Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 25

https://t.

me/Ethiopian_Digital_Library

የበይነ መረብ ፈተና አስተዳደር


ፕሮቶኮል

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት


አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ይዘት ገጽ

1. አጭር ርዕስ ................................................................................................................3

2. የቃላት ፍቺ ................................................................................................................3

3. አስፈላጊነት .................................................................................................................4

4. ዓላማ .........................................................................................................................4

5. የተፈታኞች መብትና የተፈቀዱ ነገሮች ...........................................................................5

6. የተፈታኞች ግዴታ እና የተከለከሉ ነገሮች ......................................................................5

7. የፈተና አስፈጻሚዎች ግዴታና የተከለከሉ ነገሮች ............................................................6

8. የበይነ መረብ ፈተና አስተዳደር ቴክኒካል ግብረ ኃይል ተግባርና ኃላፊነት ...........................8

9. የመፈተኛ ማዕከላት ተግባር እና ኃላፊነት ..................................................................... 10

10. የፈተና አስፈጻሚዎች ተግባርና ኃላፊነት ................................................................... 11

1. ፈታኝ ................................................................................................................... 11

2. ሱፐርቫይዘር .......................................................................................................... 14

3. ጣቢያ ኃላፊ ........................................................................................................... 16

4. የአይሲቲ ቴክኒካል ድጋፍ ሰጪ............................................................................. 19

5. የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ .................................................................................. 20

6. የፈተና ማዕከል ኃላፊ ............................................................................................ 20

11. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት የውሳኔ አሠጣጥ .................................................... 21

12. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት ቅጣት ................................................................... 22

13. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት..................................................................................... 23

14. ልዩ ልዩ ጉዳዮች .................................................................................................... 23

15. ፕሮቶኮሉን ስለማሻሻል............................................................................................ 24

16. ፕሮቶኮሉ የሚጸናበት ጊዜ ....................................................................................... 24

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library
1
https://t.me/Ethiopian_Digital_Library
መቅድም

የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚከተሉት ዋና ዋና


ዓላማዎች አሉት፡፡ እነርሱም ለተፈታኞች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ስለማጠናቀቃቸው ሰርቲፊኬት
ለመስጠት፣ ወደቀጣይ የትምህርት እርከን እንዲሸጋገሩ ለመወሰን፣ በተለያዩ ሥራዎች ላይ ሲሰማሩ
እንደምስክር ወረቀት ለማገልገል፣ እና የትምህርት ስርዓቱን ለመፈተሽ ዓላማዎች እየዋለ ይገኛል፡፡

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አስተዳደር ስርዓት ውስጥ ስርቆትና ኩረጃ ከፍተኛ ችግሮችን ሲፈጥሩ
ቆይተዋል፡፡ ለአብነትም የፍትኃዊነት ጥያቄ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለማስነሳት እንደመነሻ፣
ተቋሙ በህዝብ ዘንድ ያለውን ታማኝነትና ቅቡልነት ላይ ጥርጣሬ የመፍጠር፣ ወዘተ መሰል ችግሮች
ለረዥም ጊዜ ታይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሶስት ዋና ዋና ጊዜያዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡
አንደኛው ፈተና መሰረዝ ነው፡፡ ሁለተኛው እንደገና ፈተና መስጠት ሲሆን ሶስተኛው የመፈተኛ
ቦታን መቀየር ነው፡፡ ሶስተኛው እርምጃ ላይ የፈተና ጥያቄዎችን በማሰባጠር የጥራዞችን ቁጥር
የመጨመር፣ ጠንካራ የሆነ የፈተናውን ሚስጢራዊነትና ደህንነት የማረጋገጥ፣ ለፈተና
የሚሰማራውን የሰው ኃይል ምልመላና ስምሪትን በልዩ ሁኔታ መምራት...ወዘተ ተጨማሪ
እርምጃዎችም ይገኙበታል፡፡ ሆኖም ዘላቂ የሆነ የፈተና ስርቆትና ኩረጃን የመከላከል ሥራ ደግሞ
በወረቀት ላይ ከሚሰጠው ፈተና ይልቅ ኮምፕዩተርን በመጠቀም በበይነ መረብ በሚሰጠው ፈተና
ላይ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በመሆኑም ይህ ሰነድ ኮምፕዩተርን መሠረት ያደረገ በበይነ መረብ የሚሰጠውን ፈተና አሰጣጥን
የሚመለከቱ ጉዳዮች በአጭሩ ይዟል፡፡

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library

2
ክፍል አንድ
አጠቃላይ ጉዳዮች
1. አጭር ርዕስ
ይህ ፕሮቶኮል በበይነ መረብ የሚሰጥ ሀገር አቀፍ ፈተና ፕሮቶኮል ቁጥር 01/2016 ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡

2. የቃላት ፍቺ
1. ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ማለት እንደቅደም ተከተላቸው የትምህርት ሚኒስቴርና
ሚኒስትር ነው፡፡
2. አገልግሎቱ ማለት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው፡፡
3. የበይነ መረብ ፈተና ማለት አንድ ተፈታኝ በትምህርት ቤት ቆይታው ያገኘውን እውቀት፣
ክህሎትና አመለካከት ኮምፕዩተርን በመጠቀም የሚደረግ ትምህርታዊ ምዘና ወይም ግምገማ
ነው፡፡
4. መፈተኛ ማዕከል ማለት ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ ትምህርት ቤቶች የመጡ ተፈታኞች
ፈተና የሚወስዱበትና የፈተና መሠረተ ልማቶችና ተያያዥ ግብዓቶች ያሉበት እና
በሚመለከተው አካል እውቅና የተሰጠው ቦታ ወይም ተቋም ማለት ነው፡፡
5. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ማለት በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የወጣ የፈተና
አስተዳደደር መመሪያ ድንጋጌዎችንና ፈተና አስተዳደርን በሚመለከት በትምህርት ሚኒስቴር
ወይም በአገልግሎቱ የተላለፉ ወይም የሚተላለፉ ውሳኔዎች ማለት ነው፡፡
6. ፈተና አስፈጻሚ ማለት ፈታኝ፣ ሱፐርቫይዘር፣ ጣቢያ ኃለፊ፣ አንባቢ፣ የጉድኝንት ማዕከል
አስተባባሪ፣ የማዕከል ኃላፊ፣ እና በየደረጃው የተቋቋመ የፈተና ግብረ ኃይል አባላት ማለት
ነው፡፡
7. ትምፈአ ማለት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው፡፡
8. የተከለከሉ ነገሮች ማለት ተፈታኝ ወይም የፈተና አስፈጻሚ ለፈተና ሥራ በመፈተኛ
ማዕከላት ወይም በመፈተኛ ክፍል ውስጥ እንዲይዝ ወይም እንዲጠቀም ያልተፈቀዱ ነገሮች
ማለት ሲሆን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም አስተዳዳረዊ እርምጃና እንደአስፈላጊነቱ
አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ነገሮች ማለት ነው፡፡
9. የጾታ አገላለጽ በዚህ ፕሮቶኮል ውስጥ በወንድ የተገለጹት ሁኔታዎች በሙሉ ለሴት ጾታም
ያገለግላሉ፡፡

3
https://t.me/Ethiopian_Digital_Library
3. አስፈላጊነት
ኮምፕዩተርን በመጠቀም በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ላይ የተለያዩ ተልዖኮዎች ያሉአቸው
ተቋማት የሚሳተፉ በመሆኑ ሥራው በቅንጅት የሚመራበት፣ ድግግሞሽን ያስቀረ፣ ለሁሉም ግልጽ
የሆነና በጋራ ስምምነት የተደረሰበት ሰነድ በማዘጋጀት የፈተናውን ሥራ በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ
በመምራትና በማስተዳደር ስኬታማ እንዲሆን አስቻይ ሁኔታን መፍጠር በማስፈለጉ ነው፡፡

4. ዓላማ
1. ዋና ዓላማ
ኮምፕዩተርን በመጠቀም በበይነ መረብ ለሚሰጠው ፈተና በየደረጃው ያለው አደረጃጀትና ተሳታፊዎች
ያላቸውን ተግባርና ኃላፊነት በመለየትና በማሳወቅ ፍትኃዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ፈተና በመስጠት
ተፈታኞች በደረሱበት ደረጃ የጨበጡትን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን ነው፡፡

