Sned

You might also like

Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 45

በሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

መምሪያ

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን እና ግንባታን ስርዓት ለማስያዝና


ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ
የተዘጋጀ የንቅናቄ ሰነድ

ጥር 2016
ሀላባ-ቁሊቶ
መግቢያ

በከተማችን እየተመዘገበ ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ የዜጎች የኑሮ ዘይቤ ለውጥ በተለይም
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ላይ ከምንጊዜውም የተለየና የበለጠ መጠነ ሰፊና በተጨባጭ የሚታይ በከተማዋ
ማስፋፍያ የመስፈርና የመኖር ፍላጎት እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በከተማችን የመሬት አጠቃቀም ከዕቅድ ውጪ መሰረታዊ የመሠረተ ልማት አቅርቦት እንኳን
ማድረስ በማያስችል ሁኔታ የከተማችንን የወደፊት የዕድገት ተስፋ በሚያጨልም መልኩ እየተስፋፋ
ይገኛሉ፡፡

በአርሶ አደሩ ረገድ የከተማን መስፋፋት እንደ ስጋት በማየት በከተማችን ባሉ ማሰፋፊያ ቦታዎች በተለይ
የእርሻ መሬቱን እየከፋፈለ እንዲሸጥ በማድረግ ከቀዬው እንዲፈናቀልና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ በከተማችን
ሀላባ ቁሊቶ በሁሉም አቅጣጫ እንዲስፋፋ አድርጎታል፡፡
የቀጠለ…

ከዚህ አንጻር ያለው የግንዛቤ ችግርና የህገ ወጥ ደላላው ተግባራት ታክለው የአርሶ አደሩ ተገቢ ያልሆነ ከመሬት

መፈናቀል ለከተማችን ጤናማ ያልሆነ ዕድገት የጎላ ሚና ይጫወታል፡፡

ከዛም በዘለለ በሀላባ-ቁሊቶ ከተማ እየተስተዋለ ያለው የህገ-ወጥ ግንባታ ከህገ-ወጥነቱም ባሻገር ወረራ

በሚመስል መልኩ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ ከተማችን ዛሬ ላይ ያለችበትን ሰላምና መረጋጋት በማስቀጠሏ ላይ

ክፉ ጥላ እያጠላባት ይገኛል፡፡
… ….
የቀጠለ
የቀጠለ
በከተማችን ለቸግሩ መባባስ ህገ-ወጥ ግንባታን አፍርሶ ሰርዓት በማስያዝና የመሬት ወረራን በማስቆም ረገድ
በዘርፉ ላይ ያለውን የዳተኝነትና የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በመድፈቅ ረገድ ተጨባጭ
ውስንነቶች ይታያሉ፡፡

በከተማችን የማሰፋፊያ አከባቢ ያለአግባብ እየተገነቡ ያሉ ህገ-ወጥ ግንባታዎችና በህገ-ወጥ መንገድ የመስፈር
ሁኔታ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳይ ልዩ ትኩረት የሚሻ ሆኖ ተገኝቱዋል፡፡

ስለሆነም ይህንን ተግባር ለመከላከልና ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ይረዳን ዘንድ ይህ የንቅናቄ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
ዓላማ

መላው የከተማ ነዋሪ ህብረተሰብ በተለይ በማስፋፊያ


አከባቢ የሚገኘውን አርሶ አደራችንን ተሳትፎውን በላቀ
ደረጃ በማጎልበት በከተማችን የመሬት ሀብትን ከወረራ
በመታደግ የዜጎች ያለአግባብ መበልፀግ እናም መፈናቀል
የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ስርዓቱን ውጤታማ
በማድረግ ከተማችንን ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አከባቢ
እንድትሆን ማስቻል፡፡
ዋና ዋና ግቦች

የጉዳዩ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆነውን አርሶ አደራችንን መታደግ ተችሎዋል

