Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 14

የከበረው

የክርስትያኖች
ተስፋ ሮሜ 5.1-5
“1 እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ 2 በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ
በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን። 3-4
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም
ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ
እንመካለን፤ 5 በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ
ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።”
ሮሜ 5.1-5
• ይህ ዛሬ የምንመለከተው ሮሜ 5 ከቁጥር 1-5 ስለ ብዙ እውነቶች ይናገራል፣
• ፅድቅ በእምነት እንደሚገኝ
• ፅድቅን ያገኙ ሰዎች ሰላምን መያዝ እንዳለባቸው
• በጌታ በኢየሱስ ወደ ቆምንበት ፀጋ መግባት እንዳገኘን
• እናም አማኞች የሚመኩት በእግዚአብሔር ክብር ተስፋ እንደሆነ
• በመከራ ውስጥ ትዕግስት በፈተና ተስፋ እንደሚኖር
• በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን እንደፈሰሰ
• ስለዚህ ተስፋ እንደማያሳፍር
• ተስፋ የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ ተጠቅሷል
• ቁጥር 2 ላይ መመኪያችን በእግዚብሔር ክብር ተስፋ ነው
• ቁጥር 4 ፈተና ተስፋን ያደርጋል
• ቁጥር 5 ተስፋው አያሳፍርም
• ስለዚህም በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የተጠቀሰውን የክርስትያንን ተስፋን መመልከት
የክርስትያን ተስፋ ምንድነው?
• ተስፋ ምንድነው?

• ይሆናል ብለን የምንጠብቀውን ነገር ወደ ፊት መመልከት፣ መጠባበቅ፣ አንድን ነገር ወይንም


አንድ ሰውን ማየት ወይንም አንድ ጠቃሚ ነገርን በተጨባጭ ይሆናል ብሎ መጠባበቅ ነው

• መጽሐፍ ቅዱሳዊው ተስፋ ከዓለማዊው ተስፋ የተለየ ነው፣ የዓለም ተስፋ መጨረሻው ባዶና
አክሳሪ ነው

• መጽሐፍ ቅዱሳዊው ተስፋ ስሜትና በስሜት መንጎድ አይደለም፣ የምኞት አስተሳሰብ ወይንም
ግምት አይደለም

• መጽሐፍ ቅዱሳዊው ተስፋ የእውነታ እውቀት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በዓለት ላይ የተመሰረተ


ቤት እንደማይነቃነቅ በእግዚአብሔር ቃል ቃል ኪዳኖች ላይ የተመሰረተና የፀና ነው፡፡
• መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ተስፋ መያዝ ማለት ለነፍስ እውነተኛ ማረፊያ ማግኘት ማለት ነው

• ስለዚህም የክርስትያን የተስፋ ትርጉም ከዓለማዊውና ከስሜተኞች ትርጉም በጣም የላቀ ነው

• የአማኝ ተስፋው እርግጠኛና በነፍሱም በልቡም በአዕምሮውም እንደሚሆን የሚያውቀው ነገር


ነው
ተስፋ በብሉይ ኪዳን
• ተስፋ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በትግስት መጠባበቅ፣ እግዚአብሔርን መቆየት፣ በመከራ
መፅናት፣ የጌታን እጅ መገለጥ መጠባበቅ ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
• ችግርና መከራ ሲኖር አማኙ የእግዚአብሔርን እጅና ማዳን በተስፋ መጠባበቅ እንደነበረበት
የሚያሳይ ነው
• “ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። ከጥፋት
ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም
አጸና።” መዝሙር 40.1-2
• ስለዚህም ለተስፋ የተሰጡት የዕብራውያን ቃላት እምነት መታመን እምነትን በእግዚአብሔር
ላይ ማድረግ የሚሉና ከእምነት ጋር የተቆራኘ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ለምሳሌ፡
• “22 በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ማፍሰስ
ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን
በተስፋ እንጠባበቃለን።” ኤርምያስ 14.22
• “አንተ የእስራኤል ተስፋ ሆይ በመከራም ጊዜ የምታድነው፥ በምድር እንደ እንግዳ፥ ወደ
ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ ስለ ምን ትሆናለህ? እንዳንቀላፋ ሰው፥ ያድንም ዘንድ
እንደማይችል ኃያል ስለ ምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ፥ በመካከላችን ነህ እኛም በስምህ
ተጠርተናል፤ አትተወን።” ኤርምያስ 14.8-9
• “13 አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ
እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ። 14 አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም
እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።” ኤርምያስ 17.13-14 “2 አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ
በእኔ አይሣቁብኝ። 3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።” መዝሙር 25.2-3
የብሉይ ኪዳን አማኞችና ተስፋ
• የፀለዩት ፀሎት
• “21 አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።” መዝሙር 25.21
• “5 አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች። 6 ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ
እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች። 7 ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ በእርሱም
ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን።” መዝሙር 130.5-7
• የተመከሩት ምክር
• “14 እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ
አድርግ።” መዝሙር 27.14
• በተስፋ አለማፈር ምስክርነት
• “4 አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው። 5 ወደ አንተ ጮኹ
አመለጡም፥ አንተንም ተማመኑ አላፈሩም።” መዝር 22.4-5
• “6 አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥
የሚሹህ በእኔ አይነወሩ።” መዝሙር 69.6
• “23 ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፥ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤
ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤
እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፥ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ
አያፍሩም።” ኢሳያስ 49.23
• “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ውስጥ ስለፈሰሰ ተስፋው
የአማኞች ተስፋ እግዚአብሔር
ብቻ
• በሌሎች ነገሮች ማድረግ ውጤት የለውም
• ብልጥግና
• “7 ….. …. እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥ በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ፥ በከንቱ ነገርም
የበረታ ያ ሰው እነሆ።” መዝሙር 52.1-7
• “28 በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።” ምሳሌ 11.28
• በጣኦታት መዝሙር 115.3-11 በባዕድ አገሮች ችሎታ ኢሳያስ 20.5 በጦር ሰራዊት ኢሳያስ 30.15-
16 31.1-3
• “3 ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ። 4 ነፍሱ ትወጣለች ወደ
መሬቱም ይመለሳል፤ ያን ጊዜ ምክሩ ሁሉ ይጠፋል።” መዝሙር 146.3-7
• በሌሎች ሰዎች ላይ “5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም
ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው። 6 በምድረ በዳ
እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው
ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።” ኤርምያስ 17.5-8
• አንድ ሰው በእግዚአብሔ ታማኝነት፣ በቃሉ፣ በፍቅሩ በምህረቱ በማዳኑ በሁሉን ቻይነቱ
በትምህርቱ በጥበቡ መተማመን አለበት፡፡

