በህሬ

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 8

በህረዲን ሱነሞ የነዳጅ ማደያና ፔንሲዮን

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በስልጤ ዞን በሁልባራግ ወረዳ

በቢለዋንጃ ከተማ ዉስጥ ዘመናዊ የነዳጅ ማደያና

ፔንሲዮን ለማቋቋም ተዘጋጅቶ የቀረበ የቢዝነስ

ፕሮጀክት ፕሮፖዛል

ሚያዝያ/2015
ጠቅላላ የፕሮጀክቱ ገጽታ (EXcutive summary)

የፕሮጀክቱ መጠርያ ስም-በህረዲን ሱነሞ የነዳጅ ያማያና ፔንሲዮን

የፕሮጀክቱ ባለቤት ስም፡- በህረዲን ሱነሞ

ፕሮጀክቱ የሚቋቋምበት ቦታ አድራሻ ፡- በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ስልጤ ዞን ሁልባራግ

ወረዳ ቢለዋንጃ ከተማ

ስልክ ቁጥር ፡- 0920555060

የፕሮጀክቱ የስራ ዘርፍ ፡- በነዳጅ ንግዱ ዘርፍ ዘመናዊና ደረጃዉን የጠበቀ የነዳጅ ማደያና

በዉስጡ ደረጃዉን የጠበቀ ፔንሲዮን ማቋቋም

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገዉ መሬት ፡-2000 ካሬ (ሁለት ሺህ ካሬ ሜትር)

በፕሮጀክቱ እዉን መሆኑ ምክንያት ሊፈጥር የሚችለዉ የስራ እድል

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በፕሮጀክቱ የግንባታ ወቅት

- ቋሚ ሠራተኞች 11 ቋሚ ሠራተኞች 02
- ጊዚያዊ ሠሰራተኛ 07 ጊዚያዊ ሠሰራተኛ 20

ድምር 18 ሰዎች ድምር 22 ሰዎች

ፕሮጀክቱ በግንባታዉ ወቅትና ፕሮቸክቱ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር በአጠቃላይ ለ 40 ሰዎች የስራ እድል
ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ የመነሻ ካፒታል

 በአጠቃላይ ለኢንቨስት መንቱ የሚያስፈልግ ወጪ---------------------4.667.500.00


 ስራዉን ለማስጀመር የሚያስፈልጉ የጥሬ እቃዎች ወጪ--------1.816.800.00

የፕሮጀክቱ ጠቅላላ የመነሻ ካፒታል ምንጭ


 ከባላሃቱ የግል ቁጠባ 100 %፡--------
6.484.300.00

ጠቅላላ ድምር 6.484.300.00

የፕሮጀክቱ ጠቀሜታ
ባላሀብቱ በኬራቴ ከተማ ዉስይ ለማቋቋም ያቀዱት የነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬት ለወረዳዉ እንዲሁም
ለዚሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን የሚሰጥ ሲሆን በዋንነት ለ 40 ሰዎች የስራ እድል
በመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለዉን የስራ አጥነት ቁጥር መቀነስ ፤ በአካባቢዉ ላይ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ
ተሸከርካሪዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በቂ የሆነ የተለያዩ የነዳጅ
አይነቶችን በበቂ ሁኔታ በማቅረብ በከተማዋ ዉስጥ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ ዋጋ ዉድነትን እና እጥረትን
መቀነስ እንዲሁም በዉስጥ ደረጃዉን የጠበቀ ሱፐር ማርኬት
በመክፈትና የተለያዩ አይነት ሸቀጣ ሸቀጦችን በማቅረብ የህብረተሰብ ፍላጎት ማርካት በጥቂቱ ሲሆኑ
የፕሮጀክቱ መቋቋም እንደ ወረዳና ዞን እንዲሁም እንደ ክልልና ሀገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን ሊሰጥ ይችላል
፡፡

1. የፕሮጀክቱ መሠረታዊ መረጃ


1.1 የፕሮጀክቱ መጠርያ ፡- ኑረዲን ጀማል የነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬት

1.2 የድርጅቱ ባለቤት፡- የዚህ ፕሮጀክት ባለቤት አቶ ኑረዲን ጀማል የሚባሉ የከተማዋ የከተማዋ
ተወላጅ ዲያስፖራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ነዋሪነታቸዉ ዉስጥ ነዉ ፡፡

1.3 የድርጅቱ ናለቤት በንግድ ስራ ላይ ያላቸዉ ተሞክሮ

አቶ ኑረዲን ጀማል በአሁኑ ወቅት ነዋሪነታቸዉ በሰዉዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ዉስጥ ሲሆን በከተማዋ
ዉስጥ ከ 15 አመት በላይ በነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬቶች ዉስጥ እንዲሁም በተለያዩ ስራዎች ላይ
በመሰማራት በቂ ልምድና ካፒታል ያካበቱ ሲሆን እኚ ዲያስፖራ በዉጭ ሀገር ላይ ለረጂም አመታት በመስራት
ያካበቱትን በቂ የሆነ የንግድ ክህሎትና ካፒታል ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ ይዘዉ በመምጣት በትዉልድ
አካባቢያቸዉ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ በመወሰን ሙሉ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወረዳዋ ወና ከተማ ኬራቴ ከተማ
ዉስጥ በሚገኛ ለነዳጅ ማደያ አመቺ የሆነ 5 ሺ ካ.ሜ መሬጽ ላይ ደረጃዉን ደረጃዉን የጠበቀ የነዳጅ
ማደያና ሱፐር ማርኬት ለማቋቋም ያቀዱ ዉጤታማና ልማታዊ የሆነ ሲያስፖራ ባላሃብት ናቸዉ ፡፡

1.4 ፕሮጀክቱ የሚፈጸምበት ቦታና ግጊ


ኑረዲን ጀማል የነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬት የሚቋቋመዉ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ በኬራቴ ከተማ 01 ቀበሌ ዉስጥ በሚገኛ ለፕሮጀክቱ ተግባር
አመቺ በሆነና በዋና አስፓልት መንገድ ዳርቻ ላይ በሚገኘዉ 5 ሺህ ካ/ሜ መሬት ላይ ሲሆን
አካባቢዉ የተሟላ የመሠረተ ልማት የማብራትአገልግሎት፡ የአዉቶ ማቲክና የሞባይል ስልክ
አገልግሎት፡ በቂ የሆነ የዉሃ አቅርቦትና ሌሎች ለፕሮጀክቱ ትግበራ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች
በሚገኙበት ቦታ ላይ ነዉ፡፡
ዲያስፖራ ባላ ሀብቱ የነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬቱን ግንባታ ይህ የቢዝነስ ፕሮጀክት
ፕሮፖዛል በፍጥነት ምላሽ ተሰጥት የቦታ ርክክብ እናድትደረግ በ 2 ወርጊዜ ዉስጥ ወደ ተግባር
ለመግባት እቅድ ያላቸዉ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የግንባታ ቁሳቁሶች አቅርቦት እንዲሁም
ከነዳጅ ማደያ ዋናዉ ካምፓኒ ጋር ስምምነት የመፈራረምና ለማደያዉ አስፈላጊ የሆነ
ቁሳቁሶች የማሟላት በፍጥነት ይከናወናሉ፡፡
1.5 ፕሮጀክቱ የሚፈጸምበት ቦታ መረጃ

በሁልባራግ ወረዳ በደቡብ ብሄሮች ብ/ህ/ክ/መ/ስልጤ ዞን ወስጥ ከሚገኙት 10 ወረዳዎች ወስጥ አንዱ ሲሆን
በምስራቅ ሎግቲዉቲወድ 38 96.5 እና በሰሜን ላቲቲዉድ 7 39 በደቡብ 8.00 በምእራብ 35 15 ላይ ይገኛል
ወረዳዉ በሰሜን ከወራበ ከተማ አስተዳደር በደቡብ ከሳኩራ ወረዳና ከሀድያ ዞን በምስራቅ ከዳሎቻ ወረዳ
በምእራብ ከምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ጋር ይወሰናል ከወረዳዉ ዉስጥ ከ 96 በላይ የሚሆነዉ
የህብረተሰብ መተዳደርያወ ግብርና ማለትም እርሻና የእንሰሳት እርባታ ነዉ

