Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 30

በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር

ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ኃ/ል/ጽ/ቤት

ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ በሚገኙ የተቋማት ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ጋር


በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚደረግ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ ማስፈፀሚያ ዕቅድ

ጥቅምት 2016ዓ.ም

አዲስ አበባ
1. መግቢያ

• የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ለህብረተሰቡ


የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሐዊ
አገልግሎት በመስጠት የነዋሪውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋና ዓላማው
በማድረግ ነዋሪውን እርካታ ለማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች በመስራት ላይ
የሚገኝ ቢሆንም፣
• የአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት፣ ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት እና
አገልግሎትን በተለያዩ መንገዶች የመሸጥ፣ የቅልጥፍና እና
የውጤታማነት ማነስ የተገልጋዩ እርካታ በሚፈለገው ደረጃ
እንዳይደርስ አድርጎታል፡፡
መግቢያ የቀጠለ…

•ስለሆነም የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለማሻሻል


ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያና የብልሹ አሰራር
መታገያ ስትራጂዎችን በመንደፍ እየተገበሩ ይገኛል፡፡
•ይህም ተገልጋዩ ህብረተሰብ በተለያዩ ጊዜያት
የሚያነሷቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ደረጃ
በደረጃ እንዲፈቱ እየተደረገ ይገኛል፡፡
መግቢያ የቀጠለ…

• የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ከሚረዱ አንዱ መንገድ ተገልጋዩ ህብረተሰቡ


ስለ አገልግሎት አሰጣጡ በተለያዩ መድረኮች አስተያየትና ጥቆማ መስጠት
አንዱ ነው፡፡
• በዚህም ተገልጋዩ ህብረተሰብ አገልግሎት ከሚሰጠው ከተመረጡ የመንግስት
ተቋም ጋር ፊት ለፊት በመድረክ ውይይት እንዲያካሂዱ ማድረግና አገልግሎት
አሰጣጡን ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡
• በዚህ ሂደትም በ2015 በጀት ዓመት ከኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመሆን አንድ
የውይይት መድረክ በማካሄድ ተገልጋዩ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የበኩላቸውን
ድርሻ እንዲጫወቱ እና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎትም ለተገልጋዩ
ግልፅኝት እየፈጠሩ እንዲሄድ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
መግቢያ የቀጠለ…

• በዚህም መሰረት በ2016 በጀት ዓመትም የተገልጋዩን ተሳትፎ አጠናክሮ ለመቀጠል


እንዲቻል እና የክፍለ ከተማውን ነዋሪዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት
የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን ተሳትፎና ትብብር እንዲያደርጉ
መብታቸውን እንዲጠይቁና ግዴታቸውንም እንዲወጡ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ
ብልሹ አሰራርን በማጋለጥና በመታገል ሌብነትን ለማስወገድ የበኩላቸውን አስተዋጽዎ

እንዲያበረክቱ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ በሚገኙ ተቋማት ላይ የሚገለገሉና


ተገልጋዩን የሚወከሉ አካላትን ማወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የማስፈፀሚያ ዕቅድ
ተዘጋጅቷል፡፡
2. የመድረኩ ዓላማ

2.1. ዋና ዓላማ
•በተገልጋዩ/በነዋሪው/ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ
ችግሮችን በመተንተን መንስኤዎቻቸውን በመለየት
የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እና ችግሮቹን ከስር-
መሰረታቸው በመፍታት የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ ነው፡፡
2.2. ዝርዝር ዓላማ
֍ በየደረጃው የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት
የነዋሪውን እርካታ ማሳደግ፤
֍ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የሚፈቱ
በሚል የመለየት፣ የማደራጀት፣ መቼ፣ በማንና እንዴት እንደሚፈቱ እንዲሁም
የሚመለከታቸውን አካላት ሚና በግልጽ በማስቀመጥ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ
በመፍታት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገርና የተጀመረውን ንቅናቄ አጠናክሮ
ማስቀጠል፤
֍ ተገልጋዩን/ህብረተሰብ በተደራጀ መልኩ በማሳተፍ ግልፅ የሆኑ አሰራሮች
ስታንዳርዶች በማዘጋጀት በመተማመን አገልግሎት አሠጣጡ የተሟላ እንዲሆን
ማድረግ፤
ዝርዝር ዓላማ የቀጠለ…
֍ በመንግሰት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘንድ የሚስተዋሉ የብልሹ አሰራርና የሌብነት
ተግባራትን እና መንስኤዎቻቸውንም ጭምር አንጥሮ በማውጣት ማነቆዎችን (የአመለካከት፣
የአሰራርና የአደረጃጀት) በማስወገድ ችግሮቹን ከስር መሰረታቸው መፍታት እና በሂደትም
ተቋማዊ አቅም በመገንባት ዘላቂ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል መሰረት መጣል፤
֍ ለህብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፍትሀዊ፣ ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሁም
የውጤታማነትን መርህ መሠረት ባደረገ መልኩ በመስጠት መልካም አስተዳደርን ማስፈን፤