በማስፋፊያ አከባቢ በሚገኝ መሬት ልማታዊነትና ጠቀሜታ ላይ የጋራ አመለካከት ተፈጥሯል፡፡

በከተማ ማስፋፊያ አካባቢ በመሬት ላይ የሚፈጸም ህገ-ወጥ ተግባርን ለመከላከልየ ሚያስችል ቅንጅታዊ
አሰራር ተዘርግቶ ተተግብሯል፤ የመሬት መረጃም ተደራጅቷል፡፡

በፕላንና በመሠረተ ልማት የምትመራና ከህገ-ወጥ ግንባታ/የመሬት ወረራ ነጻ የሆነች


ከተማ ተፈጥረዋል፡፡

በከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነት ጨምሯል፡፡


ዝርዝር ተግባራት

 በከተማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የህገ-ወጥ መሬት ወረራን እና ህገ-ወጥ

ግንባታ ላይ ግልጽነት በመፍጠርና ባለቤት በመሆን በተደራጀ መልኩ እንዲቀሳቀሱ የጋራ

መግባባት ይፈጠራል፡፡

 የህገ-ወጥ ግንባታንና የመሬት ወረራን በመቆጣጠር በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችና

አጥሮች እርምጃ መውሰድ


የቀጠለ…

 በማስፋፊያ አካባቢ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጊዜያዊ የይዞታ መጠቀሚያ

ሰርተፊኬት መስጠትና የህጋዊ ካዳስተር ስርዓቱን ማጠናከር ዋና ዋናዎቹ

ናቸው፡፡

 በየደረጃ የተሰማራው አመራር በግልጽ በተቀመጡ የከተማ መሬት ወረራና ህገ-

ወጥ ግንባታ በውይይቱ መጨረሻ ላይ ተልዕኮውን ለመወጣት የላቀ የአመራር

ሚና እና ኃላፊነት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡


ህገወጥ ይዞታዎችን በተመለከተ

ህገወጥ ይዞታ ማለት፡- አግባብ ካለው አካል ፈቃድ እና እውቅና ውጭ በወረራ

የተያዘ የመሬት ይዞታዎች የምለዉን ትርጉም ይይዛል፡፡ በአገረችን በሉ ከተሞች

ይዞታዎች በሶስት መልኩ የተከፋለ ነዉ ህገዊ፤ ህገወጥና ሰነድአልባ ህገዊ ይዞታዎች

አግባብ ባለዉ አካል እዉቅና እና ይዞታ ማረጋጋጫ ሰነድ የለቸዉ የመንግስትን ግብር

በአግባቡ የሚከፍሉ በተጨማሪም የአገልግሎት ክፍያ የምከፈልበቸዉ ነቸዉ ሰነድ-

አልባም ከዚሁ ተመሳሰይ ሆኖ ነገር ግን የይዞታ ማረጋጋጫ የሌለቸዉ ነዉ፡፡


የቀጠለ…

 ህገወጥ ይዞታዎች ከላይ ከየናቸዉ ከሁለቱም ዉጭ የሆነ ጉዳቱ ብቻ የመዘነ

ነዉ፡፡

 የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ ህገወጥ ይዞታን በማፍረስ ከዚያ

ውጭ ፕላንን ታሳቢ የሚደረግ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመግታትና ቀጣይ ህገወጥ

ወረራን ለመከላከል በሚያስችል አግባብ እንዲፈጸም ይደረጋል ፡፡


የቀጠለ…

 የከተማ መሬት በተለያየ ጊዜ መሬትን ለመስጠት ህጋዊ ስልጣን

ከተሰጠው አካል እውቅና ውጪ በህገወጥነት እና በጉልበት በወረራ

መልክ እየተያዘ ለተለያዩ ተግባራት እየዋለ ይገኛል፡፡ይህ ድርጊት

የከተሞቻችን የመሬት ሀብት በከፍተኛ ደረጃ ከማመናመኑም በላይ

የመሬት አጠቃቀም ስርዓቱን ያወሳሰበውና ያዛባው ጉዳይ መሆኑን;


