Fams Training For Zone & Woreda Kabinets-Keffa, Sheka, B-Maji

You might also like

Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 63

Health Sector Financing

Reform Project

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን

የፋይናንስ አስተዳደርና አሠራር ሥርዓት

ለዞንና ወረዳ ካቢኔ አባላት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና

2007 ዓ.ም.

1
Health Sector Financing
Reform Project

የማዐጤመ የፋይናንስ አስተዳደርና አሠራር ሥርዓት

ክፍል አንድ

የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የፋይናንስ አስተዳደርና አሠራር ሥርዓት

2
Health Sector Financing
Reform Project

ማውጫ

1. ምዝገባ

1.1. የአባላት ምዝገባ (የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ)

1.2. የአባልነት መታወቂያ ካርድ አዘገጃጀት

1.3. የአባላትን መረጃ ወቅታዊ ስለማድረግ ማድረግ (የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ)

1.4. ምትክ መታወቂያ ካርድ ስለመስጠት

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና ማስተላለፍ

2.1 የመመዝገቢያ ክፍያን መሰብሰብና ማስተላለፍ

2.2 መዋጮን መሰብሰብና ማስተላለፍ 3


Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ (አማቅ) ይዘት እንደሚከተለው ይሆናል፡-


• ክልል፣ የወረዳው ማዐጤመ ተቋም ስም እና የቀበሌ ንዑስ ክፍል ስም (በራስጌ
ላይ)
• የምዝገባ ቀን (ማመልከቻው ለቀበሌ ፅ/ቤት ገቢ የተደረገበት ቀን)
• የክፍያ ሁኔታ (ከፋይ አባላት ወይም መክፈል የማይችሉ)
• የተጠቃሚ ስም
• ፆታ
• የትውልድ ቀን
• አድራሻ
• ከአባሉ ጋር ያለው ዝምድና
• መተዳደሪያ ስራ
• አስተያየት 4
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ (አማቅ) አሞላል፡


 አባላት የአባልነት ማመልከቻ ቅፁን ከቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ይወስዳሉ፤

 አስፈላጊውን መረጃ በቅፁ ላይ እንደተመለከተው በሁለት ቅጂ ይሞላሉ፤

 አባላት ቅፁን ሲሞሉ በመጀመሪያው መስመር ላይ የራሳቸውን የግል መረጃ ያሰፍራሉ፤


በተከታይ መስመሮች ላይ የቤተሰብ አባላትን ዝርዝር መረጃ ያሰፍራሉ፤
 “ከአባሉ ጋር ያለው ዝምድና” በሚለው ስር ለቤተሰብ ሃላፊው ‘አባል’ ተብሎ ይሞላል፤
ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ግን ከቤተሰብ ሃላፊው ጋር ያላቸው ዝምድና ይሞላል (ምሳሌ
የትዳር አጋር፣ ልጅ፣ ወዘተ)፤

5
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ…...
የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ አሞላል፡-

 “አስተያየት” የሚለው በቀበሌ የማዐጤመ ፅ/ቤት የሚሞላ ይሆናል፤ ይህም አባላት ቅፁን አሟልተው
ወደ ቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ሲያመጡ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ ትክክል; ወይም አይደለም ተብሎ
የሚሞላ ይሆናል፤
 “የምዝገባ ቀን” በሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ቅፁን ከአባላት ሲረከብ ቀኑን የሚገልፅ ማህተም
ያሳርፍበታል (ምሳሌ፡- ሚያዝያ 12/2007)፤
 “የክፍያ ሁኔታ” ለሚለው ክፍያን ራሳቸው ለሚከፍሉ አባላት ‘ከፋይ’ ተብሎ ሲሞላ ክፍያቸውን
ራሳቸው ለማይከፈሉት ደግሞ ‘መክፈል የማይችል’ ተብሎ ይሞላል፤
 “የአመልካች ፊርማ” በሚለው አባላት ፊርማቸውን የሚያሰፍሩበት ሥፍራ ይሆናል፡፡ 6
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

 የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ሥርጭት፡-


 አባላት የአባልነት ማመልከቻ ቅጽን በሁለት ቅጂ ሞልተው ለቀበሌ ማዐጤመ ክፍል
ያቀርባሉ፡፡
 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍል የቅጹን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ይቀበላል፤

 የተቀበለውን ቅጽ አንዱን ቅጂ ለወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት ያስተላልፋል፤ ሁለተኛውን


ቅጂ በቀበሌው ማዐጤመ ፅ/ቤት በፋይል ማደራጃ ውስጥ በጥንቃቄ ያስቀምጣል፡፡
 የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ለመታወቂያ ካርድ ዝግጅትና ለመረጃ አያያዝ ምንጭ
ሰነድ በመሆኑ በጥንቃቄ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡(የቅጹን ይዘት ይመልከቱ)

7
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ….

1.2. የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ስለማዘጋጀት


የማዐጤመ አባላት መታወቂያ ካርድ የሚዘጋጀው በወረዳው ማዐጤመ ፅ/ቤት ይሆናል፡፡

የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ሲዘጋጅ በቤተሰብ ኃላፊው ነው፤

ከፋይ አባላት መታወቂያ ካርድ የሚዘጋጅላቸው በመጀመሪያ ምዝገባ ጊዜ የመመዝገቢያ


ክፍያን ሲከፍሉ ነው፡፡
መክፈል ለማይችሉ አባላት መታወቂያ ካርድ የሚዘጋጅላቸው የወረዳ አስተዳደር መክፈል
በማይችሉ አባላት ስም የመመዝገቢያ ክፍያን ሲከፍል ነው፡፡
የወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት የመታወቂያ ካርዶችን ካዘጋጀ በኋላ ወደ ቀበሌ ማዐጤመ ንዑስ
ክፍል ይልካል፤ የቀበሌ ማዐጤመ ንዑስ ክፍልም ካርዶቹን ለአባላት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
(የካርዱን ይዘት ይመልከቱ) 8
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ….
 በቤተሰብ ስብጥር ለውጥ ምክንያት በቤተሰብ ውስጥ የመረጃ ለውጥ ሲከሰት የማዐጤመ
መታወቂያ ካርዱን በተለወጠው መረጃ መሠረት ወቅታዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
 ሆኖም ግን የመታወቂያ ካርዱ ወቅታዊ ከመደረጉ በፊት ለውጡ የአመማማቅ ከቀበሌ
ማዐጤመ ንዑስ ክፍል ወደ ወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት መላክ ይኖርበታል፤ለውጡም
በተጠቃሚዎች መዝገብ ላይ መስፈር ይኖርበታል፡፡
 ምሳሌ ፡-አንድ ህፃን በአባሉ ቤተሰብ ውስጥ ቢወለድ በመታወቂያ ካርዱ ላይ ከተዘጋጁ
ገፆች በአንዱ ላይ ፍቶ ግራፍና ሌሎች መረጃዎች ይሰፍራሉ፤ በተመሳሳይ አንድ የቤተሰቡ
አባል በሞት ቢለይ የሟችን የግል መረጃ የያዘው ገፅ ላይ ሟች ከዚህ በኋላ ተጠቃሚነቱ
መቆሙን ለማመልከት “የተሰረዘ” የሚል ምልክት ይደረግበታል፡፡

9
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …
1.3. የአባላትን መረጃ ወቅታዊ ማድረግ (የቤተሰብ አባላት መረጃን ጨምሮ)

 የአባላትና ቤተሰቦቻቸው መረጃ በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜ ሂደት ሊለወጥ ይችላል፡፡

 ይህ የቤተሰብ ስብጥር ለውጥ በውልደት፣ በጉዲፈቻ፣ በሞት፣ ወዘተ ሊከሰት


ይችላል፡፡
 አባላት ይህ ለውጥ በቤተሰባቸው በተከሰተ ጊዜ የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ
ቅፅ በመሙላት ለቀበሌ ማዐጤመ ጽ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የተከሰተው ለውጥ በመታወቂያ ደብተር ላይ ተሻሽሎ
መቅረቡን መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡

10
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅፅ (አመማማቅ) አሞላል፡


 አባላት የቤተሰብ ስብጥር ለውጥ (ለምሳሌ የልጅ መወለድ) ሲከሰት አመማማቅ ከቀበሌ
ማዐጤመ ፅ/ቤት ይወስዳሉ፤
 አስፈላጊውን መረጃ በቅፁ ላይ እንደተመለከተው በሁለት ቅጂ ይሞላሉ፤

