Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 21

ንጉሡ እና ምርኮኛው

መነሻ ሀሳብ - ሄኖክ ገለታ


ደራሲ - ቸርነት አበበ እና ሔኖክ ገለታ

ስክሪፕት ሪራይተርስ
- አድኖን ነጋሽ
- ቸርነት ታመነ
- ትዝታ ማናዬ
- ዮርዳኖስ ሙሉጌታ
- ሄኖክ ገለታ
- መላኩ ፋንታሁን
- ቸርነት አበበ

መቼት ፦ ንጉሳዊ አገዛዝ እና ስልጣኔ ያለበት (የራሳችን ጊዜ)


ገቢር-አንድ
ትዕይንት አንድ

በአንድ ጥንታዊ የሚመስል ቤተ-መንግስት ውስጥ የንጉሱ ልደት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ። ንጉሡ ፣ ንግስቲቷ ፣
ታላላቅ ተጋባዥ ባለስልጣናት እና ልዩ እንግዶች ቦታው ላይ ተገኝተው እየበሉ እየጠጡ ይዝናናሉ ። ንጉሱ ከንግስቲቱ
ጋር ሰልፊ ፎቶ እየተነሳ በደስታ ይስቃል ። ሌሎች ህብረ ዘማሪያኖች እና ዳንሠኞች እየዘፈኑ እና እየደነሱ ንጉሡን
በልዩነት ያወድሡታል ። ለንጉሱ ድግስ የተዘጋጀው የትግል ውድድር እንደጀመረ ተጋባዥ እንግዶች በትግሉ መወራረድ
ማስያዝ ይጀምራሉ ። አንድ በጣም የተራበ እና ዘኬ የለመደ ሰው የንጉሱ ድግስ ላይ ሀብታም የሚያስመስለውን ልብስ
ለብሶ ይገባል ነገር ግን አጭበርብሮ እንደገባ ታውቆበት ይያዛል ። በዚህም ንጉሱ ቅጣት ይጥልበታል ።

ደጀኔ ፦ (አጭበርብሮ የገባውን ሰው ወደ ንጉሱ ያቀርበዋል )

( ንጉሱ አጭበርብሮ የገባውን ሰው እየተመለከተ )

ንጉሱ ፦ (በንቀት ልብሱን እየነካው) ማነው የሰጠህ


በርተሚዎውስ ፦ (በሚያሳዝን ልመና )ንጉስ ሆይ እባኮን ይቅርታ ያድርጉልኝ... ምግብ ከበላሁ ሶስት ቀን
አለፈኝ..ስቃዩን መቋቋም ቢያቅተኝ ነው ልብስ ሰርቄ ወደዚህ የገባሁት

ንጉሱ :- አንተ መናጢ ምንም ብትዘንጥ ክርፋትህ ሊለቅ እንደማይችል ማሰብ ነበረብህ !

ንጉሱ ፦( እራሱን ይወጋው እና ትንሽ አዙሮት ተንገዳግዶ ይቆማል አሽከሮቹ በድንጋጤ ንጉሱን ሊደግፉት
ይሞክራሉ እንዳይነኩት በመከላከል በራሱ ይቆማል ። )

ንግስቷ ፦ የኔ ውድ እባክህን ተው ይበቃሀል ማረፍ አለብህ (ለማረጋጋት እየሞከረች)

(ንጉሱ ከመጠን በላይ ሰክሮ ንግስቲቱን ሊያስደንሳት ይሞክራል ። )

ንጉስ ፦ ትንሽ ሞቅ ብሎኝ ይሆናል የኔ ንግስት... አንቺን ለምን እንደመረጥኩሽ ታውቂያለሽ ?.. /ደጀኔ / ንገራት

ደጀኔ :- / ካለበት ፈጥኖ እየሮጠ በመውጣት / ንጉስ ሆይ እንደሷ ያለ መልከ መልካም የልብዎ ይቺን ቆንጅዬ
ንግስት...

ንጉስ:- ሂድ / በእጁ ምልክት / (ደጀኔ ወደመጣበት ፈጥኖ ይመለሳል ። ንጉሡ በርካታ በእድሜ የገፉ ልዩ
አማካሪዎቹን) ለምን እንደሆነ በትክክል ንገሯት !

/3 ቱ የንጉሡ አማካሪዎች ከያሉበት ፈጥነው ይወጣሉ ። /

1 ኛው ሽማግሌ አማካሪ ፦ ጌታዬ ሆይ ምናልባት በውበቷ ይሆን

3 ኛው ሽማግሌ አማካሪ ፦ ንጉስ ሆይ በስርዓቷ እና በደም ግባቷ ..( አንገቱን ይደፋል )


(ንጉሱ ጀርባውን ሠቷቸው ከሚስቱ ጋር ይደንሳል ። )

1 ኛው ሽማግሌ አማካሪ ፦ ይህን ውድ እና የተከበረ ዘሮን ለማስቀጠል ይሆን ወይ ግርማዊነቶ

2 ኛው ሽማግሌ የንጉሡ አማካሪ ፦ የንግስቲቷን ያህል በዚህ ዓለም የሚወዱት ሠው ስለሌለ ንጉስ ሆይ !

ንጉስ ፦ አንተ ከዚ በኋላ ከቀኝ እጆቼ መሀል አንዱ ነህ እንደውም የሳራኮስ ግዛቴ መሪ አድርጌ ሾሜ U ለሁ ። (በደስታ)

( ንጉሱ ከደጀኔ እና ከጥቂት አሽከሮቹ በስተቀር ሁሉንም እንዲወጡ ያደርጋል ። ንጉሱ ከንግስቲቷ ጋር በሀይል
እየደነሰ ሳለ በድንገት ራሱን ስቶ ይወድቃል ። አማካሪው እና የንጉሡ የወታደር አለቆች ንጉሡን ለማዳን ሀኪም
እየጠሩ ይረባረባሉ ። በርካታ ሀኪሞች ከወጣት እስከ ሽማግሌ ይመጣሉ ። ግን መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም ። ንጉሡ
ራሡን ይስታል ንግስቲቱ ደርቃ ትቀራለች ራኬብ መጥታ የንግስቲቷን እጅ ይዛ ለማረጋጋት ትሞክራለች ። )

ደጀኔ ፦(በፍጥነት ) ዞር በሉ ዞርበሉ ንጉሰ ሆይ..ንጉስ ሆይ ምን ተገትራችሁ ታያላችሁ ፍጠኑ ሀኪሞችን ጥሯቸው
ፍጠኑ !

ደጀኔ ፦ አየር ስጡት ዞር በሉ...ዞር በሉ

(ሌሎች ሰዎች ንጉሱን አንስተው ወደ ምቹ አልጋው ሊወስዱት ሲሞክሩ ደጀኔ ንጉሱን እግሩ ላይ አስተኝቶት)

ደጀኔ ፦ አትንኩት...አትንኩት ዶክተሮቹ ይምጡ

ንግስቲቷ ፦(ንግስቲቱ ብቻዋን ደርቃ ቆማለች)

ደጀኔ ፦ ንጉስ ሆይ....ንጉስ ሆይ እባክዎን ጠንክር ይበሉ ።

ራኬብ ፦( ንጉስን ስትንከባከብ ትቆይ እና ወደ ንግስቲቱ በመዞር)

ንግስት ሆይ...ንግስት ሆይ...ንግስት ሆይ

ንግስቲቷ ፦ (ንግስቲቷ በሶስተኛው ጥሪ ከገባችበት ሰመመን ትነቃለች )

ራኬብ ፦ ደ...ህ...ህ...ደህና ነሽ

ንግስት ፦ ደህና ነኝ (በእርግታ)

(ሁለት ሀኪሞች በፍጥነት ይመጣሉ ። እጁን ይዘው የንጉሱን የልብ ምት ያዳምጣሉ ንጉሱን ከነበረበት ወደ ምቹ
አልጋው እንዲወሰድ ያደርጋሉ ። ምርመራቸውን ይጀምራሉ )

ራኬብ ፦ አይዞሽ አይዞሽ ንግስት ሆይ...አትጨነቂ አስኪ ውሀ አምጡላት (ንግስቲቷን ታስቀምጣታለች )


አሽከሮቹ ፦ (ውሃ ሊያመጡ ይወጣሉ )

ራኬብ ፦ እመቤቴ አሁን ተረጋጊ ንጉሳችን መዳኑ


አይቀርም

አሽከር ፦ ውሃውን ይዛ ትመጣለች

ደጀኔ ፦ ምንድን ነው ? ንጉሳችን ምንድነው የሆነው

ሀኪም 1፦ እ..እእእእእእእእ (ለመናገር እየፈራ)