የቀጠለ…

 ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ድርጊቱ ከማሳፈር ይልቅ ይዞታው ህጋዊ

እንዲደረግ እንደ ትክክለኛ እና ተገቢ የመብት ጥያቄ እየቀረበ መሆኑ ነው፡፡

 ይህንን አሰራር በድርጊት እና በሀሳብ ጭምር ለማስፈጸም የሚንቀሳቀስ

የቢሮክራሲው አካል እና አሰራሩን እንደ ተራ ጉዳይ የሚያየው የህብረተሰብ ክፍል

በስፋት መኖሩ ነው፡፡


የቀጠለ…

 ከዚህም በተጨማሪ ድርጊቱ በአቋራጭ መንገድ እንደ መክበሪያ ስልት በመውሰድ

ቁጥሩ ቀላል የማይባል የህብረተሰብ ክፍል በተደራጀ አግባብ የተሰማራበት

መሆኑን፡፡

 ህገ-ወጥ ወረራ የሚፈጸመው ከውስጥ ኃይል ጋር በመመሣጠር በመሆኑ በህግ

የተጠያቂነት የሚፈጸምበት አሠራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ተግባራዊ ለማድረግ

ከባድ አድርጎታል፡፡
የህገወጥ የመሬት ወረራ እየተካሄደ ያለዉ በማን ነዉ?

 በከተማ ዉስጥ መኖሪያ ቤት ያላቸዉ እና ተጨማሪ ፈላጊዎች፤

 በህጋዊ መንገድ ያገኙትን ቦታዎች እንዲሁም የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን እየሸጡ

ህገወጥ ቦታዎች በመግዛት የሰሩ፤

 ከመንግሰት መዋቅር ጋር በመመሳጠር የያዙ ሰዎች፤በመንግስት የስራ ሀላፊዎች፤ የፍትህ አካላት

እና ሰራተኞች በተለያየ ደረጃ እና በተለያየ ተቋማት የሚገኙ፤የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸዉ

ግለሰቦች፤
የቀጠለ…
 የአመራሩና የባለሙያ አድርባይነት እና ተሳታፍ መሆነቸዉ

 የአርሶ አደሩ የግንዛቤ ማነስና ነገን አሻግሮ አለማየት

 በህገወጥ ደላላ አማካይነት መሬት ከአርሶ አደር የገዙ ግለሰቦች፤


የቀጠለ…

 ከዚህ አንፃር መሬትን ለግል ብልጽግና እንደ ብቸኛ መገልገያ በመቁጠር

በማንኛውም ዓይነት በአቋራጭ መንገድ ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው

የህብረተሰብ ክፍል ቀላል ቁጥር ያለው አይደለም፡፡ ይህ መሰረታዊ

የአስተሳሰብ ዝንፈት በእጅጉ ስር የሰደደ በመሆኑ በተገኘው አጋጣሚ

የህዝብና የመንግስት ሀብት የሆነውን መሬት በመውረር ለመያዝ

የሚደረገው እንቅስቃሴ አነስተኛ ነው የሚባል አይደለም፡፡


ህገ ወጥነት የሚያስከትለዉ ጉዳት

 በከተማችን በማስፋፊያ አከባቢዎች የሚገኘው የመሬት ሀብት በህገ-ወጥ መንገድ በወረራ እየተያዘ

ከፕላን ዉጪ ግንባታዎች እየተፈፀሙበት ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የመንግስትና የህዝብ የሆነውን

የመሬት ሀብት በከፍተኛ ደረጃ ከማመናመኑም በላይ መሬትን ለሚፈለገው ማህበራዊና

ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማዋልና በፕላኑ መሰረት በአግባቡ ለመምራት ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆያቷል፡፡
የቀጠለ…

