የዓለም ቤተክርስቲያን ታሪክ

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 30

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአለም መድረክ


መቅድም
•የቤተክርስቲያን ታሪክ ማለት የክርስትና እምነት ታሪክ ማለት ነው፡፡
በቤተክርቲያን ታሪክ ትምህርታችን የክርስትና እምነት የአምላክ
መገለጥ ነው፡፡ ይህም ማለት የክርስትና ሃይማኖት መሠረትና ፍጻሜ
የአምላክ በሥጋ ተገልጦ ፣ ተወልዶ ፣ ዓለሙን ማዳኑ ነው፡፡ ከዚህ
የተነሳም የክርስትና ሃይማኖት የመገለጥ ሃይማኖት ነው ይባላል፡፡
….የቤተክርስቲያን ታሪክ….
•በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን በጉዞ ላይ የገጠማትን ችግርና ምቾት
የምንማርበት ነው፡፡
•ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተው በሐዋርያት ፣
በሰማዕታት ፣ በሊቃውንት ፣ ምስክርነት የተገለጸው ፣ ለህዝብም
ለአህዛብም የተሰበከውን መልካም መንገድ ኤር 6÷16
ቤተክርስቲያናችን የምትከተል ስለሆነ የቤተክርስቲያን ልጆች ይህን
ተምረው ማወቅ ማሳወቅ ብሎም መጠበቅና ማስጠበቅ
ይገባቸዋል፡፡
ምዕራፍ አንድ
የቤተክርስቲያን ስያሜና ትርጓሜ

ሀ. የቤተክርስቲያን ትርጓሜ

 በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ‹‹ቤተክርስቲያን ›› የምንለው የክርስትና


ሃይማኖት ነው፡፡ ቃሉም የግዕዝ ሲሆን በሦስት መልክ ይተረጎማል

1. የተለየ ቤትን ያመለክታል -- ቤተ ጸሎት ማቴ 18÷20

2. ክርስቲያኖችም ቤተክርስቲያን ይባላሉ ሐዋ 5÷11

3. የክርስቲያኖች አንድነት (ማህበር) ቤተክርስቲን ይባላል


ምሳሌ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክ/ያን ሲል የክርስቲያኖችን አንድነትን ያሳያል
ለ. የቤተክርስቲያን ስያሜ

• ቤተክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ግዕዛን ካላቸው ፍጥረታት (ከመላዕክትና

ከሰው) ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ ---ሃይማኖትም ይባላል

የቤተክርስቲያን ዕድሜ በሦስት ይከፈላል

1. ሰው ከመፍጠሩ በፊት በዓለመ መላዕክት የነበረችው የመላዕክት አንድነት ፤

2. ከአዳም ጀምሮ እስከ ሐዲስ ኪዳን መግቢያ የነበሩ የደጋግ ሰዎች አንድነት፤

3. በክርቶስ ደም የተመሰረተችው የክርስቲያኖች አንድነት ናት


በክርስቶስ ደም የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን ፡-

• አንዲት ናት 1ኛቆሮ 4÷5


• የአንድ የክርስቶስ አካል ናት ቆላ 1÷18
• ቅድስት ናት ኤፌ 5÷26
• የሁሉና በሁሉ ያለች ናት ፤ ገላ 3÷25-29
• ሐዋርያዊት ናት
• በሰማይም በምድርም ያለች ናት
ሐ. የቤተክርስቲያን ታሪክ ምናጭ

1. የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ፤


2. የቤተክስቲያን አባቶች የጻፏቸው መጻህፍት ፤
3. በየጊዜው የተደረጉ ጉባኤዎች ውሳኔዎችና ሕጎች፤
4. በቁፋሮ የተገኙ መቃብሮች ፤ ቤተመቅደሶች ፤ ሥዕላቶች ፤
…. 
መ. የቤተክርስቲያን ታሪክ አከፋፈል

1. ጌታ ቤተክርስቲያን በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ከመሰረተበት


ዘመን ጀምሮ እስከ ታላቁ ቁስጥንጢኖስ ድረስ -እስከ 305
ዓ.ም.
2. ከታላቁ ቆስጠንቲኖስ መነሳት ጀምሮ ቆስጥንጥንያ በቱርኮች
እጅ እስከ ወደቀችበት ጊዜ ( ከ305 ዓ.ም. -1445 ዓ.ም. )
3. ቆስጥንጥንያ በቱርኮች ከተያዘችበት ጀምሮ እስካለንበት ዘመን
ድረስ ( ከ1445 ዓ.ም. – 2005 ዓ.ም. )
ሠ. የቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ጠቀሜታ
 

