Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ወላዲተ ቃል

ድንግል / 2/
ወላዲተ ቃል

አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር…….ድንግል


ያንቺ ለብቻ ነው ትንሣኤሽ ሲነገር >>
ስጋሽ በምድር ላይ የት አለ እንደ ፍጡር >>
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር >>

ድንግል / 2/
ወላዲተ ቃል
ሥጋሽን ሲያሳርጉ መላእክት በሰማይ….ድንግል
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ >>
መግነዝ ተረከበ ለሐዋርያት ሊያሳይ >>

ድንግል / 2/
ወላዲተ ቃል

ትንሣኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው ..….ድንግል


ሐዋርያት ጾመው ተገለጥሽላቸው >>
ተቀብራ አልቀረችም በምድር ከደጅዋ >>
ወደ ለይ አረገች እርሷም እንደ ልጇ >>
ድንግል / 2/
ወላዲተ ቃል

ለማየት ሲጓጉ የድንግል ትነሣኤ…….ድንግል


እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባኤ >>
እኛም እንጸልይ ደጃችንን እንዝጋ >>
ከወላዲት አምላክ እንድናገኝ ዋጋ >>

ድንግል / 2/
ወላዲተ ቃል

You might also like