admasu

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 9

መ/ቁ 26903

ቀን-----------------------

ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ካምባ

ከሳሽ፡-አቶ አድማሱ ጴጥሮስ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ተከሳሽ፡- አቶ ጴጥሮስ ዘዉዴ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ጉዳዩ፡- የዉርስ ሀብት ተጣርቶ እንዲሰጠኝ የቀረበ ክስ ነዉ፡፡

ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ተቀብሎ የማየት ስልጣን አለዉ፡፡

መጥሪያ በወረዳዉ ፖሊስ አማካኝነት ይደርሳል፡፡

የጉዳዩ ዝርዝር

የካምባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሳሽ የሟች እናቴ ወ/ሮ አልማዝ ሳንኬ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆኔን
በፍ/ብ/መ/ቁ 02182 በቀን 09/2016 ዓም አረጋግጦልኛል፡፡ ወላጅ እናቴ ድንገት በደረሰባት በእሳት ቃጠሎ ጉዳት
ደርሶባት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ወስጄ ስያሳክም በቀን 01/04/2016 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት
ተለይታኛለች፡፡ እናቴ ተከሳሽን አግብታ ስትኖር ብዙ ሀብት ንብረት በጋራ አፍርታለች፡፡ ሟች እናቴ ከከሳሽ ዉጪ ሌላ
ልጅ የላትም፡፡ ስለዚህ ቀጥሎ ከዘረዘርኳቸዉ ሟችና ተከሳሽ በጋራ ከፈሯቸዉ ንብረቶች የእናቴ ድርሻ ወጥቶ እንዲሰጠኝ
እጠይቃለሁ፡፡

1. በካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ በማዜ ንዑስ መኖሪያ ቤት ያለበት መጠኑ በግምት 1 ሄክታር የሚሆን

በሰሜን- ቃለሕይወት ድርጅት፤ በደቡብ-ጳዉሎስ ጮሌ ወፍጮ ቤት፤ በመሥራቅ- መንገድ፤ በምዕራብ- ጳዉሎስ ጫሬ
የሚያዋስኑ ሲሆኑ ዋናዉ መኖሪያ ቤት ያለበት ነዉ፡፡ በመኖሪያ ቤታችን 100 የሚያህሉ የተሰነጠቁ የዋንዛ ጣዉላዎች
ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በይዞታዉ ላይ ብርቱኳን-150፣ አቡካዶ-30፣ ማንጎ-20፣ ቡና-200፣ ዋንዛ-60፣ ግራቢሊያ-60
አሉበት፡፡

2. በካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ማና ጉርዴ 2 ኛ መኖሪያ ያለበት የይዞታ ስፋቱ በግምት 1 ሄክታር
የሆነ፡-

አዋሳኞች፡- በሰሜን- መንገድ፣ በደቡብ-አቶ ላፃ ላይሎ፣ በምዕራብ-ሉቃስ ቡዛኖ እና በምሥራቅ-ላፃ ላይሎ ናቸዉ፡፡
በይዞታዉ ላይ የባሕር ዛፍ ለፍልጥ የደረሰ በቁጥር 3000፤ የአበሻ ጽድ በቁጥር 50፤ የደረሰ የሸንኮራ አገዳ፤ ግራቢሊያ
በቁጥር 50፤ አቦካዶ በቁጥር 20፤ የቡና ተክል በግምት 200 ያህል ይገኙበታል፡፡

3. በማዜ ቀበሌ ልዩ ሥሙ አሸዋ ጋዴ መጠኑ በግምት 1 ሄክታር የሆነ፡-

አዋሳኞች፡-በሰሜን ጎሃ ወንዝ፤ በደቡብ-ቃለሕይወት ድርጅት ችግኝ ጣቢያ፤ በምሥራቅ-እስራኤል ዘዉዴ፤ በምዕራብ


ቃለሕይወት ድርጅት እና ጎሃ ወንዝ ናቸዉ፡፡በይዞታዉ ለፍልጥ የደረሰ ባሕርዛፍ በቁጥር 10፤ ዳላሜ ዛፍ 15፤ ፍሬ የሚሰጥ
አቦካዶ 10፤ ለመሰንጠቅ የደረሰ 20 ዋንዛ ዛፍ፤ በግምት 15 ፍሬ የሚሰጥ ብርቱኳን እንዲሁም ለጣዉላ ለመሰንጠቅ
ተቆርጦ በይዞታዉ ላይ የተኛ 6 ዋንዛ ጉማጅ ይገኛሉ፡፡
4. በማዜ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ማዜ በሚባልበት መጠኑ በግምት 2 ሄክታር የሚሆን የእርሻ ማሳ፡