3. ወሰን (scope)
ይህ የውይይት መድረክ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ በሚገኙ በተመረጡ ተቋማት የሚካሄድ
ይሆናል፡፡
3.1. የተመረጡ ተቋማት
በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄድ የውይይት መድረክ በተመለከተ
የተመረጡ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች
ተ.ቁ የተቋም ስም የተገልጋይና ባለድርሻ
አካላት የተሳታፊ ብዛት
1 የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፤ 30
2 የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 30
3 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 40
4 የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 30
5 የንግድ ጽ/ቤት፤ 35
6 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 30
7 የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት 25
8 የህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት፤ 30
9 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት 30
10 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት 20
11 ስራ አስኪያጅ 20
12 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና 20
ጠቅላላ የተሳታፊ ብዛት ድምር 340
በወረዳ ደረጃ የሚካሄድ የውይይት መድረክ በተመለከተ
ተ. የተገልጋይና
ቁ የተቋም ስም ባለድርሻ አካላት
የተሳታፊ ብዛት
1 የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፤ 20
2 የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 20
3 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 20
4 የቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት፤ 20
5 የንግድ ጽ/ቤት፤ 20
6 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 25
7 የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት 15
8 የህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት፤ 20
9 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት 20
10 የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት 20
11 ስራ አስኪያጅ 20
12 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና 20
ጠቅላላ የተሳታፊ
በክፍለ ከተማ 340 ፣በወረዳ 2880 ባጠቃላይ ብዛት ባለድርሻ
3220 ተገልጋይና ድምር አካላት እንዲሳተፉ240
ይደረጋል፡፡
4. የሚጠበቅ ውጤት

 ህዝቡ ወይም ተገልጋዩ በየተቋሙ ያሉ የአሰራር ሂደቶችን በአግባቡ ተረድቶ


እየገመገመ አስተያየት የሚሰጥበትና በቂ ተፅዕኖ የሚያሳርፍበት አሰራር
ይፈጠራል፣
 መብቱን የሚጠይቅ፣ ግዴታውን የሚወጣ በሁሉም ዘርፍ ያገባኛል የሚል
ተሳታፊና ተባባሪ ማህበረሰብ ይፈጠራል፣
 ከህዝቡ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶችን በዝርዝር በመፈተሽ
ለስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት በግብዓትነት ይጠቀማል፣
 ለህብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልፅና ተጠያቂነት የውጤታማነት መርህ
መሠረት ባደረገ መልኩ በመስጠት የህዝብ እርካታ ይረጋገጣል፤
5. የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

5.1. የቅድመ ዝግጅት ሥራ


 ዝክረ ተግባር /TOR/ ማዘጋጀት፣
 በዝክረ ተግባሩ መሰረት አካሄዱን /አመራሩን/ መወሰንና
አስፈላጊውን ሎጂስቲክ ማሟላት፣
በዝክረ ተግባሩ ላይ መድረኩ ከሚመለከታቸው አካላት
የምክክር መድረክ ማዘጋጀትና መግባባት ላይ መድረስ፣
በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የኮሚቴ /ንኡሳን ኮሚቴዎች/
አባላት ማደራጀት፣
5.2. የተግባር ምዕራፍ
የውይይት መድረኩ የሚመለከታቸው ተቋማት ከተገልጋይ
የሚነሱ ችግሮችን በመለየት፣ የችግሮቹን መንስሄዎችን
በመተንተን እና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማመንጨት፣
እንዲሁም ችግሮቹን ለመፍታት የተቋሙን ሚና እና
በመድረኩ ተሳተፊ የሆኑ የተገልጋዩን/የህዝቡን ሚና
ተንትነው ሰነድ እንዲያዘጋጁ ድጋፍ ማረግ፣
ለመድረክ ውይይቱ አስፈላጊ የሆኑ መነሻ ሰነዶችን
ከየተቋማቱ ማሰባሰብ፣
የተግባር ምዕራፍ የቀጠለ…

