Professional Documents
Culture Documents
Carrier Structure
Carrier Structure
ታህሳስ 2005 ዓ .ም
አዲስ አበባ
የመመሪያው ይዘት
•መግብያ
•የደረጃ እድገት አስፈላጊነት
•ትርጉም
•የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አሰልጣኞችና እንስትራክተሮች ፕሮፋይል
•የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ፕሮፋይል
•የተቋማት ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ምልመላና አመዳደብ
•የተቋማት ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ምልመላ መስፈርት
•የሥልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ምልመላና አመዳደብ
•የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ለደረጃ እድገት ለመወዳደር ሊያሟሉ
የሚገባቸው መስፈርቶች
•አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ለደረጃ እድገት ለመቅረብ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
•በየደረጃው የሚፈጸም የደረጃ እድገት ሥርዓት
•የዲኖችና ምክትል ዲኖች የደረጃ እድገት አፈፃጸም
•የአቤቱታ እና ቅሬታ አቀራራብ ህደት
•ልዩ ልዩ ሁኔታዎች
መግብያ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ አጠቃላይ አላማ በሀገሪቷ ብቃት፤ ተነሳሽነትና የፈጠራ
ክህሎት ያለው የሰው ሀይል በመፍጠር ድህነትን ማስወገድና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ
ማድረግ ነው፣፣ ይህም የሚተገበረው በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተና ከፍተኛ ጥራት
ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና
ተቋማት አዳድስና ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳትና ወደ እንዱስትሪው በማስተላለፍ እንዱስትሪውን
በተለይም የጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን
ማሳደግ እንዲችሉ በማድረግ ነው፣፣
04/22/2024 3
የቀጠለ ….
ከላይ የተጠቀሱትን ቁልፍ ተግባራት ለመፈፀም ወሳኙን ድርሻ የሚጫወቱት አሰልጣኞች መሆናቸው እሙን
ነው፣፣ በመሆኑም አሰልጣኞችና እንስትራክተሮች እንዲሁም ዲኖችና ምክትል ዲኖች ጥራትና ብቃት
ያለውን ሥልጠና በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እነዲወጡ ተገቢውን የማትጊያና
የጥቅማጥቅም እንዲሁም ተከታታይነት ያለው የደረጃ እድገት ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፣፣ በዚህ
መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠንቶ የፀደቀውን የደመወዝ ስኬል የአፈፃጸም መመሪያ የሲቪል ሰርቪስ
ሚኒስቴር በቁጥር ሲሰሚ/ጠ10/9/241 ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ለትምህርት ሚኒስቴር በጽሁፍ
ያሳወቀውን መነሻ በማድረግ ይህ የደረጃ እድገት አፈፃፀም መመሪያ ተዘገጅቷል፣፣
04/22/2024 4
የቀጠለ
•በመሆኑም አሰልጣኞችና እንስትራክተሮች እንዲሁም ዲኖችና ምክትል ዲኖች ሠልጣኞችን የማሰልጠን ብቃታቸውና
ያስመዘገቡት ተጨባጭ ውጤት በየጊዜው እየተገመገመ በጀማሪ አሰልጣኝነት፤ በረዳት አሰልጣኝነት፤በአሰልጣኝነት፤
በከፍተኛ አሰልጣኝነት፤ በጀማሪ ኢንስትራክተርነት፤ በረዳት ኢንስትራክተርነት፤ በኢንስትራክተርነት፤ በከፍተኛ
ኢንስትራክተርነት፤ በመሪ ኢንስትራክተርነት እና ዋና ኢንስትራክተርነት በተቀመጠው ደረጃ መመደብ እንዲችሉ የእድገት