 የቅፁ የመጀመሪያ መስመር በአባሉ (የቤተሰብ ሃላፊው) መረጃ ይሞላል፣ ይህም ለውጥ
የተከሰተበት ቤተሰብ የትኛው እንደሆነ ለመለየት ይረዳል፤
 የቅፁ ሁለተኛ እና ተከታይ መስመሮች በሌሎች ለውጥ በተከሰተባቸው የቤተሰብ አባላት
መረጃ ይሞላሉ (ለምሳሌ አዲስ በተወለደው ህፃን መረጃ)
 “የማመልከቻው ምክንያት” የሚለው ስር አዲስ የተወለደ፣ አዲስ ጉዲፈቻ ልጅ፣ በሞት
የተለየ፣ ወዘተ ተብሎ እንደለውጡ ዓይነት ይሞላል፤ 11
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ……

የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅፅ (አመማማቅ) አሞላል፡-


“አስተያየት” የሚለው በቀበሌ የማዐጤመ ፅ/ቤት የሚሞላ ይሆናል፤ ይህም አባላት ቅፁን
አሟልተው ወደ ቀበሌ ፅ/ቤት ሲያመጡ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ ‘ትክክል’ ወይም ‘ተሰርዟል’ ተብሎ
ይሞላል፤
“የማመልከቻ ቀን” የሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ቅፁን ሲረከብ ቀኑን የሚገልፅ ማህተም
ያሳርፍበታል (ምሳሌ፡-ሚያዝያ 12፣ 2007)
“የክፍያ ሁኔታ” ለሚለው ‘ከፋይ አባል’ ወይም ‘መክፈል የማይችል’ ተብሎ እንደቤተሰቡ የክፍያ
ሁኔታ ይሞላል፤
“የአመልካች ፊርማ” በሚለው አባላት ፊርማቸውን የሚያሰፍሩበት ስፍራ ነው፡፡

12
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅፅ ሥርጭት፡-


አባላት የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅጽን በሁለት ቅጂ ሞልተው ለቀበሌ ማዐጤመ
ክፍል ያቀርባሉ፤
የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የቅጹን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ይቀበላሉ፤

የተቀበሉትን ቅጽ አንዱን ቅጂ ለወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት ያስተላልፋሉ፤ ሁለተኛውን ቅጂ


በቀበሌው ማዐጤመ ፅ/ቤት ቀደም ሲል በተከፈተው ፋይል ማደራጃ ውስጥ ከአባሉ የአባልነት
ማመልከቻ ቅጽ ጋር በማያያዝ በጥንቃቄ ያስቀምጣሉ፤
የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅጽ በመታወቂያ ካርድና በሌሎች መረጃዎች ላይ
ተገቢውን ማሻሻያ ለማድረግ ምንጭ ሰነድ በመሆኑ በጥንቃቄ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡(የቅጹን ይዘት
ይመልከቱ) 13
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ…..

1.4. የምትክ ማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ፡-


አባላት የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ሲበላሽባቸው ወይም ሲጠፋ ለምትክ መታወቂያ ካርድ
መጠየቂያ የተዘጋጀውን ቅፅ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

ምትክ መታወቂያ ካርድ መጠየቂያ ቅፅ (ምመካመቅ) አሞላል፡-


አባላት የመታወቂያ ካርዳቸው ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ መታወቂያ ካርድ መጠየቂያ
ቅፅ ከቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች ይወስዳሉ፤
አስፈላጊውን መረጃ በቅፁ ላይ እንደተመለከተው በሁለት ቅጂ ይሞላሉ፤

መታወቂያ ካርድ የሚሰጠው በቤተሰብ ስለሆነ በቅፁ የሚሞላው የአባሉ (የቤተሰብ ሃላፊ)
ግላዊ መረጃ ብቻ ይሆናል፤ 14
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …
• ምትክ መታወቂያ የተጠየቀበት ምክንያት ለሚለው ስለጠፋ፣ ስለተበላሸ፣ ወዘተ ተብሎ
ይሞላል (የተበላሸ ከሆነ ምትክ ሲሰጥ የተበላሸው ተመላሽ ይሆናል)
• አስተያየት የሚለው በቀበሌ የማዐጤመ ፅ/ቤት የሚሞላ ይሆናል፤ ይህም አባላት ቅፁን
አሟልተው ወደ ቀበሌ ፅ/ቤት ሲያመጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፣ ቅጣት ከፍሏል፣ ወዘተ
ተብሎ ይሞላል
• የማመልከቻ ቀን የሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ቅፁን ሲረከብ ቀኑን የሚገልፅ ማህተም
ያሳርፍበታል (ምሳሌ ሚያዝያ 12፣ 2007)
• የክፍያ ሁኔታ ለሚለው ከፋይ አባል ወይም መክፈል የማይችሉ ተብሎ እንደቤተሰቡ የክፍያ
ሁኔታ ይሞላል
• አመልካች አባላት ፊርማቸውን በተገለፀው ስፍራ ሊያሰፍሩ ይገባል፤
15
Health Sector Financing
Reform Project

1. ምዝገባ …

የምትክ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅጽ ስርጭት፡-


አባላት የምትክ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅጽን በሁለት ቅጂ ሞልተው ለቀበሌ ማዐጤመ
ክፍል ያቀርባሉ፤
የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የቅጹን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ይቀበላሉ፤

የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት የማመልከቻ ቅፁን አንዱን ቅጂ ለወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት ምትክ
መታወቂያ ካርድ እንዲዘጋጅ ሲያስተላልፍ ሁለተኛውን ቅጂ በቀበሌው ማዐጤመ ፅ/ቤት በፋይል
ማደራጃ ውስጥ ያስቀምጣል፤
 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች አባላት ምትክ መታወቂያ ካርድ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል
ሊያደርጉ ይገባል፡፡(የማመልከቻ ቅጽን ይዘት ይመልከቱ)
16
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ
2.1 የመመዝገቢያ ክፍያን መሰብሰብና ማስተላለፍ

 ከፋይ አባላት የማዐጤመ አባልነት መታወቂያ ካርድ ማግኘት ይችሉ ዘንድ የአንድ ጊዜ
የመመዝገቢያ ክፍያ በመጀመሪያ ምዝገባ ወቅት መክፈል ይኖርባቸዋል፤
 የመመዝገቢያ ክፍያ ለመታወቂያ ካርድ ማሳተሚያና ተያያዥ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል፤

 መክፈል ለማይችሉ አባላት የመመዝገቢያ ክፍያ በወረዳ አስተዳደር በቀጥታ ለወረዳ ማዐጤመ
ፅ/ቤት ይከፈላል፡፡

17
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ …

የመመዝገቢያ ክፍያን ማሰባሰብና ማስተላለፍ ዝርዝር የስራ ሂደት


 በመጀመሪያ ምዝገባ ጊዜ ከፋይ አባላት የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ (አማቅ) ሞልተው ለቀበሌ
ማዐጤመ ፅ/ቤት ሲያስረክቡ የመመዝገቢያ ክፍያን ይከፍላሉ፤
 የመመዝገቢያ ክፍያን ለቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ሲከፍሉ የክፍያ ማረጋገጫ ደረሰኝ ይሰጣቸዋል

 የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት በገቢ ደረሰኝ ላይ እንደሚከተለው ይሞላል፡-


• “የክፍያ ቀን” በሚለው ክፍያው የተፈፀመበት ቀን ይሞላል፤
• “የከፋይ ስም” በሚለው የአባሉ/የቤተሰብ ሃላፊው ስም ይሞላል፤

18
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና ማስተላለፍ ….

የመመዝገቢያ ክፍያን ማሰባሰብና ማስተላለፍ ዝርዝር የስራ ሂደት….