ከዓለም ታሪክ አንደኛውን ክፍል ያዞ ስለሚገኝ ፤


የህዝቦችን የስልጣኔ እርምጃና ታሪክ ለማጥናት፤
የእምነታችንን ታሪክ ለማወቅ ፤
በአባቶቻችን ትምህርት የህዝቡ ጠባይ እንዴት እንደተሻሻለ
ለማወቅና
ራስንና ክርስቲያን ወገኖቻችን በእግዚአብሔር መንገድ ለመምራት
ይጠቅማል፡፡
ምዕራፍ ሁለት
አምሳል ወትንቢት በእንተ ቤተክርስቲያን

• አምሳል፡- ማለት ወደፊት ለሚሆን ድርጊት (ዘግየት ብሎ ለሚመጣ አንድ


አማናዊ ድርጊት እንደ ጊዜያዊ ምትክ የሆነና ታሪክ የሚገለጥበት
ማስረጃ ነው፡፡

• በብሉይ ኪዳን የሌዋውያን መሥዋዕት ለሐዲስ ኪዳን እውነተኛው


የክርስቶስ ክቡር ሥጋና ቅዱስ ደም ምሳሌ ነው፡፡

• ትንቢት፡- የዓለም መድህን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጡን


(መምጣቱን)የሚያበስሩት በቅዱሳት መጻህፍት የሰፈሩ ትንቡቶች ናቸው፡፡

 
የብሉይ ኪዳን ታሪክ

1. ዓለመ መላዕክት
2. የ22ቱ ደጋግ አባቶችታሪክ - ከአዳም እስከ ያዕቆብ
3. ዘመነ መሳፍንት- ከሙሴ-ሳሙኤልና ቶላ
4. ዘመነ ነገስት -ከሳያል እስከ ሲዬቅያስ
5. ዘመነ ነቢያት (ካህናት) ከሲዴቅያስ በኃላ እስከ ልደተ
ክርስቶስ
 
ምዕራፍ ሦስት
አማናዊት ቤተክርስቲያን

• በአምላክ ሰው መሆን የአማናዊት ቤተክርስቲያን ታሪክ ይጀምራል፡፡

• የክርስትና ታሪክ በምድረ ፍልስጤም ተጀመረ

ሦስቱ ማህበራት

ሀ- ፈሪሳውያን

• የሙሴን ህግና የነቢያትን መጻህፍት እንጠብቃለን የሚሉ;

• የመሲህንም መምጣት ተግተው የሚጠብቁ;

• ከትንሳኤ በኃላ ጋብቻ አለ ብለው የሚያምኑ ;


ለ- ሰዱቃውያን
• ለባህል ፣ ለስነሥርዓትና ለሃይማኖት ግድ የሌላቸው
• የሙሴን ህግ ብቻ የሚቀበሉ
• የሙታንን ትንሳኤና የመሲህን መምጣት የማያምኑ ናቸው

ሐ--ኤሴዎች
• በተዓምራት በእግዚአብሔር ኃይል አገራችን ነፃ ትወጣለች ብለው
የሚያምኑ
• መጻህፍት በመጻፍና ጸሎት በማድረስ ብዙ ጊዜ የቆዩ
• መሲሃዊ መንግስት እንደሚያቋቁሙና እነርሱም የመንግስት
ባለሟሎች እንደሚሆኑ የሚያምኑ ናቸው
 
የኢየሱስ ክርስቶስ የዘመነ ሥጋዌ ጉዞ

• ብስራት
• የኤሳቤጥ ምስክርነት
• የክርስቶስ ልደት
• የስምኦን አረጋዊ ምስክርነት
• የጌታችን ስደት ወደ ግብጽ
• የጌታችን የህፃንነቱ ጊዜ
• የክርስቶስ ጥምቀት
• የክርስቶስ ጻም
• የመጀመሪያ ተዓምር

• የክርስቶስ ትምህርትና ተዓምር

• የምስጢረ ቁርባን አመሰራረት

• የክርስቶስ መያዝና መከራ መስቀል መቀበል


• የጌታችን መቀበርና ትንሳኤ

• የጌታችን ዕርገት
የክርስትና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ መግባት

• ክርስትና በ34 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ገባ

• የኢትዮጵያ ሐዋርያ ባኮስ ይባላል


• በ328 ዓ.ም. መንበረ ጵጵስና አገኘች
• በ350 ዓ.ም. በአብርሃና አጽብሃ ዘመን ክርስትና ብሔራዊ
ሃይማኖት እንደሆነ ተደነገገ
 
