Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 64

እንደዚህ ማሰብ ስትጀምሩ

ታሸንፋላችሁ!
ገላ 1፡15-16
• ነገር ግን በእናቴ ማህፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋዉም
የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ
ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ
ጊዜ ወዲያዉ ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም
ገላ 1፡15-16)
ባርነት፣ ዕዉቀትና እዉነት
• “ለነጻነት ቁልፉ ዕዉቀት ነዉ፤ የዕዉቀት ቁልፉ
እዉነት ነዉ፤ የእዉነት ምንጩ ፈጣሪ ነዉ“
(ዶር. ማይልስ ማንሮዉ)
• አለማወቅ ትልቁ ጠላታችን ነዉ
• ከሰይጣን በባሰ የጎዳን ነገር ቢኖር ዕዉቀት ማጣታችን
ነዉ። እግዚአብሔር በሆሴዕ መጽሐፍ ሕዝቤ
ከሰይጣን የተነሳ ሳይሆን ካለማወቅ የተነሳ ጠፋ ሲል
እንሰማዋለን
ትልቁ ጠላታችን ድንቁርና
• ሰይጣን ከድንቁርና ያነሰ ጠላት ለማለት ሳይሆን እርሱ
እኛን ለማጥፋት የሚጠቀመዉ ትልቁ መሳሪያ ድንቁርና
ነዉ ለማለት ፈልጌ ነዉ
• የዚህ ዓለም ሰዎችን በማደንቆሪያ ጥላዉ ሥር በጨለማ
ያጠፋቸዋል
• የእግዚአብሔር ዕዉቀት በዙሪያችን ብዙ በበራ ቁጥር
ሰይጣን ግራ ይገባዋል
• ስለዚህ የእግዚአብሔር ዕዉቀት መገለጥ ያስፈልገናል
ከሥጋና ከደም ጋር ሳልማከር እንዴት?

• ሰዎች ለእኔ ካላቸዉ እይታና አስተያየት ዉጭ ነጻ


ሆኜ ለመኖር ማለትም ሰዎችን አማክሬ ሳይሆን
ራሴን በራሴ፣ ዉስጤን አድምጬ፣ ሐሳቤ ልክ መሆኑን
ወይም አለመሆኑን የማዉቅበትን መንገድ አለ ይሆን?
• ካለስ እንዴት ላግኝ?
• ትክክለኛ ማንነቴን የማግኘት ምስጢር ምንድነዉ?
1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን ከአንዳቸዉም ያልተጣበቀ
አዕምሮ/ልቦና ይኑርህ
• መርህ ቁጥር አንድ ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን ከምንም ያልተጣበቀ
አዕምሮ ይኑርህ የሚል ነዉ (“Have a mind that is open to
everything and attached to nothing.” Tilopa ( a
scholar of the 10th century)
• No one knows enough to be a pessimist (Wayne
Dyre). ማንም ሰዉ በእርግጠኝነት ተስፋ ለመቁረጥ የሚያበቃ በቂ
ዕዉቀት የለዉም። ማድረግ ለምንችለዉ ስለማንኛዉም ነገር፣
ገደብ ስናበጅ ወይም አዕምሮአችንን ስንዘጋዉ ሁሉን ለማድረግ
እግዚአብሔር በዉስጣችን ያስቀመጠዉን አቅም እንዘጋዋለን
ማለት ነዉ
1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን…
• ስለዚህ አዕምሮአችንን እንክፈት!
• አዕምሮአችሁን መክፈት ማለት በሌሎች ሰዎች
ለሚሰጣችሁ ለማንኛዉም የተሳሳተ ትምህርት ሁሉ
ራስን አጋልጦ መስጠት ማለት ሳይሆን
• አዕምሮአችሁ ከምኑም ሳይያያዝ የሰማችሁትን
መርምራችሁ ከተለመደዉ ዓለም ወጣ ያለዉን ትክክለኛ
ማንነታችሁን/ዉስጣችሁን የማግኘት ጉዳይ ነዉ
(ትክክለኛዉን ፓራዳይም የማግኘት ጉዳይ ነዉ)
1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን…
• በዙሪያችን የሚገኙ ሰዎች አብዛኞቹ የሚቀየሙብንን አንዳች
ነገር/ሰበብ ፍለጋ ላይ ያሉ ሰዎችን ይመስላሉ/ናቸዉምም (የሰዉ
ልጅ ሲፈልግ ተዓምረኛ ካልፈለገ ደግሞ ሰበበኛ ነዉ) ዳዊት
ድሪምስ
• በዓለማችን ባደረግኸዉ/በተናገርኸዉ ነገር ለመቀየም ሰበብ
የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥራቸዉ ብዙ ነዉ
• የማይወዱትን በማድረግህ/ባለማድረግህ፣ በመሆንህም ሆነ
ባለመሆንህ ብቻ ምን አለፋህ ሰዎች ለመቀየም/ሊቀየሙህ
ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ
• ልብ ብለህ ብታጠና ሰዎች ሊበሳጩብህና ሊቀየሙህ
የሚችሉባቸዉን 100 ምክንያቶች በቀላሉ ታገኛለህ
1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን…

• ነገር ግን ለሁሉም ነገር በተከፈተ ነገር ግን


ከማንኛዉም ነገር ጋር ባልተጣበቀ አዕምሮ በነዚህ
100 ነገሮች ማንንም አይቀየምም
• የዚህ ዓይነት አመለካከት ወይም አስተሳሰብ ያላቸዉ
ሰዎች ለሚሰሙት ወይም ለሚያዩት ነገር የሚሰጡት
ምላሽ ከሌሎቹ (ተራ ሰዎች) እጅግ የተለየ ነዉ
1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን…

• ብዙዉን ጊዜ እኛ አዲስ ብለን የምንላቸዉ ብዙ


ነገሮች ያረጁና ያፈጁ ነገር ግን በዚህ አዲስ ወቅት
በአዲስ መልክ የተገለጡልን ሀሳቦች ናቸዉ
• በነገራችን ላይ ለዉጥ ሁልጊዜም ነገሮችን ቀድሞ
በምታደርግባቸዉ መንገዶች ብቻ እስካደረግህ ጊዜ
ድረስ ሊመጣ የማይችል ነገር ነዉ
• አዕምሮህን ክፍት አድርግ ማለት በማንኛዉም ነገር
አትያዝ፣ አትጣበቅ እንደማለት ነዉ
2) የሌለህን ነገር መስጠት አትችልም