 ይህ ብቻም ሳይሆን አሁን ባለው የግብርና ምርታማነት ደረጃ የህገ-ወጥ

ግንባታ የሚከናወንበት አካባቢ የከተማው እድገት እስከሚደርስ ድረስ

የማስፋፊያ አካባቢ አርሶ አደሮች በመሬታቸው እያመረቱ የመጠቀም

ዕድላቸውን ያጠበዋል፡፡
የቀጠለ…
 በከተማችን ህገ-ወጥ ይዞታዎች መበራከት የከተማችንን የመሬት ሀብት በአግባቡ ለልማት

ለማዋል ካለማስቻሉም በላይ የከተሞችን አረንጓዴ ቦታዎችን እና ለህዝብ አገልግሎት

የተከለሉ ክፍት ቦታዎችን ጭምር በመውረር በከተሞች የመሬት ሀብት አጠቃቀም ላይ

ከፍተኛ ብክነትን አስከትሏል

 ከተሞች መሬታቸውን የተቀናጀ የከተማ ልማት ለሚያረጋግጡ ለመንገድ፣ ለሕዝብ የጋራ

አገልግሎት የሚውሉ ክፍት ቦታዎችና ለግንባታ የስብጥር ምጣኔው (30፤30፤40)

ማስጠበቅ አልተቻለም፡፡
የቀጠለ….

 በከተማችን ነባራዊ ሁኔታ መነሻነት ስንዳስስ ቀበሌዎቻችን አሁንም ድረስ

እየተፈጸመ ያለውን የመሬት ወረራ መከላከል እና መቆጣጠር መቻል

ተስኗቸዋል፡፡

 በመሆኑም ይህንን ችግር በፍጥነት በማስተካከል በከተማችን ውጤታማ የመሬት

ይዞታ አስተዳደር ስርዓት እንዲሰፍን ማስቻል በአጣዳፊነት እንዲፈጸም

የሚጠበቅ ስራ ይሆናል፡፡
የማስፋፊያ አከባቢ የህገወጥ ግንባታ አሉታዊ ተጽዕኖዎች

1.ኢኮኖሚያዊ

2.ማህበራዊ

3. ፖለቲካዊ

4.አስተዳደራዊ
ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ

 ከተሞቻችን በህገወጥ መልኩ እየተስፋፈ በሄደ ቁጥር አርሶ አደረችን አርሶ የምበለዉን

የእርሻ መሬት እየሸጠ ይጨርሳል፡፡የምሸጠዉም ምንም አይነት ቢዝነስ ፕላን በለዘገጀበት

በመሆኑ ቀድሞ ከለመደዉ የወጪ አጠቀቀም ወጥቶ ብሩ ከእጁ የማያልቅ ይመስለዉና

በአልባሌ ነገር ላይ ጫት ማቀም፤መጣጥ እና ወዘተ የመሳሰሉት አይነት የስነ-ምግባር

ጉድለት ይሻምታል በገዛ እጁ አርሶ የምበለዉን መሬት ሽጦ ከስንት አንዱ ነዉ በከተማ

መምጣት የምጠቀመዉ አልፎ ተርፎ የገባያ ኢኮኖሚ ኑሮ ዉድነት እንድባበስ ይደርጋል፡፡


የቀጠለ…

 ህገወጥ ገዝቶ የሚገነበዉ አካል ከከተማ ፕላን ቀድሞ በመሆኑ በፕላን ትግበራ ጊዜ

መንገድ ስከፋት መንገዱ ይዞት ይሄድና በዕድሜ ልኩ ለፍቶ የመጣ ልሆን

ይችላልና እሱም የአርሶ አደሩን ዕጣ ፈንታ የኢኮኖሚ ቀዉስ ላይ ይወድቃል ማለት

ነዉ፡፡
ማህበራዊ ተጽዕኖ

 እንደምተወቀዉ አርሶ አደሮቻችን የስራ ባህሉ እጅግ ደከማ ነዉ አርሶ ከመብላት

ዉጪ በእጁ የለዉን የእርሻ መሬት ሽጦ ከጨረሰ ሌላ የፈጣራ ስራ መስረት

ከልቻለ ልሆን የምችለዉ ለልመና መንገድ ይወጣል አልያም ዘርፎ መብላት

ይጀምራል፡፡ይህ በማህበራዊ ላይ የምከሰተዉ ቀዉስ የጎንዮሽ የከተማ ዕድገት

የምያመጣ ጣጣ ነዉ፡፡
ፖሊቲካዊ ተጽዕኖ
• በኢኮኖሚ የተረጋጋ ህዝብ ከሌለን የተረጋጋ ፖለቲካ ይኖራል ተብሎ አይተሳብም የተረጂዎች/ለማኞች ቁጥር

