Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 15

በምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ እና በቆላድባ ከተማ

አስተዳደር ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን የእርስበርስ


ግድያ አስመልክቶ የቀረበ የዳሰሳ ጥናት
ሀ.የጥናቱ መነሻ ምክንያት ፣
1. በወረዳው ውስጥ እየተፈፀመ ያለው የግድያ ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጨመረ በመምጣቱ፤
2. በዚህ ግድያ እየደረሠ ያለውን የሠው ልጅ እልቂት ያስከተለውን ሠብአዊ
ጉዳት ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስናልቦናዊ ጉዳት ስፋትንና ጥልቀቱን ተረድቶ
መፍትሔ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
3. ይህን የግድያ ወንጀል ለመቀነስ ብሎም ለማስቆም የሁሉም አካላት ርብርብ
አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
ለ. ከጥናቱም ሆነ ከውይይቱ የሚጠበቅ ውጤት
 ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኝ በፍጥነት ምላሽ መስጠት፣
 ችግሩን በውል መረዳት እና ምክንያቶችን ማወቅ ፣
 የቅድመ መከላከል ስራ መስራት ፣
 በመጨረሻም እየተፈጸመ ያለውን ግድያ ማስቆም።
ሐ. የዚህ የዳሰሳ ጥናት አካሔድ
ከ2010 እስከ 2015 ግማሽ ዓመት ድረስ የተፈፀመ ግድያን የሚሸፍን ሲሆን
የተጠቀምነው ዘዴ፦
 የስልክ ቃለ መጠየቅ በማድረግ ከዚህ ቀደም የነበሩትንና አሁን በስራ ላይ
ያሉትን የቀበሌ አመራሮችን ፣
 የሠላም ኮሚቴዎችን እና ግለሰቦችን፣
 የህግ ባለሙያዎችን የፖሊስ አባላትን ቃል በማካተት።
 ከሰነድ እናመዛግበት አንጻርም፦ የምርመራ መዛግብትን፣ የ24 ሠዓት መረጃን
፣ የፖሊስን የሲአር መዝገብን፣የዓቃቢህግ የቀዳሚ ምርመራ መዛግብትንና
የፍ/ቤት ውሳኔዎችን በመጠቀም የተከናወነ የዳሰሳ ጥናት ነው።
መ. በዳሠሣ ጥናቱ የተገኙ ዋናዋና ግኝቶች

፩. የግድያን ስፋት ለመለየት ተችሏል


በዚህ መሠረት፦
በ2010 ዓ.ም 41 ሠው
በ2011 .. 32 ሠው
በ2012 .. 45 ሠው
በ2013 .. 55 ሠው
በ2014 .. 67 ሠው
በ2015 .. 29 ሠው ድምር 269 ተገድሏል።
በቀበሌ ደረጃ ስንመለከት ከፍተኛ ግድያ የተፈጸመባቸው ቀበሌወች ጣናወይና 25፣
አድስጌ 19፣ ደ/ዙሪያ17፣ አረቢያ 15 ፣ አቸራ 12 ፣ አይንባ10፣ ሰንበት ደብር 9
ሠው በግድያ ምክኒያት ህይወቱን ያጣ ሲሆን፤
አነስተኛ ሠው የተገደለባቸውን ስንመለከት ደግሞ ግራርጌ፣ ሱፋንቃራ ፣ ባላንገብና ቡዋ
ናቸው ።
የገደለውን ሰው የዕድሜ ሁኔታ ስንመለከት በአብዛኛው
ከ22 ዓመት እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ናቸው፡፡
ከዚህ አሃዝ የምንገነዘበው
1.ግድያ ከዓመት ዓመት ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መሔዱ
2. ሠው የማይገደልበት ቀበሌ የሌለ ቢሆንም በከፍተኛ ደረጃ ሠው
የሚሞትባቸው ቀበሌዎች በውል የታወቁት ከ10 የማይበልጡ ናቸው
3. ወንጀል ፈፃሚዎቹ በአብዛኛው ከ30 ዓመት በታች መሆናቸውን
ያሣየናል፡፡
4. ከፍተኛ የሆነ ሠብአዊ እልቂት በግድያ ምክንያት መከሠቱን እንረዳለን

