1st Year Theory Power Point

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 23

1.1.

የንድፈ ሀሳብ/የትውር (Theory) ምንነት


 ንድፈ ሃሳብ የተለያዩ ነገሮችንና ክስተቶችን በማገናዘብ ሥርዓት
ባለውና በተጠቃለለ መልክ የሚገለጽ ወይም የሚያብራራ በተግባር
ያልተፈተነ እውቀት ነው፡፡

 ሥርዓቱ የሚገለጸው በንድፈ ሀሳቡ ሥነ አመክንዩ ባህሪ ሲሆን


የተለያዩ ነገሮችንና ክስተቶቸን የሚያገናዝብ በመሆኑ ደግሞ
የማጠቃለል ተግባር አለው፡፡

 ንድፈ ሀሳብ ከጽንሰ (Concept) ሀሳብ የሚለየው የተለያዩ


ነገሮችን የማገናዘብና የማጠቃለል ባህርይ ስላለው ነው፡፡

 ጽንሰ ሀሳብ በተወሰኑ ነገሮች መካከል ያለውን የወል ጠባይ


የሚገልጽ ሲሆን ንድፈ ሀሳብ ደግሞ የተለያዩ ጽንሰ ሐሳቦችን
የሚያቅፍና የሚያዋቅር ነው፡፡
…የቀጠለ
 በአጠቃላይ ንድፈ ሃሳብ/ቲዎሪ ሲባል ምንድን ነው? ብለን ስንጠይቅ
በክስተቶችና በነገሮች፣ በዛፎች ፣በሰዎች፣ በአገሮች፣ በክዋክብት፣
በባህል መካከል ያሉ ዝምድናዎችን የሚያጠና፣ የሚያሳይ፣ የሚተነትን፣
… ሲሆን ስለነገሮች ሁኔታ፣ ትንበያ፣ ግምት፣ መላምት የሚሰጥ ነው፡፡

 ንድፈ ሀሳብ በሚያካልለው ይዘት የተለያዩ ደረጃዎችን ይዞ እናገኛለን፡፡


እነዚህም ፡-

ንዑስ ደረጃ (micro level)፣


መካከለኛ ደረጃ (meso level) እና
ከፍተኛ ደረጃ (macro level) ናቸው፡፡
1.2. የንድፈ ሀሳብ/ትውር (Theory)፤ ቅርጾች (Form
of Theory)
 የተለያዩ ተመራማሪዎች ንድፈ ሀሳቦቻቸውን በተለያዩ መንገዶች
ይገልጻሉ፡፡ ከነዚህ መንገዶች መካከል መላምንት፣ አመክኗዊ ገለጻ ወይም
ቀመራዊ ሞዴሎች (Visual Models) ተጠቃሽ ናቸው፡፡

 በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የንድፈ ሀሳብ አይነት መላምንት ሲሆን፣


የተወሰኑ ተመራማሪዎች ንድፈ ሀሳባቸውን ተያያዥነት ባለው መላምንት
ያስቀምጣሉ፡፡

 ሶስተኛው የንድፈ ሀሳብ አይነት አንድ ተመራማሪ ንድፈ ሀሳቡን በሞዴል


መልክ ሊያቀርበው የሚችለው ነው፡፡

 በአጠቃላይ መላምቶችም ሆኑ ጥያቄዎች የሚገኙት ከንድፈ ሀሳብ ሲሆን


በውስጣቸውም በተመራማሪዎች የሚፈተሹ ተለዋዋጮች አሏቸው
(Creswell, 2003, 128-32)፡፡
1.3. የንድፈ ሀሳብ /ትውር (Theory) ጠቀሜታ በምርምር

