Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 9

ልቤ አቤት በል እንጅ

አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ


አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጎስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ
ልቤ አቤት በል እንጅ
ልቤ አቤት በል እንጅ አምላኬ ሲጣራ
በኀዘን በለቅሶ ትካዜህን አውራ
በደሌን አምኘ ይቅርታ ልጠይቅ
ሁሉን ቻይ ነህና ፍጥረትህን
የማትንቅ
አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ
አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጎስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ
መንገድ ተላልፌ ፈጣሪ
አስቀየምኩህ
በሚጠፋ ንብረት አምላኬን
ለወጥኩህ
አሁን ግን አምኘ ብዙ እንደበደልኩህ
በረከሰ አንደበት ይቅርታ ለመንኩህ
አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ
አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጎስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ
የኃጢያት መጋረጃ ፊቴን ሸፍኖታል
ኃይልን ከእኔ ርቆ መቆም ተስኖኛል
ነሽና በፊቱ ክብር ሞገስ ያለሽ
ድንግል ልመናየን አድርሽ ከልጅሽ
አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ
አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጎስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ
ጉልበት አንተ ሁነኝ መተማመኛዬ
በደሌን አጥፋልኝ ሁን አስተማሪዬ
ከበደል እንድርቅ እጅህን ዘርጋና
ዳግም እንዳልበድል አጽናኝ
በምስጋና::
አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ
አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጎስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ

መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ


ግቡ!

You might also like