“ክፍያውን የተቀበለው አካል” በሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ንዑስ ክፍል ስም ይሞላል፤

“የገንዘቡ መጠን” በሚለው የመመዝገቢያ ክፍያው መጠን ይሞላል፤

“ገንዘቡ የተሰበሰበበት መንገድ” በሚለው በጥሬ ገንዘብ ላይ ምልክት ይደረግበታል፤

“የክፍያው ምክንያት” በሚለው ለማዐጤመ አባልነት የመመዝገቢያ ክፍያ ከፈሉ


ተብሎ ይሞላል፤
“ገንዘቡን የተቀበለው” በሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ክፍል ገንዘብ ተቀባይ ስምና ፊርማ
ይሞላል፡፡

19
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ …
 የገቢ ደረሰኙ በሦስት ቅጂ ተዘጋጅቶ እንደሚከተለው ይከፋፈላል
• የመጀመሪው ቅጂ ለከፋይ ይሰጣል፤

• ሁለተኛው ቅጂ ከጥራዙ ተቆርጦ ለወረዳ ማዐጤመ ይላካል፤

• ሦስተኛው ቅጂ ሳይቆረጥ በጥራዙ ላይ ይቀራል፡፡

 የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት የተሰበሰበውን ገንዘብ በየወሩ በወረዳ ማዐጤመ ተቋም በተከፈተው
ባንክ/ማይክሮ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

 ከብር 2000 በላይ ሲሆን ግን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍል የተሟላ ሰነድ በማቅረብ ከወረዳው ማዐጤመ ተቋም ገቢ


ስለተደረገው ገንዘብ ማስረጃ(የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ) መቀበል አለበት፤
20
Health Sector Financing
Reform Project

2.የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና ማስተላለፍ …

 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ ለመውሰድ


የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡-
 የመመዝገቢያ ክፍያው የተሰበሰበበትን የገቢ ደረሰኝ ሁለተኛ ቅጂ፤

 የገቢ ማጠቃለያ ቅጽ፤(የቅፁን ይዘት ይመልከቱ)

 ገንዘቡ ገቢ የተደረገበትን የባንክ አደቫይስ/የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ደረሰኝ

 የገቢ ደረሰኝ የሚከተለው ይዘት/ገፅታ ይኖረዋል፡- (ቅፁን ይዘት ይመልከቱ)

21
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ …

2.2. መዋጮን መሰብሰብና ማስተላለፍ

 ከፋይ አባላት ማዐጤመ ተቋሙ በጥቅም ማዕቀፉ የተካተቱትን የጤና አገልግሎት ማግኘት
የሚችሉት የሚጠበቅባቸውን የአባልነት መዋጮን በቀጣይነት ሲከፍሉ ብቻ ነው፤
 መክፈል ለማይችሉ አባላት የወረዳ አስተዳደር የሚጠበቀውን የአባልነት መዋጮ በቀጥታ
ለወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት መክፈል ይኖርበታል፤

22
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ …
መዋጮን የመሰብሰብና ማስተላለፍ ዝርዝር የስራ ሂደት

 ከፋይ አባላት መዋጮን ለቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ይከፍላሉ፤ የክፍያ ማረጋገጫ ደረሰኝም
ይሰጣቸዋል፤
 “ክፍያውን የተቀበለው አካል” በሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ንዑስ ክፍል ስም ይሞላል፤

 “የገንዘቡ መጠን” በሚለው የመዋጮው መጠን ይሞላል፤

 “ገንዘቡ የተሰበሰበበት መንገድ” በሚለው በጥሬ ገንዘብ ላይ ምልክት ይደረግበታል፤

 “የክፍያው ምክንያት” በሚለው የአባልነት የመዋጮ ከፈሉ ተብሎ ይሞላል፤

 “ገንዘቡን የተቀበለው” በሚለው የቀበሌ ማዐጤመ ክፍል ገንዘብ ተቀባይ ስምና ፊርማ ይሞላል፡፡

23
Health Sector Financing
Reform Project

2. የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና


ማስተላለፍ …
 መዋጮ ሲከፈል የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት “ተከፍሏል” የሚል ማህተም በአባሉ መታወቂያ ላይ
ለዚሁ ጉዳይ ተብሎ በተዘጋጀው ስፍራ ላይ ያኖራል (ይህ ስፍራ በአባሉ መታወቂያ ሽፋን
የውስጠኛው ገፆች ላይ ይገኛል)፤

 የገቢ ደረሰኙ በሦስት ቅጂ ተዘጋጅቶ እንደሚከተለው ይከፋፈላል

 የመጀመሪው ቅጂ ለከፋይ ይሰጣል

 ሁለተኛው ቅጂ ከጥራዙ ተቆርጦ ለወረዳ ማዐጤመ ይላካል

 ሦስተኛው ቅጂ ሳይቆረጥ በጥራዙ ላይ ይቀራል፡፡

24
Health Sector Financing
Reform Project

የመመዝገቢያ ክፍያን እና መዋጮን ከከፋይ አባላት መሰብሰብና ማስተላለፍ …

 የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት የተሰበሰበውን ገንዘብ በየወሩ በወረዳ ማዐጤመ ተቋም በተከፈተው
ባንክ/ማይክሮ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 ከብር 2000 በላይ ሲሆን ግን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍል የተሟላ ሰነድ በማቅረብ ከወረዳው ማዐጤመ ተቋም ገቢ ስለተደረገው
ገንዘብ ማስረጃ(የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ) መቀበል አለበት፤
 የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ ለመውሰድ የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፡-
 የመዋጮው ክፍያው የተሰበሰበበትን የገቢ ደረሰኝ ሁለተኛ ቅጂ፤
 የገቢ ማጠቃለያ ቅጽ፤(የቅፁን ይዘት ይመልከቱ)
 ገንዘቡ ገቢ የተደረገበትን የባንክ አደቫይስ/የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ደረሰኝ
25
 የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ የሚከተለው ይዘት/ገፅታ ይኖረዋል፡- (ቅፁን ይዘት ይመልከቱ)
Health Sector Financing
Reform Project

የቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የገንዘብ ሂደት ሂደት

ከወረዳ ማዐጤመ
ተቋም የተጠቃለ
ገቢ ደረሰኝ
መቀበል

26
Health Sector Financing
Reform Project

ክፍል ሁለት

የማዐጤመ ፋይናንስ አስተዳደርና አሠራር ሥርዓት

27
Health Sector Financing
Reform Project

የወረዳ ማዐጤመ ተቋማት የፋይ/አስተዳደርና አሠራር ሥርዓት

ማውጫ
1.የዳታ ቤዝ አያያዝ
1.1 የተጠቃሚዎች መዝገብ
1.2 የመዋጮ መዝገብ
2.የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ስለማዘጋጀት
3.የማዐጤመ ተቀምን ፋይናንስ መቀበልና ማስተዳደር
3.1 ከቀበሌ ማዐጤመ ንዑስ ክፍሎች ገንዘብ ስለመቀበል
3.2 ከሌሎች የገቢ ምንጮች ገንዘብ ስለመቀበል
3.3 የባንክ ሂሳብ ቁጥር መክፈትና ገንዘብ ማስቀመጥ
4.ከጤና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ውል መዋዋል

28
Health Sector Financing
Reform Project

ማውጫ …
5. የክፍያ ጥያቄን መቀበል፣ መመርመር እና ክፍያን መፈፀም
5.1 የክፍያ ጥያቄን መቀበል
5.2 የክፍያ ጥያቄን መመርመር
5.3 ክፍያን መፈፀም
6. የማዐጤመ የሂሳብ አያያዝ ዑደት/ሽክርክር
7. የማዐጤመ ተቀም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት
8. የማዐጤመ ተቀም የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ማዘጋጀት
8.1 ስለተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሪፖርት
8.2 ስለመዋጮዎችና የመመዝገቢያ ክፍያዎች የሚቀርብ ሪፖርት
8.3 ስለአጠቃቀም የሚቀርብ ሪፖርት
9. የማዐጤመ ተቀም ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት
9.1 የበጀት ዝግጅት 29

9.2 የሩብ ዓመት እርምዳት ሪፖርቶች (የበጀት ቁጥጥር)