 የምርምር ችግርን ለመለየት፣ የትኛው ችግር ሊፈታ እንደሚገባ ግብ


ለማስቀመጥ ያለው ጠቀሜታ ነው፡፡

 የምርምሩ ችግር ትኩረት፣ ግብ ለመወሰን እና ለመበየን ያስችላል፡፡

 የንድፈ ሀሳብ ጠቀሜታ በምርምሩ የመረጃ ተገቢነት ላይ እና የንድፈ


ሀሳቡ የዕድገት ደረጃው ላይ ይወሰናል፡፡

 ንድፈ ሀሳብ አራት የእድገት ደረጃዎች አሉት፡፡ እነዚህም ክስተቶችን


መግለጽ፣ ክስተቶችን ማብራራት፣ ግንኙነቶችን መተንበይ፣ ክስተቶችን
እና ግንኙነትን መቆጣጠር ናቸው (Akintoye, 2015)፡፡
…የቀጠለ
 በመጠናዊ ምርምር (Quantitative Research) ተመራማሪዎች
መላምቶችንና ጥያቄዎችን ለመፈተሸ ፤እንዲሁም የተለዋዋጮችን
ግንኙነት ለማብራራት ሲሉ ንድፈ ሀሳብን ጥቅም ላይ ያውላሉ፡፡

 በዓይነታዊ ምርምር (Qualitative Research) ግን ይህ ሁኔታ የተለየ


ነው፡፡

 በመጠናዊ ምርምር ንድፈ ሀሳብን መሰረት ተደርጎ ሲሠራ፤ በዓይነታዊ


ደግሞ ንድፈ ሀሳብ ለማፍለቅ እና ከሥርዓተ ጾታ፣ ከመደብ፣ ከዘር እና
ከማህበራዊ ደረጃ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለማንሳት እና ለመመለስ
ሲባል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

 በተለይ ይህ ተግባራዊ የሚሆነው በኢትኖግራፊ ጥናት ሲሆን


በግራውንድ ንድፈ ሀሳብ ጊዜ ንድፈ ሀሳቡ የሚፈልቀው መጨረሻ ላይ
ከጥናቱ ነው፡፡
1.1. የስርፀታዊ/ ስርጭታዊ/ታሪካዊ-ጂኦግራፊያዊ /ፈለግ (Diffusion / Historical-Geographical
/Approach) ፤

 በ1870ዎቹ በፊላንድ አገር የተጀመረ ሲሆን፣ ዘዴውንም ያስተዋወቁት ጁልየስ


ክሮህንና ልጁ ካርል ክሮህን ናቸው፡፡

 የስርጭት ቲዎሪ የተጀመረው በ19ኛው ምዕተ ዓመት መጨረሻ በ20ኛው


ክፍለ ዘመን መጀመሪያ (ከ1890-1910) ነው፡፡

 ዘዴው Finnish Historical-Geographic Method፣ Finnish Method፣


Historic Geographic Method፣ Comparative Method እንዲሁም
Typological Method በመባል ይታወቃል (ቨርታነን፣ 443)፡፡

 ይህ ዘዴ የተለያዩ የፎክሎር ዘርፎች ከዚህ በፊት የነበራቸውን ቅርጽ (original


Form)፣ የተፈጠሩበት ቦታ፣ የተፈጠሩበትን ጊዜ፣ የነበራቸውን ምንጭና ታሪክ
በማነጻጸር ጥልቅ ጥናት ማካሄድ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው፡፡
…የቀጠለ
 ፈለጉን በተመለከተ በመስኩ ምሁራን ዘንድ የተለያዩ የክርክር ሀሳቦች
ቀርበዋል፡፡ የክርክር ሀሳቦቹ መሰረት የሚያደርጉት በታሪካዊ ጂኦግራፊያዊ ዘዴ
ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡

 ክሮህን፣ አንደርሰን፣ ቶምሰን፣ ስዋህን እና ቮንሳይድ የተሰኙት ምሁራን በዘዴው


ላይ ጥብቅና ሲቆሙ ሌሎች ደግሞ ማለትም፤ ታይሎር፣ ቭላድሚር ፕሮፕ፣
ጆንሰን እና ጎልበርግ በዘዴው ላይ የተለያዩ ትችቶችን ሲያቀርቡ ይታያሉ፡፡