የወረዳዉ የቆዳዉ ስፋት 403000 ሄ/ ር ሲሆን ከዚያም ዉስጥ 24205 ሄ/ር ለእርሻ 2943 ሄ/ር ለግጦሽ 3694
ሄ/ር በደንና ቁንቋጦ 2945 ሄ/ር በቁዋሚ ተክሎች 3860 ሄ/ር በተለያዩ አገልግሎቶች በመደር በመገዶችና
ቦሮቦሮች እንዲሁም 2613 ሄ/ር በተጎዳ መሬተር የተሸፈነ ነዉ
የወረዳዉ አግሮ ክላይ ሜቲክ ቀጠ 77% እርጥበት ወይን አደጋና 23% ደረቅ ወይን አደጋ ነዉ የወረዳዉ
አመታዊ የዝናብ መጠን በአማካይ 10 12 እስከ 15 50 ሚ/ሜ ይደርሳል የወረዳዉ አመታዊ አማካይ የሙቀት
መጠን 27 ሲሆን የወረዳዉ መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ ከባህር ጠለል በላይ 18 91 24 60 ሜትር ነዉ
ባጠቃላይ የወረዳዉ የአየር ጸባይና የአፈር ሁኔታ ለልዩልዩ የግብርና የህዝብ እድገቱ 2.8% መሆኑን መሰረት
በማድረግ ወንድ 54.463 ሴት 55.285 በድምሩም 109.748 ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ከዚህም ወስጥ
97% በገጠር እና 3% በከተማ ይኖራል የአንድ አባወራ የመረት ኢዞታ በአማካይ 1.66 ሄ/ር ሲሆን በወዳዉ
የሚመረቱ ዋናዋና ሰብሎች ስዴ፤ ማሹላ፤ በቆሎ፤ጤፍ፤ገብስ፤ ባቄላ፤በርበሬ የተለያዩ ፍራፍሬዎች ናቸዉ፡፡

ወረዳዉ በአንድ የከተማ አስተዳደርና በ 13 የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረ ነዉ የወረዳዉ ርእስ ከተማ ኬራቴ
ከሀገራቱ መደና አዲስ አበባ በስተደቡብ በ 188 ኪ/ሜ ከክልል ርእስ መዲን ሀዋሳ በስተ ሰሜን ምዕራብ በ 150
ኪ/ሜ እና ከዞኑ ዋና ከተማ ከወራቤ በስተ ደቡብ 15 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን ከተማዋን በሀለት
የተለያዩ በኩሎች አቋርጠዋልት የሚያልፍ ዋና አስባልት መገዶች ይሏትና ለሁሉም ወረዳዎችም ሆነ ለሌሎች
ዞኖች በገበያ መዳረሻነት በአዋሳኝ ቦታ ላይ የምትገኝና በፍጥነት በማደግ ላይ ያለች እንዲሁም በዞኑ ከሚገኙ
ሌሎች ከተማዎች በተሸለ ለተለያዩ የእንቨስት መንት አይነቶች የምትሆን አመቺ ከተማ ንት፡፡

1.6 የፕሮክቱ የወደፊት እቅድ

ባለሀብቱ በሰዉዲ አረብያ ርያድ ከተማወስጥ በልዩ ልዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተዉ የሚገኙ ዉጤታማና
ልማታዊ ባለሀብት ሲሆን በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ላይ ያካበቱትን ካፒያል ወደ ላቀ ኢንቨስት መንት ለመቀየር
በማሰብ በወረዳወ ዋና ከተማ ኬራቴ ከትማ ዉስጥ ኑረዲን ጀማል የነዳጅ ማደያና ሰፐር ማርኬት በሚል
ስያሜ የነዳጅ ማደያና ደረጃዉ የጠበቀ ሱፐር ማርኬት ላማቋቋም የሚስቸ ላቸው አስፈላጊው ቅደመ
ዝግጀትና በጀት አዘጌጅተዉ ወደ ተግባር ስራዉ የግብ ሲሆን ይህንን ዘመናዊ ሁለ ገብ አገልግሎቶች የሚሰጥ
የነዳጅ ማደያና ሱፐር ማርኬት ካቋቋሙ ቡኋላ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ዉስጥ በከተማዋ ዉስጥ
በሌሎች ኢንቨስት መንት ስራዎች ማለትም በዱቄት ፋብሪካና በምግብ ማቀነባበርያ ኢንዱስትሪ፤ሁለ ገብ
አገልግሎት መስጠት በሚችል ባለ አራት ፎቅ የንግድ መዕከል ህንፃ ግንባታና እንዲሁም ደረጃዉን የጠበቀ
መዝናኛና ሎጅ በከተማዋ ዉስጥ ለማቋቋም የረጂም ግዜ እስትራቴጂክ እቅድ ያላቸው ከመሆኑም በተጨመሪ
ከ 5 ዓመት በኋላ ለማቋቋም ባቀዷቸው የተለያዩ ድርጅቶች አማከኝነት ተጨማሪ ለ 65 ቋሚና ለ 70 ግዜያዊ
በድምሩ ለ 135 ሰዎች ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የወደፊት ዕቅድ ያላቸው ልማታዊ የሆኑ
ሀገር በቀል ባለሀብት ናቸው፡፡