Health Sector Financing
Reform Project

1. የዳታቤዝ አያያዝ
• የዳታቤዝ አያያዝ ማለት ከየቀበሌው የማዐጤመ ንዑሳን ፅ/ቤቶች የሚመጡትን መረጃዎች
ስርዓት ባለው መልኩ በማደራጀት ቋሚ በሆነ የመረጃ ቋት (በኮምፒዩተር ስርዓት ወይም በባህር
መዝገብ) ማስቀመጥን የሚያመለክት ነው
• ከየቀበሌው የሚመጡ መረጃዎች የሚያካትቱት፡-
• አማቅ፡ የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ
• አመማማቅ፡ የአባልነት መረጃ ማሻሻያ ማመልከቻ ቅጽ
• ምመካመቅ፡ ምትክ መታወቂያ ካርድ መጠየቂያ ቅጽ
• ገደ፡ የገቢ ደረሰኝ (አባላት የመመዝገቢያ ክፍያ እና መዋጮ ሲከፍሉ ከቀበሌ ጽ/ቤት የሚሰጣቸው
የገቢ ደረሰኝ ሁለተኛ ቅጅ)
• ገደማ፡ የገቢ ደረሰኝ ማጠቃለያ
• እነዚህን መረጃዎች ለመመዝገብ በወረዳ የመዐጤመ ጽ/ቤት በመሠረታዊነት ሁለት የምዝገባ
መዛግብት ይዘጋጃሉ፤ እነርሱም፡-
• የተጠቃሚዎች መዝገብ (አማቅ፣ አመማማቅ እና ምመካመቅ)
• የመዋጮ መዝገብ (ገደ እና ገደማ)
30
Health Sector Financing
Reform Project

1. የዳታቤዝ አያያዝ …
1.1 የተጠቃሚዎች መዝገብ
• የተጠቃሚዎች መዝገብ ማለት የተጠቃሚዎችን አስፈላጊ የሆኑ የግል ዝርዝር መረጃዎችን
በአንድ ላይ አጠቃሎ የሚይዝ ዳታቤዝ ነው
• ከቀበሌ ማዐጤመ ጽ/ቤቶች በአባልነት ማመልከቻ ቅፅ (አማቅ) ላይ የተሞሉ
• ከቀበሌ የማዐጤመ ጽ/ቤት በአመማማቅ ላይ የተሞሉ
• የመታወቂያ ካርዶች ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጡ ወይም ምትክ ሲዘጋጅ የተሞሉ ቅፆች

• የተጠቃሚዎች መዝገብ የሚከተሉትን መረጃዎች ለማስፈር ያገለግላል፡-


• የተጠቃሚዎች የግል መረጃ
• የመመዝገቢያ ክፍያን በተመለከተ
• የማዐጤመ መታወቂየ ካርድ ሲዘጋጅ (የመጀመሪያ ወይም ምትክ ሲዘጋጅ)
• ከአባልነት የወጣበት ቀን (የወጣ ካለ)
• አስተያየት
ቅፁን ይመልከቱ
31
Health Sector Financing
Reform Project

1. የዳታቤዝ አያያዝ …
1.2 የመዋጮ መዝገብ
• የመዋጮ መዝገብ የከፋይ አባላትን የመዋጮ ክፍያ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ አጠቃሎ
የሚይዝ መዝገብ ነው
• ከቀበሌ ማዐጤመ ጽ/ቤቶች የመጡ የገቢ ደረሰኝ (ሁለተኛ ቅጂ)
• ከቀበሌ የማዐጤመ ጽ/ቤት የመጡ የገቢ ደረሰኝ ማጠቃለያ
• የመዋጮ መዝገብ የሚከተሉትን መረጃዎች ለማስፈር ያገለግላል፡-
• የአባሉ መለያ ቁጥር
• የአባሉ ስም
• የክፍያ ጊዜ (ወር፣ ሩብ ዓመት፣ ወዘተ …)
• በእያንዳንዱ የክፍያ ጊዜ
• የክፍያ ቀን
• የክፍያው መጠን
• የደረሰኝ ተራ ቁጥር
• መዝገቡ ለአንድ ዓመት ወይም ለሁለት ዓመት እንዳስፈላጊነቱ ሊያገለግል ይችላል
32
ቅፁን ይመልከቱ
Health Sector Financing
Reform Project

2. የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ስለማዘጋጀት


• የማዐጤመ አባላት መታወቂያ ካርዶች የሚዘጋጁት በወረዳው ማዐጤመ ፅ/ቤት ይሆናል
• የማዐጤመ መታወቂያ ካርዶች ሲዘጋጁ በአባሉ (የቤተሰብ ኃላፊው) ስም ነው፤ ይሁን እንጂ
በአባሉ ስር የተመዘገቡ መሰረታዊ የቤተሰብ አባላትን ሁሉ ማንነታቸውን ለመለየት ያገለግላል
• ከፋይ አባላት የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ የሚዘጋጅላቸው በመጀመሪያ ምዝገባ ጊዜ
የመመዝገቢያ ክፍያን ሲከፍሉ ነው፡፡ መክፈል ለማይችሉ አባላት የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ
የሚዘጋጅላቸው ጉዳዩ የሚመለከተው አካል (የወረዳ አስተዳደር) መክፈል በማይችሉ አባላት
ስም የመመዝገቢያ ክፍያን ሲከፍል ነው
• የወረዳ ማዐጤመ ፅ/ቤት የመታወቂያ ካርዶችን ካዘጋጀ በኋላ ወደ ቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት
ይልካል፤ የቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤትም ካርዶቹን ለአባላት እንዲደርስ ያደርጋል

33
Health Sector Financing
Reform Project

2. የማዐጤመ መታወቂያ ካርድ ስለማዘጋጀት …


• በቤተሰብ ስብጥር ለውጥ ምክንያት በቤተሰብ ውስጥ የመረጃ ለውጥ ሲከሰት ለምሳሌ
በውልደት፣ በሞት፣ ወዘተ ምክንያት እና ይኸው ለውጥ ከቀበሌ ማዐጤመ ፅ/ቤት ወደ ወረዳ
ማዐጤመ ፅ/ቤት ሪፖርት ሲደረግ አዲሱ/ለውጡ በተጠቃሚዎች መዝገብ ላይ ከሰፈረ በኋላ
የማዐጤመ መታወቂያ ካርዱን በተለወጠው መረጃ መሰረት ወቅታዊ ማድረግ አስፈላጊ
ይሆናል፡፡
• ለምሳሌ አንድ ህፃን በአባሉ ቤተሰብ ውስጥ ቢወለድ አዲስ የተወለደው ህፃን የግል መረጃ ለዚሁ
ጉዳይ ተብለው በመታወቂያ ካርዱ ላይ ከተዘጋጁ ገፆች በአንዱ ላይ ይሰፍራል፡፡
• በተመሳሳይ አንድ የቤተሰቡ አባል በሞት ቢለይ የሟችን የግል መረጃ የያዘው ገፅ ላይ ሟች
ከዚህ በኋላ ተጠቃሚነቱ መቆሙን ለማመልከት የተሰረዘ ወይም የማያገለግል የሚል ምልክት
ይደረግበታል፡፡

34
Health Sector Financing
Reform Project

3. የማዐጤመ ተቀምን ፋይናንስ መቀበልና ማስተዳደር


የወረዳ ማዐጤመ ተቋም ፈንድን ከተለያዩ ምንጮች ይሰበስባል፤
የሚከተሉትንም ያካትታል፡-
• ከከፋይ አባላት የሚሰበሰብ የመመዝገቢያ ክፍያ
• ከከፋይ አባላት የሚሰበሰብ መዋጮ
• ከቅጣት ክፍያዎች
• ድሃ ተኮር ድጎማ (መክፈል ለማይችሉ አባላት)
• አጠቃላይ ድጎማ
• እርዳታ (ካለ)
• የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ (ካለ)
• ከሌሎች የገቢ ምንጮች

35
Health Sector Financing
Reform Project

3. የማዐጤመ ተቀምን ፋይናንስ መቀበልና ማስተዳደር …

3.1 ከቀበሌ ማዐጤመ ክፍሎች የሚመጣውን ገንዘብ ስለማስተዳደር

• የወረዳው ማዐጤመ ፅ/ቤት ከቀበሌ የሚቀርቡትን ማስረጃዎች/ሰነዶችን ትክክለኛነታቸውን


በማረጋገጥ የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ (ተገደ) በማዘጋጀት ለቀበሌው የማዐጤመ ፅ/ቤት ይሰጣል፡፡
• የወረዳ ማዐጤመ ክፍሎች ከቀበሌ የሚመጡትን ሰነዶች ማለትም ገንዘብ የተሰበሰበባቸውን
የገቢ ደረሰኝ ሁለተኛ ቅጂ፣የገቢ ማጠቃለያ ቅጽና ገንዘቡ ገቢ የተደረገበትን የባንክ
አደቫይስ/የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ደረሰኝ ከተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ/ተገደ/ ጋር በማያያዝ
በጥንቃቄ ፋይል ያደርጋል፡፡