እየበረከተ በሄዳ ቁጥር አሁን ላይ ያለዉ የፖለቲካ ገጽታ እንደነበረ ይቀጥላል ተብሎ ማሰብ አይቻልም
አስተዳደራዊ ተጽዕኖ
 በፕላን የልተመራ የከተማ ዕድገት የአገልግሎት ሰጪ ተቋም በስታንደርድ መሰራት መግኛት እጅግ

ይከብዳል፡፡

 በህገወጥ አከባቢ ህዝቡ የመሰረተ-ልማት ጥያቄ መብዛት ምንም እንኳን የምጠበቅበትን

የመንግስት ግብር ባይከፍልም

 የስርቆት አይነት እንድበረከት እና የፀጥታ ስጋት አከባቢ ይሆናል

 ከተማዉ በህገወጥ መልኩ ከፕላን ቀድሞ በመሄዱ ፕላን ትግበረ ጊዜ በየቦታዉ ግንባታዎችን

ለመንገድ በመፍራስ የሃብት ዉድመት እና ህዝቡ ሁከት እንድፈጠር ያደርጋል፡፡


ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ
ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታ ለመከላከል የባለ ድርሻ አካላት ሚና

የከተማ አስተዳደሩ ሚና

 የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ተቋማዊ በሆነ አግባብ መዋጋት ፤በመሬት


ልማትና ማኔጅመንት ዕቅድ ዙሪያ በየወቅቱ ማወያየት ፤የጋራ እቅድ የማዘጋጀት እና
ህብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር፡፡
 ከዛም ባሻገር ለህብረተሰቡ እና ለሚመለከታቸው አካላት ስለ መሬት ወረራ አስከፊነት
ግንዛቤ በማስጨበጥ አዲስ የህገ-ወጥ ይዞታዎች እንዳይከሰቱ ከፍተኛ እና የማያቋርጥ
ክትትል በማድረግ፡፡
ዘርፋን የሚመሩ ተቋማት /ማዘጋጃ ቤት/ ሚና

 በከተማው በሚገኙ ዝቅተኛ የአስተዳደር እርከን (ቀበሌ) በዝርዝር ስራዎችን ማዘጋጀት


፤ስራዎቻቸውን በአግባቡ ማከናወንና በተጨማሪ ለዕቅድ አፈጻጸም ክትትል የሚረዳቸውን
ቼክ ሊስት ማዘጋጀት እንዲሁም መሬት የህዝብ ሀብት መሆኑን ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ
እንዲይዝ ማድረግ
 ጊዜያዊ የአርሶ አደር የእርሻ መጠቀሚያ ሰርተፊኬት ተደራሽ ማድረግ፡፡

 የካዳስተር ዘርፉ የተደራጀ ሆኖ ውጤት ሊያሳይ በሚችል መልኩ የዘርፉን ተግባራት አፈጻጸም
እየገመገሙ የመምራትና አሁን ያለውን የመሬት አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ እየተሄደ ያለበት
ርቀት ቀጣይ ትኩረት የሚሻ እንደመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይፈልጋል፡፡
የህዝብ ክንፍ ሚና

 በከተማው ህገ-ወጥ የማፍረስ ስራ ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ መሳተፍ፤ በአጀንዳዎቹ ዙሪያ

በተመለከቱት የመታገያ ስልቶች መሰረት ተገቢውን ድርሻ መጫወት ይኖርበታል፡፡

 ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን ስርዓት በማስያዝ እና በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡን በተደራጀ

