Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 12

የመልዕክቱ ርዕስ፡

መንፈሳዊ ውጊያ!
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ኤፌሶን 6:10-
20
መግቢያ
• 1ኛ፡ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ አማኝ ማወቅ እና መረዳት የሚገባው እውነታዎች ምንድን ናቸው?
• 2ኛ፡ በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ የአማኝ ድርሻ እና ኃላፊነት ምንድን ነው?
• 3ኛ፡ የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ምንድን ናቸው?
ጸሓፊው፤ መልዕክቱ የተጻፈበት ጊዜና ቦታ

o የመልዕክቱ ጸሓፊ ጳውሎስ መሆኑን ራሱ መልዕክቱ ይገልጻል (1:1፤ 3:1 ይመ፤ ከ3:7:13፤ 4:1፤
6:19-20 ጋር ያነጻጽሩ)።
o ይህ መልዕክት ኤፌሶንን ጨምሮ ወደ ሌሎች ከተሞችም እንዲደርስ የተጻፈ ዘዋሪ ደብዳቤ
ሳይሆን አይቀርም (1:1:15፤ 6:21-23 ማብ ይመ)።
o ጳውሎስ የቆላስያስን መልዕክት በጻፈበት ጊዜ በ60 ዓ.ም. ግድም በሮም እስር ላይ እያለ ይህን
ደብዳቤ ጽፎታል (3:1፤ 4:1፤ 6:20 ይመ)።
የኤፌሶን ከተማ

o ኤፌሶን በትንሹ እስያ (በዛሬው ቱርክ) ምዕራብ ክፍል ከሚገኙት ከተሞች እጅግ የታወቀች
ከተማ ነበረች።
o የአንድ ወደብ ባለቤትም ነበረች።
o ታላላቅ የንግድ መርከቦች አቋርጠው የሚያልፉባት ቦታ ላይ የተመሰረተች ስለ ሆነች ኤፌሶን
የንግድ ማዕከል ለመሆን በቅታለች።
o ግሪኮች አርጤምስ ሮማውያን ዲያና የሚሏት ጣዖት አምላክ ቤተ መቅደስ በዚህችው ከተማ
ይገኝ ስለ ነበረ ክፉኛ ትኩራራም ነበር (ሐሥ 19:23-31 ጋር ያነጻጽሩ)።
o ጳውሎስ በኤፌሶን ሦስት ዓመት ያህል ተቀምጦ የወንጌል ስርጭት ማዕከል አድርጎአት ነበር
(ሐሥ 19:10 ማብ ይመ)።
o በዚያን ጊዜም የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወቅት አድጋ፤ ተስፋፍታ ነበር በኃላ ግን በራዕይ
2:1-7 ላይ ያለውን ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ።
የደብዳቤው (የመልዕክቱ ዋና ዓላማ)

o ኤፌሶን እንደ ሌሎች የጳውሎስ መልዕክቶች የስህተት ትምህርትን ወይም ደግሞ ኑፋቄን በተመለከተ በተለየ የሚያወሳው
ነገር የለም።
o ጳውሎስ ይሄንን መልዕክት የጻፈው የአንባቢዎችን አድማስ በማስፋት የእግዚአብሔርን የዘላለም ዕቅድና የጸጋውን ስፋት
ጥልቀት ይበልጥ እንዲረዱና እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ያለውን ታላቅ ግብ ማድነቅ እንዲችሉ ነው።

• ይሄንንም ደግሞ በስድስት ምዕራፎች ተከፍሎ ተቀምጦልናል በመሆኑም ከምዕራፍ 1:1-3:21 የመጀመሪያ
ክፍል ሲሆን እርሱም ደግሞ እግዚአብሔር በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ ኢየሱስ ለቤተክርስቲያን የሰራው
የማዳንን ሥራ የሚገልጽ ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ከምዕራፍ 4:1-6:24 ቤተ ክርስቲያን በምድር
ላይ ሳለች በክርስቶስ ኢየሱስ መስራት ያለባት ሥራ፤ ድርሻ እና ኃለፊነት የተገለፀበት ነው። ከእነዚህም
ውስጥ አንዱ ቤተ ክርስቲያን በምድር እያለች ማድረግ ያለባት መንፈሳዊ ውጊያን መዋጋት ነው።
1ኛ፡ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ማወቅ እና መረዳት
ያለብን እውነታዎች ምንድን ናቸው?
• 1.1 ውጊያ እና ሰልፍ እንዳለ ማወቅ እና መረዳት ነው ወይንም ደግሞ ክርስትና
የአልጋ በአልጋ መንገድ እንዳልሆነ ይልቁንም ደግሞ ውጊያ እና ሰልፍ ያለበት መሆኑን
ማወቅ እና መረዳት ይኖርብናል።
• 1.2 ዋነኛ ጠላታችን ስጋ እና ደም ሳይሆን ነገር ግን መንፈሳዊ የጨለማ አካል መሆኑን
ማወቅ እና መረዳት ያስፈልጋል።
• 1.3 ጠላታችን ዲያቢሎስ የሚዋጋበትን መንገድ እና ዘዴ ማወቅ እና መረዳት
ያስፈልጋል።እርሱም ደግሞ በጦር እና በቀስታ አልያም ደግሞ በጎራዴ ሳይሆን
ይልቁንም በሽንገላ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ማለት ነው።
• 1.4 በዚህ መንፈሳዉ ውጊያ ውስጥ ብቻችንን እንዳልሆንን ይልቁንም የጨለማ ግዛት
አለቆችን፤ ሥልጣናትን እንዲሁም ደግሞ ገዢዎችን በሙሉ ድል ያደረገው ጌታ
የብርታታችን እና የኃይላችን ምንጭ መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል ማለት ነው።
• 1.5 አምስተኛው እና የመጨረሻው ማወቅ እና መረዳት ያለብን እውነታ እነዚህ
የምንዋጋባቸው ዕቃ ጦሮች የራሱ የእግዚአብሔር ዕቃ ጦሮች መሆናቸውን ማወቅ
እና መረዳት ያስፈልገናል።
2ኛ፡ በዚህ መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ በአሸናፊነት እና በድል አድራጊነት
ለመመላለስ እና ለመኖር የእኛ ድርሻ እና ኃላፊነት ምንድን ነው?

• “…የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።…የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ
አንሱ።”
3ኛ፡ እነዚህን ልንለብሳቸው እና ልናነሳቸው የሚገቡ
የእግዚአብሔር ዕቃ ጦሮች ምንድን ናቸው?
• 3.1 “…ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ…” የእውነት መታጠቂያ
• 3.2 “…የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ…” የጽድቅ ጥሩር

• 3.3 “…በሰላም ወንጌል በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ…” የሰላም


ወንጌል ጫማ

• 3.4 “…በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ


ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤…” የእምነት ጋሻ
• 3.5 “…የመዳንንም ራስ ቁር...” የመዳን ራስ ቁር
• 3.6 “…የመንፈስን ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው…” የመንፈስ ሰይፍ
የሆነው የእግዚአብሔር ቃል
• 3.7 “…በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤…” በመንፈስ መጸለይ
መደምደሚያ (ማጠቃለያ)

You might also like