Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 16

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ትምህርት ቢሮ

የአንደኛ፣ መካከለኛ፣ ሁለተኛ ደረጃ : ሳይንስ ሼርድ ካምፓስና አዳሪ


ትምህርት ቤቶች

የተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ

ረቂቅ

2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

መግቢያ

0|Page
ትምህርት የዕድገት ሁሉ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ ለሁለንተናዊ ልማት መፋጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ትምህርት
ተመራማሪና ችግር ፈቺ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችልና የህብረተሰቡን አመለካከት ወደ እድገት አቅጣጫ
የሚመራ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳይንሳዊ ግኝቶች ጋር በማስተዋወቅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና
ባህላዊ ዕድገቶችን የሚያፋጥን መሣሪያ ነው፡፡

ተማሪዎች በትምህርት ቤት በጥሩ ስነምግባር በመታነጽ ለራሳቸው ለማህበረሰባቸው እና ለሀገራቸው


ጠቃሚ ዜጋ ሆነው ሊቀረጹ ይገባል፡፡

በዚህ መሠረት ት/ቤቶቻችን በተሻለ ደረጃ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማከናወን አደንዲያስችሉ
የተማሪዎችን ውጤት እና ሥነምግባር ማሻሻል ተቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል፡፡ይሁንና አሁን እየታየ
ያለው የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ችግር በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡

በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ የተማሪውን ስነምግባር በተፈለገው አቅጣጫ ማነፅ አስፈላጊ
ነው፡፡ ተማሪዎች መብትና ግዴታቸውን በማወቅ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ
ለማድረግ፤ሃላፊነታቸውን መወጣት በማይችሉትና የዲሲፕሊን ችግር የሚያሳዩ ተማሪዎችን ለማስተካከል
ብሎም አስፈላጊ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ተቋማት አንድ
ወጥ የሆነ የተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የተማሪዎች
የዲሲፕሊን መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ተዘጋጅቷል፡፡

የመመሪያው አስፈላጊነት

 ተማሪዎች መልካም ምግባርን በመላበስ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ተቆርቋሪ ችግር ፈችና መልካም
ስነ ምግባር ያላቸው ዜጐች ሆነው እንዲቀረጹ ለማስቻል፣
 ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ህግና ደንብ በማክበር በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ
ለማድረግ፤
 ተማሪዎች ችግሮቻቸውን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሃሳብ ክርክርና ውይይት ብቻ እንዲፈቱ
ለማስቻል፡፡
 ተማሪዎች መብታቸውንና ግዴታቸውን ጠንቅቀው በማወቅ በመማር ማስተማር ሂደቱ
የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ
 ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ በራስ የመተማመን መንፈስ በጋራ የመኖርና
የመረዳዳት እና የመከባበር ባህል እንዲያዳብሩ ለማስቻል፣
 አሁን ላይ በስፋት በተማሪዎች ላይ እየታየ ያለውን የሥነምግባር ግድፈት በትምህርት ቤት ሃብትና
ንብረት ላይ ብዙ ዋጋ እያስከፈለ ያለ በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ
 ተማሪዎች ቴክኖሎጂን አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ እንዳይጠቀሙ እና በአግባቡ ጠቀሜታ ላይ
እንዲያውሉ ለማድረግ

ክፍል አንድ
1|Page
ጠቅላላ

1.1. አጭር ርዕስ


ይህ መመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የአንደኛ፣የመካከለኛ፣ሁለተኛ ደረጃ እና የልዩ አዳሪ
ት/ቤት የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2. የመመሪያው ተፈጻሚነት ወሰን


የዚህ መመሪያ ተፈጻሚነት ወሰን በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ት/ቢሮ ሥር በሚገኙ
ባለቤትነታቸው በየትኛውም አካል የሆኑ የአንደኛ፣የመካከለኛ፣ሁለተኛ ደረጃ እና የልዩ አዳሪ
ት/ቤቶች ይሆናል፡፡

1.3. ትርጓሜ

በዚህ ደንብ ውስጥ ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ

1.3.1. “የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት” ማለት ከ 1 ኛ-6 ኛ ክፍል ባለው የትምህርት እርከን ውስጥ
የማስተማር አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ማለት ነው
1.3.2. “የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት” ማለት ከ 7 ኛ-8 ኛ ክፍል ባለው የትምህርት እርከን ውስጥ
አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው
1.3.3. “ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት” ማለት ከ 9 ኛ-12 ኛ ክፍል ባለው የትምህርት እርከን አገልግሎት
የሚሰጥ ማለት ነው
1.3.4. ”አዳሪ ትምህርት ቤት” ማለት ለከተማ አስተዳሩ ትምህርት ቢሮ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑትን የእቴጌ
መነን የልጃገረዶች እና የገላን የወንዶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማለት ነው
1.3.5. ‹‹የሳይንስ ሼርድ›› እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከ 9 ኛ እስከ
12 ኛ ክፍል የሣይንስ ትምህርት የሚማሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው
1.3.6. “ተማሪ” ማለት በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ ባለቤትነታቸው በማንኛውም
አካል የሆኑ የአንደኛ ደረጃ፣ የመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመደበኛ፤በማታ እና በርቀት
የትምህርት ፕሮግራም የሚማሩ ማለት ነው፡፡
1.3.7. “የትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ” ማለት የመማር ማስተማሩ ስራ የሚከናወንበት ስፍራ ማለት ነው፡
1.3.8. “ትምህርት ቤት” ማለት ማንኛውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ
የመንግስት፣መንግስታዊ ያልሆነ ፤የግል ፤የሚሽን፤የቤተ ክርስትያን ፤የመስጊድ እና የህዝብ
ት/ቤት ማለት ነው፡፡
1.3.9. “የተማሪ ዲስኘሊን ኮሚቴ” ማለት ተማሪዎች የዲሲፕሊን ግድፈት ፈጽመው በሚገኙበት ጊዜ
ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት ውሳኔ ለመስጠት በት/ቤት ደረጃ የሚቋቋም ኮሚቴ ማለት
ነው፡፡
1.3.10. “የተማሪዎች የደንብ ልብስ” ማለት በመንግስት ት/ቤቶች በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ
የተመረጠ ለተማሪዎች መለያነት የሚያገለግል ተመሳሳይ የጨርቅ ቅርፅ፤መጠን፤ጥራት እና
አዘገጃጀት ያለው ልብስ ሲሆን በመንግስታዊ ያልሆነ ፤የግል ፤የሚሽን፤የቤተ ክርስትያን