• ሁለተኛዉ መርህ የሌለህን ነገር መስጠት አትችልም ይላል (You


can’t give away what you don’t have)
• በቁጣና ፍርሃት ተሞልተህ ለሰዎች ፍቅርን ልትሰጣቸዉ
ብትሞክር ዘበት ነዉ የሚሆንብህ
• በጽንፈ አለሙ ዉስጥ ህግ አለ። The law of attraction.
አንተ ምን ዓይነት ሰዎችን ወይም ነገሮችን ነዉ የምትስበዉ።
አንተ መሳብ የምትችለዉ ለጽንፈ ዓለሙ የሰጠኸዉን ዓይነት
ነገር ነዉ።
• ለእኔ ያለኝ ነገር አንተ ነህ! (እግዚአብሔር)። ከእርሱ
(ከእግዚአብሔር) ብዙም ወሰድክ ትንሽ ምንም አይቀንስም
2) የሌለህን ነገር መስጠት…

• ያንተ መልዕክት ለጽንፈ ዓለሙ ስጠኝ፣ ስጠኝ፣


ስጠኝ የሚል ከሆነ ማለት ፀሎትህ ሁሌም ጌታ ሆይ
ያንንና ይህንን ስጠኝ የሚል ከሆነ የጽንፈ ዓለሙም
ምላሹ ተመሳሳይ ነዉ የሚሆነዉ፤ እርሱም ያን
ስጠኝ ይህንን ስጠኝ! ስጠኝ ይልሃል
• በዚህ ሁኔታ መቼም ቢሆን ወደፈለግህበት
አትደርስም፤ ሳትረካ እንደ ደኸየህ ትኖራለህ እንጂ
2) የሌለህን ነገር መስጠት…

• በተቃራኒዉ ለጽንፈ ዓለሙ፣ ወይም በአካባቢህ ላለዉ ዓለም


እንዴት ላገልግል ብለህ ብትጠይቀዉ ጽንፈ ዓለሙ አንተን
መልሶ እንዴት ላገልግልህ? ብሎ ይጠይቅሃል
• ከዓለማችሁ የምትጠይቁትን ጥያቄ ትታችሁ ምን ልትሰጡት
እንደሚፈልጉ መጠየቅ ስትጀምሩ ጽንፈ ዓለሙ ራሱ
የምትፈልጉትን ሊለግሳችሁ መጠየቅ ይጀምራል
• ልክ ፕረዘዳንት ጆን ከነዲ ለአሜሪካዊያን እንዳለዉ “አሜሪካ
ለእናንት ምን ማድረግ አለባት ሳይሆን ጥያቄአችሁ መሆን ያለበት
ለአሜሪካ ምን ላድርግ?” ነዉ መሆን ያለበት፤ ሁሌም በመስጠት
ዉስጥ መቀበል አለና
2) የሌለህን ነገር መስጠት…

• የሌለህን ለማንም ልትሰጥ አትችልምና ምን እንዳለህ


መዝገብህን ተመልከት
• ራስህን ምን ያክል ትወዳለህ? ምን ያክል ቸርነት በዉስጥህ
አለ? ምን ያክል ሰላም በዉስጥህ አለ? ምን ያክል ሀሴት
በዉስጥህ አለ?
• እነዚህ ነገሮች ካሉህና ለሌሎች የምተሰጣቸዉ ከሆነ ጽንፈ
ዓለሙ ከተትረፈረፈዉ ብልጽግናዉ መልሶና አብዝቶ
ያምበሸብሽሃል
ስጡ ይሰጣችሁማል
• በሉቃስ 6፥38 መጽሐፉ ስጡ ይሰጣችሁማል፤
በምትሰፍሩበት መሥፈሪያ ተመልሶ
ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቆነና የተነቀነቀ
የተትረፈረፈም መልካም መሥፈሪያ በዕቅፋችሁ
ይሰጣችኋል የሚለዉ ለዚህ ነዉ።
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ ለመሆን በቂ ምክንያት
የለህም/አይኖርህም
• ሦስተኛዉ መርህ ማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ በቂ ምክንያት የለዉም
ይላል (There are no justified resentments) የሚል
ነዉ
• ምንም ዓይነት በደል ባደረሰባችሁ ግለሰብ ላይ ማንኛዉንም
ዓይነት ጥላቻ ለማሳደር በቂ ምክንያት ልትሰጡ አትችሉም
• ጥላቻ የማታ ማታ የሚጎዳዉ ጥላቻዉን
የፈጠረዉን/የሚጠላዉን ግለሰብ እንጂ የተጠላዉን ሰዉ
አይደለም
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• ማንም ሰዉ በእባብ ስለተነደፈ አይሞትም፤ ሰዉ


የሚሞተዉ መርዙ በደምሥሩ እንዲሰራጭ
ስለፈቀደለት ብቻ ነዉ
• ስለዚህ በሆነ እባብ ከተነደፋችሁ እዉነት ነዉ
ተነድፋችኋል፤ ነገር ግን ጥላቻ እንደ መርዝ ወደ
ሰዉነታችሁ እንዲሠራጭና እንዲገድላችሁ
አትፍቀዱ
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• ከሕይወታችሁ ማመካኘትን አዉጡ (take blame out of


your life)
• አለማመካኘት ማለት ለምሳሌ ከታመማችሁ ችግሩ ወይም
ጥፋቱ የኔ ነዉ በሚል ጤናማ አመለካከት መቀበል ማለት ነዉ
• የገንዘብ ችግር ካለባችሁ ችግሩን የራስ አድርጎ የማየት
አካሄድ ነዉ
• የቤተሰብ ችግር ካለባችሁ፣ ጎረቤታችሁ ባይወዳችሁና
ሊያባርራችሁ እንኳ ቢፈልግ ወዘተ ችግሩ የኔ/የእኛ ነዉ ብሎ
እንደማየት ማለት ነዉ
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• በእርግጥ ችግር ፈጣሪዉ እናንተ ላትሆኑ ትችላላችሁ


