Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 11

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን

(ማርች 8) አስመልክቶ
ተዘጋጀ ሰነድ
ዲላሜ ደመቀ
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8
•ማርች 8 ሴቶች ከሚደርስባቸዉ የመብት ጥሰትና ጭቆና ተላቀዉ ወደተሻለ ጉዞ
ተሸጋግረዉ የተሰጣቸን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡና በማንኛዉም የስራ መስክ
የመሰማራትና (አመራር ሰጭነት) መብታቸዉን ለማስጠበቅ በየዓመቱ የሚያከብሩት
በዓል ነው
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሚከበርበት ዓላማ

•አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሚከበርበት ዋናዉ አላማ፡-


•ሴቶችን በቀደሙት ትዉልዶች ከነበሩበት አዘቀት አላቅቆ ወደ ተሻለ ነገር እንዲሸጋገሩ እና
ከነበረባቸዉ ድርብርብ ተጽኖ ተላቀዉ በማህበረሰቡ የደረሰባቸዉን ጭቆና ተጋፍጠዉ ማህበራዊ
፣ኢኮኖሚያዊ፣ባህላዊ እና ፖለቲከዊ አቅማቸዉን ከፍ ለማድረግ አለም አቀፍ ማህበረስብም ለህቱ
ጠባቂ በመሆንና በተለያዩ ችግሮቻቸዉ በመድረስ ጠንካራ ሰራተኛና ጠንካራ መሪ ለመሆን
•ጠንክሮ መስራት በየደረጃዉ ያለዉን ኃላፊነት በመቀበል አርያ ሆኖ መገኘት፤
•እንደ ተgማችንም የተgሙ ሴት ሰራተኞች ሙሉ መብታቸዉ ተከብሮ በተመደቡበት የስራ መደብ
በነጻነት ቅንነትና ትጋት በተሞላበት መንፈስ እንዲሰሩ ግንዛቤ ለመፈጠር ነዉ።
የማርች 8 ታሪካዊ ዳራ
• በየዓመቱ የካቲት29(march8) ቀን የዓለም የሴቶች ቀን ይከበራል።
• ከዚህ የሴቶች ቀን ጋር በተያያዘ የመብት እና የእኩልነት ጥያቄዎች አብረው ይነሳሉ።
• አንድ የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያመላክተው በዓለም ላይ 143 ሃገራት የሴቶች እና ወንዶች
እኩልነትን በሕገ መንግሥታቸው ላይ ያሰፈሩ ቢሆንም ስምንት ሃገራት ማለትም ቤልጄም፣ ካናዳ፣
ዴንማርክ፣ ሲውዲን፣ አይስላንድ፣ ሉክስንበርግ፤ ፈረንሳይ እና ሊትዌኒያ ብቻ ናቸው የሴቶች እና
የወንዶች እኩልነት መብትን የሚያረጋግጡት። ጥናቱ ትኩረቱን ያደረገውም ሥራን፣ የቤተሰብ፣
የንብረት ባለቤትነት፣ የጡረታን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ላይ ተመርኩዞ ነው።  
ነገር ግን እስካሁን በየትኛውም ሀገር የወንድ እና የሴቶች እኩልነት ሙሉ በሙሉ አለመረጋገጡን ነው
የግሎባል ጀንደር ጋፕ መዘርዝር የሚጠቁመው።
እንዴት ተጀመረ?