2|Page
፤የመስጊድ እና የህዝብ ት/ቤት ደግሞ በጋራ ስምምነት የተመረጠ ሆኖ አገልግሎት በመስጠት
ላይ ያለ የደንብ ልብስ ማለት ነው ፡፡
1.3.11. “ልዩ ፍላጎት” ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የምንላቸው በተለያዩ ምክንያቶች የመማር ችግር
ያጋጠማቸውና በዚህም ሳቢያ የረጅም ወይም የአጭር ጊዜ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን
ያጠቃልላል፣
1.3.12. “ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ” ማለት በተማሪዎች ጉዳይ ላይ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የተወሰነ ውሳኔን
ይግባኝ ለማየት በትምህርት ቤት የሚቋቋም ኮሚቴ ማለት ነው፡፡
1.3.13. ‹‹የትምህርት ማህበረብ›› ተማሪ ፤ወላጅ፤ር/መምህራን ፤ሱፐርቫዘር እና ትምህርት ቤቶችን
በተለያየ መንገድ ሊደግፉ የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍለ ማለት ነው፡፡

1.4. የጾታ አገላለጽ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለጸው ቃል ሁሉ ለሴት ጾታ ያገለግላል

1.5. ተማሪዎች ሊኖራቸው የሚገባ መብት

1.5.1. የመማር፣ ጠይቆ የመረዳትና የማወቅ ፣


1.5.2. ተማሪዎች ከማንኛውም ዓይነት የአካልና ሥነልቦና ጥቃቶች የመጠበቅ፣
1.5.3. በት/ቤቱ የትምህርት ግብዓቶች የመጠቀም ወይም አገልግሎት የማግኘት፣
1.5.4. የትምህርታቸውን ውጤትና የምስክር ወረቀት በወቅቱ የማግኘት፣
1.5.5. ስርአትና ደህንነቱ በተጠበቀ ክፍል እና ት/ቤት የመማር፣
1.5.6. ሃሳባቸውን የመግለጽና የመደመጥ መብት፣
1.5.7. ያለመሰደብ፤የግል ምስጢራዊ ጉዳዮች የመጠበቅ፣
1.5.8. ፆታን መሰረት ካደረገ ጥቃት የመጠበቅ፣
1.5.9 የት/ቤቱን ደንብና መመሪያ የማወቅና የማግኘት፣
1.5.10. ከመምህራን ጋር ተገቢ የሆነ የመማር ማስተማር ግንኙነት በመፍጠር ድጋፍና እርዳታ የማግኘት፣
1.5.11. የሚደርስባቸውን በደልና ቅሬታ በየደረጃው ላሉ የት/ቤቱ አካላት የማቅረብ፣
1.5.12. ስለመምህራን የማስተማር ክህሎት በሚዛናዊነት የመገምገም አስተያየት ሲጠየቁ የመስጠት፣
1.5.13. ከመማሪያ ክፍል ውጭ የሚከናወኑ የተጓዳኝ ትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፍ፣
1.5.14. ለተማሪዎች ከሚሰጠው ልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች የመምረጥና የመመረጥ፣
1.5.15. ከት/ቤት ወይም በቅርብ ከሚገኝ የጤና ማዕከል የመጀመሪያ ዕርዳታ የማገኘት፣
1.5.16. ልዩ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ አገልግሎት የማግኘት እና ከጥቃት የመጠበቅ መብት፣
1.5.17. በት/ቤት የዕቅድ ዝግጅትና የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሳተፍ፣
ክፍል ሁለት
የዲሲፕሊን አፈጻጸምና ውሳኔ አሰጣጥ

2.1. የዲሲፕሊን ቅጣት መሰረታዊ ዓላማ

3|Page
የዲሲፕሊን ቅጣት ዓላማ የተቋሙን (የት/ቤቱን) ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ሲሆን ተማሪው በፈጸመው ጥፋት
ወይም የዲሲፕሊን ጉድለት ተጸጽቶ ወደፊት ብቁ እና ታማኝ ዜጋ ለመሆን እንዲችል ለመርዳት ፣ ለማረምና
ለማስተማር እንዲሁም የማይታረም በሚሆንበት ጊዜ መማር ማስተማሩ እንዳይተጓጎል ከትምህርት ቤት ለማሰናበት
ነው፡፡

2.2. የዲሲፕሊን ጥፋት (ጉድለት) በፈጸመ ማንኛውም ተማሪ ላይ ፣እንደ ጥፋቱ ክብደት ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት
ቅጣቶች አንዱ ሊወሰንበት ይችላል፡፡
2.2.1. የቃል ማስጠንቀቂያ
2.2.2. የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ
2.2.3. ለአንድ ዐመት ከትምህርት ቤት ማገድ
2.2.4. ከትምህርት ቤት ማሰናበት

ከላይ ከተዘረዘሩት ውጪ የሚፈጸም ወንጀል በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከተገኘ በመደበኛው የህግ
ሥርዓት የሚዳኝ ይሆናል፡፡

2.3. የቅጣት አይነቶች አመዳደብ

በዚህ መመሪያ በክፍል 2 በአንቀጽ 2.2.1.እና 2.2.2. የተመለከቱት ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋት ቅጣቶች ሲሆኑ የተቀሩት
ማለትም በክፍል 2 በአንቀጽ 2.2.3. እና 2.2.4.የተዘረዘሩት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ቅጣቶች ተብለው የሚመደቡ
ናቸው፡

2.4. በቀላል የዲሲፕሊን ጥፋት ላይ ስለሚሰጥ ውሳኔ

የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ፤ም/ር/መምህር ወይም የክፍል ተጠሪው መምህር ወይም መምህሩ የቃል ወይም
የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሥልጣንና ሃላፊነት ይኖረዋል፡፡

ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣት ይግባኝ አይጠየቅበትም ሆኖም ተማሪው በውሳኔው ካልተስማማ ለት /ቤቱ ር/መምህር
ማቅረብ ይችላል፡፡

የቀላል ዲሲፕሊን አፈጻጸምን በተመለከተ በመመሪያው አንቀጽ 2.2.1 እና 2.2.2. መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል

2.5. በከባድ የዲሲፕሊን ክስ ላይ በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 2.2.3. እና 2.2.4. የተጠቀሰው ቅጣት በዲሲፕሊን
ኮሚቴ ታይቶ የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ ለትምህርት ቤቱ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ይመራል፡፡
2.6. በኮሚቴው ተመርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ሲቀርብለት ውሳኔ ይሰጣል፡፡የውሳኔውንም ውጤት ለሚመለከተው
አካል ያሳውቃል፡፡
2.7. በተደጋጋሚ የሚፈጸም ቀላል ዲሲፕሊን ጥፋት በከባድ ዲሲፕሊን ጥፋት ሊወሰን ይችላል
2.8. ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች
2.8.1. ት/ቤቱ በሚያወጣው የትምህርት ፕሮግራም መሠረት በሰአቱ ያለመገኘት ያለበቂ ምክንያት ማርፈድ እና
መቅረት፣
2.8.2. በሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ስርአት ላይ አለመገኘትና አለመዘመር፤
4|Page
2.8.3. በተማሪዎች መካከል አላስፈላጊ ጭቅጭቅና ንትርኮች መፍጠር፤
2.8.4. የክፍል ውስጥ ስነስርዓትን ያለማክበር በክፍል ውስጥ መረበሽ፣ መጮህ፣ መብራት ማብራትና ማጥፋት
…. ወዘተ፣
2.8.5. የግልና የጋራ ንፅህናን አለመጠበቅ፣
2.8.6. መምህራንን እና የትምህርት ማህበረሰቡን አለማክበር ፤በት/ቤቱ ውስጥ በተማሪዎች ላይ ጉዳት
ያደርሳሉ ተብሎ ከተከለከሉ ሥፍራዎች እራስን አለማራቅ፣
2.8.7. በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በግልም ሆነ በቡድን በጥሞና አለመከታተል፣
2.8.8. የክፍል ሥራ፣ የቤት ሥራ፣ የቡድን ሥራ የሚሰጡ የችሎታ መመዘኛዎችን ሠርቶ አጠናቆ በጊዜው
አለማቅረብ፣
2.8.9. የት/ቤቱ ኃላፊዎችና መምህራን በአግባቡ የሚሰጡትን ድጋፍ ምክርና መመሪያ አለመፈፀም፣
2.8.10. ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመግባባት አለመስራት፣
2.8.11. በፈተና ወቀት ከተፈቀደላቸው ተማሪዎች በስተቀር ማንኛውንም የተከለከሉ ቴክኖሎጂዎችን ይዞ
ወደ ክፍል መግባት፤
2.8.12. የትምህርት ጊዜን በማይሻማ ሁኔታ ዕውቀቱንና ጉልበቱን ለትምህርት ቤቱና ለአካባቢው
ህብረተሰብ አገልግሎት አለማዋል፣
2.8.13. ማንኛውንም የት/ቤቱን ንብረት የሆኑትን የመማሪያ መጽሐፍትን፣ መቀመጫ ወንበሮችን፣
ጥቁር እና ነጭ ሰሌዳ፤ የፕላዝማ ቴሌቪዥን ፤ሬዲዮን ፤ኮምፒዩተሮች ፤የኢንተርኔት መሰረተ
ልማትና ቁሳቁሶችን፤ የመማሪያ ክፍሎችን፣ መስኮቶችን፣ እና ሌሎች የትምህርት ቤት
ንብረቶችን በጥንቃቄ አለመያዝ ፣ አለመጠቀም እና አንዲበላሹ እና እንዲወድሙ ሙከራ
ማድረግ፣
2.8.14. ሕጋዊ ባልሆኑ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፣
2.8.15. በተለያዩ የተጓዳኝ ክበባት አለመሳተፍ
2.8.16. በትምህርት ሰዓት ያለ በቂ ምክንያት በት/ቤት ቅጥር ግቢ መዟዟር፣
2.8.17. የት/ቤቱን አጥር ዘሎ መውጣት/መግባት/በአጥር መቀበልና ማቀበል፣
2.8.18. ለትምህርት ቤቱም ሆነ ለትምህርት ማህበረሰቡ ታማኝ አለመሆን፣
የት/ቤቱን ማህበረሰብና እራሱን ተላላፊ እና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች አለመጠበቅ አለመከላከል፣
2.8.19. በት/ቤት ቅጥር ግቢ መታወቂያ ይዞ አለመገኘት እና ሲጠየቅ አለማሳየት፣

የተማሪዎች ዩኒፎርም /የደንብ ልብስ/ አጠቃቀም

2.8.20. የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ዩኒፎርም /የደንብ ልብስ/ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት
ቢሮ በሚወስነው የጨርቅ ዓይነት፤ጥራት እና ቀለም እና ስፌት ዲዛይን ያለመጠቀም፣
2.8.21. መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ዩኒፎርም /የደንብ ልብስ የጨርቅ
ዓይነት፤ጥራት እና ቀለም በትምህርት ቤቱ አስተዳደር፤ተማሪዎችና ወላጆች የጋራ ስብሰባ
በውይይት የተወሰነውን አለመጠቀም፣
2.8.22. የወንድ ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የሱሪ ቬል ስፋት ኖርማል ወይም ከ 18 ኢንች ያላነሰ

ሲሆን ይንን አለመተግበር፣

5|Page
2.8.23. የሴት ተማሪዎች የደንብ ልብስ አዘገጃጃት የቀሚስ መጠን ከጉልበት በታች ያለውን 2/3 ኛ የእግር
ክፍል የሚሸፍን መሆን ሲኖርበት ይህንን
2.8.24. ማንኛውም ተማሪ ከተወሰነው የደንብ ልብስ ዓይነት፤ጥራትና ቀለም ውጪ መጠቀም ፣
2.8.25. ከት/ቤቱ ህጋዊ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት ፅሁፍ ማሳተም፤ሌላ የጨርቅ ዓይነት ቀጥሎ
ማሰፋት እና ያልተፈቀደ የደንብ ልብስ ዓይነት ፤ቅርፅና ይዘት መጠቀም፣
2.8.26. የተማሪዎች ዩኒፎርምን በተመለከተ የማታ እና የርቀት ተማሪዎችን አይመለከትም፤