ምዕራፍ አራት
ቤተክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት እስከ ሐዋርያን አበው

• ሀ. ቤተክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት

በዓለ ጰራቅሊጦስ
• ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን ከሙታን በተነሳ በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በእሳት
አምሳያ ወረደባቸው
• በሐዋርያትና በዕለቱ ከተጠመቁ 3000 ሰዎች የመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን
ተመሰረተች
• ይህ ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ነው በማለት ዮሐንስ አፈወርቅ
አስተምሯል፡፡
ለ. አስራ ሁለቱ ሐዋርያት
1 - ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
2 - ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወ/አብዴዎስ
3 - ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ
4 - ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
5 - ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ
6 - ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሚዎስ
7 - ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ
8 - ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ
9 - ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወ/እልፍዮስ
10-ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ
11-ሐዋርያው ቅዱስ ስምዖን (ቀኖናዋ)
12-ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ
የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ሕይወት

1. ከሰዓት በኃላ ጊዜ ወስነው በማርቆስ እናት እየተሰበሰቡ


የሐዋርያትን ትምህርት ያሰሙ ነበር (ሐዋ 12÷12)
2. የወንጌልን ትምህርት በተለይም የክርስቶስን ትንሳኤ
አይተው ያረጋገጡ መሆናቸውን
3. ከብሉይ ኪዳን ስለመሲህ የሚናገሩትን ትንቢቴችን በኢየሱስ
ክርስቶስ መፈፀማቸውን አስፋፍተው ያስረዷቸው ነበር
የሰባቱ ዲያቆናት ምርጫ

• እስጢፋኖስ
• ፊሊጶስ
• ጅሮአሮስ
• ኒቁሮስ
• ጢሞና
• ጴርሜን
• ኒቆላዎስ
ሀ. እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማዕት

• በመንፈስ ቅዱስ በመመራት በየምኩራቡ እየዞረ ለአይሁድ


ዓለምን ለማዳን ስለመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳን
እያጣቀሰ ያስተምራቸው ነበር
• አይሁድ ተቃዋሚዎችንም መልስ ያሰጣቸው ነበር
• ሕገወጥ በሆነ መንገድ ይዘው ከሰሱት ፣ መሰከሩበት
• ከከተማም አውጥተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት (ሐዋ 7÷56)
ለ. ቅዱስ ፊሊጶስ

• በስደቱ ወደ ሰማርያ በመጓዝ አስተምሮ ፣ ታምራትንም


በማድረግ ብዙ ሰዎችን አጥምቋል
• ከሰማርያም ያገኘውን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አጠመቀው