 የክርክራቸውም ማጠንጠኛ መሰረት የሚደርገው በፎክሎር ዘርፎች በተለይም


ሥነ ቃል ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

 አንድ ሥነ ቃል የት እና እንዴት ይፈጠራል? ከተፈጠረ በኋላ ያለውስ ህልውና


ምን ይመስላል? በክዋኔው ዙሪያ ያሉ ሁኔታዎች ወይም ማህበረ-ባህላዊ
መልኮች ምን ይመስላል? የአንድ ተረት ተፈጥሮ አንድ ነው ወይስ ፈርጀ ብዙ
ነው የሚሉት ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡
…የቀጠለ
 በዚህ ዘዴ መሰረት አሁን የምናገኛቸውና በተለያዩ አካቢዎች በተለያየ
መንገድ የሚቀርቡ የሥነ ቃል ክፍሎች መገኛ ምንጫቸው አንድ ቦታ እና
ጊዜ ነው የሚል ማጠቃለያ አለው፡፡

 የዚህም አንድምታው እውቀትም ሆነ ፈጠራ የሚመነጨው ከአንድ


አካባቢ ነው፡፡ የለተያዩ አካባቢዎች ሊገኙ የቻሉት በሞገድ መሰል
ስርጭት ነው፡፡ የስርጭት መነሻውም አውሮፖ ነው ወደ እሚል
ማጠቃለያ ይደርሳሉ፡፡

 ይህ ዘዴ በተወሰኑ አካባቢዎች በሚገኙ ሥነ ቃል አይነቶች ብቻ ተወስኖ


ይጠና የነበረውን ጥናት በማሻሻል በተለያዩ አካባቢዎችም የሚገኙ
የፎክሎር ዘርፎች እንዲጠኑና በየአካባቢው አንድ አይነት ፎክሎር
ሳይሆን የተለያዩ አይነቶች እንዳሉ እንዲታወቁ ማድረግ መቻሉ ዘዴውን
በአዎንታ የሚያስጠቅሰው ተግባር ነው፡፡
…የቀጠለ
 ይህ ንድፈ ሃሳብ፡-
1. ዝግሞታዊ ቲዎሪ ትክክል አይደለም፤ማስተካከያ ያስፈልገዋል ከሚለው
አስተሳሰብ ነው የተነሳው፡፡ ብዙዎቹ ምሁራን ከዚያው ከቦታው ተሂዶ
ይጠናል እንጂ እንዲያው ከቢሮ ቁጭ ተብሎ በተቀመረው ነገር ላይ
አይጠናም ይላሉ፡፡ ስለዚህ Inductive እንጂ Deductive ዘዴ መሆን
የለበትም ይላሉ፡፡
2. ሌላው ሁለተኛው ነገር የአውሮፓ ብቻ ለምን? የሌሎች ሀገራትም
መጥፎውም ሆነ ጥሩው መጠናት አለበት ባይ ናቸው፡፡ ሌላውና ዋናው ጉዳይ
ግን በቅኝ ግዛት ላይ በዓለም ዙሪያ ተቃውሞው እያየለ መምጣት ነበር፡፡
3. የሀሳባቸው ማጠንጠኛ /Premise/ መላምት ባህል በዓለማችን ላይ ከአንዱ
ቦታ ወደሌላው ቦታ ሂዶ/ ተሰራጭቶ/ ይገኛል የሚል ነው፡፡ ይህም የኢንዶ
አውሮፓውያን እውቀት ነው ይላሉ፡፡ ህንድ ሀገር ቡዲሂዝምን ወስደው
በጥንታዊ የንግድ ግንኙነት በየደረሱባቸው ቦታዎች የቃል ትረካቸውን
ወስደዋቸዋል የሚል ነው፡፡
…የቀጠለ
4. ሶስተኛው Premise ደግሞ ጦርነት ነው፡፡ ካምባይሲስ የተባለ ግሪካዊ ወደ35
ሀገራትን ያስገብር ነበር፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ እውቀት ተሰራጭቷል ማለት
ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ቄሳሮች በኢምፓየር ግዛትን በማስፋት የአውሮፓ
እውቀት ብዙ ሂዷል ብሎ የማሰብ ነገር ነው፡፡

