Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 92

የ ፍቃድ አሰጣጥና የህክምና ማስረጃ

አቀራረብ መመሪያ/የተሻሻለው

ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን


ህዳር /2013
ባህር ዳር
መግቢያ
 የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 265/2011
ሲቋቋም ሊያከናውናቸው የሚገቡ ተግባራትን መሰረት ያደረገ
ተግባርና ኃላፊነት ተላብሶ እንዲንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይቀጥላል…
 ስለሆነም በአዋጅ 253/2010 በሚተዳደሩ የመንግስት
መ/ቤቶችና የመንግስት ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ
የሚችሉ የተለያዩ ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን ማዘጋጀትና
ተግባራዊ ሲደረጉ የነበሩ መመሪያዎችን ማሻሻል በአዋጅ ቁጥር
253/2010 አንቀፅ 96 ን/አንቀፅ 2 በተሰጠው ስልጣን
መሰረት አዳዲስ መመሪያዎችን እያዘጋጀ ለመንግስት መ/ቤቶች
በማውረድ ተግባራዊነቱን በመከታተል በመደገፍ በርካታ
ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በተግባር ላይ ካሉት መመሪያዎች መካከል አንዱ
የአመት ዕረፍት ፍቃድ አሰጣጥ የህክምና ማስረጃ አቀራረብ
መመሪያ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ከአሁን በፊት ተግባራዊ ሲደረግ
የነበረው የአመት ዕረፍት ፍቃድ አሰጣጥ የህክምና ማስረጃ
አቀራረብ መመሪያ በአግባቡ
ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ለአፈፃፀም ግልፀኝነት
የጎደላቸውና መስተካካል ያለባቸው ጉዳዮች ያሉ
በመሆኑና የሰራተኞችን ተጠቃሚነት ይበልጥ
ያረጋገጠ መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ ይህ
መመሪያ ማሻሻያ ተደርጎበታል ፡፡
የመመሪያው ማሻሻል አስፈላጊነት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዋጅ
253/2010 በሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ
የሚሰሩ የመንግስት ሠራተኞች የተጣለባቸውን
ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና በስራ
የደከመ አእምሯቸው እንዲታደስ የአመት እረፍት
ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ
 የሕክምና ፈቃድ፣ የዓመት እረፍት ፈቃድና የልዩ ልዩ ፈቃዶች
አሰጣጥና ማስረጃ አቀራረብን ለተገልጋይ ተደራሽ ለማድረግ
በማስፈለጉ፣
 የመንግሥት ሠራተኞች ህመም በሚያጋጥማቸው ጊዜ
ከመንግሥስትና ከግል ጤና ተቋማት እንዲሁም ከውጭ ሐገር
የሚሰጥን የህክምና ማስረጃ ተቀባይነት ላይ የነበረው አሰራር
ያሉበትን ክፍተቶች መሙላት በማስፈለጉ፣
ዓላማ
 የመንግስት መ/ቤቶች የሰራተኞችን ልዩ ልዩ ፈቃድና በሚያቀርቡት
ማስረጃ መሰረት የህክምና ፈቃድ እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታ
ለመፍጠር ነው፡፡
 የአመት ዕረፍት ፍቃድ የሚጠቀመው የመንግስት ሰራተኛው ለተወሰነ
ጊዜ በማረፍ አገልግሎቱ በታደሰ መንፈስ እንዲቀጥል ለማስቻል ነው ፡፡
 የመንግስት ሰራተኞች ቀድመው ባስቀመጡት ፕሮግራም መሰረት
እረፍታቸውን እንዲጠቀሙ ለማስቻል ነው፡፡
ክፍል አንድ
1 ጠቅላላ
አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የፈቃድ አሰጣጥና የህክምና ማስረጃ አቀራረብ
መመሪያ ቁጥር 5 /2013” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
1.2 ትርጓሜ
 የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ
መመሪያ ውስጥ፣
1.2.1 “የመንግስት መ/ቤት” ማለት ራሱን ችሎ በአዋጅ ወይም
በደንብ የተቋቋመና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመንግስት
በጀት የሚተዳደር መስሪያ ቤት ነው፣
1.2.2 “ኮሚሽን” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፣
1.2.3 “የመንግስት ሠራተኛ” ማለት በመንግስት
መ/ቤት ውስጥ በቋሚነት/በጊዚያዊነት ተቀጥሮ
የሚሠራ ሰው ነው፣
1.2.4 “የዓመት እረፍት ፈቃድ” ማለት አንድ
የመንግሥት ሠራተኛ በስራ ወቅት የደከመ
አዕምሮውን ለማደስ እንደ አገልግሎቱ መጠን
የሚሰጠው የዓመት እረፍት ፈቃድ ነው፡፡
1.2.5 “ የበጀት ዘመን” ማለት ከሐምሌ 1 ቀን
ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ሰኔ 3ዐ ቀን ድረስ ያለውን
የሥራ ዘመን የሚያመለከት ነው፡፡
1.2.6 “የአገልግሎት ዘመን” ማለት አንድ
የመንግሥት ሠራተኛ ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ
አገልግሎት መስጠት እስከሚያቋርጥበት ቀን
ድረስ ያለውን የአገልግሎት ጊዜ ነው፡፡
1.2.7 “የአገልግሎት ዘመን መቋረጥ” ማለት የመንግሥት
ሠራተኛው አገልግሎት በጡረታ፣ በራስ ፈቃድ፣ በህመም፣
በችሎታ ማነስ፣ በእስራት ፣ በቅነሣ ፣ በሞት ምክንያት ስራን
ማቋረጥ ነው፡፡
1.2.8 “በራስ ፈቃድ የአገልግሎት ዘመን መቋረጥ” ማለት
ሠራተኛው ከሚሠራበት መ/ቤት መልቀቂያ ጠይቆ
መልቀቂያ የወሰደ ወይም በስራ ገበታው ላይ ባለመገኘቱ
በጥሪ ማስታወቂያ እንዲሰናበት የተደረገ ሰው ነው፡፡
1.2.8 “ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት” ማለት በህመም፣
በእሥራት፣ ወይም በሌላ ምክንያት መደበኛ ሥራን
ለማከናወን አለመቻል ነው፡፡
1.2.9 “የህክምና ማስረጃ’’ ማለት በሀገር ውስጥና ከውጪ
ሀገር ህጋዊ ፈቃድ ከተሰጠው የህክምና ተቋም የሚሠጥ
የህክምና የምስክር ወረቀት ነው።
1.2.10 “የመንግሥት የጤና ተቋም” ማለት ሙሉ በሙሉ ወይም
በከፊል በመንግሥት በጀት የሚተዳደር የጤና አገልግሎት መስጫ
ተቋም ነው፡፡
1.2.11 “የሕክምና ቦርድ ማስረጃ ” ማለት ታካሚዎች
በሪፈራል/ስፔሻላይዝድ/ ወደ መንግስት ሆስፒታሎች
ተልከው ከታከሙ በኋላ በህክምና ቦርድ በሦስት
ሀኪሞች ፊርማ ተደግፎ የሚሰጥ ማስረጃ ነው፡፡
1.2.12 “የሕመም ፈቃድ” ማለት አግባብ ካለው የጤና
ተቋም ተኝቶ ወይም በተመላላሽ ለመታከምና
ለማገገም እንደበሽታው ሁኔታ የሚሰጥ የህመም ፈቃድ
ነው፡፡
1.2.13 “የግል የጤና ተቋም” ማለት ከጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር ወይም ከክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ በተሰጠ
ፈቃድ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ የጤና ድርጅት
ነው፡፡
1.2.14 “የአሳካሚ የህመም ፈቃድ“ ማለት አንድ
ሴት የመንግሥት ሠራተኛ አንድ ዓመት ያልሞላው
ጨቅላ ህፃን ሲታመምባት ማስረጃ የሚቀርብበት
የአሳካሚ ፈቃድ ነው፡፡
1.2.15 “የዓመት እረፍት ፈቃድ ማዛወር” ማለት
በመንግስት መ/ቤቶች የስራ ጫና
ምክንያት/ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም/
የነበረውን የዓመት እረፍት ፈቃድ ወደ ቀጣዩ
በጀት ዓመት ማዛወር ነው፡፡
1.3 ማንኛውም በወንድ ፃታ የተገለፀው የሴት
ፆታንም ያካትታል፡፡
1.4 የመመሪያው ተፈጻሚነት ወሰን፡- ይህ መመሪያ
ተፈፃሚነት የሚኖረው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 በሚተዳደሩ
መ/ቤቶችና ሰራተኞች ላይ ነው፡፡
ክፍል ሁለት
 2 የዓመት እረፍት ፈቃድ አጠቃቀም

