Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 36

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር

አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፍ ማስፈጸሚያ ማንዋል

ሰኔ 2014 ዓ.ም

አዋሳ
መግቢያ

አደረጃጀትና
ይዘት ቅንጅታዊ አሰራር

ዓላማ

ትርጓሜ የድጋፍ ስልቶች


መርሆዎች
1. መግቢያ
 ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ የድጋፍ አይነት ነው፤

አንድን አምራች ኢንተርፕራይዝ በገበያው ተወዳዳሪነት ልቆ እንዲገኝ ከሚያደርጉት

ጉዳዮች ውስጥ ውጤታማ ቴክኖሎጂ፣ የበቃና ታታሪ የሰው ሀይል ዋነኞቹ ናቸው፤

3
የቀጠለ

ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠሪያና ለአገራዊ የምርት መጠን ድርሻ ዕድገት ሰፊ ድርሻ አላቸው፤

 ተኪ ምርት በማምረትና በኤክስፖርት ገበያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፤

በሀገር ውስጥ የፈጠራ ስራዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፡፡

4
የቀጠለ

• በምርት ጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዙሪያ ቁልፍ ማነቆዎችን ለመለየትና


ለመፍታት ይህ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት
(የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/ካይዘን/፣ የቴክኒካል ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ አቅም
ግንባታ እና የኢንተርፕሩነርሽፕና ንግድ ልማት አገልግሎት) የድጋፍ ማእቀፍ
ማስፈጸሚያ ማንዋል ተዘጋጅቷል ፡፡

5
2. አጭር ርዕስ

ይህ ማንዋል የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፍ


ማስፈጸሚያ ማንዋል ተብሎ ሊጠራ ይችላል፤

6
3.ትርጓሜ
 የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ ማለት
የኢንዱስትሪዎችን ችግር የለየና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ
 የኢንተርፕሩነርሺፕ፣ ንግድ ልማትና የምክር አገልግሎት፣

 የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/kaizen/፤


 የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ እና
 የቴክኖሎጂ ድጋፍን መሰረት በማድረግ የተሟላ መረጃ በማጠናከር ድጋፍ የመስጠት ሂደት ነው::

7
የቀጠለ
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ባለሙያ ማለት

ለኢንተርፕራይዞች እንደየ እድገት ደረጃቸው የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ


ሽግግር አገልግሎት ለመስጠት የተመደበ ባለሙያ ነው፡፡

8
የቀጠለ
አምራች ማለት

- የተለያዩ ግብዓቶችን

- የማምረቻ መሳሪያዎችና ማሽኖችን

- ሂደቶችን በመጠቀም

- በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ

- የተጠናቀቁ ምርቶችን

- የሚያመርት ድርጅት ወይም ግለሰብ ነው ፡፡

9
የቀጠለ
 ቴክኖሎጂ ማለት
አንድን ግብዓት በቀላሉ ገበያ ላይ ሊውል ወደሚችል ምርት የመለወጥ ሂደት ነው፤
• ቁሳዊ ቴክኖሎጂ (Technoware) - ምሳሌ- ኮምፒውተር

• ዕውቀታዊ ቴክኖሎጂ (Humanware) - ምሳሌ- ልምድና ተሞክሮዎች

• ሰነዳዊ ቴክኖሎጂ (Infoware) - ምሳሌ - ማንዋሎችና ዲዛይኖች

• ድርጊታዊ ቴክኖሎጂ (Orgaware) – ምሳሌ - አደረጃጀቶች አሰራሮችን ያካትታል፡፡

10
የቀጠለ

የቴክኖሎጂ ሽግግር ማለት


የአመራረት ሂደትን ለማሻሻል እና በማባዛት ስርአት ያለውን ዕውቀት ማስተላለፍ ነው፤

11
የቀጠለ
ተቁ እየተሰራበት ያለ በመፅደቅ ሂደት ላይ ያለ
የአምራች ኢንዱስትሪው መረጃ
ገንዘብ (ብር) የሰው ኃይል ገንዘብ (ብር) የሰው ኃይል

1 ጥቃቅን ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ < 100ሺ <6 ≤ 250 ሺ < 10