ደጀኔ ፦ ምንድን ነው የምትንተባተበው ለምንድን ነው ንጉሳችን ያልነቃው

ሀኪም 1 ፦ ይመስለኛል ጌታዬ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገዋል

ደጀኔ ፦ እና አድርጓ ምንድነው የምትጠብቁት....ንግስት ሆይ አንድ ነገር በያቸው እንጂ

ንግስት ፦ እእ..ምም

ደጀኔ ፦ እናንተ የማትረቡ እንዴት ታላቁ ንጉሳችንን ማዳን ያቅታችኋል ድሮም የኔ ጥፋት ነው እናንተን ሀኪም ብዬ
መጥራቴ

ደጀኔ ፦ አሽከሩን ይጣራል

አሽከር ፦ አቤት

ደጀኔ:- ሀኪሞቹ ምንም ሊያደርጉለት አልቻሉም።


ዶክትር Richard ዛሬ ወደ አሜሪካ ይመለሳል :: ቅድም ድግሡ ላይ ነበር ከሀገር ከመውጣቱ በፊት በቶሎ
ወደዚህ እንዲመጣ አድርግ አሁኑኑ!/

አሽከር ፦ እንደትዕዛዝህ ጌታዬ ::

ሀኪም 2 ፦ (ንጉሱ ጋር የሚያደርጉትን ምርመራ በመጨረስ ) በጣም አዝናለሁ...ንጉሳችን ያለበት ሁኔታ በጣም
ከባድ ነው ሌሎች ምርመራዎችን የግድ ማድረግ አለበት

ደጀኔ ፦ ታዲያ ምን ትጠብቃላችሁ ፍጠኑአ... በፍጥነት አድርጉት

ሀኪም 2፦ እሱን እንኳን ማድረግ አንችልም ይሄ ካቅማችን በላይ ነው....ከፈረንጆች ውጪ እስካሁን ምርመራውንም
ሆነ መድሀኒት ሊሰራ የሚችል የለም ።

ደጀኔ ፦ ቆይ ይሄ ምን አይነት ነገር ነው....


/አሽከሩ በፍጥነት ይወጣል ። ንግስቷና አሽከሮቹ ንጉሡ እንዲነቃ በንጉስ ማራገቢያ ያራግቡለታል ። ብዙም
ሳይቆይ አሜሪካዊው ዶክተር ሪቻርድ የህክምና እቃውን በሳምሶናዊት ይዞ ይመጣል ። ዶክተሩ አማርኛ በከፊል
ይችላል ። /

ራኬብ ፦ ዶክተር ሪቻርድ መጣ (በፍጥነት )

አሽከር ፦ ጌታዬ ይኸው ዶክተር ሪቻርድ መተዋል

ደጀኔ ፦ ኦኦኦ...ተመስገን ዶክተር ሪቻርድ መጣ...ዶክተር ሪቻርድ እንኳን ደህና መጣ እባክህ

ዶክተር ሪቻርድ ፦ /የህክምና እቃውን ከሳምሶናይቱ አውጥቶ/ ወደዚህ እየመጣን ንጉሱ ምን እንደሆነ ጠባቂው
ነግሮኛል ደጀኔ...ከዛ በኋላ ንጉሱ ነቅቷል እንዴ

ደጀኔ ፦ አይ በፍፁም እስካሁን አልነቃም

ዶክተር ሪቻርድ ፦ Bp ውን ለክተኸዋል እንዴ

ሀኪም 1 ፦ አዎ ልክ አይደለም ዶክተር

ዶክተር ሪቻርድ ፦ /ነጭ መመርመሪያ መሰሪያ ይዞ ከንጉሱ ሳምፕል ከወሰደ በኋላ ቆሞ እየመረመረ ሳለ ንግስቷ እና
ደጀኔ ወደ ዶክተሩ ተጠግተው /

ንግስቷ ፦ ምንድን ነው ዶክተር

ዶክተር ሪቻርድ ፦ Wait me Please አንድ አንድ ምርመራዎችን እያደረኩ ነው

(ምርመራውን እያደረገ በመሀል ይደነግጣል ። በድጋሜ ደንግጦ ደጋግሞ ያየዋል )

ደጀኔ ፦ ምንድን ነው ዶክተር...(በድጋሜ ውጤቱን ያየዋል )... ምን ተፈጠረ ዶክተር በል ንገረኝ..ዶክተር !

ንግስቷ ፦ እያስጨነከኝ ነው ዶክተር ምን ተፈጠረ

ዶክተር ሪቻርድ :- please once አ ንድ ጊዜ አንድ ጊዜ .. /ለንጉሡ ምርመራ ያደርግለታል ከመረመረው


በኋላ ንግስቲቷ ፣ ደጀኔ ወደ አንድ ጥግ ወስዶ/ .. ንግስት ሆይ ንጉሡ በጠና ታሟል ይህንን ስል በጣም አዝናለሁ ግን

ንግስቷ ፦ ግን ምን..

ዶክተር ሪቻርድ : - ንጉሡ ከመንጋቱ በፊት ሊሞት ይችላል ።


ደጀኔ ፦ አይ...ሊሆን አይችልም በፍፁም አይሆንም !

ንግስት :-ምን ! ምን እያልክ ነው መድሀኒት የለውሞ .. ትሰማኛለህ ዶክተር የምትችለውን ነገር በሙሉ
አድርግ አሉ የተባሉ አዋቂዎችን በሙሉ ከያሉበት አስጠራ ለንጉሡ መድሀኒት ፈልግ አሁን ንገራቸው ስራህን ጀምር
ፍጠን !

ዶክተር ሪቻርድ :- ትእዛዝሽን እቀበላለሁ ንግስት ሆይ ግን ...

ንግስት :- ምንም ግን የሚባል ነገር መስማት አልፈልግም አድርግ ያልኩህን አሁኑኑ አድርግ !

/ዶክተር ሪቻርድ ፈጥኖ እየሮጠ ይወጣል ። መለከት ይነፋል ንጉሡ በጠና እንደታመመ አዋጅ ይነገራል ።

አዋጅ አዋጅ አዋጅ ንጉሰ ነገስት ዘኢዝቆጵያ በጠና ስለታመሙ መድሀኒቱን ላገኘ እና ለጠቆመ ከንጉሱ ታላቅ
ሽልማትን ይቀበላል ። ንጉሰ ነገስቱ እስኪሻላቸው ድረስ ማንም ሰው በሀዘንም ሆነ በደስታ መሰብሰብ አይችልም
ይህንን ተላልፎ ለተገኘ ግን ያለምን ቅድመ ሁኔታ በአደባባይ በስቅላት ይቀጣል ።
/መብራት ይጠፋል/

ትዕይንት ሁለት

ንጉሱ ፦( ከቆይታ በኋላ ነቅቶ መርዶውን ተረድቷል ። በድንገት ከተቀመጠበት ሊነሳ ሲል ተመልሶ ይቀመጣል )

ደጀኔ :-ንጉስ ሆይ እባክዎ እረፍት ያድርጉ ።

ንጉሡ ፦ዞር በሉልኝ እንዴት ይሄ ሁሉ ጠቢብ ተኮልኩሎ ባለበት እንዴት አንድ እኔን የሚያድን ሰው ይጠፋል
! /በመንቀጥቀጥ በንዴት ውስጥ ሆኖ እየተነሳ/ይህኔ ዶክተር ሪቻርድ ይመጣል ።

ዶክተር ሪቻርድ :- ንጉስ ሆይ እርስዎን ያጠቃዎት በሽታ ምን እንደሆነ ደርሰንበታል ነገር ግን ..

ንጉሡ :- ግን ምን ..?

ዶክተር ሪቻርድ ፦ ግን እስከ ዛሬ ድረስ መዳኒት በፍጹም አልተገኘለትም

ንጉሡ :- ፈልጉአ ሀኪሞች አይደላችሁም እንዴ እ ፈልጉ እናተ ፈረንጆች ማድረግ የማትችሉት ነገር የለም ። በሉ
ፈልጉ እና አድኑኝ

ዶክተር ሪቻርድ ፦ ንጉስ ሆይ...

