነቶች ማስተካከል ላይ ያተኩራል፡፡ ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት
የቀረበው የቴሌብር አገልግሎት ውጤታማ መሆን ተቋሙ በውድድር ምክንያት ሊያጋጥመው የሚችለውን የገቢ ጫና
ለማካካስ ስለሚረዳው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተሳታፊዎች በኩል ከተነሡ ነጥቦች መካከል ኩባንያው ካለው ብዛት ያለው የሰው ኃይል አንጻር ምርታማነትን
ማሳደግ እና ወጪ ቆጣቢ የአሠራር ሥርዓቶች /Cost Optimization/ ላይ በሰፊው ቢሠራ በሚመጣው የውድድር
ገበያ ላይ የሚያስፈልገውን መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ ትርፋማነትን አረጋግጠን መቀጠል የሚያስችል መሆኑ በሰፊው
ተነሥቷል፡፡ባለፉት ሁለት ዓመታት የፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎት ደንበኞች እድገት ላይ ያስመዘገብነውን ውጤት
በድኅረ ሽያጭ እንዲሁም አዳዲስ ደንበኞችን ከመጨመር አንጻር የማቴሪያል እና የሥራ መገልገያ መሣሪያዎች
አቅርቦትን ማሻሻል እንዲሁም የሠራተኞችን የሥራ ባህል ማሳደግ ላይ በአትኩሮት ሊሠራ እንደሚገባም ግብዓት
ተሰጥቷል፡፡ ኩባንያው ሰው-ተኮር የሆነ ስትራቴጂ ቀርጾ በመንቀሳቀስ የሥራ ከባቢዎችን፣ የሽያጭ ማዕከላትንና የኮር
ኔትወርክ ሕንፃዎችን ምቹ ከማድረግ አኳያ የሄደበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን አንስተው በቀጣይም በውጤት ላይ
በተመሠረተ አካሄድ የሠራተኞችን ደኅንነትና ውጤታማነት የሚያሳድጉ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት
በሰፊው ተነስቷል፡፡
የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸምና ስትራቴጂ ውይይት በዞንና ሪጅን ጽ/ቤቶች (3/3)
በመጪው የውድድር ገበያ መላው የኩባንያው ቤተሰብ የስትራቴጂክ ዕቅዱን በተዋረድ በመተንተን በያንዳንዱ
የሥራ ክፍል በማውረድ እና በማስፈጸም ወጪን በመቆጠብ ፣ ምርታማነትን በማሳደግ እና የአመለካከት ለውጥ
በማምጣት ኩባንያው ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን መሪ ሆኖ እንዲወጣ ለማድረግ በመተባበር ጠንክሮ መሥራት
እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የዞንና ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተሮች በሠራተኞቻቸው የነቃ ተሳትፎ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ
ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ ውይይት ተቋማዊ አቅምን ከመገንባት አንጻር እንዲሁም ማኔጅመንቱና ሠራተኞች ተናበው
መሥራትና ለአንድ ዓላማ መቆም እንዲችሉ ለማድረግ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ በተዘጋጀው መድረክ
የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ የስትራቴጂ ትግበራውን እንዲሁም የዞንና/ሪጅን ጽ/ቤቶች
አፈጻጸም በጋራ በመገምገም የኩባንያችንን ቀጣይ እድገት ለማረጋገጥ መሰል መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል
እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
ETHIO TELECOM STRATEGIC THEMES
RESOURCE
ORGANIZATIONAL MANAGEMENT & CONTINUOUS PARTNERSHIP
SECURITY UTILIZATION INCREMENTAL
IMPROVEMENT
Abebe Ambaw
Chief Network Operation & Areda Garee
Service Management officer NAAZ Operation Director
CENTRAL ADDIS ABABA ZONE
Capital Hotel| 5 August 2021
Behailu Ejigu
CAAZ Operation Director
EAST ADDIS ABABA ZONE
Skylight Hotel| 5 August 2021
Solomon Abera
Chief Customer Experience & Abdu Mohammed
Quality Management Officer NEER Operation Director
CENTRAL NORTH REGION
Getva Hotel| 5 August 2021
Ketema Dadi
Aynalem Albene CNR Operation Director
Chief Facilities and Fleet Officer
EAST REGION
Blossom| 5 August 2021
Workalemahu Dagnachew
Tewodros Hailemeskel
NNWR Operation Director
Chief Fixed Network Officer
SOUTH REGION
Haile Resort| 5 August 2021
Mahdi Jemal
Chief Strategy and Program
Habtamu Manaye
Management Officer SER Operation Director
SOUTH WEST REGION
Central Hotel| 5 August 2021
STAY SAFE!