2 አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ 100ሺ1-1.5ሚ 6 -30 250ሺ1-4ሚ 11 - 50

3 መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ 1.5ሚ1-20ሚ 31- 100 4ሚ1-40ሚ 51 - 100

4 ከፍተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ >20ሚ >100 >40ሚ >100

የሰው ሀይል ይዘቱ የኢንዱስትሪዉን ባለቤት፣ የቤተሰቡን አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ ነው፡፡

12
ዓላማ
 የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን አቅም ማጎልበት፤

 የምርት ጥራትና ምርታማነትን ወደ ተሻለ ደረጃ በየጊዜው ማሳደግ፤

 ኢንተርፕራይዞች በቴክኒክ፣ በቴክኖሎጂ፣ በአሰራርና በዋጋ ተወዳዳሪና ትርፋማ እንዲሆኑ ማድረግ፣

 ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን እንዲተገብሩ ማድረግ፤

 ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እየተፈጠረ እንዲሄድ ማድረግ፤

 የኢንዱስትሪዎቹን አገራዊ የምርት መጠን ድርሻ ማሳደግ፤

13
5. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የድጋፍ
ማዕቀፍ አስፈላጊነት
• ችግር የለየና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የኢንተርፕሩነርሺፕ የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ/kaizen/
የቴክኒካል ክህሎት የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ የምክር አገልግሎት የአሰራርና የአደረጃጀት ድጋፍ ለማድግ
ነው፡፡

• አምራች ኢንዱስትሪው በኢኮኖሚው የመሪነቱን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ

• በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚገኙ ማነቆዎች ለመፍታት

• ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማሰራጨትን ለማካተት የሚደረግ ድጋፍ ለማሳለጥ

14
6. የማኑዋሉ የተፈፃሚነትወሰን

• ተደራጅተው ወይም በግላቸው የሚያመርቱትና ከአገልግሎት ወደ አምራች ዘርፍ የመጡት

የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ላይ ተግባራዊ ይሆናል

15
7. የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር
አገልግሎት መርሆዎች

• የከፍተኛው ኢንዱስትሪ መሰረት መሆናቸውን መረዳት

• ግልጽነት፣ ፍትሀዊ፣ ተጠያቂነትና ታማኝነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት

• ለስርአተ ጾታ ለአካል ጉዳተኞችና ለኤች አይ ቪ ኤይድስ ተጠቂዎች ትኩረት መስጠት

• ሞዴል ኢንዱስትሪዎችን መነሻ በማድረግ ድጋፉን መሰጠት

16
የቀጠለ

• በኢንዱስትሪው ውስጥ የፈጠራ ስራዎችንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉ ማድረግ፤

• የሰው ሀይል ጉልበትን በሰፊው የሚጠቀም የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫ መከተል፤

• የድጋፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ከተለያዩ ተቀማት ጋር በቅንጅት መስራት፤

• የኢንዱስትሪዎች እድገትና ጥቅም የእኔም ጥቅም ነው ብሎ በማመን ድጋፍ ማድረግ፤

17
የቀጠለ

በድጋፎቹ ውስጥ የጠባቂነት አመለካከት የሚያነጥፍ ስርዓት መከተል፤

በምርታማነት በጥራት ደረጃና በዋጋ ላይ የተመሰረተ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የገበያ ተወዳዳሪነት

