Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 57

እንን ደህና መጡ!

የተሻለ የልጅ አስተዳደግና


አያያዝ ዘዴ ሥልጠና
ለወላጆችና ተንከባካቢዎች
የተዘጋጀ
ሚያዝያ 2007
አርባ ምንጭ
• መግቢያ
ይህ የተሻለ የልጅ አስተዳደግና አያያዝ የማሰልጠኛ ሰነድ የተዘጋጀው የማህበረሰብ በጎ ፍቃድ
ተንከባካቢዎች/አሳዳጊዎች እና ወላጆችን ስለ ዘመናዊና የተሻለ የልጅ አስተዳደግና አያያዝ ለማሰልጠን
ታስቦ ነው ፡፡ እነዚህ የማህበረሰብ በጎ ፍቃድ ተንከባካቢዎች/አሳዳጊዎች እና ወላጆችሰራተኞች
በኮከብ ብርሃን ፕሮግራም ውስጥ የታቀፉትን በኤች፣አይ፣ቪ ኤድስና በሌሎች የተለያዩ ችግሮች የተነሳ
ወላጆቻቸውን አጥተው በከፍተኛ ደረጃ ለችግር የተጋለጡትን ህፃናት ተንከባካቢዎች/ወላጆች ስልጠና
በመስጠት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ይጠበቃል፡፡ በርካታ ህፃናት በደረሰባቸው አስቸጋሪ የህይወት
ልምድና ሁኔታዎች የተነሳ ለስሜታዊና ለባህሪያዊ ችግሮች ተጋላጭ ሆነዋል፡፡ የእነዚህ ህፃናት
ተንከባካቢዎች ህፃናቱን ለማሳደግ አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ ቢሆንም ኃላፊነታቸውን
በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት የተለያዩ ክፍተቶች/ችግሮች አሉባቸው፡፡ ይህውም የልጅ ልጆችን
በማሳደግ ሂደት በእድሜ የገፉ በመሆናቸው ምክንያት ባለመማርና ብቻቸውን ህፃናትን የማሳደግ
ኃላፊነት ይጠቀሳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ሥልጠና ለህፃናት ተንከባካቢዎች የተሻለ የልጆች አስተዳደግና
አያያዝ እውቀታቸውን፣ አመለካከታቸውንና ክህሎቶቻቸውን ለማሻሻል ይረዳቸዋል፡፡
ይህ ስልጠና እያንዳንዱ ሁለት ስዓት ተኩል የሚፈጅ አምስት ክፍሎችን ያካትል
• ክፍል አንድ፡- የልጅ አስተዳደግን መረዳት
• ክፍል ሁለት፡- ልጆችን በሚገባ መረዳት
• ክፍል ሶስት፡- የልጅ አስተዳደግና አያያዝ ክህሎቶች /ቁጥር አንድ/መወያየትና ስነስርዓት
ማስተማር(ገደብ ማበጀት)
• ክፍል አራት፡- የልጅ አስተዳደግና አያያዝ ክህሎቶች /ቁጥር ሁለት/ ልጆችን በስነ-ምግባር ማነፅና
ማስተካከል
• ክፍል አምስት፡- ለልጆች ጥሩ ምሳሌ/ አርአያ መሆን/
ከስልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች
 ተንከባካቢዎች ስለልጆች እንክብካቤ እና ባህሪ ያላቸውን አመለካከት
ማሻሻል
 ተንከባካቢዎች በልጆች አያያዝ ክህሎታቸው የራስ መተማመን
ስሜታቸው እንዲዳብር ማስቻል
 የሕፃናት ተንከባካቤዎችን ጫናና ጭንቀቶች መቀነስ
 በተንከባካቢዎችና በልጆች መካከል ያለውን ግንኙነት ማሻሻል
 የልጆችን ባህሪ ማሻሻል
 በልጆች ላይ የሚተገበረው አካል ቅጣትና ተገቢ ያልሆነ የስነ-ስርዓት
እርምጃ አወሳሰድን መቀነስ
 የልጆችን ሁለንተናዊ ደህንነት ማሻሻል ናቸው፡፡
ክፍል 1
የልጆች አስተዳደግን መረዳት
የልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ ማለት አንድን ልጅ ከህፃንነቱ ጀምሮ ወደ
አዋቂነት የእድሜ ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ መንከባከብ/ማሳደግ ፣ ልጆች ብቃት
ያላቸው ሆነው እንዲያድጉ ማገዝ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ሃላፊነት የሚጠይቅ ተግባር
ነው ፡፡
ለዚህም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች የሚከተሉት ሃላፊነቶች ይጠበቅባቸዋል፡፡
• የልጆችን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ፡፡ ለምሳሌ
• አካላዊ ፍላጎቶ፡ ምሳሌ፡-(ምግብ፣ ውሀ፣ ልብስ፣ መጠለያ ወዘተ)
• ስሜታዊ ፍላጎቶች፡ ምሳሌ፡- (መወደድን/ፍቅርን የማግኘት ፍላጎት ፣ ቤተሰብ
ውስጥ ማደግ ፣ የሚናገሩት እንዲደመጥ እና ስሜታቸውን እንድንረዳቸው መፈለግ ፣
ተቀባይነት ማግኘት ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር እንዲጫወቱ ፈቃድ ማግኘት
• ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ
• ልጆች ሲታመሙ ወደ ህክምና መውሰድ እና
ደህንነታቸውንም መከታተል፡፡
በተጨማሪም ጥሩ የልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ እንዲኖር የሚከተሉትን ሃላፊነቶች
መተግበር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
 ልጆችን በቅርበት ማወቅ እና መረዳት
 ተገቢውን ፍቅር እንክብካቤ፣ ድጋፍ እና ማበረታቻ መለገስ
 በመተማመን በመፈቃቀር በመከባበር ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት መፍጠር
 ልጆችን በአዎንታዊ መንገድ መልካም ስነ-ምግባር እንዲያዳብሩ ክትትል ማድረግ
 በልጆቹ የእድሜ መጠን ሊከበሩ የሚገባቸው ህጎች እና ደንቦች በማውጣት ከጥፋት
እና ከአደጋ እንዲጠበቁ ማድረግ
 የልጆቹን የእለት ተእለት አጠቃላይ እድገት እና ለውጥ መከታተል እና
 መልካም ምሳሌ መሆን አለባቸው
 አብዛኞቹ አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን በጣም የሚወዱ እና የተሻለውን
ነገር ሁሉ ልጆቻቸው እንዲያገኙ ይፈልጋሉ
 ግን ደግሞ እንደ አብዛኛው ሰው እነሱም ፍጹም አይደሉም
በልጅ አስተዳደግ ስርአታችን ላይ ተፅእኖ
የሚያሳድሩ ጉዳዮች
እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ ህገደንቦች አሉት። እነዚህም
ህገደንቦች ጥሩም መጥፎም ሊሆኑ ይችላሉ።
እነዚህንም አንዳንድ ግዜ ትክክል ያልሆኑ ግን ትክክል ናቸው ብለን ስለምናምን ተቀብለን
እንተገብራቸዋለን ለምላሌ፡-
 የሴት ልጅ ግርዛት
 ያለእድሜ ጋብቻ
 ልጆችን የቤት ውስጥ ስራተኛ ማድረግ
 ሴት እና ወንድ ልጆች በቤት ውስጥ በእኩል አይን አለማየት
 ወንድ ልጅን ትምህርት ቤት ልኮ ሴት ልጅን እቤት ማስቀረት
 የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳተኛ ልጆችን ከሌሎች ልጆች ጋር እኩል ያለማየት እና ያለማሳደግ
በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ እና በልጆች አስተዳደግ እና አያያዝ አዎንታዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ
ህገደንቦች በልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡
ለምሳሌ፡-
 የጎረቤትን ልጅ እንደራስ ልጅ አድርጎ መቆጣጠር፣ መምከር፣ ወላጆች ሲታመሙም ሆነ በሞት
ሲለዩ ጎረቤቶች ለታማሚዎችም ሆነ ለልጆቻቸው የሚሰጡት ድጋፍ
 የልጆችን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማማላት
 መከባበር
ጥሩ የልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ እንዲኖር የማህበረሰቡ አስተዋፅኦ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነው፡፡
 የማህበረሰቡ አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ ህጎች እና ደንቦች ማክበር እና መጠቀም
ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ማበረታታት
 ከማህበረሰቡ የወረስናቸው በልጅ አስተዳደግ እና አያያዝ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያላቸውን
ህገደንቦች አለመጠቀም እና እንዲወገዱ ከህብረተሰቡ ጋር ሆኖ ማስተማር
 ለማህበረሰቡ ለልጆች አስተዳደግ/አያያዝ ላይ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅእኖዎች ምንነት
ማስተማር እና ማስረዳት፡፡