1.7 የፕሮጀክቱ የአፈፃፀም ስልት

በወረዳው ካሉት ከተማዎች አንዱ በሆነችው ቢለዋንጃ ከተማ ውስጥ በህረዲን ሱነሞ የነዳጅ ማደያና
ፔንሲዮን በሚል ስያሜ ለማቋቋም የታቀደውን የነዳጅ ማደያና ፔንሲዮን ግንባታዎን የመገንባት ስራዉ
የሚከናወነዉ ይህ የቢዝነስ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ከሚመለከታቸዉ አካላት ተቀባይነት አግኛቶ ለፕሮጀክቱ
ትግበራ አስፈላጊ የሆነዉን የቦታ ርክክብ እና የስራ ፍቃድ ከተገኘ ቡኋላ ሲሆን ይህ እንደተጠናቀቀ በቀጥታ
ግንባታዉን ለማከናወን የሚያስችል የቦታ ፕላን ወይም ዲዛይን በባለ ሞያ በማሰራት ወደ ትግበራ ስራዉ
የሚገባ ሲኖን ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በማቅረብ የግንባታ ስራው በፍጥነት የሚጀመር
ስሆን ከዚሁ ጎን ለጎን ነዳጅ ማደያውን ለማቋቋም አስከፈላጊ የሆኑ ማሽኖችን የሚቀበሩ የነዳጅ ታንከሮችና
ሌሎች አስወፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን የማቅረብ ስራው ይከናወናል፡፡ በዝህም መሰረት ማደያውን የማቋቋም
የታቀደበት ቢለዋንጃ ከተማ በአቅራቢያው ለግንባታ የሚሆኑ የጥሬ ዕቃዎች ማለትም የድንጋይ፣ የአሻዋና
የቦረቦር አፈር እንዲሁም በቂ የሆነ የሰው ሓይል አቅርቦት በበቂ ሁኔታ የሚገኘበት በመሆኑ የመሬት ርክክብ
ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ስራዎችን እና የነዳጅ ማደያ
ማሽኖችን ተከላና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሟልቶ በማጠናቀቃ ስራ ለማስጀመር የሚያስችለውን
በቂ በጀት በማዘጋጀት ወደ ቅድማ ትግበራ ስራው ልገባ ችሏል፡፡
በዝህም መሰረት በህረዲን ሱነሞ የነዳጅ ማደያና ፔኒስዮን በሚል ስያሜ በቢለዋንጃ ከተማ ውስጥ ለማቋቋም
የታቀደው የቢዝነስ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በውስጡ 04 የተለያዩ ዓይነት የተሸከርካሪ ነዳጆች መቅጃ ማሽን
ያለው የነዳጅ ማደያ፣ 01 ደረጃውን የጠበቀ ለፔንሲዮን የሚሆን ንንባታ እንዲሁም አንድ የተለያየ አገልግሎት
የሚውል ግንባታ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋል፡፡