ንጉሱ፦ይሄ እኮ ለናንተ ቀላል ነው ።በሉ የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ እሰጣችኋለሁ ወርቆች ዳይመንዶች ምንድን ነው
የምትፈልጉት ? .. . ደጀኔ በል ፍጠን የሚፈልጉትን በሙሉ ስጣቸው

ዶክተር ሪቻርድ ፦ ንጉስ ሆይ አንዴ ተረጋግተው ያድምጡኝ ይሄ በሽታ (...ስሙ ይነገራል) እንደሚያስቡት ቀላል
አይደለም በዚህ በሽታ ተይዞ በህይወት የተረፈ የለም .. .ይህንን ስል በጣም አዝናለሁ ህመሞ ጊዜ አይሰጥም
ምናልባትም በሂወት ለመቆየት ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው የቀሮት ::

ንጉሱ፦አፍህን ዝጋ ! በቃህ! ከዚህ በኋላ አትድንም ትሞታለህ የሚል ቃል ከአፋችሁ እንዳይወጣ ትሰማኛለህ ዶክተር
/ሀኪሙን አንቆት / እኔ መሞት አልፈልግም እየሰማኝ ነው ! መሞት አልፈልግም !

ዶክተር ሪቻርድ :- ንጉስ ሆይ ንጉስ ሆይ እባክዎን ይረጋጉ ባይሆን አንድ መፍትሄ አለኝ አንድ ጀርመናዊ " ጆርጆስ
አግሪኮላ " የተባለ እውቅ ሀኪም አለ

ንጉሱ :- እና ..?

ዶክተር ሪቻርድ ፦ እሱ አለ የተባለ ሀኪም ነው እንዲያውም ለምርምር ወደ ኬንያ መጥቷል እሱን ማስጠራት እንችል
ነበር ..ርርር..?

ንጉሡ :-እና ለቀብሬ ነው የሚመጣው...ከፊቴ ጥፉ ! እነዚህን የማይረቡ ደደብ ጠቢባን ወደ እስር ቤት


አስገቧቸው ። ጠባቦች!!

/ሴት የንጉሱ ጠባቂዎች ጠቢባን የተባሉትን በሙሉ ወደ እስር ቤት ፈጥነው ያስገባሉ ። ንጉሡ ህመሙ
እየጠናበት እየደከመ ይመጣል ። ሌሎች በርካታ ሀኪሞች ከያሉበት እየተፈለጉ ወደ ንጉሡ ይመጣሉ ግን መፍትሄ
የለም ። ንጉሱ ጠቢቦችን ካባረረ በኋላ አዙሮት ይወድቃል ሴት ጠባቂዎች ቀደም ሲል የነበሩትን ጠቢባን ወደ እስር
ቤት ይወስዷቸዋል ኮረስ ዶክተሮች ንጉሱን ለማዳን ይረባረባሉ ግን መፍትሄ የለም ። /
(የሴት ጠባቂዎች አለቃ ወደ ቀሩት ዶክተሮች እየተመለከተች )

ሴት የጠባቂዎች አለቃ ፦ እስር ቤት አስገባቸው !

ንጉሡ ፦ አይ እነሱ መድሃኒቱን ይፈልጉ እና በቅርብ ተከታተሏቸው::

የሴት ጠባቂዎች አለቃ :-እንደትእዛዝዎ ንጉስ ሆይ ..

ንጉስ ፦ በሉ ቀጥሉ

ደጀኔ :-ንጉስ ሆይ
ንጉስ ፦ምንድነው ? በዚህ ሰዓት ስለገንዘብ ምንም ነገር ማየትም ሆነ መስማት አልፈልግም እኔ መዳን ብቻ ነው
የምፈልገው !

ደጀኔ ፦ግን ንጉስ ሆይ ..

ንጉስ :- ግን ምን ?

ደጀኔ :- (ወደ ንጉሱ ጆሮ ተጠግቶ ሹክ ይለዋል) ::

ንጉስ :- (ንጉሱ በንዴት ይመለከተዋል )

ደጀኔ፦ንጉስ ሆይ አሁን ጊዜው እንዳልሆነ አውቃለሁ ግን ሰውየው እንደእብድ እየጮሀ ለንጉሱ መፍትሄ አለኝ እያለ
ነው ።

ንጉሱ ፦ አስገባው

ደጀኔ ፦እንደ ትዛዝዎ ንጉስ ሆይ... አስገቡት / ያለቅጥ በግድ ግብር የሚያስከፍሉት ምስኪን ሠው በሁለት ሴት
ጠባቂዎች ታጅቦ እየተጎተተ ይገባል / ::

ሰውየው ፦ፈጣሪ ጨርሶ ይማሮ ጌታዬ

ንጉስ ፦ /እያመመው እያጣጣረ/ አንት ጥጋበኛ ገንዘቤን በልተህ የምታመልጥ መስሎህ ነበር አይደል ?! አሁን ምን
ልትነግረኝ ነው በል ተናገር

ሠው ፦ ንጉስ ሆይ ይቅርታ ያድርጉልኝ እና በየጊዜው ከእርሶ የተበደርኩትን ገንዘብ በሙሉ እየከፈልኩ እኮ ነው ግን


ወለዱ ከተበደርኩት ገንዘብ ሶስት እጥፍ ነው ይሄን ሁሉ ገንዘብ ከየት ብዬ አመጣዋለሁ ንጉስ ሆይ ?

ንጉስ፦እሱን ገንዘቡን ከመውሰድ በፊት ነበር ማሰብ የነበረብህ ማስጠንቀቂያዬን ችላ ብለህ ተደብቀህ ነበር ግን ማንም
ሰው ከኔ እጅ ማምለጥ አይችልም በሉ ንብረቱን በሙሉ ወርሳችሁ .. ውሰዱና አሁኑኑ ወደ ሲኦል ላኩት ። / ገዘፍ ያሉ
እና ለየት ያለ ልብስ የለበሱ ሴት

የንጉሡ ጠባቂዎች ሰውዬውን ይይዙታል / ::

ሠው ፦ንጉስ ሆይ እባክዎን ጊዜ ይስጡኝና እከፍላለሁ ::

ሴት ጠባቂ 1፦ ቀጥል ተራመድ ... !

ሠው :-ንጉስ ሆይ እባክዎ አይግደሉኝ ... እባክዎ አንድ ጊዜ አዳምጡኝ

ንጉስ :- ውሰዱት እና ስጋው ለአሞራዎቼ ስጡት!

ሠው ፦ /እየወሠዱት በጩኸት / ንጉስ ሆይ .. ንጉስ ሆይ ለአንድ ደቂቃ ካዳመጡኝ የህመምዎን መድሃኒት


እሰጦታለሁ !

ንጉስ :- ቆይ! /ሴት ጥበቃዎቹ ይዘውት ይቆማሉ / ንጉሱ አሽከሮቹን ተደግፎ ሰይፍ በመምዘዝ ሰውየው አንገት
ላይ ይደቅናል |የታል ታዲያ መድሃኒቱ ለህመሜ መድሃኒቱን ካገኘህልኝ እዳህን በሙሉ እሰርዝልሃለሁ በህይወትም
እንድትቆይ እፈቅድልሃለሁ በል ንገረኝ ::

ሠው :-ንጉስ ሆይ መድሀኒቱ እንኳን... እኔ ጋር የለም

ንጉስ :- ስለዚህ እኔን እያሞኝህ ነው ፡፡ / ንጉሱ ሊሰይፈው ሲል|

ሠው ፦ እንደሱ አይደለም ንጉስ ሆይ አንድ ጊዜ እባክዎ ያዳምጡኝ ንጉስ ሆይ ::

ንጉሱ ፦ አንተ ጭራሽ በኔ ህመም ለመሳለቅ ትሞክራለህ ?

ሠው :- አረ በፍጹም ነገሩ ወዲህ ነው ንጉስ ሆይ እኔ ስለ ህክምና ምንም የማውቀው ነገር የለም ..ግን
ህይወትዎን የሚያድን ከበሽታው የሚፈውስ ነገር ነው አሁን የምነግሮት ::

ንጉስ :-ልቀቁት ና ወደዚ ምንድንነው?

ሠው :- አንድ ታላቅ ጠቢብ አለ እርሱ የማይፈውሰው አንድም በሽታ የለም

ንጉስ ፦ አይ እሱን እንኳ ተወዉ

ሠው ፦ ግድ የሎትም ንጉስ ሆይ ይህ ሠው ከሁሉ ይለያል ::

ንጉስ :- አንተ ጊዜዪን እየገደልክ ነው !

ሠው ፦ አይደለም ንጉስ ሆይ ግድየሎትም ይህ ሰው ከህመምዎ ያድኖታል እርሱ ጋር ሄዶ ከበሽታው ሳይድን የተመለሰ


የለም ።

ንጉስ ፦ ማን ...ማነው ይህሰው የት ነው ያለዉ አሁን?

ሠው ፦ እዚሁ ጌታዬ

ንጉስ :- እዚህ የት?

