Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 38

የመንግስት ተቋማት የለውጥ

አመራር፣አደረጃጀትና አሰራርን ለማሻሻል


የወጣ መመሪያ
ቁጥር 50/2014
ነሐሴ/2014 ዓ/ም
በዚህ ስልጠና የሚዳሰሱ ጉዳዮች
1. የመመሪያው ዓላማ፣
2. የለውጥ መሪ ባህሪያት፣
3. የለውጥ አሰራር አቅጣጫ

4. የተቋማት ተግባርና ኃላፊነት


5. የከፍተኛ አመራር ተግባርና ኃላፊነት

6. የማኔጅመንት ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት


7. የሥራ ቡድን አደረጃጀት

8. የዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች ተግባርና ኃላፊነት


9. ድጋፍና ክትትል የሚከናወንበት ስልት፣
10. የማበረታቻ ስርዓት፣
11. በየደረጃው ያሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ተቋማት ተግባርና
ኃላፊነት
12. የተቋማት የለውጥ አመራር አደረጃጀት እና አሰራር መመሪያ ከሠራተኛ
የስራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ጋር ያለው ግንኙነት
1. የመመሪያው ዓላማ
 የተቋሙን ተግባርና ሃላፊነት ለማሳካት በለውጥ አመራር ተግባራት ታግዞ
በመተግበር ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆን ማስቻል፡፡
 በተቋሙ ውስጥ ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ከብልሹ አሰራር የጸዱ፣
ሌብነትን የሚታገሉ፣ ቁርጠኛ የሆኑ፣ ለለውጥ ዝግጁ የሆኑ፣ በሥራ
ብቃታቸውና በአርዓያነታቸው የሚታወቁ እና የተሻሉ ፈፃሚዎች ወደ
ደረሱበት ደረጃ እንዲደርሱ ማስቻል፤
የቀጠለ …
 እርስ በርስ የመማማርና የመገነባባት ባህልን ለማዳበር የመማማሪያ ሥርዓት
በመዘርጋት፣ አንዱ ያለውን እውቀትና ልምድ ለሌላው የሚያካፍልበትን ስርዓት
በመዘርጋት በፈፃሚዎች መካከል የተቀራረበ አቅም መፍጠር እና ቡድናዊ ስሜት
እንዲኖር ማስቻል፣
 በተቋሙ ውስጥ ኮከብ ሠራተኞችን በማፍራት አጠቃላይ የሰው ሃብታችንን
በማብቃትና በመጠቀም፣ አደረጃጀትንና አሰራርን በማሻሻል ዕቅድን በጥራት
በማቀድ፣ አፈፃፀምን በመገምገምና ክፍተቶችን ለይቶ በማረም እንዲሁም
የአሰራር ጥራትና ቅልጥፍናን በማሳደግ የተገልጋይን እርካታ ማረጋገጥ ነው፡፡
2. የለውጥ መሪ ባህሪያት፡-