• ችግሩ የናንተ ባይሆን እንኳ ችግሩን የራሳችሁ አድርጎ ማየቱ
ለጤንነታችሁ/መፍትሔ ለማምጣቱ ሂደት ጠቃሚ አካሄድ
ነዉ
• ወደዚህ (ችግሩ የኔ ነዉ ወደ ማለት) ደረጃ መድረስህ
በቀጣይነት ወደ ጤንነት እና ብልጽግና እንድትገባ ዕድሉን
ይሰጠሃል ማለት ነዉ
• በመንፈሳዊ ነገርህ ቱጃር/ሚልዬነር ያደርግሃል ማለት ነዉ
• እዉነተኛ ብልጽግና በመንፈስ ብልጽግና ይጀምራል
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• የደረሰብኝን ችግር ወይም ጉዳት ሰዎች እንዲያስወግዱልኝ


የምጠብቅ ከሆንኩ ግን ለዘላለምም ላያደርጉት ይችላሉ፤
ስለዚህ እኔ ሰበቡን/ብለሙን ወስጄ ባስተካክለዉ ይሻላል
ማለት ነዉ
• በዚህ አመለካከት ወደ ከፍተኛዉ ደረጃ ስትደርስ በጥላቻ
ምትክ ፍቅር መርጨት ትጀምራለህ
• በመንገድህ ምንም ቢመጣብህ በጥላቻ ወይም ሌሎችን
ምክንያት በማድረግ ፋንታ ሙሉ ሃላፊነቱን ራስህ ወስደህ
ወደ ፊት መቀጠል ትፈልጋለህ
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• ጥላችን መተዉ ማለት በምንም ሁኔታ ዉስጥ ከዉስጤ


ፍቅርን ብቻ ለማመንጨት የምሞክርበት ዓለም ማለት ነዉ
• ወደዚህ ደረጃ ስትደርስ ሕይወት ያላቸዉ ፍጥረታት በሙሉ
በዉስጥህ ጠላትነት እንደሌለ አረጋግጠዉ በሰላም አብረዉህ
ይኖራሉ
• ለጥላቻ ፍቅርን እንደ ምላሽ ለሚሰጡ ሰዎች ጽንፈ
ዓለሙም ሆነ ፍጥረት በሙሉ ወዳጃቸዉ ይሆናል
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• የቴዲ ስታለር ታሪክ…


• የተጫማደደ ሱሪ፣ ያልተበጠረ ጸጉር፣ ያልታጠበ
ፊት፣ ደብተሩን አንድም ቀን በንጽሕና የማይይዝ፣
አርፋጅ፣ ሞዛዛ ፊት ያለዉና ፈገግታም ሆነ ደስታ
የራቀዉ ምስኪን ተማሪ፤
• በጥቅሉ ማንም በቀላሉ ሊወድደዉ የማይችል
ዓይነት ልጅ ነበር ተዲ ስታለር
ተዲ ስታለር

• በአንደኛ ክፍል ካርዱ ላይ “ቴዲ በሥራዉና በባሕርዉ ጥሩ ተስፋ


የሚሰጡ ነገሮች ይታይበታል፤ ነገር ግን በቤቱ ድህነት አለ”
• በሁለተኛ ክፍል ካርዱ ላይ “ቴዲ የተሸለ መሥራት ይችላል፤ ነገር
ግን እናቱ በፀና ታማለችና ቤት ሲሄድ የሚረዳዉ የለም”
• በሦስተኛ ክፍል ካርዱ “ላይ ቴዲ ጥሩ ልጅ ነዉ፤ ፊቱ ግን ኮስታራ
ነዉ፤ ለመማር ይዘገያል፤ በዚህ ላይ እናቱ ዘንድሮ ሞታለች”
• በአራተኛ ክፍል ካርዱ ላይ “ቴዲ በጣም ዘገምተኛ ነዉ፤ ነገር ግን
ጸባዩ ጥሩ ነዉ፤ አባቱ ለትምህርቱ ምንም ትኩረት አያደርግም”
Paradigm shift (የልቦና ዉቅር ለዉጥ)

• አምስተኛ ክፍል ሲማር ታህሣስ የገና ስጦታ ለመምርሁ


ለሚስዝ ቶምፕሰን ይዞላት ሄደ
• የቴዲ ስጦታ በቡላ ወረቀት የስኮች ቴፕ ተለጣጥፎበት በላዩ
ላይ በቴዲ እጅ ጽሑፍ “ለሚስዝ ቶምፐሰን፤ ከቴዲ ስታለር”
የሚል ነበር
• ሚስዝ ቶምፕሰን የእሽጉን ወረቀቱን ቀድዳ ስጦታዉን
ስትመለከተዉ አንድ ግማሽ ብልቃጥ ርካሽ ሽቱና ጎዶሎ
ጬሌዎችን የያዘ አንድ የአንገት ጌጥ ተመለከተች
Paradigm shift (የልቦና ዉቅር ለዉጥ)

• ተማሪዎች ስጦታዉን ሲመለከቱ ሁሉም ቴዲን ሊያሳፍሩት


እየተሽኮረመሙ ሳቁበት
• መምህራቸዉ ግን ቶሎ ብላ ጬሌዉን በአንገቷ አጠለቀች፤
ሽቱዉንም በእጇና በደረቷ ረጭታ “እንዴት ያለ ደስ የሚል
ሽቱ! ሽታዉ ደስ አይልም? ጬሌዉስ አያምርብኝም?“ ብላ
ስትጠይቃዉ
• ልጆቹ ወዲያዉ ተለዉጠዉ “እዉነት ነዉ ቲቸር ደስ ይላል!
ለኔም! ለኔም!” እያሉ ሁሉም ከሽቱዉ እንድትረጭባቸዉ
ይጠይቋትና ይጋፉ ጀመር
Paradigm shift (የልቦና ዉቅር ለዉጥ)