2.1 የዓመት እረፍት ፈቃድ ቀናት


2.1.1 ማንኛውም አዲስ ተቀጣሪ የመንግሥት
ሠራተኛ የአስራ አንድ ወራት አገልግሎት ከመስጠቱ
በፊት የዓመት እረፍት ፈቃድ የማግኘት መብት
የለውም፡፡
2.1.2 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 የተገለጸዉ ቢኖርም
በአንድ የሲቪል ሰርቪስ ተቋም ከአንድ አመት በላይ
አገልግሎ እንደ አዲስ ወደ ሌላ የሲቪል ሰርቪስ ተቋም
የተቀጠረ እና ያልተጠቀመበትን ህጋዊ የአመት እረፍት
ፈቃድ ከነበረበት መስሪያ ቤት ያቀረበ ሠራተኛ አዲስ
በተቀጠረበት መስሪያ ቤት የ11 ወር ቆይታ ሳይጠበቅበት
የሙከራ ጊዜውን እንዳጠናቀቀ ከመቀጠሩ በፊት የነበረውን
የመጨረሻ የአንድ አመት ፈቃድ ብቻ መጠቀም ይችላል::
2.1.3 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.1.1 የተገለፀው እንደተጠበቀ
ሆኖ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ አሥራ አንድ ወሩን
ካጠናቀቀ በኋላ በተቀጠረበት በጀት ዓመት ለሰጠው
አገልግሎት የዓመት እረፍት ፈቃዱ በአገልግሎቱ መጠን
ተሰልቶ እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
2.1.4 አንድ አመት ያገለገለ የመንግስት ሠራተኛ 20 የስራ
ቀናት የአመት እረፍት ፈቃድ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ
ያገለገለ ሠራተኛ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት አንድ የሥራ
ቀን እየታከለበት የዓመት እረፍት ፈቃድ ያገኛል ፡፡
 ሆኖም ለአንድ የበጀት ዓመት የሚሰጠው የዓመት ዕረፍት
ፈቃድ በጠቅላላው ከ30 የሥራ ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡

2.1.5 ከላይ በንኡስ አንቀፅ 2.1.4 የተገለፀው


ቢኖርም አንድ የመንግስት ሠራተኛ የተዛወረ
(የተጠራቀመ) የአመት እረፍት ፈቃድ ካለው በአንድ
የበጀት አመት ከ30 ቀን በላይ መጠቀም ይችላል፡፡
2.1.6 አንድ ጊዜያዊ ሠራተኛ ለቋሚ የመንግሥት
ሠራተኛ የተፈቀደውን የዓመት እረፍት ፈቃድ
የማግኘት መብት አለው፡፡
2.2 ስለ ዓመት እረፍት ፈቃድ አጠያየቅ፣
2.2.1 ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የዓመት
እረፍት ፈቃድ የመጠየቅ እና የመውሰድ መብት
አለው፡፡
2.2.2 የመንግሥት ሠራተኛው የዓመት እረፍት የመጠየቅ እና
የመውሰድ መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ ውስጥ
የዓመት እረፍት ፈቃዱን የሚጠቀምበትን ጊዜ አስቀድሞ
ማሣወቅ አለበት፡፡
2.2.3 የዓመት እረፍት ፈቃድ መጠቀሚያውን
በቅድሚያ ያላሣወቀ ወይም ፕሮግራም ያላስያዘ
የመንግሥት ሠራተኛ ፈቃድ በሚጠይቅበት ጊዜ
ከስራው አኳያ ታይቶ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ሆኖም
ፈቃዱን በጠየቀበት ጊዜ አጣዳፊ ሥራ ካለ መ/ቤቱ
ፈቃዱን ለመስጠት አይገደድም፡፡
2.2.4 በመ/ቤቱ ስራ ጫና ምክንያት ወይም
በሰራተኛው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካልሆነ
በስተቀር የመንግሥት ሠራተኛ በበጀት ዓመቱ
ባሳወቀው የዓመት እረፍት ፕሮግራም መሰረት
እረፍቱን የመውሰድ ግዴታ አለበት ፡፡ እንዲሁም ወደ
ሚቀጠለው በጀት ዓመት ሊዛወርለት አይችልም ፡፡
2.3 የዓመት እረፍት ፈቃድ አሰጣጥ፣
2.3.1 የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት/ ቡድን
በየበጀት አመቱ መጀመሪያ እስከ ሐምሌ 30 ቀን
ባለው ጊዜ የመንግሥት ሠራተኛው የዓመት እረፍት
ፈቃዱን የሚጠቀምበት ፕሮግራም መሙያ ቅጽ
ለኃላፊ ወይም ም/ኃላፊ/ ለእያንዳንዱ
ዳይሬክቶሬት/ቡድን በመላክ ተሞልቶ እንዲላክለት
ያደርጋል ፡፡
 2.3.2 ተጠሪነታቸዉ ለመ/ቤት ኃላፊ ወይም ም/ኃላፊ
የሆኑ ሠራተኞች በኃላፊያቸዉ/ ም/ኃላፊያቸው/በተወካይ
ኃላፊያቸው አማካኝነት፣ በዳይሬክቶሬት/በቡድን የታቀፉ
ሠራተኞች ደግሞ በዳይሬክተራቸው/ቡድን መሪያቸው
አማካኝነት ሠራተኞች የዓመት እረፍት ፈቃዳቸውን
የሚጠቀሙበትን ጊዜ እንዲሞሉ በማድረግ ስምምነት
ላይ የደረሱበትን አማራጭ ከሠራተኞቻቸው ጋር
በመፈራረም መረጃውን የሰው ሀብት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት/ ቡድን እስከ ሐምሌ 30 ድረስ
እንዲደርስ ያደርጋሉ ፡፡
2.3.3 ሠራተኞች ባቀረቡት ፕሮግራም መሠረት የዓመት
እረፍት ፈቃድ ጥያቄያቸውን ማቅረብና መጠቀም ቢችሉም
አስቀድመው ያሳወቁትን ፕሮግራም ከአቅም በላይ በሆነ ችግር
ምክንያት መለወጥ ቢፈልጉ ተጠሪነታቸዉ ለመ/ቤት
ኃላፊ/ም/ኃላፊ የሆኑ ሠራተኞች ከኃላፊያቸዉ/ተወካይ
ኃላፊያቸዉ፣ በዳይሬክቶሬት/በቡድን የታቀፉ ሠራተኞች
ደግሞ ከዳይሬክተራቸው/ቡድን መሪያቸው ጋር በመስማማት
የበጀት አመቱ ሳይቀየር የዓመት እረፍት ፈቃድ መውጫ
ጊዜያቸውን ሊቀይሩ ወይም ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡
2.3.4 አስገዳጅ በሆነ ምክንያት የአንድ በጀት አመት ወደ
ሁለተኛው ፣ የሁለተኛው በጀት ዓመት ፈቃድ ወደ ሶስተኛው
ዓመት የተላለፈለት ሰራተኛ እየሰራበት ያለውን የበጀት
ዓመት ጨምሮ የሁለት/የሶስት ተከታታይ ዓመታት ፈቃዱን
በአንድ ዓመት ውስጥ በፕሮግራም የመጠቀም መብት አለው፡፡
ሆኖም ከሦስቱ አመት የመጀመሪያውን ዓመት(ወደ 4ኛው
በጀት ዓመት የማይዛወረውን) የአመት እረፍት ፈቃድ
መጠቀም የሚችለው በመጨረሻው በጀት ዓመት እስከ ሰኔ
30 ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡
2.3.5 በመንግሥት መ/ቤት ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት
ሠራተኞች የዓመት እረፍት ፈቃዳቸውን በፕሮግራም
መጠቀም አለባቸው፡፡

2.3.6 ሠራተኛው ፈቃዱን በሚወስድበት ጊዜ በእረፍት ላይ


የሚቆይበትን የወር ደመወዝ በቅድሚያ ሊወስድ ይችላል፡፡

2.3.7 የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ፈቃድ ወስዶ


አገልግሎቱን በገዛ ፈቃዱ ያቋረጠ የመንግሥት ሠራተኛ
አገልግሎት ያልሰጠበት ጊዜ ታስቦ በፈቃድ ላይ እያለ
የተከፈለውን ደመወዝ እንዲመልስ ይደረጋል፡፡
2.3.8 ተሿሚዎች ከኃላፊነት ተነስተዉ
የመንግስት ሠራተኛ ሆነዉ ከተመደቡበት ጊዜ
ጀምሮ የአመት እረፍት ፈቃድ የማግኘት መብት
አላቸዉ፡፡ የአመት እረፍት ፍቃድ አሰጣጡም
በበጀት አመቱ የሚያገለግሉበትን ጊዜ ያህል ታስቦ
ይሆናል፡፡
2.4 የዓመት እረፍት ፈቃድን ወደ ሚቀጥለው በጀት
ዓመት ስለማዛወር፣
2.4.1 የዓመት እረፍት ፈቃድ ወደ ሚቀጥለው በጀት
ዓመት የሚዘዋወረው ሠራተኛው የዓመት እረፍት
ፈቃዱን በሥራ ጫና ምክንያት መጠቀም ባለመቻሉ
ተጠሪነታቸዉ ለመ/ቤት ኃላፊ የሆኑ ሠራተኞች
የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ምክትል ኃላፊ
በዳይሬክቶሬት/በቡድን ለታቀፉ ሠራተኞች
በዳይሬክተሩ/ቡድን መሪው ዝውውሩ ሲፈቀድ ብቻ
ነው፡፡
2.4.2 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.4.1 የተገለጸዉ
ቢኖርም ተጠሪነታቸዉ ለመ/ቤት ኃላፊ የሆኑም ሆነ
በዳይሬክቶሬት/በቡድን ለታቀፉ ሠራተኞች የሁለት
በጀት ዓመት ሙሉ ፈቃድ ወደ ሦስተኛ በጀት ዓመት
የሚዛወር የአመት እረፍት ፈቃድ ሲኖራቸዉ የዓመት
እረፍት ፈቃድ ዝዉዉሩ የሚተላለፈው የመ/ቤቱ
ኃላፊ /ተወካይ ሲያፀድቀው ይሆናል፡፡
2.4.3 የዓመት እረፍት ፈቃዱ ጥያቄ ወደ ሁለተኛ
በጀት አመት ሲዛወር ሠራተኛው በሞላው ቅፅ
መሠረት ተጠሪነታቸዉ ለመ/ቤት ኃላፊ የሆኑ
ሠራተኞች የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ምክትል
ሀላፊ ዳይሬክቶሬት/ቡድን ለታቀፉ ሠራተኞች
በዳይሬክተሩ/በቡድን መሪው ውሣኔ ፕሮቶኮል ይዞ
ከሠራተኛው የግል ማህደር ጋር መያያዝ አለበት፡፡
2.4.4 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 2.4.3 የተገለጸዉ ቢኖርም ወደ
ሦስተኛ በጀት አመት ሲዘዋወር ሠራተኛው በሞላው ቅፅ
መሠረት የመ/ቤቱ ኃላፊ ውሣኔ በፕሮቶኮል ይዞ ከሠራተኛው
የግል ማህደር ጋር መያያዝ አለበት፡፡
2.4.5 የመንግሥት ሠራተኛው የዓመት እረፍት ፈቃዱን
ለመጠቀም የሥራው ሁኔታ ቢከለክለውም ከ3ኛው በጀት
ዓመት በኋላ የሚደረግ ዝውውር ተቀባይነት የለውም፤ ወይም
ሠራተኛው ይዛወርልኝ ብሎ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፡፡
ክፍል ሦስት