5. ሌላው Premise የሃይማኖት ሰዎች ወደሌላው ተንቀሳቅሰው ዕውቀትን


ተምረው ይመጡ ነበር፡፡ ከኢትዮጵያም ወደግሪክ ሄደው ጥበብን ተምረው የመጡ
ሰዎች እንደነበሩ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

6. ሌላው Premise ስደት ነው፡፡ ይህንን ቲዎሪ የስርጭት ቲዎሪ ነው ስንል የባህል
ስርጭት ማለታችን ነው፡፡ አውሮፓውያን ወደኢትዮጵያና ወደሌሎች አገሮችም
ውስጥ መጥተው አጥንተው ከየት ተነስቶ የት እንደሄደ ከዚያም የት እንደደረሰ
ናሙና በመውሰድ መነሻውን ያጠናሉ፡፡ መልእክቶቹንም ይጨምቁና ያነጻጽራሉ፡፡
በየአገራቱ እየዞሩ ይተረጉማሉ፡፡ ያነጻጽራሉ፡፡ ይተነትናሉ፡፡ Bascom አንዲትን
ተረት መነሻ በማድረግ ለማረጋገጥ 42 አገራትን ዞሯል፡፡
…የቀጠለ
የዚህ ንድፈ ሃሳብ/ቲወሪ ጥንካሬ፤
 Comparative Cultural study በባህል ላይ የንጽጽር ጥናት
አካሂደዋል፡፡ በዚህም ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ቲዎሪውን በጣም
ነው ያሣደጉት፡፡ ተመሳሳይነቱን በ Comparative፣ ልዩነቱን ደግሞ
በContrust አሳይተዋል፡፡ በንጽጽር ሥራቸው ላይ Motif አውጥተዋል፡፡
 Motif ማለት የባህሉን ዋና ወይም ቁልፍ የሆነ ሀሳብ አንድ አረፍተ ነገር
በማይሞላ ሀሳቡን ማውጣትና ልክ እንደ ርዕስ አድርጎ ማስቀመጥ ነበር፡፡
Values / እንደሚሉት ዓይነት በIndex ማስቀመጥ ነው፡፡ Index ደግሞ
ማብራሪያ አለው፡፡
 Philologyን አጠናክሯል፡፡ Philology የሃይማኖትንና የቋንቋን ዝምድና
ስለሚያጠና በዚህ ውስጥ ይካተታል፡፡
 ድክመቱ ደግሞ የተወሰነ የዓለማችንን ክፍል እንደመነሻ አድርጎ
መውሰዱ ነው፡፡
1.2. አዝግሞታዊ ለውጥ ትውር/ፈለግ (Evolutional
Theory/Approach)
 በዚህ ቲዎሪ ፎክሎር የታየበት አቅጣጫ ነው፤በ1818 ጀምሮ ነው ይህ
ቲዎሪ የተነሳው፡፡

 የፎክሎር ጥናት በንድፈ ሃሳብ ደረጃ መጠናት የተጀመረው በአዝግሞተ


ለውጥ ፈለግ አማካኝነት ነው፡፡

 ከዚያ በፊት ግን የአውሮፓ ብሄርተኝነት ተስፋፋ፡፡ በየሀገራቱ መካከል


የብሄርተኝነት ጥያቄዎች ተነሱ፡፡ በዚህ የብሄርተኝነት ጥያቄ የድንበር
ማካለል ስለተጀመረ የእኔ ወሰን እስከዚህ ድረስ ነው፤ እስከዚያ ድረስ ነው
ማለትን አስነሳ፤የሉዓላዊነትን ጥያቄ መጣ፡፡
…የቀጠለ
 በሀገራቱ መካከል ፉክክር አመጣ፡፡ ፉክክሩም ጤናማ አልነበረም፡፡
ግጭትን፣ ጦርነትን፣ ወዘተ. አስከተለ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ዞሮ ዞሮ
አተኩረው የነበሩት በማንነት ጥያቄ ላይ ነበር፡፡ እኛ ከመቼ ወዲህ
ከእናንተ ጋር ተዋውቀን እናውቃለን፡፡ ዝምድና የት አለን የሚሉትን
መሰረት አድርጎ መጠየቅ ተጀመረ፡፡