መልኩ በሰፈር እና በብሎክ ክፍት የመሬት ሀብቱን በመቁጠር ተረክቦ እንዲጠብቅ ክፍት

የመሬት ሀብት ተቆጥሮ ለሰፈሩ ነዋሪዎች ርክክብ መፈጸሙን በውል ማረጋገጥ በዕቅዱ

መሰረት ያልተከናወነ ተግባር ሲኖርም የሚመለከተው አካል፤ በአግባቡ ተጠያቂ መሆኑን

ማረጋገጥ ተገቢ ይሆናል፡፡


በየደረጀ ያለዉ የአመራር ሚና

ከበታች አመራሩ እስከ ከፍተኛ


አመራሩ ለተግባሩ ባለቤት
እስከመሆን ድረስ

በተግባሩ ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ


በተመደበበት ቀበሌ ሚናውን ተግባራዊነቱ
እንዲወጣና ስለተግባሩ አፈፃፀም መገምገም፡፡
የደላላው ሚና

ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ግንዛቤ


ይሰጣቸዋል፡፡ ከዛም በተለይ ህገ-ወጥ
የሆኑ ፍቃድ የሌላቸው ደላላዎች በህግ
አግባብ የሚታዩ መሆናቸውን በአንክሮት
እናያለን፡፡
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች

በዚህ ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው ከሚገመቱ ችግሮች ውስጥ

 በዚህ ተግባር የፈረጠሙ ደላሎች ቅንጅታዊ አሰራር የጠነከረ መሆን፣

 በንቅናቄው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ በመሆኑ አቀናጅቶ የመምራት ውስንነት ፤

 ንቅናቄውን የአንድ ወቅት የዘመቻ ስራ አድርጎ መመልከትና ስራዎችን በዘላቂነት ማንቀሳቀስ ያለመቻል

ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ለችግሮች መፍቻ ልንከተላቸው የሚገቡን መፍትሄዎች

 ባለድርሻ አካላትን በቅንጀት ለመምራት የሚያስችል የክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት

አፈጻጸሙን መከታተል፤

 የንቅናቄው ባለቤት የሆነው ህዝቡ እና አጋር አካላት አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት ወደ ንቅናቄ

እንዲገቡ ማድረግና ወቅታዊ የሆነ የአፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ናቸው፡፡

 የንቅናቄውን ስራ ከተደረገ በሃላ የተግባሩን ቀጣይነቱን ማረጋገጥ፤

 ከደላሎች ጋር በጉዳዩ ላይ መግባባትና ህገ-ወጦችን ከተግባሩ መነጠል፣


በየደረጀዉ ያለዉ የህገ -ወጥ ግንባታ ግብረ ኃይል ቁልፍ ተልዕኮዎች

 የከተማችን ማስፋፊያ አከባቢ የመሬት ኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የአመለካከት ትግል


በማድረግ የከተማችን ዙሪያ አርሶ አደሮች ከተማችን ሲሳፋ ተጠቃሚ እንሆናለን የሚል
አመለካከት እንዳይዙ ማድረግ

 የከተማችን ማስፋፊያ አከባቢ አርሶ አደሮችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና በግብርና


ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ሙሉ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
 የከተማችን የገጠር ትስስርና መደጋገፍን በማጠናከር የአብሮነት ስሜት መፍጠር
የቀጠለ
የቀጠለ … …..

 የከተማችን ማስፋፊያ አከባቢን በህገወጥ ግንባታ ሳይሆን በፕላን እንድመራ መድረግ

 የከተማችን የዙሪያ ገጠር ይዞታን በቅንጅት መመዝገብና መረጃ መስጠት

 በከተማችን ማስፋፊያ አከባቢ በሊዝ ደንብና በመመሪያው የአርሶ አደሩን

ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተመላከቱ ጉዳዮች በተጨባጭ የተመለሱ መሆናቸውን

ማረጋገጥ እንዲሁም ለከተማ ልማት መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች የካሳ

አከፋፈልና አጠቃቀም ላይ አርሶ አደሮችን ማወያየትና በማህበር አደራጅቶ ድጋፍ

በማድረግ ወደ ስራ ማስገባት
የቀጠለ…

 የህገ-ወጥ ግንባታንና የመሬት ወረራን በመቆጣጠር በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችና አጥሮች ያፋርሳል

