Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 23

በገቢዎች ሚኒስቴር መካ/ቁ2/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት

የስጋትና ህግ ተገዥነት ስትራቴጂ የስራ ሂደት


በታክስ ህግ ተገዥነት
ጽንሰ ሀሳብ እና መርህ ላይ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሰነድ

ታህሳስ 2016 ዓ/ም

ግዴታዬን እወጣለሁ መብቴን እጠይቃለሁ!


የሥልጠናው ይዘት

 የታክስ ህግ ተገዥነት ጽንሰ ሀሳብ


 የግብር ከፋዮች መሰረታዊ ግዴታዎች
 የታክስ ህግ ተገዥነት መገለጫዎቹ
 የታክስ ህግ ተገዥ አለመሆን መገለጫዎቹ
 የታክስ ህግ ተገዥነት ጠቀሜታዎች
 የህግ ተገዥነት አለመኖር ምክንያቶች
 የታክስ ህግ ተገዥነት ዝርዝር ባህሪያት
 የመስተንግዶ አይነቶችን መወሰን
2
የስልጠናው አስፈላጊነት

 ከታክስ ህግ ተገዥነት አኳያ የግብር ከፋዮች መሰረታዊ ግዴታዎችን

ማስገንዘብ
 በአሰራር ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ላይ ምክክር በማድረግ

ችግሮች የሚፈቱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ የተዘጋጀ


የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው፡፡

3
ትርጉም

 ለህግ ተገዥ መሆን፡-በተለያዩ ህጎች የተቀመጡትን ግዴታዎች ለመወጣት

መቀበል ወይም መስማማት ወይም ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡


 ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አንጻር የህግ ተገዥነት ማለት ሚ/ር መ/ቤቱ

እንዲያስፈጽም የተሰጡትን የጉምሩክና የታክስ ህጐችን፣በፈቃደኝነት በማክበር


የግብርና የታክስ ግዴታዎችን መወጣት ማለት ነው፡፡
 ለህግ ተገዥ አለመሆን፡- ማለት የግብርና የቀረጥ ግዴታዎችን በትክክለኛው

መንገድ አለመወጣት ነው፡፡

4
የቀጠለ...

5
የግብር ከፋዮች መሰረታዊ ግዴታዎች
1. ለግብር ከፋይነት መመዝገብ( Register):-የጣት አሻራ መስጠት፣መለያ ቁጥር
ማውጣት፣ሂሳብ መዝገብ መያዝ፣ ለተ.እ.ታ መመዝገብ፣

2. ማስታወቅ (Filing):-የሥራ ግብር፣ የቤት ኪራይ ገቢ፣ የትርፍ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት
ታክስ ወዘተ፣

3. ሪፖርት ማድረግ( Reporting):-ትክክለኛ መረጃ/ከዲክላሬሽን ጋር በተያያዘ የመስጠት


ግዴታ፣

4. ታክስ/ግብር መክፈል( Payment):-የታክስ/ግብር ግዴታዎችን በፈቃደኝነት


በትክክለኛው አግባብ የመወጣት ሁኔታ ሌሎች የታክስ ህግ ተገዥነት መገለጫዎችን
ማክበር

6
የታክስ ህግ ተገዥነት መገለጫዎቹ
ከአገር ውስጥ ታክስ አንጻር፡-
 በግብር ከፋይነት መመዝገብ እና በግብር ስርአቱ መታቀፍ፣

 ትክክለኛውን መረጃ ለግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ማሳወቅ፣

 ለግብር አወሳሰን የሚረዱ የሂሳብ ሰነዶችን በአግባቡ መያዝ፣

 የሚጠበቀውን ግብር በወቅቱ ማስታወቅ እና መክፈል

 የተቀመጡ የተመላሽ፣ኪሳራ የማሳወቅ መብቶችን በአግባቡ መጠቀም፣

7
የቀጠለ..

ከጉምሩክ አንጻር
 ትክክለኛውን ዋጋ፣ ታሪፍ፣ የዕቃን መግለጫ እንዲሁም ዕቃው የተመረተበትን

ሀገር በሰነድ ማስታወቅ ወይም ዲክለር ማድረግ፣


 በሰነድ ከተገለጸው ውጪ ዕቃን አለማስገባት፣

 የጉምሩክ ስነስርአት ያልተፈጸመባቸውን ዕቃዎች ወደ ሀገር አለማስገባት፣

 የመጋዘን፣ የቀረጥ ነጻ እና ሌሎች መብቶችን በአግባብ መጠቀም

8
ለታክስ ህግ ተገዥ አለመሆን መገለጫዎቹ
ከአገር ውስጥ ታክስ አንጻር፡-
 በግብር ከፋይነት አለመመዝገብ

 ግብርን በወቅቱ አለማሳወቅ እና አለመክፈል

 የተሳሳተ መግለጫ መስጠት (ገቢን ማሳነስ እና ወጪውን ማብዛት)

 የማይገባውን ተመላሽ መጠየቅ፣

 አላግባብ በተደጋጋሚ ኪሳራ ማሳወቅ

 ደረሰኝ አለመቁረጥ

 የሽያጭ መመዝገቢያን ማሽን በአግባብ አለመጠቀም ወዘተ.