36
Health Sector Financing
Reform Project

3. የማዐጤመ ተቀምን ፋይናንስ መቀበልና ማስተዳደር …


3.2 ከሌሎች የገቢ ምንጮች ገንዘብ ስለመቀበል
• ድሃ ተኮር/ተናጠል/ ድጎማ ፡-መክፈል ለማይችሉ አባላት የወረዳ አስተዳደር የሚያደርገው ድጋፍ
ነው፡፡
• አጠቃላይ ድጎማ ፡- በፌደራል መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ክፍያው በክልል ጤና ቢሮ በኩል
የሚተላለፍ ነው፡፡ የአጠቃላይ ድጎማ መጠን ስሌት የሚሆነው የጠቅላላ አባላትን (የከፋይ
አባላት እና መክፈል የማይችሉ አባላት) ጠቅላላ የመዋጮ ክፍያ መጠን የተወሰነ መቶኛ ነው፡፡
• የተናጠል ድጎማና አጠቃላይ ድጎማ ለማዐጤመ ተቋማት የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ሲደረግ
የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት በሂሳብ ቋት ውስጥ እንዲካተት ያደርጋል፤የገቢ ደረሰኙንም
ገንዘቡን ላስተላለፈው አካል እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

37
Health Sector Financing
Reform Project

3. የማዐጤመ ተቀምን ፋይናንስ መቀበልና ማስተዳደር …


3.3 የባንክ ሂሳብ ቁጥር መክፈት እና ገንዘብ ማስቀመጥ
• ማዐጤመ ተቋሙ የሚሰበስበው ገንዘብ በሙሉ በባንክ/ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ውስጥ
የሚቀመጥ ይሆናል፤ ስለዚህ በወረዳው ውስጥ በአቅራቢያው በሚገኝ ባንክ/ማይክሮ ፋይናንስ
ውስጥ በተቋሙ ስም የባንክ ሂሳብ ይከፈታል፡፡
የባንክ ሂሳብ ስለመክፈት
• ማዐጤመ ተቋሙን የሚያስተዳድረው መ/ቤት ሃላፊ ለማዐጤመ ተቋሙ በስሙ የባንክ ሂሳብ
ይከፈትለት ዘንድ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ባንክ ያመለክታል፡፡
• የሂሳብ ቁጥሩ ፈራሚዎች የሚሆኑት የአስፈፃሚው መ/ቤት ሃላፊ እና የወረዳው ማዐጤመ
ፅ/ቤት ቡድን መሪ ይሆናል፡፡ በጊዜ ሂደት የፈራሚዎች ለውጥ የተከሰተ እንደሆነ የአስፈፃሚው
መ/ቤት ሀላፊ ለባንኩ የተከሰተውን የፈራሚዎች ለውጥ እና ለውጡ ተግባራዊ የሚሆንበትን
ቀን ወዲያውኑ ለባንኩ ያሳውቃል፡፡

38
Health Sector Financing
Reform Project

4. ከጤና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ውል መዋዋል


ብቃት ያላቸውን የጤና አገልግሎት ሰጪዎች መለየት

• የማዐጤመ ተቋማት በወረዳው ውስጥ ወይም በአቅራቢያው ከሚገኙ የጤና አገልግሎት


ሰጪዎች ውስጥ ብቃት ያላቸውን በመለየት የአገልግሎት አሠጣጥ ውል ይዋዋላሉ፡፡
• በማዐጤመ ተቋሙና በአገልግሎት ሰጪው መካከል የሚደረገው ስምምነት ዓላማ የሚሆነው
የጤና አገልግሎት ሰጪው ለማዐጤመ ተቋሙ አባላት የጤና አገልግሎት መስጠት ሲሆን
ማዐጤመ ተቋሙ ደግሞ ለአባላቱ ለተሰጠው የጤና አገልግሎት ክፍያን መፈፀም ይሆናል፡፡
የውል ስምምነት ናሙናውን ይመልከቱ፡-

39
Health Sector Financing
Reform Project

5. የክፍያ ጥያቄን መቀበል፣ መመርመር እና ክፍያን መፈፀም


5.1 የክፍያ ጥያቄን መቀበል
• የማዐጤመ ተቋሙ እና የጤና አገልግሎት ሰጪዎች በገቡት የውል ስምምነት መሰረት
የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የክፍያ መጠየቂያ ሰነዶችን የሩብ ዓመቱ ከተገባደደ በኋላ
ባሉት አስር ቀናት ውስጥ ለማዐጤመ ተቋሙ ያቀርባሉ፡፡
• የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የክፍያ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ በተጠቃለለ/በተቀናጀ
ሁኔታ ይሆናል (የአገልግሎት ፍጆታ ሪፖርት - አፍሪ ይጠቀማሉ)፤ ማለትም
የአገልግሎት ፍጆታ ሪፖርት ቅፅ ላይ በመሙላት ያቀርባሉ፡፡
• ይህ ቅፅ ሁለቱ ወገኖች የውል ስምምነት ሲፈራረሙ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች
የማዐጤመ ተቋሙ ተጠቃሚዎች የተጠቀሙትን አገልግሎቶች መዝግበው ሪፖረት
ያደርጉበት ዘንድ ማዐጤመ ተቋሙ ለጤና አገልግሎት ሰጪዎች ይሰጣቸዋል፡፡
የአገልግሎት ፍጆታ ሪፖርት ቅፅን ይመልከቱ፡-

40
Health Sector Financing
Reform Project

5. የክፍያ ጥያቄን መቀበል፣ መመርመር እና ክፍያን መፈፀም ...


የአገልግሎት ፍጆታ መዝገብ (በተቋሙ የሚያዝ 3ኛው መዝገብ)
• የማዐጤመ ተቋሙ በበኩሉ በአገልግሎት ሰጪዎች የሚቀርብለትን የአገልግሎት ፍጆታ ሪፖርት
(አፍሪ) በመረጃ ማጠናቀሪያ መዝገብ ላይ አስፍሮ ይይዛል (የአገልግሎት ፍጆታ መዝገብ
ይይዛል)፡፡
• በማዐጤመ ተቋሙ የአገልግሎት ፍጆታ መዝገብ (ዳታቤዝ) ላይ የሚያዘው መረጃ ለማዐጤመ
ተቋሙ የሚከተሉትን ለማወቅ ያስችለዋል፡-
• ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የሚጠቀሙትን የጤና አገልግሎት ዓይነት
• የጤና አገልግሎት ወጪ በእያንዳነዱ የአገልግሎት ዓይነት
• የአጠቃቀም ምጣኔ (ከተጠቃሚዎች ሲሰላ)
• የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የውል ስምምነቱን በማክበር ስለመተግበራቸው
• ከጤና አገልግሎት ሰጪዎች መካከል በብዛት በተጠቃሚዎች የሚዘወተረውን
• የህመም ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ተጠቃሚዎችን ዕድሜና ፆታ፣ ወዘተ

41
Health Sector Financing
Reform Project

5. የክፍያ ጥያቄን መቀበል፣ መመርመር እና ክፍያን መፈፀም ...


5.2 የክፍያ ጥያቄን መመርመር
የክፍያ ጥያቄን አግባብ ያለውና ትክክለኛ መሆኑን መመርመር የሚከተሉትን
ያካትታል፡-
• በሪፖርቱ የተጠቀሰው የተጠቃሚዎች ስም እና መለያ ቁጥር አግባብ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ
• የተጠቀሱት ተጠቃሚዎች የወቅቱን የሩብ ዓመት ክፍያ የከፈሉ (active) መሆናቸውን ማረጋገጥ (ከክፍያ
መዝገብ ጋር ማስተያየት)
• የተጋነነ የክፍያ መጠን በሪፖርቱ ውስጥ ከተጠቀሰ አገልግሎት ሰጪው ለምን ከፍ ያለ መጠን እንዳቀረበ
ምክንያት እንዲገልፅ ይጠየቃል
• በሪፖርቱ ውስጥ የቀረበው የተጠቃሚዎች ብዛት ከተለመደው መጠን ከፍተኛ ሆኖ ከተገኘ የሪፖርቱ
ትክክለኛነት በናሙና ዳሰሳ እንዲረጋገጥ ይደረጋል (ማለትም ከተጠቃሚዎች ውስጥ የተወሰኑትን
እንደናሙና በመምረጥ በሪፖርቱ እንደቀረበው አገልግሎት ማግኘት አለማግኘታቸውን በመጠየቅ
ማረጋገጥ ማለት ነው)
• አንዳንድ ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ በአገልግሎት ሰጪው ድርጅት ዘንድ በአካል በመገኘት (ኢንስፔክሽን)
የሪፖርት አቀራረቡን ትክክለኛነት ማለትም በሪፖርቱ የቀረበውን እና የተጠቃሚዎችን የግል የህክምና
ካርድ በማስተያየት አግባብነቱን በምርመራ ማረጋገጥ
42
Health Sector Financing
Reform Project

5. የክፍያ ጥያቄን መቀበል፣ መመርመር እና ክፍያን መፈፀም ...


