17th Nation Nationalities Peoples Day Seminar

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 70

የሕብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት ምንነት፤ ባህሪያት እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ም/ቤት እና በአማራ ብሔራዊ ክልል ም/ቤት ለ17ኛዉ


የኢትዮጵያ ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተዘጋጀ

Date
Place
ህብራዊ ማንነት- ድርና ማግ
ከራስ-ደጀን እስከ ዳሎል (ድርብ ጌጥ)
የብዝሃ-ሐይማኖት ምድር
የገለፃው ይዘቶች




3-ክ






2-ል

-ሕ
1






-





















-


































መግቢያ፤
 የብሔር፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ከአገራችን ብሔራዊ በዓላት
(national holiday) መካከል አንዱ ሆኖ መከበር ከጀመረ 17 ዓመታት
ሆነው፡፡
 በዓሉ መከበር የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም መነሻ ያደረገው አሁን ስራ ላይ
ያለውን የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት የፀደቀበትን ዕለት ነው፡፡ (ህዳር 29) – 8
December 1994፡፡
በዓሉ ከአገራዊ ለውጡ ወዲህም በእርሾነት ተወስዶ በተለያዩ የአደባባይ
ትዕይንቶች፤ በኮንፈረንሶችና በበጎ አድራጎች ስራዎች እየተከበረ ነው፡፡
 አሁን ላይ 17ኛው የብሔር፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ሕብረ-ብሔራዊ
አንድነታችን ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በሲዳማ
ብሔራዊ ክልል አስተናጋጅነት በአዋሳ ከተማ በድምቀት ይከበራል፡፡
በዓሉ በሁሉም ክልሎች በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ሲሆን የዝግጅቱ አካል
የሆነው ይህ የፓናል ውይይት በፌዴሬሽን ምክር ቤትና በክልላችን ምክር
ቤት መሪነት የተዘጋጀ ነው፡፡
….
 የፓናል ውይይታችን ከምንገኝበት አገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ
አንፃር እና ለበዓሉ ከተመረጠው መሪ ሃሳብ ጋር በሚጣጣም
መልኩና የኢትዮጵያን አንድነት በማጠናከር ጉልህ ድርሻ ባለው
የህብረ-ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት ላይ እንዲያተኩር በማሰብ፡-

 “የሕብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርዓት ምንነት፤ ባህሪያት እና


የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ” በሚል ርዕሠ-ጉዳይ ላይ ውይይት
ለማድረግና ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
የውውይት መድረኩ ዓላማ

 ሀገራችን በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ከፍሎች


በፌደራል ስርዓት ዉስጥ እንደሚኖር ዜጋ በህብረ-ብሄራዊ
ፌደራል ስርዓት ላይ ተቀራራቢ የሆነ ግንዛቤ የሚይዙበት
ውይይት ማካሄድ፤
 ዜጎች የህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ግንባታ ላይ
የበኩላቸዉን አስተዎጽኦ ማበርከት የሚያስችል ተጨማሪ
አቅም መፍጠር፤
 ህብረ-ብሄራዊ አንድነት እና ዘላቂ ሰላም የሚያጠናክሩ
ተግባራትን ማከናወን ናቸው፡፡
ክፍል 1- ፌደራሊዝምና ሕብረ-ብሔራዊ
ፌደሬሽኖች
የፌደራሊዝም ፅንሰ-ሃሳብ



















:
:






















































:
:



































:
:

























ፌደራሊዝም





-



































.
ፌደራሊዝም ሌሎች መርሆዎቹና ባህሪያት እንዳሉ ሆነው የጋራ
አስተዳደር /Shared rule/ እና የግል አስተዳደር /Self rule/
አጣምሮ የሚገነባ ስርዓት ናቸው::

Federalism has been


ፌዴራሊዝም የተማከለ እና
represented as centralizing
ያልተመከለ የመንግስት አደረጃጀት
and decentralizing ideology
አስተሳሰብና በሁለቱ መካከል ያለውን
as well as a doctrine of
ሚዛን የሚገልፅ እሳቤ ነው
balance( Burgess 2006)
የፌደራሊዝም እሴቶች፡- ሰብዓዊነት፣ እኩልነት፣ ነፃነት፣ ፍትህ፣ የሌላን
ጉዳይ እንደራስ አድርጎ የማየት፣ መቻቻል፣ እውቅና መስጠት፣ መከባበር የሚሉ
ናቸው::

የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ የሰው ልጆች የግል


የጋራ አስተዳደርና የራስ አስተዳደር እና የጋራ ጉዳዩቻቸዉን አቻችለዉ አንድ ላይ
መርሆዎች የፌዴራሊዝም ፅንሰ-ሀሳብና እንዲኖሩ የሚያስችላቸው በርካታ መሰረታዊ
ፍልስፍና የሚገልፁ ወይም የሚወክሉ እሴቶችን በውስጡ ያካተተ ነው፡፡
ናቸው፡፡
የፌዴራል ፖለቲካ ስርዓቶች(Federal Political Systems)

የፌዴራሊዝም አስተሳሰብ አካል የሚለብሰውና ተግባራዊ የሚደረገው


በፌዴራላዊ ፖለቲካዊ ስርዓቶች ነው፡፡
 ኮንፌደሬሽን
 ፌደሬሽን
 ፌደራሲ
 አሶሼትድ ስቴትስ
I. ኮንፌደሬሽን

(የተገደበ ኮንፌደራል መንግስት እና


ጠንካራ የኮንፌዴሬሽን አባል
መንግስታት)