ሠው ፦እስር ቤት ከምርኮኞችህ ውስጥ አንዱ ነው።

ንጉስ ፦ ከአሜሪካ እስከ ጀርመን ታላላቅ ጠቢባን የሚባሉትን በሙሉ አስመጣሁ ግን ማንም ሊፈውሰኝ አልቻለም እና
አንድ ተራ ምርኮኛ ከህመም ይፈውሰሃል እያልከኝ ነው?

ሠው ፦ አዎ ልጄ ታማብኝ ብዙ ጠቢባን ጋር ተንከራተቼ መፍትሄ ላጡለት ህመም እርሱ ጋር ወስጃት በደቂቃዎች


ውስጥ ነው የፈወሳት ! እርሱ ጋር ጎባጣው ይቀናል ፣ ድውይ ይፈወሳል ይህን ሁሉ ተአምር በአይኔ በብረቱ ነው ቆሜ
የተመለከትኩት እመኑኝ ብቸኛ የመዳን ተስፋዎ እሱ ነው ክቡርነቶ
(ንጉሱ ነገሩን በጥልቀት ካጤነው በኋላ)

ንጉስ ፦ ይህ ሰው የሚለው እውነት ከሆነ ወደ እስረኞች ወስዳችሁት የሚለውን ሰው ከታሣሪዎች መሀል ፊልጋችሁ
በፍጥነት ይዛችሁልኝ ኑ ፍጠኑ!

/ ጓጕሡ ይበልጥ እየደከመ ነው ። አራት ሴት ቆነጃጅት ጥበቃዎች አጅበውት ሰውየውን ይዘውት ይሄዳሉ ።
ይሄኔ ራኬብ ንግስቷን ደግፋ እያረጋጋች ይዛት ወደመድረኩ ትገባለች ጊዜያዊው የንጉሱ ተንከባካቢ ንጉሡን
ይንከባከበዋል/

ንጉሱ ፦ዞርበሉልኝ ንግስቴ የታለች እሷን ብቻ ነው የምፈልገው .. . የኔ ውብ ንግስት የታለች !


ራኬብ ፦ (ፋታ) ይቅርታ ያድርጉልኝ እና ጌታዬ ንግስታችን በተፈጠረው ነገር በጣም ተደናግጣለች
ለዛም ነው አጠገቦ መሆን ያልቻለችው ::

ንጉስ ፦ የኔ ውድ አስጨነኩሽ አይደል ::

ንግስቷ ፦ እባክህ ራስህን አታድክም ጠንከር በል

ንጉሱ ፦ (በደከመ ድምፅ) አፈቅርሻለሁ

/ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጠባቂዎች እና ሰውየው ሶስት ምርኮኛ ሰዎችን ወደ ንጉሱ ያቀርባሉ :: በምርኮ የተያዙት
ሰዎች ተመሳሳይ አቋም እና መልክ ያላች ናቸው /::

ሴት ጠባቂ :-ንግስት ሆይ ንጉሱን ያድናሉ የተባሉት ሰዎች መተዋል ፈቃድሽ የሚሆን ከሆነ ...

ንጉሱ ፦ ሰዎች ( እያቃሰተ)

ንግስት :- /እንዲያስገቧቸው በእጇ ምልክት ትሰጣለች ጠባቂዎቹ በምርኮ የተያዙ ሰዎችን ያስገቧቸዋል
...ጠባቂዋ ለራኬብ በጆሮዋ ትነግራታለች ። ራኬብ ደግሞ ከጠባቂዋ የሰማችውን ለንግስቲቱ ሄዳ በጆሮዋ
ትነግራታለች ) እዚህ ምን እየሆነ ነው ...

ንጉሱ ፦ደጀኔ ለምንድን ነው እነዚህን ፊቴ አምጥታችሁ የምትገትሩብኝ !

ደጀኔ ፦ጌታዬ በርግጥ ልክ ኖት ሰውየው...

ንጉሱ ፦ አፍህን ዝጋ !ምንድን ነው እያደረክ ያለኸው ሰውየው የታለ (በጩኸት)

እየቀለድክብን ነው አንተ ሽማግሌ ?

የንጉሱ ጠባቂዎች ፦( ወደ ሽማግሌው ሲጠጉ ሽማግሌው በፍርሃት) እንደሱ አይደለም ጌታዬ ጉዳዩ ከተፈጠረ
አመታት ተቆጥረዋል

ንጉሱ ፦ እና
ሰውየው ፦ እና... የጠቢቡ መልክ አምታቶኛል ጌታዬ

ንጉሱ ፦ አንተ ሽማግሌ ይሄ ሁላ ዘመን ኖረህ ከማን ጋር መቀለድ እንዳለብህ አታውቅም ግን አታስብ ዳግመኛ
ወደማትመለስበት እልክሀለው ።

(ንጉሱ ሽማግሌው እንዲገደል በእጁ ምልክት ትዕዛዝ ሰጥቶ ሽማግሌው ሊገደል ሲል ንግስቲቱ ታስቆመዋለች)

ንግስት ፦ ቆይ ! (በፍጥነት እየጮኸች )

ንጉሱ፦( ንጉሱ በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት ዞሮ ያያታል )

ንግስቷ ፦ ( ንግስቲቷ በአንገቷ ለንጉሱ ምልክት በመስጠት እንዲረጋጋ ታደርጋለች ። ወደ

ምርኮኞች በመሄድ )

ንግስት ፦ ንጉሴን ከዚህ በላይ አታናዱት...አሁን አንድ የመጨረሻ እድል ብቻ እሰጥሀለሁ የምትለው ጠቢብ የትኛው
ነው ?

ሰውየው ፦ እእ..

ንግስት ፦ ሽሽ...ምንም እድል የለህም ትፋሽህን አታባክን የማትፀፀትበትን ነገር በደንብ አስብና ተናገር ...አስብ
ጠቢቡን የምታስታውስበት ትንሽዬ ፍንጭ እንኳን ፈልግ ....ነገሩን ቀለል እናድረገው መቼም ይህ ሰው እየተናገረ
ያላው ከናንተ ውስጥ ስለአንዳችሁ ነው ። ከናንተ ውስጥ ታላቅ ጠቢብ እንዳለ ይህ ሰው ተናግሯል አሁን ብዙ ጊዜ
የለንም ንጉሴን አድኑት እና በምትኩ ከናንተ ውስጥ አንድ ሰው ከዚህ የምርኮ ህይወት ነፃ ይወጣል :: ቤተሰቡም
እንዲሁ ገንዘብ ፣ ወርቆች ፣ ውድ ጌጣጌጦች የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል ታዲያ እውነተኛው ጠቢብ ማነው ?

3 ኛው ምርኮኛ ፦እኔ ነኝ

ንጉሱ፦ ጎበዝ !አንተ እውነት ጠቢብ ከሆንክ የምትፈልገውን ነገር አደርግልሀለሁ ገንዘብ ፣ ወርቅ ፣ መሬት
የመረጥከውን እሰጥሀለው አሁን በል መድሀኒቱን መቀመም ጀምር ይሄ የምን መድሀኒት ነበር ::

3 ኛው ምርኮኛ ፦ እእ...እሷ የብርድ ናት

ንጉሱ ፦ ( ምርኮኛው እያጭበረበረ መሆኑን ሲያውቅ አሽከሮቹን በእጁ ምልክት ትዕዛዝ በመስጠት እንዲገደል
ያደርጋል )

ንጉሱ ፦ የምቀልድበት ጊዜ እንደሌለኝ አይታችኋል ያ የተረገመ ጠቢብ ተብዬ ማነው...(ወደ ምርኮኞቹ እየጠቆመ)
አንተ ወይስ አንተ (በማለት ይጠይቃል) ....አንተ በጣም ብልህ ሰው ትመስላለህ በል ንጉስህን አድነው እና ሽልማትህን
ውሰድ...የምለውን አልሰማህኝም...ነው ወይስ ቆጥረህ የማትጨርሰውን ገንዘብ ካሁኑ መቁጠር ጀምረህ ነው በል
አሁን ሂድና መድሀኒቱን አዘጋጅተህ ስጠኝ (ንጉሱ ወደ ሁለተኛው ሰው ይመጣል)

ምርኮኛ 2 ፦(ትንሽ ከተራመደ በኋላ አንገቱን አቀርቅሮ ይቆማል )


ንጉሱ ፦ሰውዬ መድሀኒቱን አዘጋጅ እያልኩህ እኮ ነው የምናገረው አይሰማህም እንዴ ?

የሴት ጠባቂ አለቃ ፦ ንጉስ ሆይ...