መሰላሉ ተቀምጦላቸዋል፣፣ ይህ የእድገት መሰላል አስፈላጊውን ውጤት እንዲየስገኝ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተርነት የሥራ
ውጤታቸውን እየተገነዘቡ ሥልጠናውን በብቃት በመምራት ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ሠልጣኞችን በማፍራት የእድገት
መሰላሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ እንዲወጡ ለማድረግ የሚየስችል ተገቢው
የሥራ አፈፃጸም ግምገማ ሥርዓትም ተዘርግቷል፣፣
የቀጠለ
ይህ “ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ችድገት
እንዲሁም የዲኖችና ምክትል ዲኖች ምልመላና ምደባ አፈፃፀም መመሪያ ”ውጤት ተኮር ሥልጠና ሥርዓቱን በሚገባ
ወደ ተግባር በመለወጥ የስትራቴጂው ቁልፍ ግቦች መሳካት እንዲችሉ፤ በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ልማት ረገድ
ያለው ሥራ ወሳኝ በመሆኑ ይህ መመሪያ የተቋማት አሰልጣኞች ማትጊያ ሥርዓትን ለመተግበር እንዲያስችል ተደርጎ
በሀገር አቀፍ ደረጃ /ወጥ በሆነ መልኩ/ ተግባራዊ እንዲሆን ተዘገጅተዋል፣፣
የቀጠለ
1.2. ትርጉም
ዲን ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠ፤ የመንግስትን ፖሊስና ስትራቴጂ ለመተግበር ቁርጠኝነት
ያለው፤ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ካሉት የኤ ደረጃ ወይም የቢ ደረጃ
አሰልጣኞች መካካል በክልሉ ወይም ከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና
ኮሚሽን/ኤጀንሲ/ቢሮ ተወዳድሮ የሚመደብ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋምን
በበላይነት የሚመራ ኃላፊ ነው፡፡
ምክትል ዲን ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠና የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለመተግበር
ቁርጠኝነት ያለው ከቢ ደረጃ ወይም ከኤ ደረጃ አሰልጣኝ መካከል አብዛኛው ስልጠና ከሚሰጥባቸው
የሙያ ዘርፎች ተወዳድሮ የሚመደብ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የውጤት ተኮር
ስልጠና የሥራ ሂደትና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን የሥራ ሂደትን በበለቤትነት
የሚመራና በምክትል ዲንነት ደረጃ የሚመደብ ማለት ነው፣፣
04/22/2024 8
የቀጠለ
04/22/2024 9
የቀጠለ
04/22/2024 10
የቀጠለ
04/22/2024 11
1.3. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ፕሮፋይል
1.3.1. C-ደረጃ አሰልጣኝ
የዉጤት ተኮር ሥልጠና ሥርዓትንለመተግበር የሚያስችል በፌዴራል ወይም በክልል/ከተማ አስተዳደር ደረጃ
የተዘጋጀውን/የሚዘጋጀውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አመራር የወሰዱ/ለመውሰድ ዝግጁ የሆኑ
1.4.2. የምክትል ዲኖች ፕሮፋይል
04/22/2024 14
1.5. የተቋም ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ምልመላ እና አመዳደብ
04/22/2024 15
ከላይ የተቀመጠው የዲኖች እና ምክትል ዲኖች ፕሮፋይል እንደተጠበቀ ሆኖ ለምልመላ ዕጩ ሆነው የሚቀርቡት
ዲኖች ወይም ምክትል ዲኖች በተጨማሪ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አላባቸው፡፡
1.5.1. በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የተቋም ዲን ለመሆን የሚያስችል ብቃት ያላቸው፣ አመለካከታቸው የጠራና
የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለመተግበር ቁርጠኛ የሆኑ
