Professional Documents
Culture Documents
Criminal Power Point
Criminal Power Point
Criminal Power Point
መግቢያ
መንግሥት የህብረተሰብን ሠላምና ፀጥታ እንዲሁም የግለሰብን መብትና
ነፃነት የማስከበር ሃላፊነት አለው፡፡ ይሄንን ሃላፊነት ህገ መንግስቱ
በሚፈቅደው እና በሚያዘው መሠረት ተገባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ
እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች አንዱ የወንጀል ህግ
መደንገግ እና ይህንን ህግ የተላለፉ ሰዎች ወደ ህግ ማቅረብ ይጨምራል፡፡
የወንጀል ህጉ ዓላማና ግብ በሕገ መንግስቱ ላይ የደነገጉትን የሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስከበር ዙሪያ ከፍተኛ ሚና አለው እያንዳንዱ
ዜጋ ወይም የመንግስት አካል በህገ መንግስቱ ላይ የተጣለውን ግዴታ
ካልተወጣ እና ከጣሰ የወንጀል ህጉ አስፈላጊውን ምላሽ ይሰጣል፡፡
በወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ንፁህ ግለሰቦች ሣይጐዱ የመንግስትና የህዝብ
ጥቅም ሣይስተጓገሎል ጥፋተኞች እንዲቀጡና ከጥፋታቸው እንዲማሩ
ማድረግ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡
የወንጀል ህግ አላማ
ለጥቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፤ህዝቦቹን፤ ነዋሪዎቹን
ሰላም፤ ደህነነት፤ሥርዓት፤መብትና ጥቅም መተበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡
(የወንጀል ሕግ አንቀፅ 1)
የወንጀል ሕግ ግብ
የወንጀል ሕግ ግብ
ወንጀል ምንድነው ? ፤
443.
ምስክርነት ተጠርቶ አለመቅረብ አንቀፅ 448
በአደጋ ላይ የሚገኝ ሰውን አለመርዳት አንቀፅ 575.
ወንጀል
ቀጥታ ሀሳብ
ተዘዋዋሪ ሀሳብ
ከባድ ቸልተኝነት
ቀላል ቸልተኝነት
1. ህጋዊ ፍሬ ነገር [ Legal element ]
ህጋዊ ፍሬ ነገር ማለት አንድን ድርጊት ወንጀል ነው ለማለት በመጀመሪያ ደረጃ
ድርጊቱ እንዳይፈፀም ያስቀጣል ወይም ያስጠይቃል ወይም ይሄ ድርጊት ወንጀል
ነው የሚል የተፃፈ ወይም የተደነገገ ድርጊት ወይም የተፃፈ ህግ ሲኖር ነው ፡፡
አይቻልም፡፡
በመንግስት መስሪቤቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ክስ የሚቀርበው
በዐቃቤ ህግ ነው፡፡ በመሆኑም በእነዚህ ተቋማት የሚገኙ የሕግ
ባለሙያዎች የወንጀል ጉዳይ ሲገጥም የሰነድ ሆነ የሰው ማስረጃዎች ካሉ
እነዚህን በማጠናከር አቤቱታውን ለፓሊስ በማቅረብ ፓሊስም
መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ በማስተላለፍ መዝገቡ እንዲደራጅ በማድረግ ክስ
ይመሰርታል፡፡በዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተ በኋላ የተቋሙ የህግ
ባለሙያዎች ቀጣይ ስራ መዝገቡ የደረሰበትን ደረጃ መከታተል ብቻ
ይሆናል፡፡
የሙስና ወንጀሎች
የሙስና ወንጀል ምንነት
የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 በአንቀፅ 4(2) ላይ
ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በግዥ ወይም
በሽያጭ ወይም በሚያከናውናቸው ተግባራት ማናቸውንም ጥቅም ያገኘ ወይም የወሰደ እንደነገሩ
ሁኔታ ከ1 ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና እስከ 3000 ብር የቀላል የገንዘብ መቀጮ
ወይም ከ 10ዓመት የማይበልጥ ፅኑ እስራት እና ከ100 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት
እንደሚያስከትል ነው፡፡
የተወሰደውን ወይም የተገኘውን ጥቅም በፍ/ብሄር ከሶ የማስመለሱ ተግባር የተጠበቀ መሆኑን