፪. የግድያውን መንስኤ ለማወቅ


ተችሏል
በዚህ መሰረት፦
1.በደም ምለሣ የሞተው 92 ሠው፣
2.በእለታዊ ግጭት የሞተው 46 ሠው፣
3.በመሬት ምክንያት የሞተው 35 ሠው፣
4. ከጦር መሣሪያ አያያዝ ጉድለትና ጥይት ተኩስ 29 ሠው
5. በውንብድና /ዝርፊያ የሞተው 25 ሠው
6. በማይታወቅ ምክንያት /ተጠርጣሪው ያልታወቀ/23 ሠው
7. ሴትን ምክንያት በማድረግ 19 ሠው
ከዚህ አሃዝ የምንረዳው፦
1.በደም ምለሣ ምክንያት የሚሞተው ከፍተኛውን ቁጥር ይዟል
የአስከፊነቱ ጥግ፦
 የገደለው አይሞትም በጉዳዩ ላይ የሌሉበት፣ ሥለ መፈፀሙም
ምንም እውቅና የሌላቸው መሞታቸው
 የዝምድና ደረጃው ራቅ ያለውን ጭምር መሞቱ
 አንድ ተገድሎበት እያለ ተጨማሪ ሰው መግደሉ
 መገዳደሉ መቆሚያ የሌለው መሆኑ
 እርቅ ከተፈፀመ በሗላ ጭምር እርቅን አፍርሦና መተማመን
አጥፍቶ ግድያ የሚፈፀም መሆኑ
 አጥፊው በህግ እርምጃ ከተወሰደበት በሗላም ጭምር ታርሞ
ከወጣ በሗላ የሚገደል መሆኑ
2. በእለታዊ ግጭት የሚሞተውን በተመለከተ
 የሚጋደሉት በሠላም አብረው ቆይተው ድንገት በተፈጠረ ግጭት
ነው
ይህ የራሡ አባባሽ ምክንያት አለው እነሱም
 አስካሪ መጠቶች እስከ ገጠር ቀበሌ በስፋት መሰራጨቱ፣
 የጦር መሣሪያን መጠጥ ቤት ይዞ መግባቱ እርምጃው ፈጣን
እንዲሆን አድርጓል፣
 የሥራ አጥ መብዛትና ቁማር ቤቶችና አልባሌ መዋያዎች በስፋት
መኖራቸው፣
3. በመሬት ምክንያት የሚሞተውን በተመለከተ አባባሽ ምክንያቶች
1.ቤተሠብ አድሏዊ በሆነ መንገድ ከመሬት ውርስ መንቀል፣
2. መሬት አስተዳደር በሚሠጣቸው ትክክል ያልሆኑ
ማስረጃወች፣የቀበሌ የመሬት ኮሚቴ ፣ከወል መሬት ጋር
በተያያዘ፣የማ/ፍርድ ብቶች ሀሰተኛ ውሳኔና የእርቅ ዉሎች
3.የፍትህ አካላት በሚሰጡት የተዛባ ውሳኔ ፣የማ/ፍርድ ቤቶች ሀሰተኛ
ውሳኔና የእርቅ ዉሎች እንዳለ ሆኖ የተወሰነባቸውም ውሳኔውን
ባለመቀበል መብት ባገኘው ተከራካሪ ላይ የግድያ እርምጃ
መውሰዱ ማሳያ ጃንጓ ፣ አንባጓሊት ፣ገንደዋ ወንድም ወንድሙን
ወይም ግድያው በቤተሠብ መካከል እንዲሆን አድርጓል።
4. ከጦር መሳሪያ አያያዝ ጉድለት እና ጥይት ተኩስ አንፃር
1.ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ላይ በተለይ በለቅሦ ፣ በሠርግ ፣ በክርስትና
በሌሎች በሚተኮስ ጥይት እና መሣሪያ በመባረቁ ምክንያት
2. የጦርመሣሪያ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር
1177/2012 በአግባቡ ስራ ላይ ባለማዋሉ ምክንያት
3. የጦር መሳሪያ መብዛቱ እና ልቅ መሆኑ የራሳቸውን ቤተሠብ
ጭምር የሚገደሉበት ሁኔታ መኖሩ በተለይም የደ
5. በወንብድና አማካኝነት የሚፈፀም ግድያን በተመለከተ
የሚፈፀመው ፡-
1.የጦር መሣሪያን ለመውሠድ፣
2. የቤት እንሰሳት ለመውሠድ፣
3.ሌሎች የገንዘ ብጥቅሞችን ለመውሠድ፣
ማሣያዎች፡ ፈንጃ ቆብላ የተፈፀመው፣ ሠራቫ ዳብሎ፣ ቆላድባ
ከተማ የተፈፀሙ የውንብድና ወንጀሎች ህይዎትን የቀጠፋ
ናቸው።
6. በማይታወቅ ምክንያት የተገደሉ
 ሰው በከንቱ መቶ መገኘት ምክንያቱ ከላይ የተገለፀት ውስጥ
አንዱ ሊሆን እንደሚችል ቢገመትም በትክክል ምክንያቱን
ለማወቅ አይቻልም፡፡
7. ከሴት ጋር የተያያዙ ምክንያቶች
1.አብረዋቸው የኖሩትን የትዳር አጋር በልጃቻቸው ፊት በመግደል
2. የፈታትን ሚስት ያገባውን ሰው በመግደል
እነዚህ ከዚህ በላይ የተገለጹት በቀጥታለግድያ ምክንያት ሊሆኑ
የሚችሉ ሲሆን
አባባሽ ወይም ቀጥተኛ ያልሆኑ ምክንያቶች
ሀ የማህረሰቡ ችግር/ተራው ማህረሰብ/
 ግድያን አለማውገዝ
 ደም መመላለስን እንደ ጀግንነት መለኪያ መቆጠሩ
 ደም ያልመለሰን ዝቅ አድርጎ ማየቱ
 ገዳዩን በመያዝ ሂደት አጋዥ አለመሆኑ
 እውነትን ለመመስከር አለመፈለጉ
 አጥፊዎችን ለህግ አሳልፎ አለመስጠቱ
ለ.የተማረው ህብረተሰብ ክፍል
 ቤተሠቡን መለወጥ አለመፈለጉ /አለመቻሉ
 አንዳንዱ መሣሪያ ጭምር ገዝቶ የሚሰጥ መሆኑ
 አጥፊውን በህግ ሲያዝ ጉዳዩን ለማበላሸት የሚደረግ ጥረት
መኖሩ
ሐ. የፀጥታ አካላት
 የወንጀል ስጋቶችን ቀድሞ ያለማምከን
 ተፈላጊውን ተባብሮ ያለመያዝ ፣
 በኦፕሬሽን ወቅት ሚስጥር ማውጣት
 መ.የፍትህ አካላት
 የቅድመ መከላከል ሥራ አናሣ መሆን ፣
 የግንዛቤ ስራ እጥረት ፣
 የምርመራ ጥራት ችግር፣
 ከክስ ጋር የተያያዙ ችግሮች ፣
 የፍርድ ወይም የቅጣት ተመጣጣኝነት ችግር፣
 ነፃ መልቀቅ ፣
 ፍርደኛን ቀጣቱን ሳይጨርስ በአሞክሮና በይቅርታ በፍጥነት መልቀቅ፣