 የተቋሙን ተልዕኮ፣ ራዕይ እና ስትራቴጅያዊ ግቦችን


በውጤታማነት የሚያሳካ፣
 የለውጥ መሳሪያዎችን በእምነት ይዞ የሚፈፅምና የሚያስፈፅም፣
 የሰው ሃይሉን በማብቃት፣ አሰራርን በየጊዜው በማሻሻል እና
አደረጃጀቱን በመጠቀም የተቋሙን እቅዶች በውጤታማነት
የሚፈፅም፣
የቀጠለ …
 የለውጥ መሳሪያዎችን በተቋሙ ወይም በቡድኑ በዘላቂነት
የሚያስተገብር፣
 እራሱን ለለውጥ ዝግጁ ያደረገና ሥራዎችን ከለውጥ ጋር
አጣጥሞ የመሄድ ብቃት ያለው፣
 በተቋሙ ውስጥና ውጭ ለሚከሰቱ የለውጥ ፍላጎቶች ፈጣን
ምላሽ የሚሰጥ፣
የቀጠለ …
ለውጡ ከሚፈልገው አዲስ አሰራር ጋር ፈጥኖ በመላመድና
ለተቋሙ ግብ ስኬቶች ዘላቂነት ጉልህ ሚና የሚጫወት፣
በሥራውና በሥነ-ምግባሩ አርአያ የሆነ፣ ተቆራርጦ በመስራት
የተቋሙን ህጎች /አሰራሮች/ በተሟላ ሁኔታ የሚፈፅምና
የሚያስፈፅም፡፡
3. የለውጥ አሰራር አቅጣጫ
 አመታዊ እቅድን በማዘጋጀት እና ለፈፃሚ አካላት በማውረድ ከሰራተኞች፣
ከአጋር አካላት፣ ከሲቪክ ማህበራት እና በተዋረድ ከሚገኙ ተቋማት ጋር
ትውውቅ ማካሄድ፡፡
 እቅድ አፈጻጸምን ከሰራተኞች፣ ከአጋር አካላት ጋር በየሩብ አመቱ፣
ከማኔጅመንት፣ ከየዳሬክቶሬት ወይም የስራ ክፍሎች ጋር በየወሩ፣
ዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች በስራቸው ካሉ ፈጻሚዎች ጋር በየ15 ቀን
መገምገም፡፡
የቀጠለ …
 በተዋረድ ከሚገኙ ተቋሞች ጋር በየሩብ አመቱ እቅድን መሰረት ያደረገ
የአፈጻጸም ሪፖርት እና ግብረ-መልስ ግንኙነት ማድረግ፡፡
 አመራር ከአመራር፣ የክልል ዳይሬክቶሬት ከዞን ቡድኖች፣ የዞን ቡድን
ከወረዳ ቡድኖች ጋር የአፈጻጸም ሪፖርት እና ግብረ-መልስ ግንኙነት
ማድረግ፡፡
የቀጠለ …
 አጠቃላይ ሠራተኞች የተቋሙን አፈፃፀም ከመገምገም አኳያ በሩብ አመት
አንድ ጊዜ ከለውጥ ተግባራት ጋር በተያያዘ ተግባራትን እንዲገመግሙ
ማድረግ፡፡
 እያንዳንዱ አመራር እና ፈፃሚ የተሰጡትን የግብ ተኮር እና የባህሪ ብቃት
እቅዶችን መነሻ በማድረግ በጋራ የመገምገም፣ ችግሮችን የመለየት እና
የመፍትሔ አቅጣጫ የማስቀመጥ ተግባር ማከናወን፡፡
የቀጠለ …
 በተግባር የተፈተሹና በስራ ላይ ያሉ አሰራሮችን በተጨባጭ ሊያሻሽሉ የሚችሉ
ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት፣ ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ መቀመርና ማስፋት
እንዲሁም ልምድ ልውውጥ ማድረግ፡፡
 የአቅም መገንቢያ ስልጠና በተለይም በሰራተኞች የእቅድ አፈፃፀም ምዘና ወቅት
የታዩ የአቅም ክፍተቶችን ለመፍታት የክህሎት፣ የተግባር እና ግምገማዊ ስልጠና
ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፡፡
የቀጠለ …
 እያንዳንዱ ሰራተኛ ከእውቀት፣ ከክህሎት፣ ከአመለካከት እና ከተልዕኮ
ውጤታማነት አኳያ ያለበትን ደረጃ ማወቅ፣ ያሉ ክፍተቶችን መሰረት
በማድረግ የእርስ በርስ የመማማሪያ ሰነድ በማዘጋጀት በየወሩ ውይይት
ማካሄድና ክፍተቶችን መሙላት፡፡
 ስራ ላይ በዋሉ ልዩ ልዩ ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ፣
የተገልጋዮችን አስተያየት በመሰብሰብ እና የህግ ሰነዶችን በማሻሻል ለተገልጋዩ
ተገቢውን ምላሽ መስጠት፡፡
የቀጠለ …

 ፈጣን ለውጥ አምጭ መሳሪያዎችን አሟልቶ አገልግሎት መስጠት ማለትም


የተቋሙ ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ ዋና ዋና ተግባራት፣ ባጆች፣ የአስተያየት
መስጫ መዛግብት፣ የአስተያየት መስጫ ሳጥን፣ ቅጻቅጾች፣ የባለጉዳይ
ማረፊያ፣ የማስታወቂያ ቦርዶች እና የአቅጣጫ ጠቋሚዎችን ማሟላት፡፡
 ለተገልጋዮች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ያመች ዘንድ ከክፍል
ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቻለ መጠን የተቀራረቡ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
የቀጠለ …