1.5.2. ግንበር ቀደም አሰልጣኝ/ኢንስትራክተር በመሆን አርአያ ሆነው ሌሎች ግንበር ቀደም እንዲሆኑ ያደረጉ
1.5.4. በሚያሰለጥኑበት ሙያ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሠልጣኞች ድጋፍ በማድረግ የጎላ አስተዋፅኦ ያደረጉ
1.5.5. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም ያለበትን የክልል/የአከባቢውን የሥራ ቋንቋ የሚችሉ መሆን
አለባቸው፡፡
04/22/2024 16
1.6. የዲኖችና ምክትል ዲኖች ምልመላ መስፈርት
1.7.4. ፈተና/የፅሑፍ፣የቃል/35%
04/22/2024 19
1.9. አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ለደረጃ እድገት ለመቅረብ መሟላት ያለባቸው
መስፈርቶች
1.9. 1. የሲ ደረጃ አሰልጣኞች ለደረጃ እድገት ለመቅረብ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
ተ. የውድድር ደረጃ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
ቁ
በጀማሪ አሰልጣኝነት ቢያንስ 2 ዓመት ያገለገለ
04/22/2024 20
የቀጠለ
04/22/2024 24
የቀጠለ
04/22/2024 25
የቀጠለ
04/22/2024 27
የቀጠለ
የአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደሞዝ ደረጃ እድገት አሰጣጥ ሂደት ዓይነቶች እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
1.9.4.1. ከአንድ ደረጃ ወደሚቀጥለው የደረጃ ተዋረድ አምዳዊ እድገት/Vertical Career/ የሚሰጠው
ለየደረጃው በተቀመጡት የማቆያ ጊዜያትና በተገኙት የሥራ የግምገማ ውጤቶች ላይ ተመስርቶ የሚከናወን
ይሆናል፡፡
1.9.4.2. የጎናዊ የእርከን ደሞዝ ጭማሪ/Horizontal Career/ የሚሰጠው አጠቃላይ የመንግስት ሠራተኞች
እርከን ጭማሪ በሚለቀቅበት ጊዜ ይሆናል፡፡
1.9.4.2.1. ከጥር 1 እስከ ሰኔ 30 መካከል አዲስ ለሚቀጠሩ ወይም በደረጃ ዕድገት ሁለት እርከንና በላይ ያገኙ
ወይም በዲሲፕሊን ከደረጃ ዝቅ ያሉ አሰልጣኞች መደበኛ የደሞዝ ጭማሪ የሚያገኙት ከሐምሌ 1
ቀን ጀምሮ ነው፡፡
1.9.4.2. በሐምሌ 1 እና ታህሳስ 30 መካከል አዲስ የተቀጠሩ ወይም በደረጃ እድገት ከሁለት እርከንና ከዚያ
በላይ ያገኙ ወይም በዲሲፕሊን ከደረጃ ዝቅ ያሉ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች መደበኛ ጭማር
የሚያገኙበት ከጥር 1 ጀምሮ ይሆናል፡፡
04/22/2024 30
1.9.4.3. የትምህርት ማሻሻያ የደሞዝ ዕድገት ጭማሪ አሰጣጥ
የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ደመወዝ አከፋፈል በሀገር ውስጥ እውቅና ካላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከሀገር ውጪ ትምህርታቸውን አሻሽለው
ለሚመለሱ አሰልጣኞች ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
04/22/2024 31
1.10. በየደረጃው የሚፈፀም የደረጃ እድገት ሥርዓት
የአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት በተቋም የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ ተቋቁሞ ለደረጃ እድገት የሚቀርቡ
አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ውድድሩ በተቋም ደረጃ ከተከናወነ በኋላ ተግባራዊ የሚሆነው በተቋሙ ማኔጅመንት
ታይቶ ለተቋሙ ቦርድ ሲፀድቅ ነው፡፡
•በዘመኑ ለደረጃ እድገት የሚቀርቡ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ለደረጃ እድገቱ ከመቅራባቸው በፊት
