Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 59

አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች

 ማብራሪያ፡- ዓለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች ዓለም አቀፍ


ይዘት ያላቸው ስለሆነ በማንኛውም መንገድ ላይ ለመንቀሳቀስ
አሽከርካሪዎች የመንገድ ዳር ምልክቶች የሚያስተላልፉትን
መልዕክትና ትርጉም አውቀው በተግባር ላይ የማዋል ግዴታ
አለባቸው፡፡
የመንገድ ዳር ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ በሶስት
ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም

ሀ. የሚያስጠነቅቁ
ለ. የሚቆጣጠሩና
ሐ. መረጃ ሰጪ ይባላሉ፡፡
የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡-

 ከፊት ለፊት የሚያጋጥመንን ነገር አስቀድሞ በማሳየት ከወዲሁሀ


ጥንቃቄ እንድንወስድ የሚያደርጉ ሲሆኑ እነርሱም

– ቅርፃቸው ባለሦስት ማዕዘን


– ጠርዛቸው በቀይ ቀለም የተቀባ
– መደባቸው ነጭ ሲሆን የሚያስተላልፉት መልዕክት በጥቁር
ቀለም በተሠራ ስዕል (ቀስት) ነው፡፡
የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች
• የምታሽከረክርበት መንገድ ወደቀኝ ስለሚታተፍ
ተጠንቅቀህ አሽከርክር

* አስጊ ወይም አደገኛ መንገድስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

* ተማሪዎች የሚበዙበት አካባቢ ስለሆነ ተጠንቅቀህ አሽከርክር


• ጠመዝማዛ መንገድ ስለሆነ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

• በስተቀኝ ያለው መንገድ እየጠበበ ስለሚሄድ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

• በስተግራ ያለው መንገድ እየጠበበ ስለሚሄድ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

• መዝጊያ ያለው የባቡር ሃዲድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር


• እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ
አሽከርክር
• እየጠበበ የሚሄድ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ
አሽከርክር
- ባለአንድ አቅጣጫ የነበረውመንገድ ለጊዜው
በሁለቱም አቅጣጫ ስለተፈቀደ ተጠንቅቀህ እለፍ

- የሚያንሸራትት መንገድ ከፊት ለፊትህ ስላለ ተጠንቅቀህ


አሽከርክር

- ወደ ወንዝ ዳርቻ የሚወስድ መንገድ ስለሚያጋጥምህ


ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ አሽከርክር
 በመሰራት ላይ ያለ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

- ወደ ግራ የሚታጠፍ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

- ወደ ቀኝ የሚታጠፍ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

- መጀመሪያ ወደ ግራ ቀጥሎ ወደ ቀኝ የሚታጠፍ መንገድ ስላለ ተጠንቅቀህ


አሽከርክር

- መጀመሪያ ወደ ቀኝ ቀጥሎ ወደ ግራ የሚታጠፍ መንገድ


ስላለ ተጠንቅቀህ አሽከርክር
- ናዳ ያለበት መንገድ ስለሚያጋጥምህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተጠንቅቀህ
እለፍ