የተከለከሉ የተማሪዎች የፀጉር አቆራረጥ እና አያያዝ

2.8.27. የፀጉርን ንፅህና አለመጠበቅ፣


2.8.28. ማንኛውንም አይነት የፀጉር ቀለም መቀባት፤
2.8.29. የወንድ ተማሪ ፀጉራቸውን በአጭሩ አለመቆረጥ፤
2.8.30. ሴት ተማሪዎች ፀጉራቸውን አለማበጠርና አለማስያዝ፤
2.8.31. ለሴት ተማሪዎች ተንጠልጣይ የጀሮ ተንጠልጣይ ጉትቻ ማድረግ፤ እና ከጆሮ ውጭ የትኛውም
የሰውነት አካል ላይ ለማጌጥ ተብሎ ማስበሳትና ጌጦችን ማድረግ፤
2.8.32. ወንድ ተማሪ የጀሮ ጌጥ ማድረግ፤
2.9. ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት

ለአንድ ዓመት ከትምህርት ቤት የሚያሳግድ ጥፋት

2.9.1. በትምህርት ቤት ውስጥ የስርቆት ድርጊት ፈጽሞ መገኘት፣


2.9.2. ሴት ተማሪዎችን መተንኮስ፣ ማስፈራራት፣
2.9.3. ቁማር መጫወት እና ከመሳሰሉ ሕገወጥ ድርጊቶችና ጥፋቶች አለመራቅ፣
2.9.4. ሲጋራ ማጨስ፣ ቬፒንግ/ኢ-ሲጋሬት/፤ ኢ-ሊኩዊድ፣/ መጠቀም የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ
መገኘት፣ሺሻ ተጠቅሞ መምጣት ጫት ቅሞ መምጣት ሌሎች አደንዛዥ ዕጾችን ተጠቅሞ
መምጣት፣
2.9.5. ት/ቤቱና ወላጅ ባላወቁት እና አሳማኝ ባላሆኑ ምክንያቶች ከት/ቤት በአመቱ የትምህርት
ካላንደር 10% መቅረት አሳማኝ በሆኑ ምክንያቶች 2 ዐ% በላይ መቅረት፤
2.9.6. የት/ቤቱን ንብረት ሆንብሎ መስበር፣ ማበላሸት ማጥፋት፣
2.9.7. በፈተና ወቅት ሁከት መፍጠር ፣ የፈተና ሰርዓቱ እንዲደናቀፍ ማድረግ መኮረጅና ማስኮረጅ፣
2.9.8. የት/ቤቱን መምህራን፤ ሠራተኞችና ኃላፊዎችን መሳደብና ማንጓጠጥ እና ለመደብደብ
መሞከር፤
2.9.9. ተማሪዎችን መደብደብ ንብረት መንጠቅ ማስፈራራት፣
2.10. ከትምህርት ቤት እስከ መጨረሻው የሚያሳግድ ጥፋት
2.10.1. አደገኛ የሆኑ ስለታማ እና የጦር መሳሪያዎችን በት/ቤት ቅጥር ግቢ ይዞ መገኘት፣
2.10.2. በፈተና ወቅት ስልክ፣ታብሌት ይዞ መምጣት፤ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ መጠቀም ተገቢ ያልሆነ
ተግባር ማከናወን፤ (ተማሪ የሚያወናብዱ መረጃዎች ማስተላለፍ፤ ወዘተ)
2.10.3. ሴት ተማሪዎችን መደባደብና ሰብአዊ መብታቸውን መጣስ፣
6|Page
2.10.4. ማንኛውም ጾታዊ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት መፈጸም
2.10.5. ትምህርት ሴኩላር በመሆኑ በት/ቤት ግቢ ውስጥ ሀይማኖታዊና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን
ማካሄድ፣
2.10.6. በማንኛውም የቡድን ጸብ እና አምባጓሮ ተግባር ላይ መሳተፍ ፣
2.10.7. ከኢትዮጵያዊ እሴቶች ያፈነገጡ እና ህጋዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን እና በዓላትን ማክበር እና
መፈጸም ለምሳሌ /ዋተርዴይ፤ክሬዚ ዴይ፤እራቁት ቀን ከለር ዴይ ወዘተ…/
2.10.8. በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም በአካልና በጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ የጦር መሳሪያ ይዞ
መገኘት፣
2.10.9. የት/ቤቱን ንብረት ሆን ብሎ ለጉዳት ማጋለጠ፣
2.10.10. በት/ቤት ውስጥና አካባቢ ሴት ተማሪዎችን መድፈር፣
2.10.11. በፈተና ወቅት ለሌላ ተማሪ መፈተን ወይም ለራስ ማስፈተን፣
2.10.12. የተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ አቅርቦ መገኘት፣
2.10.13. መምህራንና የትምህርት ቤቱን ሠራተኞች መደባደብ፣
2.10.14. ለአንድ ዓመት ቅጣት ተፈጻሚ የሆነ ተግባርን በድጋሚ በተመ

2.11. የቅጣት ቅደም ተከተሉን ባለመጠበቅ ስለሚሰጥ ውሳኔ


በዚህ መመሪያ መሰረት የተፈጸመው የዲሲፕሊን ጥፋት ክብደት ተመዝኖ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 2.2. ስር
ከተዘረዘሩት የቅጣት አይነቶች መካከል ቅደም ተከተሉ ሳይጠበቅ አንዱን ለመወሰን ይቻላል፡፡
2.12. ከትምህርት ገበታ ሊያሳግድ የሚችል የቅጣት አወሳሰን

ከትምህርት ገበታ ሊያሳግድ የሚችል ጥፋት በተማሪዎች ሲፈጠር የክፍል ኃላፊ መምህሩ በየጊዜው የተመዘገበ
መረጃ ፤ከወላጁ ጋር የተደረገ ውይይት፣ ተማሪው የፈረመበት፣ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት አጠቃላይ የተማሪውን
ባህሪ ሊገልፅ የሚችል መረጃ በት/ቤቱ ር/መምህር በኩል ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ያቀርባል፡፡

2.13. ከላይ የተመለከተውን መነሻ በማድረግ የት/ቤቱ የዲስኘሊን ኮሚቴ በተማሪው ላይ አግባብነት ያለው እርምጃ
ይወስዳል፣
2.14. ተማሪው ከትምህርት ገበታው ከታገደበት ጊዜ ጀምሮ በ 5 ቀን ውስጥ ለዲሲፕሊን ኮሚቴው መቅረብ
ይኖርበታል፡፡
2.15. ተማሪውን ከትምህርት አግዶ ማቆየት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እግዱ የሚፈጸመው በትምህርት ቤቱ ር /መምህር
ይሆናል፡፡
2.16. ውሳኔ ሳያገኝ ከ 15 ቀናት በላይ የቆየ ተማሪ ያለምንም ተጨማሪ ሥነሥርአት ወደ ትምህርት ገበታው
እንዲመለስ ይደረጋል፡፡
2.17. ተማሪው ከትምህርት ገበታው የታገደበትን ምክንያትና ታግዶ የሚቆይበትን ጊዜ እግዱን በሰጠው አካል
በጽሁፍ ይገለጽለታል፡፡
2.18. እግዱ የማገጃው ትእዛዝ በጽሁፍ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