3 የዓመት እረፍት ፈቃድን በገንዘብ ስለመቀየር

3.1 በሥራ ላይ ያሉ ወይም መ/ቤቱን የሚለቁ የመንግሥት

ሠራተኞች የዓመት እረፍት ፈቃድ በገንዘብ ስለሚቀየርበት ሁኔታ፣

3.1.1 የመንግሥት ሠራተኛው ወደ ሶስተኛው በጀት ዓመት

የተላለፈውን ሙሉ የዓመት እረፍት ፈቃድ ከጠየቀ የበጀት ዓመቱንና

አስቀድሞ የተላለፈለትን የዓመት እረፍት ፈቃድ በበጀት ዓመቱ

በሚያሲዘው ፕሮግራም መሠረት ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀም

ይደረጋል፡፡
3.1.2 ከላይ በተራ ቁጥር 3.1.1 የተጠቀሰው ቢኖርም በዚህ
መመሪያ ክፍል ሁለት አንቀጽ 2.4 ንዑስ አንቀጽ 2.4.2
መሠረት ወደ 3ኛ በጀት ዓመት የተዛወረውን የአንድ ዓመት
እረፍት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ በገንዘብ ተለውጦ እንዲሰጠው
የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን አሰሪው መ/ቤቱም
የሠራተኛውን የዓመት እረፍት ፈቃድ ጥያቄውን ተቀብሎ
ማስተናገድ ይኖርበታል፡፡
በስራ ጫና ምክንያትም ወደ 3ኛው የበጀት ዓመት
የተዛወረውን የአንድ ዓመት የዓመት እረፍት
ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ የሚሰጠው ይሆናል ፡፡
ሆኖም ግን ከስራ ጫና ውጭ ወደ 3ኛው የበጀት
ዓመቱ የተዛወረ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወደ
ገንዘብ ተቀይሮ እንዲሰጥ አይደረግም፡፡
 
3.1.3 አገልግሎቱ የተቋረጠ የመንግስት ሠራተኛ የዓመት
እረፍት ፈቃዱ ለአንድ ወይም ለሁለት ተከታታይ የበጀት ዓመት
በመንግሥት ሥራ ምክንያት በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወደ
ሁለተኛው ወይም ሶስተኛ የበጀት ዓመት የተላለፈ ከሆነ
የዓመት እረፍት ፈቃዱ ሙሉ በሙሉ በገንዘብ ተቀይሮ ለራሱ
ወይም ለተተኪዎች እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ሥራውን በገዛ
ፈቃዱ ለቆ ወደ ሌላ የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት የተቀጠረ
ሠራተኛ
ከሆነ ግን ፈቃዱን በገንዘብ ተቀይሮ የሚሰጠው የዓመት እረፍት ፈቃድ

አይኖርም፡፡ ነገር ግን ወደ ሌላ የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት የማይቀጠር

ከሆነ ያልተጠቀመበት ዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ይሰጠዋል፡፡

3.1.4 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3.1.3 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ

ሠራተኛው በዝውውር ወይም በምደባ ወይም በድልድል ወይም

በደረጃ እድገት ይሰራበት የነበረውን መ/ቤት ለቆ ወደ ሌላ መ/ቤት

የሚዛወር ወይም የሚመደብ ወይም የሚያድግ ከሆነ ሠራተኛው ወደ


ተዛወረበት ወይም ወደ ተመደበበት ወይም ወደ አደገበት
ያልተጠቀመበትን የዓመት እረፍት ፈቃድ
ከማስተላለፍ ባሻገር የዓመት እረፍት ፈቃዱ በገንዘብ
የሚቀየርበት አግባብ አይኖርም፡፡
3.1.5 ከላይ በንዑስ አንቀጽ 3.1.4 የተገለፀው እንደተጠበቀ
ሆኖ ሠራተኛው የሞላው የፈቃድ ፕሮግራም ሳይደርስ ወይም
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት አሳልፎት እያለ ስራው ከተቋረጠ
በበጀት ዓመቱ ውስጥ የሰራበት ጊዜ ታስቦ በገንዘብ ተቀይሮ
ይሰጠዋል፡፡
 ነገር ግን ሠራተኛው በራሱ ፈቃድ መልቀቂያ ጠይቆ
በሌላ የሲቪል ሰርቪስ ተቋም የሚቀጠር ከሆነ
በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ውሳኔ የአመት እረፍት
ፈቃዱ ወደ ሚቀጥለው በጀት ዓመት የተዛወረ
ስለመሆኑ በክሊራንሱ ላይ መገለፅ ይኖርበታል፡፡
3.1.6 አገልግሎቱ የተቋረጠ የመንግስት ሰራተኛ
የዓመት እረፍት ፈቃዱ ወደ ገንዘብ ሲቀየር
ለሠራተኛው የሚከፈለው ያልተጣራ የወር ደመወዙ
በ30 ቀኖች በማካፈል ሰራተኛው ባለው የዓመት
እረፍት በስራ ቀኖች ብቻ ተባዝቶ የሚገኘው ገንዘብ
ነው፡፡
3.1.7 የአንድ የዓመት ዕረፍት ፈቃዱ ወደ ሦስተኛው
በጀት ዓመት የተዛወረለት በስራ ላይ ያለ መንግሥት
ሠራተኛ ፈቃዱ በገንዘብ ሲለወጥ ወደ የ3ኛው
በጀት ዓመት የአንድ
ዓመት እረፍት ቀናቱ ብቻ ያልተጣራ የወር ደመወዙ
በ30 ቀኖች በማካፈል ሰራተኛው ባለው የዓመት
እረፍት በስራ ቀኖች ብቻ ተባዝቶ የሚገኘው ገንዘብ
ነው፡፡
3.2 በሞት ስለሚለይ የመንግሥት ሠራተኛ የዓመት
እረፍት ፈቃድ እና የ3ኛ ወገኖች መብት፣
3.2.1 የመንግሥት ሠራተኛው በሞት ሲለይ በህጋዊ
መንገድ እየተዛወረለት ያልወሰደው የዓመት እረፍት
ፈቃድ እና በሞት በተለየበት አመት ያልወሰደው
የአመት እረፍት በሞት እስከተለየበት ድረስ ያለው
ታስቦ በሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት/
ቡድን እየተረጋገጠ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ
ገንዘብ ተቀይሮ በህይወት ሳለ በጽሁፍ ላሳወቃቸው
የትዳር ጓደኛው ወይም በስሩ ይተዳደሩ ለነበሩ
ቤተሰቦቹ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ሆኖም በጽሁፍ
ያሳወቃቸው በሌሉበት ሁኔታ ለህጋዊ ወራሾች
እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡
3.2.2 በሞት የተለየ የመንግሥት ሠራተኛ በዓመት
እረፍት ላይ የነበረ ከሆነ እና የዓመት እረፍት ሲወጣ
በቅድሚያ የወሰደው የወር ደመወዝ ካለ ለቤተሰቦቹ
ከሚከፈል የ3 ወር ደመወዝ ላይ እንዲመለስ
አይጠየቅም፡፡
3.3 ሌሎች ፈቃዶች
3.3.1 የወሊድ ፈቃድ
ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፣
ሀ) ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ
ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት
ፈቃድ ይሰጣታል፤
ለ) ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ
ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ
ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ
እወልዳለሁ ብላ
ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ
ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90
ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት
ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ
የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች
ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ
እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ
ያልወለደች እንደሆነ እስከ ምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት
የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ
ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት
ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት
ፈቃዷ ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን
የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ
የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በአዋጅ ቁጥር
253/2010 አንቀጽ 42(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም
ፈቃድ መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት
ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ
የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ
ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ
ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ
አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ
ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ

ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት


ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን
ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር
ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ
ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
11. ወልዳ የተቀጠረች የመንግስት ሠራተኛ ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ
ከህክምና ተቋም መቸ እንደወለደች የሚገልጽ ማስረጃ እስከቻለች ድረስ
ከተቀጠረች በኃላ ያላት ቀሪ የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡ ሆኖም ግን
የቅድመ ወሊድ ፈቃድ አይሰጥም ፡፡ በዚህ ምክንያት የሙከራ ጊዜ ሥራ
አፈፃፀማቸው የወሊድ እረፍታቸውን ጨርሰው ከመጡ በኃላ የሙከራ
ቅጥሩ የስራ አፈፃፀም ውጤት እንዲሞላ ይደረጋል፡፡
12. ማንኛዋም ሴት የመንግስት ሠራተኛ አንድ ዓመት ያልሞላውን ሕፃን
ልጇን ለማሳከም በህክምና ለተረጋገጠ ጊዜ ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ
ይሰጣታል
3.3.3. የጋብቻ ፈቃድ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ሲያገባ 3 የሥራ ቀናት የጋብቻ ፈቃድ
ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
2. ማንኛውም የጊዜያዊ ሠራተኛ ሲያገባ ለቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ
የተሰጠው መብት ይኖረዋል፡፡
3.3.4. የሐዘን ፈቃድ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛ፣ተወላጅ፣ ወላጅ ወይም
እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚቆጠር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ የሞተበት
እንደሆነ ደመወዝ የሚከፈልበት 3 ተከታታይ ቀናት የሐዘን ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡
2. ሠራተኛው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ ከተመለከቱት ውጭ
የቅርብ ዘመድ ወይም ወዳጅ የሞተበት እንደሆነ ደመወዝ
የሚከፈልበት የአንድ ቀን የሐዘን ፈቃድ ይሠጠዋል። ሆኖም በዚህ
ምክንያት የሚሠጥ የሐዘን ፈቃድ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ከ6
ቀናት መብለጥ የለበትም።
3. ማንኛውም የጊዜያዊ ሠራተኛ የትዳር ጓደኛ፣ተወላጅ፣ ወላጅ
ወይም እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚቆጠር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመድ
የሞተበት እንደሆነ ለቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ የተሰጠው መብት
ይኖረዋል፡፡
3.3.5 ከደመወዝ ጋር ስለሚሰጥ ልዩ ፈቃድ
ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ፡-
ሀ/ ከፍርድ ቤት ወይም ከሌሎች በህግ ስልጣን ከተሰጣቸው
አካላት መጥሪያ ሲደርሰው የተጠራበት ጉዳይ ለሚጠይቀው
ጊዜና
ለ/ በሕዝብ ምርጫ ስልጣን የሚይዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን
ለመምረጥ ሲሆን ምርጫው ለሚወስድበት ጊዜ ከደመወዝ ጋር
ልዩ ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
ሐ/ የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ በሕዝብ
ምርጫ ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድበት
ወቅት እና ምርጫው በሚከናወንበት ጊዜ ከደመወዝ ጋር ፈቃድ
እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡
መ/ ማንኛውም ጊዜያዊ ሠራተኛ ለቋሚ የመንግሥት ሠራተኛ
የሚሰጠው ልዩ ፈቃድ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡
ክፍል አራት
 የህክምና ፈቃድ ማስረጃ አሰጣጥና አቀራረብ
4.1 የሕመም ፈቃድ መስጠት የሚችሉ የጤና ተቋማት፡-
4.1.1 የመንግሥት ጤና ኬላዎች/ክሊኒኮች/ በክልል ደረጃ ያለው
የፖሊስ ክሊኒክ፡-
በተቋማቸው ለታየ ታካሚ ቢበዛ እስከ 3 ቀናት ፈቃድ ሊሰጡ
ይችላሉ፡፡ ህመምተኛው ካልተሻለውና ተጨማሪ የህመም ፈቃድ
ማስረጃ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከበቂ ማብራሪያ ጋር 3
ቀናት ተጨማሪ ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
4.1.2 ጤና ጣቢያዎች/ የቤተሰብ መምሪያ
ክሊኒኮች/ሜሪስቶፕስ፡-
 የህክምና አገልግሎት ለተሰጠው ታካሚ የህመም ፈቃድ
መስጠት ካስፈለገ ቢበዛ እስከ 1ዐ ቀናት የሚደርስ ፈቃድ
ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ህመምተኛው ካልተሻለውና ተጨማሪ
የህመም ፈቃድ ማስረጃ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከበቂ
ማብራሪያ ጋር ለተከታታይ 5 ቀናት ፈቃድ በመጨመር
በድምሩ የ15 ቀናት ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ይሁን እንጅ፡-
 በጤና ጣቢያው የሚሰጠው የሕመም ፈቃድ በጤና መኮንን ቢ.ኤስ.ሲ
ነርስ ወይም ሃኪም ባለበትና ክትትል ባደረገበት ሁኔታ ሊሆን ይገባል፡፡
ለ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4.1.2 /ሀ የተጠቀሱ ባለሙያዎች
በሌሉበት ተቋም የሕመም ፈቃዱ በነርስ ሊሰጥ ይችላል፡፡
4.1.3 የግል መለስተኛ ክሊኒኮች፡-
በተቋማቸው ለታዬ ታካሚ ቢበዛ የሶስት ቀናት ፈቃድ መስጠት የሚችሉ
ሲሆን ለታካሚው ተጨማሪ ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌላ
ተጨማሪ ሦስት ቀናት መስጠት ይችላሉ፣
4 1.4 የግል መካከለኛ ክሊኒኮች፡-
የህክምና አገልግሎት ለተሰጠው ታካሚ የህክምና ፈቃድ
መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እስከ 5 ቀናት የሚደርስ የህመም
ፈቃድ ሊሰጡ የሚችሉ ሲሆን ታካሚው ሊሻለው ካልቻለና
ተጨማሪ ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከበቂ
ማብራሪያ ጋር ሌላ 3 ቀናት በማከል በድምሩ እስከ 8 ቀናት
ድረስ መስጠት ይችላሉ
4.1.5 የግል ከፍተኛ ክሊኒኮች/የግል ልዩ ክሊኒኮች ፡-
አገልግሎት ለሰጡት ታካሚ የመንግሥት ሠራተኛ የህመም
ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እስከ 1ዐ ቀናት የሚደርስ
የህመም ፈቃድ ሊሰጡ የሚችሉ ሲሆን ታካሚው ሊሻለው
ካልቻለና ተጨማሪ ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ 5
ቀናት በመጨመር በድምሩ እስከ 15 ቀናት ድረስ ሊሰጡ
ይችላሉ፣
4.1.6 የግል ሆስፒታል
ለታከመ የመንግሥት ሠራተኛ የህመም ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ
ከሆነ እስከ 15 ቀን የሚደርስ የህመም ፈቃድ መስጠት
ይቻላል፡፡ ህመምተኛው ካልተሻለውና ተጨማሪ የፈቃድ
ማስረጃ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከበቂ ማብራሪያ ጋር
በተከታታይ 15 ቀናት ፈቃድ በመጨመር በጠቅላላው 3ዐ
ቀናት ፈቃድ መስጠት የሚቻል ሲሆን በተጨማሪ የሚሰጠው
የህመም ፈቃድ ተቀባይነት የሚኖረው በስፔሻሊስት ወይም
በቋሚ የሆስፒታሉ ሀኪም ሲፈረም ብቻ ነው፡፡
4.1.7 የመንግሥት ሆስፒታሎች፡-
አገልግሎት ለተሰጠው ታካሚ የህመም ፈቃድ መስጠት አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010
አንቀጽ 43 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የህክምና ፈቃድ
መስጠት ይችላሉ፡፡አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙትም ታማሚው
በጡረታ እንዲገለል ውሳኔ አስተላልፈው ለአሰሪ መስሪያ ቤቱ
ማሳወቅ ይችላሉ፡፡
4.1.8 በውጭ ሀገር የሚገኙ የጤና ተቋማት የሚሰጧቸው
የህክምና ማስረጃዎች የጤና ጥበቃ ሚ/ር በሚሰጠው አቻ
ግመታ መሰረት በአገር ውስጥ ካሉ የመንግስትም ሆነ የግል ጤና
ተቋማት የሚሰጧቸው የህክምና ማስረጃዎች
በሚስተናገዱበት አግባብ እኩል ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡
 4.2 የሚሰጠው የህክምና ማስረጃ ሊያሟላቸው የሚገቡ