- ከፊት ለፊትህ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

- መንገዱ ፊትለፊትና ወደ ግራ የሚያስኬድ ስለሆነ ተጠንቅቀህ አሽከርክር

- መንገዱ ፊትለፊትና ወደ ቀኝ የሚያስኬድ ስለሆነ ተጠንቅቀህ አሽከርክር


 መንገዱን እንስሳት ስለሚያቋርጡ ፍጥነትህን
ቀንሰህ ተጠንቅቀህ እለፍ

- ዝቅ ብለው የሚበሩ አውሮፕላኖች ስላሉ ተጠንቅቀህ


አሽከርክር

- የባቡር ሃዲዱን ለማቋረጥ የሚቀር ርቀት በሜትር


ተጠንቅቀህ አሽከርክር
A. 250 ሜ
B. 170 ሜ
C. 100 ሜ
- ወደፊት ክብ አደባባይ አለ

- መገናኛ መንገዱ ወደ ግራና ወደ ቀኝ የሚታጠፍ እንጂ ፊት


ለፊት የማያስኬድ ስለሆነ ተጠንቅቀህ እለፍ

- ባለ 4 አቅጣጫ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ቆመህ


ለተሸከርካሪዎች እና ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት
ተጠንቅቀህ እለፍ

- በመንገዱ ላይ ጠባብ ድልድይ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ


እለፍ
- ቁም የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን በመቀነስ
ተጠንቅቀህ

- ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ወደ ፊት ስለአለ ፍጥነትህን


በመቀነስ ተጠንቅቀህ እለፍ

- በመንገዱ ላይ የባቡር ሃዲድ ማቋረጫ ስላለ ተጠንቅቀህ


አሽከርክር

- በመንገዱ ላይ ከባድ ካሚኒዎች ስለሚበዙ ተጠንቅቀህ


አሽከርክር
- የተበላሸ መንገድ ስለሚያጋጥም ተጠንቅቀህ አሽከርከር

- ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ


አሽከርከር

- የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪዎች ስለሚያጋጥምህ ተጠንቅቀህ


አሽከርከር
የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች በ3 ንዑሳን
ክፍሎች ይከፈላሉ
እነዚህም
 የሚከለክሉ
 የሚያስገድዱ
 ቅድሚያ የሚያሰጡ

* በተለይ የሚቆጣጠሩ ከሌሎች አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በተለይ የመቅጣት ስልጣን አላቸው፡፡
የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች

- እነዚህ ምልክቶች በምልክቶቻቸው ላይ የሚያሳዩትን ነገር ማድረግ


ፈፅሞ ክልክል ነው የሚሉ ናቸው፡፡

- መሰረት የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች ማለት ቅርፃቸው ክብ


ሲሆን ዙሪያቸው በቀይ ቀለም የተቀቡ ሆነው መደባቸው ነጭ
የሚያስተላልፉት መልዕክት በጥቁር ቀለም በተሰራ ስዕል ቀስት ወይም
በፅሁፍ ነው፡፡
የሚከለክሉ ምልክቶች
- ለማንኛውም ተላላፊ የተዘጋ መንገድ በሞተር
ኃይል እንዲሁም በእጅ የሚገፉትንም
ጨምሮ ማለፍ የተከለከለ ነው

- ከሁለት እግር በላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሸከርካሪዎች ምልክቱ


ከተተከለበት ሥፍራ ጀምሮ “መጨረሻ” የሚል ሌላ ምልክት
እስከሚታለፍበት ድረስ መቅደም የተከለከለ ነው

- መሽቀዳደም የተከለከለ ነው ለሚለው ትዕዛዝ መጨረሻ


- ለእግረኞች ማለፍ የተከለከለ ነው

- ምልክቱ ባለበት አቅጣጫ እያሽከረከሩ ማለፍ የተከለከለ ነው

- ማቆም ክልክል ነው የሚለው ትዕዛዝ ምልክት መጨረሻ

- ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ


ሀ. መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ
ድረስ ወይም
ለ. በውስጡ መጨረሻ የሚል ጽሑፍ ያለበትን የዚህ
አይነት ምልክት እስታልፍ ድረስ ተሸከርካሪህን ማቆም ፍፁም የተከለከለ ነው
- ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ማቆም ፈጽሞ የተከለከለ ነው

-- ለከባድ መኪኖች ማለፍ የተከለከለ ነው

-- ወደ ግራ ዞሮ መመለስ የተከለከለ ነው
-- ወደ ቀኝ ዞሮ መመለስ የተከለከለ ነው

-- ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ


ሀ. የሚቀጥለውን መገናኛ መንገድ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስታልፍ ድረስ
ወይም
ለ. መጨረሻ የሚል ጽሁፍ የተፃፈበት የዚህ ዓይነት ሌላ ምልክት እስክታልፍ ድረስ
ተሸከርካሪን በማዘግየት ማቆም የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን ሾፌሩ ሣይወርድ ሰው
ማውረድም ሆነ መጫን ይቻላል

-- ለሳይክል ማለፍ የተከለከለ ነው

-- ጠቅላላ ክበደቱ በምልክቱ ላይ ለከመለከተው በላይ ለሆነ ማንኛውም


ዓይነት ተሸከርካሪ ማለፍ የተከለከለ ነው
-- መንገዱ ወደፊት የማይቀጥል ስለሆነ ማለፍ የተከለከለ ነው

-- ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ላይ ከፊት ላይ ከፊት ለፊት ለሚመጣ


ተሸከርካሪ ቅድሚያ ሳይሰጡ ማሽከርከር ክልክል ነው

-- በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ


እንዳያልፍ የተከለከለበት መንገድ
-- ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለበት መንገድ