5.3 ክፍያን መፈፀም

• የማዐጤመ ተቋሙ ለአባላት ለተጠው አገልግሎት የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበ ከጠቅላላ ክፍያው
75% ወዲያውኑ ይከፍላል፤የተቀረውን 25% ደግሞ የአገልግሎት ሰጪው የክፍያ መጠየቂያ
ሪፖርት አግባብነትና ትክክለኛነት ከተረጋገጠ በኋላ በአስር ቀናት ውስጥ የሚከፍል ሲሆን
ተቀባይነት የሌላቸውን ሂሳቦች በማስላት ከክፍያ ጥያቄው ላይ ተቀናሽ ያደርጋል፡፡
• ማዐጤመ ተቋሙ ማናቸውንም ክፍያ የሚፈፅመው ከባንክ ሂሳብ ቁጥሩ በባንክ ዝውውር
ይሆናል፡፡
• በባንክ ዝውውር ለተደረገው ክፍያም ተገቢው የክፍያ ሰነድ ይዘጋጃል፡፡

የክፍያ ሰነድን ይመልከቱ፡-

43
Health Sector Financing
Reform Project

6. የማዐጤመ የሂሳብ አያያዝ ዑደት (ሽክርክር)


የማዐጤመ የሂሳብ አያያዝ ዑደት ምንነት
• የማዐጤመ የሂሳብ አያያዝ ዑደት በስራ እንቅስቃሴ ሂደት የተዘጋጁ መነሻ ሰነዶችን መሰረት
በማድረግ በተቋሙ የተፈፀሙ ሁሉንም የሂሳብ እንቅስቄሴዎች የመመዝገብ፣ ዝውውር
የማድረግ እና ማጠቃለያ ሪፖርቶች ማዘጋጀት ያጠቃልላል፡፡
• የተጠቃለለ ገቢ ደረሰኝ (ተገደ)፣ የክፍያ ሰነድ እና የጆርናል ቫውቸር የሂሳብ እንቅስቃሴዎች
ልውውጦችን ለመመዝገብ በግብዓትነት የሚያገለግሉ ጠቃሚ መነሻ (ምንጭ) ሰነዶች ናቸው፡፡
(የሰነዶቹን ይዘት ይመልከቱ)

44
Health Sector Financing
Reform Project

የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ አያያዝ……የቀጠለ

የማዐጤመ የሂሳብ ሽክርክር/Accounting Cycle/

የሂሳብ የሂሳብ የሂሳብ ሌጀር የሙከ


የማስተካከ
ምዝገባ እንቅስቃ ካርዶች ያ

መነሻ ሴ ምዝገባዎ
ሚዛን
ሰነዶች መዝገብ ች ጊዜያዊ ሂሳቦችን
መዝጋት

የመስሪያ ቅጽ

የሂሳብ መግለጫዎች
45
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት


የሂሳብ ሪፖርቶች
• የማዐጤመ ተቋሙ በአንድ የሂሳብ ዘመን ያከናወናቸውን የሂሳብ እንቅስቃሴዎች
በማጠቃለል የተቋሙን የመጨረሻ ውጤት ያሳያሉ፡፡
• የማዐጤመ ተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ውጤቶች የጠራ ምስል እና ያለበትን የሂሳብ
ሁኔታ ለተቋሙ የስራ አመራርና ለባለ ድርሻ አካላት ያሳያል፡፡
• በተጠቀሰው የሂሳብ ጊዜ የተካሄዱ ልውውጦችን አጠቃሎ በሚያሳይ መልኩ በአጭሩ
መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
• በአጠቃላይ የሂሳብ ሪፖርቶች የማዐጤመ የሂሳብ አያያዝ ሂደት የመጨረሻ ውጤቶች
ናቸው፡፡
 

46
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


የሂሳብ ሪፖርቶች አላማዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
• ለማዐጤመ የስራ አመራርና ቦርድ ለዕቅድ ዝግጅትና ውሳኔ የመስጠት ስራ የመረጃ ምንጭ
በመሆን ያገለግላሉ፡፡
• ለሁሉም የማዐጤመ ባለድርሻ አካላት (ቦርድ፣ የስራ አመራር፣ አባላት፣ ወዘተ) የተቋሙን
የገቢ እና የወጪ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለመገምገም እና ትንበያ ለማድረግ
አስሰፈላጊውን መረጃ ይሰጣሉ፡፡
• እንዲገለፁ፣ እንዲገመገሙ፣ ትንበያና ግምት እንዲሰጣቸው በሚፈለጉ ጉዳዮች ዙርያ
የተወሰዱ ታሳቢ ሁኔታዎችን በግልፅ ለማሳየት በምንጭነት ያገለግላሉ፡፡
ለማዐጤመ ተቋም ጠቃሚ እና አግባብነት ያላቸው የሂሳብ መግለጫዎች፡-
• የገቢና የወጪ መግለጫ
• የሃብት እና እዳ መግለጫ

  47
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


7.1 የገቢና ወጪ መግለጫ ማዘጋጀት
• የገቢና ወጪ መግለጫ የማዐጤመ ተቋም የስራ እንቅስቃሴ ውጤትን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
• በተቋሙ በአንድ የሂሳብ ዘመን (ወር፣ሩብ ዓመት ወይም ዓመት) የተገኘ ገቢን እና የተደረገ
ወጪን በማነፃፀር ያሳያል፡፡
• በተቋሙ ገቢና ወጪ መካከል ያለው ልዩነት የተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ውጤት ያሳያል፡፡
• የገቢና ወጪ መግለጫ በእያንዳንዱ ወር፣ ሩብ ዓመትና ዓመት መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
 

48
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


የማዐጤመ የገቢ ምንጮች የሚከተሉትን ያካትታል፡-
• የመመዝገቢያ ክፍያ
• መዋጮ
• ቅጣት
• ድሃ ተኮር ድጎማ
• አጠቃላይ ድጎማ
• ዕርዳታ
• የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ
• ሌላ ገቢ

የማዐጤመ ተቋም ወጪዎች ለህክምና ጤና አገልግሎት የሚደረጉ ክፍያዎች ናቸው


• የማማከር ክፍያ
• ላብራቶሪዎቸ
• የኢሜጂንግ አገልግሎቶች
• ፕሮሲጀሮች/ቀዶ ጥገና
• መድሃኒቶችና አላቂ ዕቃዎች
• አልጋ/የሕሙማን መስተንግዶ
• ሌሎች ወጪዎች
49
 
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …

ማስታወሻ፡
• የማዐጤመ ተቋማት በወረዳም ሆነ በቀበሌ ደረጃ በነባር የመንግስት ፅ/ቤት ውስጥ
በመሆን ስራቸውን የሚያከናውኑ በመሆኑ የአስተዳደርና የስራ ማስኬጃ ወጪዎች
ማለትም የደመወዝ፣ አበል፣ የመጓጓዣ እና የቀን ወጪዎች፣ የቢሮ መገልገያ ቋሚና
አላቂ ዕቃዎች፣ ግብዓቶች፣ ወዘተ በሚመለከታቸው የመንግስት ፅ/ቤቶች የሚሸፈን
ይሆናል፡፡