•የክብረ በዓሉ ጅማሮ በአዉሮጃዉያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1908 ነዉ።በወቅቱ አስራ አምስት ሺ (15000) የሚሆኑሴቶች
በኒዉዮርክ ከተማ ላይ የስራ ሰዓት መሻሻል (ማጠር) የተሻለ ክፍያና ሴቶች በምርጫ መሳተፍ አለባቸዉ በሚል የተቃዉሞ
ሰልፍ አካሄዱ። ከአንድ አመት በኃላም የአሜሪካ ሶሻሊስት ፓርቲ የመጀመሪያዉን የሴቶች ቀን አወጀ።
•ቀኑን አለም አቀፍ የማድረግ ሀሳቡ የመጣዉ ክላራዜትኪን በምትባል ግለሰብ አማካኝነት ነዉ።በዴንማርክ ኮፐንሃገን
ተወላጅ በሆነችዉ ኮፐንሃገን በአዉሮፓዉያኑ ዘመን አቆጠተር በ1910 ዓ.ም የሴት ሰራተኞች ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ
ነበር ሃሳቡን ያነሳችዉ ።
•በወቅቱ ከ17 ሀገሮች የተዉጣጡ100 ሴቶች የተሳተፉበት ሲሆን በሰጠችዉ ሃሳብ ሙሉበሙሉ ነዉ
የተስማሙበት።ለመጀመሪያ ጊዜም በኦስተሪ፣ዴንማርክ ፣ጀርመንና ሲዊዘርላንድ እንደ አዉሮፓዉያን ዘመን አቆጣጠር
1911ዓም ተከበረ በአሉም በአለም አቀፍ ደረጃ የፋዊ ሆኖ መከበር የጀመርዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ክብረ
በዓሉን ማክበር በጀመረዉ በአዉሮፓዊኑ ዘመን አቆጣጠር በ1975ዓም ነዉ።
•ለመጀመሪያ ጊዜ’’ያለፈዉን ማክበር የወደፊቱን ማቀድ’’በሚል የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ባወጣዉ መሪ -ቃል በ1996ዓም በአለም አቀፍ ደረጃ በደመቀ
ሁኔታ ተከበረ።
በተለያዩ ሃገራት ማርች 8 አከባበር ሁኔታ
• በሩሲያ ዕለቷ ሶስት አራት ቀናት ሲቀራት አበቦች በመሰጣጣት የከበራል
• በቻይና የአገሪቷ ምክር ቤት ባስቀመጠው መሰረት ሴቶች በዚያች ቀን ግማሽ ቀን ብቻ
እንዲሰሩና ግማሽ ቀን እንዲያርፉ ቢደረግም በርካታ አሰሪዎች ሁልጊዜም ይህን አይከተሉትም
• በጣልያን ላ ፌስታ ዴላ ዶና ተብላ የምትጠራው ይህች ዕለት ሚሞሳ ተብላ የምትጠራውን
አበባ ስጦታ በመለዋወጥ ያከብሯታል።
• አሜሪካ ሙሉ የማርች (የመጋቢት) ወር የሴቶች ታሪክ ወር የሚል ዕውቅና ተሰጥቷል።
በአገሪቱ መሪዎች ዘንድ ዕውቅና በተሰጣት በዚች ወርም የአሜሪካ ሴቶች አስተዋፅኦ
ይዘከራል።
በሃገራችን ኢትዮጵያ…
 በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት
ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ (የህክምና፣ የተዋልዶ ጤና፣የምግብ፣የንጽህና መስጫ፣
የአልባሳት፣ የመጠለያ)
 ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች በዘላቂነት የሚቋቋሙባቸውን የስራ መስኮች/የገቢ ማስገኛዎች
መለየት
 ሙያዊ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ
 የመነሻ ካፒታል/ብድር ማፈላለግ
የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 መሪቃል
• በዓሉ በዚህ መሪ-ቃል መከበር ያስፈለገበት ዋናዉ ዓላማ የልማት ሃይል የሆኑትን የሀገራችን
ሴቶች ማንኛዉም ማህበረሰብ ችግራቸዉን በመረዳት ለማገዝ ያላቸዉ ኃላፊነት ከፍተኛ
መሆኑን ለማስገንዘብ እና እያንዳንዱ ማህበረሰብ እኔ የህቴ ጠባቂ ነኝ ብሎ ራሱን በማሳመን
ለሴቶች እንክብካቤ እና ድጋፍ በማድረግ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያሳድጉበት መንገድ መፍጠር
ነዉ።
• በመሆኑም ማንኛዉም ሴት ከወንዶች ጎን(እኩል) በመቆም በማንኛዉም የስራ ኃላፊነት እኩል
ተሳትፊ መሆን ያለባት መሆኑአን ለማስገንዘብና በቤት ዉስጥ የሚደርስባትን ጫና ለማቃለል
ማንኛዉም ማህበረሰብ ከጎኑአ ያለ መሆኑን ለማስረጽ “እኔ የህቴ ጠባቂ ነኝ‘’ በሚል መሪ-ቃል
የሴቶችን የብልጽግና ጉዞ ለማሻገር ንቅናቄ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ።
የዘንድሮ ማርች 8
• የዓለም ዐቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 “ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት”
በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ47ኛ ጊዜ ተከብል።
• መሪ ቃሉ ሁሉን አካታች የዲጂታል አገልግሎትን ለማስፋት የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት
ላይ መስራት በማስፈለጉ ነው የተመረጠው፡፡
• ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፆታ እኩልነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ዙሪያ በስፋት
መስራት እና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን በማዳበር በሴቶች የኢኮኖሚ አቅምን
የማመጣጠን ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል፡፡
ከተቋማችን አንጻር
• የሴቶች አቅም ለማጎልበት የተላያዩ ስራዎችን መስራት
• ሴቶች የንግግር ክህሎታቸዉን የሚያዳብሩበት ስልጠና ማዘጋጀት
• ሴቶች በተቋሙ ማንኛውም ተግባር ላይ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአሰራር ስርዓት
መዘርጋት
• የላቀ አፈፃፀም ያላቸውን ሴት ሰራተኞች ማበረታታት
• የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በፆታና በእድሜ የተተነተነ
መረጃ ማድረስ

You might also like