2. ዝርዝር ዓላማዎች
ይህ ፕሮቶኮል የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች ይኖሩታል፤

ሀ. ሚስጢራዊነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትኃዊ የፈተና አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር


ማስቻል
ለ. የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በመከላከል በራሳቸው የሚተማመኑ እና ለቀጣይ የትምህርት
ደረጃ በቂ ዝግጅት ያደረጉ ተማሪዎችን ለመለየት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር
ሐ. የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ በፈተና የሚገኘው የተፈታኞች
ውጤት ተአማኒነት ያለው መረጃ ሆኖ እንዲያገለግል ለማስቻል
መ. ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ አስተማማኝ እና ምቹ የፈተና አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር
ለማስቻል

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library

4
ክፍል ሁለት

የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች


5. የተፈታኞች መብትና የተፈቀዱ ነገሮች
1. ማንኛውም የበይነ መረብ ተፈታኝ እስክሪብቶና የስሌት ጥያቄዎችን ለማስላት የሚውል ባዶ
ወረቀት ወደ መፈተኛ አዳራሽ ይዞ መግባት ይችላል፡፡
2. ለመፈተን የሚያገለግል ኮምፕዩተር ወይም ታብሌት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የማግኘት
መብት አላቸው፡፡
3. ተፈታኞች ፈተና በሚወስዱበት ጊዜ ብርሃናማ ክፍል፣ መቀመጫ ወንበርና መፈተኛ ጠረጴዛ
የማግኘት መብት አላቸው፡፡
4. ተፈታኞች ከፈተና ጥያቄዎች ውጭ ማንኛውንም ከፈተና አስተዳደር ጋር የተገናኙ ገለጻ
የሚፈልጉ ጉዳዮችን መጠየቅና ምላሽ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
5. ተፈታኞች ከፈተናው አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ዝርዝር ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመፈተኛ
ማዕከል በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተፈታኞች ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ የማግኘትና ወደ ፈተና አዳራሽም ይዘው
መግባት ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ቤት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ይዘው
መግባት ይችላሉ፡፡

6. የተፈታኞች ግዴታ እና የተከለከሉ ነገሮች


1. ማንኛውም ተፈታኝ አጤሬራ፣ ስልክ፣ ሃርድ/ፍላሽ ድስክ፣ ስማርት ሰዓት፣ የጌጥ መነጽር፣
ጌጠኛ ቀለበት፣ ማጂክ ጃኬት፣ ቁልፍ ወይም ምንም ዓይነት ድምጽና ምስል
የሚቀዱ/የሚቀርጹ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል ውስጥ መግባት
የተከለከለ ነው፡፡
2. ፈተና በሚሰጥባቸው ኮምፕዩተሮች ላይ በሚመለከተው አካል ደህንነቱ ያልተረጋገጠ
የትኛውንም ዓይነት መተግበሪያ መጫን ወይም ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የተከለከለ
ነው፡፡ ሆኖ ሲገኝም የፈተና ውጤት ከመሰረዝ በተጨማሪ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ
ያደርጋል፡፡
3. ፈተና እየተሰጠ ባለበት ወቅት በማንኛውም አማራጭ የመፈተኛ ኮምፕዩተሮችን በመጠቀም
የኤሌክትሮኒክ መልዕክት ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን መላክም ሆነ መቀበል በጥብቅ የተከለከለ
ነው፡፡ ሆኖም ሲገኝ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፈተናው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ አግባብነት
ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

5
4. ማንኛውም ተፈታኝ ከመፈተኛ ክፍል ውጭ ሆኖና ለፈተና ሥራ ተለይቶ እውቅና ከተሰጠው
ኮምፕዩተር ውጭ ለመፈተን መሞከር ወይም መፈተን በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ሆኖ ከተገኘ
የፈተና ውጤቱ ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል፤ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
5. ለፈተና ሥራ የሚያገለግሉ የይለፍ ቀሎችን (Password) በማንኛውም ሁኔታ ለሶስተኛ
ወገን አሳልፎ መስጠት ወይም ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መያዝ ወይም በቀላሉ ተገማች
ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ዓይነ ስውራን ተፈታኞች ለአንባቢዎቻቸው
ወይም የአካል ጉዳት ያለባቸው ተፈታኞች ለረዳቶቻቸው ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
6. ማንኛውም ተፈታኝ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ እና ማንነቱን በግልጽ ለመለየት
የሚያስችል የትምህርት ቤት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ወይም የወሳኝ ኩነት ምስክር
ወረቀት ይዞ የመገኘትና ሲጠየቅም የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ
ካርድ ሳይዙ መፈተን የተከለከለ ነው፡፡
7. ተፈታኞች በሐኪም ከታዘዘ መድኃኒት ውጭ ወደ መፈተኛ ክፍል ምንም ዓይነት
መድኃኒትና መድኃኒት መውሰጃዎችን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
8. ተፈታኞች ወደመፈተኛ አዳራሽ ምግብና ውሃ ይዘው መግባት የጠከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን
በጤና ምክንያት የግዴታ መጠቀም ያለባቸው ሲሆኑ ከመፍተኛ ከፍል ውጪ (በር አካባቢ)
አስቀምጠው ለፈታኝ መምህር እያሳወቁ ሲፈቀድላቸው መጠቀም ይችላሉ፡፡
9. ተፈታኞች የተሟላ አካላዊ ፍተሻ ተደርጎና ማንነታቸው በግልጽ ተለይቶ ወደ መፈተኛ
አዳራሽ የሚገቡ ይሆናል፡፡ ለዚህም የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡
10. አካላዊ ፍተሻ ሳይደረጉ ፈተና ወዳለበት ሰርቨር እና ኮምፕዩተሮች አካባቢ ወይም ክፍሎች
ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
11. በግልጽ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው ወደ መፈተኛ ክፍሎች ይዞ መግባት እና ፈተና
የሚሰራባቸውን ኮምፕዩተሮች እንዲነካካ ወይም እንዲጠቀምባቸው መፍቀድ በጥብቅ
የተከለከለ ነው፡፡

7. የፈተና አስፈጻሚዎች ግዴታና የተከለከሉ ነገሮች


1. ማንኛውም ፈታኝ፣ ሱፐርቫይዘርና ሌላ ፈተና አስፈጻሚ ስልክ፣ ሃርድ/ፍላሽ ድስክ፣ ስማርት
ሰዓት፣ የጌጥ መነጽር፣ ጌጠኛ ቀለበት፣ ማጂክ ጃኬት፣ ቁልፍ ወይም ምንም ዓይነት ድምጽና
ምስል የሚቀዱ/የሚቀርጹ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል ውስጥ
መግባት የተከለከለ ነው፡፡
2. ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለበይነ መረብ ፈተና የተመደበ የማዕከል ኃላፊ እና
የፈተና ጣቢያ ኃላፊ አስቸኳይ ሙያዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮችን ወደማዕከል ለመላክና
ምላሹንም ለመውሰድና ለመተግበር እንዲያስችለው ዘንድ ስልክ የሚጠቀም ይሆናል፡፡