ቀልጣፋ ስርዓት መከተል፤

የምርታመነትንና የተኪ ምርትን የአሰራር ስርአት አቅጣጫ መከተል፤

 አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ላይ ያተኮረ የአሰራር አቅጣጫ መከተል፤

18
8. የአገልግሎቱ የድጋፍ ስልቶች
• ድጋፉ በመስኩ የሙያው ባለቤቶች እንዲሰጥ ማድረግ

• ከአገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ለሚያደርጉ ትኩረት ሰጥቶ መደገፍ

• ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ወደ ዘርፉ ለሚቀለላቀሉ ትኩረት መስጠት

• ከሙያ ደረጃ የብቃት አሀዶች በመነሳት ስልጠና መስጠት

• ያደጉ አገሮችን እና የሀገር ውስጥ ተሞክሮ እንደመነሻ መጠቀም፤

• የኢንዱስትሪውን ክፍተት በዝርዝር በመረጃ በመያዝ ፤

• ስልጠናን በምዘና ማረጋገጥ

19
9. የድጋፍ ስልቱ ይዘቶች

ሀ/ የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ (ካይዘን) አቅም ግንባታ

ለ/ የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ

ሐ/ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ

መ/ የሥራ ፈጣሪነት /ኢንተርፕርነርሽፕ አቅም ግንባታ

20
9.1 የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ (ካይዘን) አቅም ግንባታ

• ከሁለት የጃፓን ቃላት ካይ (KAI) መሻሻል እና ዘን (ZEN) መልካም

የማያቋርጥ መልካም ለውጥ ማለት ነው ይህም ከእለት ተእለት ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረግ

የአሰራር ፍልስፍና ነው

9.2 የቴክኒካል ክህሎት አቅም ግንባታ

• ክፍተትን መሰረት አድርጎ በተለያዩ የሙያ ደረጃዎችና የብቃት አሀዶች ውስጥ ካሉ የስልጠና አይነቶች

በተግባር ስልጠና የመስጠት ሄደት ነው 21


9.3 የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ
• አዋጭና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን \አዳዲስ አሰራርን\ በመቅዳትና በማመንጨት ለኢንዱስትሪዎች
የማስተላለፍ ሂደት ነው

9.4 የሥራ ፈጠራነት /ኢንተርፕርነርሽፕ አቅም ግንባታ


• የደንበኞች አያያዝ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፣የንግድ ዕቅድ ዝግጅት፣ የስራ ፈጠራ ተግባራትን
ማከናወኛ መንገድ ነው

22
10. በድጋፍ የሚካተቱ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች

• ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማምረቻ

• ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ

• የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበሪያ

• የብረታ ብረት ስራዎች ማምረቻ

• የእንጨት ስራዎች ማምረቻ

• የዕደ ጥበብ ዉጤቶች - የአሸንጉሊትና የሙካሽ ሥራ /ካባ ማምረቻ

23
የቀጠለ

• ጌጣጌጥ

• የኬሚካልና የኬሚካል ዉጤቶች ማምረቻ

• የግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ

• ብረት ያልሆኑ የማዕድን ውጤቶች ማምረት - ሸክላና የብርጭቆ ወረቀት መስታወትና የመስታወት
ውጤቶችን

• የኮምፒወተርና የኢሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማምረቻ

24
11. አደረጃጀትና ቅንጅታዊ አሰራር

በፌደራልና በክልል የኢንተርፕራይዞቸ ልማት አደረጃጀቶች፣ ዘርፍን ለመደገፍ የተቋቋሙ ተቋማት፣

የማኑፋክቸሪንግ ልማት ማእከላት፤

 በፌደራልና በክልል የሚገኙ የትምህርት፣ የስልጠና እና የምርምር ተቋማት፤

 በቅንጅት በመስራት ለጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚደረገውን የኢንዱስትሪ

ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት ድጋፍ ስኬት በጋራ ይረባረባሉ፡፡

25
11. የአስፈጻሚ፣ የፈጻሚ እና የባለድርሻ አካላት ሚና
 የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተግባርና ኃላፊነት
 ሀገር አቀፍ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የድጋፍ ማዕቀፍ
እንዲዘጋጅ በማድረግ አፈጻጸሙን መገምገም፤
 የዘርፉን ልማት ለማፋጠን የሚረዱ ህጎችና ደንቦችን ከወቅቱ ሁኔታ ጋር እየፈተሸ የሚሻሻሉ ህጎችን
ለመንግሥት ማቅረብና ሲፈቀድም በተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ፣

26
የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

የትምህርትና ስልጠና ደረጃዎች እና የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ ማውጣትና መከታተል፤

የክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮችን አካባቢ ተፈጥሮ ጸጋ ጥናት በጋራ ማካሄድ፤