 የዚህን ልዩነትና ተመሳሳይነት ለማወቅ ፎክሎር የመረጃ ምንጭ


በመሆን አገለገለ፡፡ ይህ በሚት እንዲህ የሚል አለ አይደል እንዴ፤ ይሄ
በአፈ ታሪክ እንዲህ ይል የለም ወይ ማለትን አስከተለ፡፡ በአጠቃላይ
ጥንተ አመጣጥን መመርመር ተጀመረ፡፡ የእነሱን ጀግንነት፤ ታላቅነት
ማመልከት ጀመሩ፡፡ ይህ ደግሞ በፎክሎር ላይ ምሁራን እንዲያተኩሩ
አደረጋቸው፡፡
…የቀጠለ
 የአዝግሞተ ለውጥ ቲዎሪ የተነሳው የዳርዊንን ንድፈ ሀሳብ ተከትሎ
ነው፡፡ ዳርዊን በስነ ፍጥረት ላይ ባደረገው ጥናት የአዝግሞተ ለውጥ
ቲዎሪ መጣ፡፡ ‹‹ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል፡፡›› እንደሚባለው ቀስ
በቀስ የሰው ልጅ እየተለወጠ እንደሄደ የሚያሣይ ሲሆን ይህም በብዙ
ሚሊዮን ያስቆጠረ ሂደት ነው፡፡

 የዳርዊን (1809-1882) ቲዎሪ በመጣበት ጊዜ ነበር ዝግመታዊ ለውጥ


ቲዎሪ የተነሳው፡፡

 ይህንን ቲዎሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀነቀኑትና የጀመሩት ሁለት ሰዎች


ናቸው፡፡ ቅኝ ግዛትን ማስፋፋት፣ ሀብት ፍለጋ… ስለነበር
ከኮሎኒያሊዝም አይዲዮሎጂ ጋር የተጣመረ ስለሆነ ይሄንን ለማገዝ ነው
የተመሰረተው፡፡ መስራቾቹም፡-
…የቀጠለ
1ኛ፡- Lewis Henry Morgan (1818–1881) የነበረ በአሜሪካ ውስጥ
Cultural Evolutionism የሚል ትምህርት ቤት አቋቋመ፡፡

2ኛ፡- Sir Edward Burnett Tylor (1832–1917) በጣም ግዙፍ የሆኑ


ሥራዎችን አቅርቧል፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የአንድ ዘመን ሰዎች ናቸው፡፡
ታይለር Primitive Societies የሚል መጽሐፍ አሳተመ፡፡ እነዚህ ሁለት
ሰዎች ለሁለት ክፍለ ዘመናት ያህል ብዙ ምሁራንን አፈሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች
በመስራችነት ይጠቀሳሉ፡፡

 በተለይ በMorgan መጽሃፍ ውስጥ የምናገኘው ህብረተሰብ ሦስት


የአዝግሞተ ለውጥ ደረጃዎች እንዳሉትና እነዚህንም ደረጃዎች ማለፍ
እንዳለበት አስረድቷል፡፡ መስመራዊ የሆኑ የህብረተሰብ ደረጃዎቹም
የአዝግሞተ ለውጥ ደረጃዎች ይባላሉ፡፡ እነሱም፡-
…የቀጠለ
 Savagery ፤ የአህዛባውያን
 Barbarism ፤የባርባሪዝም
 Civilization ፤የስልጣኔ ናቸው፡፡