6
3. ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለበይነ መረብ ፈተና የተመደበ የፈተና ጣቢያ ኃላፊው
እራሱ ፈታኝ በሚሆንበት ጊዜ ስልክ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ በምትኩ የማዕከል ኃላፊ
ስልክ የሚጠቀም ይሆናል፡፡
4. ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ የትኛውንም ዓይነት ለፈተና ሥራ የሚያገለግል የይለፍ ቃሎል
(Password) በስራ አጋጣሚ ቢያገኝ ላልተፈቀደለት ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ወይም
ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መያዝ ወይም በቀላሉ ተገማች ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
5. ፈታኞችና ሌሎች የፈተና አስፈጻሚዎች በደብዳቤ ተለይቶ ከተፈቀደለት ሰው በስተቀረ
የፈተና ሥራ የሚሰራባቸውን ኮምፕዩተሮች በሌላ ሰው እንዳይነኩ የመከላከልና እና ሆኖም
ሲገኝ ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
6. ማንኛውም ፈተና አስፈጻሚ በተመደበበት መፈተኛ አዳራሽ ላይ ብቻ የሚሰራ ሲሆን
ማንነቱን በግልጽ ለመለየት የሚያስችል መለያ ባጅና የቀበሌ መታወቂያ ይዞ የመገኘትና
ሲጠየቅም የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡
7. ፈታኞችና ሌሎች የፈተና አስፈጻሚዎች የተሟላ አካላዊ ፍተሻ ማድረግ እና ማንነታቸው
በግልጽ መለየት ባስፈለገ ጊዜ ሁሉ የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡
8. ፈታኞች ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተኛ ክፍል ውስጥ በፈተና ሰዓት እስካለ ድረስ
የፈተናውን ጥያቄዎች ከፍቶ እየሠራ መሆኑን እና በመጨረሻም በትክክል ጨርሶ ማስረከቡን
(submit ማድረጉን) የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ በኃላ እስከ 30 ደቂቃ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት
ይችላል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከአንድ ሰዓት በፊትና ፈታኝ መምህር
ሳይፈቅድ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
10. በመብራት ወይም በኢንተርኔት ወይም በሌላ ምክንያት ፈተናው ሳይጀምር ቢዘገይ ወይም
በመሃል ቢቋረጥ አስፈላጊው የሰዓት ማሻሻያ ተደርጎ ተፈታኙ ለፈተናው በተመደበው ሰዓት
ላይ እንዲፈተን ይደረጋል፡፡
11. በግልጽ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው ወደ መፈተኛ ክፍሎች ይዞ መግባት እና ፈተና
የሚሰራባቸውን ኮምፕዩተሮች እንዲነካካ ወይም እንዲጠቀምባቸው መፍቀድ በጥብቅ
የተከለከለ ነው፡፡
12. ፈተና ሊሰጥ አንድ ሳምንት ሲቀረው የሙከራ ፈተና ከመለማመድ ውጭ እና ፈተና
በሚሰጥበት ወቅት የመፈተኛ ኮምፕዩተሮችን ተጠቅሞ ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ መስራት
የተከለከለ ነው፡፡
13. ፈታኞች በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ያሉ ተፈታኞች ምንም ዓይነት የተከለከሉ ነገሮችን
አለመያዛቸውንና አለመጠቀማቸውን የማረጋገጥ፣ የመከላከልና ተፈጽሞም ቢገኝ እርምጃ
የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡
14. ከተፈቀደለት ሰው በስተቀረ መፈተኛ ክፍል መግባትና መፈተኛ ኮምፕዩተሮች መነካካት
በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
15. በግልጽ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው ወደ መፈተኛ ክፍሎች ይዞ መግባት እና መፈተኛ
ኮምፕዩተሮች እንዲነካካ ወይም እንዲጠቀምባቸው መፍቀድ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library

7
ክፍል ሶስት
ተግባርና ኃላፊነት
8. የበይነ መረብ ፈተና አስተዳደር ቴክኒካል ግብረ ኃይል ተግባርና ኃላፊነት
1. የፌዴራል ፈተና አስተዳደር አብይ ግብረ ኃይል አባላት
1. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር …..………….ሰብሳቢ
2. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተሮች ………...አባል
3. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ ….....አባል
4. የት/ት ሚኒስቴር አይሲቲና ዲጂታል ት/ት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ………..…አባል
5. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፈተና አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ..ጸሐፊ

2. የፌዴራል ፈተና አስተዳደር አብይ ግብረ ኃይል አባላት ተግባርና ኃላፊነት


1. በፈተና ማዕከላት ለፈተና ስራ የሚሆን መሰረተ ልማት መሟላቱን ፈተናው ከመሰጠቱ
አስቀድሞ ያረጋግጣል፤
2. በሚጠበቀው ደረጃ የፈተና መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸውን መፈተኛ ማዕከላት
በመለየት እንዲሟሉ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ጥረት ያደርጋል፤
3. ለተፈታኞ የሚቀርብ ፈተና በማስፈተኛ ፕላትፎርም ላይ በሚጠበቀው የጥራት ደረጃ
መሆኑን ያረጋግጣል እና አጠቃላይ የፈተናው ሂደት ይከታተላል፤ ይደግፋል፡፡
4. አስፈላጊው በጀትና ሌሎች ሎጂስትኮች በአግባቡ መሠራታቸውን እና መመደባቸውን
ያረጋግጣል፣ ይከታተላል ይደግፋል፡፡
5. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዳስፈላጊነቱ ግብረ ኃይሉን እንደገና
ሊያዋቀር ይችላል፤

3. የፌዴራል ፈተና አስተዳደር ቴክኒካል ግብረ ኃይል አባላት


1. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፈተና አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ..ሰብሳቢ
2. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ ………...አባል
3. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ….አባል
4. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና እርማት ዴስክ ኃላፊ……....አባል
5. ከትምህርት ሚኒስቴር አይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት (አንድ ተወካይ……….አባል
6. ከኢትዮጵያ ትምህርት ምርምር ኔትወርክ (አንድ ተወካይ) ………………….….አባል

8
4. የፌዴራል ፈተና አስተዳደር ቴክኒካል ግብረ ኃይል አባላት ተግባርና ኃላፊነት
ቴክኒካል ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና
አስተዳደርና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡-
1. የበይነ መረብ ፈተና ሥራ ውጤታማና ስኬታማ እንዲሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና
ድጋፍ ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው ጋር በትብብርና በቅንጅት ይሠራል፡፡
2. የሰው ኃይል ስምሪቱ በቂ መሆኑንና በአግባቡ ተመልምሎ መሰማራቱን ያረጋግጣል፣
ይከታተላል፤ ይደግፋል፡፡
3. ሌሎች የበይነ መረብ ፈተናን በሚመለከት ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዮችን ያከናውናል፡፡
4. የአፈፃጸም ሪፖርትን በጹሁፍ ለለፈተና አስተዳደርና አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና
ዳይሬክተር ያቀርባል፡፡

5. የክልል/የከተማ አስተዳደር የበይነ መረብ ፈተና ቴክኒካል ግብረ ኃይል አባላት


1. የክልሉ/ከተማ አስተዳደደሩ የፈተና ዘርፍን የሚመራ ምክትል ቢሮ ኃላፊ … ሰብሳቢ
2. የክልሉ/ከተማ አስተዳደደሩ አይሲቲ ልማት ዳይሬክተር ………………..…….አባል
3. የክልሉ/ከተማ አስተዳደደሩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ (ተወካይ)…………..…….አባል
4. የክልሉ/ከተማ አስተዳደደሩ የፈተና አስተዳደር ዳይሬክተር …………………….አባል

6. የክልል/የከተማ አስተዳደር የበይነ መረብ ፈተና ቴክኒካል ግብረ ኃይል ተግባርና ኃላፊነት
1. በክልሉ ወይም ከተማ አስተዳደሩ በፈተናው ለሚሳተፉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች
በበይነ መረብ ፈተና አስተዳደርና በመተግበሪያው አጠቃቀም ላይ ሥልጠና ይሰጣሉ፡፡
2. በመፈተኛ ማዕከላት/ክፍል ያሉ ኮምፕዩተሮች ላይ መፈተኛ Safe Exam Browser
ይጭናሉ፣ በትክክል መስራት መቻላቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
3. በመፈተኛ ማዕከል የሚገኙ ኮምፕዩተሮች በትክክል የሚሰሩ መሆናቸውንና ከኢንተርኔት
ጋር በአግባቡ የተገናኙና ፈተና መስጠት የሚያስችሉ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
4. ለተፈታኞች በልምምድ ወቅት የ”User Name and Password Reset” ተግባርን
ያከናውናሉ፡፡
5. በፈተና መስጫ ማዕከል ላይ የሚገኙ የፈተና መስጫ መሠረተ ልማቶችና ተያያዥ
ፋሲሊቲዎች ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ከሚመለከታቸው ጋር አብረው
ይሰራሉ::

9
6. ፈተና መስጫ ማዕከሉ መጠባበቂያ ጄኔሬተር መኖሩን እና በትክክል መስራት የሚችል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፤ ከሌለም እንዲኖር ከሚመለከታቸው ጋር አብረው ይሰራሉ፡፡
7. ተፈታኞች የመፈተኛ መተግበሪያውን መጠቀም እንዲችሉ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡
8. በፈተና ወቅት ለፈታኞችና ለሌሎች በፈተና ላይ ለተሰማሩ የፈተና አስፈጻሚዎች ሙያዊ
ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡
9. የሀገር አቀፍ የቴክኒካል ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባል በመሆን ይሠራሉ፤ የፈተናውን ሥራ
ይከታተላሉ፣ ይደግፋሉ፡፡
10. የበይነ መረብ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚያግዙ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡

9. የመፈተኛ ማዕከላት ተግባር እና ኃላፊነት


መፈተኛ ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎችን፣ ኮሌጆችን፣ ትምህርት ቤቶችን የሚመለከት ሲሆን በነዚህ
ማዕከላት ሊተገበሩ የሚገባቸው የበይነ መረብ ፈተና አስተዳደር ዋና ዋና ተግባራትና ጥንቃቄዎች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከል ሲገቡ በቂ አካላዊ ፍተሻ አድርገውና ማንነታቸው
በትክክል ተለይተው የሚገቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ይህን ተግባር ከሚፈጽሙ አካላት
ጋር ይተባበራል፡፡
2. ፈተናው የሚሰጥበትን ኮምፕዩተር እንዲያስተዳደረው ሙሉ “Access” የሚኖረው ሰው
የተፈቀደለት ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህም ሰው በቂ የቴክኒክ ሥልጠና የወሰደና ስለሥራው
እውቀት፣ ክህሎትና መልካም ስነምግባር ያለው መሆኑ ተረጋግጦ በመፈተኛ ማዕከሉ
የበላይ ኃላፊ በደብዳቤ የሚወከል ይሆናል፡፡
3. ፈተናው የሚሰጥባቸውን ኮምፕዩተሮችና ሌሎች መሠረተ ልማቶችና ፋሲሊቲዎች
እንዲሁም መፈተኛው ቦታ የተሟላ አካላዊና የሳይበር ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን
ያረጋግጣሉ፡፡
4. ለፈተናው አገልግሎት የሚውሉ ማንኛቸውም ኮምፕዩተሮችም ሆኑ ሰርቨሮች latest
antivirus, firewall, having an ability to prevent unauthorized access በተሟላ
መልኩ ያላቸው መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
5. ቅድሚያና ድህረ የሳይበርና አካላዊ ዳህንነት ፍተሻ ኃላፊነት ባለው አካል ይደረጋል፤
ስምምነት የተደረሰባቸው የማስተካከያ ሐሳቦች ወዲያውኑ ይተገበራሉ።
6. ፈተናው የሚሰጥባቸው ኮምፕዩተሮች እስከቀጣይ የፈተና ፕሮግራም ድረስ ሱፐርቫይዘር
ባለበት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል (Shut down ይደረጋል)፡፡ ቀጥሎ ሥራ በሚጀመርበት

10
ሰዓት ቀደም ብሎ በተመሳሳይ መልኩ ይከፈታል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥገና
የሚያስፈልጋቸው ኮምፕዩተሮች ሲኖሩ በሚመለከተው የሥራ ኃላፊ እውቅናና ፍቃድ
ሊሠራ ይችላል፡፡ ለዚህም መፈተኛ ማዕከሉ ኃላፊ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
7. ፈተናው ሲሰጥ ቢያንስ ለሶስት ሰዓታት ሙሉ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ቀድሞ
ተፈትሾ የተረጋገጥ ጄኔሬተር መኖሩን ያረጋግጣል፤ በትክክል መስራቱንም ይከታተላል፡፡

10. የፈተና አስፈጻሚዎች ተግባርና ኃላፊነት

1. ፈታኝ
ፈታኝ ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር ነው፡፡ በአንድ የፈተና ጣቢያ ከተመዘገቡ ተፈታኞች ውስጥ
ከ30 – 40 የሚደርሱ በአንድ መፈተኛ ክፍል ያሉ ተፈታኞችን በፈታኝነት ይመራል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
• ስለፈተና አስተዳደደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር ውል ይዋዋላል፣ የፈተና
ሥራን በተመደበበት የፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍል በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
የመፈተኛ ክፍል እና ተፈታኞች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
• ፈታኙ በሚፈትንባቸው ቀናት ሁሉ ፈተናው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ለፈተና ጣቢያ
ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ በሰዓቱ ተገኝቶ ሪፖርት ካላደረገ በቅርብ ኃላፊ በኩል
በሚቀርበው ሪፖርት መሰረት በሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድ ይደረጋል፤
• አንድ ፈታኝ በአማካይ 30 - 40 ተፈታኞችን የመቆጣጠርና የመፈተን ግዴታ
አለበት፡፡ሆኖም እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታና እንደ መፈተኛ ክፍሎችና አዳራሾች
የመያዝ አቅም ከአማካኙ የተፈታኝ ቁጥር በላይ ሊፈትን ይችላል፤
• ተፈታኞችን በሚፈተኑበት ክፍል/አዳራሽ በር ላይ በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም ተከተል
በማሰለፍ እና የምዝገባ መታወቂያ /Admission Card/ በማየት መቀመጫ ያስይዛል፡፡
በተጨማሪም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ የተፈታኞችን ማንነትና የምዝገባ ቁጥር
ያረጋግጣል፤
• ተፈታኞች በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጫቸውን ከያዙ በኋላ
ኮምፕዩተሮችን እንዲከፍቱ ያደርጋል፡፡ የራሳቸውን የይለፍ ቃል በመጠቀም በአግባቡ
እንዲፈተኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ይከታተላል፡፡

11
• ተፈታኞች ከእርሳስ፣ ከእስክርቢቶ፣ ከባዶ ወረቀት እና ከማስመሪያ በስተቀር ሌሎች
የተከለከሉ ነገሮችን ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ሞባይልና ካልኩሌተር/ የመሳሰሉትን
ወደ ፈተና ክፍል ይዘው እንዳይገቡ ይቆጣጠራል፤
• የፈተናውን የጥያቄ ቅርጽና ይዘት አስመልክቶ ከተፈታኞች የሚቀርብ ማንኛውንም ጥያቄ
ማስታወሻ ይዞ በሱፐርቫይዘሩ አማካይነት ለጣቢያ ኃላፊ ያቀርባል፡፡ ከዚህ ውጭ
ለተፈታኞች የመሰለውን ማስተካከያ መስጠት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፤ ከጣቢያ ኃላፊ
በሚሰጠው ምላሽ መሠረት ተገቢውን ማስተካከያ ያደርጋል፡፡
• ማንኛውንም ዓይነት የፈተና ደንብ የተላለፈ ተፈታኝ ሲገጥመው ከሱፐርቫይዘሩ የግል
የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግሮች ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፅ በመውሰድ ሞልቶና ፈርሞ
ለሱፐርቫይዘሩ ያቀርባል፡፡ በቡድን የተፈፀመ የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግር ሲገጥመው
ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላትና በመፈረም ለሱፐርቫይዘሩ ያቀርባል፤
• የየፈተናውን መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ሰዓት ያስከብራል፤
• እያንዳንዱ ተፈታኝ የተመዘገበበትን የት/ዓይነት ለመፈተኑ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ቅፅ
(Attendance Sheet) ላይ የጻፈው የምዝገባ ቁጥርና የፈተናው ዓይነት ትክክለኛነት
በተፈታኙ ስምና ፊርማ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
• በፈተና ወቅት ተፈታኞችን ከመቆጣጠርና የፈተና አሰጣጥ ደንብ ከማስከበር ውጭ በፈተና
ክፍል ወይም አዳራሽ ውስጥ ፈተና ማንበብ ወይም ሌላ ሥራ መሥራት በፍፁም
አይፈቀድም፤
• ተፈታኞች የሚያጋጥማቸው ችግር ሲኖር ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በቅርብ ላለው
ሱፐርቫይዘር ወይም ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል፤
• ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ዘግይተው የሚመጡ ተፈታኞች ወደ ፈተና አዳራሽ
አንዳይገቡ ይከለክላል፡፡ እንዲሁም ፈተናው ከተጀመረ 1፡00 ሰዓት ሳይሞላ ተፈታኞች
እንዲወጡ አይፈቅድም፡፡ በተፈቀደላቸው ሰዓት የሚወጡ ተፈታኞች ሲኖሩ በአግባቡ
ፈተናውን አስረክበው (Submit ብለው) መውጣታቸውን ያረጋግጣል፡፡
• ተፈታኞች በፈተና ክፍል ውስጥ ሲጋራ ማጨስና፣ ማስቲካ ማኘክ፣ ኮፊያ ማድረግ፣ ልብስ
መከናነብ፣ ዕቃ መዋዋስና የመሳሰሉትን ተግባራት እንዳይፈጽሙ ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፤
• በጣቢያ ኃላፊው በታወቀ ምክንያት የጊዜ ገደብ ለውጥ ካልተገለጸ በስተቀር ለእያንዳንዱ
የትምህርት ዓይነት በተፈቀደው ጊዜ መሠረት ፈተናው እንዲካሄድ ያደርጋል፤
• ፈተናው ተጀምሮ አስኪጠናቀቅ ድረስ ተፈታኞች የቀራቸውን ጊዜ በየ30 ደቂቃው
ያስታውሳል፤