ለተወሰነ አላማ የጋራ መንግስት


ወይም የኮንፌዴራል መንግስት
የሚመሰረትበት ነው፡፡

የኮንፌደራል መንግስቱ
ቀጥታ በህዝብ የማይመረጥ
ከአባል መንግስታቱ ስልጣን ተቆርሶ የሚሰጠዉ
የራሱን ገቢ የማይሰበስብ (በመዋጮ
የሚተዳደር)
 የኮንፌዴሬሽን አባል መንግስታት በማንኛውም ጊዜ የኮንፌደራሉ
መንግስቱ ይሁንታ ሳያስፈልጋቸው መዉጣት የሚችሉበት እድል
አላቸው፡፡
ኮንፌዴሬሽን የፌዴራል ስርዓት በመስራች አባላቱ ቋሚ ህብረት
ለመገንባት ያላቸው ቁርጠኝነት ዝቅተኛ መሆኑን መገንዘብ
ይቻላል፡፡
በአሁኑ ስዓት የኮንፌዴሬሽን ስርዓት የሚከተሉ ሀገራት የሉም
ብሎ መደምደም ይቻላል
ሆኖም ታሪካዊ ምሳሌዎች:-
 ሲዊዘርላነድ 1291 እከ 1847፣ ዩናትድ ስቴትስ ኦፍ
 አሜሪካ 1776- 1789 መጥቀስ ይቻላል ( ዋትስ 1996)
II. ፌደሬሽን
በስምምነታቸውም መሰረት የፌዴራል መንግስቱ በተሰጠው የስልጣን ወሰን በራሱ እንዲሁም
አባል መንግስታት በተሰጣቸው የስልጣን ወሰን በራሳቸዉ የሚወስኑበትና በትብብርና
በቅንጅት የሚሰሩበት ስርዓት ነዉ፡፡

ጠንካራ የፌዴራል መንግስት እና ጠንካራ የፌደሬሽኑ አባል መንግስታት)

በህዝብ የተመረጡ እና
ቀጥታ ከህዝብ ጋር የሚገናኙ
በተለያዩ አግባቦች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ

የፌደራል ስርዓት የሚመሰረተው የፌዴሬሽኑ አባል መንግስታት በእኩልነት መርህ በጋራ


ተወያይተው እና ተስማምተው በሚያፀድቁት የቃል-ኪዳን ሰነድ ወይም ህገ-መንግስታዊ ስርዓት
ነው፡፡
II. ፌደሬሽን
(ጠንካራ የፌዴራል መንግስት እና ጠንካራ የፌደሬሽኑ አባል መንግስታት)

በፌዴሬሽኑ የፌዴሬሽኑን
አንድነት የሚመለከቱ እና
የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው
ለፌደራል መንግስቱ የሚሰጡ ሲሆን
•ለፌዴሬሽኑ አባል መንግስታትም ከባቢያዊ ጉዳዩችን የሚመለከቱ
ስልጣኖች ተለይተው ይሰጣሉ፡፡

በአብዛኛዉ ፌደሬሽኑ የሚመሰረትበት ትርክት:-


•አብሮነት፤ በጋራ ማደግ፤ በጋራ ችግሮችን መፍታት፤ወንድማማችነት፤
•አንዱ በአንዱ ላይ እምነት ማሳደር፤
• ከባባያዊ ፍላጎትና አቅምን ከሀገራዊ
• ፍላጎትና አቅም እሰተሳሰሮ መሄድ፤
•ጠንካራ የጋራ ሀገር መፍጠር
• ወዘተ… በመሆኑ
በመሆኑም ፌዴሬሽኑ
የፌደሬሽኑ አባል
የተመሰረተበት ህገ-
መንግስታት ከመለየት ይልቅ
መንግስታዊ ስርዓት በአንድ
አካል በቀላሉ የማይሻሻልና
ቋሚ የሆነ ፖለቲካል ህብረት
ለመመስረት ያላቸው
ፌደሬሽን
ረዘም ያለ ጊዜ እንዲያገለግል
ተደርጎ የሚቀረፅ ነው፡፡
ቁርጠኝነት ከፍተኛ ነው፡፡
ፌደሬሽኖች

ክልሎች (የአካባቢ መንግስታት)

መራጮች

የፌደራል (ማዕከላዊ) መንግስት


ፌደራሲ (Federacy)

ፌዴራሲ ሰፊ ያልሆነ ሀገር ከአንድ ሰፊ የፊደሬሽን ቅርጽ ካለዉ


የፌደራል ስርዓት ከሚከተል መንግስት ጋር ከፌዴሬሽን አባል
መንግስታት በተለየ ግንኙነት (Asymmetrically) ሲጣመር
የሚመሰረት የፖለቲካ ስርዓት ነው፡፡

በፌደራሲ የሚጣመረው መንግስት ከሌሎች የፌዴሬሽን አባል


መንግስታት አንፃር ከፍተኛ የሆነ ራሱን የማስተዳደር ስልጣን ያለው
ነው፡፡
ሆኖም በፌደራሲ የተጣመረው መንግስት በፌደራል
መንግስቱ ወይም በጋራ ስልጣን ላይ የሚኖረው
ተፅዕኖ አነስተኛ ነው፡፡