ተስፋና ውጤቱ በአዲስ ኪዳን
• ሮሜ 5.1-5 ላይ ሦስት ጊዜ የተነገረው ተስፋ የሚለውን ቃል የሚጠቀምበት ልክ እንደ
ብሉይ ኪዳን እምነት ወይንም መታመን በሚለው እውነታ ላይ ተመስርቶ ስለሚመጣ
እርግጠኛ ነገር ነው
• ቁጥር 2 በእግዚአብሔርም ክብር እንመካለን
• ቁጥር 4 ትግስትም ተስፋን ያደርጋል
• ቁጥር 5 በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለፈሰሰ ተስፋ
አያሳፍርም
• መጽሐፍ ቅዱሳዊው ተስፋ የሚያቀርበው ሀሳባዊ የማይጨበጥ ነገርን አይደለም ነገርን
የሚጨበጥን የሚገለጥን እውነት ነው ያም የተመሰረተው በማይለወጠው በእግዚአብሔር
ቃል ላይ ነው

• “10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም


የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።” 1 ጢሞቴዎስ 4.10

• የፍጥረት ተስፋ
• “19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና። 20 ፍጥረት
ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም፤ 21 ተስፋውም
ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር
ከተስፋ ጋር የተያያዙ ነገሮች
• ትግስት ሮሜ 5.3-4
• ፅናት “2-3 በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም
ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና
በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት
እናመሰግናለን፤” 1 ተሰሎንቄ 1.3
• ፍቅር ሮሜ 5.5
• ክብር “27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ
ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ
በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።”
• ትንሳኤና ክብሩ ሐዋርያት 23.6 24.15
• መፅናናት 1 ተሰሎንቄ 4.18
• ፅድቅ ገላትያ 5.5
• የዘላለም ሕይወት “በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት
እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት
ተስፋ ሰጠ፥” ቲቶ 1.2
• የክርስቶስ ዳግመኛ መገለጥ “የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና
የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥” ቲቶ 2.13
• ክርስቶስን መምሰል “ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም
የክርስትያን ተስፋ ወዴት
ይመራል?
• ተስፋ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የሚሰጥ ትክክለኛ ምላሽ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን አብርሃም
በአዲስ ኪዳን ደግሞ ማርያምን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ምንም እንኳን በእድሜው ቢያረጅም
ተስፋ በሌለው ነገር ላይ በእግዚአብሔር ተስፋ አደረገ ሮሜ 4.18
• ወደ ደስታ “12 በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤” ሮሜ 12.12
• በጌታ ድፍረት
• “12 እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥” 2 ቆሮንቶስ 3.12
• እምነትና ፍቅር
• “3-5 ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ በሰማይ ከተዘጋጀላችሁ ተስፋ የተነሣ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ
እምነታችሁ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተን፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን
አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ስለዚህም ተስፋ በወንጌል እውነት ቃል
አስቀድማችሁ ሰማችሁ።” ቆላስያስ 1.4-5
• ሰላም፣ ፅድቅም እውነተኛ እረፍትም የእምነት ጉዞና ሕይወትን ያስገኛል
• ተስፋ በአማኞችን ላይ የሚያመጣው ውጤት
• ቅድስና ፍቅር
• እውነተኛ አገልግሎት መዘጋጀት ይቅርታ

You might also like