-- ጠቅላላ ርዝመቱ በምልክቱ ላይ ከተጠቀሰው ሜትር በላይ ለሆኑ


ተሸከርካሪዎች ማለፍ የተከለከለ

-- ለሳይክል ማለፍ የተከለከለ ነው


-- የከተማ ወሰን መጨረሻ

-- ከፍታቸው በምልክቱ ከተመለከተው በላይ ማለፍ የተከለከለ ነው

-- የጎን ስፋታቸው በምልክቱ ላይ ከተገለፀው በላይ ለሆኑ


ተሸከርካሪዎች ማለፍ የተከለከለ ነው

-- ወደ ከተማ ክልል እየተቃረብክ ስለሆነ የከተማ ህግና ደንብ ሣያከብሩ


ማሽከርክር የተከለከለ ነው
የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች
 በምልክቶቻቸው ላይ የሚያሳዩትን ነገር ብቻ እንድንፈፅም የሚያስገደዱ ናቸው በአጭሩ
የሚያስተላልፉት መልዕክት አድርግ የሚል ይሆናል፡፡

 ቅርፃቸው ክብ፣ መደባቸው ውሃ ሰማያዊ

 ትዕዛዛቸውን ያልፈፀመ አሽከርካሪን የመቅጣት ስልጣን አላቸው


የሚያስገድዱ ምልክቶች
 ቀጥታና በስተቀኝ ብቻ አሽከርክር

- ቀጥታና በስተግራ ብቻ አሽከርክር

-- በመንገዱ ላይ የማሽከርከሪያ አነስተኛ ፍጥነት

- የአነስተኛ ፍጥነት መጨረሻ


 ቀስቱ በሚያመለክተው ፊትለፊት ብቻ አሽከርክር

- ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ ብቻ ማቆም ይፈቀዳል

- ቀስቱ በሚያመለክተው ወደ ግራ ብቻ አሽከርክር

-- ለብስክሌቶች ብቻ ማሽከርከር የተፈቀደ


 በሠዓት የተሰጠ ዝቅተኛ የፍጥነት ገደብ

- ቀስቱ በሚያመለክተው ወደ ቀኝ ብቻ ታጠፍ

- ቀስቱ በሚያመለክተው ወደ ግራ ብቻ ታጠፍ

-ቀስቱ በሚያመለክተው ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ብቻ


አሽከርክር
ቅድሚያ የሚያሰጡ ምልክቶች
 በመስቀለኛና በመንገዶች ላይ በመተከል ቅድሚያ በሚገባን ቦታ
ላይ ቅድሚያ መስጠት እንድንሰጥ የሚያደርጉን ናቸው፡፡

 በመቅጣት ስልጣናቸው ከፍተኝነት ይታወቃሉ፡፡

 ቅርፃቸውና መደባቸው የተለያየ ነው፡፡


ቅድሚያ የሚያሰጡ ምልክቶች
 ቁም ቀድመው ለገቡ ተሸከርካሪዎች ቅድሚያ ስጥ

-የምልክቱን መጨረሻ የሚለውን እስከምታገኝ ድረስ የማቋረጫ


መንገዶችን የማለፍ ቅድሚያ አለህ

- የማቋረጫ መንገዶችን የማለፍ ቅድሚያ አለህ የሚለው ምልክት


መጨረሻ
 ከፊት ለፊት ለሚመጣ ተሸከርካሪ ቅድሚያ ስጥ

- ወደ መገናኛው መንገድ ቀድመው ለገቡ ቆመህ


ቅድሚያ ስጥ
ዓለም አቀፍ የመንገድ መሀል መስመሮች ፡-

 በአስፋልት መንገድ ላይ የሚሰመሩ መስመሮች ሲሆኑ ዋና


ተግባራቸውም መንገዶችን በአንድና በሁለት አቅጣጫ ለመለየት
ለመከፋፈልና በተጨማሪም የመንገድ ዳር ምልክቶችን መትከል
አዳጋች በሆነበት አካባቢ ምልክቶችን ተክተው ለአሽከርካሪዎች
ስለመንገዱ ሁኔታ በመግለፅ ትዕዛዝ የሚያስተላልፉ ናቸው፡፡
የመንገድ መሀል መስመሮች በ2 ይከፈላሉ፡-