የፌደራሲ ምሳሌዎችን ለማየት ፖርታሪኮ ከ


ዩናይትድ ሰቴትስ ኦፍ አሜሪካ እንዲሁም ቡታን
ከህንድ ( ዋትስ 1996)
አሶሼትድ ስቴትስ

አሶሽትድ ስቴት ልክ እንደ ፌደራሲ ስርዓት ሰፊ ያልሆነ


ሀገር ከሌላ ሰፊ የፌዴሬሽን መንግስት ከአባል
መንግስታት ልዩ በሆነ
ግኑኙነት(Asymmetrically)ሲጣመር የሚመሰረት
የፌዴራል ፖለቲካዊ ስርዓት ነው፡፡
 በዚህ ስርዓት የሚፈጠረው ግንኙነትም ከሌሎቹ
የፌዴራል መንግስታት ጋር ሲነፃፀር ራሱን በራሱ
የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን ለተጣማሪው የሚያስቀር
መሆኑ ነፃነቱ ከፍተኛ ነው፡፡
በፌዴራል መንግስቱ ወይም በጋራ ስልጣን ላይ
የሚያሳድረው ተፅእኖም ዝቅተኛ ነው፡፡
የሁለቱ መንግስታት ግኑኝነትም ቀደም ብሎ
በተደረገ ስምምነት በአንዳቸዉ ተናጥላዊ ፍላጎት
ሊቋረጥ ይችላል፡፡
አሶሽትድ ሰቴትስ ምሳሌዎችን ለማየት የዩናትድ
ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ከማርሻል አይላንድስ እና
ኒዊዚላንድ ከኩክ አይላንድስ ( ዋትስ 1996)
ከዚህ በላይ ተዘረዘሩት የፌደራል ፖለቲካዊ ስርዓት
የሚጋሩ አደረጃጀቶች
በተጨማሪም፣
 ዩኒየን፣
ሊግ፣
ኮንዶሚኒየም፣
 ያልተማከለ አህዳዊ ስርዓት
ተጠቃሽ የሆኑ የፌዴራል ፖለቲካል ስርዓት ባህሪ
የሚጋሩ አደረጃጀቶችን መጥቀስ ይቻላላል ፡፡
1.2. የፌዴሬሽኖች የጋራ ባህሪያት እና የተለያዩ የሚያደርጓቸዉ ጉዳዮች
የፌደሬሽኖች የጋራ ባህሪያት
 ለረጅም ጊዜ በፌደራሊዝም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፡-
 ፌደሬሽኖችን በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉና በመዋል ላይ
የሚገኙ ፌደራላዊ የመንግስት አደረጃጀቶች ናቸዉ (ዋትስ 1996; በርገስ
2006; ኤላዛር 1987)፡፡
1. ከሁለት ያላነሱ መንግስታት መኖር
2. የተጻፈ እና ጠንካራ የማሻሻያ ሂደትን የሚከተል ህገመንግስት መኖር
3. ህገመንግስታዊ የሆነ የስልጣን ክፍፍል
4. ሁለት ም/ቤቶች መኖር
5. በፌደሬሽኑ ዉስጥ አለመግባባቶች ቢፈጠሩ አለመግባባቱን
የሚፈታ ተቋም መኖር
6. የመንግስታት ግንኙነት የሚያሳልጡ ሂደቶች መኖር
ከሁለት ያላነሱ መንግስታት መኖር

ፌዴሬሽኖች ህገመንግስታዊ ዕወቅና ያላቸዉ ቢያንስ ሁለት


መንግስታት ይኖራቸዋል፡፡
 ሁለቱ መንግስታት ህገ-መንግስታዊ ስልጣን አክብሮ
መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዎል፡፡
 ሁለቱ መንግስታት የተሰጣቸዉን ስልጣንና ኃላፊነት
ለመወጣት ትስስርና ቅንጅት የማይቀር የስርዓቱ ገጽታ
ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የተጻፈ እና ጠንካራ የማሻሻያ ሂደትን የሚከተል
ህገመንግስት መኖር

ህገ-መንግስቱ የአባል መንግስታት ባደረጉት ውይይትና ድርድር የተስማሙባቸውንና


የተቀበሉኣቸውን ስምምነቶች በፅሁፍ የሚሰንድበት የቃል-ኪዳን ሰነዳቸዉ ነው፡፡

ህገ-መንግስታዊ የሆነ የስልጣን ክፍፍል


 በህገ መንግስቱ ህግ የማውጣት፣የመፈፀም እና የመተርጎም
እንዲሁም ገቢ የመሰብሰብ እና ወጭ የማዉጣት
ስልጣኖችን ለፌዴራል መንግስቱ፣ ለአባል መንግስታት
 ለብቻ የሰጠ /ፌደራል -ክልል/
 የጋራ ሥልጣን
የቀጠለ…
ቀሪ ስልጣን
 የማዕቀፍ ስልጣን
በፌደራሊዝም አስተሳሰብ ስልጣን ለመከፋፈል የሳብሲዲያሪቲ
መርህን መከተል ከባቢያዊ መንግስታት በሚችሉት መጠን ድረስ
የከባቢያቸዉን ችግር እንዲፈቱ ማስቻል
መርሁ የስልጣን መከፋፈል መነሻ የታችኛዉን አስተዳደር እርከን
በማድረግ፣
በታችኛዉ አስተዳደር እርከን አቅም በተሻለ መንገድ መፈጸም
የማይችሉ ጉዳዩች ቀጥሎ ላለዉ እርከን መሰጠት፣
ፌደሬሽኖችን የተለያዩ የሚያደርጉ ጉዳዮች
በዓለም ላይ የሚገኙ ፌደሬሽኖች የጋራ ባህሪያት ያሏዋቸዉ ቢሆንም ሁሉም አንድ
አይነት አይደሉም፡፡
ፌደሬሽኖች ከአመሰረታቸዉ፣
ከሚከተሉት የአስተዳደር ስርዓት፣
እንዲሁም ከሚገኙበት ማህበራዊ ፤ኢኮኖሚዊና
 ፖለቲካዊ ነባረዊ ሁኔታ ጋር የተያያዙ የተለዩ የሚያደርጓቸዉ ጉዳዩች አሉ
1.ህብረ-ብሄራዊ እና ህብረ-ብሄራዊ ያልሆኑ ፌደሬሽኖች
2. ስልጣን በግልጽ የተከፋፈለበት (ፕሬዜዳንታዊ) እና ስልጣን የተዋሀደበት
( ፓርላሜንታዊ) የመንግስት አወቃቀር የሚከተሉ ፌዴሬሽኖች
3. የተመጣጠነ እና ያልተመጣጠነ ስልጣን ያላቸዉ የፌደሬሽኑ አባል መንግስታት
ያቀፉ ፌዴሬሽኖች
4. ኮመን ሎዉ (Common Law) እና ሲቪል ሎዉ (Civil Law) የሚከተሉ ፌደሬሽኖች
የተማከሉ እና ያልተማከሉ ፌዴሬሽኖች
ክፍል ሁለት - ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራል
ስርዓትና ኢትዮጵያ
በዚህ የሁለተኛው ክፍል፡-
 ህብረ ብሄራዊ ማለት ምን ማለት ነው?
ብዝሀ ማንነትን ለማስተናገድ የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች
ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ትችቶች
ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት መድሃኒት ወይስ እርግማን ?
ህብረ-በሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት እና የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ
ህብረ ብሄራዊነትን ለመገንባት የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች የሚሉት
ነጥቦች ይነሳሉ፡፡
ህብረ-ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች፡-