ንጉስ፦ ዝምበይ (በፍጥነት) አትሰማም ደንቆሮ ነህ

ጠባቂዋ ፦ ንጉስ ሆይ ሰውየው ...

ንጉስ፦ ዝምበይ ! አፍሽን ዝጊ አልኩ እኮ ከመጣ ጀምሮ አንዲት ቃል እንኳን አልተነፈሰም !

ደጀኔ ፦ ጌታዬ ሰውየው ሊሰማዎት አይችልም

ንጉሱ ፦ ለምን (በትዕቢት)

ደጀኔ ፦ምክኒያቱም ማረሚያ ቤት ውስጥ በእርምት ሰዓት አደጋ ደርሶባቸው ከተመዘገቡ ታራሚ ሰዎች መካከል አንዱ
ነው ::

ንጉሱ ፦እና

የጠባቂዎች አለቃ ፦ ይቅርታ ጌታዬ ይህንን ቀድሜ ስላንነገርዎት...ግን ሰውየው መናገርም ሆነ መስማት አይችልም ።

ንጉሱ ፦ ወደዛ ውሰዱልኝ ይሄን ደንቆሮ!(በጩኸት እያለው ሳለ ትንፋሽ ያጥረዋል ሁሉም ይረባረባሉ) ::

(መስማት የተሳነውን ሰው ጠባቂዎች ይወሰዱታል )

ንጉሱ ፦ (ወደ ገዘሙ እየተመለከተ) ስለዚህ እውነተኛው ጠቢብ አንተነህ ማለት ነው :: ግን እውነተኛው ጠቢብ
አንተ መሆንህን ምን ማረጋገጫ አለኝ ?

ተበዳሪው ሰውየው ፦ አስታወስኩ... አስታወስኩ ጌታዬ (በደስታ እና በጩኸት)

ንጉሱ ፦ ለምንድን ነው የምትጮህብኝ ምንድን ነው ያስታወስከው

ሰውየው፦እውነተኛው ጠቢብ ቀኝ እጁ ላይ ትንሽዬ ጠባሳ አለ እንደውም ልጄ አይታው ምንሆነ ነው እያለች


ጠይቃው ነበር እርሱም መድሀኒት ሲቀምም አደጋ እንደረሰበት እእ...

ንጉሱ ፦ (ያስቆመዋል )በቃ አሁን ከጠቢቡ ውጩ ማንንም ማየት አልፈልግም ....ውሰዱት ይሄንን ደንቆሮ (ንጉሱ
የህመም ስሜት ይሰማው እና መተንፈስ ይሳነዋል ማጣጣር ይጀምራል ። )

/ ተበዳሪው ሰው ራሡን በመነቅነቅ አዎ ይላል /


ንግስት ፦ እውነት እንደተባልከው ሀኪም ከሆንክ እባክህ ንጉሴን
አድነው.... ስምህ ማን ይባላል ። /
ገዝሙ ፦ / ዝም/

ንግስት :- እውነት እንደሚባለው ሀኪም ነህ ?.. እያናገርኩህ እኮ ነው ? /ብላ ንግስቲቷ ወደ ገዝሙ ስትጠጋ
በድንገት ቀሚስዋ ጠልፋት ከደረጃው ላይ ልትወድቅ ስትል ገዝሙ ፈጥኖ ይዞ ያተርፋታል። ገዝሙ ህይወቷን
ያድንላታል።ንግስቷ በጣም ትገረማለች የሁሉም ሰው ዓይን እነሱ ላይ ያርፋል ቤተ መንግስቱ ፀጥ ረጭ ይላል

ንግስቲቷ በልዩ አስተያየት ትመለከተዋለች ። /

ንግስት :- አመሰግናለሁ ! እባክህ ንጉሱን ልታየው


ትችላለህ የፈለከውን ያክል ገንዘብና የምትፈልገውን ነገር በሙሉ እናድርግልሃለን ንጉሱን ብቻ አድነው ።

ገዝሙ :- አልችልም !

ንግስቷ:- ከዚህ በኋላ በምርኮም አትኖርም ነፃ ትወጣለህ እባክህ እየለመንኩህ ነው እንዳልኩህ የምትፈልገውን ነገር
በሙሉ እንሰጣለን ምንድነው የምትፈልገው ?

ንጉሱ ፦ /አያጣጣረ ያያል /

ገዝሙ :-ምንም አልፈልግም

የጥበቃዎች አለቃ ፦ /ወደ ገዝሙ መጥቶ / ንጉሳችንን ብታክመው እና እድልህን ብትጠቀም ጥሩ ነበር ግን ከዚ ሠዓት
ጀምሮ በህይወት እንድትኖር አልፈቅድለህም ..ተንበርከክ !
/ገዝሙ በቀላሉ ፈርቶ የሚምበረከክ ሠው አልሆነም የጥበቆች አለቃ በጦር ደረቱን ሊወጋው ሲሰነዝር ንግስቷ
ታስቆሟለች /

ንጉስ :- / በሀይል ያቃስታል አይኑ ተገለባብጦ ንጉሡ ሊሞት ማጣጣር ይጀምራል/

ንግስቷ :- ቆይ .. አቁም እባክህ እባክህ አንድ ነገር አድርግ ? እባክህ /የንጉሡ ተንከባካቢዎች ይረባረባሉ ። /
ገዝሙ ወደ ንጉሡ ሄዶ አንድ ነገር አውጥቶ ለንጉሡ ያጠጣዋል ንጉሡም በቅፅበት ማቃሠቱን አቁሞ ሀይል
እና ብርታት ያገኛል ንጉሡ ራሱን እያወቀ ሲመጣ ከስቃዩ እንዲታገስ ያደረገው ቡትቶ የለበሰው ሰው በመሆኑ
ተገርሟ ል :: /
አንጓ ሰባት
ንጉሡ ፦ አንተ ማነህ ...ማነህ አንተ ..

ጠባቂው ፦ ከምርኮኞች ውስጥ አንዱ ነው ንጉስ ሆይ

ንጉሡ ፦ እንደተባለውም አንተ ጠቢብ ነህና ጨርሰህ አድነኝ በምትኩ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ገንዘብ ፣ ወርቅ፣
መሬት ... ?

ገዝሙ ፦ ምንም !

ንጉሡ ፦ በል አትፍራ ንገረኝ በሉ የሚሞቅ ልብስ አምጡለት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ አድርጉለት ! በል ንገረኝ ቀኝ
እጄ አደርግሀለሁ ስልጣንም እሠጥሀለሁ እሾምሀለሁ !
ገዝሙ :- አይ ያንተን ሹመት አልፈልግም ግን ካንተ አንድ ነገር እፈልጋለሁ ::

ንጉስ :- አንተ አድነኝ እንጂ የምትፈልገውን ነገር በሙሉ እሰጣለሁ ምንድን ነው ?

ገዝሙ :- ድርድር !! ..ካንተ ጋር መደራደር እፈልጋለሁ

ንግስት ፦ ይቅርታ ይደረግልኝ ንጉስ ሆይ .. /ገዝሙን/ ግን አንተ ማን ስለሆንክ ነው ከንጉሴ ጋር ለድርድር


የምትቀርበው ?

ንጉስ ፦ የኔ ንግስት አንቺ ወደ ክፍልሽ ግቢ .. የምን መደራደሪያ ነው ..በምን ጉዳይ ..?

ገዝሙ :- በቅድሚያ ከመደራደራችን በፊት እንደኔ በግፍ እየተደበደቡ በምርኮ ሆነው እየታረዙ ያሉ ንፁሀን ደህ
ወገኖችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ልቀቅ ካሣም ይከፈላቸው !

ንጉሡ :- ምን እያልክ ነው እነሱ ወንጀለኞች ናቸው

ገዝሙ ፦ ንፁሃን ናቸው!

ንጉሡ :- እነሡን እርሳቸው ..ላንተ ግን የምትፈልገውን ነገር በሙሉ አደርግልሃለሁ በል መድሀኒቱን ስጠኝ
የምትፈልገውንም ጠይቀኝ ?

ገዝሙ :- በምርኮ የያዝካቸውን ሰዎች በሙሉ ከህፃን እስከ አዋቂ በሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ያጎርካቸውን አሁኑኑ
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ልቀቃቸው ያለበለዚያ በፍጹም መድሀኒት የሚባል ነገር ከኔ አትጠብቅ።

ንጉሡ፦ ምን እያልክ ነው?

ደጀኔ :-እንዴት እንዴት ነው ንጉሱን የምትናገረው አንተ የማትረባ !