ምዕራፍ ሦስት

3. ስለዲሲፕሊን ኮሚቴ መቋቋምና አሰራር


7|Page
3.1. የዲሲፕሊን ኮሚቴ ስለ ማቋቋም
በየትምህርት ቤቱ ጉዳዮችን እየመረመረ የውሳኔ ሃሳብ ለትምህርት ቤቱ ርዕስ መምህር ወይም ምክትል ርዕስ
መምህር የሚያቀርብ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ይቋቋማል፡፡
3.2. የኮሚቴው አባላት ስብጥር
3.2.1. የተማሪዎች የዲሲፕሊን ኮሚቴ ስብጥር
የተማሪ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡፡ የኮሚቴው አወቃቀርም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ሀ. በርዕሰ መምህሩ የሚሰየም አንድ ሰው ---------------------------------------- ሰብሳቢ
ለ. በርዕሰ መምህሩ የሚሰየም አንድ ሰው-------------------------------------------አባል
ሐ. ከተማሪዎች ፓርላማ/ካውንስል 2 ተወካይ አንዷ ሴት ----------------አባል
መ. ከትምህርት ቤቱ መሰረታዊ መምህራን ማህበር አንድ ተወካይ ----------- አባል
ሠ. የወላጅ፣ የተማሪ፣ መምህር ህብረት ወ.ተ.መህ/ ተወካይ -------------------አባል
ረ. የት/ቤቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ተወካይ ------------------------------- አባልና ጸሀፊ
3.3. የኮሚቴ አባላት መመዘኛ
ማናቸውም የኮሚቴ አባል፡-
3.3.1. በጠባዩና በስራ አፈጻጸሙ የተመሰገነ፣
3.3.2. ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በዲሲፕሊን ጉድለት ያልተቀጣ፣
3.3.3. መምህራንና ሰራተኞች በትምህርት ቤቱ ወይም በተቋሙ ግቢ ውስጥ ቢቻል ከሁለት አመት በላይ
አገልግሎት ያላቸው ሊሆን ይገባል፡፡
3.4. የኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን
3.4.1. ከትምህርት ቤቱ የተመረጡት የኮሚቴ አባለት የአገልግሎት ዘመን ሁለት
አመት ይሆናል፡

3.4.2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3.4.1. እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ ሲሆን ተወካዮች ለአንድ ጊዜ
በድጋሚ ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
3.5. ከኮሚቴው አባልነት ስለመሰረዝና ከስብሰባ ስለመነሳት

3.5.1. የኮሚቴው ሰብሳቢ ወይም ማንኛውም አባል ክስ ከቀረበበት ተማሪ ጋር ፀብ ያለው ወይም በስጋ
ወይም በጋብቻ ዝምድና ያለው መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ ወይም ከሳሽ በሚሆንበት ጊዜ ለዚያ ጉዳይ ብቻ
ከኮሚቴው አባልነት እንዲነሳ ይደረጋል፡፡
3.5.2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3.5.1. በተገለፀው መሰረት የኮሚቴ ሰብሳቢው ከሰብሳቢነት የሚነሳ
ከሆነ የቀሩት የኮሚቴ አባላት ከመሃከላቸው ለዚህ ጉዳይ ብቻ ሌላ ሰብሳቢ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡
3.5.3. ማንኛውም የኮሚቴ አባል ራሱን ከጉዳዩ በማግለልና ሌላውን አባል ለማስጠላት ከባለጉዳዩ ጋር
እንዳይገናኝ ሚስጥር ያወጣ ወይም ቃለጉባኤዎችን መረጃዎችንና ጽሁፎችን ለባለጉዳዩ ያሳየ ወይም
ያጋለጠ ወይም የሰጠ እንደሆነ በዚህ መመሪያ ከባድ ጥፋት ናቸው ተብለው የተዘረዘሩትን እንደፈጸመ
ተቆጥሮ ከኮሚቴው አባልነት ይሰረዛል፡፡ በምትኩም ስልጣን ባለው የበላይ ኃላፊ እንዲሰየም ይደረጋል፡፡
3.6. የኮሚቴው ምልአተ ጉባኤና ድምጽ አሰጣጥ