 በመንገዱ አቅጣጫ የሚሰመሩና


 በመንገዱ አግድመት የሚሰመሩ ናቸው፡፡

 በመንገዱ አቅጣጫ የሚሰመሩት ለተሽከርካሪ መተላለፊያ ብቻ


ሲያገለግሉ በመንገዱ አግድመት የሚሰመሩት ደግሞ
ተሸከርካሪን ማቆሚያና እግረኛን ለማሳለፍ የሚረዱ ናቸው፡፡
በመንገዱ አቅጣጫ የሚሰመሩ
 1.1 አንድ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ መስመር
ለ2 እኩል ሲከፈል የተቆራረጠውን መስመር አቋርጦ ዞሮ
መመለስና መታጠፍ የሚከለክል ምልክት እስከሌለ ድረስ ዞሮ
መመለስና ግራ ታጥፎ መሄድ መስመሩንም አቋርጦ ሌላን
ተሸከርካሪ መቅደም ይቻላል፡፡
 አንድ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ባልተቆራረጠ /በድፍን/ ነጭ
መስመር ለ2 እኩል ሲከፈል ወደ ግራ ታጥፎ መሄድ፣
መስመሩን አቋርጦ ሌላን ተሸከርካሪ መቅደምና በስተግራ ወደ
ኋላ ታጥፎ መሄድ አይቻልም፡፡
አንድ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠና
ባልተቆራረጠ /በድፍን/ ነጭ መስመር ለ2 እኩል ሲከፈል
 ባልተቆራረጠው /በድፍኑ/ በኩል ሆነን ስንጓዝ
 ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ አይቻልም
 ወደ ግራ መታጠፍ አይቻልም
 ሌላን ተሸከርካሪ ለመቅደም መስመሮቹን ማለፍ አይቻልም
 በተቆራረጠው መስመር በኩል ሆነን ስንጓዝ
 መስመሮቹን አቋርጦ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ይቻላል
 ወደ ግራ መታጠፍ ይቻላል
 መስመሮቹን አቋርጦ መታጠፍ ይቻላል
 መስመሮቹን አቋርጦ ሌላን ተሸከርካሪ መቅደም ይቻላል
አንድ ባለ 2 አቅጣጫ መንገድ በነጭ መስመር በተሰራ
ደሴት ለ2 እኩል ሲከፈል
 የደሴት መስመሩን አቋርጦ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ አይቻልም
 የደሴት መስሩን አቋርጦ ወደግራ ታጥፎ መሄድ አይቻልም
 የደሴት መስሩን አቋርጦ ሌላን ተሸከርካሪ መቅደም አይቻልም
 ዞሮ መመለስ /መታጠፍ/ የፈለገ አሽከርካሪ ደሴቱን ሳይረግጥ
ወደቀኝ አስፍቶ ወደ ግራ መዞር /መታጠፍ/ ይችላል፡፡
አንድ ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ
መስመር በረድፍ ሲከፋፈል
 የተቆራረጠውን መስመር አቋርጦ ረድፍ መለዋወጥ በጥንቃቄ
ሌላን ተሸከርካሪ መቅደም በግራና በቀኝ ታጥፎ መሄድ
ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚያው መንገድ ላይ ዞሮ መመለስ
አይቻልም፡፡
 በመታጠፊያ መንገዶች ላይ ተተክለው ስለሚገኙ ልዩ ልዩ
አንፀባራቂ ምልክቶች እነዚህ ምልክቶች በመታጠፊ ወይም
አደገኛ ኩረባዎች እና መንገዱ ፊት ለፊት በማይቀጥልበት
መንገናኛ ስፍራ ላይ አሽከርካሪዎች የመንገዱን ክልል አልፈው
 እንዳይወጡ የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች ናቸው፡፡
የትራንስፖርት ህጎች እና ደንቦች
የፍጥነት ወሰን (ገደብ)
 የፍጥነት ወሰን ገደብ በሀገራችን በሁለት ይከፈላል፡፡

በከተማ ክልል ውስጥ እና


ከከተማ ክልል ውጪ ናቸው፡፡
ከከተማ ክልል ውጪ

.
የተሸከርካሪው አይነት በከተማ ክልል ውስጥ

1ኛ ደ/አ/ጎ 2ኛ ደ/አ/ጎ 3ኛ ደ/አ/ጎ
.