• ያን ዕለት ከትምህርት ሰዓት በኋላ ሌሎች ተማሪ


ልጆች ወደቤታቸዉ ሲሄዱ ቴዲ ግን መምህሩን
ሚስዝ ቶምፕሰንን ተከትሎአት ወደ ቢሮዋ ሄደ።
ሚስዝ ቶምፕሰንንም “ቲቸር ዛሬ እናቴን መሰልሽኝ፤
ጠረንሽም እናቴን እናቴን ይሸታል፤ የእናቴ ጬሌም
አምሮብሻል። ለማንኛዉም ስጦታዬን ስለተቀበልሽኝ በጣም
አስ ብሎኛል” አላት
Paradigm shift (የልቦና ዉቅር ለዉጥ)

• ሚስዝ ቶምፕሰን ያን ሌሊት አልተኛችም፤ የቴዲ


ድምጽ በልቦናዋ እያንቃጨለ ዕረፍትና እንቅልፍ
ነሳት፤ ባሰበችዉ ቁጥረ አንጀቷ ተንሰፈሰፈ፣ ዓይኗ
ብዙ አነባ፤ ለቴዲ ነፍሷ አዘነ፤ ተከዘች፤ በፀፀትም
አለቀሰች
• በፈጣሪዋ ፊት ኃጢአቷን እየተናዘዘች ከልቧ ንሰሐ
ገባች። በእንብርክክም ሆና እግዚአብሔር ኃጢአቷ
ይቅር እንዲላት ተማጸነችዉ
Paradigm shift (የልቦና ዉቅር ለዉጥ)

• በነጋታዉ ሚስዝ ቶምፕሰን አዲስ ሰዉ ሆነች፤ መምህራቸዉ


ብቻ ሳትሆን፣ በተለይም ለቴዲ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ
ሆነችለት። ከዚያች ዕለት ጀምራ ተማሪዎቿን ማስተማር ብቻ
ሳይሆን ልታፈቅራቸዉና እናት ልትሆናቸዉ ቆረጠች። በዘመንዋ
ብቻ ሳይሆን እርሷም ካለፈች በኋላ ከእነርሱ ጋር የሚቆይ
ስጦታ ልትሰጣቸዉ አለመች። ለደካማ ተማሪዎች ሁሉ ልዩ
ዕርዳታ አደረገችላቸዉ፤ በተለይም ለቴዲ
• በዓመቱ መጨረሻ ቴዲ ያልተጠበቀ ማሻሻያ አሳየ፤ በክፍሉ
ተማሪዎችን በብዙ ነገሩ ደርሶ ያዛቸዉ፤ አንዳንዶችንም
በለጣቸዉ።
መስጠት የሚፈጥረዉ ተዓምር
• ቀጥሎ ባሉ ዓመታት ቴዲ የት እንደደረሰ ሚስዝ
ቶምፕሰን አላወቀችም፤ ምክንያቱም ትምህርቱን
ሊቀጥል ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ነበርና።
• ከዕለታት አንድ ቀን ሚስዝ ቶምፕሰን እንዲህ የሚል
ደብዳቤ ደረሳት፡- ከዉድ ሚስዝ ቶምፕሰን ይህን
የምነግርሽን ዜና ከሁሉ አስቀድመሽ አንቺ
እንድታዉቂ እፈልጋለሁ፤ እኔ በክፍሌ 2ኛ ወጥቼ
አልፌአለሁ። ዉድ ልጅሽ ቴዲ ስታለር።
መስጠት የሚፈጥረዉ ተዓምር
• ከአራት ዓመት በኋላ ሚስዝ ቶምፕሰን ሌላ ደብዳቤ
ደረሳት፤ እንዲህ የሚል፤ “ዉድ ሚስዝ ቶምፕሰን
በክፍሌ አንደኛ ወጥቼ እንደተመረቅሁ አስተማሪዎቼ አሁን
ነገሩኝ፤ ይህን ደግሞ ከሰዉ ሁሉ አስቀድመሽ አንቺ
እንድታዉቂ እፈልጋለሁ፤ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት
ቀላል አልነበረም፤ ነገር ግን ወድጀዋለሁ።” ቴዲ
ስታለር።
መስጠት የሚፈጥረዉ ተዓምር
• ከሌላ አራት ዓመት በኋላ አሁንም ሚስዝ ቶምፕሰን ሌላ
ደብዳቤ አገኘች፤ እንዲህ የሚል። ዉድ ምስዝ ቶምፕሰን
“ከዛሬ ጀምሮ ስሜ ዶክተር ቲዮዶር ስታለር ይባላል፤ ደስ አይልም?
ይህን ከሰዉ ሁሉ በፊት አንቺ እንዲታዉቂ ስለፈለግሁ አስቀድሜ
ጻፍኩልሽ፤ በሚቀጥለዉ ወር ላገባ ነዉ፤ ማለት በ27
እንቅጩን ማወቅ ከፈለግሽ። በሠርጌ ዕለት እናቴ በሕይወት
ብትኖር በምትቀመጥበት መጥተሽ እንድትቀመጪ
እፈልጋለሁ፤ አንቺ አሁን ያለሽን ብቸኛ ቤተሰቤ ነሽ፤ አባቴ
ባለፈዉ ዓመት ሞቷል።” ዉድ ልጅሽ ሚስዝ ቶምፕሰን።
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥዉስጥ ለመሆን በቂ
ምክንያት የለህም/አይኖርህም
• ሚስዝ ቶምፕሰን በቴዲ ሠርግ ተገኝታ በእናቱ ቦታ
ተቀመጠች፤ ይገባታል፤ ለቴዲ መቼም ቢሆን የማይረሳዉን
ዉድ ነገር ሰጥታዋለችና።
• እናም ቴዲ አመሰገናት፤ እዚህ እንድደርስ ምክንያት የሆንሽዉ
አንቺ ነሽና አመሰግንሻለሁ አላት፤ ሚስዝ ቶምፕሰንም
ማመስገን ያለብኝ እኔ እንጂ አንተ አይደለህም፤ ለሕይወቴ
ለዉጥ ምክንያቱ አንተ ነህና የሚል ምላሽ ሰጠች።
• በጥላች ምትክ ፍቅር ስንሰጥ ጽንፈ ዓለሙ የሚሰጠንን
ብልጽግና በዚህ ድንቅ ታሪክ ዉስጥ እንመለከታለን
3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ…

