4795412

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 6

3.4.1 ሥጋት ማለት ምን ማለት ነው?

ሥጋት ማለት በአንድ ተቋም ዓላማ ላይ በአጭር ጊዜ አልያም


በረጅም ጊዜ አሉታዊ ተፅዕኖ ለማሳደር የሚችል ሁኔታ ሲሆን
ሊከሰት የሚችለውን ሥጋት አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዳ
ሁኔታን በመፍጠር ሥጋትን ለመቀነስ ከተቻለም ለማስወገድ
የሚያስችል አሠራርን መዘርጋት የሥጋት ሥራ አመራር ሊባል
ይቻላል፡፡ የሥጋት ዓይነቶች ሁለት ሲሆኑ እነርሱም ውጫዊ
ወይም ውስጣዊ ተብለው ይለያሉ፡፡ በመሆኑም ለግብር/ለታክስ
መሰወር ወይም መጭበርበር ምክንያት የሚሆኑ ውስጣዊም ሆነ
ውጫዊ ሁኔታዎች ለግንዛቤ ያክል የሚከተሉት ተጠቃሾች
ናቸው፡፡
ውስጣዊ ሥጋት
 ስለ ግብር ከፋዮች በቂ እና የተደራጀ መረጃ ያለመያዝ፣
 የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር መኖር፤
 ግዴታቸውን ባልተወጡ ግብር ከፋዮች ላይ አስተማሪ የሆነ
እርምጃ ያለመውሰድ፤
 ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት ተግባራቸውን
ያለማከናወን፤
 ዕቅድን መሠረት አድርጎ ያለማከናወን፤
 ያለውን የሰው ኃይልና ሀብት በአግባቡ ያለመጠቀም፤
ውጫዊ ሥጋት
 በግብር ወይም ታክስ ከፋይነት ያለመመዝገብ፣
 የግብር/የታክስ ህጉን በሚገባ ተገንዝቦ ያለመፈፀም፣
 ግብር ከፋዮች በፍቃደኝነት ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ ያለመሆን
 አጋርና ተባባሪ ወገኖች /ድር ጋር ያለው ቅንጅት ደካማ መሆን፣ ወዘተ….
 ከላይ የተዘረዘሩ ነጥቦች ለግብር ወይም ታክስ መሰወር ምክንያቶች
ናቸው፡፡ በመሆኑ እነዚህን ሥጋቶች አንድ በአንድ የሥጋት ደረጃቸውን
መመዘንና እርምጃ መውሰድ ተገቢነት አለው፡፡
3.4.2 በሥጋት መመዘኛ ወቅት ትኩረት ሊደረግባቸው
የሚገቡ ጉዳዮች
ግብር ከፋዮች በተፈቀደላቸው የሂሣብ ጊዜ ገቢያአቸውን
ያለማስታወቅ፣
ገቢን አሳንሶ ማስታወቅ፤
በተደጋጋሚ ጊዜያት ባዶ/Nill/ ሪፖርት ማድረግ፣
ሽያጭን በደረሰኝ ያለመከናወን፤
በግብር ወይም በታክስ ከፋይነት ያለመመዝገብ፤
ተገቢ ያልሆነ የግብዓት ታክስ ተመላሽ መጠየቅ፣
በግብር ከፋዩ ስም የተመዘገቡ ንግዶችን አጠቃሎ ሪፖርት
ያለማቅረብ፣
የተሳሳተ የሂሣብ ሪፖርት ማቅረብ፣
ግብይት እያካሄዱ ሣለ ባዶ ሪፖርት ማቅረብ፣
ከንግድ ድርጅቱ ጋር ግኝኙነት የሌለውን የሂሣብ ሠነድ ማቅረብ፣
ግኑኝነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚካሄድ ግብይት ወጪን ከፍ አድርጎ ገቢን
አሳንሶ ማሳየት፣
ንግዱን ያቋረጡ በማስመሰል ይህንኑ ተመሣሣይ ንግድ በቤተሰብ ስም
ማስመዝገብ፣ /ሚስት፣ ልጅ፣ አባት፣ ወንድም፣ እህት ወዘተ…/
ግዥንና ሽያጭን መሰወር፣
በተደጋጋሚ ጊዜያት ተመላሽ መጠየቅ፣
በተለያዩ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ገቢ እና ወጪን ማከናወን፤
ከድርጅቱ ጋር ግኑኝነት የሌለውን የባንክ ብድር የወለድ ወጪ ማቅረብ፣
በብድር ለተካሄደ ግንባታ የተከፈለ ወለድንና ኢንሹራንስን የግብር ዘመን
ወጪ አድርጎ ማቅረብ፣
የንግድ ማስፋፊያ ግንባታ ላይ የተከፈለ ግብአትን ግንባታው ማምረት
ሣይጀምር የግብአት ታክስ ማቀናነስ ወዘተ………
ከላይ የተዘረዘሩና ሌሎች መመዘኛ ታሳቢዎችን በመወሰድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ
የሚገኙ ግብር ከፋዮችን ከዚህ በታች በቀረበው ሠንጠረዥ መሠረት በሥጋት
ደረጃቸው ቅደም ተከተል መለየት ያስፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሠንጠረዡን
ለመጠቀም እንዲያስችል ግብር ከፋዮችን በደረጃቸው፤ በንግድ ዘርፍ
እንዲሁም በሌሎች መረጃዎች የተለየና የተደራጀ መረጃ መያዝ ያስፈልጋል፡፡

You might also like