 Savagery፡- ከእንስሳት ያልተለየ፤ደመነፍስ የሆነ ነው፡፡


 Barbarism፡- ከእንስሳት የተለዬ ግን ያልሰለጠነ ነው፡፡
 Civilization፡- በዚህ የስልጣኔ ደረጃ ፊደል ተቀርጾ ጽሕፈት
የተጀመረበት ዘመን ነው፡፡ በየድንጋዩ፣ በየዋሻው… ላይ መጻፍ
የተጀመረበት፣ ህግን (ሀሞራቤን)፣ አንድን የከተማ አስተዳደር
የመፍጠር፣ ሃይማኖትን የመከተል ነገር ተጀምሯል፡፡ በፎክሎር በዛፍም
በጊንጥም… ይታመን ሁሉም እምነት እኩል ነው፤ አንድ ነው፡፡ ‹‹The
greatest Religion, Folk Religion>> እየተባለ ድንበር ይጣልበታል፡፡
…የቀጠለ
 በአጭሩ በCivilization ደረጃ ለቋንቋው ፊደል ተቀርጾ ጽህፈት
ሲጀምር ነው፡፡ ከተማን መቆርቆር፣ አስተዳደር ሲገነባ፣ ህግ ሲኖረው፣
ማህበረሰብ ሲፈጠር ነው፡፡ ይህ ደረጃ እስካሁን ድረስ ያለውን
ያካትታል፡፡

 የባህል አዝግሞተ ለውጥ ምሁራን አውሮፓን ያዩት ፊደል ቀርጾ


ጽሕፈት ስላለው፣ የማምረቻ መሣሪያዎች ስላሉት፣ የሰለጠነ ዓለም
ነው ሲሉ ሌላውን ግን ሳቬጅና ባርባሪዝም ብለው ከፈሉት፡፡

 ምእራቡን ግን የሥልጣኔ ብርሃን አድርገው ቆጠሩት፡፡ ሌላውን ዓለም


ደግሞ ወደ Civilization እንዲመጣ ቅኝ አገዛዝ በጣም አስፈላጊ ነው
ብለው አረጋገጡ፡፡ የሳቬጅና የባርባሪዝም እምነት በዘንዶ፣ በውሃ፣
በዛፍ፣..ስለነበረ ይህንን ተከታይ ሁሉ በሰለጠነው ሃይማኖት መተካት
አለበት አሉ፡፡
…የቀጠለ
 ለማጠቃለል ያህል፡- Cultural Evolution Theory ባህርያቱ፡-

1. በዚህ ቲዎሪ አተያይ ሁሉም ባህሎች በተመሳሳይ የዕድገት ደረጃዎችና


በተመሳሳይ በቅደም ተከተል ሥርዓቶችና እርከኖች ያልፋሉ የሚል አቋም
ያለው ነው፡፡
2. መስመርን ተከትሎ አንድ አቅጣጫ የሚሄድ አዝግሞተ ለውጥ አለ፡፡ ይሄ
ደግሞ ክዝቅተኛው ወደከፍተኛው ወይም ወደተሻለው አቅጣጫ
የሚያመራ ነው፡፡
3. ይህ የአጠናን መንገዱ Deductive የሚባለው ነው፡፡ ከአጠቃላይ ቲዎሪ
ወደዝርዝር፣ ወደአንድ ወደተለየ ጉዳይ የሚያመራው ቲዎሪውን
ለማረጋገጥ ነው ማለት ነው፡፡
4. የአፍሪካ ህዝቦች ባርበሪክ ናቸው ካለ የሚለካቸው በሳቬጀሪ ነው ፡፡ አፍሪካ
ሃይማኖት የለውም፡፡ ስለዚህ ሃይማኖት ቢኖረው ሊሰለጥን ይችላል፡፡
ጣሊያኖች ኢትዮጵያን የወረሩት ክርስቲያን ለማድረግ ነው ብለው ነበር፡፡
ግን አገሪቷ ከዚያ በፊት ክርስቲያን ነበረች፡፡
…የቀጠለ
5. አውሮፓ ተኮር ነው፡፡ EuroCentric ይባላል፡፡ አውሮፓን ልክ እንደጸሐይ ነው
የሚያያት፡፡ ሌላው ዓለም ሰለጠነም አልሰለጠነም በአውፓውያን ችሮታ ነው፡፡
Ethno Centric ነው፡፡ የእነሱን ሀገር ባህል፣ ቋንቋ፣ ህጎች፣ ሁሉንም የዕድገት
መገለጫዎች እንደ ትልቅ ነገር ነው የሚቆጥረው፡፡