ንጉሡ ፦ ሽሽሽሽሽ ... አንተ ብቻ መድሃኒቱን በቶሎ አዘጋጅ አሁኑኑ እዚ ቤተመንግስት ውስጥ ያሉ ምርኮኞችን
ልቀቋዋቸው ።

/ ሁለት ወታደሮች ወታደራዊ ሠላምታ ሠተው ወደ መድረኩ ጀርባ ይሄዳሉ /

ንጉሡ ፦ ይኸው የምትፈልገውን ሁሉ እያደረኩል ነው ከመንጋቱ በፊት መድሃኒቱን ስጠኝ የምትፈልገውን እቃ በሙሉ
አሁን ያመጡልሃል ደጀኔ /መጣራት /?

ደጀኔ ፦ አቤት ንጉስ ሆይ

ንጉስ ፦ የሚፈልገው ነገር በሙሉ አቅርቡለት ፍጠኑ !

/በዚህ ሰዓት ከጀርባ በርካታ ምርኮኞች ከእስር ተፈተው ሲወጡ ድምፃቸው ይሰማል / ።
ንጉስ :-በል ጀምር በህይወት ለመቆየት ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው የቀረኝ በል ተስፋ ሰጥተህኛል ይኸው የምትፈልገውን
ነገር በሙሉ እያደረኩል ነው ምንድነው የምትጠብቀው ?

ገዝሙ :- 2 ቅድመ ሁኔታዎች ይቀሩኛል ::

ንጉሡ ፦ እኔ ላለመሞ እዚ እየታገልኩ አንተ በህመሜ ትመፃደቃለህ ?!.. በፍጹም በነፃ ልለቃቸው ቀርቶ ልገላቸው
የምፈልጋቸውን እነዛን የተረገሙ ወንጀለኞች ላንተ ስል ለቅቄያለሁ ቆይ እኔን ሳታድን ከዚህ በህይወት መውጣት
የምትችል ይመስልሀል ?

/በዚህ ሰዓት የንጉሡ ሁሉም ጠባቂዎች ወደ ገዝሙ ጦራቸውን ሰብቀው ይጠጋሉ አንደኛው ጠባቂ የገዝሙ ደረት ላይ
ጦሩን ያስደግፋል/

ገዝሙ ፦እኔን በፍጹም መንካት አትችልም ምክንያቱም ብቸኛ የመዳን ተስፋህ ነኝ /በመረጋጋት ንጉሡ ወደ
ገዝሙ ተጠግቶ አንገቱን ያንቀዋል/

ንጉሡ :- ምንድነው የምትፈልገው ?!!

ገዝሙ ፦ መጀመሪያ ንግስቲቷ ወደዚ ትምጣ ከዛም የምፈልገውን እናገራለሁ !

ንጉሡ ፦ /ጥቂት ከተመለከተው በኋላ ንግስቷን ያስጠራታል ። ንግስቷ ከአጃቢዋ ጋር ትገባለች ንጉሱ በክብር
ይቀበላታል ። / ይኸው መታለች በል አሁን ቀጥል ምንድነው የምትፈልገው ::

ገዝሙ ፦ ሚስትህን ላገባት እፈልጋለሁ ።


/ ንግስቷም፣ንጉሡም ፣አሽከሮቹ ፣አማካሪዎቹም ሁሉም ይደነግጣሉ። ጸጥታ መድረኩ ላይ ይሰፍናል። ንጉሡ እግሩ
ይክደዋል አገልጋዮቹ ይደግፉታል ። /

ንጉሡ ፦ ምን ..ምን እያልክ ነው ሀይሌን ፣ክብሬን፣ ሞገሴን ውቧን ንግስት ፣ሚስቴን እኮ ለእንዳንተ አይነቱ
አሳልፌ ልሰጥ? ይህን ሰው ከፊቴ ዞር አርጉት ውሰዱትና መድኃኒቱን ሰርቶ እስኪያመጣው ድረስ እስኪበቃው
አሰቃዩት ! / አሽከሮቹ ገዝሙን እያዳፋት ይዘውት ይሄዳሉ /

ንጉስ ፦ ደጀኔ በፍጥነት ጠቢባኑን በሙሉ ሰብስብ ይህ ሰው የሚያቀውን የህክምና ጥበብ ተረድተው መድሀኒቱን
ይፈልጉ!

ደጀኔ ፦ እንደትእዛዝዎ ንጉስ ሆይ !


/ መብራት ይጠፋል /
(ገዝሙ እና ንግስቷ በሻዶ እየታዩ )
ንግስት ፦ የኔ ፍቅር ለምን ይህንን አደረክ...ራስህን አደጋ ላይ መጣል የለብህም !
ገዝሙ ፦ ከዚህ በላይ ተሸሽገን መኖር የለብንም ነፃነታችንን ማወጅ አለብን
ትዕይንት ሶስት

እዛው ምሽት ላይ ንጉሱ በጣም ታሟል ሊሞት እጅግ በጣም ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርቶታል። ንግስቷ የተጨነቀች
እያስመሠለች ሁሉም ተጨንቀው ቆመዋል።

ንጉሡ፦ እነዚህን ደደብ ጠቢባኖች ሁሉንም ወስዳችሁ ወደዛ እስር ቤት አጉሯቸው ጭራሽ ሌላ በሽታ ጨመሩብኝ
...በቶሎ ገዝሙን ይዛችሁት ኑ ፍጠኑ!! / እያቃሰተ አሽከሮቹ ገዝሙን ደም በደም ሆኖ ይዘውት ይመጣሉ ።
/ .... ... የምትፈልገውን ነገር በሙሉ እሰጥሀለሁ ሚስቴም .. (እጇን ይዞ ). ሚስቴም ከአሁን በኋላ ያንተ ነች
እባክህ አጥፍቼ ሊሆን ይችላል ... ይቅር በለኝ ሞቴ ተቃርቧል ጀንበር ልትወጣ ነው በጣት የሚቆጠሩ ደቂቃዎች ብቻ
ነው የቀሩኝ እኔ መሞት አልፈልግም ከዚህ በላይ በቃህ በል አሁን መድሃኒቱን ስጠኝ ።
(ገዝሙ ወደ ንጉሡ ተጠግቶበት በትንሽ ብልቃጥ መድሃኒት አውጥቶ ያጠጣዋል :: ብዙም ሳይቆይ ንጉሡ ከህመሙ
መለስ ይላል ። አሁን ንጉሱ ያምነዋል ።

ገዝሙ ፦ይኸው እኔ ማድረግ የምችለው ይህን ያህል ብቻ ነው ፡፡ አሁን ንግስትህን ወደ ቤቴ ይዣት መሄድ እፈልጋለሁ )

ንጉሡ ፦ (በእጅ ምልክት) ትችላለህ :: /በቆሪጥ እያየው ገዝሙ ወደ ንጉሡ ሚስት ሄዶ እጇን ይዞ ሊሄድ ሲል
ንጉሡ ሙሉ በሙሉ የዳነ መስሎት ንጉሡ ፊቱን አዙሮ ገዝሙ ላይ ጦር ያስመዝ ዝበታል /

ንጉሡ :- ስታስበው ከዳንኩኝ በኋላ የማፈቅራት ሚስቴን ለእንዳንት አይነቱ አሳልፌ የምሰጥ ይመስልሃል ? ሞኝ !
ንግስቱን ከገዝሙ ይወስድበታል ::
/ደጀኔ የተለየ አሳሳቅ ይስቃል የንጉሱ ጠባቂዎች የገዝሙን እጆች ከንግስቷ ለይተው እያዳፉ አንበርክከው በዕቃ
በተደረገ ውሃ ውስጥ እየነከሩ ትንፋሽ እያሳጠሩት ያሰቃዩታል /

ገዝሙ ፦ (ትንፋሽ እያጠረው ) ቆይ ! ከሰከንዶች በኋላ እግርህ ይክድሀል ከደቂቃ በኋላ ፈጽሞ መቆም አትችልም
የሰጠሁህ መዳኒት ማስታገሻ እንጂ እውነተኛውን መድሃኒት አይደለም ይሄን እንደምታደርግ እርግጠኛ ነበርኩ ። ለዛ
ነው የመጨረሻውን መደራደሪያ አሁን የማቀርብልህ ።

/ውሃ ውስጥ እየነከሩ ትንፋሽ እያሳጠሩት ያሰቃዩታል በመጨረሻም በሀይል ይደፍቁታል ። ንጉሡ እግሩ ሲክደው
ይደነግጣል ጠባቂዎቹ ይደግፉታል አሽከሮቹ ገዝሙን ደንግጠው ይለቁታል /

ንጉሡ :- ምን ...ምንድነው የምትፈልገው

ገዝሙ ፦ /እያለከለከ / በቅድሚያ በመላው ሀገሪቱ በማጎሪያዎችህ ውስጥ አጉረህ ያሉትን ድሃ ምስኪን ህዝቦች ልቀቅ
!