9
ለታክስ ህግ ተገዥ አለመሆን መገለጫዎቹ
ከጉምሩክ አንጻር
 ዋጋ ማሳነስና ማብዛት

 ታሪፍ ቁጥር ማሳሳት

 የምርት ሀገርን ማሳሳት

 የዕቃውን መግለጫ ማሳሳት

 በሰነድ ከተገለጸው ብዛት እና አይነት የተለየ ዕቃን ማምጣት

 የቀረጥነጻ፣የመጋዘንና ሌሎች ልዩ መብቶችን አላግባብ መጠቀም የመሳሰሉት

ይስተዋላሉ፡፡ 10
የታክስ ህግ ተገዥነት ጠቀሜታዎች
• ለመንግስት/ለሚኒስቴር መ/ቤቱ

 ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የሀገርን ወጪ በሀገር ገቢ ለመሸፈን ያስችላል፣

 የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ይረዳል፣

 ለህግ ማስከበርና ቀረጡን ለመሰብሰብ የሚወጡ ወጪዎችን ይቀንሳል፣


• ለግብር ከፋዩ

 የግብር መብታቸውን እና ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ይረዳል፣

 ከአላስፈላጊ ወጪ በማዳን ጊዜንና ገንዘብን ይቆጥባል፣

 መስተንግዶን ያቀላጥፋል፣መልካም ስምንም ያተርፋል፣

11
የህግ ተገዥነት አለመኖር ምክንያቶች
ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አኳያ
 የአመራር ውስንነት፣

 የሲስተም(ኔትወርክ)ና የአሰራር ችግሮች መኖር፣

 የአዋጆች፣ህጐችና ደንቦች መብዛትና በቂ ስልጠና አለመሰጠቱ፣

 ከግብር ከፋዩ ጋር ተቀራርቦ የመሥራት ውስንነት፣

 ፍትሀዊነት የሌለው የቁጥጥር ስርአት መኖር፣

 የተቋሙ ሠራተኞች የሥነ ምግባር፣ የሥራ ዲሲፒሊንና ብቃት ክፍተት፣

በዋናነት የሚነሱ ናቸው፡፡ 12


የህግ ተገዥነት አለመኖር ምክንያቶች
ከግብር ከፋዩ አንጻር
 የግብር ህጉን እና አሠራሩን በደንብ አለማወቅ፣

 ቸልተኝነት እና ትኩረት አለመስጠት፣

 ለማጭበርበር መፈለግ በተለይ አላግባብ የመበልጸግ ፍላጎት፣

 ለታክስ ያለው አመለካከት ዝቅተኛ እና የተሳሳተ መሆን፣

 የሌሎች ተጽዕኖ/ሌሎች ግብር ከፋዮች፣ ቤተሰብ፣

13
የታክስ ህግ ተገዥነት ዝርዝር ባህሪያት
የግ/ከፋዮች ህ/ተገዥነት ባህሪያት በዋናነት በአራት ይከፈላል
1. ለህግ ተገዥ የሆኑ፣

2. ለህግ ተገዥ መሆን እየፈለጉ የማይሳካላቸው፣

3. ለህግ ተገዥ ላለመሆን የሚሞክሩ ግን ትኩረት ቢሰጣቸው ለህግ ተገዥ የሚሆኑ፣

4. ለህግ ተገዥ ላለመሆን የቆረጡ/የወሰኑ፣በዚሁ መነሻነት

• ሚኒስቴር መ/ቤቱ ግ/ከፋዮችን በህግ ተገዥነት ደረጃቸው በመለየት የመስተንግዶ


ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

14
የቀጠለ..
የህግ ተገዥነት ላይ ተጽእኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች የህግ ተገዥነት ፒራሚድ
BISEP MODEL

የህግ ተገዥነት የህግ ተገዥነት ስትራቴጂ


ደረጃዎች/መገለጫዎች

ከፍተኛ
ለህግ ተገዥ ላለመሆን ሙሉ የህግን አቅምን
የቆረጡ መጠቀም
ቢዝነስ
ኢንድስተሪ
ለህግ ተገዥ ያልሆኑ
መለየትና
ትኩረት ቢሰጣቸው
መከላከል
የሚያከብሩ

ለህግ ተገዥ
ግብር ከፋይ ለህግ ተገዥ ለመሆን
ፈልገው የማይሳካላቸው እንዲሆኑ መደገፍ

ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ
የተቋሙ ጥረት ሁሉም ግብር አሰራርን
ለህግ ተገዥ ከፋዮች ለህግ ተገዥ እንዲሆኑ ማቀላጠፍ
የሆኑ መስራት ነው
ሳይኮሎጂያዊ ዝቅተኛ

15
የቀጠለ..
1. ለህግ ተገዥ የሆኑ መገለጫ ባህሪያት
 ወቅቱን ጠብቀው ፋይል የሚያደርጉ፣

 ወቅቱን ጠብቀው የሚከፍሉ፣

 ትክክለኛውን ታክስ እና ተመላሽ የሚያስታውቁ፣

 ተገቢ የሆኑ ሰነዶችን የሚያቀርቡ፣

 ያልተለመዱ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው የባለሙያ ምክርን የሚጠይቁና ጥሩ