ልጆች የወላጆች/አሳዳጊዎች እና የማህበረተሰቡ የአስተዳደግ ነፀብራቅ እና


ውጤት ናቸው፡፡
 የቤተሰቦቻችንን ወይም የማህበረሰባችንን ደንቦች መከተል መጥፎ
አይደለም፡፡
 ነገር ግን እነዚያ ደንቦች በልጆቻችን ላይ ጉዳት የማያደርሱ መሆናቸውን
ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
 ለወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በጣም አስፈላጊ ሊሆን የሚገባው ነገር
የልጆቻቸው ደህንነት መሆን አለበት፡፡
የልጅ አስተዳደግ አይነቶች/ዘይቤዎች
ቁጥጥር የበዛበት የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ
 ለልጆቻቸው ብዙ ህጎችን ያወጣሉ ልጆቻቸ
 እነዚያን ህጎች በማያከብሩ ጊዜ ይቀጣሉ
 ህጎችን ለምን እንዳወጡ እንኳን አይገልፁም ሲጠየቁም
“የምልህን ብቻ ፈፅም” የሚል ምላሽ የሚሰጡ ናቸው
 ለልጆቻቸው ስሜታዊ ፍላጎቶች የማይጨነቁ ወይም
ደንታ የሌላቸው ናቸው

ምክንያታዊ የሆነ የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ


 ጥቂት ህጎች አሏቸው
 ለልጆቻቸው ፍላጎቶች ትኩረት ይሰጣሉ
 የልጆቻቸውን ጥያቄዎች ለማዳመጥ ፈቃደኞች ናቸው
 ልጆቻቸውን ከመቅጣት ይልቅ ይቅርታን የሚያደርጉ እና
ፍቅርን የሚለግሱ ናቸው
ልቅ የሆነ የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ
 ለልጆቻቸው የሚያወጡት ምንም አይነት ህግ የላቸውም
 ከልጆቻቸው የሚፈልጉት ወይም ልጆቻቸው እንዲያደርጉ
የሚጠብቁት ነገር በጣም ጥቂት ነው
 ልጆቻቸው ጥፋት በሚያጠፉ ጊዜም ስርአት አያስይዙም
 ወላጆች/አሳዳጊዎች ሳይሆኑ የልጆቻቸው ጓደኞች ነው
የሚመስሉት

ለልጆቻቸው ትኩረት የማይሰጡ ወላጆች የሚከተሉት


የአስተዳደግ ዘይቤ
 በልጆቻቸው ደስተኞች አይደሉም
 ከልጆቻቸው እንዲያደርጉ የሚፈል¹ቸው ነገሮች እጅግ በጣም
ጥቂቶች ናቸው
 ለልጆቻቸው ፍላጎቶች ትኩረት አይሰጡም
 ከልጆቻቸው ጋር የሚያደርጉት የመወያየት ወይም የሀሳብን
የመለዋወጥ ሁኔታ በጣም ውስን ነው፡፡
 ልጆቻቸውን ከነጭራሹም ቸል ሊሏቸውም ይችላሉ
የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ በዚህ የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ ውስጥ የሚያድጉ ልጆች
- ታዛዦች
ቁጥጥር የበዛበት የልጅ አስተዳደግ - በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ
ዘይቤ - የማይደሰቱ እና የሚፈሩ ይሆናሉ
- ስለራሳቸው ያላቸው ግምት ዝቅተኛ ይሆናል
- ከሰዎች ጋር መግባባትን/መቀራረብን በተመለከተ
ችግር ያጋጥማቸዋል
- የሚያጋጥማቸውን የተስፋ መቁረጥ ስሜት
መቋቋም አይችሉም

ምክንያታዊ የሆነ የልጅ አስተዳደግ - ደህንነት ይሰማቸዋል


ዘይቤ - በራስ መተማመን ይኖራቸዋል
- ስሜቶቻቸውን መቆጣጠር የሚችሉ ይሆናሉ
- ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙ ነት መመስረት ይችላሉ
ልቅ የሆነ የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ - ስሜቶቻቸውን መቆጣጠር አይችሉም
- ብዙ ጊዜም አመፀኞች ይሆናሉ
- አድገው በሀላፊነት ቦታ ላይ በሚሆኑበት ጊዜም
ችግር ያጋጥማቸዋል
- በትምህርት ቤት ውስጥም ችግሮች
ሊያጋጥሙአቸው ይችላሉ
ለልጆቻቸው ትኩረት የማይሰጡ - ደስተኞች አይሆኑም
ወላጆች - ራሳቸውን ያለመቆጣጠር ችግር ይኖርባቸዋል
- በራሳቸው አይተማመኑም
- በትምህርት ቤታቸውም ውስጥ ችግር ያጋጥማቸዋል
 ወላጆች/አሳዳጊዎች የሚከተሏቸው የልጅ አስተዳደግ ዘይቤዎች በልጆች ስሜቶች እና
ባህሪያት ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡
ምክንያታዊ የሆነው የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ በጣም ጥሩ የልጅ አስተዳደግ ዘይቤ ነው
 ምክንያታዊ የሆነ የልጅ አስተዳደግ የሚከተሉ ወላጆች/አሳዳጊዎች ለልጆቻቸው ፍቅርና
እንክብካቤን መስጠት ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸው እንዲያከብሩላቸው የሚፈልጓቸው የተወሰኑ
ደንቦችም አሏቸው
የተለያዩ የልጆች ፀባይ/ባህሪ
ፀባይ/ባህሪ ማለት ልጆች በተለያዩ የእለት ከእለት መስተጋብራቸው ( ከቤተሰብ ፣ ከጓደኛቸው ፣በትምህርትቤት እና
በጠቅላላው ህብረተሰብ) የሚያሳዩአቸው ተፈጥሮአዊ ባህርያት ናቸው፡፡

የተለያዩ ልጆች ፀባይ በአምስት መሰረታዊ ክፍሎች ይከፈላል

ቅብጥብጥነት የሚታይባቸው ህፃናት


o የመረጋጋት ባህሪ ይጐላቸዋል
o በአንድ ጉዳይ ላይ በአትኩሮት መቆየት አይችሉም
o ነገሮችን በፍጥነት ይዘነጋሉ
o ለመወያየትና መግባባት የሚያስቸግሩ ናቸው

በጣም ፈጣንና ኃይለኝነት የሚታይባቸው ህፃናት


o በቀላሉ የሚከፉና የሚናደዱ
o የሚፈልጉትን ለማግኘት ሃይልና ጉልበትን የሚጠቀሙ
o አንዳንድ ተግባራትን በደመ-ነፍስ የሚከውኑ
o ችግር ፈጣሪ የሆነ ባህሪያትን የሚያሳዩ
ክፍል 2
ልጆችን መረዳት
ተቃራኒ/ተቃውሞ የሚያበዙ ህፃናት
o ተቃዋሚዎችና የበላይነት ማሳየት የሚፈልጉ
o ከሚጠበቅባቸው ተቃራኒ የሆኑ ባህሪያትን የሚያሳዩ
o የሚያስደስታቸውን ነገር ማወቅ የሚያስቸግር

ስሜታዊነት የሚታይባቸው ህፃናት


o ፈሪና ድንጉጥ የሚሆኑ
o ስሜቶቻቸውን በከፍተኛ ደረጃ የሚገልጹ
o አይናፋር የሆኑና ከሌሎች ጋር ያላቸውን መስተጋብር ዝቅተኛ የሆነ
o በሁኔታዎች መለዋወጥ (ለምሳሌ ት/ቤት ሲቀሩ) የሚከፉ

ብቸኝነት የሚያጠቃቸው ወይም በራሳቸው ዋሻ የሚኖሩ


o ዝምተኝነት የሚያበዙ
o ከአካባቢያቸው ከመግባባት ይልቅ በምናብ ዓለም መሆንን የሚመርጡ
o በቀላሉ የመሰልቸትና የመድከም ስሜት የሚታይባቸው
o በአዳዲስና ለየት ባሉ ገጠመኞች የማይማረኩ
ቅብጥብጥነት
የሚታይባቸው የአስተዳደግ ዘዴ
· የህፃናት ቅብጥብጥነት ባህሪ ላይ ብዙ አትኩሮት አለመስጠት
· ስለሚያሳዩዋቸው ባህሪዎች እንዲያስተውሉ መምከር
· ህፃናቱ አንድን ተግባር በአንድ ጊዜ ብቻ እንዲያከናውኑ ማገዝ
ፈጣንና ኃይለኛነት የአስ ተ ዳደግ ዘ ዴ
የሚታይባቸው ህፃናት  ትዕግስተኛ መሆን
 ፍቅር ፣ ወዳጅነትና እንክብካቤ ማሳየት
 ሃሣቡን በቃላት እንዲገልጽ ማበረታታት
 ህፃኑ ስለሚያሳያቸው ባህሪዎች እንዲያስብና ራሱን እንዲቆጣጠር መርዳት