ጉዳዮች፡-
 4.2.1 ሕክምናውን የሰጠው ተቋም የራስጌና የግርጌ

ማህተም ማድረግ፣
4.2.2 የታካሚው ስም ከነአያቱ ፣ለሕክምና የቀረበበት ቀን የተደረገ
የሕክምና ዓይነት፣ የተሰጠ የሕክምና ፈቃድ ካለ በፊደልና በአሃዝ
ይገለፃል፡፡
4.2.3 የህክምና ማስረጃው በህክምና ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም
ህክምናውን በሰጠው ባለሙያ የተፈረመ መሆን ይኖርበታል፡፡
4.2.4 የማስረጃው የፕሮቶኮል ቁጥርና ቀን የተሟላ ሊሆን ይገባል፣
4.2.5 የሕክምና ማስረጃው ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት፡
ክፍል አምስት
የሕመም ፈቃድ
5.1 የሕመም ፈቃድ
5.1.1 ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ሥራ
መሥራት ያልቻለ እንደሆነ ደመወዝ የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድ
ይሰጠዋል፡፡
1. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሙከራ ጊዜውን ላጠናቀቀ
የመንግሥት ሠራተኛ የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ
ቢወስድም ሕመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው አስራ ሁለት ወር
ጊዜ ውስጥ ከስምንት ወር ወይም በአራት ዓመት ውስጥ ከአሥራ ሁለት ወር
አይበልጥም፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚሰጥ የሕመም ፈቃድ
ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሙሉ ደመወዝ ጋር እና ለሚቀጥሉት
ሁለት ወራት ከግማሽ ደመወዝ ጋር ይሆናል፡፡
3. በንዑስ ቁጥር /2/ ሥር የተገለፀው ቢኖርም የኢች. አይ.ቪ/ኤድስ
ህሙማን የሆኑ ሠራተኞች ለ8 ወራት ሙሉ ደመወዝና ለቀሪዎች
አራት ወራት ደግሞ ግማሽ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፣
4. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ከታመመ የህክምና
ማስረጃ የሚቀርብበት የአንድ ወር የሕመም ፈቃድ ከደመወዝ ጋር
ይሰጠዋል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ሲታመም፣
ሀ) ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመው በስተቀር
በተቻለ ፍጥነት መታመሙን ለመሥሪያ ቤቱ ማሳወቅ
አለበት፣
ለ) በተከታታይ ከሦስት ቀናት ወይም በአንድ የበጀት ዓመት
ውስጥ ከስድስት ቀናት በላይ በሕመሙ ምክንያት ከሥራ
የቀረ እንደሆነ ለመታመሙ የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ
አለበት፡፡
6. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት ሠራተኛ በዓመት
ፈቃድ ላይ እያለ መታመሙን የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ
ካቀረበ የዓመት ፈቃዱ ተቋርጦ የሕመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
7. በንዑስ ቁጥር (6) መሠረት የተቋረጠው የዓመት ፈቃድ
የሕመም ፈቃዱ እንደተጠናቀቀ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡
ክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ጉዳዮች
6.1 የህክምና ማስረጃ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው
በቅድሚያ የመንግስት ሰራተኛው በሚሰራበት የስራ ቦታ
አቅራቢያ ከሚገኝ የመንግስት የህክምና ተቋም ሪፈር
ተደርጎ ወደ መንግስት ከፍተኛ የህክምና ተቋም ህክምና
አገልግሎት
6.2 በዚህ መመሪያ ውስጥ ያልተካተቱ ፈቃዶች
በመንግሥት መ/ቤቶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
6.3 የጤና ባለሙያዎች ለሚሰጧቸው የህክምና ፈቃድ
ማስረጃዎች በጋራም ሆነ በተናጠል ተጠያቂነት አለባቸው፣
6.4 ከሙያው ሥነ-ምግባር ውጭ ተገቢ ያልሆነ የህክምና
ማስረጃ መስጠት ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
6.5 የመንግሥት መ/ቤቶች የሚቀርቡላቸውን የህክምና
ማስረጃዎች ትክክለኛነት የማጣራት ኃላፊነት አለባቸው፡፡
6.6 የሚሰጠው የሕክምና ፈቃድ ተከታታይና ቅዳሜና እሁድን
እንዲሁም ሌሎች የበዓላት ቀናትን ያካትታል፡፡
6.7 ታካሚዎች የሚያቀርቡት የህክምና ማስረጃ የሰራተኛው
የቅርብ ሀላፊ ካየው በኋላ በክልል በሰው ኃብት አስተዳደር
ዳይሮክተሬት በሜትሮፖሊታን ከተሞች፣በዞን፣ በወረዳ፣ በመካከለኛ
ከተማ በአንስተኛ ከተማ፣ በክ/ከተማና በሌሎች ከተማ
አስተዳደሮች ደግሞ በሰው ኃብት አስተዳደር ሠራተኞች
አማካኝነት ተረጋግጦ ከሠራተኛው የግል ማህደር እንዲቀመጥ
ይደረጋል፡፡
6.8 በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር
253/2010 አንቀጽ 96 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ይህን
መመሪያ የመለወጥ፣ የማሻሻል ወይም በሥራ ላይ በሚውልበት
ጊዜ ማብራሪያ ወይም ትርጉም የመስጠት ኃላፊነት የሲቪል
ሰርቪስ ኮሚሽን ነው፡
6.9 በሰኔ ወር 2011 ዓ/ም ወጥቶ በሥራ ላይ የነበረው የፈቃድ
አሰጣጥና ማስረጃ አቀራረብ መመሪያና ይህንን አስመልክቶ
የተላለፉ ሰርኩላሮች በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡
6.10 ይህን መመሪያ በተዛባ መልኩ ወይም ያለአግባብ
የሚያስፈጽም ማንኛውም አካል ወይም የስራ ኃላፊ አግባብ
ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል
6.11 በዚህ መመሪያ አሰራር ላይ የሚኖር ቅሬታ በስራ ላይ
ባለው የቅሬታአቀራረብ ሥርዓት መሰረት ተፈፃሚ
ይሆናል::
6.12 ይህ መመሪያ ከፀደቀበት ህዳር/ 2013 ዓ/ም ጀምሮ
የፀና ነው፡
ሙሉቀን አየሁ
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
ኮሚሽነር
ህዳር/2013ዓ.ም
ባህር ዳር
ተቀጽላ-1
የሠራተኞች የዓመት ፈቃድ መጠየቂያ ቅጽ፣
ሀ/ ፈቃድ ጠያቂ፣
ስም የአገልግሎት ዘመን ቀደምሲል
ለመ/ቤቱ ባቀረብኩት የዓመት እረፍት ፈቃድ መውጫ
ፕሮግራም መሠረት ከ ዓ.ም የዓመት እረፍት ፈቃዴ ከ
ዓ/ም እስከ ዓ.ም ድረስ ለ-------ቀናት
የሙሉ ቀን/የግማሽ ቀን ፈቃድ እንዲሰጠኝ እጠይቃለሁ፡፡
ለስራ ብፈለግ በ-------------------
ከተማ------------------------- ቀበሌ
----------------------- ስልክ ቁጥር አድራሻ
የምገኝ መሆኔን እገልፃለሁ፡፡
የጠያቂው ፊርማ ቀን
ለ/ ፈቃድ ሰጪ
ሠራተኛው ያቀረቡት የዓመት እረፍት ፈቃድ ጥያቄ አስቀድመው
ባሣወቁት ፕሮግራም መሠረት ስለሆነ ከ ቀን ዓ.ም
ጀምሮ የ ቀን የዓመት እረፍት የሙሉ ቀን/የግማሽ ቀን
ፈቃዳቸው እንዲሰጣቸው ተስማምቻለሁ፡፡
የቅርብ ኃላፊ /ሂደት መሪ/አስተባባሪ ስም ፊርማ
ቀን
ሐ/ ሠራተኛው ያቀረቡት የዓመት እረፍት ፈቃድ ጥያቄ
አስቀድመው ባሣወቁት ፕሮግራም መሠረት ቢሆንም የሥራ
ሂደቱ ካለበት ወቅታዊና አስቸኳይ ሥራ አኳያ የዓመት እረፍት
ፍቃዳቸውን መጠቀም ስለማይችሉ በዚህ የበጀት ዓመት
ወደ-----------------
ወር/----------------ዓ.ም እንዲዛወርላቸው
ወስኛለሁ፡፡
የቅርብ ኃላፊ /ሂደት መሪ/አስተባባሪ ስም ፊርማ
ቀን
መ/ ሠራተኛው ያቀረቡት የዓመት እረፍት ፈቃድ ጥያቄ
አስቀድመው ባሣወቁት ፕሮግራም መሠረት ቢሆንም የሥራ
ክፍሉ ካለበት ወቅታዊና አስቸኳይ ሥራ አኳያ የዓመት እረፍት
ፍቃዳቸውን መጠቀም ስለማይችሉ ወደ ሚቀጥለው የበጀት
አመት ቢዛወርላቸው የሚል የውሳኔ አስተያየት አለኝ፡፡
የቅርብ ኃላፊ/ሂደት መሪ/አስተባባሪ ስም ፊርማ
ቀን
ሠ/ የሠራተኛው የዓመት እረፍተ ፈቃድ መውጫ ጊዜ
ወደሚቀጥለው የበጀት ዓመት እንዲራዘም ወስኛለሁ፡፡
የመ/ቤት ኃላፊ/ም/ኃላፊ/ ተወካይ ስም ፊርማ
ቀን
ረ/ በሰው ኃብት ልማት ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት
የሚሞላ
ሠራተኛው አስቀድመው ባሳወቁት ፕሮግራም መሠረት
ያቀረቡት ጥያቄ ስለሆነ ከ እስከ ዓ.ም ጀምሮ ከ
ዓ.ም ፈቃዳቸው ቀን------- የተሰጣቸው ሲሆን
ፈቃዳቸውን እንደጨረሱ
በ-------------------------------ቀን
--------------------- ዓ.ም በምድብ የስራ
ቦታቸው ላይ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላላ ያላቸው የዓመት ፈቃድ የተወሰደ
ቀሪ
የ201
የ201
የ2ዐ1
ጠቅላላ ያላቸው መሆኑን
እንገልፃለን፡፡
ያዘጋጀው የ/ሀ/ል/ስ/አ/ ደጋፊ ሥራ ሂደት ባለሙያ ስም ፊርማ
ተቀጽላ-2
ቁጥር
---------------------
ቀን
--------------------------
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የ ቢሮ/ኮሚሽን/ጽ/ቤት/ኤጀንሲ/ባለስልጣን/መምሪያ
የሠራተኞች የዓመት እረፍት ፈቃድ መውጫ ፕሮግራም ማሻሻያ ቅጽ
እኔ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት የተባልኩ የዚሁ መ/ቤት ባልደረባ
ሀ/በ
ምክንያት ቀደም ሲል ባቀረብኩት ፕሮግም መሠረት የዓመት
እረፍት ፈቃዴን መጠቀም ስላልቻልኩ በዚሁ በጀት ዓመትከ
ቀን ዓ.ም ጀምሮ መጠቀም እንድችል የፕሮግራም
ሽግሽግ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ፡፡
የሠራተኛው/ዋ/ ስም ፊርማ ቀን
ለ/ ያቀረቡትን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት የዓመት
እረፍት ፈቃድ መውጫ ፕሮግራም ማሻሻያውን ተቀብየዋለሁ፡፡
የቅ/ኃላፊ/የስ/ሂ መሪ/አስተባባሪ ስም ፊርማ
ቀን
ሐ/ በ