በማሰብ ሊከፈል የማይገባ መሆኑን እያወቀ የገቢ ጥቅም እንዲሰበሰብ ያዘዘ እንደሆነ
ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት
በማሰብ በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም በከፊል ለራሱ ያደረገ
እንደሆነ እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና 10ሺህ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል ይላል፡፡
በጉድለት የሚረጋገጠው ገንዘብ ቀላል የማይባል እና የድርጅቱን የገንዘብ ዓቅም የሚፈታተን ነው፡፡
የሆነ ዋስ እንዲያቀርቡ ማድረግ እና በሥራ ላይም አስፈላጊውን ክትትል በማደረግ የቅድመ መከላከል
1.የስርቆት ተግባራት
ማንም ሰው የማይገባውን ሃብትና ንብረት ለማግኘት በማሰብ ንብረትነቱ የድርጅቱ የሆነውን
የማይንቀሳቀስ እና የሚንቀሳቀስ ንብረት የወሰደ ወይም ከራሱ ንብረት ጋር የቀላቀለ እንደሆነ
እስከ 5 ዓመት ድረስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ከዚህ ጋር በተገናኘ አንድ
ሰው ለፈፀመው ድርጊት በወንጀል ተቀጣ ማለት ከፍ/ብሄር ነፃ ነው ማለት አይደለም ፡፡
የወንጀል ቅጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የወሰደውን ንብረት በፍ/ብሄር ተከሶ እንዲመለስ
ይደረጋል፡፡
ከቆጣሪ ውጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት የኃይል ስርቆት መፈፀም ጋር በተገናኘ ለራስ ወይም
ለሌላ አካል ጥቅም ለማስገኘት የኃይል ማሰራጫ ላይ ወይም ሌላ ሰው ከዘረጋው መስመር
ኤሌክትሪክ ኃይል በመውሰድ የማይገባ ጥቅም ያገኘ እንደሆነ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ እስራት
ወይም 20ሺ ብር መቀጮ እንደሚያስከትል የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 በአንቀፅ
28 ላይ ተደንግጓል፡፡
2. በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል
በሃሰት በተዘጋጀ ሰነዶቸ ወይም ወደ ሃሰት በተለወጠ ሰነድ እያወቀ መገልገል እንደ
ወንጀል ክብደቱ ታይቶ እስከ 10 ዓመት እንደሚያስቀጣ የወንጀል ህጉ 378
ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡በየትኛውም መስሪያ ቤት በተጨባጭ የሚስተዋሉ
የሃሰተኛ የት/ት ማስረጃ ሰነድ መጠቀም በዚህ ድንጋጌ መሰረት ያስጠይቃል፡፡
3. የተቋሙን ንብረት ያለአግባብ መገልገል/ማባከን
ማንኛውም ሰው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት
በአደራ የተሰጡትን ወይም የተረከበውን የመንግስት ወይም የህዝብ ንብረት
አሳልፎ የሰጠ፣የጣለ፣የሸጠ፣የለወጠ፣ያስያዘ እና ጉዳት እንዲደርስባቸው ያደረገ
እንደሆነ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል(የወንጀል ሕግ አንቀፅ
677)፡፡በመስሪያ ቤታችን የሚስተዋለው እንደ የሥራ መሳርያ
ማከራየት፤የድርጅቱን ዕቃ መሸጥ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ያስጠይቃል፡፡
ምንም እንኳን ድርጊቱ በቸልተኛነት የተፈፀመ ቢሆንም እስከ አንድ አመት
በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣ ልብ ልንል ይገባል፡፡
4.የሥራ ኃላፊነትን ባለመወጣት የሚፈፀም ወንጀል
ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ የሥራ ግዴታ ተግባሩን በአግባቡ ሳይፈፀም
በመቅረቱ በመንግስት ፤በህብረተሰቡ ወይም በግለሰብ ጥቅም ላይ ጉዳት ያደረሰ
ከሆነ ከ1000 ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ
ቀላል እስራት ያስቀጣል በማለት የወንጀል ሕጉ በአንቀፅ 420 ላይ ይደነግጋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ግዜ የድርጅታችን የጥገና ክፍሎች የኤሌክትሪክ መስመር
ተበጥሶ መውደቁን እየተነገራቸው በአፋጣኝ አስፈላጊውን ጥገና ባለማድረጋቸው
በስው እና ንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡ሌላችም ክፍሎች እንዲሁ
የስራ ድርሻቸውን በአግባቡ ባለመወጣት በድርጅታችን ላይ ጉዳት ሲደረስ
ይስተዋላል፡፡ለምሳሌ ሆን ብሎ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎችን በወቅቱ ቢል
እንዳይከፍሉ ማዘግየት እና ሌሎች የስራ ኃላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በዚህ
ድንጋጌ ሰር የሚያስጠይቅ መሆኑን ሁሉም ልብ ሊለው ይገባል፡፡
5. ለፍትህ እርዳታ መስጠትን እምቢ ማለት
ማንም ሰው በምስክርነት ወይም በተከሳሽነት ወይም በልዩ አዋቂ ምስክርነት ማስረጃ እንዲያቀረብ
ታዞ ሳያቀርብ የቀረ ፤ ምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ በህግ መሰረት ተጠርቶ ሳይሰጥ የቀረ እንደሆነ
ከሁለት ወር በማይበልጥ እስራት ወይም ከ1000ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል በማለት
የወንጀል ህጉ በአንቀፅ 448 ላይ ይደነግጋል፡፡
ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው በህግ ወይም በሙያው ደንቦችን ለህዝብ ደህንነት ወይም ሰላም
ሲባል ወንጀሎችን ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት አለማስታወቅ ከ1000 በማይበልጥ መቀጮ
ወይም ከ6ወር በማይበልጥ እስራት ያስቀጣል በማለት የወንጀል ህጉ በአንቀፅ 443 ላይ ይደነግጋል፡፡
ማንኛውም ሰው ከመንግስት ስራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሕግ በተፈቀደው
ወይም ከፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት በመንግስት ሠራተኛ
ሲጠየቅ ቀርቦ ለማስረዳት ተገቢውን መልስ ለመስጠት ፣ሰነዶችን
ለማቅረብ ወይም ለማስመርመር እምቢተኛ ከሆነ ወይም ያልተባበረ
እንደሆነ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ የመንግስትን ሥራ ያደናቀፈ
እንደሆነ ከ5 ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም በመቀጮ
ይቀጣል በማለት የወንጀል ህጉ በአንቀፅ 338 ላይ በግልፅ
ያስቀምጣል፡፡
6.በኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት ማድረስ
ማንኛውም ሰው በባለ ፍቃዱ የተገጠመለትን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ያሰናከለ ወይም
እንዲሰናከል የፈቀደ ወይም የኤሌክትሪክ ፍጆታን እንዳይመዘገብ ያደረገ እንደሆነ
እስከ 5 ዓመት በእስራት እንደሚያስቀጣ የኢነርጂ አዋጅ 810 /2006 አቀንፅ
29 ይደነግጋል፡፡
ማንኛውም ሰው የራሱ ያልሆነውን ዕቃ፣ መሳርያ፣ ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ
ዋጋ ያሳጣ ወይም እንዳያገለግል ያደረገ እንደሆነ እስከ 3 ዓመት የሚደርስ እስራት
ወይም በመቀጮ የሚያስቀጣ ሲሆን የወደመው ንብረት የቴሌ ወይም የመብራት
ሃይል የተዘረጋ መስመር ከሆነ እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ
የወንጀል ህጉ አንቀፅ 690(2) ይደነግጋል፡፡
የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው ድርጅቶች በወንጀል ሕግ ተጠያቂ
የሚሆኑበት አግባበብ