ያከናወኗቸውን ተጨባጭ ተግባራት የሚገልፅ ዝርዝር መረጃ በየተቋሙ በሚመለከተው ምክትል ዲን አማካኝነት
ለኮሚቴው ይቀርባል፡፡
•ተቋሙ በየዘመኑ ለደረጃ እድገት ውድድር የሚቀርቡትን አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች በዝርዝራቸው ለይተው
በግልፅ ማስታወቂያ ያሳውቃል፡፡ በሥራ ምክንያት በአካባቢው የሌሉ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ቢኖሩ
ማረጃቸውን የተቋሙ የሰው ኃይል አስተዳደር ለኮሚቴው ይቀርባል፡፡
•ኮሚቴው ተገቢ ቃለጉባኤ በመያዝ ለደረጃ እድገቱ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟሉትን በየደረጀው የዕድገት መሰላል
መሠረት አጣርቶ ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለተቋሙ ማኔጅመንት ያስተላልፋል፡፡
•የተቋሙ ማኔጅመንት ከደረጃ እድገት ኮሚቴ የቀረበለትን ዝርዝር መረጃ ካጣራና ከገመገማ በኋላ ለተቋሙ ቦርድ
አቅርቦ ያፀድቃል፡፡
1.11. የዲኖች እና ምክትል ዲኖች የደረጃ እድገት አፈፃፀም
ዲኖች እና ምክትል ዲኖች በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት መሰላል በደረሱበት ደረጃ ላይ ደረጃው
የሚያስገኝላቸውን ደመወዝ ያገኛሉ፣ በሚያሰዩት ተጨባጭ ጥረትና ውጤት እንዲሁም በቆይታቸው ወቅት ለዓመቱ
የተቀመጠውን የሙያ ብቃት ምዘና ግብ አማካይ ያሟሉ በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት መሰላል
መሰረት ወደሚቀጥለው ደረጃ ያድጋሉ፡፡
1.11.1. የተቋም ምክትል ዲኖች እና ሥልጠና ዘርፍ አስተባባሪዎች የደረጃ እድገት አፈፃፀም
የተቋም ምክትል ዲኖችና ሥልጠና ዘርፍ አስተባባሪዎች የደረጃ እድገት ኮሚቴ አባል ሆነው ዕድገቱ የሚመለከታቸው
ከሆነ ከኮሚቴው አባልነት ወጥተው በሌሎች የኮሚቴው አባላት እድገታቸው እንዲታይ ይደረጋል፡፡
04/22/2024 34
1.12. የአቤቱታ እና ቅሬታ አቀራራብ ሂደት
በዚህም መሠረት፣
ቅር የተሰኙ አሰልጣኞችና ጉዳዩን ለቅርብ አለቃ ወይም ለሚመለከተው ኋላፊ በማቅረብ ውይይት
ኢንስትራክተሮች በተደረገበት ቀን ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻቸውን ለመስሪያ ቤቱ የቅሬታ
አጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
ከፍ ሲል በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የቅሬታውን ማመልከቻ ሊያቀርብ ያልቻለ
ከሆነ ከአቅም በላይ የሆነው ምክንያት በተወገደ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡
04/22/2024 35
ለ. ቅሬታ ማጣራት
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
የእያንዳንዱ የአሰልጣኝና ኢንስትራክተር የደረጃ እድገት የራሱ የቆይታ ጊዜ ያለው ስለሆነ አሰልጣኞች
/ኢንስትራክተሮች በደረሱበት ደረጃ የቆይታ ጊዜአቸውን ሳያሟሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው
ተለይተው ቆይተው ሲመለሱ መጀመሪያ ከሥራ ገበታቸው ከመሄዳቸው በፊት በነበሩበት ደረጃ ተመልሰው የቆይታ
ጊዜያቸውን ጠብቃውና ተገምግመው የደረጃ እድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች በጤና ችግር ምክንያት በማሰልጠን ሥራ ሊቀጥሉ ካልቻሉ ይኻው በሀኪም ቦርድ
ሲረጋገጥ የቴ/ሙ/ት/ሥ/ጽ/ቤት/ቢሮ/ኮሚሽን/ኤጀንሲ ቀርቦ በሌላ ሥራ መደብ ቦታ ካለ በቋሚነት ወይም
በጊዜያዊነት ተዘውረው እንዲሰሩ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላ የደረጃ እድገቱም የሚታይላቸው ከህመሙ
ተሽሎኣቸው ወደ አሰልጣኝነት ወይም ኢንስትራክተርነት የሥራ መደብ ተመልሰው ሲመደቡና ዕድገቱ የሚፈልጋውን