12
• ሕጋዊ ምዝገባ አካሂደው ፈተናው ሲሰጥ ያልተገኙ ተፈታኞችን በትክክል በማረጋገጥ
የምዝገባ ቁጥራቸውን በተፈታኞች መቆጣጠሪያ ቅጽ (Attendance Sheet) ግርጌ
በተዘጋጀው ቦታ ላይ ያሰፍራል፤ ፊርማውንም ያኖራል፤
• ፈተናው እንደተጠናቀቀ ሁሉም ተፈታኝ Log Out ማድረጉን ያረጋግጣል፡፡ ካልሆነም
ያደርጋል፡፡ መፈተኛ ኮምፕን ይዘጋቸዋል (Shut Down ያደርጋል)፡፡ ሁሉም ተፈታኝ
በአግባቡ መፈተኑን እና ቀሪ ካለ እና ሌሎች የተስተዋሉ ችግሮች ካሉ ከተሟላ የውሎ
ሪፖርት ጋር ወዲያውኑ ለሱፐርቫይዘር ያስረክባል፤
• ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በፈታኝነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ስልክ /ሞባይል/ይዞ
ፈተና ክፍል ውስጥ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ሞባይሉን ሌላ ቦታ
አስቀምጦ የመግባት ኃላፊነት አለበት፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጣቢያ ኃላፊ ለማዕከል
ሪፖርት የሚደረግ ችግር ካጋጠመ የኮምፕየተሩን ስክሪን ፎቶ አንስቶ ለመላክ ብቻ ሊገባ
ይችላል፡፡
• የፈታኝነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣
ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ
በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
• መፈተኛ ክፍሉ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑንና ፈተና ለማስፈተን ዕውቅና
የተሰጠው መሆኑኑ አረጋግጦ ይረከባል።
• በህግ ከተፈቀደለት ተፈታኝና ቁሳቁሶች ውጭ ማንኛውም በፈተና ክፍል የተከለከሉ
ቁሳቁሶች ወይም መሣሪያዎች ቀድመው በክፍሉ ውስጥ በማንኛውም ቦታ አለመቀመጣቸውን
እና ተፈታኞችም አለመያዛቸውን ያረጋግጣል፣
• መፈተኛ ክፍል የገቡ ተፈታኞች ሁላቸውም አቴንዳንስ መፈረማቸውን እና የፈረሙት
እያንዳንዳቸው ፈተናውን በአግባቡ ሠርተው ማስረከባቸውን ያረጋግጣል።
• ኮምፕዩተሮቹ ለቀጣይ ፈተና ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
• የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡
• ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

13
2. ሱፐርቫይዘር
ሱፐርቫይዘር ተጠሪነቱ ለጣቢያ ኃላፊ ነው፡፡ በአንድ የፈተና ጣቢያ ሁለት የመፈተኛ ክፍሎችን
ይመራል፡፡ ይከታተላል፤ ይደግፋል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ፈተና ጣቢያ የመፈተኛ
ክፍሎች ከሁለት በታች ከሆኑ ሱፐርቫይዘር መመደብ ሳያስፈልግ በጣቢያ ኃላፊ የሚመሩ
ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት የመፈተኛ ክፍሎች ከ2 - 3 ሲሆኑ አንድ ሱፐርቫይዘር፣ የመፈተኛ
ክፍሎች ከ4 - 5 ሲሆኑ ሁለት ሱፐርቫይዘር፣ የመፈተኛ ክፍሎች ከ6 - 7 ሲሆኑ ሶስት
ሱፐርቫይዘር በሚል አሰራር ተጨማሪ ሱፐርቫይዘር እንደአስፈላጊነቱ እንዲመራ ይደረጋል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
• ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር ውል ይዋዋላል፣
የመፈተኛ ክፍል ፈታኞች እና አንባቢዎች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
• ከጣቢያ ኃላፊው ጋር በመተባበር ፈተናው በሥነ ሥርዓት እንዲከናወን የማድረግ
ኃላፊነት አለበት፤
• የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን የፈተና አሰጣጥ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል፤
• ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል እንዳይገባ
ያደርጋል፡፡ ፈተናው ተጀምሮ 1፡00 ሰዓት ካልሞላ ተፈታኙ ፈተናውን ሰርቶ
ቢያጠናቅቅም እንዳይወጣ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ተፈታኙ ከመፈተኛ ክፍል ከወጣ
በኃላ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ከግቢው እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
• ተፈታኞች በሚቀመጡባቸው ዴስኮች መካከል በተቻለ መጠን በቂ ርቀት መኖሩን
ያረጋግጣል፤
• ተፈታኞች ጎን ለጎን ለመኮራረጅ የሚያደርጉት ጥረት ካለ ይከላከላል፤ ሆኖ ከተገኘም
እርምጃ ይወስዳል፡፡
• በፕሮግራሙ መሠረት የተመደበ ሱፐርቫይዘር በተመደበበት ጣቢያ ፈተናው ከመጀመሩ
አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ በመገኘት ሥራውን ያከናውናል፡፡ በተጨማሪም የጣቢያ
ኃላፊውን በመርዳት በጣቢያው መቆየት ይኖርበታል፡፡ በፈተና ሥራ ላይ ያረፈደ ወይም
የጣቢያ ኃላፊው እስኪያሰናብተው በጣቢያው ያልቆየ እንደሆነ በቅርብ ኃላፊ በኩል
የፈፀመው ግድፈት ተገልጾ ተፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድበት ሊያውቅ
ይገባል፡፡

14
• አንድ ሱፐርቫይዘር ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የተመደበባቸውን ክፍሎች
በማስተባበር ፈታኞችና ተፈታኞች ተግባርና ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን
በቅርበት ይቆጣጠራል፤
• በእያንዳንዱ መፈተኛ ክፍል የትምህርቱ የሥም መቆጣጠሪያ በአግባቡ መወሰዱን፣
ተፈታኞችም በሚፈተኑት የት/ዓይነት መሠረት በስም መቆጣጠሪያ ቅፅ ላይ
መፈረማቸውን በማረጋገጥ፣ ተጓዳኝ ቅፃቅጾች በአግባቡ መሞላታቸውን በማረጋገጥና
ከፈታኞች በመረከብ ለጣቢያ ኃላፊው ያስረክባል፤
• ፈታኝ በተጓደለበት ሁኔታ በፈታኝነት ተመድቦ የሚሰራ ሲሆን ክፍያው ግን
በሱፐርቫይዘር ስሌት ይፈፀምለታል፤
• በተመደበባቸው ክፍሎች በመዘዋወር ተፈታኞች በተቀመጡበት ኮምፕዩተር ላይ
ጥያቄዎችን እየሠሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ በስም መቆጣጠሪያ ቅፁ ላይ በትክክል
መፈረማቸውንም ያረጋግጣል፡፡
• የመፈተን ተግባርና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ፈታኞች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ
ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፤
• የፈተና ሥነ ሥርዓት ጉድለት የፈፀሙ ተፈታኞች ሲያጋጥሙ እንደአስፈላጊነቱ የግል
ወይም የቡድን የተፈታኞች የፈተና ደንብ መተላለፍ ሪፖረት ማቅረቢያ ቅጾችን ከፈታኙ
ጋር በመሙላትና በመፈረም ወዲያውኑ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
• በፈተና አሰጣጥ ሂደት ወቅት ከተፈታኞች በፈታኞች አማካይነት የሚቀርቡለትን
ችግሮች ማስታወሻ ይዞ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
• ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በሱፐርቫይዘርነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ስልክ
/ሞባይል/ ይዞ ወደ ፈተና ክፍሎች ውስጥ መግባትም ሆነ በአካባቢው መዘዋወር በጥብቅ
የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ሞባይሉን ሌላ ቦታ አስቀምጦ የመግባት ኃላፊነት
አለበት፤
• የሱፐርቫይዘርነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ
ይፈርማል፣ ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን
በማረጋገጥ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ
ይፈርማል፡፡
• የጣቢያ ኃላፈው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡በፈተና አሰተዲደር
ዙሪያ ከጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣ ይተገብራል፣
ፈተና አፈፃፀሙንም በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል፤