• በዉስጣችሁ እጅግ ድንቅ ሙዚቃ አለ


• ድንቅ ሙዚቃችሁን በዉስጣችሁ እንደያዛችሁ አትሙቱ!
ተጫወቱት!
• በጽንፈ ዓለሙ አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም፤
• ሁላችንም እዚህ የመጣነዉ በዓላማና በእግዚአብሔር ድንቅ
ዕቅድ ነዉ
• ብዙዎቻችን ግን በዉስጣችን ለምንሰማዉ ሙዚቃ
ማሸብሸብ/መሰለፍ ስለምንፈራ ሳንኖር እንዳንሞት
እፈራለሁ
ስቲቭ ሐርቬይ
• አባቴ የቀን ገቢዉ 5 ዶላር ነዉ፤ አምስት ልጆች ነበሩት፤
እኔ አምስተኛዉ ልጅ ነኝ፤ ከትምሀርት ቤት
ተባርርያለሁ፤ ሁለት ጊዜ ንብረቴን በሙሉ
አጥቻለሁ፤ ቤት አጥቼ በመኪናዬ ዉስጥ አድር
የነበረበት ጊዜም ነበር፤ ሥራ አጥነት ምን እንደሆነ
አዉቃለሁ፤ አሁን ሦስተኛ ትዳሬ ላይ ነኝ
• እግዚአብሔር ግን ነገሬን ለወጠዉ፤ አሁን
ተሳክቶልኛል፤ የልጅነት ሕልሜን እያየሁ ነዉ።
ትርጉም ያለዉም ኑሮ እኖራለሁ
ስቲቭ ሐርቬይ
• በልጅነቴ አንድ ሕልም ነበረኝ፤ በቴሌቪዥን ታዋቂ
ወይም የቴሌቪዥን ስታር መሆን፤ ኮሚዲያን ወይም
ሰዎችን የማሳቅና የማስደሰት ሥራ እንዲኖረኝም
እመኝ ነበር። እናም በትምህርት ቤት መምህራችን
አንድ ቀን የወደፊት ምኞታችሁን ጻፉ ስትለን እኔ
ይህን በቴለቪዥን ታዋቂ ኮከብ የመሆን ሕልሜን
በወረቀት ጽፌ ሰጠኋት። የክፍል መምህራችንም
ጽሑፌን አንብባ ስታበቃ ወደ ፊት ጠርታኝ በክፍሉ
ተማሪዎች ፊት አቆመችኝ
ስቲቭ ሐርቬይ
• እኔም ሕልሜን የወደደችና በተማሪዎች
ልታስጨበጭብልኝ ያቆመችኝ መስሎኝ በደስታ ወደ
ፊት ወጣሁና ቆምኩ። ሌላዉ የኔ ችግር ንግግር
የማልችል አፈ ትብ ልጅ መሆነ ነበር። ለካስ መምህሬ
ሕልሜን አልወደደችዉም፤ ይባስ ብላ ፈጽሞ
የሕልሜ ሰዉ ልሆን እንደምችል አላመነችኝም
ስቲቭ ሐርቬይ
• ከቤታችሁ ማን ቴሌቪዥን ላይ ታይቶ ያዉቃል? ብላ
ጠየቀችን፤ እኔም እየተንተባተብኩ ገና መልስ ልሰጣት
ስንተባተብ አከታትላ በቴሌቪዥን ታዋቂ ለመሆን ምን
እንደሚያስፈልግ ለመሆኑ ታዉቃለህ? አለችኝ፤ ለሁለተኛ
ጊዜ አ… አ… አ… አ… እያልኩ ገና መልሴን ልሰጣት
ስንተባተብ አቋርጣኝ ከናንተ ሰፈር ማን በቴሌቪዥን ታዋቂ
ሰዉ ወጥቶ ያዉቃል? አለችኝ
• አከታትላ ለጠየቀችኝ በርካታ ጥያቄዎች ለአንዱም ጥያቄ
እንኳ በአግባቡ መልስ ሳልሰጥ ጥያቄዎቿን ጨርሳ ወደ ራሷ
ድምዳሜ ደረሰች
ስቲቭ ሐርቬይ
• እርሱም “አንተ ንግግር እንኳ የማትችል ተብታባ መቼም
ቢሆን የቴሌቪዥን ኮከብ መሆን አትችልም!” የሚል ነበር
• በዚህ አነጋገሯ ሞራሌን ክሽሽ አድርጋ ሕልሜን መና
አድርጋ ወደ ወንበሬ መለሰችኝ
ስቲቭ ሐርቬይ
• ዛሬ ላይ ግን ታሪኬ ተቀይሮአል
• “የሚገርመዉ ነገር” አለ ስቲቭ “የሚገርመዉ እኔ
በየዓመቱ ለዚህች የቀድሞ መምህሬ ዓለም አቀፍ የኮሞዲ
ፕሮግራሞቼን በጥሩ ቴሌቪዥን እንድትከታተል ፍላት
ስክሪን ቴሌቪዥን በየዓመቱ እየገዛሁ እልክላታለሁ፤
ምክንያቱም ፕሮግራሜ እንዲያመልጣት አልፈልግምና”
ብሎአል
ስቲቭ ሐርቬይ
• መምህሬ ሞራሌን ብትሰብርም እግዚአብሔር ግን ፀሎቴን
ሰማኝ፤ ሕልሜን እዉን አደረገልኝ።
• “ሌላዉ” ይላል ስቲቭ ሐርቬይ “ሌላዉ ድህት እጅግ
አስመርሮኝ ስለነበር አንድ ትልቅ ፀሎት ፀለይኩ፤ እንዲህ
ብዬ፤ “ጌታ ሆይ ድህነት አስመርሮኛል፤ እባክህ ሀብታም
አድርገኝ፤ ሐብታም ብታደርገኝ በቴሌቪዥን መስኮት
ላገኘሁት ሰዉ ሁሉ አንተ ሀብታም እንዳደረግኸኝ
እናገራለሁ”
• እነሆ ዛሬ ሀብታም ሆኜ ድንቅ ሥራዉን እናገራለሁ። ታዲያ
ይህን የማደረገዉ በሰጠኝ ድንቅ ስጦታዬ (ኮሞዲ) ነዉ
ስቲቭ ሐርቬይ ይጠይቃል
• እናንተስ ትጸልያላችሁ? ፀሎታችሁ ምንድነዉ?
• ያዕቆብ በመልዕክቱ ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤
ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም
አትችሉም፤ ትጣላላችሁ፤ ትዋጉማላችሁ፤ ነገር ግን
አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም (ያዕ 4፥2)። እነዚህ ሰዎች
ሕልማቸዉን አላገኙም። ነገር ግን “ለምንድነዉ ያላገኙት?”
መልሱን በሚቀጥለዉ ቁጥር ታገኛላችሁ።
• 4፥3 ላይ “ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ
በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም” ይላል
4) ዝምታን ዕቀፍ /አሰላስል