 የተገልጋዮችን አስተያየቶች በግብዓትነት መጠቀምና ግብረ-መልሱን


በማስታወቂያ ቦርዶች ላይ ይፋ ማድረግ ፡፡
 የተተኪነት አሰራርን በማጎልበት ተገልጋዮች በጊዜና በወቅቱ ቀልጣፋና
ውጤታማ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
 በአመት አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ አገልግሎት አሰጣጥን በሚመለከት
የዳሰሳ ጥናት መደረግ አለበት፡፡
የቀጠለ …

 የዜጎች ቻርተር ወይም የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በማዘጋጀት እና


እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው በመከለስ ግልጽነትና ተጠያቂነት የተላበሰ
አገልግሎት መስጠት፡፡
 በየጊዜው የሚደረጉ የስራ ግምገማዎች እና የእርስ በርስ መማማሪያ
ሰነዶች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን በሃርድ እና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ
መያዝና መጠቀም፡፡
4. የተቋማት ተግባርና ኃላፊነት
 የለውጥ መሳሪያዎች አተገባበራቸውን በየደረጃው ላሉ የሲቪል ሰርቪስና
የሰው ኃብት ልማት ተቋማት በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት ማቅረብ፤
 በተዋረድ የሚገኙ ተቋማትን መደገፍ፣ መከታተል፣ ማብቃትና ማወዳደር እንዲሁም
በየሩብ አመቱ ሪፖርት መቀበልና ግብረ-መልስ መስጠት፤

 በድጋፍና ክትትል፣ በሪፖርት እና በዳሰሳ ጥናት የሚታዩ ክፍተቶችን መሰረት


በማድረግ ስልጠና አዘጋጅቶ መስጠት፤
የቀጠለ …
 ወደ መስሪያ ቤቱ የሚቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞችን በለውጥ መሳሪያዎች
አተገባበር ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፤
 የለውጥ መሳሪያዎችን በቁርጠኝነትና በእምነት ይዞ በዘላቂነት መፈጸም፤
 እያደገ ለሚሄደው የተገልጋይ ፍላጎት ምላሽ በመስጠትና የሰራተኞችን
ክህሎት በማሳደግ በተቋሙ ውስጥ ወረቀት አልባ ግንኙነቶችን በማጠናከር
አሰራሮችን በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ማድረግ፤
የቀጠለ …