የፌደሬሽኖቹ ዋነኛ እሳቤ ልዩነቶችን ባከበረ


መልኩ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ብዝሃነት
ባለበት ሀገር ዉስጥ ህብረ- ብሄራዊ ፌደራሊዝም
የተሻለ አማራጭ ነዉ የሚል ነዉ፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት እና ህብረ-ብሄራዊ ፌደሬሽን
ህብረ-ብሄራዊነት ሁለት ቃላትን አጣምሮ የያዘ ሀረግ ነው፡፡
 -ህብር እና ብሄራዊነት፡፡
ህብር የሚለው ቃል
 - ብዙ፣ መልከ ብዙ፣ አይነተ ብዙ፣ የተለያዩ ቀለሞችን የሚያመላክት ሲሆን፣
ብሄር “አንድ ማህበረሰብ ነን የሚል እሳቤ ያላቸዉ፣ የሚጋሩት የጋራ ባህል
በግልጽ ከሚታወቅ መልክዐ ምድር ጋር ራሳቸዉን የሚያይዙ፤ ያለፈ የጋራ
ጉዳይ እና የወደፊት የጋራ ፕሮጀክት አለን ብለዉ የሚያስቡና ራስን በራስ
የማስተዳደር ጥያቄ ያላቸዉ ሰዎች የተሰባሰቡበት ቡድን ነዉ" (ጉብናወር 1999)
ህብረ-ብሄራዊነት -የተለያዩ ብሄሮች በአንድነት በጋራ መኖርን የሚገልፅ ነው፡፡
የህብረ ብሄራዊነት መገለጫዎች
ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ብዝኃነትንና ሕብረትን በማጣመር
አንድነትን የሚያስቀጥል ሥርዓት ነው።
ብዝኃነት ማለት በአንድ ሃገር ውስጥ በተለያዩ
ማንነቶች(ባህል፣አምነት፣ቋንቋ…) የሚገለፁ የተለያዩ ቡድኖች ግልፅ በሆነ
አሰፋፈር ወይም ታሪካዊ ምንጭ መኖር.
ሕብረት ማለት ደግሞ ብዝኃነትን በማክበርና በጋራ ጥቅምና ፍላጎት ላይ
በመመሥረት አብሮ የመቀጠል ውሳኔ ወይም ስምምነት ማለት ነው።
ብዝኃነትንና ሕብረትን አስታርቆ ለመሄድ ከብዝኃነት የሚመነጩ ነገር ግን
በሕብረት የሚሟሉ ፍላጎቶች መኖራቸው የግድ ይላል። በተጨማሪም
ለጋራ ጥቅም ሲባል የተከወነ የጋራ ታሪካዊ ፍፃሜም መኖርን ይሻል፡፡
የኢትዮጵያዊያን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት መሰረቶች
ለህብረ ብሄራዊነት መሰረቶች
1.ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለማቋረጥ የእርስ በእርስ ግንኙነት
የማድረጋቸው ሂደት
2.በርከት ያሉ ሀገር አቀፍና ኢትዮጵያን መሰል የሆኑ የወል የባህል ቅርሶች
መኖር( ለምሳሌ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች፣ባህላዊ በዓላት፣ቅርሶች)
3.በየግዜው የውጭ ኃይል በአገሪቱ ላይ ጣልቃ ለመግባት በሚቃጡበት ጊዜ
ለመከላከል አብረው በጋራ መቆማችው (ዶናልድ ሌቪን ታላቋ ኢትዮጵያ
1975 39)
የንግድ እንቅስቃሴ (ሲራራ)፣ እምነቶች፣ ቋንቋዎች (አፍሮ እስያዊ፣ኒሎ
ሰሃራ)፣ ገበያዎች ህዝቦቹን ከአንድ ማንነት በላይ ሄደው አስተሳስረዋል
የቀጠለ ….
 የአኗኗር ዘይቤያችን( እርሻ፣እንሰት፣ከብት እርባታ)
 ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን፡-አበልጅ፣አይን አባት፣ጉዲፈቻ፣የክርስትና
አባት፣ጉርብትና፣እድሮች፣እቁቦች፣ጌዝ፣ወንፈል፣መድረሳ፣የቄስ ትምህርት
ቤት፣ለመንግስት ያለን እሳቤ፣ይህ እነዲያው በረጅም የታሪክ ዘመናቸንና የአብሮነት
ዘመናችን የተገነባ መሆኑን
ሀገራችንን ህዝቦች ከአንድ እመቨነት፣ቋንቋ፣ቦታ፣ብሄር..በላይ የሚያስተሳስሩትን
እነዚህን ማህበረ ባህላዊ እሴቶች ጎልተው እንዲወጡ መስራት፣ከፍተኛ ተቋማት
ተማሪዎቻቸው እነዚህ ሀገር በቀል ተቋማት በታሪክ ያለቸው ሚናን እዲገነዘቡ
በውይይት፣በድራማ፣በስነ ጽሁፍ እንዲያውቁ እንዲገነዘቡ ማድረግ
የባህል፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የአሰፋፈር፣ የገበያና የንግድ፣ እንዲሁም ሰፋ ያለ
ማኅበራዊ ትስስርና መወራረስ መኖር ብዝኃነትንና ሕብረትን ለማስቀጠል እጅግ
አስፈላጊ የሆኑ መስተጋብሮች ናቸው።
 ስለሆነም ሕብረብሔራዊ ፌዴራሊዝም በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረት ወይም
አንድነትና ማንነቶች የሚጎለብቱበት ውህድ ነው።
ያለፉ የፖለቲካ ስረዓቶች የብሄር ማንነትን ለመስከበር የሄዱበት ርቀት የሚደንቅ
ቢሆንም የሚያስተሳስሩንን የህብረት መሰረቶች ግን የዘነጉ ነበሩ::
የህብረ ብሄራዊነትና የአንድነት መድረክ
የክልላችን ህብረ-ብሔራዊነት እንደ ምሳሌ

አማራ ብሔራዊ ክልል


የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መርሆዎች
የቃል ኪዳን ማሰሪያ የሆነ ሕገመንግሥት መኖርና መከበር

በስምምነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ሕብረት መኖር

ብዝኃነት የሚያንፀባርቅ የፖለቲካ አወቃቀር በማዕከልና በክልሎች


መከተል

መከባበር፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ ወይንም በጋራ የመኖር እሴቶችን


ማጎልበት
የፌዴራላዊ አደረጃጀት፡-

ባለብዙ ብሔር በሆኑ ሀገራት ብዝኃነትን እና ከዚያ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ


የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በአንጻራዊ ሁኔታ በተሻለ
መልኩ ለማስተዳደር ብሔሮች በሰፈሩበት መልክዓምድር ራሳቸውን
የማስተዳደር ሉዕላዊ ሥልጣን መስጠትን በአንድ በኩል የጋራ ጉዳያቸውን
የሚመሩበት የፌደራል መንግስትን ሁሉንም በሚወክል መልኩ መመስረት
በሌላ በኩል የያዘ ስርዓትን መመስረት እንደ አንድ የተሻለ አማራጭ
ተደርጎ ይወሰዳል::
የአገራት አፈጣጠርና የብሔረ-አገር ግንባታ
ሞዴሎች
 በአንድ ሀገር ያሉ ብዝኃነቶችንና የፖለቲካ ፍላጎቶችን አስታርቆ ህዝብን
ለመምራት ሦስት ዓይነት መንግስታዊ የአወቃቀር ሞዴሎች በተለያዩ
የዓለም ሀገሮች እየተተገበሩ እንዳሉ የምርምር ውጤቶች ያሳያሉ::
 Liberal State Model(የመጀመሪያው ለቡድን መብት ብዙ ትኩረት
ባለመስጠት ለግለሰብ መብት ሰፊ ቦታ የሚሰጥ ነው)
 Nationalist (hegemonic) State Model
 multi-national State Model ህብረ ብሄራዊ አደረጃጀት ይባላሉ፡፡
ህብረ ብሔራዊ ሞዴል
ብዝሃነትን ያከበረ፤ የተሳሰረና የተዋሀደ ማንነትን፤ የግልና የቡድንን መብት
የሚያማክል ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ሞዴል
የተለያዩ ክስተቶች፤ የግዛት መስፋፋት ይዘቶች መስተጋብሮች ወዘተ
በመነጨ የተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ እምነቶች፤
ቋንቋዎች፤ ባህልና ታሪክ ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል
ይህን መሰረትያደረገ የሀገር ግንባታና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ
ለሰላምና ለሀገር ግንባታ፤ ለግጭት መቀነስ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል
ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርዓት ሞዴል አንድ ህዝብ ከሌላዉ ህዝብ በቋንቋ
ወይም በእምነት ሊለይ ቢችልም ሁሉንም ህዝቦች የሚያስተሳስር ብዙ
ሌሎች ገመዶች አንዳሉ ያስረዳል::
ህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት…
 በመደብ፤ በጉርብትና፤ በኑሮ ሁኔታ፤ እድር፤ በሞያ ማህበር፤ በፖለቲካ
ድርጅትና አመለካከት፤ በሃይማኖት አገርን ከውጭ ወራሪ ሃይል በጋራ
መመከትንና የጋራ ዜግነትን ወዘተ) መኖራቸዉ ግምት ውስጥ ያስገባል
እነዚህን በርካታ የግንኙነት ገመዶች ተጠቅሞ የህዝቦችን ግንኙነት
ማጠናከርና በአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና እድገት ማረጋገጥ ያስችላል
ይህ ሞዴል ለሀገረ መንግስት ምስረታ ልዩነትን ከማጉላት ይልቅ ህዝቦች
ለበርካታ ረዥም ዘመናት አብሮ የቆየ የንግድ፡ የጋብቻ፡ የአብሮ መኖር
መስተጋብር በመጉላት ያተኮረ ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርዓት
እንዲመሰርቱ ማድረግ ይቻላል ይላል፡፡
በህብረ-ብሔራዊ ሞዴል የሚቀርቡ ምሁራዊ ትችቶች
ከህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሶስት
ዋና ዋና የሆኑ አከራካሪ ጉዳዩች፣
የመንግስት መፍረስ (state disintegration)፤

የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነት ( political polarization)፤

የዉስጥ ህዳጣን ቡድኖች ( internal-minorities) መብት


አለመከበር ጋር ተያይዞ
1. የመንግስት መፍረስ (state disintegration)

ብሄርን መሰረት አድርገዉ ለተመሰረቱ ክልሎች ጠቃሚ የሆኑ


-ማበረታቻዎችን
- የፖለቲካል አቅም /ሀብት / በማቅረብ
 በተመረጡ የፖሊሲ መስኮች ቀላል የማይባል ስልጣን ያለዉ ራስ ገዝ የሆነ
የክልል ፓርላሜንት፤ ፈጻሚ አካልና ፓብሊክ ሰርቪስን በቀላሉ ወደ አንድ
ራሱን የቻለ ነጻ መንግስት ብሄራዊ ተቋማት መቀየር ይቻላል፡፡
ነገር ግን ህብረብሄራዊ የሆኑ ሃገሮች ለችግሮቹ የሚጋለጡት ፌደራል
ስለሆነ ሳይሆን ፌደራል የሆኑ ችግሮችን በአግባቡ ሰለማይፈቱና አሃዳዊ
ስርዓት የማይሆን አማራጭ ስለሆነባቸዉ ነዉ (ዋትሰ 2007)
2. ፖለቲካዊ ዋልታ ረገጥነት (political polarization)
ሌላዉ ህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ላይ የሚነሳዉ ትችት ብሄሮችን
መሰረት ያደረገ መልካምድራዊ አደረጃጀት በብሄሮች መካከል ያለ
ልዩነትን ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ ዋልታ ረገጥ የሆነ የፖለቲካ
አካሄድ አግባቦች እንዲጎለብቱ ያደርጋል የሚል ነዉ፡፡
ይህን በትንቅንቅ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ዳይናሚክ እንዲኖር
የሚያነሳሳዉ ምክንያት
-ህብረብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት ህጋዊ በሆነ መልኩ ለሁለት ለሚወዳደሩ
የብሄረ-መንግስት ፕሮጀክቶች እዉቅና ስለሚሰጥና የጋራ መንግስቱ ከራስ ገዝ
መንግስቱ ጋር ስለሚያፋጥጥ ነዉ (ሮደር 2009)
ለዚህ ችግር እንደ መፍትሄ የሚወሰደዉ

