Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 7

ባለ ውለታዬ

ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ


ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ

በሩን ቢዘጋብኝ ስምኦን ጨክኖ


ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /2/

ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ


ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ሥራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ
ማዕረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /2/

ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ


ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ

ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ


ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ኃጢአትም በእነርሱ
በሰላም ሂጂ ብሎ ምሮኛል ንጉሡ /2/
ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ
ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ

የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ


በሠራልኝ ሥራ በዕድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ /2/

ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ


ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ
የጽድቅ በር ነሽ
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /2/
እመቤታችን ለእኛ ምርኩዝ ነሽ
>> ከለላ ሆንሽን
>> የእሳት ሙዳይ
>> እሳት ታቀፈሽ
>> በብርሃን ተከበሽ
>> ወርቅ ለብሰሽ
>> ከሴቶች ሁሉ
>> አብ መረጠሽ
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /2/
እመቤታችን ድንግል ሆይ ልጆችሽ
>> ዘውትር ይጠሩሻል
>> ስምሽን ለልጅ ልጅ
>> ያሳስቡልሻል
>> በተሰጠሽ ጸጋ
>> በአማላጅነትሽ  
>> ምሕረትን አሰጪን
>> ከመሐሪው ልጅሽ
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /2/
እመቤታችን ያልታረሰች እርሻ  
>> ዘር ያልተዘራባት
>> የሕይወትን ፍሬ  
>> ሰጠችን የእኛ እናት
>> የታረደው መሲሕ  
>> እናቱን ወደዳት
>> በቀኝ ቆማለች  
>> ድንግል እመቤት ናት
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማዕታት ምዕራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /2/
እመቤታችን የእውነት ደመና  
>> ዝናብ የታየባት
>> ወዳናለች ድንግል  
>> የታተመች ገነት
>> ክብርት ለሆነችው  
>> ኑ እንዘምርላት
>> ደስ ይበልሽ እንበል  
>> ለብርሃን እናት

You might also like