2. የፕሮጀክቱ የምረት፣ የግንባታ፣ የሰው ኃይልና የግብዓት ትንተና

2.1 የፕሮጀክቱ የምርት ዕቅድ


በህረዲን ሱነሞ ነዳጅ ማደያና ፔንሲዮን በምርትነት የሚያቀርበው የተለያየ አይነት የተሸከርካሪ የነዳጅ
ምርቶችን፣ የተለያየ አይነት የተሸከርካሪ ዘይቶችና ቅባቶች ሽያጭ እንዲሁም በፔንሲዮን የተለያየ የማረፊያ
አገልግሎት ለማቅረብ ዕቅድ አለው፡፡ በዝህም መሰረት ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው ይህ ዘመናዊ የነዳጅ
ማደያና ፔንሲዮን ስራ በሚጀምርበት ወቅት 02 የመኪና ናፍጣ መቅጃ፣ 01 የቤንዚን መቅጃና 01 የነጭ ጋዝ
መቅጃ ማሽኖች እንዲሁም 01 ባለ 30 መኝታና ካፌና ሬስቶራንት የለው ፔንሲዮን ይኖሩታል፡፡ በዝህም
መሰረት በነዳጅ ማደያው ውስጥ የሚከተሉት 02 የመኪና ናፍጣ መቅጃ ማሽኖች በቀን 1800 ሌትር የመኪና
ናፍጣ፣ ከ 01 የቤንዚን መቅጃ ማሻን በቀን 700 ሌትር ቤንዚን እንዲሁም ከ 01 የነጭ ጋዝ መቅጃ ማሽን 200
ሌትር የነጭ ጋዝ በየቀኑ የሸጣል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ ሲሆን በፔንሲዮኑ ውስጥ በሚሰጥ 30 የመኝታ
አገልግሎት በየቀኑ በአማካይ 25 አልጋ አግልግሎት ይሰጣል ተብሎ ታቅዶ 20 በ 450 ብር 9000 ብር በቀን
በአልጋ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ የካፍቴሪያና ሬስቶራነት ስራምው በቀነ 150 የተለያዩ አይነት ምግቦችና እሰከ
200 የካፍቴሪያ አገልግሎቶች ቢቀርቡ ይገኛል ተብሎ የታቀደው የቀን ገቢ 50000 ይሆናል ተብሎ ታቅዷል፡፡
ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በማደያውና በፔንሲዮኑ በ 03 ዓመት ውስጥ ለሽያጭ ለማቅረብ
የታቀዱትን የተለያዩ ዓይነት የነዳጅ ምርቶችን፣ የመኝታ አገልግሎት፣ ካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት
እንዲሁም የተሸከርካሪ ዘይትና ቅባቶችን አቅርቦት የየዕለቱን በማስላት የዓመቱን ስሌት በ 10% በማሳደግ
እንዲሁም በመኃል ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ ምርቶችን እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች እጥረት ታሳቢ
በማድረግ በአመቱ ውስጥ ካሉት 365 ቀናት ውስጥ የ 300 ቀናትን ብቻ ታሳቢ በማድረግ በማደያው ለገበያ
ሚቀርቡ የምርትና የአገልድሎት አይነቶችን ዝርዝር የዕቅድ መጠን ከታች ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 1፡- የፕሮጀክቱ የምርት/ የአገልግሎት ዕቅድ ዝርዝር መግለጫ

ተ. ለሽያጭ የሚቀርቡ ልዩልዩ ምርቶችና መለ የዓመቱ የሽያጭ/አገልግሎት ተጠቃሚች ጠቅላላ


ቁ አገልግሎቶች ኪያ መጠን ድምር
1 ኛ ዓመት 2 ኛ ዓመት 3 ኛ ዓመት
1 ለሽያጭ የሚቀርብ የመኪና ናፍጣ ሌት 540,000 594,000 653,400 1,787,40
/1800*300 ቀን/ ር 0