• አራተኛዉ መርህ “ዝምታን ዕቀፍ” (Embrace silence or


meditate.) የሚል ነዉ
• በጽንፈ ዓለሙ የሁሉም ምንጭ የሆነ አንድ አምላክ ብቻ አለ
እርሱም እግዚአብሔር ነዉ
• ይህ ሁሉን የፈጠረዉ፣ ሁሉን የሚያንቀሳቅሰዉ ሁሉን
የሚያኖረዉ ሃይል አይቆረጥም፤ አይቆራረጥም፤
አይካፈልም፤ አይከፋፈልም፤ ፍጹም አንድ ነዉ
4) ዝምታን ዕቀፍ

• የሚታየዉ ዓለም ግን ተቆራርጦአል ተከፋፍሎአል፤ ለምሳሌ


ወንድና ሴት፣ ወፍራምና ቀጭን፣ አጭርና ረጅም ወዘተ
• ማግኔት ሁሉ ሁለት ዋልታ እንዳለዉ (ሰሜንና ደቡብ) ይህ
የሚታየዉ ዓለም ዳይኮቶሚ/ተጻራሪ ነዉ
• ዝምታን ማቀፍ (መዲቴሽን) ግን ይህን ዳይኮቶሚ
ያገናኝልናል። ሙዚቃን የሚፈጥረዉ በኖታዎች መካከል
የሚገኘዉ ፀጥታ ነዉ (It is the silence between the
notes which makes the music.) እንደሚሉት ነዉ
4) ዝምታን ዕቀፍ

• እነዚህ አሁን እኔ የማወራቸዉ ቃላት የሚወጡት ከዝምታ


ነዉ
• ወደ ዝምታ መግባት ማለት መከፈል ወደማትችለዉ
አንድነት (እንቲመሲ) መግባት ማለት ነዉ
• ከዚያ ዝምታ ነዉ እነዚህን ቃላት ይዘህ የምትመጣዉ።
መዲቴሽንን ስትለማመድ ወደ ምንጭህ ትደርሳለህ
• መዲቴሽን ከምንጭህ ጋር እንድትገናኛ ያደርግሃል፤ ወደ
መንፈሳዊ መነቃቃት እንኳ ለመድረስ በፀጥታ መዲቴት
ማድረግ እጅግ መሠረታዊ ነዉ
ሪቻርድ ወምብራንድ
• ከ14 ዓመት የእሥራት ዓመት 3ቱን በሶሊቶሪ ኮንፋይንመንት
• ድምጽና ብርሃን በሌለበት ግራጫ ቀለም ባለዉ እሥር ቤት
(የወታደሮች ጫማ እንኳ ሆን ተብሎ ከስፖንጅ የተሠራ)
• በዚያ ጨለማ በየሌሊቱ 304 የዝምታ ስብከቶችን ፀጥ ላለዉ
ጨለማ እሰብክ ነበር
• ከእሥር የተፈታሁ ዕለት 2ቱ ሲቀሩ ሁሉንም በወረቀት
አሰፈርኩ ብሎአል
5) ግለ ታሪክህን ተወዉ

• አምስተኛዉ መርህ “ግለ ታሪክህን መተዉ” ነዉ (giving up


your personal history).
• ካርሎስ ካስትኔዶ እንዳለዉ ግለ ታሪክ እንደማያስፈልገኝ
ገባኝ ወደ ማለት መድረስ አለብህ
• ልክ እንደመጠጥ ሱሰኛ/ጠጪ ሰዉ፣ መጠጡን እንደሚተወዉ
እኔም ግለ ታሪኬን መተዉ አለብኝ
• ግለ ታሪካችሁን ከጣላችሁ ከጫና ታመልጣላችሁ
• ግለታሪካችን ሁላችንም ተሸክመን የምንዞረዉ አንድ ያረጀ
ከረጢት/ኮሮጆ አድርጎ ማየት መልካም ነዉ
5) ግለ ታሪክህን መተዉ

• ግለ ታሪካችን/አሮጌዉ ከረጢት ያለፈዉ ሕይወታችን


(ታሪካችን) ነዉ
• እነዚህ ያለፉ ታሪኮቻችን ይዘዉናል/ተጣብቀዉብናል
• አንዳንዴ ቆም ብለን ከከረጢቱ እያወጣን ራሳችንን
የምንቀባዉና የምናበላሽበት ብዙ ነገሮች አሉን
• ያለፈዉን ታሪካችሁን ያዙትና ወርዉሩት (ከመወርወራችሁ
በፊት በደንብ መያዛችሁን አረጋግጡ)
• በባለፈዉ ቁስልና ሕመም ትዝታና ሰመመን ዛሬን አትኑሩ፤
እርሱ ዉሸት ነዉ፤ ያለፈ ታሪክ ነዉ፤ አይጠቅማችሁም
5) ግለ ታሪክህን መተዉ
• በኋላዬ ያለዉን እየረሳሁ በፊቴ ያለዉን ለመያዝ
እዘረጋለሁ (ፈል 3፥13) ይህ ስለገባዉ ነዉ
6) ችግርን በፈጠረዉ አዕምሮ በዚያዉ አዕምሮ
ችግሩን ልትፈቱት አትችሉም
• ስድስተኛዉ መርህ “ችግሩን በፈጠረዉ አዕምሮ ችግሩን ልትፈቱት
አትችሉም” ይላል (You can’t solve a problem with
the same mind that created it).
• በሕይወትህ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ በመጀመሪያ
ማድረግ ያለብህ አዕምሮህን/አስተሳሰብህን መለወጥ ነዉ
• እነዚህ ነገሮች የሚፈጠሩት በአዕምሮህ ነዉ ልታጠፋቸዉም
የምትችለዉ በአዕምሮህ ነዉ
• ከእዉነት ጋር ያለህን ስምምነት እንደገና አድርገዉ
እንደማለት ነዉ
እዉነት ምንድነዉ ?
• ዮሐ 18፡38 ጵላጦስ “እዉነት ምንድነዉ ?” አለዉ
• ይህንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ መጥቶ “እኔስ
አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም” አለ ይላል
• እዉነት አንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገዉን ለሌላዉ
ማድረግ ነዉ፤ አንተ እንዲደረግብህ የማትፈልገዉን
በሌላዉ አለማድረግ ነዉ
• በአጭሩ እዉነት ባልንጀራህን እንደራስህ መዉደድ ነዉ
6) ችግሩን በፈጠረዉ አዕምሮ…