፫. እየተፈፀመ ያለው የግድያወንጀል ምን


ጉዳት እንዳአስከተለ ለማወቅ ተችሏል።
ሀ· ሠብአዊ ጉዳቱ
• የሠው ልጅ በህይዎት የመኖር መብት አለው ይህን መብቱን በህግ በተደነገገ
ከባድ ወንጀል ሲፈፅም የሞት ቅጣት ሲፈረድካልሆነ በቀር
ውጭ በምንም መልኩ ሠው ህይዎቱን አያጣም ።
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 15
 አለምአቀፍ የሠብአዊ መብት ዲክላሬሽን በአንቀፅ 3 ፡፡
በወረዳችን ከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ በግድያ
ምክኒያትየሚሞተው ሰው ሲታይ በህይወት የመኖር ሰብአዊ
መብት ከመጣሱም በላይ እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ጉዳት ከፍተኛ
ነው።
ለ· ማህበራዊ ጉዳት
 ልጆች ያላሣዳጊ እየቀሩ ነው፣
 ቤተሰብ እየተበተነ ነው፣
ለምሣሌ፡- 269 ሟቾች አሉ በውስጣቸው በአማካኝ 4
ቤተሠብ አሉ ብንል 1076 ቤተሠብ ይበተናል ማለት ነው
/ያለተንከባካቢ እየቀረ ነው
የሚፈናቀለውን እንይ፡- 321 ተጠርጣሪ እና ፍርደኛ አለ
321X4 = 1284 ሠው እየተፈናቀለ ነው አሁን አሁን የመች
ቤተሰብም እየተፈናቀለ ነው።
ሐ.ኢኮኖሚያዊ ጉዳት
 አምራች ነው የሚፈናቀለው፣
 ሠፊ መሬት ጦም እያደረ ነው፣
 ቤት እየተቃጠለ ነው ፣
 እንሰሳት እየሞቱ ነው ፣
መ.የስነ-ልቦና ጉዳት
 የገዳይም ሆነ የሟች ቤተሠብ በጭንቀት ፣ በሃዘን እና ፍርሃት
ውስጥ ናቸው
 ከዛሬ ነገ በእኔ ላይ ደም ይመለሣል የሚለው ስጋት ብዙ ነው፡፡
፬.መወሠድ ያለበት መፍትሔለመለየት አስችሏል
 ሁላችንም ሚናችን መወጣት ይገባል፣
 የቅድመ መከላከል ሥራ መስራት፣
 የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ በስፋት መስራት ፣
 በአጥፊዎች ላይ ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ/ተመጣጣኝ
ቅጣት መጣል ፣
 ፍርደኛ ፍርዱን ጨርሶ እንዲወጣ ማድረግ፣
 የሠላም ኮሚቴን በማጠናከር እርቅን ተግባራዊ ማድረግ ፣
 የፍትህ አካልት በዚህ ጉዳይ ላይ በልዩ ትኩረት በቅንጅት እንዲሰሩ
ማድረግ ፣
 ጥራቱን የጠበቀ ምርመራ፣ ክስ እና ፍርድ እንዲኖር መስራት
 ከህግ የራቁ ተጠርጣሪዎችና ፍርደኞችን ወደ ህግ ማቅረብ ዋና
ዋናዎች ናቸው፡፡
አመሰግናለሁ//

You might also like