2 ለሽያጭ የሚቀርብ ቤንዚል/700*300 ሌት 210,000 231,000 254,100 695,100


ቀን/ ር
3 ለሽያጭ የሚቀርብ ነጭ ጋዝ /200*300/ ሌት 60,000 66,000 72,600 198,600

4 የፔንሲዮን፣ ካፌና ሬስቶራንት አገልግሎት በብር 17,700,00 19,470,00 21,417,00 58,587,0
0 0 0 00

5 ለሽያጭ የሚቀርብ ዘየትና ቅበቀቶች ሌት 9,000 9,900 10,890 29,790



2.2 የፕሮጀክቱ የግንባታ ፍላጎትና የወጪ ዕቅድ
በቢለዋንጃ ከተማ ውስጥ በህረዲን ሱነሞ ነዳጅ ማደያና ፔንሲዮን በሚል ስያሜ ለፕሮጀክቱ ትግበራ በሆነ
2,000 ካሬ ሜትር መሬት ለይ ተግባራዊ ለማድረግ በቅድሚያ ይህ የቢዝነስ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል የሁንታን
አግኝቶ ከሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶት ቦታውን እንደተረከበ በአፈጣኝ ወደ ትግበራ
ስራው በመግባት የተለያዩ ግንባታዎችን የሚያከናውን ሲሆን ከነዝህም ውሰጥ የነዳጅ ማደያ ማሽኖችን
የተከላና የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቦቴዎችን የመቅበርና የማደያውን ዘመናዊ ሼድ ስራ፣ የፔንሲዮን እና ካፌና
ሬስቶራንት ግንባታ ስራ፣ የቢሮና የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ስራ፣ የዘበኛና የሰራተኞች ማረፊያ ግንባታ ስራ፣
የግቢ አጥር ስራ፣የውሃና ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስረዋችንና ሌሎች የወደፊት የፕሮጀክቱን የማስፋፊያ
ግንባታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በባለሙያ የቦታው ፕላንና ዲዛይን በማሰራት ግንባታው የሚከናወን
ይሆናል፡፡ በዝህም መሰረት ፕሮጀከረቱን ለማቋቋምና ስራ ለመጀመር በመጀመሪያው ዙር የሚያስፈልጉትን
የግንባታ አይነቶች፣ መጠንና የወጪ ዕቅድ ዝርዝር መግለጫ ከታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ በዝርዝር
ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 2 :- የፕሮጀክቱ የግንባታ ፍላጎትና የወጪ ዕቅድ ዝርዝር መግለጫ

ተ.ቁ የግንባታው አይነትና ስፋት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ


1 የፔንሲዮን ግንባታ በግንብ ካ.ሜ 01 2,000,000 2,000,000
500 ካሬ ስፋት
2 የነዳጅ ማደያ ማሽኖች ካ.ሜ 01 1,500,000 1,500,000
ሼድ በብረት
3 የታነከሮች መቅበሪያ ቦታ ቁጥር 04 80,000 320,000
ዝግጅት
4 የቢሮ ሬሰብሽን እና ቁጥር 03 75,000 225,000
መጸዳጃ ቤቶች
5 የሰራተኞች ማረፊያና ቁጥር 02 45,000 90,000
የዘበኛ ቤት
6 የግቢ ኤሌክትሪክናየቧንቧ ቁጥር 02 10,000 20,000
መስመር ዝረጋታ
7 የግቢ አጥር ስራ በብሎኬት ቁጥር 01 100,000 100,000
ጠቅላላ ድምር 1,780,000

2.3 የፕሮጀክቱ የሰው ኃይል ፍላጎትና ዝርዝር ደመወዝ የወጪ ዕቅድ

ይህ ዘመናዊ ፔንሲዮንና ነዳጅ ማደያ እውን ሆኖ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ለ 11 ቋሚና 07 ግዜያዊ በድምሩ
18 ሰዎች የስራ ዕድል የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ በፕሮጀክቱ የግንባታ ወቅትም በአከባቢው ለሚኖሩ
የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች ሰፋ ያለ የስራ ዕድልይፈጥራል፡፡