8|Page
3.6.1. በኮሚቴው ስብሰባ ላይ ሰብሳቢውን ጨምሮ ከግማሽ አባላት በላይ ከተገኙ ምልአተ ጉባኤ ይሆናል፤
ከተገኙ አባላት ቢያንስ አንዱ የተማሪ ተወካይ መሆን ይኖርበታል፡፡
3.6.2. ኮሚቴው ሰብሳቢ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢቀር የቀሩት አባላት ከመካከላቸው ለጊዜው
ሰብሳቢ ይመርጣሉ፡፡
3.6.3. አከራካሪ ጉዳይ ሲገኝ የኮሚቴው አስተያየት የሚያልፈው በድምጽ ብልጫ ሲሆን የቀረበ ሀሳብ እኩል
በእኩል የተከፈሉ እንደሆነ ሰብሳቢው ባለበት ወገን የቀረበ ሀሳብ ያልፋል፡፡ ሆኖም በሃሳብ የተለየ አባል
የተለየበት ምክንያት በቃለ ጉባኤ ይሰፍራል፡፡
3.7. ስለ ዲሲፕሊን ክስ አመሰራረትና ሁኔታ
የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረትና ጉዳዩ በዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲጣራ በትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ም/ር መምህር
ሲታዘዝ በትምህርት ቤቱ የሰው ኃይል አስተዳደር የዲሲፕሊን ክሱን ይመሰረታል፡፡
3.7.1. የዲሲፕሊን ኮሚቴው ሰብሳቢ የዲሲፕሊን ክስ ተዘጋጅቶ ማስረጃዎቹ ተጠናቀው ሲቀርብለት
ተከሳሹ ለተነገረበት ጥፋት መከላከያ ለማቅረብ እንዲችል መጥሪያ ይልክለታል፡፡
3.7.2. የሚላከው መጥሪያ ተከሳሹ የተነገረበትን ዝርዝር ጥፋት በዲሲፕሊን ኮሚቴው ስብሰባ ላይ
የሚያቀርብበትን ቀን ሰአትና ቦታ በመግለጽ የዲሲፕሊን ክሱን በጽሁፍና ማስረጃዎች ቅጂ እና የክስ
ማስታወቂያ መያዝ አለበት፡፡
3.7.3. ተከሳሹ ለቀረበበት ክስ መልስና የመከላከያ ማስረጃ የሚያቀርብበትን ጊዜ የክሱ ጽሁፍ
ከደረሰው ቀን ጀምሮ ከሶስት ቀን ማነስ የለበትም፡፡
3.7.4. የተከሳሹ አድራሻ ያልታወቀ እንደሆነ በኮሚቴው ስብሰባ ላይ የሚገኝበት ቀን ሰአትና ቦታ
ተገልጾ የጥሪ ማስታወቂያ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ እንዲቆይ
ይደረጋል፡፡ በተወሰነ ጊዜ ተከሳሹ ካልቀረበ ተከሳሹ በሌለበት ክሱ ተሰምቶና ተመርምሮ ውሳኔ
ይሰጣል፡፡
3.7.5. የዲሲፕሊን ኮሚቴው የዲሲፕሊን ክሱ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በ 10 ቀናት ውስጥ የውሳኔ
ሃሳብ ለትምህርት ቤቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3.8. የዲሲፕሊን ኮሚቴ አሰራር
3.8.1. ኮሚቴው በዚህ መመሪያ የተሰጠውን ተግባር በሚያከናውንበት ጊዜ የሚያስፈልጉትን
ማህደሮች፣ መረጃዎችና ሰነዶች አስቀርቦ ማየት እንዲሁም አግባብነት ያለውን የሰው የምስክር
መጥራትና መስማት ይቻላል፡፡
3.8.2. ኮሚቴው በተማሪው ላይ የቀረበውን ክስ በሚያጣራበት ጊዜ
3.8.3. የተከሳሹ ሙሉ ስም ከነ አያት
3.8.4. ተከሳሹ የተከሰሰበትን ጭብጥ
3.8.5. ክሱን ያረጋግጣሉ ተብለው የቀረቡትን የጽሁፍ ሆነ የሰው ምስክርነት ማስረጃዎች፣
3.8.6. በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኘውን የተከሳሹን የግል ማደር፤ለቀረበው ክስ አግባብነት
ያላቸውን ህጎች፣ ደንቦችና፣ መመሪያዎች፤ የጽሁፍና የሰው ማስረጃዎች፤አግባብነት አላቸው ብሎ
የሚገምታቸውን ማስረጃዎች እንደአስፈላጊነቱ በማስቀረብ መመርመር ይቻላል፡፡
3.9. ኮሚቴው የቀረበውን ክስ በማስረጃ በሚያጣራበት ጊዜ

9|Page
3.9.1. ለተከሳሹ ክሱና ማስረጃው በጽሁፍ እንዲደርሰውና የመከላከያ መልሶችን በጽሁፍ የማቅረብ
መብት እንዲጠበቅለት
3.9.2. የከሳሹ ምስክሮች ሲቀርቡ ተከሳሹ በተገኘበት ቃላቸውን እንዲሰጡና የተከሳሹም
የሚፈልገውን የመስቀለኛ ጥያቄ እንዲያቀርብ እንዲሁም የተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ
በሚሰማበት ጊዜ ከሳሽ ተገኝቶ የመስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ መብት እንዲጠበቅለት፣
3.9.3. ተከሳሹ የመደመጥ፣ የመከራከርና በበኩሉ የመከላከያ ማስረጃዎችና ክርክሮቹንም የማቅረብ
መብቱ ተጠብቆ ክሱ በማስረጃ እንዲጣራ የማድረግ፣
3.9.4. የዲሲፕሊን ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ከደረሰው የዲሲፕሊን ጉደለት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆንና
ለተመሳሳይ ጥፋትም ተመሳሳይ ቅጣት እንዲሰጥ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
3.9.5. የስብሰባው ቃለ ጉባኤ በትክክል እየተጻፈና እየተዘጋጀ አባላቱም እንዲፈርሙበት ሆኖ በጥንቃቄ
መቀመጥ አለበት፤
3.9.6. ከሳሽና ተከሳሽ እንዲሁም ምስክሮች የሚሰጡትን ቃል በትክክልና በጥንቃቄ መመዝገብና ቃል
ሰጭዎች በስብሰባው መጨረሻ ላይ እንዲፈርሙበት መደረግ አለበት፡፡
3.9.7. በሁለቱም ወገን የሚቀርቡ ማስረጃዎች ተመዝግበውና ለኮሚቴው ቀርበው ከታዩ በኋላ
ፋይሉን አደራጅቶ በጥንቃቄ ማስቀመጥ አለበት፤
3.9.8. ለተከራካሪ ወገኖች፣ለምስክሮችና ለሌሎች አስረጂዎች የሚሰጡ መጥሪያዎች እንዲሁም
ሌሎች ደብዳቤዎች የተዘጋጁና ሰብሳቢው እየፈረመባቸው ለሚመለከተው ተማሪ
መድረሳቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል፣

3.10. ለዲፕሊን ኮሚቴው ስለሚቀርቡ የጽሁፍ ማስረጃ


3.10.1. ተከሳሹ ለተነገረበት ጥፋት ማፍረሻ ወይም መከላከያ የሚሆነውን የጽሁፍ ማስረጃ ወይም
ምስክሮች ማቅረብ ይችላል፡፡
3.10.2. ተከሳሹ እንዲቀርብለት ወይም ግልባጭ እንዲሰጠው የጠየቃቸው የጽሁፍ
ማስረጃዎች፣ከጭብጡ ጋር አግባብነት ያላቸውን መሆኑን ሲያምንበት እንዲቀርብ
የሚመለከተውን ክፍል ሊጠይቅ ይችላል፡፡
3.10.3. ትምህርት ቤቱ በኮሚቴው ሲጠየቅ የጽሁፍ ማስረጃ አቅርቦ የማሳየት ወይም ትክክለኛ
ግልባጩን የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
3.10.4. ተከሳሹ ጭብጡን የሚያስረዱለት ምስክሮች እንዲጠሩለት ስማቸውንና አድራሻቸውን
ዘርዝሮ ጥያቄውን ካቀረበ ኮሚቴው እንዲጠሩና ቀርበው እንዲመሰክሩ ለማድረግ ይቻላል፡፡
3.11. የዲሲፕሊን ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ አቀራርብ
3.11.1. ኮሚቴው የቀረበለትን የከባድ የዲሲፕሊን ክስ መርምሮ የውሳኔ ሃሳቡን ለትምህርት ቤቱ የበላይ
ሀላፊ አቅርቦ በኃላፊው እንዲወሰን ያደርጋል ፡፡
3.11.2. በምርመራው ውጤት ላይ ተመስርቶ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የቀረበለት የዲሲፕሊን ጉዳይ
ተቀባይነት የሌለው ከሆነ ውድቅ መሆኑን ከነምክንያቱ በመዘርዘር የውሳኔ ሃሳብ ለትምህርት ቤቱ
የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡

10 | P a g e
3.11.3. የቀረበው ክስ በሙሉ ወይም በከፊል በማስረጃ የተረጋገጠ ከሆነ እንደ ነገሩ ክብደት ለተፈጸመው
ጥፋት ተመጣጣኝ የሆነ የዲሲፕሊን ቅጣት በዚሁ መመሪያ በተራ ቁጥር 2.2. ከተዘረዘሩት
የዲሲፕሊን ቅጣቶች ውስጥ አንዱን የቅጣት ውሳኔ ሀሳብ ለሚመለከተው ኃላፊ ያቀርባል፡፡
3.11.4. የዲሲፕሊን ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ በትምህርት ቤቱ የበላይ ኃላፊ ውሳኔ ተሰጥቶበት በጽሁፍ
ለተከሳሽ እስኪሰጥ ድረስ በሚስጢር መጠበቅ አለበት፡፡
3.11.5. የዲሲፕሊን ኮሚቴው ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የትምህርት ቤቱ የበላይ ኃላፊ በአምስት የስራ
ቀናት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ለተከሳሹ በጽሁፍ እንዲሰጠው መደረግ አለበት፡፡
3.12. የዲሲፕሊን ቅጣት አወሳሰን
3.12.1. የተማሪ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በዚህ መመሪያ 3.2.1.በተቋቋመው ኮሚቴ ታይቶ የውሳኔ ሃሳብ
የሚቀርብ ሲሆን በሚቀርብለት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ውሳኔ መስጠት የሚችለው የትምህርት ቤቱ
ርዕሰ መምህር ም/ርዕሰ መምህር ወይም ይሆናል፡፡
3.12.2. በዲሲፕሊን የሚወሰን ቅጣት የማናቸውንም ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ አለመጠበቁ
በዲሲፕሊን የሚወሰነው ቅጣት የማናቸውም ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ ስለማይከተል ስለዲሲፕሊን ጉድለት
አፈጻጸም በዚህ መመሪያ የተገለጸውን በመከተል የፍ/ቤት ወይም የሌላ መስሪያ ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ
ራሱን በቻለ ተለይቶና ተጣርቶ መወሰን አለበት ፡፡
3.13. የዲሲፕሊን ቅጣት በሪከርድነት ስለሚቆይበት ጊዜ
3.13.1. ለቀላል ዲሲፕሊን ቅጣት ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለአንድ አመት
3.13.2. ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ዓመት ይሆናል

ክፍል አራት
4. የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ስለማቋቋም እና የቅሬታ አቀራረብ ስነ-ስርዓት
4.1. የቅሬታዎች የማስተናገጃ ስነ-ስርዓት ዓላማ
4.1.1. ለቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት፣
4.1.2. ለቅሬታዎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን በማረም እና
4.1.3. ሁሉንም በኩልነት ለማስተናገድ የሚያስችልና ፍትሀዊ የሆነ አሰራር በማስፈን የሰመረ ግንኙነት
እንዲዳብር ማድረግ ይሆናል ፡፡
4.2. የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ስለማቋቋም
በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅሬታን አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ለበላይ ሀላፊ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በዚህ መመሪያ ተቋቁሟል ፡፡ ሆኖም የዲሲፒሊን ኮሚቴ አባል የሆነ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባል
ሆኖ ሊሰየም /ሊወከል/ አይችልም፡፡
4.3. የኮሚቴው አባላት
የተማሪዎች ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡፡ የኮሚቴው አወቃቀርም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ሀ. በርዕሰ መምህሩ የሚሰየም አንድ ------------------------------------ ሰብሳቢ
ሐ. ከተማሪዎች ፓርላማ/ካውንስል 2 ተወካይ አንዷ ሴት ------------------አባል

11 | P a g e
ሐ. ከትምህርት ቤቱ መሰረታዊ መምህራን ማህበር አንድ ተወካይ ------------ አባል
መ. ከትምርት ቤቱ የሥርዓተ ጾታ ተወካይ አንድ ------------------------------- አባል
መ. የወላጅ፣ የተማሪ፣ መምህር ህብረት ወ.ተ.መህ/ አንድ ተወካይ ---------------አባል
ረ. የት/ቤቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ተወካይ ------------------------------- አባልና ጸሀፊ
4.4. በበላይ ሃላፊው ስለሚሰየሙ አባላት አሰያየም
በዚህ አንቀጽ 4.3. የተመለከቱት የኮሚቴው አባላት የሚሰየሙት ከትምህርት ቤቱ ይሆናል፡፡
4.5. የኮሚቴ አባልነት መመዘኛ
ማናቸውም የኮሚቴ አባል፡-
4.5.1. በመልካም ስነ ምግባሩና በስራ አፈጻጸሙ የተመሰገነ፣
4.5.2. ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በዲሲፕሊን ጉድለት ያልተቀጣ፣
4.5.3. ከተማሪዎችና ወ.ተ.መ..በስተቀር ሌሎች ቋሚ የመንግስት ሰራተኞች የሆነና በመንግስት መስሪያ
ቤት ውስጥ ከሁለት አመት በላይ አገልግሎት ያለው ሊሆን ይገባል፡፡