 የዜጎችን አገልግሎት እርካታ በማሳደግ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣


 የለውጥ መሣሪያዎችን በመጠቀም የስራ ክፍሉን ዕቅድ በውጤታማነት
ያከናወኑ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የለውጥ አመራር አደረጃጀትና አሠራሩ ከግብር ይውጣ የፀዳ እንዲሆን
በአንክሮ መስራት፡፡
5. የከፍተኛ አመራሩ ተግባርና ኃላፊነት
 የተቋሙ ተልዕኮና ራዕይ እንዲሳካ በየጊዜው ስትራቴጂክ አሰራሮችን
በመንደፍ ከፍ ያለ የዕቅድ አፈፃፀም እና የተገልጋይ እርካታ እንዲረጋገጥ
አቅጣጫ ማስቀመጥ፣
 በተቋሙ የለውጥ ተግባራት የዕቅድ ማስፈፀሚያ ሆነው እንዲተገበሩ ስራን
በመገመገም እና የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ውጤታማ አሰራር
እንዲኖር ማድረግ፣
የቀጠለ …
 በየሳምንቱ የተቋሙን አሰራር በመፈተሽ፣ አደረጃጀቱን በማጠናከር እና
ብቃት ያለው የሰው ኃይል እንዲፈጠር ስልት በመቀየስ ውጤታማ የዕቅድ
አፈፃፀም እንዲኖር አቅጣጫ ማስቀመጥ፣
 አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በተቋሙ አደረጃጀት
መሰረት ያሉትን ክፍተቶች በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ
ማድረግ፡፡
6. የማኔጅመንት ኮሚቴ ተግባር እና ኃላፊነት
 በየወሩ የሁሉንም የስራ ቡድን አፈፃፀም ሪፖርት በማቅረብ ውይይት
በማድረግ የተቋሙን የዕቅድ ግቦች መሳካትና አለመሳካታቸውን
መገምገም፤ አፈጻጻማቸው እንዲሻሻል አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
 በተከታታይ በተደረገው ስራን ማዕከል ያደረገ ግምገማ መሰረት ከፍተኛ
አፈፃፀም ያላቸውን የስራ ቡድኖች በመለየት በየሩብ አመቱ ያሉበትን
ደረጃ ማስቀመጥ፡፡
የቀጠለ …
 ከለውጥ ጋር በተያያዘ የሚያደርገው ውይይት የስራ ቡድን አመራር
የአመለካከት፣ የክህሎት እና የስነ-ምግባር ችግር ሊያሻሽል የሚችል እና
ሌሎች የአስተዳደር ውሳኔ ከሚጠይቁ አጀንዳዎች ጋር ሳይቀላቀል ለብቻው
ጊዜ ተመድቦለት ውይይት ማካሄድ፣
 ሌሎች አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ፕሮግራም ወጥቶላቸው
ራሳቸውን ችለው ውይይትና ግምገማ ማካሄድ፣
የቀጠለ …
 የማኔጅመንት ኮሚቴ የደረሰበትን መደምደሚያ የተቋሙ ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት
በ3 ወር አንድ ጊዜ የተደራጀ ሪፖርት ማቅረብ የልምድ ልውውጥ ማድረግ እና የተሟላ
ቁመና ያለው ፈፃሚ ለማፍራት የስራ ቡድኑ ግምገማ በቀጣይነት እንዲካሄድ ማድረግ።
 የስራ ግምገማው በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በአመለካከት እና በስነ-ምግባር ረገድ ያሉት
ክፍተቶች የሚሞሉበት የስልጠና ባህሪ ያለው እና ሰራተኞች በሙሉ ነፃነት
የሚሳተፉበት መድረክ እንዲሆን ማድረግ፡፡
7. የስራ ቡድን አደራጀጀት
 ቁጥራቸው ከ3-15 የሰው ሀይል ያላቸው ዳይሬክቶሬቶች /ቡድኖች/ በአንድ የስራ ቡድን
ተደራጅተው በየ15 ቀን ዓርብ ከሰዓት በኋላ ስራን መሰረት ያደረገ ውይይት ያደርጋሉ፡፡
 ከ3 በታች የሆኑ አባላት ከሚቀርባቸው የስራ ቡድን እንዲደራጁ ማድረግ በስራ ቡድን
ውስጥ ያሉ ሁሉም አባላት እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ እና የበለጠ በአመለካከት፣ በክህሎት
እና በውጤታማነት ረገድ ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት እና መማማር እንዲችሉ
ማድረግ፣
የቀጠለ …
 በአንድ ዳይሬክቶሬት ወይም ቡድን ስር 2 እና ከዚያ በላይ የስራ ቡድኖች ያላቸው
ዳይሬክቶሬቶች ወይም ቡድኖች በየወሩ በጋራ እየተሰበሰቡ የዕቅድ አፈፃፀማቸውን
እንዲገመግሙ ማድረግ፡፡
 ሁለትና በላይ የስራ ቡድን አደረጃጀት ሲኖር አንዱ ቡድን በዳይሬክተሩ /በቡድን መሪው/
የሚመራ ሆኖ ሌሎች ቡድኖች በስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ከፍተኛ ወይም የተሻለ
አፈፃፀም ባላቸው ባለሙያዎች እንዲመሩ ማድረግ፡፡
 ለኃላፊ ተጠሪ የሆኑ ሰራተኞች ከሚቀርባቸው ዳይሬክቶሬት /ቡድን/ ጋር በመሆን
ስራቸውን እንዲገመግሙ ማድረግ፡፡
8. የዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተግባር እና ኃላፊነት