 አዝግሞተ ለውጥ ከ200 ዓመታት በላይ በጣም ተሰራጭቶ ዓለምን


አጥለቅልቆ ነበር፡፡ ከቅኝ ግዛት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሠራ ቲዎሪ ነው፡፡

 አፍሪካ ማጥ ውስጥ ነው ያለችው፡፡ አሁንም ከማጡ አትወጣም፡፡ ብዙ ጥረት


ይጠይቃታል፡፡ ራሷን እንዳትችል የምትተማመንበት ነገር በውስጧ የላትም፡፡
ምርጫ እንኳን ሳይቀር በአውሮፓውያን በራሳቸው ፍላጎት ስር ነው፡፡

 በምእራብ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ህዝቦች ራሳቸውን ከፍ ያደረጉ እየመሰላቸው


ራሳቸውን ረስተው ሌላውን ሰላም ሲሉ የፈረንሳይኛ ተናጋሪ ነን ይላሉ፡፡ እኛ
ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች ባንገዛም ከተጽዕኖው አልተረፍንም፡፡
…የቀጠለ
 አሁን Neo Cultural Revolution ላይ ነን፡፡ ድሮ ከነበረው ሉላዊነት ላይ
ስለሆን ማለት ነው፡፡ ለፎክሎር የተሰጠው ብያኔ ከሁለት አቅጣጫ ነው፡፡
ይሄውም የአውሮፓውያን እውቀት የዓለም ብርሃን ተደርጎ ተወስዷል፡፡

 የአፍሪካው ግን ጨለማ፣ ለእድገት ለመሻሻል የማይጠቅም፣ እንቅፋት


ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ፎክሎሩ ግን የሳቬጀሪና የባርባሪዝም ተደርጎ
ሲወሰድ ነቀፌታ ስለበዛ ከላይ ያሉትን አትባሉም፡፡ ግን Primitive,
Uncivilized ናችሁ ብለዋል፡፡ ይህም የ3ኛው ዓለም መገለጫ ነው፡፡
…የቀጠለ

 በኋላ ደግሞ ኋላ ቀር ባህል ተባለ፡፡ አሁን በምንገኝበት ክፍለ ዘመን ላይ


ደግሞ Illitrate ተባለ፡፡ ጎጂ ባህል መባል መጣ፡፡ ሱርማዎች ሳግኒ
የሚባል በዓመት 3 ጊዜ በብትር የመደባደብ የጨዋታ በዓል አላቸው፡፡
አንዱ መንደር ከሌላው መንደር ጋር እየተጋጠሙ በመወዳደር
ይጫወታሉ፡፡

 አሸናፊው ቡድን የአካባቢውን ሰላም ያስጠብቃል፡፡ እነዚህ ብሄረሰቦች


ራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ ነው ይህንን የሚያደርጉት፡፡ ይህንን
አይረባም አይባልም፡፡ ተደባድቦ ከተሸነፈ ሚስቱ ትፈታዋለች፤ ይናቃል፤
ፈሪ ተደርጎ ይቆጠራል፤ ያላገባም ሚስት አያገኝም፡፡ ከሰፈርም ሊባረር
ይችላል፡፡ ይህንን የመሳሰሉ ጨዋታዎች በአውሮፓም ይከናወናሉ፡፡
…የቀጠለ

 በዚህ ንድፈ ሃሳብ/ቲዎሪ ውስጥ ፎክሎር የተበየነው ተቆፍሮ እንደተገኘ


አፅም ነው፡፡ ጥንት የነበረ ማለት ነው፡፡ ደንደስ 1965 Intrpreting
Folklore ፤Ben Amos Foklore in text 1984 አንብቡ፡፡ ይህ ቲዎሪ
ከባህል ልማት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው፡፡
አመሰግናለሁ!!!!

You might also like