ንጉሡ ፦ ይህ ነው የመጨረሻው መደራደሪያህ ?

ገዝሙ ፦ አይ የመጨረሻው መደራደሪያዬ ወንበርህ ነው !


ንጉሡ :- ምን !

ገዝሙ ፦ ስልጣንህን ልቀቅ !!! እስከ ዛሬ እየበደልክ በአምባገነንነት ደሀውን ስትጨቁን ፍርድ ስታጓድል ኖረሃል ከዚህ
በላይ ግን ይበቃሃል አዋጅ አስነግር ስልጣንህን ልቀቅ ፊርማህንም ፈርም ሰነዱን በእጄ ስጠኝ ያኔ እውነተኛውን
መድሃኒት እሰጥሀለሁ ::

ንጉሡ ፦ ምናባህ ነው ያልከው አንተ ደደብ ../ በንዴት እየጮህ እየተንደፋደፈ ወደ ገዝሙ ሄዶ ያንቀዋል / ይሄኔ
የንጉሡ አማካሪ ይመጣል ። /

ልዩ አማካሪ :- ንጉስ ሆይ .. ንጉስ ሆይ እባክዎ ይረጋጉ ችግሩን ፈተነዋል .. አምጧቸው /አሽከሮቹ የገዝሙን እናት
እና የ 16 ዓመት እህት ከሽማግሌ ወንድ አያታቸው ጋር እያዳፉ ይዘዋቸው ይገባሉ ..አማካሪው ለንጉሡ
በጆሮው ሹክ ብሎ ይነግረዋል/

ገዝሙ ፦ እማዬ ?...እህቴ

/ንጉሱ ፊቱ በደስታ ያበራል :: ንጉሡ ተደግፎ ወደ ገዝሙ እናት እና እህቱ ሄዶ እናቱን በጥፊ ይመታታል ። እህቱን
ከእናቷ እና ከአያቷ ይነጥላታል ። /

ገዝሙ ፦ ልቀቃቸው ልቀቃቸው አንተ የተረገምክ (ገዝሙ ይመታል ) እነሡ ምንም አያቁም ተዉ ከፈልክ እኔን
ግደለኝ !

ንጉሡ ፦ አሁን መድሃኒቱን የማታመጣ ከሆነ ይሄ ሊሞት አንድ ሀሙስ የቀረው ሀያትህን ጥቂት ገፋ አድርጌ
እገላግልልሀለሁ ፣ እናትህን እዚሁ ዓይንህ እያየ ወደ ሲኦል እልካታለሁ ። እህትህን ደግሞ መላው አሽከሮቼ
ሲጫወቱባት ያድራሉ እየተፈራረቁ ሁሉም አንድ በአንድ አይንህ እያየ እዚሁ ይደፍሯታል ። 10 ደቂቃ ብቻ ነው
የምሠጥህ ::

/አራት ወንድ አሽከሮች እህቱን አንበርክከው ይይዟታል እናቱን ሆዷን ይረግጧታል ሽማግሌ ሀያቱን በጥፊ መተውት
በእንብርክክ ያስኬዱታል ገዝሙ እንደ እብድ ይሆናል ንጉሱ በስቃያቸው ይደሰታል ገዝሙ በሀሳቡ ሲጸና ንጉሱ በእጅ
ምልክት እጁን ጥቂት ከፍ አድርጎ ወደታች ሲያደርግ (ይሄ ትዕዛዝ መስጫው ነው) ሀያቱን በጨርቅ ውስጥ አፍነው
ይገሉበታል / (በሰው ስቃይ የሚደሰት ወታደር ገፀ-ባህሪ ሀያቱን ይገልበታል ። )

ገዝሙ ፦ አያቴ... አያቴ ...እማ ምንድን ነው ያደረከው አንተ የማትረባ ደደብ አያቴ እማዬ ( ለቅሶ እህቱ እና
እናቱም በመራር ሀዘን ያለቅሣሉ ። )

ንጉሡ ፦ (ንጉሱ አሽከሮቹን የገዝሙን እህት እንዲደፍሯት እዛው በእጁ ምልክት ሰቶ ያዛቸዋል አሽከሮቹ እህቱን
ሊደፍሯት ይታገሏታል እህቱ እያለቀሠች ትጮሀለች)

ገዝሙ ፦ /ንዴት / ተዉ አቁሙ የማትረቡ .. እሺ እሺ አቁም ተዉ ተዉ (እያለቀሠ) የምትፈልገውን በሙሉ


አደርግልሀለሁ ...

ንጉሱ :-ወደህ ነው !
የገዝሙ እናት :- (እየተሰቃዩ) ልጄ እንዳታደርገው ይሄ አረመኔ ሞት ነው የሚገባው

እህት ፦ ወንድሜ እባክህ ተው እኛ እናልፋለን

ንጉሡ ፦ ሽሽሽ !! አታላዝኑብኝ / ገዝሙ ወደ ንጉሡ መድሀኒቱን ይዞ ይጠጋል / ::

እህት ፦ ግን ብዙ ምስኪኖች ነፃ ይወጣሉ ምንም ነገር ቢያደርግ የፈለገውን ነገር በፍፁም እንዳትሠጠው ይህንን እድል
ለብዙ አመታት ስንጠብቀው ነበር ይኸው ዛሬ ቀኑ ደርሶ ፈጣሪ ይህንን ታላቅ የነፃነት ቀን ሰጠን እባክህ አታባክነው
ወንድሜ መቼም ደግመን አናገኘውም ።

ንጉሱ ፦ በቃሽ !

እህት ፦ እኛ ብቻ አይደለንም ለነጻነታችን ሲሉ በየሜዳው አሁንም ሺዎች እየወደቁ ነው :: ነፃነት ያለ መስዋዕትነት


አይመጣም ወንድሜ

ንጉሡ ፦ አፍሽን ዝጊ ! (ንጉሡ በጥፊ ይመታታል)

ገዝሙ :- አንተ ግን አውሬ ነህ መቼም አትለወጥም ለስልጣን ለገንዘብ ስትል ምንም ነገር ታደርጋለህ ያኔም አሁንም
ያው ነህ ተጫኔ !
/ንጉሡ በእውነተኛ ስሙ ስለተጠራ በጣም ደንግጧል ልጅቷን ከመድፈር በእጁ ምልክት ሰቶ ያስቆማቸዋል/

ንጉሱ :- ይህን ስሜን ከልጅነት ጓደኞቼ ውጪ ማንም አያውቀውም ! ማነህ አንተ

ገዝሙ ፦ (ጥቂት ረጋ ብሎ እንባ እየተናነቀው ያሣለፉትን ይነግረዋል)

ተማሪ እያለን ስልጣን ይዘህ መሪ መሆን እንደምትፈልግ ትነግረን ነበር ። ንጉሰ ሀገራችንን ልታሳድግ በቅንነት
ልታገለግል ፣ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብለህ ለፍትህ እንደምትቆም፣ ህዝብህን በታማኝነት እንደምታገለግል ሁሌም
ትነግረን ነበር :: እኛም ካንተ ጋር ብዙ ጊዜ ደጋግመን ስለሰማነው እኩል አብረንህ እንልና እርስ በእርስ ተያይተን
:: ግን ስልጣን የማይቀይረው ሰው የለም አንተም እዚህ ወንበር ላይ ስተቀመጥ ረከስክ ሰውነትህን ረሳህ
እንስቅ ነበር
ሞትህ ቀርቶ የምትታመም አይመስልህም ነበር ግን አሁን ራስህን ተመልከት :: / ገዝሙ ንጉሱን በዚህ ሁሉ ሂደት
ውስጥ እያወራው መድሀኒቱን ይሠጠዋል /

ንጉሡ ፦ ገ ..ገዝሙ ? /ንጉሱ መዳኒቱን ከዋጠ በኋላ ጭራሽ ህመሙ ይብስበታል/ (ሣል) ስለዚህ ልትገለኝ
ነው... እ እ እ ..ምንድን ነው ያደረከው መዳኒት ስልህ ግን አንተ ምን ሰጠኸኝ ?