 ዳይሬክተሮች ወይም ቡድን መሪዎች በየወሩ በለውጥ መሳሪያዎች በመታገዝ


የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሚመለከታቸው ቅርብ ኃላፊ ማቅረብ፡፡
 በየ15 ቀኑ አርብ ከሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የቡድን አባላት በሚያቀርቡት
ሪፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተመስርተው ውይይት ማድረግ፣
 ፈፃሚዎች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የዕቅድ
አፈፃፀማቸውን በመገምገም የባለሙያዎችን ደረጃ በየሩብ አመቱ ማስቀመጥ፣
የቀጠለ …
 የስራ ቡድኖች በውይይት ወቅት የሚወያዩት እንዲፈጽሙት ከተሰጣቸው ተግባራት
ውስጥ ያከናወኗቸውን አፈፃፀም፣ ያጋጠሟቸውን ችግሮች፣ የሰጧቸውን መፍትሄዎች
እና በሚቀጥለው 15 ቀን ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ጉዳዮች ለይተው ማስቀመጥ፣
 በየቡድኑ የሚካሄድ ውይይትና ግምገማ በተቻለ መጠን የሁሉንም የስራ ቡድን አባላት
አፈፃፀም ለማሻሻል የሚያግዝ፣ በተሟላ ዝግጅት የሚመራ፣ በውጤታማነት፣
በእውቀት፣ ክህሎትና በስነ-ምግባር ረገድ ያሉትን ክፍተቶች በማስተካከል ለሰራተኛው
አቅም በሚፈጥር መንገድ ማካሄድ፣
የቀጠለ …
 የሚደረገው ውይይት እና ግምገማ በምንም መንገድ የማይቋረጥ እና ሰራተኞች
አልተሟሉም በሚል የማይታለፍ በእቅድ የሚመራ አስገዳጅ ተግባር ሲሆን በተቀመጠው
ቀን ለመወያየት የማያስችሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የቀጣዩ 15 ቀን ውይይት
ከመድረሱ በፊት አመች ቀን ተመርጦ ውይይት ማድረግ፣
 ውይይቱ እንደ አጀንዳዎች ስፋት ሊረዝም ወይም ሊያጥር ስለሚችል የሚስተናገዱ
ባለጉዳዮች ካሉ እንዳይጉላሉ አስቀድሞ ባለጉዳዮችን ማስተናገድ፤
9. ድጋፍ እና ክትትል የሚከናወንበት ስልት
 የለውጥ መሣሪዎችንና የግብ ተኮር ተግባራትን ያካተተ የሥራ ማረጋገጫ ዝርዝር በየሩብ
ዓመቱ በማዘጋጀት ለፈፃሚዎች ማውረድ፣
 በስራ ማረጋገጫ ዝርዝር መሰረት በየሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