አዋሳኞቹ፡-በሰሜን-ጎሃ ወንዝ፤ በደቡብ-መንገድ፤ በምሥራቅ-አብርሀም ፆና እና በምዕራብ-መንገድ ናቸዉ፡፡ በይዞታዉ


ላይ ብርቱኳን 60፣ አቡካዶ-10፣ ማንጎ-10፣ ዋንዛ-15፣ ግራቢሊያ-40 እና ሙዝ-100 አሉበት፡፡

5. በማዜ ቀበሌ ለዩ ሥሙ ቦልኪሶ በሚባልበት ስፋቱ በግምት 2 ጥማድ የሚሆን

አዋሳኞቹ፡-በሰሜ-አቶ አየለ አባይነህ፤ በደቡብ የመስኖ ቦይ፤ በምሥራቅ-ካሌብ ከተማ እና ባባ ድርኮ፤ እንዲሁም
በምዕራብ እስራኤል ዘዉዴ ናቸዉ፡፡ በይዞታዉ በቁጥር 30 የብርቱኳን ተክል አለበት፡፡

6. ለሟች እናቴ የቀብር ወጪ እንዲሆን ከተከሳሽ ጋር ማሳ ለአንኮ ሶርባ ቃለሕይወት ኅብረት በ 160,000(አንድ
መቶ ስልሳ ሺህ) ብር ያኮናተርን ስንሆን ከኮንትራቱ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብሩን) ብቻ ለቀብር የተጠቀምን
ስንሆን ቀሪ 110,000(አንድ መቶ አሥር ሺህ) ብር በከሳሽ እጅ ይገኛል፡፡

ከቡር ፍ/ቤቱን የምጠይቀዉ ዳኝነት

ከፍ ሲል የተዘረዘሩ ንብረቶችን ሟች እናቴ ከተከሳሽ ጋር በጋራ ያፈራቻቸዉ መሆኑን በማጣራት የሟች እናቴን
ድርሻ ለከሳሽ እንዲደርሰኝ እንዲወሰን ዳኝነት እጠይቃለሁ፡፡

ተከሳሽ የሟች እናቴን ድርሻ ብቸኛ ወራሽዋ ለሆንኩት ለከሳሽ እንዲሰጠኝ በአካባቢ ሽማግሌ ስጠይቅ ከሳሽ
ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለመክሰስ የተገደድኩኝ ስለሆነ ለዚህ ክስ ያወጣሁትን ወጪ ኪሳራ የመጠየቅ መብቴን
እንዲከብርልኝ ስጠይቅ ይህ እዉነት ነዉ፡፡

ቀን

ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ካምባ

ከሳሽ፡-አቶ አድማሱ ጴጥሮስ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ተከሳሽ፡- አቶ ጴጥሮስ ዘዉዴ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ጉዳዩ፡- የዉርስ ሀብት ተጣርቶ እንዲሰጠኝ የቀረበ ክስ ነዉ፡፡

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 223 መሠረት የሚከተሉትን ምስክሮቼን አቀርባለሁ፡፡


የሰነድ ማስረጃ

1. የወራሽነት ማረጋገጫ ዉሳኔ 1 ገጽ


2. በሟች እናቴ እና በተከሳሽ ሥም የተሠራ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ከካምባ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ቤት
በትዕዛዝ እዲያስቀርብ

የሰዉ ምስክሮች

1. ወ/ሮ ብርሃን ሻዉሌ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ


2. አቶ ዮሐንስ ያግሌ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ
3. አቶ ሰጉዴ ጮዴ፤ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ
4. አቶ ከበደ ከተማ፤ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

መ/ቁ 26903

ቀን-----------------

ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ካምባ

ከሳሽ፡-አቶ አድማሱ ጴጥሮስ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ተከሳሽ፡- አቶ ጴጥሮስ ዘዉዴ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