4.6. የአገልግሎት ዘመን


4.6.1. የኮሚቴ አባለት የአገልግሎት ዘመን ሁለት አመት ይሆናል፡፡ሆኖም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ እንደገና
ለአንድ የአገልግሎት ዘመን ሊመደብ ወይም ሊመረጥ ይችላል፡፡
4.6.2. ከላይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4.6.1. የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር
ወይም በሚመለከተው የበላይ ኃላፊ የሚመደቡ የኮሚቴ አባላት እንደአስፈላጊነቱ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡
4.7. የኮሚቴ ስብሰባ
4.7.1. የቅሬታ ስብሰባ
4.7.1.1. የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ለስራው ባስፈለገ መጠን በማንኛውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
4.7.1.2. በኮሚቴው ስብሰባ ላይ ሰብሳቢውና ሌሎች ሶስት አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
4.7.1.3. የኮሚቴው ውሳኔ የሚያልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል፡፡ ድምጽ እኩል ለእኩል የተከፈለ
እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ያቀረበው ሃሳብ ያልፋል፡፡ በሀሳብ የተለየው አካል የተለየበትን ምክንያ
በግልጽ ማስፈር አለበት፡፡
4.8. ከአባልነት ስለመሰረዝና ከስብሰባ ስለመነሳት
4.8.1. ማንኛውም የኮሚቴ አባል ክስ ከቀረበበት ሰራተኛ ጋር ፀብ ወይም የስጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው
መሆኑ ሲረጋገጥ ለዚያ ብቻ ከስብሰባው እንዲነሳ ይደረጋል፡፡
4.9. ማንኛውም የኮሚቴ አባል
ሀ. በኮሚቴው በመለየት ላይ ያለን ጉዳይ በሚመለከት ሚስጥር ያባከነ
ለ.የኮሚቴውን ስራ በማናቸውም አኳኋን ያደናቀፈ ፣ወይም
ሐ.በዚህ መመሪያ አንቀጽ 28 የተመለከቱትን መመዘኛዎች ያጓደለ እንደሆነ ከአባልነት ሊሰረዝ ይችላል፡፡
4.10. ቅሬታ የማቅረብ መብት
4.10.1. ማንኛውም ተማሪ ህጋዊ መብቴ ተጓድሎብኛል ወይም በደል ተፈጽሞብኛል በማለት ቅር የተሰኘ
እንደሆነ ቅሬታውን እንዲታይለትና የመፍትሄ እርምጃ እንዲወሰድለት ቅሬታውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
የማቅረብ መብት አለው፡፡
4.10.2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
12 | P a g e
4.11. የቅሬታ ማመልከቻ
4.11.1. ቅሬታው እንዲሰማለት የሚፈልግ ተማሪ የቅሬታ ማመልከቻውን ለመስሪያ ቤቱ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
ለማቅረብ ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው ከዲሲፕሊን ኮሚቴ መፍትሄ ካላገኘ ነው፡፡
4.11.2. የቅሬታ ማመልከቻ የሚከተለውን መያዝ አለበት
ሀ. የአመልካች ስምና አድራሻ
ለ.የክፍል ደረጃ እና ሴክሽን
ሐ.የቅሬታ የቀረበበት አካል
መ.የቅሬታው መንስኤ
ሠ.ደጋፊ ማስረጃዎች /ካሉ/
ረ.የሚሻውን መፍትሄ
ሰ.ቀንና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
4.11.3. የቅሬታቸው መንስኤ አንድ አይነት የሆነ የቅሬታ ማመልከቻቸውን በተወካያቸው አማካይነት በቡድን
ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
4.11.4. ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜና ገደብ
4.11.4.1. ቅር የተሰኘ ተማሪ ውሳኔው ከተወሰነ በ 5 ቀን ውስጥ ጉዳዩን ለትምህርት ቤቱ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
ሊያቀርብ ይችላል፡፡
4.11.4.2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4.11.4.1. በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
የቅሬታውን ማመልከቻ ሊያቀርብ ያልቻለ ተማሪ ከአቅም በላይ የሆነው ምክንያት በተወገደ በአስር የስራ
ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡
4.11.5. ቅሬታውን ስለማጣራት
4.11.5.1. የትምህርት ቤቱ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማመልከቻ ሲቀርብለት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 4.11.
የተደነገገውን አሟልቶ የቀረበ መሆኑን በማረጋገጥ ተቀብሎ ይመዘግባል፡፡
4.11.6. ኮሚቴው
ሀ. የቅሬታ ማመልከቻውንና አግባብ ያላቸውን ማስረጃዎች በመመርመር፣
ለ. ከአመልካቹ እና በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ከሰጠው የስራ ኃላፊ ጋር በመወያየት እና
ሐ. አግባብ ያላቸውን ህጎች፣ ደንቦች መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶች በማገናዘብ፣ የቀረበለትን ቅሬታ ያጣራል፡፡
4.11.7. ኮሚቴው የምርመራውን ውጤትና የውሳኔ ማመልከቻውን ከቀረበለት ቀን ጀምሮ እጅግ ቢዘገይ አምስት የስራ
ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው የበላይ ኃላፊ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
ክፍል አምስት
5. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

5.1. የማስረጃ ወጭ
የማስረጃዎች አቀራረብ የገንዘብ ወጭ የሚያስከትል ከሆነ ማስረጃው እንዲቀርብለት የሚፈልገው ወገን
ለሚያቀርበው ማስረጃ የሚያስፈልገው ወጭ ራሱ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተከሳሹ ማስረጃ ይሆኑኛል ያላቸው በከሳሹ
ትምህርት ቤት ይዞታ ስር ከሆነና በዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲቀርብ ከታዘዙ የሚያስከትለው ወጪ እንዲሸፍን
አይጠየቅም፡፡

13 | P a g e
5.2. ተከሳሽ የሚከራከርለት ሰው ለመወከል ስለመቻልተከሳሽ በዲሲፕሊን ወይም በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ላይ
በሚከራከርበት ጊዜ የመረጠውን ሰው ይዞ ለመቅረብ፣ ለመወከል ወይም እንዲከራከርለት ለማድረግ መብት አለው፡፡
ይህንንም ተከሳሽ ኮሚቴው ፊት ቀርቦ በጽሁፍ ማስታወቅ አለበት፡፡
5.3. ከዚህ በፊት በተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያነት ሲያገለግል የቆየው በዚህ መመሪያ ተሸሯል፡፡

5.4. ይህ መመሪያ በየጊዜው እየታየ በትምህርት ቢሮ የሚሻሻል ይሆናል፡፡

5.5. ይህ መመሪያ ከየካቲት 2 ዐ 15 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የትምህርት ቢሮ

የካቲት 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

14 | P a g e
15 | P a g e

You might also like