1 የግል አውቶሞቢል (ሞተር ሳይክል) ጠቅላላ ክብደቱ ከ3500 ኪ.ግ. በታች የሆነ በሰዓት 60 ኪ.ሜ በሰዓት 100 ኪ.ሜ በሰዓት 70 ኪ.ሜ በሰዓት 60 ኪ.ሜ

2 የንግድ (የኪራይ) ጠቅላላ ክብደቱ ከ3500-7500 ኪ.ግ ለሚመዝኑ በሰዓት 40 ኪ.ሜ በሰዓት 80 ኪ.ሜ በሰዓት 60 ኪ.ሜ በሰዓት 50 ኪ.ሜ

3 ከባድ ካሚዮን ከነተሳቢው እንዲሁም የእርሻ መሳሪያዎች ጭምር በሰዓት 30 ኪ.ሜ በሰዓት 70 ኪ.ሜ በሰዓት 50 ኪ.ሜ በሰዓት 40 ኪ.ሜ
 1ኛ/ ደረጃ አውራ ጎዳና ማለት፡- አንድን አገር ከሌላ ጎረቤት አገር
ጋር የሚያገናኝ መንገድ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ኢትዮጵያን
ከኬንያ፣ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወዘተ የሚያገናኝ መንገድ ማለት
ነው፡፡
 2ኛ/ ደረጃ አውራ ጎዳና ማለት፡- በአንድ አገር ላይ ሆኖ ክፍለሀገርን
ከክፍለ ሀገር ጋር የሚያገናኝ መንገድ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ክፍለሀገራት አሉ፤ አዲስ አበባን ከጎንደር፣
አዲስ አበባን ከጅማ፣ ባሌ፣ ደሴ፣ ሐረር ወዘተ… ጋር የሚያገናኙ
መንገዶች ናቸው፡፡
 3ኛ/ ደረጃ አውራ ጎዳና ማለት፡- በአንድ ከተማ ውስጥ ሆኖ ወረዳን
ከወረዳ ቀበሌን ከሌላ ቀበሌ ጋር ውስጥ ለውስጥ የሚያገናኝ መንገድ
ማለት ነው፡፡ (መጋቢ መንገድ ይባላል)