ለመንግስት ገቢይደረጋል

 በህገወጥ ግንባታዎች ላይ የተሳተፉ አካለት ህገዊ እርምጃ መውሰድ የከተማ ዕድግት እስክደረሰዉ ድረስ አርሶ

የምበለዉን የእርሻ መሬቱን በህገወጥ መንገድ የምሸጠዉን አርሶ አደሮችን እርምጃ የመዉሰድ ስራ ይሰራል፡፡

 በህገወጥ መልኩ አርሶ አደሩን በመፋነቀል ገዝቶ የገነበ አካል በህግ እንድጠየቅ እና መሬቱ ደግሞ መሬት ባንክ

የመድረግ ስራ ይሰራል

 በህገወጥ አከባቢ ግንባታ ስሰሩ የተገኙ አናጺዎች በህግ እንድጠየቁ ይደረጋል

 በተለያየ መንገድ ደአርሶ አደርን መሬት ለመሻሸጥ የምንቀሳቀስ ደላላዎችን በህግ እንድጠየቁ ይደረጋል
የግብረ ኃይሉ አባላት በዞን ደረጃ

1. የዞኑ አስተዳደሪ ------------------------------ሰብሳቢ

2. የዞኑ ከተማ ልማትና ኮ/መ/ኃላፊ------------ም/ሰብሳቢ

3. የከተማው ከንቲባ -------------------------------ጻሐፊ

4. የዞኑ ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ -------------------አባል

5. የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ -------------------አባል

6. የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ------------------አባል

7. የዞኑ ከተማ ል/ኮ መ/መሬት/ዘ/ኃላፊ-----------አባል

8. የዞኑ ከተማ ል/ኮ/መ/ፕላንዘ/ኃላፊ---------------አባል

9. የከተማው ማዘጋጃ ቤት መሬት/ዘ/ኃላፊ---------አባል


የግብረ-ኃይሉ አባላት በከተማ አስተዳደር ደረጃ

1. የከተማ አስተዳደር ካንቲባ-------------------------------ሰብሳቢ

2. ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ------------ ----------------ም/ሰብሳቢ

3. የከተማው ማዘጋጃ ቤት የመሬት ዛርፍ ኃላፊ ---------------------ጻሐፊ

4. የከተማው ማዘጋጃ ቤት ኮንስትራክሽን ዛርፍ ኃላፊ---- -----------አባል

5. የከተማው ማዘጋጃ ቤት ፕላን ልማት ዛርፍ ኃላፊ ------------------አባል

6. ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ----------------------------አባል

7. ከከተማ ዓቃቤ ህግ ጽ/ቤት የሚወከል አንድ አቃቤ ህግ ባለሙያ ----አባል

8. ከከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የሚመደብ አንድ ፖሊስ ---- -----አባል


 በተጫመሪም የሶስቱም አድሱ ቀበሌ አስተዳደሪዎች ….አባልየሆኑበት ግብረ-ኃይል በከተማው ከንቲባ /
አስተዳዳሪ ይቋቋማል
የግብረ-ኃይሉ አባላት ከተማ ማዘጋጃ ቤት ደረጃ

 ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ-----ሰብሳቢ
 የከተማው ማዘጋጃ ቤት የመሬት ዛርፍ ኃላፊ — ም/ሰብሳቢ
 የከተማው ማዘጋጃ ቤት ፕላን ዛርፍ ኃላፊ --አባል
 የማዘጋጃ ቤት ኮንስትራክሽን ዛርፍ ኃላፊ --አባል
 የ3ቱም ቀበሌ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች -- አባል
 የማዘጋጃ ቤቱ ቴክኒክ ባላሙያ ቲም የሆኑበት ግብረ-ኃይል በማዘጋጃ ቤት ስራ
አስኪያጅ ይቋቁማል፡፡
የግብረ-ኃይሉ አባላት በቀበሌ ደረጃ