የቆይታ ጊዜ ሲያሟሉ የእድገቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
የቀጠለ
አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ከአንድ ደረጃ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለማደግ በሚያደርጉት ሂደት በመጀመሪያው
የእድገት ውድድር ከወደቁ በ2ኛ ጊዜ ለውድድር ለመቅረብ የተከታዩን አንድ አመት ሁለት የግምገማ ውጤት
በማካተት ባሉበት ደረጃ ለአንድ ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ ወደሚቀጥለው ደረጃ ካለፉ ለሚቀጥለው ደረጃ ዕድገት
የሚቀርቡት ዕድገቱን ካገኙበት ቀን ጀምሮ የመቆያ ጊዜ ጠብቆ ይሆናል፡፡
የቀጠለ
ይህም በአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት ሂደት ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊሰጥ የሚችል ዕድል ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ካሉት ደረጃዎች በአንዱ ላይ ብቻ የሚሰጥ ዕድል ሆኖ በሌለው ደረጃ ላይ በድጋሚ የዚህ አይነቱ ዕድል
ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የማቆያ ጊዜኣቸውን እየጠበቁ ለእድገት የሚቀርቡ
ይሆናል፡፡ ተወዳድረው ካላለፉ ባሉበት ደረጃ የተሰጣቸውን የቆይታ ጊዜ ጠብቀው ሊቀርቡ ይችላሉ ማለት ነው፡፡
ለዲኖችና ም/ዲኖች አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የሚሰጥ የደረጃ ዕድገት ለሥራ ረስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች
ባለሙያዎችን ለመሳብና ለማናቃቃት ከሚደረጉ የአበል ክፍያዎች እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጋር ግንኙነት
አይኖረውም፡፡
04/22/2024 39
የቀጠለ
በዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ የሚሰጡ ውሳኔዎች የመንግስት ሠራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃፀም ደንብን መሠረት
በማድረግ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
ለሙያ ብቃት ምዘና የተሰጠ ማስረጃ የሚያገለግለው የልህቀት ማዕከሉ ለወሰነው የቆይታ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
04/22/2024 40
የቀጠለ
የማህበረሰብ ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከላት በገበያ ፍላጎት ላይ በመመርኮዝ የደረጃ I እና II እንዲሁም አጫጭር
ሥልጠናዎችን በመስጠት በርካታ ስራ አጥ ዜጎችን አብቅቶ ወደ ስራ ለማሰማራት የሚያግዙ ማዕከላት ሆነው
በሲ- ደረጃ ከፍተኛ አሰልጣኝ የሚመሩ ይሆናሉ፡፡
ዲኖች እና ምክትል ዲኖች በየጊዜው የሚያስመዘግቡት የስራ አፈፃፀም ውጤት ከከፍተኛ ነጥብ በታች ሆኖ
ከተገኛ በኃላፊነት ሊቀጥሉ አይችሉም፡፡
ለደረጃ እድገት የሚቀርቡ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች አገልግሎት የሚያዘው በመንግስት ተቋም ውስጥ
በአሰልጣኝነት ያገለገሉበት ጊዜ ብቻ ታሳቢ ተደርጎ ይሆናል፡፡
በግል ተቋማት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ወይንም በቢሮ በመስራት የተገኛ የስራ ልምድ በተቋም ውስጥ
ለሚደረግ የደረጃ እድገት ውድድር አይያዝም፡፡ እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ከሥራ ቦታ የተለየበት ጊዜ ወይም
ለትምህርትና ሥልጠና ተብሎ ከ3 ወር በላይ የተሰጠ ፍቃድ ለደረጃ እድገት የቆይታ ጊዜ ታሳቢ አይሆንም፡፡
04/22/2024 41
04/22/2024 42