• በዚህ ዓለም እጅግ ከምንቸገርባቸዉ ነገሮች አንዱ ተሳስተን


እንደነበር ማመን ነዉ (sorry seems to be the hardest
word)
• መሳሳታችንን ማመን ማለት በሕይወታችን ስንለማመድ
የቆየንባቸዉ ነገሮች እንደማይሠሩ አስተዉለን መቀየር
እንዳለብን መቀበል ማለት ነዉ፤ ይህን ለማድረግ ማወጅ
ወይም የግድ የበደለኝነት ስሜት ሊሰማን አይገባም
• ግንኙነትን ዘላቂ ለማድረግ በምንወደዉ ግለሰብ መጥፎ ነገሮች
ሳይሆን መልካም ነገሮች ላይ ትኩረታችንን ማድረግ ይኖርብናል
7) ራስህን መሆን ወደምትፈልገዉ እንደደረስህ አድርገህ
ተመልከት
• ሰባተኛዉ መርህ “ራስህን መሆን ወደምትፈልገዉ እንደደረስህ
አድርገህ ተመልከት” ይላል (treating yourself … as if you
already were… what you would like to become.)
• ሁሉም ይቻላል፤ ነገር ግን የሚያስከፍለዉ ዋጋ አለ
• በሀሳብህ ወደ ደረስህበት በእርግጥ በተግባርም ትደርሳለህ
• በምድርላይ መሆን የምትፈልገዉን እንዳትሆን የሚከለክልህ
አንድ ሰዉ ብቻ ነዉ (አንተ ራስህ!)
• በዚህ ዓለም ላይ ልታሻሽለዉ እንደምትችል እርግጠኛ
የሆንክበት አንድ ነገር ቢኖር ራስህን ነዉ (Aldous Huxley)
8) ለአምሳለ መለኮትነትህ ዋጋ መስጠት

• ስምንተኛዉ መርህ “ለአምሳለ መለኮትነትህ ዋጋ መስጠት” ነዉ


(treasuring your divine part taking) ከፈጣሪ ጋር
እንደተገናኘህ ማወቅ ነዉ (የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ)
• ፈጣሪ የሁሉንም ፀጉር ያበቅላል፤ የሁሉንም ልብ እንዲመታ
ያደርጋል፣ የሁሉንም አበቦች እንቡጥ ይከፍታል፤ ፍጥረት ሁሉ
ከእርሱ ተገናኝቶአል፤ በእርሱ ተደግፎአል
• ዳዊት በመዝ 104፡29 ፊትህን ስትሰዉር በድንጋጤ ይሞላሉ፤
እስትንፋሳቸዉንም ስትወስድባቸዉ ይሞታሉ፤ ወደ አፈራቸዉም
ይመለሳሉ፤ መንፈስህን ስትልክ እነርሱ ይፈጠራሉ፤ የምድርንም
ገጽ ታድሳለህ ይላል
8) ለአምሳለ መለኮትነትህ ዋጋ መስጠት

• ጳዉሎስም በሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ


ያለዉን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ ሰማይና የምድር ጌታ ነዉና
እጅ በሠራዉ መቅደስ አይኖርም፤ እርሱም ህይወትንና
እስትንፋስን ሁንም ለሁሉ ይሰጣልና… ይላል። ቁ 26 ላይ ወረድ
ብሎ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰዉን ወገኖች ሁሉ ከአንድ
ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ
መደበላቸዉ። ቢሆንም ከእያንዳንዳቸዉ የራቀ አይደለም።
ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች አግሞ እኛ ደግሞ ዘመዶቹ
ነንና ብለዉ እንደ ተናገሩ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤
እንኖርማለን ይላል
9) ከእግዚአብሔር ስትገናኝ ራስህን ማወቅ ትጀምራለህ

• ዘጠነኛዉ መርህ Self-discovery requires Divine


encounter. “ከእግዚአብሔር ስትገናኝ ራስህን ማወቅ
ትጀምራለህ” የሚል ነዉ
• የአንድ ነገር ዓላማዉ ከሠሪዉ ወይም ከፈጣሪዉ ተወስኖ
የመጣለት እንደመሆኑ ፍጥረት ፈጣሪዉን ሲያዉቅ ሁሉም
ነገር ትርጉም ይሰጣል
• ለሰዉ ልጅ በዚህ ምድር ላይ ትልቁ ክስተት ከፈጣሪዉ ጋር
መገናኘቱ ነዉ። ሙሴ ከእግዚአብሔር ሲገናኝ አምላኩን
አወቀ፤ ሥራዉን (የሕይወት ዘመን አሳይንመንቱን) አገኘ።
9) ከእግዚአብሔር ስትገናኝ ራስህን ማወቅ ትጀምራለህ

• ጳዉሎስ በደማስቆ መንገድ የገጠመዉ ከእግዚአብሔር ጋር


መገናኘት/ዲቫይን ኤንካዉንተር በሐዋ. ሥ 22፥13 ላይ
ይታያል
• እግዚአብሔር ሐናኒያን ልኮ “የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን
ታዉቅ ዘንድና ጸድቁን ታ ዘንድ፣ ከአፉም ድምጽ ትሰማ ዘንድ
አስቀድሞ መርጦሃል፤ ባየኸዉና በሰማኸዉ በሰዉ ሁሉ ፊት ምስክር
ትሆንለታለህና” አለዉ
• እዉነተኛ ማንነታችንን እስከምናዉቅ ድረስ መሆን ወደሚገባን
ሁኔታ መራመድ አንችልም (Charlotte P. Gilman)
10) ጥበብ የሚያደክማችሁን ሀሳብ ሁሉ መተዉ ማለት ነዉ