የማሽከርክር ስርዓት

 በተሸከርካሪዎች መካከል ሊኖር ስለሚገባ


ርቀትና የፍጥነት መጠን
 እጅግ በጣም ተጠጋግቶ ማሽከርከር ለአደጋ መፈጠር አንደኛው
ምክንያት ነው፡፡
 ግጭቶችንም ያበዛል ስለዚህ ተሸከርካሪዎች ተከታትለው
የሚጓዙበት ጊዜ ሁሉ ከፊት ካሉት ተሸከርካሪዎችና በተከታዮች
መካከል በቂ ርቀት መኖር ይገባዋል፡፡
 በመሆኑምበእያንዳንዱ 10ኪ.ሜ የመኪና ፍጥነት ውስጥ
ከምትከተለው መኪና ቢያንስ 6T@ ወይምየአንድ አውቶቡስ
ርዝማኔ ያህል ወደኋላ ራቅ በማለት ማሽከርከር ያስፈልጋል፡፡
 የፍጥነት ርቀት እንሽርት
 - ፍጥነት በኪ.ሜ በሰዓት 40-50ኪ.ሜ የ3 መኪናዎች
ርዝማኔ ያህል የ20 ሜ ርቀት
 - ፍጥነት በኪ.ሜ በሰዓት 50-60 ኪ.ሜ የ4 መኪናዎች
ርዝማኔ ያህል የ25 ሜ ርቀት
 - ፍጥነት በኪ.ሜ በሰዓት 70-80 ኪ.ሜ የ5 መኪናዎች
ርዝማኔ ያህል የ30 ሜ ርቀት
 - ፍጥነት በኪ.ሜ በሰዓት 90-100 ኪ.ሜ የ6 መኪናዎች
ርዝማኔ ያህል የ36 ሜ ርቀት
 - ፍጥነት በኪ.ሜ በሰዓት 100-110 ኪ.ሜ የ7 መኪናዎች
ርዝማኔ ያህል የ43 ሜ ርቀት
ህጎች እና ደንቦች
 ከፊት ለፊት በኩል ትርፍ የሚወጣ ጭነት ከ1 ሜትር መብለጥ
የለበትም፡፡
 ከኋላ በኩል ተርፎ የሚወጣ ጭነት ከ2 ሜትር መብለጥ
የለበትም፡፡
 ቀን ትርፍ ጭነት ላይ ከፊትና ከኋላ ቀይ ጨርቅ 30 ሳ.ሜ ካሬ
መሆን አለበት፡፡ ማታ ከፊት ለፊት ነጭ (ቢጫ) መብራት
ማንጠልጠል ከኋላ በኩል ቀይ መብራት ማንጠልጠል
 አንድ የተበላሸ መኪና በሌላ መኪና ሲጎተት በመሀላቸው ያለው
ርቀት ከ3 ሜትር መብለጥ የለበትም፡፡
 አንድ አሽከርካሪ በቀን ውስጥ ያለዕረፍት ከ4ሰዓት በላይ
መንዳት የለበትም፡፡
 ፈካ (ውሃ) ቦይ መሄጃ ባለበት አካባቢ በ5ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም
አይቻልም፡፡
 በባቡር ሃዲድ አካባቢ በ6 ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መነካካት
(መቀያየር) አይፈቀድም፡፡
 አንድ የተበላሸ መኪና በከተማ ክልል ውስጥ ከ6 ሰዓት በላይ መቆም
አይችልም፡፡
 በባቡር ሃዲድ አካባቢ በ6 ሜትር ክልል ውስጥ መኪና ማቆም ይቻላል፡፡
 በሁለተኛ የመንጃ ፍቃድ ሹፌሩን ጨምሮ ከ8 ሰው በላይ መጫን
አይፈቀድም፡፡
 ለአንድ አሸከርካሪ በቀን (በ24 ሰዓት ውስጥ) ከ8 ሰዓት በላይ
መንዳት አይፈቀድለትም፡፡
 በመስቀለኛ መንገድ ላይ የእግረኛ ማቋረጫ ምልክት ባለበት
አካባቢ እንዲሁም በማንኛውም ድርጅት መውጫና መግቢያ
በሮች በ12 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም ክልክል ነው፡፡
 በአውቶቡስ ማቆሚያ ሥፍራ አካባቢ
 ሀ. ከፊትና ከኋላ በ15ሜትር ባነሰ ክልል ውስጥ
 ለ- የመንገድ ስፋት ከ12 ሜትር በታች ከሆነ በአውቶብስ
ማቆሚያ ትይዩ በ30 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም የተከለከለ
ነው፡፡
 በባቡር ሃዲድ አካባቢ በ20 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም
ክልክል ነው፡፡
 በማንኛውም ድርጅት በሆስፒታልም ጭምር በአንፃሩ በትይዩ
በ25 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም ክልክል ነው፡፡
 በመስቀለኛ መንገድ በባቡር ሃዲድ አካባቢ በ30 ሜትር ክልል
ውስጥ አቅጣጫ መቀያየርና መሽቀዳደም አይፈቀድም፡፡
 የመንገድ ጠርዝ ቀኛችንን ይዘን ስናቆም 40 ሳ.ሜ. ያህል
ጠብቀን መቆም አለብን፡፡
 አንድ የተበላሸ መኪና ክልል ውጭ ከ48 ሰዓት በላይ መቆም
ክልክል ነው፡፡
 ፍሬቻ የምናሳየው ከመዞራችን በፊት በ50 ሜ ክልል ውስጥ
መሆን አለበት፡፡
 በጨለማ (በምሽት ጊዜ) ከፊት ለፊት የሚመጣ ተሸከርካሪ
በ50 ሜ. ክልል ውስጥ ከሆነ ረጅሙን መብራት መጠቀም
አይፈቀድም፡፡
 በጠመዝማዛ (ኩርባ) መንገድ ላይ ለማየት አስቸጋሪ በሆነ ቦታ
በ50ሜ. ክልል ውስጥ ማቆም ክልክል ነው፡፡
 አንድ የተበላሸ መኪና መንገድ ላይ ሲቆም ከፊትና ከኋላ በ50
ሜትር ክልል ውስጥ ባለሦሥት ማዕዘን አንፀባራቂ ምልክት
ማስቀመጥ አለብን፡፡
 የአደጋ አገልግሎት መስጫ አሽከርካሪዎች አንድ አንቡላንስ
የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ሲጓዝ /ሲሄድ/ ከኋላቸው
በ100 ሜትር ክልል ውስጥ ተከትለን መሄድ /መጓዝ አይቻልም
ክልክል ነው፡፡
 በሚቀድመውም በሚያስቀድመው መኪና መካከል በቂ ርቀት
ሳይኖር መቅደምክልክል ነው፡፡
 17. እግረኛን ለማሳለፍ የቆመን መኪና ቀድሞ ማለፍ ክልክል ነው፡፡
 18. ያተቆራረጠ ድፍን መስመር በመጣስ መኪናን መቅደም ክልክል
ነው፡፡
 19. የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪዎ ለስራ በሚሰማሩበት ጊዜ መውደም
ክልክልነው፡፡
 20. ሌላውን ተላላፊ የሚያሰናክል አኳኋን ማቆም ወይም መቅደም
ክልክል ነው፡፡
 እግረኛ ማቋረጫ ባለበት ወይም ከመስቀለኛ መንገድ በ12ሜ
ክልል ውስጥ ማቆም ክልክል ነው፡፡
 22. በግል መውጫና መግቢያ በራፍ ላይ ወይም መንገዱ ስፋት
12ሜ ያነሰ በሆነ አካባቢ ማቆም ክልክል ነው፡፡
 23. ቁም የሚል ምልክት ካለበት ስፍራ በ12ሜ ክልል ውስጥ
ማቆም ክልክል ነው፡፡
 24. በነዳጅ ማደያ መግቢያ 12ሜ ክልል ውስጥ ማቆም
ክልክል ነው፡፡
 ሆስፒታል ከጤና ጣቢያ ከቀይ መስቀል ከዕሳት አደጋ መከላከያ
መግቢያ በሮች ከ12ሜ ባነሰ ርቀት እና ከመግቢያው መካከል
ጀምሮ ከመንገዱ ግራና ቀኝ በ25 ሜ ክልል ውስጥ ማቆም
ክልክል ነው፡፡
ድንገተኛ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በፍሬን ተጠቅሞ
ተሸከርካሪ የማቆሚያ ርቀት
ፍጥነት የማስተዋል ጊዜ ርቀት ፍሬን የመያዣ ርቀት አጠቃላይ የማቆሚያ
በ0.75 ሰኮንድ ርቀት