የጣልቃ ገብ አመልች፡-ወ/ሮ አበበች ዘነበ

ጉዳዩ ጣልቃ ገብ ወደ ክርክሩ ለመግባት እንዲፈቀድላት ባቀረበችዉ ማመልካቻ ላይ የበኩለን መልስ አቀርባለሁ፡፡

ለጣልቃ ገብ አቤቱታ ከሳሽ የምሰጠዉ መልስ

በአንድ ክርክር ለመሳተፍ የሚፈልግ ሰዉ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 41 መሠረት በጉዳዩ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለዉን መብት
በግልጽ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል፡፡ አመልካች ጣልቃ ለመግባት በምክንያትነት ያቀረበችዉ ነገር የለም፡፡ አመልካች
በተከሳሽ ተዘርዝረዉ የቀረቡትን ይዞታዎች ዘርዝራ የይዞታዎቹ ተጠቃሚ ነኝ ትበል እንጂ በምን መነሻ ተጠቃሚ
እንደሆነች አልገለጸች፤ የይዞታዎቹ ተጠቃሚም አልነበረችም፡፡ ስለዚህ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችላትን መብት
ሳትገልጽ ያቀረበችዉ አቤቱታ ተቀባይነት ሊኖረዉ አይገባም፡፡

ጣልቃ ገብ ወደ ክርክሩ ለመግባት ያስችለኛል ስትል በሰነድ ማስረጃነት በቁጥር 0813502 በተመዘገበ በይዞታ ማረጋገጫ
ደብተር ላይ በቤተሰብ አባነት ተመዝግብያለሁ ብላለች፡፡ ለካምባ ዙሪያ ወረዳ አርሶአደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር
የተሰጠዉ በ 1997 ዓም መሆኑ ይታወቃል፡፡ አመልች በተራ ቁጥር 6 ላይ የተከሳሽ 2 ኛ ሚስት እንደሆነች በሚያስመስል
መልክ ራሷን ገልጻለች፡፡ ይህም በዚሁ አቤቱታዋ በተራ ቁጥር 6 ላይ ተከሳሽን በ 10 ዓመታት ዉስጥ ማግባቷን ገልጻለች፡፡
ይህ ከሆነ በ 1997 ዓም በተሠራ በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ላይ በእዉነትም እሷም ሆነ ልጆቼ የምትላቸዉ ግለሰቦች
ተመዝግበዉ ከሆነ ይህ በተከሳሽ፤ በጣልቃ ገብ እና በካምባ ዙሪያ ግብርና ጽ/ቤት ካለ ሰዉ ጋር ተመሳጥረዉ የከሳሽን
መብት ለመጉዳት በህዝብና በመንግስት ሰነድ ላይ የተፈጠረ የማጭበርበር ተግባር ነዉ፡፡ ይህቺ ግለሰብ በ 1990 ዎቹ
ቀርቶ በ 2000 ዎቹ ዉስጥም የማትታወቅ ናት፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ሟች እናቴ በሴት አቅሟ ለፍታ ያገኘቻቸዉ ይዞታዎች
በ 1997 ዓም የወጣ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርን በማጭበርበር ከህግ ዉጪ ለመበልጸግ የተሠራ ተግባር መሆኑን ፍ/ቤቱ
ሊረዳ ይገባዋል፡፡ ይዞታዎቹ ሟች እና ከሳሽ ብቻችን እየተጠቀምን የነበርን ይዞታዎች ቢሆኑም ተከሳሽ በሌላ ቦታ
የሚኖር ሆኖ በሟች ባለቤትነት ብቻ ከእኛ ጋር በቤተሰብ አባልነት ተመዝግቧል፡፡ ነገር ግን ይህ ምዝገባ በሚከናወንበት
ጊዜ የጣልቃ ገብ አመልካች ከከሳሽ ጋር ብቻ ሳይሆን ከተከሳሽም ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት አልነበራትም፡፡ ስለዚህ
በርግጥም በሰነዱ ላይ የጣልቃ ገብ አመልካች ሆነች ሌሎች ግለሰቦች ተመዝግበዉ ከሆኑ ፍርድ ቤቱ ከካምባ ዙሪያ ወረዳ
ግብርና ጽ/ቤት በማጣራት ድርጊቱ ከባድ ወንጀል በመሆኑ በተከሳሽ፤ በጣልቃ ገብ አመልች እና በመ /ቤቱ በጉዳዩ ላይ እጁ
ያለበት ሰዉ ላይ የወንጀል ምርምራ እንዲጀመር ለፖሊስ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እናመለክታለን፡፡