15
• መፈተኛ ክፍሎችና ዙሪያቸው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገላቸው መሆኑን
ያረጋግጣል፣ እንዲሆኑም ይሠራል፣
• የተከለከሉ ቁሳቁሶችና መሣሪያዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥና ዙሪያ እንዳይኖሩ
ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል፣ ይከላከላል።
• የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ሲከሰቱም ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ይሰራል፣
ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል።
• ፈተና በሚሰጥበት ዕለት ከጣቢያ ኃላፊ የተረከባቸውን ቅጻቅጾች በአግባቡ በመሙላት
ወይም መሞላታቸውን በማረጋገጥ ለጣቢያ ኃላፊ ያሰረክባል፣ ይከታተላል፡፡
• ፈታኞችን እና አይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢን ያስተባብራል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
• ሥራውን አጠናቆ የተሟላ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡

3. ጣቢያ ኃላፊ
ፈተናው በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሆነ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ
ሲሆን በትምህርት ቤት ሲሆን ተጠሪነቱ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት ይሆናል፡፡
ይህ አደረጃጀት የመፈተኛ ጣቢያን መሰረት በማድረግ የሚሠራ ሲሆን በአንድ የፈተና ጣቢያ
የተመዘገቡ ተፈታኞች በአንድ የፈተና ጣቢያ የሚፈተኑ ከሆነ አንድ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ
የሚመደብ ሲሆን ተፈታኞቹ ብዛታቸው ከፍተኛ ከሆነ ሁለት ጣቢያ ኃላፊ ሊመደብ ይችላል፡፡
የፈተና ጣቢያው የተፈታኝ ብዛት 30 (ሰላሳ) እና ከዚህ በታች ከሆነ የጣቢያ ኃላፊው
የሱፐርቫይዘር እና የፈታኝነት ኃላፊነትን ደርቦ ፈተናውን ያስተዳድራል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
• ፈተናው በዩኒቨርሲቲ ከሆነ ከጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ጋር በትምህርት ቤት ከሆነ
ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ
ሁኔታ ውል ይዋዋላል፤ የፈተና ሥራን በተመደበበት የፈተና ጣቢያ በበላይነት ይመራል፣
ይከታተላል፣
• የፈተና አስፈጻሚዎችና የፈተና ጣቢያው ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
• ለሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች፣ አንባቢዎች እና ተፈታኞች በፈተና ጣቢያ ደረጃ
አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣

16
• በተለያዩ ምክንያቶች አድሚሽን ካርድ ይዘው ባለመምጣታቸው ወደ ፈተና አዳራሽ
እንዳይገቡ ለሚከለከሉ መደበኛ ተፈታኞች ከአገልግሎቱ ከተላከው ዝርዝር ማረጋገጫ
(Master List & Photo Album) ተማሪዎች ስለመሆናቸው ተገቢውን ማረጋገጫ እንዲሰጥ
በማድረግ ወደ ፈተና ክፍል እንዲገቡ ያደርጋል፣
• በጣቢያው ውስጥ ያሉ ተፈታኞችን፣ ፈታኞችን ሱፐርቫይዘሮችንና ፖሊሶችን
ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ በወቅቱ መፍትሔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ
ውሣኔ ይሰጣል፡፡ ከአቅም በላይ ከሆነም ከሚመለከተው ኃላፊ ጋር በመነጋገር ወይም
ባለው የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ለተከሰተው
ችግር አፋጣኝ መፍትሄ በመስጠት ስለአፈፃፀሙ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች
አገልግሎት የጽሑፍ ሪፖርት ያቀርባል፤
• ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል እንዳይገባ
ያደርጋል፡፡ ፈተናው ተጀምሮ 1፡00 ሰዓት ሳይሞላ ከፈተና ክፍል እንዳይወጣ
ይቆጣጠራል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከመፈተኛ ክፍል
የሚወጣ ከሆነ ከግቢው እንዲወጣ ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፡፡
• የፈተና ሥራዉን የሚመራበትና የሚያስተባብርበት አመቺ የሆነ ጊዜያዊ ቢሮ ከፈተና
መስጫ ማዕከል ተረክቦ የሚሰራጩና የሚሰባሰቡ የፈተና ሪፖርቶችንና ቅጻቅጾችን
ያደራጃል፡፡ በፈተና ወቅት በአካባቢው በመንቀሳቀስ እገዛ ለሚሹ ሱፐርቫይዘሮችና
ፈታኞች ድጋፍ ይሰጣል፤
• ማናቸውንም ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተጓዳኝነት የሚሞሉ ቅፃቅጾችን በአግባቡ እየተሞሉ
መሆናቸውን ያረጋግጣል፤ ሪፖርት አደራጅቶ ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡
• በፈተና አሰጣጥና በልዩ ልዩ የፈተና የሥነ ሥርዓት ጉድለት ከፈተና ስለሚታገዱ
ተማሪዎች በፈታኝና በሱፐርቫይዘር በግልና በቡድን የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግሮች
ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጾች ላይ ተሞልተው በሚቀርቡለት ሪፖርቶች መሠረት ውሣኔ
ያስተላልፋል፤
• መፈተኛ ኮምፕዩተሮች በአግባቡ መስራታቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤ ጉድለት
ሲኖርም ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር በመሆን ይፈታል፡፡
• የትምህርት ቤት አመራር ወይም የኮሌጅ ዲን/ትምህርት ክፍል ኃላፊ ወይም ተወካይ
በፈተና አሰጣጥ ወቅት የማህተም፣ የቢሮና የጠቅላላ አገልግሎት ሥራ በመሥራት
ለፈተናው ሥራ መሳካት አስተዋፅኦ እያዲያበረክቱ ያደርጋል፤

17
• ማየት ለተሳናቸው ተፈታኞች በደንብ ማንበብ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ
የሚችሉ ፈታኞችን ወይም የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ተፈታኞች የተመደቡ
ረዳት ጸሐፊዎችን ትክክለኛነታቸውን አረጋግጦ ይመድባል፡፡ እነዚህ ፈታኞች ጥያቄ
በሚያነቡበት ጊዜ ተዘዋውሮ በመመልከት በትክክል የማያነቡና የተገቢውን ድጋፍ
ማድረግ የማይችሉ ካጋጠመው ወዲያውኑ እንዲለወጡ በማድረግ ሁለተኛ
እንዳይመደቡም ያደርጋል፤
• በፈተና አሰጣጥ ወቅት በቀጥታ በፈተና አሰጣጡ ሂደት ከሚሳተፉ ሰዎች በስተቀር ወደ
ፈተና ጣቢያው ቅጥር ግቢ ወይም መፈተኛ አካባቢ ማንም ሰው እንዳይገባ ያደርጋል፤
• እያንዳንዱን ፈተና በመጀመሪያ ሰዓቱ ያስጀምራል፤ ሰዓቱ ሲያበቃም ተፈታኞች
መስራት እንዲያቆሙ ያስደርጋል፤
• በፈተና ጣቢያ የሚሞሉ ቅጻቅጾች በፖስታ ውስጥ ተከተው እንዲታሸጉ ያደርጋል፤
በታሸገው ፖስታ ላይም የትምህርት ቤቱ ወይም የዩኒቨርሲቲው ወይም የከምፓሱ
ማህተም እንዲያርፍበት ያደርጋል፤
• በፈተና ጣቢያው ውስጥ ፈተና መስጫ ኮምፕዩተሮችና መሠረተ ልማቶች ላይ በፈተና
ወቅት እንዳይበላሹ ተገቢው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያደርጋል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፤
• የመፈተኛ ግቢና ክፍል ተገቢው የደህንነት ጥበቃ እየተደረገለት መሆኑን ያረጋግጣል፤
ይከታተላል፤ ያስተባብራል፡፡
• በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ በፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈታኞች እና በፈተና
አስፈፃሚዎች በግልም ሆነ በቡድን የሚፈጸሙ የፈተና ደንብ መተላለፍ መረጃዎችን
በደንብ መተላለፍ ቅጽ ላይ በማስሞላት ከፈታኝና ሱፐርቫይዘር ጋር ተፈራርሞ
ለማዕከል አስተባባሪ ወይም ለትምፈአ ያሰረክባል።
• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞችን ለፈተና ስራ አገልግሎት የተሰጡ
ቁሳቁሶችን ለማዕከል አስተባባሪ ያስረክባል፣
• በአንድ የፈተና ጣቢያ የተፈታኞች ቁጥር 30 እና በታች ሲሆን ፈታኝና ሱፐርቫይዘር
ሳያስፈልገው ራሱ ይፈትናል፡፡ ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤ የፈታኝና የሱፐርቫይዘር
ሚናንም ደርቦ ይወጣል፡፡
• በፈተና ጣቢያው የፈተና አስፈጻሚዎችን አሰራር ሂደት ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ
ተፈታኞችን በአግባቡ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ በፈተና አስተዳደር ዙረያ ከማዕከል