10 ኪ.ሜ በሰዓት 3.35 ሜትር 2.74 ሜትር 6.09 ሜትር

20 ኪ.ሜ በሰዓት 6.7 ሜትር 7.01 ሜትር 13.71 ሜትር

30 ኪ.ሜ በሰዓት 10.05 ሜትር 13.72 ሜትር 23.77 ሜትር

40 ኪ.ሜ በሰዓት 13.40 ሜትር 24.69 ሜትር 38.09 ሜትር


የሰከንዶች ሕግ
 ርቀትን ርቀትን ጠብቆ የማሽከርከር ዋኛ መፍትሔ የ3 ሰከንድ
ሕግ ነው፡፡ የ3 ሰከንድ
 ሕግ ማለት ተሸከርካሪ በ3 ሰከንድ የሚሄደው ርቀት ነው፡፡
በመንገድ ላይ ስናሽከረክር ከፊታችን ላው ተሸከርካሪ ምን ያህል
ርቀት ላይ እንዳለን ለማወቅ የ3 ሰከንድ ሕግ የላቀ ጠቀሜታ
አለው፡፡ ከፊትህ ያለው ተሸከርካሪ ያለበትን ቦታ ምልክት ያዝና
አንድ ሺህ አንድ፣ አንድ ሺ ሁለት፣ አንድሺህ ሶት በማለት
ቁጠር፡፡ ቁጥሩን ሳትጨርስ ከቦታው ከደረስክ ተጠግተህ
እያሽከረከርክ ስለሆንክ የተወሰነ ማራቅ ጠበቅብሃል
ማለት ነው
 ከፊት ለማየት የሚከለክል ነገር ካለ ፍጥነትህን በመቀነስ ቢያንስ
ከ3 ሰከንድ ወደ 4 ሰከንድ ከፍ አድርግ፡

Thank you

You might also like