ከሰነዶቹየተገኙ ጠቃሚመረጃዎች መለየት፣ ማደራጀትና


መተንተን፣
ለውይይት መድረኩ የሚሆን የውይይት ሰነድ ማዘጋጀት፣
የውይይት መድረክ የሚካሄድባቸውን ቦታዎችመለየትና
ማዘጋጀት፣
የውይይት መድረኩ የሚካሄድባቸው ተቋማት በመድረኩ ተሳታፊ
የሆኑ ተገልጋይ/ህዝብ እንዲለዩ እና ጥሪ እንዲያስተላልፉ
ማድረግ፣
የውይይት መድረኩን ማዘጋጀት፣
1. የማጠቃለያ ምዕራፍ

 በውይይት መድረክ የሚነሱ ሃሳቦችን፣ አስተያየቶችን እንዲሁም


ጥያቄዎችን በመሰብሰብ መረጃዎቹን ማደራጀት፣
 የተገኙ ግብዓቶችን በማካካተት የተነሱ ችግሮችን፣ የሚፈቱበትን
ጊዜ/ በረጅም ጊዜ፣ በመካከለኛ እና በአጭር ጊዜ እንዲሁም በማን
እንደሚፈታ የሚፈታውን አካል ባከተተ ሁኔታ እቅድ እና የድረጊት
መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ ማድረግ፣
 በድርጊት መርሃ ግብሩ መሰረት ሱፐርቪዥን ማካሄድ ችግሮች
መፈታታቸውን ማረጋገጥ፣
6. የውይይት መድረኩን ለማካሄድ የተደራጀ አደረጃጀት

6.1 አብይ ኮሚቴ አደረጃጀት


ይህ ኮሚቴ አጠቃላይ የህዝብ የውይይት መድረኩን በበላይነት
የሚከታተልና የሚመራ ሲሆን ቀጥሎ የተመለከተውን አባላት ያካተተ
ይሆናል፡፡
ወ/ሮ ፀሐይ ኪባሞ ሰብሳቢ
አቶ ግዛቸው ጥላሁን ም/ሰብሳቢ
አቶ ታደለ በቀለ አባል
አቶ አብዩ ጌታቸው አባል
ሶስቱም አማካሪዎች አባል
የወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች
አባል
6.1.1. አብይ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት
 የህዝብ የውይይት መድረኩ ውጤታማ እንዲሆን በበላይነት
ይመራል፣ ያስተባብራል፤
 በድርጊት መርሀ ግብሩ መሰረት መድረኩን ለማስፈፀም
የሚያስችል በጀት እና አስፈላጊ ግብዓት እንዲመደብ ያደርጋል፤
 የህዝብ የውይይት መድረኩን ይገመግማል፤ አቅጣጫ ይሰጣል፤

6.2.የቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀት


 የሰው ኃ/አስ/ል/አስተባባሪ ………………………ስብሳቢ
 የሪፎርም ቡድን ……………………………..........አባል
 ኮምዩኒኬሽን አስተባባሪ …………………..........አባል
የቴክኒክ ኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት፡-

 የህዝብ የውይይት መድረክ ዕቅድ ማዘጋጀት


 ዕቅዱን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት
 በተቋማት የሚዘጋጀውን የውይይት መድረክ ሰነድ ድጋፍ ማድረግ
 የኮሚኒኬሽን ስራ መስራት፡-
ባነሮችን እንዲዘጋጁና እንዲለጠፉ ማድረግ
ለሚዲያዎች ጥሪ ማስተላለፍና የፕሮግራሙን ሂደት እንዲዘግቡ ማድረግ፣
የመድረኩን አጠቃላይ ሂደት በድምጽና በምስል በመቅረጽ መረጃውን
ማደራጀት፣
የመድረክ አስተዋዋቂ ማዘጋጀት፣
6.3. የሎጂስቲክስ ኮሚቴ አደረጃጀት
ይህ ኮሚቴ አጠቃላይ የውይይት መድረኩን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊ
ግብዓቶችን በማሟላት ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠር የሚያደርግ አካል
ሲሆን የሚከተሉትን አባላት ያካተተ ይሆናል፡፡

• የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ … ሰብሳቢ


• ከግዥ ቡድን…………………………………………………………አባል
• ፋይናንስ ቡድን ………………………………….…………...... አባል

6.3.1 የሎጂስቲክስ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት


• የህዝብ የውይይት መድረኩ የሚካሄድበት ቦታ አዳራሽ ማመቻቸት፤
• በዕለቱ ለሚሳተፉ አካላት የምሳ እና የሻይ ቡና መስተንግዶ ማመቻቸት፤
7. የውይይት መድረኩ የሚከናወንበት ቦታ እና የሚወስደው ጊዜ

በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚካሄድ መድረክ


በክፍለ ከተማ ደረጃ 340 ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ
ሲሆን መድረኩ ጥቅምት 13/2016 የሚካሄድ ይሆናል፡

በወረዳ ደረጃ የሚካሄድ መድረክ

በወረዳ ደረጃ በ12 ቱም ወረዳዎች በእያንዳንዳቸው 240


ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ሲሆን በዚሀም ጥቅምት
12 /2016 የሚካሄድ ይሆናል፡፡
8. የአፈጻጸም አቅጣጫ
8.1 በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚካሄድ መድረክ
 የህዝብ የውይይት መድረክ ዕቅድ ማዘጋጀት

 በዕቅዱ መሰረት ከሚመለካተቸው አካላት ጋር መወያየትና ኦረንቴሽን መስጠት

 ውይይት ለማካሄድ የሚያስችል ሰነድ ተቋማት እዲያዘጋጁ ድጋፍ ማድረግ

 የአዳራሽና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን ማሟላት

 በዕለቱ የውይይቱን መክፈትና ማጠቃለል በዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲከናወን ይደረጋል፤

 የመድረኩ የግብዓትና በጀት በክፍለ ከተማው የሚሸፈን ይሆናል፡፤

 የህዝብ መድረኩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግ

 ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን በማካካተት የተነሱ ችግሮችን፣ የሚፈቱበትን ጊዜ/በረጅም ጊዜ፣


በመካከለኛ እና በአጭር ጊዜ እንዲሁም በማን እንደሚፈታ የሚፈታውን አካል ባከተተ ሁኔታ
እቅድ እና የድረጊት መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ ማድረግ፣እና ማጸደቅ፣
8.2በወረዳ ለሚካሄድ መድረክ
 የህዝብ የውይይት መድረክ ዕቅድ ማዘጋጀት

 በዕቅዱ መሰረት ከሚመለካተቸው አካላት ጋር መወያየትና ኦረንቴሽን መስጠት

 ውይይት ለማካሄድ የሚያስችል ሰነድ ተቋማት እዲያዘጋጁ ድጋፍ ማድረግ

 የአዳራሽና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን ማሟላት

 በዕለቱ የውይይቱን መክፈትና ማጠቃለል በወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲከናወን


ይደረጋል፤
 የመድረኩ የግብዓትና በጀት በወረዳው የሚሸፈን ይሆናል፡፤

 የህዝብ መድረኩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግ

 ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን በማካካተት የተነሱ ችግሮችን፣ የሚፈቱበትን ጊዜ/በረጅም ጊዜ፣


በመካከለኛ እና በአጭር ጊዜ እንዲሁም በማን እንደሚፈታ የሚፈታውን አካል ባከተተ ሁኔታ
እቅድ እና የድረጊት መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ ማድረግ፣እና ማጸደቅ፣
8.3 በተቋማት/በጽ/ቤት የሚከናወኑ ተግባራት

በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ማዘጋጀት


በውይይት መድረኩ የሚተፉ ተገልጋይ/ ባለድርሻ አካላትን
በመለየት
ለተሳታዎች ጥሪ ማስፈላለፍ፣
በዕለቱ የተዘጋጀውን ሰነድ ለተሳታዎች ማቅረብ
ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት መቀበል
በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ምላሽ
መስጠት
የተነሱ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ በዕቅድ እንዲመለስ
ማድረግ፤
የውይይት መድረኩ የተሳካ እንዲሆን ማድረግ
9. የመድረክ ዝግጅቱ የጊዜ ሰሌዳ
ተ.
ቁ የሚከናወነው ተግባር ተግባሩ የሚከናወንበት ጊዜ