ተቃራኒ /ተቃውሞ የሚያበ


የአስተዳደግ ዘዴ
 አይናደዱ መናደድዎ የልጅዎን ተቃውሞ ያባብሰዋል
 ደግና የተረጋጋ ልብ ይዘው የልጁን ችግር ለመረዳት ይሞክሩ
 ህፃኑ ደረጃ በደረጃ እንዲለወጥና ግትርነቱን እንዲያስወግድ ይርዱት

ስሜታዊነት የሚታይባቸው የአስተዳደግ ዘዴ


ህፃናት ሁሌም ልጅዎን ለመረዳት ይሞክሩ
· የተረጋጋ ግን ጽኑ አቋም ያሳዩት
· አዳዲስ ገጠመኞችን እንዲፈትሽ ያግዙት

ብቸኝነት የሚያጠቃው ህፃን የአስተዳደግ ዘዴ


· ንቁ ለመሆንና በአቋምዎ ለመጽናት ይሞክሩ
· የህፃኑን አትኩሮት ለማግኘት ጥረት ያድርጉ
በህፃናት ፀባዮች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮች
1.1 የዘር ውርስ፡- ወላጆች በዘር ለልጆች የሚያወርሷቸው
1.2 አካባቢ፡- ህፃናቱ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው አካባቢዎች ቤት፣ ት/ቤት፣ ጐረቤቶች ወዘተ…
 ህፃናቱ ከእነዚህ ቦታዎች የሚያገኟቸው ልምዶች ሰብዕናቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ
 ህፃናት ከቤተሰብ የሚያገኟቸው ልምዶች በሰብዕናቸው ላይ በእጅጉ ተፅዕኖዎች ያሳድሩባቸዋል
ምክንያቱም፡-
o ብዙ ጊዜያቸውን ከቤተሰብ ጋር ስለሚያሳልፉ
o ለእነርሱ እንክብካቤ የሚያደርጉ ግለሰቦች ተፅዕኖ ስለሚያሳድሩባቸው
o መልካም ያልሆኑ ባህሪዎች በሚያሳይ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ህፃናት ደስተኝነት ርቋቸው የተከፉ
አልያም ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ስለሚያድርባቸው
o ቁጣና ረብሻ/ፀብ እየተመለከቱ የሚያድጉ ህፃናት ፈሪ ወይም የኃይለኝነት ፀባይ ስለሚያዳብሩ
1.3 የውልደት ቅደም ተከተል፡- አንድ ህፃን ታላቅ ወይም ታናሽ በመሆኑ ምክንያት ወላጆች የሚያደርጉት
እንክብካቤ
1.4 ስርዓተ ፆታ፡- አንድ ህፃን ወንድ ወይም ሴት በመሆ“†¨ ምክንያት እንዲያሳዩ የሚጠበቅባቸው
ባህሪያት ለምሳሌ፡-
o ሴት ልጅ ዝምተኛ መሆን አለባት
o ሴት ልጅ የተነገራትን መፈፀም አለባት
o ወንድ ልጅ አያለቅስም
o ወንድ ልጅ ጠንካራ መሆን አለበት
1.5 ዕድሜ፡- ህፃናት እንደ ዕድሜ ደረጃቸው ባህሪያቸው የተለያየ ነው፡፡ ነገር ግን እያደጉ ሲመጡ
ባህሪዎቻቸውና ሰብዕናቸው እየተለወጡ ይመጣሉ፡፡
ወላጆች/አሳዳጊዎች የተለያየ ፀባይ ወይም ባህሪ ላላቸው ልጆች የተለያየ ዘዴ በመጠቀም በተገቢው
መንገድ ለማሳደግ የሚደረጉ እንክብካቤዎች
 ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጆችን ፀባይ ወይም ባህሪ ለመረዳት እና አስፈላጊውን እንክብካቤ ለማድረግ ግዜ
መስጠት አለባቸው
ልጆች ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ፀባይ ብቻ ሳይሆን ሊቀየሩ ይችላሉና መቀበል እና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት
እያደጉ ሲሄዱ ሲለወጡ የተወሰኑ ባህሪያት ግን ልጆች እያደጉም ቢሄዱ መሰረታዊ ለውጥ ሊያሳዩ አይችሉም
በዚህም የስብእናቸው መግለጫ ሆኖ ይቀጥላል ለዚህም መቀበል እና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል፤
ጥሩ የሆኑ የልጆቸ ባህሪያት እንዲጠናከሩና አንዳንድ አስቸጋሪ ባህሪያቶችን ግን የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር
በማድረግ ለማስተካከል መሞከር ያስፈልጋል።
ህፃናት ከዕድገት ደረጃቸው አንፃር የሚያሳዩት ባህሪና የማያስፈልጓቸው ድጋፎች
ዕድገት ፍላጐቶች ባህሪያት ምን መደረግ አለበት

ጨቅላ/አራስ • ምግብ ከ 0-6 ወር ያሉት ማቀፍ ለልጅዎ የአእምሮ እድገት በጣም


(0-1 ዓመት) • እንቅልፍ • ማልቀስ አስፈላጊ ነው
• ንፅህና • ፈገግ ማለት፣ ድምጽ አቅፎ ልጆችን እሹሹ ማለት ለልጆች
• ምቾት መስጠት በማውጣት አእምሮ እንደ ምግብ ነው በአእምሮ
ህዋሶች መካከል ያለውን ግኑኝነትን ይገነባል
(መታቀፍ፣ መነካካት፣ • የአሳዳጊን ትኩረት ለመሳብ በዚህ ደረጃ ላይ ላሉ ልጆችዎ ማድረግ
ማባበል)፣ ጥረት ያደርጋሉ ያለብዎ
• ከወላጆች ወይም ከ 6 ወራት - 2 ዓመት ልጅዎ ምን እንደፈለገ ለማወቅ ይሞክሩና
ከተንከባካቢዎች ጋር • ፍርሃት ሲሰማቸው መልስ ይስጡ
ቅርበት በተንከባካቢያቸ ውስጥ ልጅዎ ምን እንደፈለገ ለማወቅ ይሞክሩና
ድብቅ ማለት መልስ ይስጡ ለምሌ፤- መታቀፍ ከፈለገ
• አሳዳጊዎቻቸው ሲለዩዋቸው ማቀፍ፤ንፅህና ከፈለገ ማፀዳዳት፤ እረቦት
መነጫነጭና መረበሽ ከሆነ ማብላት
ልጅዎ እንዲተማመንብዎ ያድርጉ ልጀዎ
• ሲችሉ ተንካባቢያቸ ሁሌም በአጠገቡ መሆንዎን ማወቅ
ተከትሎ መሄድ ይፈልጋል፡፡
ዕድገት ፍላጐቶች ባህሪያት ምን መደረግ አለበት

የሚውተረተሩ • ነፃ ሆኖ አካባቢን ነገሮችን ለማወቅ ጉጉ መሆን ስለ አዲስ ነገሮች ማወቅ የልጅዎ የማወቅ ጉዞ አንዱ
(1-3 ዓመት) መቃኘት የተለያዩ ነገሮችን ክፍል ነው፡፡ ስለዚህች ዓለምም አስደናቂነት
• ብዙ ቃላትን ማዳበር ለማወቅ/ለመስማት ወዘተ የሚማረው በዚህ መንገድ ነው፡፡፡ ሁሉም ልጆች
• አዳዲስ ነገሮችን ጉጉት ያድርባቸዋል መንካት መቅመስና ተመራመሮ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡
ለመከወን መሞከር፣ • ፍላጐቶች ባለመሟላታቸው ይህም ለአእምሮአቸው ዕድገት በጣም አስፈላጊ
መልበስና ማውለቅ ምክንያት አምርሮ ማልቀስ ነው፡፡
እናም ዕድሉን መጮህና ያገኙትን ነገር
ለማግኘት መሞከር መምታት/መወርወር የሚውተረተረው ልጅዎ ደህንነት በተሞላው መንገድ
• ስሜታቸዉን መመራመር ከቻለ በቶሎ ብዙ ነገሮችን ለማወቅ
መቆጣጠር ይማራሉ ይችላል የእሱ ዓለምም ደህንነት ያላት እንደሆነች
ይማራል በዚህ ደረጃ ላይ የእርስዎ ኃላፊነት የልጅዎን
የማደግ ነፃነት መኮትኮትና ማሳደግ ነው፡፡
ለነፃነት ያለውን ፍላጎት እንደሚያከብሩለት ለመማር
ያለውንም ጠንካራ ፍላጎት እንደሚደግፉለት ማወቅ
ስለሚፈልግ ይህን ያድርጉ
በዚህ ደረጃ ላይ የእርስዎ
ኃላፊነት የልጅዎን የማደግ ነፃነት መኮትኮትና
ማሳደግ ነው፡፡
ለነፃነት ያለውን ፍላጎት እንደሚያከብሩለት ለመማር
ያለውንም ጠንካራ ፍላጎት እንደሚደግፉለት ማወቅ
ስለሚፈልግ ይህን ያድርጉ ፡፡
ዕድገት ፍላጐቶች ባህሪያት ምን መደረግ አለበት