• ዘጠነኛዉ መርህ “ጥበብ ማለት የሚያደክማችሁን ሀሳብ ሁሉ መተዉ


ማለት መሆኑን ማወቅ” ነዉ (Wisdom is avoiding all
thoughts which weakens you). ሰሎሞን እጅግም
ምርምር ሰዉነትን ያደክማል ይላል
• ሐሳብ ሁሉ ሀይል አለዉ፤ ልክ እንደማንኛዉ በጽንፈ ዓለሙ
እንደሚገኝ ነገር ማለት ነዉ
• የምታፍሩ ከሆነ ሃፍረት የጥበብ ሃይላችሁን ይወስድባችኋል
• ፍርሃት፣ ሃፍረት ወዘተ ሀሳባችንን የሚቆጣጠሩ ከሆነ ጥበባችን
ይዳከማል ማለት ነዉ። ከሚያዳክማችሁ ከማንኛዉም ሀሳብ
ሰፈር ቶሎ ዉጡ
10) ጥበብ የሚያደክማችሁን ሀሳብ…

• እናንተ በሄዳችሁበት የምታገኙት የምትጠብቁትን ያንኑ ነዉ፤


ጉዳዩ የሚሆነዉ እንደአመለካከታችሁ ነዉ
• ሀሳባችሁን ስትለዉጡ ዓለማችሁን ትለዉጣላችሁ (when
you change the way you look at things the
things you look at change)
• እናንተን አሁን ባላችሁበት ቦታ ያስቀመጣችሁ እስካሁን
ያደረጋችኋቸዉ የምርጫችሁ ድምር ዉጤት ነዉ
እንደዚህ ማሰብ ስትጀምሩ ታሸንፋላችሁ!

• 1) ለሁሉም የተከፈተ ነገር ግን ከምንም ያልተጣበቀ


አዕምሮ ይኑርህ
• 2) የሌለህን ነገር መስጠት አትችልም
• 3) በማንኛዉም ዓይነት ጥላቻ ዉስጥ ለመሆን በቂ
ምክንያት የለህም/አይኖርህም
• 4) ዝምታን ዕቀፍ
• 5) ግለ ታሪክህን መተዉ
እንደዚህ ማሰብ ስትጀምሩ ታሸንፋላችሁ!

• 6) ችግሩን በፈጠረዉ አዕምሮ ችግሩን ልትፈቱት አትችሉም


• 7) ራስህን መሆን ወደምትፈልገዉ እንደደረስህ አድርገህ
ተመልከት/ቁጠር
• 8) ለመለኮታዊነትህን (በመልኩና በአምሳልህ ስለመፈጠርህ)
ዋጋ መስጠት
• 9) ከእግዚአብሔር ስትገናኝ ራስህን ማወቅ ትጀምራለህ
• 10) ጥበብ የሚያደክማችሁን ሀሳብ ሁሉ መተዉ ማለት ነዉ
እስከዚህ ከመጣን ከዚህ በኋላ ወዴት እንሂድ?

• Now that we’ve come this far, where do we go


from hear?
• እስከዚህ ድረስ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ከመጣን አሁን ከዚህ
በኋላ ወዴት እንሄዳለን?
• እኛ እየጨረስን ነዉ ብለን ስናስብ እርሱ ገና እየጀመረ ነዉ
• This is not the end. This is not the beginning of
the end. Yet it may be the end of the beginning
• ይህ መጨረሻዉ አይደለም፡፡ የመጨረሻዉ መጀመሪያም
አይደለም፤ ምናልባት ይህ የመጀመሪያዉ መጨረሻ ነዉ
የዉይይት ጥያቄዎች
1. ነጻ ሆናችሁ የትኛዉንም ሀሳብ ለመስማት ምን ያክል ነጻ
ናችሁ?
2. ምንድነዉ ያላችሁ? ያላችሁን እየሰጣችሁ ነዉ? የሌላችሁን
ለመስጠት ሞክራችሁ የተቸገራችሁበትን ጊዜ/ዘመን
ታስታዉሳላችሁ?
3. አሁን በልብህ የምትጠላዉ ሰዉ አለ? ካለ ከዚህ ትምህርት
በኋላ ምን ልታደርግ ወሰንህ?
4. የጽሞና ጊዜህ እንዴት ነዉ? የማሰላሰል ልምድህ ምን ያክል
የዳበረ ነዉ? ለማሰብ ጊዜ ሰጥተህ ታዉቃለህ?
የዉይይት ጥያቄዎች
5. ያለፈዉን ታሪክህን ዛሬን በሚጎዳ መልኩ አብዝተህ
ታስታዉሳለህ እንዴት መርሳት የምትችል ይመስልሃል
6. ችግር ለማቃለል አዳዲስ ሀሳብ የማፍለቅ ወይም ሌሎች
ያፈለቁትን ሀሳብ የመቀበል አዝማሚያህ ምን ይመስላል
7. የወደፊቱን ስታስብ ራስህን ምን ሆነህ ተመለከተዋለህ
8. እግዚአብሔር በአንተ ትልቅ ሥራ እየሠራ እንደሆነ
አዘዉትሮ ይሰማሃል የሕይወት ዘመን አሳይንመንትህ ግልጽ
ነዉ
የዉይይት ጥያቄዎች
9. ለየት ባለ መልኩ የገጠመህ ዲቫይን
ኤንካዉንተር/እግዚአብሔርን የተገናኘህበት
አጋጣሚ ታስታዉሳለህ
10.በአገልግሎትህም ሆነ በሕይወትህ የሚያበረታህ
ሳይሆን የሚያደክምህ ሐሳብ አለ ካለ ከዚህ ሐሳብ
መዉጣት የምትችልበት መንገድ ምንድነዉ
When you change the way you look at
things the things you look at change

You might also like