የላብራቶሪ የምርት ፍተሸ በተመጣጣኝ ዋጋ ፍተሻ አገልግሎት መስጠት፣

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲያድግና እንዲስፋፋ ማድረግ፣

27
የቀጠለ
 የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተግባርና ኃላፊነት

የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ዕቅድ የማቀድና አፈጻጻሙን መከታተል፣

የአስፈጻሚና የፈጻሚ አቅም መገንባት፣

የድጋፍ ማዕቀፍችን እና ድጋፎቹን ለማስፈጸም የሚረዱ ሰነዶችን ማዘጋጀት፤

የዘርፉን ልማት ችግሮች ለመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን በማከናወን የመፍትሄ


አቅጣጫ በማስቀመጥ ክትትል ማድረግ፤

28
 የክልልና የከተማ አስተዳደር የመዋቅር አካላት ተግባርና ኃላፊነት

የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ባለሙያዎችን መመደብ፣

የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ማቀድ፣
መከታተል፣ አፈጻጸሙንም መገምገም፤

ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሰጪዎች ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና ለዘርፉ ባለሙያዎች ድጋፉን


አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲዘጋጁ በስሩ ያሉትን መዋቅሮች ማስተባበር፣

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግልት መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ማጠናቀር፣ ሪፖርት ማዘጋጀትና ለሚመለከተው


አካል ማስተላለፍ፤

29
የቀጠለ

ምቹና ቀልጣፋ የምርት፣ የጥሬ እቃ እና የፋይናንስ አሰራርን መዘርጋት፣

የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን እንዲተገበር ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራትና

መከታተል፤

ዘርፉን የሚያግዙና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የሥራ አመራርና

ሌሎች እነደ አስፈላጊነቱ የሚዘጋጅ ተግባር ተኮር ሥልጠናችዎን ማዘጋጀትና መስጠት፣

30
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ባለሙያ ተግባርና ኃላፊነት

የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን የድጋፍ ማእቀፍ መሰረት ድጋፍ መስጠት፤

የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤

ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ስለ ቴክኖልጂና ማምረቻ መሣሪያዎች አጠቃቀም፣ አያያዝና ጥገና
ሥልጠናና የምክር አገልግልት መስጠት፣

አዋጭ ቴክኖልጂዎች በመተንተን መምረጥ፣ የዲዛይንና ናሙና ማዘጋጀትና ፈትሾ በማረጋገጥ ለአብዥዎች ስልጠና
በመስጠት ማሰራጨትና መከታተል፣

የኢንተርፕራይዞችን ልማት አፈጻጸም በሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት ሪፖርት በየደረጃዉ ላሉ አካላት በየወሩ
ማቅረብ፤
31
12. ከተጠቃሚዎች የሚጠበቁ ኃላፊነቶች

• አገልግሎቱን ከሚሰጡ ተቋማት ጋር በውል ከተቀመጠው ውጪ ከባለሙያዎች ጋር ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት


አለመፍጠር፣

• ህጋዊ በመሆን ፣

• የሚሰጡ ድጋፎችን በመቀበል ለመለወጥ ዝግጁ የሆን፣

• የመንግስት ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎችን በቅንነት በመቀበል የሚፈልጉትን ህጋዊ መረጃዎችን


መስጠት፣

• የሚሰጠውን ድጋፍ በመጠቀም ለለውጥ መትጋት፣


32
13. ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ

የተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋት


ግብረ-መልስ
ወቅታዊ መረጃ መያዝ
ክትትልና ድጋፍ

33
13. የተጠያቂነት ሥርዓት

- ይህንን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፍ ማስፈጸሚያ

ማንዋል ከማስፈጸም አንጻር በዚህ ማንዋል ተግባርና ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ኃላፊነታቸው በአግባቡ

ባይወጡ በተቀመጠው የውስጥ አሰራር ስምምነት መመሪያ መሰረት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

34
14. ማኑዋሉን ስለማሻሻል

ይህ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፍ ማስፈጸሚያ ማንዋል እንደ አስፈላጊነቱ

በባለድረሻ አካላት ተሳትፎ እና እንዲሁም በፌደራል /በክልል /ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ሊሻሻል ይችላል፡፡

35
O
EM
A X
LL
GA

You might also like