•ነገሮችን ተመራምሮ • በምናብና በእውነተኛ ዓለም  የልጆችን የማወቅ ጉጉትን ካከበርን የመማርን ደስታ
እንቦቃቅላ ማወቅና በተግባር መካከል ያለውን ልዩነት ይለማመዳሉ ይህ ስሜትም ት/ቤት በሚገቡበት ጊዜ
መማር የመረዳት ችግር አብሮዋቸው ይቆያል
(3-6 ዓመት) • መተባበርን መማር • ስሜቶቻቸውን በትወና መልክ የልጆቻውን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚሞክሩና
መግለጽ መልሶቹን እንዲያገኙ የሚያግዙዋቸው ወላጆች
• ብዙ ንግግር ማብዛት ልጆቻቸውን ብዙ ነገር እያስተማሩዋቸው ነው፡፡
• ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ሁሉንም ነገር ላያውቁ ይችላሉ ዋናው ነገር ሐሳባቸው
• በእጃቸው ያለ ነገር ማጣትና ነው
ማጋራት አለመፈለግ መልሶችን መፈለግና ለችግሮች መፍትሄዎችን መስጠት
• እንዲሁም ወረፋ/ተራ እንዲቻል በርካታ መረጃ መፈለጊያ መንገዶች አሉ
መጠበቅን አለመፈለግ እነዚህም በራሳቸው የሚያዝናኑ ናቸው
እነዚህን ነገሮች የሚማሩ ልጆች ችግሮች
በሚያጋጥሙዋቸው ጊዜ ከሌሎች የበለጠ በራሳቸው
የሚተማመኑ ይሆናሉ
ትዕግሥትን ይማራሉ በተጨማሪም ለመማር መፈለግ
ጥሩ ነገር መሆኑን ይማራሉ፡፡
ልጆች የህይወት ጉዞዋቸውን እችላለሁ ብለው ከጀመሩ
በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙዋቸውን ችግሮች
ለመፍታት የሚችሉ ይሆናሉ
ስለዚህም በዚህ ደረጃ ላይ ላሉ ልጆች ማድረግ ያለብዎት
የማወቅ ጉጉታቸውን ያክብሩላቸው
ለልጆችዎ ጥያቄዎች መልሶች ይፈልጉላቸው
ወይም መልሶችን በመፈለግ ያግዙዋቸው
ዕድገት ፍላጐቶች ባህሪያት ምን መደረግ አለበት
ታዳጊ • ነፃነትን • በጣም ንቁ መሆን ከ15- በዚህ ደረጃ ላይ ላሉ ልጆቻችሁ አብራችኋቸው ጊዜ
(7-11 በእጅጉ 20 አሳልፉ
ዓመት) መሻት ደቂቃ በላይ አንድ ቦታ እንደ ቤተሰብ ሆናችሁ ስሩ
መቀመጥ አለመቻል ስለ ጓደኞቻቸው አዋሯዋቸው
• የአውቃለሁ ዓይነት ጭንቀቶቻቸውንና ፍርሃቶቻቸውን አዳምጡ
ባህሪያትን ማሳየት እና ውጤቶቻውን አድንቁላቸው
ለወላጆች መልስ መስጠት በኑሮ ውስጥ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት ችግሮች
• ብስጭትና ቁጣን ንገሩዋቸውና በእነዚያ ወቅትም ለማገዝ አብራችኋቸው
ለመቆጣጠር እንደምትሆኑ አሳውቁዋቸው
መቻል ታማኝ ሁኑላቸው
• ስለ ራሳቸው ማወቅ ፍቅር አሳዩዋቸው
• ስሜታቸው በቀላሉ የሚነካ በራስ መተማመናቸውን ገንቡላቸው
መሆን ማንነታቸውን ፈልገው እንዲያገኙና በማንነታቸው
• ስሜታቸው በፍጥነት እንዲኮሩ አግዙዋቸው
የሚለዋወጥ መሆን በራሳቸው ችሎታ እንዲተማመኑ አበረታቱዋቸው
• የበላይነት ለማሳየት በት/ቤት ጉዳዮች ውስጥ ይካፈሉ/ይሳተፉ
መሞከር አንድ ነገር በት/ቤት የተለያ ክንውኖች ላይ ይገኙ
በማጣታቸው ምክንያት አስተማሪቻቸውን ይወቁ
ደስተኝነትን ስለ ቤት ሥራዎቻቸው ጠየቁዋቸውና አግዟቸው
• ማጣት በሚያነቡት ነገር ላይ ፍላጎት አሳድሩና አወያዩዋቸው
ቅርብ ሁኗቸው ነገር ግን ርቀታችሁን ጠብቁ
ዕድገት ፍላጐቶች ባህሪያት ምን መደረግ አለበት
ጉርምስና/ • ነፃ መሆንን • ከወላጆች ጋር ከመሆን ይልቅ  በዚህ ጊዜ ልጆችዎ ወደ አዋቂነት እየተጠጉ
አፍላነት • ከአቻዎቻው ጋር ከአቻዎቻቸው ጋር ለመሆን ያሉ ስለ ማንኛውም ነገር ከእርሰዎ ጋ ሊወያዩ
(12-18 መሆን መሻት የሚችሉ ናቸው፡፡
ዓመት) • በራስ • ለፆታዊ ግንኙት ፍላጎት መኖር
ለመተማመን • ምናልባት አደገኛ/ጐጂ ባህሪያት  በዚሀ ደረጃ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች
በአቻዎቻቸው ውስጥ መግባት ሊያደርጉዋቸው የሚገቡ ነገሮች
ተቀባይነትን • ተደጋጋሚ የሆነ የስሜት
ማግኘት መለዋወጥ  ከልጆቻው ጋ ያለውን ግኑኝነት ማጠናከር
• የራሳቸውን • ተቃውሞና እልኸኝነትን ማሳየት  ልጆች የሚፈጽሙዋቸውን ተግባራት
ማንነት መቅረፅ • የራሳቸውን ምርጫና ውሳኔ መከታተል
• ስለ ተቃራኒ ፆታ ለመስጠት መሞከር  የልጆቻቸውን የነፃነት ስሜት በአዎንታዊ
ግንኙነት መማር • ፈታኝና ሃይለኝነትን ማሳየት መልክ እንዲጠቀሙበት መርዳት
• የቤት ውስጥ ሥራዎችን
መስራት አለመፈለግ
• ከቤት ውጪ ያሉ ግለሰቦችን
እንደ አጋዥና አርአያ አድርገው
መውሰድ
ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት
የአካልም ሆነ የአእምሮ ችግር ያለባቸው ልጆች በማህበረሰባዊ ህይወት ውስጥ በሙሉ
ለማሳተፍ በይበልጥ ይቸገራሉ ለምሳሌ
• የአካላዊ እገዳዎች፡- መራመድ ወይም ደረጃ መውጣት የሚሳናቸው ልጆች
• የአስተሳሰብ እገዳዎች፡- የተለያዩ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮአዊ ችግር ያለባቸውን
ልጆች ያለመረዳት፣ ክብር እና ተቀባይነትን አለማሳየት
• የውይይት/የሃሳብ ልውውጥ እገዳዎች፡- የአካልም ሆነ የአእምሮ ጉዳት ያለባቸው
ልጆች የሚፈልጉትን ሃሳብ መግለፅ ስለሚዳግተቸው፣ በቤት ፣ በትምህርት ቤት እና
በህብረተሰብ ውስጥ ችግር ይፈጥርባቸዋል፡:

የአእምሮ እንዲሁም የአካል ጉዳት ያለባቸውን ልጆ በህብረተሰብ ውስት ተሳታፊነት


እንዲኖራቸው እና የመካተት ስሜት እንዲሰማቸው የሚከተሉት ሁኔታዎች
ያስፈልጋሉ
• በጥንካሬ እና በጉብዝናቸው ላይ ማተኮር
• በአካል/በአምሮ ጉዳተኝነታቸው ምክንያት አለመገመት
• የሚፈልጉትን ነገር እራሳቸው እንዲናገሩ እንዲያደርጉ መገፋፋት
• የተለዩ ሰዎች/ልጆች አድረገን አለማየት እና ከሌሎች ልጆች/ ሰዎች ጋር እኩል
ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት
ህፃናት እያደጉ ሲሄዱ በአራት የተለያዩ አቅጣጫዎች ለውጦች እንደሚያሳዩ
አካላዊ ዕድገት፡ የሚያመለክተው
• የሰውነት ቁመትና ክብደት/ይዘት
• አካላዊ ቅልጥፍና ጥንካሬ ቅንጅት (ራስን መቆጣጠር መታጠፍ)

አዕምሮአዊ ዕድገት የሚያመለክተው


• የአስተሳሰብ
• ምክንያታዊነት
• ሃሣብን የማቀናጀት
• ማጥናት/ነገሮችን በአዕምሮ ማስቀመጥ
• ቋንቋ መጠቀም
• ችግሮችን መፍታት

ማህበራዊ/መስተጋብር፡-
• ከሌሎች ህፃናት ጋር የመግባባት መጫወት
• የጨዋታ ቁሳቁሶችን መጋራት. ወዘተ
• ከአዋቂዎች ጋር መግባባት

የስሜት/ስነልቦና ዕድገት፡-
• ከዕድሜያቸው አንፃር የሚጠበቁ ስሜቶችን ማሳየት
• ከሁኔታዎች አንፃር የሚጠበቁ ስሜቶችን ማሳየት
ህፃናት እያደጉ ሲሄዱ እንደሚያሳዩት ባህሪ ፍላጐቶቻቸውም ይለዋወጣሉ
• የተለያዩ ባህሪያት በማሳየትም ፍላጐቶቻውን ይገልፃሉ
• ተንከባካቢዎች ህፃናት በየደረጃ የሚያሣዩትን ባህሪዎች መረዳት አለባቸው
ይህም አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ያስችላቸዋል
ክፍል 3
ከልጆች ጋር መወያየትና ስነ-ሰርዓት ማስተማር
በጥሞና የማዳመጥ ክህሎት

በጥሞና ማዳመጥ
• ልጅ በሚናገርበት ወቅት በጥሞና ማዳመጥ፡፡
• ስራ ላይ ከሆንን ስራችንን ማቆም፡፡
• በስራ ተወጥረን ከሆነ “አሁን ስራ ላይ ነኝ በሁዋላ መነጋገር እንችላለን?” በማለት
እሺታውን መጠየቅ
• አመቺ ጊዜ ፈልጎ ልጁን ማነጋገር
አይን ለአይን መተያየት
• በአይን መተያየት መግባባትን ያሻሽላል
• በልጅ እና በወላጅ መካከል ያለውን ርቀት ይቀንሳል
• በልጁ ቁመት ወረድ በማለት ወይም ወለል ላይ በመቀመጥ
ዐይን ለዐይን ለመተያየት ይረዳል
ልጆች እንዲናገሩ ዕድል መስጠት
• ልጅ በሚናገር ጊዜ ያለማቁዋረጥ
• ተናግሮ ሲጨርስ ማመስገን
የልጆችን ንግግር በፍላጎት መከታተል
• የልጅትዋ ወይም የልጁ ሃሳብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ማሳየት
• ልጆቹን “እውነት?” “እስኪ በደንብ ንገረኝ” “በጣም ደስ ይላል” በማለት
ማበረታት
• አሳዳጊዎች ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት መፍጠር አለባቸው፡፡
• ጥሩ ግንኙነት መፍጠር የሚቻለዉ ጥሩ በሆነ መግባባት ብቻ ነው፡፡.
• ጥሩ ግንኙነት ደግሞ ጥሩ የማዳመጥ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡
ከልጆች ጋር መነጋገር
ልጁ/ትዋ በትክክል እያዳመጠች መሆኑን ማረጋገጥ:
• የልጁን ስም መጥራት፡፡
• ንግግር ከመጀመራችን በፊት ጥሩ የሆነ የአይን ለአይን
ግንኙነት መኖሩን ማረጋገጥ፡፡
 ወደአይን ጠርዝ በማየት
• በእኛና በልጁ መሃል ያለውን ርቀት መቀነስ፡
• አይን ለአይን መተያየት.
• አስፈላጊ ከሆነ ወለል ላይ ቁጭ ወይም በርከክ ማለት
 ከልጆዎ ጋር ይነጋሩ እንጂ ልጆን አይናገሩ
• ከልጅ ጋር መነጋገር የሁለት ወገን ንግግር ነው፡
• አሳዳጊው/ዋ እና ልጁ/ጅትዋ ሁለቱም መናገር እና
መደማመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
• ልጅን መናገር ማለት የሁለት ወገን ምልልስ ማለት
ሳይሆን የአንድ ወገን(የወላጅ) ብቻ ንግግር ማለት
ነው፡፡
በትህትና መናገር
• ፍቅርንና አክብሮትን በሚገልጹ ቃላት ማናገር
• አሳፋሪና ልጁን/ጅትዋን የሚያሳፍሩ/ የሚያሸማቅቁ
ቃላቶችን ያለመጠቀም
ትእዛዛትን ቀለል ማድረግ፡
• በአንድ ጊዜ አንድን ስራ ብቻ ማዘዝ
• ህጻናት በአንድ ጊዜ ብዙ ትእዛዛትን መቀበልና መፈጸም ይቸገራሉ፡፡

 የድምጻችን ቃና ከመልእክታችን ጋር የተመሳሰለ እንዲሆን ማድረግ


• አንድን ነገር እንዲፈጽሙ ለማዘዝ የድምጻችን ቃና ጠንከር ያለ መሆን
አለበት፡፡
• ጠንከር ያለ ካልሆነ ለልጆቹ የሚሰጠው ትርጉም ትእዛዙ አስፈላጊ
አይደለም የሚል ነው፡፡

 አታድጉ ከማለት የሚያደርጉትን በአዎንታዊ መንገድ ማዘዝ


• ለምሳሌ “በሩን አትስበረው” ከማለት “በሩን ቀስ ብለህ ዝጋው” ብንለው
የተሻለ ይሆናል፡፡

 ልጃችንን መረዳት
• ብዙ ንግግርን ማሰወገድ
• “ተረድቼሃለሁ” “ስሜትህን አውቃለሁ” የሚሉ ቃላቶችን መጠቀም
• ቤተሰቤ ተረድቶኛል ብሎ የሚያስብ ልጅ ከወላጁ/ ካሳዳጊው ጋር
ያለው መግባባት የተሻለ ነው፡፡
• ተንከባካቢዎች / አሳዳጊዎች ከልጆቻቸው ያላቸውን ጥሩ ግንኙነት
ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ አለባቸው
• ይህንን ጥሩ ግንኙነት መፍጠር የሚቻለው
• በጥሩ መግባባት ብቻ ነው
• ጥሩ ተግባቦት ደግሞ ጥሩ አድማጭነትንና አዎንታዊ ንግግርን ይጠይቃል
ለልጆቻችን ገደብ ማበጀት

ከልጆች ባህሪ አንፃር ገደብ ማለት አንድ መጥፎ ባህሪ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የሚያሳይ
ህግ ነው፡፤ ከልጆች ባህሪ ጋር በተያያዘ ገደብ ማበጀት እና በተግባር ላይ ማዋል ልጆች መልካም ባህሪን
እንዲይዙ በአውንታዊ እና ጥሩ በሆነ መንገድ የሚመራ ነው፡፤
ገደቦች ስኬታማ እንዲሆኑ የሚከተሉትን ነጥቦች መረዳት ያስፈልጋል
 ገደቦችን መገደብ ያስፈልጋል
o የገደቦችመብዛት ቁጥጥር ወደበዛበት የልጁ አስተዳደግ ዘይቤ ይመራል
o የገደቦች መብዛት ልጆችን በራሳቸው እንዳይማሩ ያደርጋል
o ገደቦች በምናወጣበት ጊዜ አስፈላጊ የሆኑት ገደቦች ላይ ብቻ ትኩረት መስጠት
ገደቦች ሁልጊዜ ምክንያታዊ መሆን አለባቸው
• የምናወጣቸው ገደቦች ልጆቹ የሚተገብሩዋቸው ሊሆኑ ይገባል
• የምናወጣቸው ገደቦች የልጆቻችንን እድሜና ችሎታ ያገናዘበ መሆን አለበት

