Professional Documents
Culture Documents
ስምምነት ሰነድ
ስምምነት ሰነድ
ስምምነት ሰነድ
ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ከጽ/ቤቶች መካከል የተደረገ ትስስር ሰነድ
ለ2ዐ15 በጀት ዓመት እቅድ ትግበራ የተዘጋጀ
ነሀሴ 2ዐ14 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
መግቢያ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ የማገናኘት
ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ፅ/ቤቱ ያቀዳቸው የስራ እቅዶች በተቀናጀና በተሳካ ሁኔታ
ለማከናወን ከሚመለከታቸው አካላትና ተቋማት ጋር የውጭ ትስስር ሰነድ መፈራረም
አስፈላጊ መሆኑን ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ይህ የ2015 በጀት ዓመት የውጭ የስምምነት ሰነድ በበጀት አመቱ የሚታቀዱትን
እቅዶችና የሚወረዱት ስኮር ካርዶች አፈፃፀም እንዲሁም አገልግሎቱን ለተገልጋዩ ተደራሽና
ቀልጣፋ ለማድረግ በክፍለ ከተማው ካሉ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የስራ ትስስር ሰነድ
እንደሚከተለው ተዘጋጅተዋል ፡፡
የትስስሩ አላማ
በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስር ካሉ ተቋማት ጋር በትስስር በሚከናወኑ ተግባራት ላይ እርስ በርስ
በመቀናጀትና በመደጋገፍ ፅህፈት ቤቱ ያቀዳቸው እቅዶችና ያስቀመጣቸውን ግቦች በስኬት
ለማከናወን ፡፡
የትስስሩ ወሰን
የጋራ ስምምነቱ ጽህፈት ቤቱ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ ጽህፈት
ቤቶችና ባለድርሻ አካላት መካከል ይሆናል ፡፡
ስምምነቱ የሚቆይበት ጊዜ
የተቋሙ ተልዕኮ
በቢሮው የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም ዘመናዊ ፣ግልጽ እና ፈጣን ምላሽ
መስጠትን ባህሉ ያደረገ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋትና በዘርፉ መሪ ሚና በመጫወት
ብሎም በመንግስትና በህዝብ መካከል ጥራት ያለውና እና ለሁሉም ነዋሪ ተደራሽ የመረጃ
ፍሰት እንዲኖር በማድረግ፡-
የህዝብን ትክክለኛ የመረጃ ፍላጎት ማርካት ፤ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን በቀጣይነት ማሳደግ
የሀገራችንና የከተማዋን መልካም ገጽታ መገንባት፤
በዋና ዋና ሀገራዊና ከተማ አቀፋዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባበትን መፍጠር፤
የጥቆማና እቅድ ዜና
ሁነቶችን ማደራጀት
አካቢያዊ ቅኝት
የመጽሄት ዝግጅት
የብሮሽር ዝግጅት