ምክንያት ቀደም ሲል ባቀረብኩት ፕሮግም መሠረት የአመት


እረፍት ፈቃዴን መጠቀም ስላልቻልኩ ወደ ቀጣዩ
የ--------------------------------- በጀት
ዓመት እንዲዛወርልኝ እጠይቃለሁ፡፡
የሠራተኛው/ዋ/ ስም ፊርማ ቀን
መ/ ከላይ የቀረበውን ምክንያት ከግምት ውስጥ በማስገባት
የዓመት እረፍት ፈቃድ መውጫ ፕሮግራማቸው ወደ
-----------------------በጀት ዓመት እንዲዛወር
ወስኛለሁ፡፡
የመ/ቤት ኃፊ/ምክትል ኃላፊ/ተወካይ ስም
ፊርማ ቀን
ተቀጽላ-3
የሠራተኞች የዓመት እረፍት መውጫ ፕሮገራም ቅጽ፣
የሠራተኛው /ዋ/ ስም
የሥራ መደቡ መጠሪያ
ጠቅላላ ያላቸው የዓመት ፈቃድ
የ ……………………………….
የ ……………………………….
የ ……………………………….
ጠቅላላ ድምር ……………………………
ተቁ ፈቃድ የሚወስድበት ጊዜና ዓ.ም የሚወስደው ምርመራ
የፈቃድ
ቀን
ብዛት
የሠራተኛው /ዋ/
ስም ………………….
ቀን……………………
ፊርማ ……………………

የቅርብ ኃላፊ/የስ/ሂ/መሪ/አስ/
ስም ……………….
ፊርማ ……………………..
ቀን ……………………..
የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት/ቡድን
ስም…………………………………..
ፊርማ …………………………..
ቀን ………………………..
አመሰግናለሁ!!

You might also like