ገዝሙ :- የሰጠሁህ መዳኒት የሚሰራው ከግማሽ ሰዓት በኋላ ነው አሁን የምትፈልገውን ይኸው አድርጌልሀለሁ
እናቴን እና እህቴ ልቀቃቸው

ንጉሱ ፦ /ገዝሙ ይዞት የነበረውን መዳኒት ነጥቆት/ አንተ በትክክል እዚ የመጣሀው እኔን ገለህ ስልጣኔን ለመውረስ
ነው:: የምታድነኝ መስሎኝ ብዙ እድል ሰጥቼህ ነበር ግን አንተ ልትጠቀምበት አልቻልክም ግማሽ ሰዓት ቀርቶ
ሽርፍራፊ ደቂቃዎች እንኳን የሉኝም ከዚህ በላይ ግን በፍፁም ልታገስህ አልችልም :: /አጠገቡ ካለው ወታደር ወገብ
ላይ ሰይፉን ሲመዝ |

ንግስት :- (ፈጠን ብላ በማስመሰል) የኔ ጌታ ሌላ መፍትሄ እንፈልግ እንደምታየው በድርቅናው ቀጥሏል


ምንም ብናደርጋቸው በቀላሉ የሚሆን አይደለም ጊዜያችንን ነው እየወሰዱብን ያሉት ያለንን ከማድረግ በቀር ምንም
አማራጭ የለንም ትክክለኛውን መድሀኒት እንዲሠጠን የግድ እህቱን እና እናቱን መልቀቅ አለብን እሱ በእጃችን ነው

ንጉሡ ፦ አይ ይሄ መቼም ሊሆን አይችልም !

ንግስት ፦ የኔ ጌታ ከአንተ ህይወት የሚበልጥ ነገር አለ አሁን ጨረቃ ከመጥለቋ ጀንበርም ከመውጣቷ በፊት ያንተን
ህይወት ማዳን አለብን ::

ጓጉሡ ፦ ይሄ ምናምንቴ ማን እንደሆንክ ነው የምታስበው የማደርገውን እኔ አውቃለሁ እናቱንም እህቱንም ውሰዱና


እንደፈለጋችሁ ተጫወቱባቸው :: / አሽከሮቹ የተባሉትን ያደርጋሉ /

ገዝሙ ፦ አቁም ! ምን እያደረጋችሁ ነው አቁሙ !እማዬ እህቴ. . ተው እየለመንኩህ ነው አድነኝ አልክ


መድሀኒት ሰጠሁህ ከዚህ በላይ ምንፈለክ

ንጉሡ ፦ ዶክተሩን ጥሩት !... (3 ሀኪሞች ወደ ንጉሡ ይመጣሉ) ይህ ሰው የቀመመውን መድሃኒት ምንነት በደንብ
አረጋግጥ እና መድሃኒቱን በቶሎ ስጠኝ ።

ዶክተር 1፦ እንደትእዛዝዎ ንጉሴ ሆይ ... /የገዝሙ እናትና እህት ከወታደሮቹ ጋር ይታገላሉ ። /

ንጉሡ ፦ እ.. ጨረሳችሁ

ዶክተር 2፦ እያለቀ ነው ጌታዬ ... በቃ እንደውም አልቋል ንጉስ ሆይ / እየቀመሙ /

ንጉሡ ፦ (ንጉሡ በደስታ ወደ ገዝሙ ተጠግቶ) አየህ አንተ መቼም ልታሸንፈኝ አትችልም የኛ ነጻ አውጪ ማን
ግንባርን እንበል አንተ ተራ ከማን ጋር እየተጋፈጥክ እንደሆነ አልገባህም ::

ገዝሙ ፦ /ፊቱ ላይ ይተፋበታል /

ንጉሡ ፦ /ፊቱን በንፁህ ጨርቅ ጠርጎ በጥፊ ይመታዋል / ውሻ ! ግን ከዚ በኋላ እንድትተነፍስ በፍጹም
አልፈቅድልህም !
/ንጉሡ ሰይፉን ይመዛል .. ንግስቷ ትደነግጣለች ግራ ትጋባለች ከመድረኩ ጀርባ እናቱንና እህቱን ንጉሡ
ያስደፍራቸዋል ይሄኔ ገዝሙ ንጉሱን በራሱ ሠይፍ ተቀብሎ ሊገለው ሲታገል ደጀኔ ወይንም ጨካኙ የንጉሡ አሽከር
ገዝሙን ከኋላ ወግቶ ይገድለዋል። የመብረቅ መብራት ብልጭ ድርግም ይላል /ንግስቷ ገዝሙ እና ንጉሱ
ከመጣላታቸው ቀደም ብላ ከመድረኩ ጀርባ በመሄድ እናት እና እህቱን ሊደፍሯቸው የሚረባረቡ ወታደሮቹን ሄዳ
ታስቆማቸዋለች

በመጨረሻም ገዝሙ ተወግቶ ይወድቃል ። ጥቂት ፀጥታ መድረኩ ላይ ይሠፍናል ። ንግስቷ አፏን አፍና ታለቅሣለች

ንጉሡ ፦( ቶሎ ቶሎ እየተነፈሠ ) ዶክተር በል መድሀኒቱን አምጣው ::

ዶክተር 1 ፦ እሺ ጌታዬ

ንጉሡ :- /መድሀኒቱን እስኪያመጣለት የገዝሙ አስክሬን ላይ ይተፋበታል ንጉሡም ሊሞት ተቃርቧል /. . (


እያቃሰተ ).. በሉ ፍጠኑ እንጂ .. እ መድሃኒቱን ስጡኝ ።

ዶክተር 2 ፦ ን ... ንጉስ ሆይ መዳኒቱን ማዘጋጀት አልቻልንም

ንጉሡ ፦ አ..አልቻልንም .. ማለት ምን ማለት ነው ?

ዶክተር 1፦ አንድ የጎደለ ነገር አለ እየፈለግን ነበር ግን ይሄን ነገር እኛ አናውቀም

ንጉሡ ፦ እናንት ደደብ ሀኪሞች ሂዱ ከዚ ጥፉ / ንጉሡ እየተደነባበረ እያሣለ መድሀኒቱን ደበላልቆ ይጠጣዋል ንግስቷ
፦ /ገዝሙን እያየች ታለቅሳለች /

(ንጉሡ መድሀኒቱን ከጠጣው በኋላ ሀይለኛ የመብረቅ መብራት በሀይል በርቶ ይወድቃል)

ንጉሡ ፦ ልጃችንን አ.. አደራ አ ..አፈቅርሻለሁ !

ንግስቷ ፦ የገዝሙን እጅ ሆዷ ላይ አስደግፋ በመያዝ ትንሽ ከቆየች በኋላ በወደቀበት አቅፋው ታለቅሳለች ንጉሡ ይህን
እያየ እንደ አውሬ በአራት እግሩ መሄድ ይጀምራል የጠጣው ቀይ መድሀኒት ልብሡ እና አፉ ላይ ተደፍቶ ሠይጣን
መስሏል እንደ እንስሳም እንደ እብድም ሆኖ ከአሽከሮቹ አንዱ የሆነውን የጠባቂዎቹ አለቃን ይነክሰዋል የተነከሰው
ጠባቂም እንደ ንጉሱ እያበደ ልብሱን እየቀዳደደ ከመድረኩ ይወርዳል ።
የነበሩት በሙሉ ሌላ ሰው እንዳይመርዝ ሊገድሉት ያሳድዱታል የገዝሙ እናትና እህት መጥተው ገዝ ሙን
አቅፈውት ያለቅሳሉ::
/መብራት ይጠፋል /

/አዋጅ በስፖት ላይት ይነገራል /።

አዋጅ ነጋሪ ፦ አዋጅ አዋጅ አዋጅ በመላው ማጎሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ንፁሀንን በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
አሁን ይለቀቁ ንጉሡ የሀገራችን ስጋት በመሆኑ እስካሁንም በርካቶች ላይ ጥቃት በማድረሱ ንጉሱን ባገኘበት ለገደለ
10 ሚልዮን ፍራንክ የወረታ ክፍያ ያገኛል :: ከዛሬ ጀምሮ በህዝብ የተመረጠ ንጉስ እስኪሾም ንግስታችን ይህን ሀገር
እየመራች ትቀጥላለች:: በነገው ዕለት የነፃነት አርማችን የሆነው የገዝሙ የቀብር ስነ ስርዓት ስለሚፈጸም
መላው ህዝብ የቀበሩ ቦታ ላይ ይገኝ ።

"ዘላለማዊ እረፍት ለነፃነታችን ሲሉ ለተሠው ሰማዕታት እናት አባቶች እህት ወንድሞቻችን ይሁን፡፡ ንግስት
እየሩሳሌም ንግስተ ነገስት ዘ ኢዝቆጲያ!

/ስፖት ላይት ይጠፋል /


~ አበቃ ~

You might also like