የገቢና ወጪ መግለጫ ቅጹን ይመልከ፡-

50
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


 በጠቅላላ ገቢና ወጪ መካከል ያለው ልየነት ብልጫ ወይም ጉድለት ይሆናል፡፡
• ጠቅላላ ወጪ ከጠቅላላ ገቢ ሲበልጥ ጉድለት ይባላል፤ በተቀራኒው ከሆነ ደግሞ
ብልጫ ይባላል፡፡
• ማዐጤመ ተቋም አዎንታዊ ውጤት (ብልጫ) እንዲኖረው ጥረት ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
• ይህ ብልጫ ግን ትርፍ ለሚያስገኙ አገልግሎቶች መዋል የለትም፤ ይልቁንም
የተቋሙን ፋይናንስ ዘለቄታዊነት ለመደገፍ በተቀማጭነት ይቀመጣል፡፡
• ብልጫም ሆነ ጉድለት ወደ ተቀማጭ ሂሳብ የሚደመር ይሆናል፡፡
 

51
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


7.2 የሃብት እና ዕዳ ሂሳብ መግለጫ ማዘጋጀት
• የሃብትና እዳ ሂሳብ መግለጫ ማዐጤመ ተቋም በአንድ የሂሳብ ዘመን ማብቂያ (የወር፣ የሩብ
ዓመት እና/ወይም ዓመት መጨረሻ) ያለውን የሂሳብ/የገንዘብ አቅም ደረጃ ለማሳየት
ይጠቅማል፡፡
• የሃብትና ዕዳ መግለጫ በሂሳብ ዘመኑ መጨረሻ የማይዘጉ የሂሳብ ሚዛኖችን ማለትም ሃብት፣
ዕዳዎች እና የተጣራ ሀብት ሂሳብ ሚዛኖችን ለማወቅ ያስችላል፡፡
• እነዚህ ሂሳቦች በሃብት እና እዳ ሂሳብ መግለጫ የሚታዩ በመሆኑ በተለምዶ የሀብት እና ዕዳ
ሂሳብ መግለጫ ሂሳቦች ተብለው ይጠራሉ፡፡
 

52
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


የሃብት ሂሳቦች ከማዐጤመ አግባብ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
• በገንዘብ ማስቀማጫ ውስጥ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ
• በባንክ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ
• የሚሰበሰብ ገንዘብ/ሃብት
• አላቂ ዕቃዎች
• ቋሚ ዕቃዎች
• ሌሎች ንብረቶች
እዳዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
• ብድር
• የሚከፈሉ ዕዳዎች
የተጣራ ሀብት ሂሳቦች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
• መጠባበቂያ
• በመጠባበቂያ ላይ የሚታይ ለውጥ
53
Health Sector Financing
Reform Project

7. የማዐጤመ ተቋም የሂሳብ ሪፖርቶች ማዘጋጀት …


• በመሰረታዊ የሂሳብ አያያዝ መርህ መሰረት የሚከተለው የሂሳብ ዐረፍተ ነገር ሁልጊዜ
በእኩልነት መታየት አለበት፡-
ሀብት = ዕዳዎች + የተጣራ ሀብት
• ሃብት ማለት የተቋሙ አጠቃላይ ንብረት ሲሆን፤ የተጣራ ሀብት ማለት የተቋሙ ንብረት
ከዕዳዎች ውጪ ያለው እንዲሁም እዳዎች ደግሞ ተቋሙ መክፈል ያለበት እዳ ማለት ነው፡፡
• በመጠባበቂያ ላይ የሚታይ ለውጥ በተቋሙ በአንድ የሂሳብ ዘመን የስራ እንቅስቃሴ የተገኘን
ብልጫ ወይም ጉድለት ያሳያል፡፡ የዚህም ሚዛን በሀብትና ዕዳ ሂሳብ መግለጫ ላይ በመጠባበቂያ
ሂሳብ ውስጥ ተጠቃሎ ይታያል፡፡
(የሀብትና ዕዳ መግላጫ ይዘትን ይመልከቱ)

54
Health Sector Financing
Reform Project

8. የማዐጤመ ተቋም ስራ አንቅስቃሴ ሪፖርት ማዘጋጀት


8.1 ስለተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሪፖርት
• ስለተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሪፖርት የሚከተለውን መረጃ ማሳየት ያስችላል
• በወሩ መጀመሪያ ያሉ አባላትና ተጠቃሚዎች
• አዲስ የተመዘገቡ አባላትና ተጠቃሚዎች
• በወሩ ውስጥ ከተቋሙ ያቋረጡ አባላትና ተጠቃሚዎች
• በወሩ መጨረሻ ያሉ አባላትና ተጠቃሚዎች

• ይህን አሃዛዊ መረጃ ከተጠቃሚዎች ወርሃዊ ማጠቃለያ መዝገብ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወርሃዊ የተጠቃሚዎች ማጠቃለያን ይመልከቱ፡-

55
Health Sector Financing
Reform Project

8. የማዐጤመ ተቋም ስራ አንቅስቃሴ ሪፖርት ማዘጋጀት …


ወርሃዊ የተጠቃሚዎች ማጠቃለያ
• ወርሃዊ የተጠቃሚዎች ማጠቃለያ (ወተማ) በአባላት ቁጥር ዙሪያ ያለውን ለውጥ ለመፈተሸ
ጠቃሚ ነው፡፡
• በየወሩ ያለውን የአባላት ቁጥር እድገትና ያለውን የአዲስ ተመዝጋቢዎች እና ያቋረጡ አባላት
ሁኔታ ለማየት ያስችላል፡፡
• የወረዳውን ማዐጤመ ተቋም ለማስተደደር ካለው ጠቀሜታ በተጨማሪ ይህ መረጃ
በእያንዳንዱ ቀበሌ ያለውን የአዲስ አባላት ምዝገባ ሁኔታ ለመከታተል እንዲሁም በወረዳው
መካሄድ ያለበትን የቅስቀሳና አድቮኬሲ ስራ ጠቋሚ ነው፡፡
• ከዚህ በተጨማሪ በየወሩ ያለውን የተጠቃሚዎች ቁጥር ማወቅ
• በገቢ ማሰባሰብ፣
• በጤና አገልግሎት አጠቃቀም፣
• የነፍስ ወከፍ አማካይ ወርሃዊ ወጪ፣ ወዘተ
የመሳሰሉ ጠቋሚዎችን ለማስላት መሰረት (ዲኖሚኔተር) ይሆናል፡፡
56
Health Sector Financing
Reform Project

8. የማዐጤመ ተቋም ስራ አንቅስቃሴ ሪፖርት ማዘጋጀት …


8.2 ስለመዋጮዎችና የመመዝገቢያ ክፍያዎች የሚቀርብ ሪፖርት
ወርሃዊ የመዋጮና የመመዝገቢያ ክፍያዎች ማጠቃለያ
• ወርሃዊ የመዋጮና የመመዝገቢያ ክፍያዎች ማጠቃለያ በእያንዳንዱ ቀበሌ ያለውን የመዋጮና
የምዝገባ ክፍያ መረጃ በአንድ ላይ ሰብስቦ ለመያዝ ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡
• ይህ ማጠቃለያ በማዐጤመ የሂሳብ ሪፖርቶች የተቀመጠውን የገቢ መጠን በተጓዳኝ የመዋጮና
የምዝገባ ክፍያዎች ማጠቃለያ የተገኘውን ውጤት ጋር ለማነጻጸር ይጠቅማል፡፡
• ከዚህ በተጨማሪ የረጅም ጊዜ ትርፋማነት ሬሾ፣መዋጮዎች ከወጪ ጋር ያላቸውን ግንኙነት
የሚያሰላ ሬሾ የመሳሰሉትን አመላካቾች ለመለካት ያገለግላል፡፡

ወርሃዊ የመዋጮና የመመዝገቢያ ክፍያዎች ማጠቃለያ ይመልከቱ፡-

57
Health Sector Financing
Reform Project

8. የማዐጤመ ተቋም ስራ አንቅስቃሴ ሪፖርት ማዘጋጀት …


8.3 ስለአጠቃቀም የሚቀርብ ሪፖርት
ወርሃዊ የጤና አገልግሎት አጠቃቀም ሪፖርት በሁለት መንገድ ተጠቃሎ ሊቀርብ
ይችላል፡-
• ለአገልግሎቶች ፍጆታ የወጣ የወጪ ማጠቃለያ በእያንዳንዱ ቀበሌ
• ለአገልግሎቶች ፍጆታ የወጣ የወጪ ማጠቃለያ በእያንዳንዱ አገልግሎት ሰጪ ተቋም