የምንጠይቀዉ ዳኝነት

በይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ላይ የተፈጸመ ወንጀል ካለ ተጣርቶ በተከሳሽ፤ በጣልቃ ገብ አመልካች፤ በግብርና ጸ /ቤት እጁ
ያበት ሰዉ እና በይዞታዉ ማረጋገጫ ላይ የፈረመ የቀበሌ ሊቀመንበር ላይ የወንጀል ምርምራ እንዲጀመር ትዕዛዝ
እንዲሰጥልን፤

የጣልቃ ገብ አመልካች ወደ ክርክሩ ለመግባት የሚያስችላት በቂ ምክንያት የላትም ተብሎ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን፤
ቀን 20/05/2016 ዓም

ለጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠ/ሲ/ማ/ፈ/ዉ/መ/ክ/ ዋና የሥራ ሂደት

አርባ ምንጭ

ጉዳዩ፡-የጥብቅና አገልግሎት ዉል እንዲመዘገብ ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡

ዉል ሰጭ/ጪዎች፡-

1. አቶ አድማሱ ጴጥሮስ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ዉልተቀባይ፡-አቶ ኢሳያስ ጎይሳ ጎቤ፤ አድራሻ አርባ ምንጭ ከተማ

የጥብቅና ፍቃድ የክልል 775 እንዲሁም የፌደራል የጥብቅና ፈቃድ 5410/15

እኔ/ እኛ ዉል ሰጭ/ጪዎች አቶ/ወ/ሮ አድማሱ ጴጥሮስ ከአቶ ጴጥሮስ ዘዉዴ ጋር ባለኝ /ን በፍ/ብሔር ክስ ጉዳይ ዉል
ተቀባይ ጠበቃ በመሆናቸዉ ከመጀመሪያ ደ/ፍ/ቤት ጀምሮ ጉዳዩ የመጨረሻ ዉሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ቀርበዉ
እንዲከራከሩና መልስ እንዲሰጡ በጠቅላላዉ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ብር ለዉል ተቀባይ ለመክፈል ተስማምችያለሁ፡፡

እኔ የዉል ተቀባይ ከላይ በተገለጸዉ መሠረት የሙያ ሥነምግባር በሚያዝዘዉ አግባብነት በትሕትና በታማኝነት የሙያ
አገልግሎት ለመስጠት የተስማማሁ ስሆን ቅድመ ክፊያ ብር 15,000/አሥራ አምስት ሺህ ብር-) ከዉል ሰጪ መቀበሌን
እያረጋገጥኩ ቀሪዉን ገንዘብ ጉዳዩ የመጨረሻዉ ውሳኔ ከማግኘቱ በፊት ለመቀበል ወድጄ ፈርሚያለሁ፡፡

ዉል የተደረገበት ክርክር በማነኛዉ መንገድ እልባት ቢያገኝና ቢያልቅ ደንበኛዉ ስምምነት የተደረገበትን የጥብቅና
አገልግሎት ክፊያ ሳያጓድሉ ለመክፈል ተስማምተዋል፡፡

ይህ ዉል በተዋዋዮች መካከል ከተፈረመበት ዕለት ጅምሮ በፍ/ህ/ቁ 1731 መሠረት የጸና ይሆናል፡፡
ዉል ሰጭ/ጪዎች ስምና ፊርማ ተቀባይ ስምና ፊርማ

1. አቶ አድማሱ ጴጥሮስ

ቀን 20/05/2016 ዓም

ለጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠ/ሲ/ማ/ፈ/ዉ/መ/ክ/ዋና የሥራ ሂደት

አርባ ምንጭ

የጥብቅና አገልግሎት ዉክልና ማስረጃ

በፍ/ህ/ቁ 2005 እና 1731 መሠረት የተደረገ የሙያ ዉል ሰነድ

ጉዳዩ፡-የጥብቅና አገልግሎት ዉል እንዲመዘገብ ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡

ዉል ሰጭ/ጪዎች፡-

አቶ አድማሱ ጴጥሮስ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ዉልተቀባይ፡- ኢሳያስ ጎይሳጎቤ አድራሻ አርባ ምንጭ ከተማ ጫሞ ቀበሌ

የክልል የጥብቅና ፍቃድ ደረጃ አንድ ደብተር ቁጥር 775 እና የፌደራል የጥብቅና ፈቃድ ቁጥር 5410

ለዉክልና ተቀባይ የምሰጠዉ ዉክልና ተቀባይ ጠበቃ በመሆናቸዉ እንደ እኛ ሆኖ በማናቸዉም ፍ /ቤት እና በሌሎች
ፍትህ አካላት ዘንድ ቀርቦ ክስ እንዲ መሥርቱ እንዲከራከሩ መልስ እንዲቀበሉ እና እንዲሰጡ ይግባኝ እንዲጠይቁ
መጥሪያ እንዲቀበሉ አፈጻጸሞችን እንዲከታተሉ የዉሳኔ ግልባጭ እንዲቀበሉ በማለት በፍ/ሥ/ሠሥ/ህ/ቁ 63 መሠረት
ለጠበቃ መወከሌ ታዉቆ ማስረጃ እንዲሰጠኝ በማክበር አመለክታለሁ፡፡

ዉክልና ሰጭ/ጪዎች ስምና ፊርማ ዉክልና ተቀባይ ስምና ፊርማ

አቶ አድማሱ ጴጥሮስ
መ/ቁ 26903

ቀን-----/07/2016 ዓም

ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት

ካምባ

አመልች፡-አቶ አድማሱ ጴጥሮስ ጠበቃ ኢሳያስ ጎይሳ

ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠኝ ስለማመልከት ይሆናል፡፡

በቀን 26/07/2016 ዓም በጣልቃ ገብ ለጣልቃ ገብ ጥያቄዋ ላይ ምላሽ በጽሑፍ እድንሰጥ ታዝዘን በትዕዛዙ መሠረት
አቅርበናል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለቀን 17/07/2016 ዓም ክስ ለመስማት መቀጠሩን ሰምችያለሁ፡፡ ይሁንና በዚሁ ቀን አሰቀድሞ
በምዕራብ ዓባያ ወረዳ የግራ ቀኝ ምስክር ለመስማት የተቀጠረ አጀንዳ ጋር ተጋጭቶብኛል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ማመልከቻ ጋር
አያይዤ ያቀረብኩትን የአጀንዳዬን ግልባጭ 1 ገጽ ተመልክቶ ፍ/ቤቱ ቀጣይ ቀጠሮን ለ 4/07/2016 ዓም፤ወይም
ለ 08/08/2016 ዓም እንዲቀይርልኝ ሲያቀርብ ይህ እዉነት መሆን በመሃላዬ አረጋግጣለሁ፡፡

መ/ቁ---------------

ቀን---------------

ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት


ካምባ

የአፈ/ከሳሽ፡- አቶ አድማሱ ጴጥሮስ ዘዉዴ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

የአፈ/ተከሳሽ፡-አቶ ጴጥሮስ ዘዉዴ አድራሻ ካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ

ገዳዩ፡- እንደፍርድ እንዲፈጽም የቀረበ ክስ ነዉ፡፡

የክሱ ዝርዝር

ግራ ቀኛችን በፍ/መ/ቁ 26903 በሆነዉ ላይ ከሳሽ የሟች እናቴ ድርሻ ንብረት እንዲሰጠኝ ክስ አቅርቤ ተከራረናል፡፡ ይህ
ፍ/ቤት ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በክሴ ተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሰዉ ይዞታና ቤት ዉጪ ያሉ ይዞታዎች እና በይዞታዎች ላይ
ያሉ ንብረቶች ለሁለት እኩል እንዲካፈል ወስኗል፡፡ በመሆኑም ክቡር ፍ/ቤቱ ቀጥሎ ያሉ ንብረቶች የጋራ ስለሆኑ
እንዲከፋፈሉ እጠይቃለሁ፡፡