የሆነ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ያላቸው ናቸው፡፡

16
የቀጠለ..
2. ለህግ ተገዥ ለመሆን የሚጥሩ በተለያየ ምክንያት ግን የማይሳካላቸው መገለጫ ባህሪያት

 አልፎ አልፎ የሚያስታውቁ ወይም ዘግይተው የሚከፍሉ፣

 ደረጃቸውን እና ተመላሻቸውን የሚያሳስቱ፣

 የተሳሳተ ስሌት የሚያቀርቡ፣

 የተለየ ነገር ሲገጥማቸው የባለሙያ ምክር የማይጠይቁ፣

 በስጋት ደረጃ ሊለዩ የሚችሉ ናቸው፡፡

17
የቀጠለ..
3. ለህግ ተገዥ ለመሆን የማይፈልጉ ግን ጥቂት ትኩረት ቢሰጣቸው በቀላሉ የሚመለሱ መገለጫ ባህሪያት

 በአጠቃላይ ተቀባይነት በሌለበት ጊዜ ውስጥ ታክሳቸውን የሚያስታውቁ እና የሚከፍሉ ሆነው በዚህ

ምክንያት የሚመጣባቸውን ማንኛውንም ስጋት ለመቀበል የተዘጋጁ፣

 ደረጃቸው እና ተመላሽ መግለጫቸው ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ታስቦ የሚገለጽ፣

 የታክስ መጠናቸው ካሉበት ኢንዱስትሪ የወጣ ወይም ያልተመጣጠነ፣

 ጥሩ ያልሆነ የህግ ተገዥነት ታሪክ ያላቸው እና ምንአልባትም አንድን አይነት ጥፋት በየዓመቱ የሚደጋግሙ፣

 በስጋት ሥራ አመራር ሊለዩ የሚችሉ፣

18
የቀጠለ..
4. ለህግ ተገዥ ላለመሆን የወሰኑ መገለጫ ባህሪያት

 በታክስ ስርአቱ ያልተመዘገቡ ሆነው በሶስተኛ ወገን ጥቆማ የሚያዙ ወይም የተመዘገቡ ሆነው ሁልጊዜ

ያለማቋረጥ ዘግይተው የሚያሳውቁና የሚከፍሉ

 ሆነብለው ገቢያቸውን የሚያሳንሱ፣ ወጪን የሚያጋንኑ

 እውነተኛ ያልሆነ ሰውነት የሌለው ተቋምን የሚያስመዘግቡ

 ከግብር የተሰወሩ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የሚያካሂዱ

 አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ሲጠየቁ የማይሰጡ

 የፍርድ ቤት፣ የውርስ ሪከርድ ያላቸው

 በስጋት ለመለየት አንዳንዴ የሚያስቸግሩ ሊሆኑ ይችላሉ

19
የመስተንግዶ አይነቶችን መወሰን
ለህግ ተገዥ ለሆኑ

 የግብር ስርአቱን ቀላል፣ ግልፅ፣ ቀልጣፋና ሊተገበር የሚችል ማድረግ

 አስፈላጊውን እርዳታ እና ምክር መስጠት

 ማበረታታት አና እውቅና መስጠት

ለህግ ተገዥ መሆን እየፈለጉ የማይሳካላቸው


 አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ

 ህጉን እና አሰራሩን እንዲረዱት በቂ ስልጠና እና ትምህርት መስጠት

 ህግ እንዲያከብሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት/ ቅጾች፣ ግኑኝነቶች፣ሂደቶች

20
የመስተንግዶ አይነቶችን መወሰን
ለህግ ተገዥ ላላመሆን የሚሞክሩ ትኩረት ቢሰጣቸው ሊመለሱ የሚችሉ
 የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎችን መጻፍ፣ ቅጣቶችን መጣል፣ በኢንተለጀንስ መከታተል፣ ኦዲት

ማድረግ፣
 ግዴታዎቻቸውን በግልፅ ማሳወቅ/ማስቀመጥ ሲሆኑ፣

ለህግ ተገዥ ላለመሆን የቆረጡ/የወሰኑ


 በኢንተለጀንስ መከታተል

 ንብረት መያዝ ወይም መውረስ

 በህግ መጠየቅ

21
ማጠቃለያ
• አክብሮ መንቀሳቀስ ለግብር ከፋዩም ሆነ ለተቋሙ ከፍተኛ ጥቅም ያለው
ሲሆን በተለይ፡-
– ለግብር ከፋዩ የህግ ተገዥነት ወጪን በመቀነስ በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ

– ለተቋሙ ደግሞ የአስተዳደራዊ ወጪን በመቀነስ ያቀደውን ገቢ ለመሰብሰብ ከፍተኛ


አስተዋጽዖ አለው

– ስለሆነም ሁሉም ግብር ከፋይ ለህግ ተገዥ በመሆንና ህገ ወጥነትን በመከላለከል

የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

22
አመሰግናለሁ!

23

You might also like