 የአሰራር ሂደቱን በመገምገም ውጤትን መሰረት ያደረገ ድጋፍ፣ ክትትልና


ግምገማ ማድረግ፣
 ድጋፍና ክትትሉን መሰረት በማድረግ ክፍተትንና ጥንካሬን በለየ መንገድ
ግብረ-መልስ መስጠት፣
10. የማበረታቻ ስርዓት
 የእቅድ አፈጻጸም ምዘና ውጤትን መሰረት በማድረግ ኮከብ ሰራተኞችን ማበረታታት፣
 የማበረታቻ ሥርዓቱ በበጀት አመቱ መጨረሻ የተቋሙን፣ የዳይሬክቶሬቱን ወይም
የቡድኑ እና የፈጻሚዎችን እቅድ አፈጻጸም በቅደም ተከተል መገምገም፣
 የተቋሙን እቅድ ከማሳካት አንጻር በጣም ከፍተኛና ከፍተኛ አፈጻጸም ላገኙ
ሰራተኞች በውጤታቸው ቅደም ተከተል መሰረት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለሚወጡ
ሠራተኞች ሸልማት እንዲሰጥ ማድረግ፡፡
የቀጠለ …
 ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በቅልጥፍናና በውጤታማነት ለማከናወን እንዲሁም
በቡድኖች መካከል የውድድር መንፈስ ለመፍር እንዲችሉ በየ6 ወሩ በሥራቸው የሚገኙ
አደረጃጀቶችን አፈፃፀም በመመዘን በደረጃ መለየት፡፡ በበጀት አመቱ መጨረሻም
በየተቋሙ የእውቅናና ሽልማት ስርዓት ማከናዎን፡፡
 ምዘናው የሚከናወነው የተቋሙ ማኔጅመንት ኮሚቴ በሚያቋቁመው ከመስሪያ ቤቱ
ሰራተኞች መካካል ከየዳይሬክቶሬቱ ወይም ከየቡድኑ በተውጣጣ ቡድን እንዲሆን
ማድረግ፤
የቀጠለ …
 የማበረታቻ ሥርዓቱ የሚከናወነው በበጀት አመቱ መጨረሻ የተቋሙ
አቅም በፈቀደው መጠን ተገቢውን ማበረታቻ ማድረግ፡፡
 የሚሰጠው ሽልማት ንብረት ከሆነ በህጋዊ ሞዴል እና ገንዘብ ከሆነ
ደግሞ በተቋሙ የባንክ አካውንት ገቢ ሆኖ ጥቅም ላይ እንዲውል
ማድረግ፡፡
11. በየደረጃው ያሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ተቋማት ተግባር እና ኃላፊነት
 በየ3 ወሩ የሁሉንም ተቋማት የለውጥ አፈጻጸም የሚመለከት የፅሁፍ ሪፖርት
በማዘጋጀት በየደረጃው ለሚገኝ ጠቅላላ አመራር ኮሚቴ አቅርበው ያስገመግማሉ፣
 የለውጥ መሳሪያዎችን አተገባበር በሚመለከት በተዋረድና በጎንዮሽ ለሚገኙ ተቋማት
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፣ ሪፖርት ይቀበላሉ፣ ይገመግማሉ፣ ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፣
ያወዳድራሉ ውጤቱንም ይፋ ያደርጋሉ፣
 ከሲቪል ሰርቪስ ጋር የተያያዙ ልዩ ልዩ መመሪያዎች፣ ማንዋሎችና የሪፎርም ተግባራት
ላይ የአቅም መገንቢያ ስልጠና ይሰጣሉ፡፡
12. የተቋማት የለውጥ አመራር አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ከሰራተኛ የስራ
አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ጋር ያለው ግንኙነት

 የሰራተኛው የእቅድ አፈጻጸም ውጤት የሚሞላው በየጊዜው በሚደረጉ ስራን መሰረት


ያደረጉ ግምገማዎች፣ በፈጻሚው የሚቀርቡ ሪፖርቶች እና ውይይቶች ላይ የተደራጀ
መረጃ በመያዝ ይሆናል፡፡
 በየደረጃው ያለው አመራር በስሩ የሚገኙ ተቋማትንና የስራ ክፍሎችን አፈጻጸም
የመከታተል፣ የመደገፍ እና የስራ ቡድኑ ያለበትን ዝርዝር ሁኔታ በየጊዜው ከሱ በላይ

ላለው አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፤


የቀጠለ …
 በየተቋሙ ያሉ የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ባለሙያዎች በአብክመ የተሻሻለው
የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 ዓ.ም በአንቀጽ 76 ከተዘረዘሩት

ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ የተቋሙን የለውጥ ተግባራት አፈጻጻምን

በተመለከተ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ወቅታዊ መረጃ ለተቋሙ ኃላፊ


ያቀርባሉ፡፡
 ተቋሙ ሌሎች አማራጮችን በማየት ከአቤቱታና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎች ይልቅ
ሌላ የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ብሎ ካመነ ባለሙያ በመመደብ ወይም
በመወከል ስራውን ማሰራት ይችላል፡፡
13. መመሪያውን አለመፈጸም የሚያስከትለው ተጠያቂነት

 በዚህ መመሪያ የተደነገገውን በማወቅም ሆነ በቸልተኝነት ያልፈጸመ


ወይም እንዳይፈጸም ያደረገ ማንኛውም ኃላፊ ወይም የመንግስት
ሠራተኛ አግባብ ባለው የወንጀል፣ የፍትሐብሔር እና የአስተዳደር ሕግ
መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

You might also like