 ገደቦች ግልጽ መሆን አለባቸው


• የምናወጣቸውን ገደቦች ልጆቹ ሊረዱት ይገባል
• የሚያከብሩዋቸው ገደቦች ለምን እንደሚጠቅሙዋቸው ማሰረዳት ያስፈልጋል
• ልጆች በይበልጥ የተረዱትን ህግ ማክበር ይወዳሉ
ገደቦች ቀጣይነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል
• የምናወጣቸው ገደቦች በየቀኑ የሚለዋወጡ መሆን የለባቸውም ይህንን ለማድረግ ልጆችን ግራ ማጋባት
ይሆናል
• በቤት ውስጥ የሚገኙ ተንከባካዎች ከአንድ በላይ ከሆኑ ሁሉም የሚስማሙባቸውን ገደቦች ማውጣት
አስፈላጊ ነው ይህ ደግሞ ለልጆች የተቀላቀለ መልእክት ማስተላለፍን ይቀርፋል
 ገደቦች በአዎንታዊ መንገድ ሊነገሩ ይገባል
• የማያደርጉትን ከመንገር የሚያደርጉትን መንገር ያስፈልጋል ለምሳሌ “ወንበሩ ላይ አትንጠልጠል”
ከማለት ኪስህ ውስጥ አድርግ ማለት

 የገደቦችን መጣስ ተከትለው የሚመጡ ቅጣቶችን ማሰቀመጥ


• ገደቦችን በመጣስ ስለሚከተሉ ቅጣቶቹ ማሰብ.
• ቅጣቶቹ
o አግባብ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል
o ልጁ በሚያሳየው ያልተፈለገ ባህሪ መጠን ሊወሰኑ ይገባል
o የልጁን እድሜ ያገናዘበ ሊሆን ይገባል
o አካላዊ ቅጣትን የሚያስከትል መሆን የለበትም

 የልጆችን አመለካከት /አስተያየት መቀበል


• አንዳንድ ጊዜ ልጆች ገደብ ማስቀመጥ ላይ ጥሩ ሃሳብ ሊያመጡ ይችላሉ
• ልጆች በገደብ ማውጣት ስራ ላይ በሚሳተፉበት ጊዜ ላወጡት ገደብ ተገዢ ይሆናሉ
• በገደቦቹ ላይ አንዳንዴ አሳዳጊው/ወላጆች ከልጆች ጋር መስማማት ላይጠበቅባቸው ይችላል.
የእድገት ደረጃ ገደብ

ጨቅላ (0-1) •ንፁህ ከሆኑ፤ካራባቸው፤እንዲሁም ካላመማቸው እቀፉኝ ብለው ሲያስቸግሩ


አለማቀፍ
•ጡት በሚጠቡበት ወቅት ለመንከስ ሲሞክሩ ማስቆም
የሚውተረተር (1-3) • በትክክለኛ መንገድ መፀዳዳት(ፖፖ መጠቀም፣እጅ መታጠብ

እንቦቃቅላ (3-6) • መጫቻዎችን በጥሩ መንገድ መያዝ ያለመስበር አለማበላሸት


• የምሳ እቃቸውን በአግባቡ መያዝ(አለመጣል)
•የጓደኞቸቸውን መጫወቻ አለመቀማት

ታዳጊ(7-11) •የግል ንፅህናቸውን መጠበቅ


• ትንንሽ የቤት ውስጥ ስራ መስራት
•ጥናት ማጥናት

ጉርምስና/አፍላነት • በጊዜ መግባት


(12-18) •ጓደኞችን ለቤተሰብ ማስተዋወቀቅ
•የግል ንፅህናቸውን መጠበቅ
• የቤት ውስጥ ስራ መስራት
ልጆች ምግብ እና መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ የስነስርአት ማስጠበቂያ ህግ እና
ገደብ ለደህንነታቸው አስፈላጊ ነው
• ገደቦች/ህጎች ለልጆች ጥበቃ ; ጥሩ ባህሪ እንዲኖራቸው ለማድረግ ; እና ከችግር
እንዲወጡ ለማድረግ ይረዳቸዋል
• ገደቦች ልጆችን የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል
• ገደቦች በሚወጡበት ጊዜ ልጆች የወላጆቻቸው እንክብካቤ እንዳላቸው ይሰማቸዋል
•ገደቦች ልጆች ኃላፊነት እንዲሰማቸው እና በራሳቸው የሚተማመኑ እንዲሆኑ
ያደርጋቸዋል
ክፍል 4
የልጅ አስተዳደግና አያያዝ ክህሎት (ክፍል 2)
ልጆችን በስነ-ምግባር ማነጽና መከታተል
የልጆችን ተገቢ ያልሆኑ ባህርያ መረዳት
ተገቢ ያልሆኑ የልጆች ባህርያት ማለት ልጆች የቤት ውስጥ ደንብን እየተረዱ ለደንቡ ተገዢ ሳይሆኑ ሲቀሩ
የሚያሳዩት ባህሪ ነው::
ለልጆች ተገቢ ያልሆነ ባህሪያት ምክንያቶች
 ልጆች ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉላቸው ይፈልጋሉ
 ልጆች እንደማንኛውም የሰው ፍጥረት ከሚያስፈልጓቸው መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው ማለትም ምግብ፣
መጠለያ፣ ልብስ እና እረፍት በተጨማሪ የስሜቶቻቸው እና የስለ ልቦና ፍላጎቶቻቸው መሟላት
ይኖርባቸዋል፡፡
 እኛ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት የምናሳያቸው ባህሪዎች እና የምንወስዳቸው
እርምጃዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ • ውሃ ሲጠማን ቀድተን መጠጣት
• ብቸኝነት ሲሰማን ጓደኞቻችንን ፈልገን ማግኘት
• ችግሮች ሲያጋጥሙን ለጓደኞቻችን ማከርና የመሳሰሉትን ይጥቀሱ፡፡
 ነገር ግን ልጆች ፍላጎቶቻቸውን ለመግለፅ በንግር የመጠቀም አቅማቸው አነስተኛ ነው፡፡ ስለዚህም
ፍላጎቶቻቸውን ለመግለፅ የተለያ ባህሪዎችን ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ባህሪዎች ደግሞ ያልተገቡ ምንልባትም
ጥፋቶች ሆነው ልናገናቸው እንደምንችል ማብራራት፡፡
 ልጆች የቤት ውስጥ ደንቦችን አይረዱም
 አንዳንድ ደንቦች ከልጆች እድሜና ችሎታ በላይ ይሆናሉ
 አንዳንድ ጊዜ ከተለያ ተንከባካቢዎች የሚቃረኑ ድንቦች የሚተላለፉ ሲሆን
እነዚህም ልጆችን ግራ የሚያጋቡ ይሆናሉ
 ልጆች ገደቦችን ለመፈተሸ ይፈልጋሉ
 ልጆች ተንከባካቢዎቻቸውን ለመፈተን/ማየት ይፈልጋሉ
 ልጆች ገደቦች እውነት መሆናቸውንና ተንከባካቢዎቻቸውም ምን ያህን ተግባራዊ
እንደሚያደርጓቸው ማይት ይፈልጋሉ
 ልጆች ራሳቸውን ለመቻል እንደዚሁም የተንከባካቢዋች ክትትልና ቁጥጥር እንዲኖር ይፈልጋሉ
 ልጆች በሚያድጉበት ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ራሳቸውን መቻልና ቁጥጥር ያስፈልጋቸዋል ይህ
ፍላጎታቸው መሟላት ካልቻለ ደግሞ ያልተገቡ ባህሪዎችን ያሳያሉ
 የልጆች ያልተገቡ ባህሪያት በተንከባካቢ ሲበረታታ
 ተንከባካቢዎች ባለማወቅ ልጆች ያሳዩትን ያልተገቡ ባህሪዎች ተከትሎ ፍላጎቶቻቸው የሚሟሉ
ከሆነ እነዚያው ያተገቡ ባሪዎችን ማሳየታቸውንነ ይቀጥላሉ፡፡ ለምሳሌ ሲያለቅሱ ሲጮሁ የሚፈልጉት
ነገር ይደረግላቸዋል፡፡
 ልጆች አጓጉልና ያተገቡ ባህሪያትን ከሌሎች ይቀዳሉ
 ልጆች ተንከባካቢዎች የሚያሳዩትን ባህሪ ይቀዳሉ ሶጮሁ ይጮሀሉ፣ ሲገሙ ይገረማሉ ወዘተ

• ልጆች ብዙ ጊዜ በተለያ ምክንያቶች ያልተገቡ ባህርያትን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡


• በዘብዛኛው ልጆች ተገቢ ያሆኑ ባግርያት መከሰት ተንከባካቢዎች ተጠያቂዎች
ናቸው፡፡
• ስለዚህም ወላጆች/ተንከባካቢዎች/ የልጆቹን ያተገባ የባህሪ ችግር መንስዔ
መረዳትና ፍላጎቶቻቸውን በአግባቡ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሥነ-ምግባር እና ቅጣት
ሥነ ምግባር ቅጣት
የቅጣት ዓላማ ልጆችን በሚጎዳ ወይም ጥሩ ባልሆነ መልኩ
ልጆች እንዳያደርጉ የምትፈልጉት ነገር እንዳያደርጉ ማስቆም
የ ው ጤ ታ ማ ሥነ ምግባር ዓላማ ልጆች በህርያቸውን መቆጣጠርን ነው
አንዲማሩ ይረዳል ይህም ቅጣትን ስለሚፈሩ ሳይሆን ጥሩና መጥፎ
ብለው ባሏቸው ሀሳብ መሰረት እንዲመሩ ያደርጋቸዋል

ለምሳሌ ታማኝ የሚሆኑት ታማኝ ባለመሆናቸው


እያዛለሁ ብለው ሳይሆን ያለመሆን ትክክል አይደለም
ብለው ስለሚያምኑ ወይም ስለሚያስቡ ነው፡፡

 ልጆች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ ይረዳል • ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያጭበረብሩ



 ለአፍላ ወጣቶች መጠቀም ይቻላል ያስተምራቸዋል
• በአፍላነት የዕድሜ ደረጃ ላይ ላሉ ወጣቶች

 የልጆችን በራስ መተማመን ይገነባል አይሰራም
• በራስ መተማመንን ያቀጭጫል

 ችግሮችን በውጤታማ መንገዶች ለመፍታት • ልጆች በኃይል የሚፈጸሙ ድርጊቶች ብቻ

ጥሩ ምሳሌ ያስቀምጣል ተቀባይነት ያላቸው የችግሮች መፍትሄዎች
መንገዶች እንደሆኑ ያስተምራቸዋል
 በመግባባትና በርህራሄ አእምሮ እንዲያድግ • ቅጣት ብዙውን ጊዜ የሚመነጨው ከንዴት

የሚያድግ ነው፡፡ ነው ግቡም (ብዙ ጊዜ ሳናውቀው) ሌላውን
· ልጆችን ውስጣዊ የሆነ የራሳቸው ሥነ ምግባር በአካልም ሆነ በሥነ ልቡና በመጉዳት
እንዲኖራቸው ማስተማርን ግብ ያደረገ ነው፡፡ ማብረድ ነው፡፡

· ንዴታችንን መልካም ላልሆኑ ባህርዮች የሚሰጠው ምላሽ • ቅጣት ብዙውን ጊዜ መልካም ያልሆነውን

የሚከተሉት ውጤቶች ይኖሩታል ባህሪይ ወዲያው ያስቆማል፡፡ ሆኖም
o ስህተቶችን እንደ መማሪያ አጋጣሚዎች የምንጭበረበረው አጭር ዕድሜ ባላቸው
የማየት ችሎታ ውጤቶች ነው፡፡
o ትብብር
o ኃላፊነት • ልጆች በመቀጣታቸው ምክንያት

o ለችግሮች መፍትሄ የመፈለግ ችሎታን ስለሚወስኑት ውሳኔ ብዙም አያውቁም፡
የማዳበር ፡ ሆኖም የወደፊት ባህርይ መሰረት
የሚያደርገው በደመ ነፍስ በተወሰኑት
ውሳኔዎች ላይ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት
አሳዳጊዎች ቅጣት በረዥም ጊዜ
ስለሚያስከትላቸው ውጤቶች ማወቅ
ይኖርባቸዋል፡፡
 ሥነ ምግባር ልጆች እንዴት በሥነ ሥርዓት •ቅጣት ለህፃኑ የሚነግረው መጥፎ እነደሆነ
መኖር እንዳለባቸው ያስተምራል ብቻ ነው በምትኩ ምን ማድረግ እነዳለባቸው
 ሥነ ምግባር ለልጆች ስሜት ሊሰጥ ይገባዋል፡ አይነግራቸውም ስለዚህም ቅጣ ለልጆቹ
ካደረጉት አንድ መልካም ያልሆነ ባህርይ ምንም ስሜት አይሰጣቸውም፡
ጋርም የተያያዘ ሊሆን ይገባዋል • ቅጣት ብዙውን ጊዜ ልጆቹ ካደረጉት
 ሥነ ምግባር ልጆች ስለ ራሳቸው ጥሩ ነገር መልካም ያልሆነ ነገር ጋር አየያያዝም
እንዲሰማቸው ያግዛል፡ ስህተቶቻቸውንም
እንዲያርሙም ዕድሉን ይሰጣቸዋል፡ ለሚወስዳቸው
እርምጃዎችም ተጠያቂ ያደርጋቸዋል
o ስነ ስርአት ማስያዝ ለማስተማሪያነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ተደርገው መታሰብ
ይኖርባቸዋል፡፡
o ህፃናት ሲወለዱ የሚጠቅማቸውንና የሚጎዳቸውን ትክክለኛ እና ስህተት የሆኑ
ባህሪዎችን ተምረው አይወለዱም፡፡
o ስለዚህ እነዚህን ባህሪዎች ማስተማር የወላጆች/ተንከባካቢዎች ሃላፊነት
ይሆናል፡፡
ልጆችን መልካም ስነ-ምግባር ማስተማር
ልጆችን መልካም ስነ ምግባር ለማስተማር የሚያስችሉ የተመረጡ አማራጮችን
መጠቀም አስፈላጊ ነው እነዚህም አማራጮች
• በልጆች መልካም ባህሪዎች ላይ ማተኮር መልካም ባህሪያቸውን ማድነቅ ማመስገን እና
መሸለም
• ያልተገቡ ባህሪዎችን በጎና መጥፎ ጎኑን ከልጆች ጋር በመነጋገር በፍጥነት እንዲቆም
ማስወሰን
• ቅጣት መጣል ልጆች ያልተገቡ ባህሪዎች በሚያሳዩበት ጊዜ በአነስተኛ ቅጣት
በመጠቀም መቅጣት
• የተለያዩ ስጦታዎችን ጥቅማ ጥቅሞችን መንፈግ/መከልከል፡፡ ልጆች ግዴታቸውን
ለመወጣት እንዲገነዘቡ ያስተምራቸዋል
• ማዕቀብ መጣል ልጁ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ ምክንያት የሚወደውን ነገር እንዳያገኝ
ማድረግ
• የጊዜ ቅጣት ይህ ዘዴ የሚያገለግለው ለትንሽ ልጆ ሲሆን ልጆን ከመጫወቻቸው
በማራቅ እና ችላ ማለትም ይሆና
ወላጆች/አሳዳጊዎች
• ልጆቻችሁን መልካም ስነ-ምግባር ለማስተማር የምትጠቀሙባቸው መንገዶች ሁሉም ልጆቻችሁ
ሊያውቁት ይገባችዋል፡፡
• ልጆቻችሁን መልካም ስነ-ምግባር ለማስተማር የምትጠቀሙባቸው ከመጠቀማችሁ በፊት ልጅዎን
ለምን ያልተገባ ባህሪ እንደሚያሳዩ ይተጠይቋቸዉ
• ለትንንሽ ልጆችና የምንጠቀምበት የስነ-ምግባር ማስተማርያ ለትላልቅ ልጆች ሲሆን እንደማይችል
መረዳት፡፡
• ወላጆች የሚጠቀሙበት መንገድ ለመምረጥ የልጆችን እድሜ ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
ያስታዉሱ፤ ስነ-ምግባር ለማስተማር ወይም ያልተፈለገ ባህሪ ወደፊት እንዳይደግሙት ለማድረግ ነዉ፤

o ስለ ልጅነት ጊዜያችሁ አስቡ


o የተቀጣችሁበትን አንድ ጊዜ አስቡ
o አቀጣጡ በምን ሁኔታ ነበር?
o በዚያን ጊዜ በአካላችሁና በስሜታችሁ ላይ ምን
አስከተለባችሁ?
ልጆችን መከታተል
ልጆችን የመከታተልና እንደ ሁኔታው ድጋፍና ማስተካከያ ማድረግ ቀጣይነት ያለው እና ከጨቅላነት
እስከ እራሳቸውን ችለው ከቤተሰብ እስኪለዩ ድረስ የሚቀጥል ስራ ነው።
• ከትትል ማድረግ ማለት ልጆች የሚያሳዩአቸውን ባህሪያት መገምገም የስነ ስርአት ገደብ አውጥቶ
ማስፈፀም ማለት ነው፡፡
• ልጆች የወደፊት ህይወታቸውን እንዲመርጡና እንዲወሰኑ መርዳት፡፡
• ለትንንሽ ልጆች በቅርበት የውሉአቸው ሁኔታ መከታተል ነው
• ለትላልቅ ልጆች ቸልዳንድ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ ለሆን ይችላል
ለምሳሌ
o የት እንደዋሉ
o ከማን ጋር እንደዋሉና የሰዎቹን ማንነት ማወቅ
o ምን ሲሰሩ እንደዋሉ
o ከቤት የሚወጣበትና የሚገባበት ጊዜና ሰዓት ሁሉ ለይቶ ማወቅና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት

ልጆችን የመከታተልና ወቅታዊ ድጋፍ ማድረግ ለልጆች እድገት ትልቅ ጠቀሜታ አለው ለምሳሌ
• ክትትል ልጆችን ከተለያዩ አደጋዎች ለመጠበቅ ያስችላል፤
• ልጆች ወደያማያስፈልግ ባህሪ ሲገቡ ወቅታዊ እርምት ለማድግ ይረዳል፤
• የልጆቻችንን ጓደኞች በጎ ተፅእኖ እንዳላቸው ለማወቅ ይረዳል፤
• ልጆች በወጣትነት እድሜአቸው ቀጣይ ህይወታቸውን የሚያበላሹ ችግሮች ውስጥ እንዳይገቡ
ይከላከላል፤
• ልጆችን መከታተል ማለት ከልጆቻችን ጋር ውሎ ማደር ማለት አይደለም
• ተገቢ የሆነ ክትትል ማድረግ ማለት
o ስለ ውሎው ጥያቄ መጠየቅ፣የሚያሳያቸውን ባህሪዎች መገምገም
o የስነ-ስርዓት ገደብ አውጥቶ ማስፈፀምና
o ለልጁ የወደፊት ህይወት የሚነጀውን እንዲመርጥ እና እንዲወስን እገዛ ማድረግ
ማለት ነው፡፡
ክፍል 5
ጥሩ ምሳሌ/አርአያ መሆን
ጥሩ አርኣያ ወይም ምሳሌ መሆን ማለት፡- መልካም ስነ ምግባር የተሞላበትን ባህሪያት ለልጆቻችን
በማሳየት ልጆቻችን ደግሞ ስነስርአት እና ግብረገብ ያላቸው መልካም ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
ለልጆቻችን ጥሩ አርአያ ለመሆን
• ልጆቻችን እንዲማሩ የምንፈጋችውን ባህሪ ማሳየት
• የምናደርገውና የምናወራው ተመሳሳይ መሆን አለባቸው
• ስህተቶቻችን በመንገር ይቅርታ መጠየቅ
• ለሌሎች አክብሮትንና ፍቅርን ማሳየት
• መልካም የሆኑ ጓደኞች መምረጥ
• የራሳችንን ባህሪዎች መገምገም እና ማስተካከል
• ይቅርታ ማድረግን መልመድ
• በተቻለ መጠን ያልተፈለገ ባህሪቶችንን ማስወገድ
ወላጆች/ተንከባካቢዎች ለልጆቻችን ጥሩ አርአያ ወይም ምሳሌ ለመሆን ማሻሻል መከተል ያለብን
• ልጆች በጣም ተመልካቾች ናቸው፡፡ በአብዛኛዉ ከሚሰሙት ይልቅ ከሚያዩት ይማራሉ፤
• የሚያጋጥመን ችግርና መከራ በጣም የሚያስተምሩን ናችዉ፡፡ይህም ማለት ልጆቻችን በቅርበት
ስለሚመለከቱን ከምናደርገዉና ለችግራችን ከምንሰጠዉ መፍትሄ ሁለ ይማራሉና፤
• ማንም ሰው ፍፁም እንዳልሆነ ሁሉ አንዳንድ ግዜ ስናጠፋ ጥፋተኛ መሆናችንን ገልፀን ይቅርታ
መጠየቅ ፤
• ልጆቻችን የተለያዩ ባህሪያቶችን በቀላሉ ከኛ ስለሚወርሱ በምናገረውና በምናደርገው ሁሉ ከፍተኛ
ጥንቃቄ በማድረግ እኛን እያዩ እንዲማሩ መርዳት
ማንም ሰው ፍፁም እንዳልሆነ
• አንዳንድ ጊዜ ስሜታዊ ሆነን ጥፋት ልንሰራ እንደምንችል ስናስበው ልንፀፀትበት
የምንችለለውን አባባል ልንናገር እንችላለን፡፡
• ሁልጊዜም የምንፈልገውን ያህል ደግ ላንሆን እንችላለን ትልቁ ነገር ከስህተታችን
ታርመን ለማሻሻል መጣሩ ላይ ነው፡፡
• ለልጅዎ ማድረግ የሚችሉት ምርጥ ነገር ጥሩ/መልካም ምሳሌ መሆን ነው፡
ስሜታችንን መቆጣጠር
አንድ ወላጅ/አሳዳጊ ንዴቶች በሚከተሉት ንድትን መቆጣጠር ይችላል፡፡
• ራስን በመቆጣጠር እና ለብቻችን ሆነን ስሜቶቻችንን በማርገብ ንዴቶቻችንን በልጆቻችን ላይ አለመወጣት
• በተናደድን ወቅት እርምጃ አለመውሰድ፣ እራስንም ትንፋሽ በመሳብ እና በማስወጣት ማቀዝቀዝ
• በንዴት ወቅት ከመናገር መቆጠብ
• የተናደድንበትን ነገር በተደጋጋሚ ከማሰብ የተለያዩ መፍትሄዎችን መሻት
• ይቅር የማለት ልምድ ማዳበር
• የአካል እንቅስቃሴ ብቃት ማድረግ
• ራስን ማዝናናት መልመድ
• እርዳታ እና ምክር መጠየቅ
የጭንቀት ምልክቶች በአስተሳሰብ፣ በአካል፣ በባህሪ እንዲሁም ስሜታው መልኮችን ይይዛሉ፡፡
• የማስታወስ፣ አትኩሮት ማድረግ አለመቻል፣ ውድቀቶችን ብቻ ማየት በተደጋጋሚ መጨነቅ
• የጨጓራ ማቃጠል ፣ ማስቀመጥ/ሆድ ድርቀት፣መፍዘዝና መድከም፣የደረት ህመም፣ልብ ምት መፍጠን፣
በተደጋጋሚ ጉንፋን መያዝ
• መነጫነጭ፣ ዘና ማለት አለመቻል፣የውጥረት ስሜት፣የብቸኝነትና የመገልገል ስሜት፣ድብርትና ደስታ
ማጣት
• በብዛት ወይም በጥቂት መመገብ እንዲሁም መተኛት፣ ራስን ማግለል፣ ሃላፊነትን መሸሽ፣ የሲጋራ የመጠጥ
እና የእፅ ሰለባ መሆን፣ ስንበሳጭ ጥፍር መንከስ ፀጉር መንጨት ወዘተ

ጭንቀትን ለማስወገድ ምን ማድረግ አለብን


• የሚያስጨንቅዎት ነገር ምንድን ነው? የጭንቀት መንስኤውን በማውጣት ለጓደኛ ወይም ለሃይማኖት
አባት ማማከር
• ማድረግ የምንችለውን ብቻ ማድረግ
• የምንችለውን ያህል መሞከር፡ የሚችሉትን ካደረጉ ጉዳዩን ለመርሳት መሞከር
• ፀሎት ማድረግ፣ ስፖርት መስራት፣ ራስን ማዝናናት መልመድ፣ በአከባቢ ያለ አማካሪ ባለሙያ ጋር ሄዶ
መፍትሄ መሻት
የጭንቀት ምልክቶችን

በአስተሳሰባችን ላይ የሚከሰቱ ስሜታዊ ምልክቶች

• የማስታወስ ችግር · መተጫነጭ


• አትኩሮት ማድረግ አለመቻል · ዘና ማለት አለመቻል
• ውድቀቶችን ብቻ ማየት (መልካ ነገሮችን · የውጥረት ስሜት
አለማየት) · የብቸኝነትና የመገለል ስሜት
• በተደጋጋሚ መጨነቅ/ማሰብ · የድብርትና በጥቅሉ ደስታ ማጣት

በአካ ላይ የሚከሰት የባህሪ ለውጦች

• የጨጓራ ማቃጠል ስሜት · በብዛት ወይም በጣም ጥቂት መመገብ በብዛት

• የማስቀመጥ ወይም የሆድ ድርቀት ወይም በጣም ጥቂት መተኛት


የመፍዘዝና የመድከም · ራስን ማግለል

• ደረት አካባቢ የሚፈጠር ህመም · ሃላፊነትን መሸሽ/ችላ ማለት


• የልብ ምት መፍጠን · የሲጋራ መጠጥና ሌሎች አደንዛዥ እጽ ሰለባ

• በተደጋጋሚ ጉንፋን መያዝ መሆን

· ስንበሳጭ የተለያ ነገሮችን ማድረግ (ጥፍር

መንከስ፣ ፀጉር መሳብ/መንጨት

You might also like