18
አስተባባሪው የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና
አፈጻጸሙንም በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል።
• የጣቢያው ውስጥና ዙሪያው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑን ያረጋግጣል
• ማንኛውም የተከለከሉ ቁሳቁሶች/ዕቃዎች በጣቢያው የሌሉ ወይም ተፈትሸው የተወገዱ
መሆኑን ያረጋግጣል
• ተፈታኞች ወደ ፈተና ጣቢያው ሲገቡ በአግባቡ መፈተሻቸውን ይከታተላል፣ ጉድለት
ሲኖር ለእንዲስተካከል ከሚመለከታቸው ጋር ይሠራል
• ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞች፣ ለአይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢዎች እና መልስ ወረቀት
አደራጆች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
• ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ፈተናው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሆነ
ከጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

4. የአይሲቲ ቴክኒካል ድጋፍ ሰጪ


በአንድ የፈተና ማዕከል አንድ የአይሲቲ ድጋፍ ሰጪ ይመደባል፡፡ ተጠሪነቱ በዩኒቨርሲቲ ሲሆን
ለማዕከል ኃላፊ በትምህርት ቤት ሲሆን ለጣቢያ ኃላፊ ይሆናል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት
• መፈተኛ ኮምፕዩተሮች የሚሰሩ መሆናቸውን እና አስፈላጊ የሆኑ መተግበሪያዎች
ቀድመው የተጫነላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ እንዲጫኑም ያደርጋል፡፡
• መፈተኛ ኮምፕዩተሮችና መሠረተ ልማቱ አካላዊና የሳይበር ደህንነት ጥበቃ
የተደረገላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤
• በፈተና ዕለት የአይሲቲ ቴክኒካል ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ድጋፍ
ያደርጋል፡፡ ይከታተላል፡፡
• ከዋናው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር በተጨማሪ ቢያን ለሶስት ተከታታይ ሰዓታት
የሚሰራ በቂ ነዳጅ ያለው ጄኔሬተር መኖሩን ያረጋግጣል፡፡
• ሌሎች ከማዕከል ኃለፊና አስተባባሪ የሚሰጡ ሥራዎችን ይሠራል፡፡
• ሪፖርቱን ለማዕከል ኃላፊ ሲያሰርከብ ክሊራንስ ይወስዳል

19
5. የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ
የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ተጠሪነቱ ለፈተና ማዕከል ኃላፊ ነው፡፡ በዋናው የፈተና ማዕከል
(ዩኒቨርሲቲ) እና/ወይም የፈተና ንዑስ ማዕከላት (ካምፓስ/ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት) አንድ
የፈተና ጉድኝት አስተባባሪ ይመደባል፡፡ እንደአስፈላጊነቱም ተጨማሪ የጉድኝት ማዕከል
አስተባባሪ ሊመደብ ይችላል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
• ፈተና በሚሰጥበት ማዕከል ለሚያስተባብራቸው የፈተና ጣቢያዎች የሚያስፈልገውን በቂ
የሚሰሩ ኮምፕዩተሮች መኖራቸውን ያረጋግጣል፡፡
• ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከማዕከል ኃላፊው ጋር ውል ይዋዋላል፣
የፈተና ሥራን በተመደበበት የጉድኝት ማዕከል (ቦታ) በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
• ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣
• ፈተና በሚሰጥበት ተፈታኞች በአግባቡ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ ክፍል መግባታቸውን
ያረጋግጣል፡፡ ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅት ይሠራል፡፡
• ለጣቢያ ኃላፊዎች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ በስሩ ያሉ ጣቢያ ኃላፊዎችን
ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፡፡
• ከማዕከል ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
• ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከማዕከል ኃላፊው በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

6. የፈተና ማዕከል ኃላፊ


የፈተና ማዕከል ኃላፊ ተጠሪነቱ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው፡፡ በዋናው
የፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና ንዑስ ማዕከላት (ካምፓስ ወይም ኮሌጅ ወይም ትምህርት
ቤት) አንድ የፈተና ማዕከል ኃላፊ ይመደባል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ ከስሩ የተመደቡትን የጉድኝት
ማዕከል አስተባባሪዎችን በሃላፊነት የሚመራ ሰው ነው፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
• ለተመደበበት የፈተና ማዕከል ለተደለደሉ በበይነ መረብ ተፈታኞች የሚበቃ ያክል
ብዛት ያለው የሚሰራ ኮምፕዩተር መኖሩን ያረጋግጣል፡፡
• የበይነ መረብ ፈተና የሚሰጥባቸው ኮምፕዩተሮችና ሌሎች መሠረተ ልማቶች የደህንነት
ጥበቃ እየተደረጋላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

20
• የበይነ መረብ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከል ሲገቡ በአግባቡ እየተፈተሹ
መግባታቸውንና ለዚህም በቂ የሰው ኃይል መመደቡን ያረጋግጣል፡፡
• ለፈተና ሥራ የተመደቡት ፈታኞችና ሌሎች የሥራ አስፈጻሚዎች በሰዓቱ በተመደቡበት
መገኘታቸውን ያረጋግጣል፡፡
• እንደአስፈላጊነቱ በማዕከሉ የተመደቡ ተፈታኞችንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ታሳቢ
በማድረግ ረዳት በአገልግሎቱ ሊመደብለት ይችላል፡፡
• የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችን ያሰለጥናል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
• በተመደበበት ማዕከል የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት
ይመራል፡፡
• በፈተና አስተዳደር ዙሪያ ከአገልግሎቱ የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት
ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና አፈጻጸሙን በተመለከተ ለአገልግሎቱ ሪፖርት ያቀርባል፤
• የፈተና አስፈጻሚዎች በፈተና አሰጣጥ ቆይታቸው ስለሰጡት አገልግሎት የቆይታ እና
የሙያ አገልግሎት ክፍያ በመመሪያው መሰረት እንዲከፈላቸው ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
• ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ በጽሑፍ ከአገልግሎቱ ይወስዳል፡፡

ክፍል አራት
የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት
ቅጣት፣ የውሳኔ አሠጣጥ እና የቅሬታ አቀራረብ
11. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት የውሳኔ አሠጣጥ
1. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌዎችን በተላለፉ ተፈታኞች ላይ የሚወሰድ ማንኛውም እርምጃ
በፈታኝ፣ በሱፐርቫይዘርና በጣቢያ ኃላፊ የተረጋገጠ እንዲሁም በፈተና አስተዳደር ሥራ
ክፍል ተጣርቶ የቀረበና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት የበላይ አመራር ውሳኔ
የተሰጠው ይሆናል፡፡
2. በፈታኝና በሌሎች ፈተና አስፈጻሚዎች ላይ የሚተላለፉ የቅጣት ውሳኔዎች ከፈተና ማዕከል
ኃላፊ በሪፖርት የቀረቡ፣ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የበላይ አመራር የታዩ
ሆነው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በትምህርት ሚኒስቴር፣ በትምህርት ቢሮዎች እና
በዩኒቨርሲቲዎች በኩል የሚፈጸም ሲሆን አግባብነት ባላቸው ህጎች የመጠየቅ ጉዳይ
በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት በኩል በአቃቤ ህግ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