አንድ ፌደራላዊ ስርዓት ተሳስረዉ ለመቀጠል


የወሰኑ ብሄሮች
-ተወራራሽና ተመጋጋቢ የሆነ ማንነትን
እየገነቡ የመሄድ ነው፡፡
3. የዉስጥ ህዳጣን ቡድኖች (internal-minorties) መብት አለመከበር
ሌላዉ ሶስተኛዉ ትችት ከአፈጣጠሩ ከመነሻዉ መልከምድርና
ብሄርን በጥብቅ ማቆራኘት ጋር ተያይዞ የሚታየዉ ክፈተት ነዉ፡፡
ጽንሰ ሀሳቡ ለብሄሮች የሰፈሩበትን መልካዓምድር መሰረት አድረጎ
ራስ ገዝ አስተዳደር ሲሰጥ ብሄሮች የሚገኙበት መልካምድር
አንድ ወጥ የሆነ አድርጎ በማየት በተግባር በመሬት ላይ የሚታየዉን
ብዝሃነት ግንዛቤ ዉስጥ አላስገባም የሚል ነዉ፡፡
 አንዳንድ አጥኝዎች በንደፈ ሃሳብ ደረጃም ሆነ ከተግባራዊ
አፈጻጸም መነሳት በህብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ይህ እጥረት
እንደሚታይበት አጉልተዉ አሳይተዋል( ፓሌርሞ 2015 ‚ ኮስለር
2015)
ህብረብሄራዊ ፌደራሊዝም መድሃኒት ወይስ ርግማን?
 ዉይይቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ የወጡ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ
ደጋፊዎቹ እንደ መድሃኒት ሲያዩት የሚቃወሙት ደግሞ እንደ
ርግማን ያዩቷል፣
ሆኖም ህብረብሄራዊ ፌደራሊዝም መድሃኒት ነዉ ወይስ ርግማን?
 የሚለዉን ጥያቄ በተሟላ መልኩ መመለስ የማይቻልና
የህገመንግስታዊ ቅርጹን ብቻ አይቶ ይህ ነዉ ማለት አጠቃላይ
ስዕሉን አይሰጥም፣
 ጉዳዩ በነባራዊ ሁኔታዎች የሚወሰን ነዉ ብሎ መውሰድ የተሻለ
ነዉ፡፡
ህብረ-ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት እና የሃገራችን ነባራዊ
ሁኔታ
 የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሲዳሰስ ሀገራችን ህብረ-
ብሄራዊ የሆነች ሀገር መሆኗን እንደ ነበራዊ ሀቅ መወሰድ
ተገቢ ነዉ ፡፡
 ከአንድ ብሄር በላይ ለሀገሪቱ ፖለቲካ ወሳኝ በሆነበት
ሁኔታ፣
ተጽኖ ፈጣሪ ( አውራ) ወደ ሆነዉ አንድ ብሄር መዋጥ
ተግባራዊ ሊሆን የሚችል አማራጭ ሆኖ
የሚቀርብበት እድል በሌለበት ህብረ ብሄራዊ ስርዓት
የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
የተገኙ መልካም ነገሮች፣
የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል
በሕገመንግሥት ደረጃ ያረጋገጠ እና ተግባራዊ መደረግ የተጀመረ
መሆኑ
ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን በተግባር የሚገልጹበት
ሕዝባዊ ቦታ መገኘታቸው እና መግለጻቸው፣
በሌላው ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ እንዲታወቅ እና የሃገሪቱ
ባህል አንድ አካል መሆኑን እውቅና እንዲያገኝ መደረጉ
ማንነት የኩራት ምንጭ መሆን መጀመሩ
ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣
የብሔር መብትንና ሀገራዊ አንድነት አመጣጥኖ አለማየት፣
ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች መበራከትና ያልተመጣጠነ
እድገት እንዲኖር ማድረጉ
አካባቢያዊ አቅምንና ሀብትን በአንድ ማዕከል የማከማቸት ዝንባሌ
መኖር
ለሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን
ያለማከናወን፣
ስለፌዴራላዊ ሥርዓት አጠቃላይ ባህሪያት፣ ሥርዓቱ ስለሚገነባበት
እሴቶች እና መርሆዎች፣ እንዲሁም ሥርዓቱ የሚጋጥሙት
ተግዳሮቶች እየተፈቱ ስለሚሄዱበት አግባብ ተፈላጊው አመለካከት
እና አስተሳሰብ እንዲዳብር የተሠራው ሥራ አናሳ መሆን፣
ምክረ-ሃሳቦች
 በፌደራሊዝም ፅንሰ-ሃሳብ፤ ፍልስፍናና መንግስታዊ አስተዳደር
ሳይንሳዊ አረዳድ እና ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ መገንባት፤
 ፌደራሊዝም የዓለም ህዝቦች የሚመሩበት አንድ የመንግስታዊ አስተዳደር
እንጅ አንድ የሆነ ቡድን ኢትዮጵያ ላይ የጫነው ጉዳይ አይደለም፤
 ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያክሉ እና ከ28 ያላነሱ የተባበሩት መንግስታት አባል
አገራት የሚመሩበት እና ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ፤
 ፌደራሊዝም በክፍለ-ዘመናችን ከዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ቅርፅ እና
እሳቤዎች የሚመደብ መሆኑን ልብ ማለት ይጠቅማል፡፡
ምክረ ሃሳቦች፣
ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚያግዙ የጋራ እሴቶችን ለይቶ
መገንባት፣
 ብዝኃነትን ያከበረ የተሳሰረና የተዋሐደ ማንነት መገንባት
-ለዚህ አንዱ የሚመከረዉ ዜግነትን ከብሄር መነጠል ነዉ፡፡ ልዩነቱ ረቀቅ
ያለ ቢሆንም ጠቃሚ የሆነ ጉዳይ ነዉ
 ዜግነት የአንድ ሀገር አባል ከመሆን ጋራ የሚመጣ መብትና ግዴታ ሲሆን
የፖለተካዊና ህጋዊ ሁኔታን የሚያመላክት ስለሆነ በመርህ ደረጃ የተለያዩ ብሄራዊ
ማንነት ያላቸዉ ህዝቦች ነገር ግን በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ሊጋሩት የሚችል
ጉዳይ ነዉ፡፡
በሕዝቦችመካከል መተማመንን የሚፈጥሩ ተግባራትን ማከናወን
-ሕዝቦች ከሚለያያቸው የሚያገናኛቸው በርካታ ገመዶች
መኖራቸውን በማሳወቅ
-የእርቅና የአንድነት መድረኮችን በመፍጠር
-ሕዝቦቻችንን የሚያስተሳስሩት ድርብርብ ማንነቶች መኖራቸውን
በማሳየት፣
-የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉም ሚዛናቸውን የጠበቁ ማድረግ
- የሚወጡ ፖሊሲና የሕግ እይታዎችም በብዝኃነት እና በአንድነት
ዙሪያ ሚዛን የጠበቁ ማድረግን
መተማመንን የመፍጠር ሥራ መሥራት
 ከብሔረ-አገር ግንባታ እና ከህብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ጋር
የሚያያዙ የህዝብ መዋቅራዊ ጥያቄዎችን በብሄራዊ ምክክሩ (On
the coming national dialogue) ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት
ሰጥቶ መስራት፤
 ከህገ-መንግስት ጋር የተያያዙ መዋቅራዊ ጥያቄዎችን፤
 ከታሪክ ትርክት ጋር የተያያዙ አረዳዶችን፤
 ከሰንደቅ ዓላማ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ወ.ዘ.ተ …
የበይነ መንግሥታት ግንኙነቶችን ማጠናከር (ከክልል ክልል መንግስታዊና
ህዝባዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር)፤
የመንግሥታት ግንኙነት መጠናከር፣ በሚታወቅ እና መተንበይ በሚቻል
አግባብ መከናወኑ፣
-መንግሥታት እርስበርስ የሚደርጉት ግንኙነት በጨመረ ቁጥር
ትምምኑና ትብብሩ እየጨመረ መሄዱ በመካከላቸው የሚፈጠሩ
አለመግባባቶችን በቀላሉ ለመቅርፍ ያስችላል፡፡
-በጋራ በሚጋሩት ወሰን አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን ተጠቃሚ
የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ አቅደው የሚተገብሩበት እድል ሰፊ
ይሆናል፤
ለምሳሌ፡- የአማራና ቤንሻንጉል ክልል የጋራ ትብብር ፕሮጀክት፤ የአማራ
እና የአፋር ክልል የጋራ ትብብር ፕሮጀክት፤ የቤንሻንጉልና የኦሮሚያ
ክልል የጋራ ፕሮጀክት ጸ/ቤት ወ.ዘ.ተ… ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ሕገመንግሥታዊነትን ማስፈን
-የፌዴራል ሥርዓት አንዱ መገለጫው ሕገመንግሥታዊነቱ ነው።
-የፌዴራል ሥርዓት ያለ ሕገመንግሥት የማይታሰበውን ያህል
-ሕገመንግሥት ደግሞ ያለ ሕገመንግሥታዊነት የታሰበለትን ዓላማ
ሊያሳካ እና ዴሞክራቲክ የሆነ፣ የተረጋጋ እና ቀጣይነት ያለው
የፌዴራል ሥርዓት እውን ሊያደርግ አይችልም።
-ስለሆነም ሕገመንግሥታዊነትን ማክበር የሚያስችል
የአመለካከት እና የአስተሳሰብ ሥራዎችን መሥራት ይህን
በተግባር መግለጽ ያስፈልጋል::
ክፍል 3 - ህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት
እና የሰላም ግንባታ
የህብረ-ብሔራዊ የፌደራል ስርዓትና የሰላም ቁርኝት

 ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት በራሱ ተፈላጊ፣ ጠቃሚና ብዝኃነትን


ባቀፈ አንድነት ውሰጥ መኖር ለሰው ልጆች በራሱ የመጨረሻ ግብ ተደርጎ
ቢወሰድም ሥርዓቱ በትክክልና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መተግበር ለሰላም
ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
 በሰላም ጥናት፣ ሰላም የሚለው ጽንሰ ሃሳብ አሉታዊ መልክ ያለው ሰላም
(Negative Peace)፣ግጭት (ብጥብጥ ማቆም) አለመኖር እና
አዎንታዊ መልክ ያለው ሰላም (positive peace) ለግጭት መንስኤ
ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን ከመሠረቱ ለመለወጥ መዋቅራዊ ለውጥላይ
መሥራት፣ መዋቅራዊ የሆነ ግጭት አለመኖር፣ ማኅበራዊ ፍትሕ መኖር
ወዘተ… በሚያጠቃልል መልኩ ከፋፍሎ ማየት የተለመደ ነው (ጋልቱንግ
1975)።
የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ከመነሻው ……
በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የሚመሠረት እና ሁሉም ፍትሐዊ እና
ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በራስ አስተዳደር እና የጋራ አስተዳደር
የሚሳተፉበት፣
 የከባቢያቸውን አቅም እና ፍላጎት ከሀገራዊ ልማትና ፍላጎት ጋር
አስተሳስረው የሚተገብሩበት፣
 የእኩል ተጠቃሚነት ዕድል የሚፈጥሩበትና ማንም የማይገለልበት
ስለሚሆን አዎንታዊ ሰላም ለማስፈን የሚያስፈልጉ መዋቅራዊ ለውጦችን
በማምጣት፣
ማኅበራዊ ፍትሕን ማረጋገጥና መዋቅራዊ የሆኑ ግጭቶችን ማስወገድ
የአዎንታዊ ሰላም መሠረት አድርጎ ማየት ይቻላል።
ይህ የሚሆነው ግን ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ከተተገበረ እና
በዚህ ጽሑፍ ቀደም ባሉት ክፍሎች በዝርዝር የቀረቡት ለሥርዓቱ
ተግባራዊነት አስፈላጊ የሆኑ እሴቶችና መርሆዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ
እየዳበሩ ከሄዱ፣ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሚዛናዊ ሆኖ ሥርዓቱን
በሚያጠናክር መልኩ እየፈቱ ለመሄድ የሚያስችሉ ተቋማትንና የአሠራር
ሥርዓቶችን እያጠናከሩ መሄድ ሲቻል ነው።
 ከሰላም ጽንሰ ሃሳብ ጋር ተያይዞ ጆን ጋልቱንግ (1975) የሰላም ሦስቱ
ዘዴዎች ( three approaches to peace) ማለትም ሰላም
መጠበቅ (Peacekeeping)፣ ሰላም መፍጠር
(Peacemaking)፣ ሰላም መገንባት (Peace building) በሚል
ጽንሰ ሃሳቡን ይበልጥ ያብራራዋል።
ሰላም ግንባታ ግጭትን ከማስተዳደር እና ከመፍታት አልፎ ትራንስፎርም
የማድረግ ጉዳይ ይጨምራል።
ትራንስፎርም ለማድረግ ደግሞ ማካተትን፣ ሶሻላይዜሽን፣ ማኅበራዊ
ካፒታልን በግጭት ዙረያ ያለን አመለካከት እና አሰተሳሳብ መቀየርን፣
በማኅበረሰቡ ውስጥ እርስ በእርስ እና በመንግሥት እና ማኅበረሰብ
መካከል የሚኖሩ የግንኙነት አግባቦችን ማስተካከል ይጠይቃል።
 በሃገራችን አሉታዊ ሰላም እንኳ ለማምጣት ከሚታዩ ችግሮች እና
የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ራስን በራስ ከማስተዳደር፣ በጋራ
ጉዳዮች ላይ እኩል ተሳትፎ ከማድረግ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚከሰቱ
ችግሮች ምንጩ ሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት ነው የሚል እይታ
በተወሰኑ ክፍሎች እንዳለ ይታወቃል፡፡
 ሆኖም ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሚዛን ጠብቆ
ከተተገበረ የግጭት ምንጭ ሳይሆን በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ የሰላም
ግንባታ መሠረት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የእኔ ነው የማይለው
ሥርዓት ሰላምን ሊገነባ አይችልምና፡፡ ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት
ግን የሁሉንም ፍላጎት አንጻራዊ በሆነና በተሻለ መንገድ ማስተናገድ
የሚችል በመሆኑ ሰላምን ይገነባል።
 ከዚህም ሌላ የሰላም እሴቶችን ብንመለከት ለምሳሌ፡- መቻቻል፣
ዕውቅና መስጠት፣ መከባባር፣ የሃሳብ ልዩነትን መቀበል፣ የሰላም መገንቢያ
መሣሪያዎች ሲሆኑ እነዚህ እሴቶች የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት
እሴቶች በመሆናቸው የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ዴሞክራሲዊ
በሆነ አግባብ ማጠናከር የሰላም ግንባታ ጉዳይ ነው፡፡
ሌላው የግጭት መንስኤዎች እንደ ግጭቱ አውድ ብዙና የተለያዩ
ቢሆኑም ዙሮ ዙሮ በሃብት ላይ ከመወሰን ጋር ስለሚያያዝ ይህን
ውሳኔ ለመስጠት ከሚኖር ሥልጣን ጋር መቆራኘታቸው
አይቀርም፡፡
በመሆኑም ሰላም ለመገንባት ከሥልጣን ጋር ያለንን እይታ
ማስተካከል፣ የሕዝብን ልዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነትን መቀበልና
ለተፈጻሚነቱ መሥራት፣ ሥልጣን ለመያዝም ሆነ ለመልቀቅ
ሕገመንግሥታዊ ሥርዓትን ተከትሎ መሆን እዳለበት ማመንና
መቀበል በአጠቃላይ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት መገንባትንና
ሕገመንግሥታዊነትን መተግበር ይጠይቃል።
በመሆኑም በህብረ-ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ውስጥ ህገ-
መንግስታዊነት ከሰፈነ እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት በህዝቦች
መግባባት ቅቡልነት ካገኘ ሁሉም ጉዳይ በንግግር እና በውይይት፣ ሕግና
ሕግን ተከትሎ ስለሚፈጸም ቀጣይነት ያለው ሰላምን የማረጋገጥ እና
ሰላምን እየገነቡ መሄድ ያስችላል።
 ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሂደቱ አካታች እና ሁሉም አካላት በተለይም
ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ማኅበረሰቦች ድምጽ የሚሰማበትና ተሳትፏቸው
በተገቢው የሚረጋገጥበት መሆን ይኖርበታል።
 በተለይ በባለ ብዙ ብሔር፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወዘተ. በሆኑ ፌዴሬሽኖች ውስጥ
ውሳኝ ጉዳይ ይሆናል። የአመለካከት፣ የአስተሳሰብ ሆነ የባህል፣ የቋንቋ፣
የብሔር ብዙኃነትን በማካተት ሁሉንም የፌዴራል የስምምነቱ አካል
ማድረግ ጠቃሚ ነው። ይህ ጉዳይ የሕብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት
መሠረታዊ መገለጫ ስለሆነ ሁሉም ማኅበረሰብ የተካተተበት ሥርዓት፣
የሰላም ግንባታ መሠረት እንደሚሆን አጠያያቂ አይሆንም።
በመጨረሻም የሁሉም ነገር ግጭትም ሆነ ሰላም መነሻው ሃሳብ በመሆኑ
ሰላምን ለመገንባት ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሃሳብን የመገንቢያ ዘዴዎች፣
ሃሳብን የማዋዋጥ ዘዴ፣ የማስማማት ዘዴ፣ የመተባበር እና የማቀናጀት
ዘዴና እምነትን እየፈጠሩ የመሄድ ዘዴ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ዘዴዎች
ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት እየተገነባ የሚሄድባቸው ዘዴዎች
ስለሆኑ ሰላም ግንባታ እና ሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ግንባታን
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች አድርገው ያሳዩናል።
ማጠቃለያ
 ልዩነትን የሚያስተናገድ አንድነትን መገንባት ትልቅ የፖለቲካ ጥበብን
ይጠይቃል
አንድ ማንነትን መርጦ ከማጉላትና በዚሁ በተቃኘ የፖለቲካ እንቅስቃሴን
ከማራመድ የህዝቦችን በርካታ ማንነቶች (plural identities) ግምት
ያስገባ አካሄድን መከተል
ሚዛንን የጠበቀ አካሄድ መከተል
ሕገመንግሥታዊነት እና ፌዴራላዊ አስተሳሰብን እየገነቡ መሄድን
የሚጠይቅ ፌዴራላዊ ሂደት መሆኑን ግንዛቤ ያስገቡ ፖሊሲዎችንና
ስትራቴጅዎችን በየጊዜው እየነደፉ መንቀሳቀስ ይጠይቃል፡፡
“ሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ
ሰላም!”

You might also like