 
የሐዋርያት ሲኖዶስ

• ስለ ነገራተ ቤተክርስቲያን የሚሰበሰቡ የቤተክርስቲያን


አባቶች ጉባኤ ነው
• ስለ ስርዓተ ቤተክርስቲያን
• ስለ ካህናት አገልግሎት

• ስለ ቤተክርስቲያን አስተዳደርና ውሳኔዎች ይሰጡበታል


ቤተክርስቲያን ከአይሁድ ጋር ያደረገችው ትግል

• የአማኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የአይሁድ ቁጣ ጨመረ

• ከአይሁድ ወደ ክርስትና የመጡት ሳይቀሩ አሕዛብ እንደነርሱ


የጸጋው ተካፋዮች መሆናቸው ወደ ግጨትም አደረሳቸው

• እንዲውም አህዛብን ክርስትና ከመቀበላቸው በተጨማሪ


የሙሴን ህግ መቀበልና መፈፀም አለባቸው የሚል ክርክር አነሱ

• በ50 ዓ.ም. የተደረገው ሲኖዶስ ተገቢውን ውሳኔ አስተላለፉ


ቤተክርስቲያን ከአህዛብ ጋር ያደረገችው ትግል

 በጌታችን ትዕዛዝ መሠረት ሐዋርያው በአህዛብ ምድር ወንጌል መስበክ


በመጀመራቸው የክርስትና እምነት ተስፋፋ

 የጣዖት አምልኮ በወንጌል እየተተካ መጣ

 የገባር ሥርዓት ተቀነሰ ለባሮቹ የነፃነት ወንጌል ተሰበከላቸው

 የአህዛብ ኩራትና ትዕቢት በወንጌል ፈራረሰ

 በወንጌል የመጡ ለውጦች የአህዛብን ነገስታትና መኳንንት አላስደሰታቸውም

 በሐዋርያት ላይ ክስ ፣ ስቃይና ግድያ አስከተለ


ቤተክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት አበው

 ከ70 እስከ 160 ዓ.ም. ስረስ ያለው ዘመን ነው


 ሐዋርያት አባቶች በሐዋርያት መንበር የተተኩበትና
ያስተማሩት
 መጻህፍት ጽፈው ወደ ሌላ ቋንቋ ተተረጎመበት ጊዜ ሲሆን
 በዓላውያን ነገስታት ሰይፍ ሰማትነት ተቀብለዋል

 
ምዕራፍ አምስት
ቤተክርስቲያን በዘመነ ሰማዕታት
ከ64 እስከ 313 ዓ.ም. ድረስ ያሉትን ዘመናት ያካትታል እንደ ሰማዕትነቱ
ክብደት ዘመኑ ነሁለት ይከፈላል

1. ከ64 እስከ 212 በጠቅላላው ክርስቲያኖቹን አጥፍቺው በሚል አዋጅ


ስላልታወጀ ክርስቲኖች በስቃይም በሰላምም ይኖሩ ነበር፡፡

2. ከ213 እስከ 312 ዓ.ም. ክርስቲያኖች እንደጠፉ አዋጅ የታወጀበትና


ያለርህራሄ የተጨፈጨፉበት ዘመን ነው፡፡

• ይህ ዘመን ቤተክርስቲያን ብዙውን ቅርሷን ያጣችበት ፣ በአንጻሩ

ቤተክርስቲን ከቤተ አይሁድ ወጥታ ወደ ቤተ አህዛብ የገባችበትና ጸንታ


የተስፋፋችበት ዘመን
የቀጠለ …ቤተክርስቲያን በዘመነ ሰማዕታት…

የዘመኑ ቄሳሮች
• ነሮን
• ድምጥያኖስ
• ትራጀን
• ዳክዮስ
• ድዮቅልጢያኖስ
ምዕራፍ ስድስት
ቤተክርስቲያን በዘመነ ቆስጠንጢኖስ

የሚላኖ ውል

1. በታላቁ የሮም ገዛት የሚገኙ ክርስቲያኖች እንደ ማንኛውም እምነት


ተከታዮች ሃይማኖታቸው በሚያዘው ቀኖናና ሕግ አምልኮታቸውን
ለመግለጥ ይችላሉ፡፡
2. ባለፋት ዘመናት ይሠራበት የነበረው ክርስቲያኖችን የማቃወምና
የሚያወግዝ ሕግ ከዛሬ ጀምሮ የተሻረ ነው፡፡

3. ክርስቲያኖች እምልኮታቸውን የሚገልጡበት ቦታ ቢያስፈልጋቸው በነጻ


ይሰጣቸው፡፡ የተወሰደባቸው ቦታ ካለ ካሣ ለመጠየቅ መብት አላቸው፡፡
ቆስጠንጢኖስ ለቤተክርስቲያን ካሰከበረላት መብቶቸ
ዋናዎቹ
1. ቤተክርስቲያን ከግብር ነፃ ናት
2. ከመንግስቱ ገቢ ሁሉ ለቤተክርስቲያንም የተወሰነ ድርሻ /ዓሥራት
በኩራት ቀዳምያት/ አላት፡፡
3. ዕለተ እሁድ የክርስቲያኖች የበዓል ቀን እንድትሆንና በንጉሠ
ነገሥቱም ግዛት ውስጥ ሥራ እንዳይሠራባት፡፡
4. ቤተ ክርስቲያን ኑዛዜ የመቀበል ውርስ የመውረስ መብተ አላት
5. በክርስቲያኖች መካከል ለሚፈጠሩ አንዳንድ አለመግባባቶች
ለኤጲስ ቆጶሳት የዳኝነት ስልጣን ሰጥተቸዋል

ብ ሔ
ዚ አ
እ ግ ግ ል
ለ ድ ን
ሐት ቱ ር
ብ ላ ዲ ክ ቡ
ወ ስ ወ ሉ

ወ መስ ቀ
ለ ን
ወ አ ሜ

You might also like