ሠንጠረዥ 3:- የፕሮጀክቱ የሰው ኃይል ፍላጎትና የደመወዝ ዝርዝር የወጪ ዕቅድ መግለጫ

ተ.ቁ የስራ መደብ የቅጥር ብዛት የወር የዓመት ጠቅላላ የ 03 ዓመት


ሁኔታ ደመወዝ ደመወዝ ደመወዝ
1 የድርጅቱ ስራ ቋሚ 01 5000 60,000 180000
አስኪያጅ
2 አካውንታንት ቋሚ 01 4500 54,000 162,000
3 የግዢ ሰራተኛ ቋሚ 01 4500 54,000 162,000
4 የሽያጭ ሰራተኛ ቋሚ 03 3000 36,000 108,000
5 ዋና ገንዘብያዥ ቋሚ 01 3000 36,000 108,000
6 የነዳጅ ቀጂ ቋሚ 04 2500 36,000 108,000
7 ጽዳት ሰራተኛ ኮንተራት 02 1500 18,000 54,000
8 ዘበኛ ኮንተራት 03 1500 18,000 54,000
9 አትክልተኛ ኮንተራት 02 1500 18,000 54,000
ጠቅላላ ድምር 27 648,000 1,134,000

2.4 የፕሮጀክቱ ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች፣ የማሽነሪና የፈርኒቸር ፍላጎትና ዝርዝር የወጪ ዕቅድ


የነዳጅ ማደያውና ፔንሲዮን ገበያው በቋሚ ንብረትነት አስፈላጊ የሆኑትን ግብአቶች ለድርጅቱ የምርት
ትግበራ አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበት ጊዜ አስፈላጊ የሆኑትን ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎችን፣ ማሽነሪዎችንነ
ፈርኒቸሮችን አቅርቦትን የሚያጠቃልል ሲሆን የነዝህን ግብኣቶች አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ይህ የቢዝነስ
ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ፍቃድ ተሰጥቶት ወደ ግንባታና ወደ ሌሎች ቅድመ ትግበራ ስራዎች እንደተገባ በአንድ
አመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን ግብአቶች የሟሟላትና ግቢውን የማስዋብና የማሳመር
ስራዎች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያስፈልጉትን ግብኣቶች በዓይነትና
በመጠን ከወጪ እቅዳቸው ጋር በዝርዝር ከታች ባለው ሠንጠረዥ ተገልጾዋል፡፡

ሠንጠረዥ 4፡- ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሆኑ የቋሚ ንብረቶች አይነትና ዝርዝር የወጪ ዕቅደ መግለጫ

ተ.ቁ የእቃው አይነት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ


1 የልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች 2,840,000
1.1 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቁጥር 04 650,000 2,600,000
ታንከር
1.2 የተለያዩ ዘይትና ነዳጅ ቁጥር 10 3,000 30,000
ማስቀመጫ በርሜሎች
1.3 የውሃ ሮቶ 10 ሺ ሌትር ቁጥር 02 45,000 90,000
1.4 ሌሎች እቃዎች በዙር 02 60,000 120,000
2 ማሽኖችና ልዩ ለዩ እቃዎች 860,000
2.1 የነዳጅ መቅጃ ማሽን በሴት 04 160,000 640,000
2.2 የእሳት አደጋ ማሽን ቁጥር 02 45,000 90,000
2.3 ካሽ ሬጅስተር ቁጥር 01 10,000 10,000
2.4 ሌሎች ማሽኖች በሴት 02 60,000 120,000
3 የቢሮና የፔንሲዮን እቃዎች 879,000
3.1 አልጋ ከነቁሳቁሱ ቁጥረ 15 45,000 675,000
3.2 ዴሰክ ቶፕ ኮምፒውተርና ቁጥር 02 30,000 60,000
ፕሪነተር
3.3 ካዘና ቁጥር 02 12,000 24,000
3.4 ሌሎች በዙር 02 60,000 120,000
ጠቅላላ ድምር 4,579,000

2.5 የፕሮጀክቱ የአላቂ እቃዎች /ግብኣቶች ፍላጎት የወጪ ዕቅድ


የነዳጅ ማደያውና ፔንሲዮኑ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ስኬታማነት በየወቅቱ አስፈላጊ የሆነ ግብአቶች
በበቂ መጠንና ጥራት ተለይተው የሚቀርቡ ሲሆን ከነዝህ ውስጥ በዋናነት የመኪና ናፍጣና ቤንዚል፣ ነጭ ጋዝ፣
የአልጋ አገልግሎትና የተለያዩ አይነት የተሸከርካሪ ዘይቶችና ቅባቶች እና ሌሎች ወጪዎችን የካተተ የወጪ
መግለጫ ሰንጠረዥ ለይ ተመላክቷል፡፡

You might also like