ዝክረ ተግባር /TOR/ ማዘጋጀት፣ዝክረ ተግባር /TOR/ በፕሮሰስ


1 ካውንስል ማጸደቅ፣ እስከ ጥቅምት 6 /2016 ዓ.ም

ለተመረጡ ተቋማት ኦረንቴሽን መስጠት


2 ጥቅምት 7 /2016 ዓ.ም
የውይይት ሰነድ እንዲያዘጋጁ ማድረግ

3 እስከ ጥቅምት 9/ 2016 ዓ.ም

የውይይት መድረኩ የሚካሄድባቸው ተቋማት በመድረኩ


ተሳታፊ የሆኑ ተገልጋይ/ህዝብ እንዲለዩ እና ጥሪ
4 እንዲያስተላልፉ ማድረግ፣ እስከ ጥቅምት 9/ 2016 ዓ.ም

የውይይት መድረኩን ማዘጋጀት በክፍለ ከተማ የሚካሄድ


መድረክ ጥቅምት 13/2016 ዓ.ም
5
በወረዳ የሚካሄድ መድረክ
ጥቅምት 12/2016ዓ.ም

የመድረኩን ሪፖርት ማዘጋጀት


6 ከጥቅምት 14 እስከ 23/ 2016 ዓ.ም
10. ለውይይት መድረኩ የሚያስፈልግ በጀት

ተ.ቁ አይነት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ በብር

1 የአዳራሽ ኪራይ በቀን 1 20000.00 20000.00

4 ባነር(በክፍለ ከተማ) በቁጥር 6 400*6 2,400

5 አበል በቀን 340 200 68,000.00

6 የምግብ በቁጥር 340 700 238,000.00

7 የሻይ ቡና መስተንግዶ በቁጥር 340 600.00 204,000.00

8 የታሸገ ውሀ (በቀን 2) በቁጥር 340 20 6,800.00

ጠቅላላ ድምር 539,200


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማዕከል እስከ ወረዳ የተመረጡ ተቋማትና
ጽ/ቤቶች ከተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ጋር ለሚያካሂዱት ውይይት መነሻ ሰነድ
ማቅረቢያ ቢጋር

ክፍል አንድ
 መግቢያ
 የመድረኩ ዓላማ
 ወሰን
 ከመድረኩ የሚጠበቅ ውጤት
ክፍል ሁለት
 ባለድርሻ አካላትን መለየትና ሚናቸውን የሚገልጽ ነባራዊ ሁኔታ ባጭሩ
ክፍል ሶስት
አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል አንጻር የተከናወኑ ተግባራት፡-

֍ ከተገልጋይ ቅሬታ አቀባበልና አፈታት አኳያ

֍ አገልግሎቶችን በስታንዳርድ ከመፈጸም አንጻር

֍ ተጠያቂነት ስርዓትን ከማስፈን አንጻር የተጠየቁ አመራሮችና ሠራተኞች፤

֍ አገልግሎቶችን ለተገልጋይ ግልጽ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት


በተለይ የዜጎች ቻርተርን ከመተግበር አኳያ አዲስ በተጠናው አደረጃጀት
መሰረት፤
֍ አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከማስደገፍ አንጻር የተከናወኑ
ተግባራት ካሉ ለዓብነት ይገለጽ፤
የቀጠለ…

֍ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የተስተዋሉ የአገልግሎት


አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከመለየትና ከመፍታት
አኳያ የተከናወኑ ተግባራት ለዓብነት በማሳያ ቢቀርብ፤
֍ ከተገልጋይ የተሰጡ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት በመጠቀም
የተሻሻሉ አፈጻጸሞችና የተሰጡ ግብረ መልሶች ስለመኖራቸው
(ማሳያ ማቅረብ)
֍ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከመታገል አኳያ የተዘረጋ የአሰራር
ስርዓት ስለመኖሩ፤
ክፍል አራት
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፣

በአጭር ፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የሚፈቱ


የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ
አሰራር ችግሮች፣
ማጠቃለያ
አመሰግናለሁ!
አመሰግናለሁ!!
ለለውጥ እንስራ!!

You might also like