• ወርሃዊ የአገልግሎት ፍጆታ ማጠቃለያ በቀበሌ እና በአገልግሎ ሰጪዎች የወጣውን ወጪ


አጠቃሎ ለማቅረብ ጠቃሚ ነው፡፡
• ይህ ማጠቃለያ በማዐጤመ የሂሳብ ሪፖርቶች የታዩ ወጪዎችን በአገልግሎት ፍጆታ ማጠቃለያ
ከቀረቡት ወጪዎች ጋር ለማነፃፀር ይጠቅማሉ፡፡
• ከዚህ በተጨማሪ በማጠቃለያው በጥቅል የሚታዩ አሃዞች የማዐጤመ ቁልፍ መለኪያ
መስፈርቶች ናቸው፤ ምክንያቱም በርካታ የማዐጤመ ክትትልና ግምገማ ጠቋሚዎች በእነዚህ
አሃዞች ላይ ተመስርተው የሚሰሉ ናቸው፡፡
ወርሃዊ የአገልግሎት ፍጆታ ማጠቃለያ በቀበሌ እና በአገልግሎት ሰጪ ይመልከቱ፡- 58
Health Sector Financing
Reform Project

9. የማዐጤመ ተቋም ዕቅድ እና በጀት ማዘጋጀት


በጀት ማለት የማዐጤመ ተቋም በተወሰነ የጊዜ ገደብ (በአብዛኛው ጊዜ አንድ ዓመት)
ለማከናወን የታቀዱ የስራ እንቅስቃሴዎችን ለመፈፀም በተሟላ (ምሉዕ) እና ይፋዊ
በሆነ መንገድ አሃዛዊና በሚለኩ ነጥቦቸ የሚገለፅ እቅድ ነው፡፡
የበጀት ዋነኛ አላማዎች
• ዝርዝር የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት
• ቅንጅታዊ አሰራር፣ ትብብርና የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር
• የስራ አፈጻጸም ግምገማ ለማድረግ የሚያስችል ማዕቀፍ ለማግኘት
• የማዐጤመ ተቋም ወጪዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር
የበጀት ዝግጅት ሁለቱ መሰረታዊ ተግባራት እቅድ ዝግጅትና ቁጥጥር ናቸው፡-
• እቅድ ዝግጅት ከመጀመሪያ የሃሳብ ጥንሰሳ እስከ የበጀት ዝግጅት ድረስ ያሉትን ሁሉንም ሂደቶች
ያጠቃልላል፡፡ በጥንቃቄ የተዘጋጀ እቅድ ለሁለተኛው የበጀት ተግባር (ማለትም የቁጥጥር ስራ) ክንውን
ማእቀፍ ያበረክታል፡፡
• ቁጥጥር በተግባር በተጨባጭ የተገኙ ውጤቶችን በበጀት ከተቀመጠው አሃዝ ጋር ለማነፃፀር
ያስችላል፡፡ በዚህ ረገድ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ለመገምገም እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልዩነቶች
ላይ ማስተካከያ በማድረግ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል፡፡
59
Health Sector Financing
Reform Project

9. የማዐጤመ ተቋም ዕቅድ እና በጀት ማዘጋጀት …


9.1 የበጀት ዝግጅት
• በጀት በማዐጤመ ተቋም የስራ አስፈፃሚዎች ከተዘጋጀ በኋላ በማዐጤመ ቦርድ ይፀድቃል፡፡
• በጀትን የመጠቀም ትኩረት/ፍላጎት በተለይ የአፈፃፀም ክትትል ላይ ያጠነጥናል፡፡ የበጀት
አፈፃፀም ክትትል ለማዐጤመ እንደሌሎች መስሪያ ቤቶች ሁሉ በስራ እንቅስቃሴ
ያስቀመጣቸውን እቅዶች እውን የማድረግ ተግባሩን በየጊዜው ከሚገኙት ውጤቶች አንጻር
ለመፈተሸ የተለየ ጠቀሜታ አለው፡፡
• በጀት በሁለት ክፍሎች በድጋሚ ተቧድነው የተቀመጡ የሂሳብ ትንበያዎች ያቀርባል፡፡
• እነዚህም
• የገቢ ትንበያ (የገቢ ዓይነቶች)
• የወጪ ትንበያ (ለአገልግሎት ሰጪዎች የሚደረጉ ክፍያዎች) ናቸው፡፡

• የማዐጤመ በጀት በተቋሙ ስራ አመራር ክትትል ለማድረግ እንዲያስችል በየወሩ ተከፋፍሎ


መቀመጥ አለበት፡፡
የበጀት ዝግጅት ቅፆችን ይመልከቱ፡-
60
Health Sector Financing
Reform Project

9. የማዐጤመ ተቋም ዕቅድ እና በጀት ማዘጋጀት …


• የበጀት ዝግጅት ለዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት መስጠትን ይጠይቃል፤ በመሆኑም በበጀት ዝግጅት
ላይ የሚሳተፉ ሁሉ ጠቃሚ ነገሮችን/እርምጃዎችን እንዳይዘሉ/እንዳይተው ጥንቃቄ ማድረግ
ያሻል፡፡
• በጀት በሚያዘጋጁበት ወቅት የሚከተለውን ዝርዝር የማገናዘቢያ ነጥብ ይጠቀሙ፡-
• ተግባራትን በዕቅድ ያስፍሩ
• የገቢ ርእሶችን ያዘጋጁ
• የወጪ ርዕሶችን ያዘጋጁ
• ረቂቅ በጀቱን ለግብረ መልስ ያቅርቡ
• የገቢና ወጪ በጀትን በማጠናቀቅ ለአጠቃቀም ዝግጁ ያድርጉ
• በመጨረሻ የማዐጤመ ተቋም የስራ አስፈፃሚ የተዘጋጀውን በጀት ለክለሳ ለቦርድ ያቀርባል፡፡
በጀቱ በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይፀድቃል፡፡ በጠቅላላ ጉባኤ በጀቱ ከጸደቀ በኋላ በተቋሙ ስራ
አስፈፃሚ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
• ምክኒያታዊና ትርጉም ያለው የበጀት ዝግጅት በጀቱ ተግባራዊ ከሚሆንበት ዓመት አስቀድሞ
መጀመር አለበት፡፡ በጀቱ ተግባራዊ ከሚሆንበት ዘመን ቢያንስ አንድ ወር በፊት መጠናቀቅ
ይኖርበታል፡፡
61
Health Sector Financing
Reform Project

9. የማዐጤመ ተቋም ዕቅድ እና በጀት ማዘጋጀት …


9.2 የሩብ ዓመት እርምዳት ሪፖርቶች (የበጀት ቁጥጥር)
• የበጀት ዝግጅት ቁጥጥር ተግባር ጠቃሚው ነገር በተጨባጭ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችን
(እርምዳት ሪፖርቶች) በበጀት እቅዱ ከተያዘው መረጃ ጋር ማነጻጸር ነው፡፡
• የእርምዳት ሪፖርቶች በዕቅድ ከተያዘው የጊዜ ገደብ (በየሩብ ዓመቱ) በጀትና በተግባር የተገኙ
የአፈጻጸም ውጤቶች ጋር በማነጻጸር ይቀርባሉ፡፡
• የሩብ ዓመት የእርምዳት ሪፖርቶች በበጀት እና በተግባር በተገኙ ውጤቶች መካከል ያለውን
ልዩነት ለማሳየት ይዘጋጃሉ፤ ማለትም ተጨባጭ የተገኘውን የአፈፃፀም ውጤት በተጓዳኝ
ከተዘጋጀ እቅድ ጋር በማነጻጸር በማሳየት ማለት ነው፡፡
• በእቅድ በተያዘው በጀት እና በተግባራዊ አፈጻጸም መካከል ከፍተኛ ልዩነት ካለ በጥንቃቄ
ተመርምሮ ለስራ አመራር ብሎም ለቦርድ ቀርቦ አግባብ ያለው ውሳኔ እንዲሰጥበት መደረግ
ይኖርበታል፡፡

የሩብ ዓመት እርምዳት ሪፖርት ማዘጋጃ ቅፅን ይመልከቱ፡-

62
Health Sector Financing
Reform Project

አመሰግናለሁ!!

63

You might also like