ሀ/ የቀበሌዎቹ አስተዳደሪዎች ……….ሰብሳቢ


ለ/ የቀበሌዎቹ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጆች ……ም/ሰብሰቢ
ለ/ የማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ዘርፍ ቡድን መሪ ........አባል
ሐ/ የቀጣና ሊቀመንበር ..................… አባል
መ/ የቀበሌ ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር..............……አባል
የዞን ግብረ ኃይል ተግባርና ሃላፊነት
o በከተሞች ማስፋፊያ አከባቢ በመሬት ልማታዊነትና ህገ ወጥነት ላይ የጋራ
አመለካከት መፍጠር
o የከተሞችና የዙሪያ ወረዳ ድንበር በአግባቡ መለየቱንና መካለሉን ያረጋግጣል፡፡
o በከተማ የማስፋፊያ አከባቢ በመሬት ላይ ማንኛውም ህገ ወጥነት ሲፈጸም ግብረ
ኃይሉን በማቀናጀት አስቸኳይ የእርምት ዕርምጃ እንድወሰድ አስፈለግውን ድጋፍ
የደርጋል፡፡
o የግብረ ኃይሉን አጠቃላይ እንቅስቃሴና የተግባር አፈጻጸም በየወሩ በመገምግም
ለክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የጽሁፍ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
በከተማ ደረጃ የሚቋቋመው ግብረ-ኃይል ተግባርና ኃላፊነት፡-

ሀ/ የሊዝ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ጠንቅቆ በመረዳት ተግባሩን በዕውቀትና በጥብቅ ዲስፕሊን ይፈጽማል፣

ለ/ ህገ-ወጥ ግንባታዎችን ያፈርሳል፣ አጥፊዎችን ለህግ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣

ሐ/ ህገ-ወጥ ግንባታ ለመከላከል ከተቋቋሙ ከሌሎች አካላት ጋር በትብበር ይሰራል፣

መ/ በቀበሌና በመንደር ደረጃ በየቀኑ ህገ-ወጥ ግንባታና መሬት መስፋፋትን ተከታትሎ ሪፖርት

የሚያደረግ ኮማንድ ፖስት ከከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን እንዲደራጅ ያደረጋል፡

ሠ/ የኮማንድ ፖስት መረጃ በማደራጀት ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረበል፣ ያስወስናል፣

ረ/ ለህገ-ወጥ ግንባታና ለመሬት ወረራ የተጋለጡ አከባቢዎችን በመለየት በቋሚነት የሚጠበቅበትን

ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
በቀበሌ ደረጃ የሚቋቋም ግብረ-ኃይል ተግባርና
ኃላፊነት
ሀ/ በከተማ ደረጃ የተቋቋመው ግብረ-ኃይል የሚሰጧቸውን ተግባራት ያከናውናል፣
ለ/ ዕለት ተዕለት በቀበሌው ውስጥ የሚከሰት ህገ-ወጥ ግንባታን ይከታተላል፣ ህገ-
ወጥ ግንባታዎችን ያፈርሳል‹ አጥፊዎችን ለህግ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
ሐ/ በቀበሌና በመንደር ደረጃ በየዕለቱ ህገ-ወጥ ግንባታና መሬት መስፋፋትን
ከሚከታተለው ኮማንድ ፖስት ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣ የዕለት፣ የሳምንት
ሪፖርት ለማዘጋጃ ቤት ወይም ለከተማ አስተዳደር ያቀርባል፡፡
የክትትል፣ ድጋፍ እና ግብረ-መልስ ስርዓት

በዚህ ረገድ ህብረተሰቡ እና መንግስት ተገቢውን ሚናቸውን ለመወጣት የጋራ ዕቅድ የሚኖራቸው
ሆኖ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ከህዝቡ ጋር በታቀደ የግንኙነት ጊዜ እየተገናኙ
ስራው የደረሰበትን መገምገም ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአፈጻጸም ስልት

ይህ ተግባር ከፍተኛ በሆነ የህዝብ ግንኙነት ስራ ታጅቦ በልማት ሠራዊት ቅኝት በተደራጀና በተቀናጀ
የህብረተሰብ ውይይትና ተሳትፎ መከናወን ያለበት ተግባር ነው፡፡አግባብነት ያላቸው አካላት ሁሉ
ለዚህ ተግባር ተፈጻሚነት ይተባበራሉ፡፡
አመሰግናለሁ!
Thank you

በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ወሳኝ ነው!!

You might also like