21
3. አግባብነት ባላቸው በሌሎች ህግች የተደነገጉትን የወሳኔ አሠጣጥ ሂደቶችን የሚከተል
ይሆናል፡፡

12. የፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት ቅጣት


1. ማንኛውንም የተከለከሉ ነገሮችን ፈጽሞ የተገኘ ተፈታኝ እንደየጥፋቱ የፈተና ውጤቶ
በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል፡፡ አግባብነት ባለው ህግ ይጠየቃል፡፡
2. የተጣለበትን ግዴታ ያልተወጣ ተፈታኝ እንደየጥፋቱ የፈተና ውጤቱ ይሰረዛል፡፡ አግባብነት
ባለው ህግ ይጠየቃል፡፡
3. ማንኛውም የቅጣት ውሳኔ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የወጣውን የፈተና
አስተዳደር መመሪያን ይከተላል፡፡
4. ማንኛውም ፈታኝ ወይም ሌላ የፈተና አስፈጻሚ በፈተና ስርቆትና ኩረጃ ላይ የተሳተፈ
እንደሆነ በታዳጊ ተፈታኞች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጉዳት እንዳደረሰ፣ የመንግስትን
አገልገሎት እነዳስተጓጎለ፣ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንዳደረሰ እና
ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለመፍጠር እንደተባበረ ተደርጎ ተወስዶ ከአስተዳደራዊ እርምጃ
በተጨማሪ አግባብ ባለው ህግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
5. ማንኛውም ፈታኝ በፈተና ወቅት ተፈታኝ የሚጎዳና የፈተና ስርዓቱን የሚያውክ ነገር
ከተሰጠው ኃላፊነት ውጭ ፈጽሞ ብገኝ ከአስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ አግባብነት ባለው
ህግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ፈታኝና ሌላ የፈተና አስፈጻሚ በማርፈድ ወይም በመቅረት ወይም በመሃል
በሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሳያገኝ ጥሎ በመውጣት የፈተና ስርዓቱን
ቢያስተጓጉል ወይም ተያያዥ ጉዳት እንዲፈጠር ቢያደርግ ከአስተዳደራዊ እርምጃ
በተጨማሪ አግባብነት ባለው ህግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡
7. ማንኛውም በፈተና አስፈጻሚ ግብረ ኃይል ውስጥ የሚሰራ የፈተና አስፈጻሚ የፈተናውን
ሂደት የሚያውክ ወይም ለኩረጃና ለስርቆት በር የሚከፍት ነገር በመፈተኛ ማዕከል ወይም
በመፈተኛ ክፍል አድርጎ ቢገኝ ከአስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ አግባብነት ባለው ህግ
የሚጠየቅ ይሆናል፡፡

22
13. የቅሬታ አቀራረብና አፈታት
1. ከፈተና አስተዳደር ጋር የተገናኙ ማንኛውም ቅሬታዎች ለአገልግሎቱ የፈተና አስተዳደር
ሥራ አስፈጻሚ በበይነ መረብ፣ በአካል፣ በጽሑፍ፣ በቃል ማቅረብ ይቻላል፡፡
2. ከፈተና አስተዳደር ድንጋጌዎች መተላለፍ ጋር ተያይዞ በተላለፉ ውሳኔዎች፣ በተወሰዱ
እርምጃዎች ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም አካል ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልገሎት
ማቅረብ ይችላል፡፡
3. የፈተና አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቅሬታዎችን ቢበዛ ቅሬታው ከቀረበለት ሰዓት አንስቶ
በአምስት ቀናት ውስጥ አጣርቶ ምላሽ ይሰጣል፡፡
4. በአገልገሎቱ በተሰጠው ምላሽ ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም አካል ለፈተና አስተዳደርና
አገልግሎት ዘርፍ ቀጥሎም ለዋና ዳይሬክተር ማቅረብ ይችላል፡፡

ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ጉዳዮች
14. ልዩ ልዩ ጉዳዮች
1. መፈተኛ ማዕከላት
የመፈተና ማዕከላት ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች ወይም ዩኒቨርሲቲዎች ወይም እውቅና የተሰጠው
በቂ የፈተና መሠረተ ልማት የተሟለላቸው ቦታዎች ይሆናል፡፡

2. የመፈተኛ ክፍል አደረጃጀትና የሰው ኃይል ስምሪት


1. አንድ የመፈተኛ ክፍል ከ30-40 ተፈታኞችን የሚይዝ ይሆናል፡፡
2. ለአንድ መፈተኛ ክፍል አንድ ፈታኝ ይመደባል፡፡ ፈታኙ ከማንኛውም የሙያ ዘርፍ
የሠለጠነ ሊሆን ይችላል፡፡
3. ለሁለት መፈተኛ ክፍሎች አንድ ሱፐርቫይዘር ይመደባል፡፡ ሱፐርቫይዘሩ የአይሲቲ
ባለሙያ መሆን ይኖርበታል፡፡
4. ለአንድ የፈተና ጣቢያ ወይም ትምህርት ቤት አንድ የጣቢያ ኃላፊ ይመደባል፡፡
5. ከአንድ የፈተና ጣቢያ በላይ ተፈታኞች በአንድ ማዕከል የሚፈተኑ ከሆነ የማዕከል ኃላፊ
ይመደባል፡፡
6. ለአንድ የፈተና ማዕከል አንድ ስነየር የአይሲቲ ባለሙያ ይመደባል፡፡

3. የፈተናው የማለፊያ ነጥብ


የፈተናው የማለፊያ ነጥብ በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መሠረት 50 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡

23
4. ተጠያቂነት
በዚህ ፕሮቶኮል ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የጣሰ ወይም እንዲጣሱ ያደረገ ወይም እንዲጣሱ
የተባበረ ማንኛውም ተፈታኝ፣ ፈታኝና ሌሎች የፈተና አስፈጻሚዎች አግባብነት ባለው በሀገራችን
ህጎች፣ ደንብና አስተዳደራዊ መመሪያያዎች መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

5. በፈተና አስተዳደር ድንጋጌ ጥሰት መነሻ የተያዙ ቁሳቁሶች አስተዳደር


ማንኛቸውንም የተከለከሉ ነገሮችን በመፈተኛ ማዕከል ወይም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ይዞ የተገኝ
ማንኛውም ተፈታኝ ከፈተናው ይሰናበታል፡፡ የተከለከለ ቁሳቁስ ይዞ የተገኘ ተፈታኝ አግባብነት ባለው
ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ቁሳቁሱም በፍትህ አካላት ለመረጃነት ሊያዝ ይችላል፡፡ ሪፖርቱንም በጽሐፍ
ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡

6. ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተፈታኞች


1. ህጻናትን ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች ሲኖሩ ሌላ ሴት ረዳት ይዞ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
ማንኛውንም ወንድ ረዳት ይዞ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
2. በእርግዝና ላይ ያሉ ተፈታኞች ሲኖሩ በፈተና ወቅት በፈተና ክፍል ውስጥ ወይም
ኮሪደር ላይ ብቻቸውን ተለይተው መቀመጥ ወይም በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ካሉት
መፈተኛ ቦታዎች ቅድሚያ ተሰጥቶአቸው መቀመጥ ይችላሉ፡፡
3. ለዓይነ ስውራን ተፈታኞች አንባቢ፣ የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ረዳት ፈታኝ
መምህር የሚመደብ ይሆናል፡፡

15. ፕሮቶኮሉን ስለማሻሻል


ፕሮቶኮሉን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሊያሻሽለው
ይችላል፡፡

16. ፕሮቶኮሉ የሚጸናበት ጊዜ


ፕሮቶኮሉ በዋና ዳይሬክተሩ ተፈርሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

https://t.me/Ethiopian_Digital_Library
እሸቱ ከበደ ጊቾሮ (ዶ/ር)
ዋና ዳይሬክተር

24

You might also like