1. በካምባ ዙሪያ ወረዳ ማዜ ቀበሌ በማዜ ንዑስ መኖሪያ ቤት ያለበት መጠኑ በግምት 1 ሄክታር የሚሆን፡-

በሰሜን- ቃለሕይወት ድርጅት፤ በደቡብ-ጳዉሎስ ጮሌ ወፍጮ ቤት፤ በመሥራቅ- መንገድ፤ በምዕራብ- ጳዉሎስ ጫሬ
የሚያዋስኑ ሲሆኑ ዋናዉ መኖሪያ ቤት ያለበት ነዉ፡፡ በመኖሪያ ቤታችን 100 የሚያህሉ የተሰነጠቁ የዋንዛ ጣዉላዎች
ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በይዞታዉ ላይ ብርቱኳን-150፣ አቡካዶ-30፣ ማንጎ-20፣ ቡና-200፣ ዋንዛ-60፣ ግራቢሊያ-60
አሉበት፡፡

2. በማዜ ቀበሌ ልዩ ሥሙ አሸዋ ጋዴ መጠኑ በግምት 1 ሄክታር የሆነ፡-

አዋሳኞች፡-በሰሜን ጎሃ ወንዝ፤ በደቡብ-ቃለሕይወት ድርጅት ችግኝ ጣቢያ፤ በምሥራቅ-እስራኤል ዘዉዴ፤ በምዕራብ


ቃለሕይወት ድርጅት እና ጎሃ ወንዝ ናቸዉ፡፡በይዞታዉ ለፍልጥ የደረሰ ባሕርዛፍ በቁጥር 10፤ ዳላሜ ዛፍ 15፤ ፍሬ የሚሰጥ
አቦካዶ 10፤ ለመሰንጠቅ የደረሰ 20 ዋንዛ ዛፍ፤ በግምት 15 ፍሬ የሚሰጥ ብርቱኳን እንዲሁም ለጣዉላ ለመሰንጠቅ
ተቆርጦ በይዞታዉ ላይ የተኛ 6 ዋንዛ ጉማጅ ይገኛሉ፡፡

3. በማዜ ቀበሌ ልዩ ሥሙ ማዜ በሚባልበት መጠኑ በግምት 2 ሄክታር የሚሆን የእርሻ ማሳ፡

አዋሳኞቹ፡-በሰሜን-ጎሃ ወንዝ፤ በደቡብ-መንገድ፤ በምሥራቅ-አብርሀም ፆና እና በምዕራብ-መንገድ ናቸዉ፡፡ በይዞታዉ


ላይ ብርቱኳን 60፣ አቡካዶ-10፣ ማንጎ-10፣ ዋንዛ-15፣ ግራቢሊያ-40 እና ሙዝ-100 አሉበት፡፡

4. በማዜ ቀበሌ ለዩ ሥሙ ቦልኪሶ በሚባልበት ስፋቱ በግምት 2 ሄክታር የሚሆን

አዋሳኞቹ፡-በሰሜ-አቶ አየለ አባይነህ፤ በደቡብ የመስኖ ቦይ፤ በምሥራቅ-ካሌብ ከተማ እና ባባ ድርኮ፤ እንዲሁም
በምዕራብ እስራኤል ዘዉዴ ናቸዉ፡፡ በይዞታዉ በቁጥር 30 የብርቱኳን ተክል አለበት፡፡

ለሟች እናቴ የቀብር ወጪ ማሳ ለአንኮ ሶርባ ቃለሕይወት አኮናትረን ከቀበር ወጪ ቀሪ 110,000(አንድ መቶ አሥር
ሺህ) ብር በከሳሽ እጅ ይገኛል፡፡

የምጠይቀዉ ዳኝነት

ከላይ የተዘረዘሩት ንብረቶች የጋራ እኩል እንዲካፈል ስለተወሰነ ክቡር ፍ/ቤቱ በዉሳኔዉ መሠረት እንዲፈጽምልኝ
ዳኝነት ያቀረብኩት እዉነት ስመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ህ/ቁ 92 መሠረት አረጋግጣለሁ፡፡

You might also like