Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 100

Current Church Challenges and

Their Solutions
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮቶች እና

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን


የዋናው ቢሮ
ትምሕርትና ሥልጠናዓ.ም
ሕዳር/2016 መምሪያ
በዚህ ትምሕርት የምንዳስሳቸው ርዕሰ-ጉዳዮች፡-

መፍትሔዎች
የአመራር
የሐሰት ተግዳሮቶች
የዘረኝነትና ትምህርት እና
የብሔር አሰራር
ድህረ ዘመናዊ
ተግዳሮቶች ተግዳሮቶች
የግል
መንፈሳዊ
ሕይወት
ተግዳሮቶች
መግቢያ
ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል የመጣው ከግሪኩ “አክሊሽያ” ሲሆን ትርጉሙም “ተጠርቶ የተሰበሰበ ህዝብ”
ማለት ነው፡፡ ከአለም ተጠርቶ የእግዚአብሔርን አላማ ለአለም የሚያገለግል የሠዎች ስብስብ ማለት ነው፡፡
ይህም የእግዚብሔር አላማ ታላቁ ተልእኮ ማቴ 28፥18-20 እና ታላቁ ትዕዛዝ ማቴ 22፥37-40 ላይ የተገለጸው
ነው። በነዚህ ሁለት ታላቁ ተልእኮና ታላቁ ትእዛዝ በየትኛውም ዘመንና ቦታ እንዲሁም አውድ የምትገኝ ቤተ
ክርስቲያን እንድትፈጽመው የተሰጣት ዘመን ዘለል መለኮታዊ መመሪያ ነው።

ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንማረው የቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና ድክመት የሚለካው ይህንን ታላቅ
ተልእኮ እና ትእዛዝ ለመፈጸም በእነርሱ ዘመንና አውድ የተገለጡ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ
ተግዳሮቶችን በእውነት ቃል ጸንተው በማሸነፋቸውና የክርስቶስ ምስክር በመሆናቸው መጠን ነው።

በኢትዮጵያ አሁን ባሉት ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት እየተሰራ ያለው መንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም
ወንጌልን ማሰራጨት፣ ያመኑትን ደቀመዝሙር ማድረግ እና የሰዎችን ሁለንተና ማገልገል በጥቅሉ ሲታይ ከሁሉም
አቅጣጫ በብዙ ወቅታዊ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈ ይገኛል፡፡ የዚህ ትምህርት አላማም ወቅታዊ የሆኑ የቤተ
ክርስቲያንን መንፈሳዊ ሕይወት እና ተልእኮ እየጎዱ ያሉ ዋና የሆኑ ተግዳሮቶችን በማሳየት ቤተ ክርስቲያን ባላት
የአገልግሎት መንገዶች ምእመኑ ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር አገልጋዮችን ለማስታጠቅ ነው።
1. የግል መንፈሳዊ ሕይወት ተግዳሮቶች

• ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኛቸው ተቀብለው ዓመታትን ያስቆጠሩ፣ ነገር ግን በመንፈሳዊ ህይወት


እድገታቸው ብዙ ለውጥ የማይታይባቸው ያልበሰሉ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ውስጥ በብዛት
መገኘታቸው በየጊዜው ለውይይት የሚነሳና አነጋጋሪ ጉዳይ እየሆነ ከመጣ ሰንበትበት ብሏል፡፡ እንዲህ
ሲባል ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ ክርስቲያናዊ አምልኮአቸውና ኑሮአቸው በእሁድ ማለዳ ያልተወሰነ፣
አማኞች በምድራችን የሉም ማለት አይደለም፡፡

• ጌታን አሁን ካለንበት የሕይወት ደረጃ የተሻለ ማወቅ፣ ማገልገልና ማስደሰት የሁላችንም ምኞት ነው፤ ነገር
ግን በአካላዊ ወይም በአእምሮአዊ የዕድገት ሂደቱ አንድ ነገር እንደጎደለው ሰው ክርስትናን በሕይወት
ሙላት እየኖርነው አይደለም። እርግጥ ክርስቲያኖች መሆናችንን ያሳዩልናል ብለን የምናስባቸው አንዳንድ
ትልልቅ ምልክቶች አሉ፣ ሆኖም ግን አላረኩንም፣ እግዚአብሔርም ወደሚፈልገው የብስለት ልክ ውስጥ
አላደረሱንም፡፡ በመሆኑም በብስለት ላለማደጋችን እና የተጠራንለትን ተልእኮ ላለመፈጸማችን
ምክንያቶች የሆኑ ነጥቦችን እንደሚከተለው እናነሳለን።
1.1 የድነትን ደስታ አለመለማመድ
• ለክርስቲያን ሕይወት ወቅታዋ ተግዳሮት አንዱ የድነትን ደስታ አለመለማመድ ነው።
ለክርስቲያኖች መዳን ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በማመን እና
ለኃጢአት ይቅርታ በመስቀል ላይ የመሞትን መስዋዕትነት በመቀበል፣ ከኃጢአት እና ከዘላለም
ፍርድ የመዳን ጽንሰ-ሀሳብ ነው።
• የክርስቲያን ድነት ደስታ ማለት የአንድ ሰው ኃጢአት ይቅርታ እንደሚደረግለት እና የዘላለም
ሕይወትን በማግኘቱ የሚገኘውን የደስታ፣ የሰላም እና የነጻነት ስሜትን ያመለክታል።
ለእግዚአብሔር ጸጋ ጥልቅ እርካታ እና ምስጋና ምላሽም ነው።

• ይህ ደስታ በተለያዩ መንገዶች ሊገለጽ ይችላል፤ ለምሳሌ ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ


በኩል ዘወትር ምስጋና ማቅረብ ፣ ሌሎችን ማገልገል ወይም በቀላሉ ውስጣዊ ሰላም ሊሰማን
ይችላል።
የክርስቲያን የመዳን ደስታን ያለማሳየት ምልክቱ በተስፋ፣ በሰላምና በአመስጋኝነት
እጦት እየጎደለ መኖር ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ያለን እምነት
ማነስ የድነትን ደስታ እንዳንለማመድ እንደሚያደርግ እናያለን። አንድ ሰው የመዳን ደስታን
ካላሳየ አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎችና ዝግጅቶች ላይ ተስፋ እንደሌለው ሊያመለክት ይችላል።

የክርስቶስ ሰላም የድነት ደስታ መገለጫ ነው። የሰላም እጦት በክርስቲያን ሕይወት ከታየ የድነት ደስታውን እየተለማመደ እንዳልሆነ
የሚያሳይ ነው።
''ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር
በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።
አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን
በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።'' (ፊል 4፥6-7)
አንድ ሰው ደስታ ካላሳየ በልባቸውና በአእምሮው ውስጥ ሰላም እንደሌላቸው ሊያመለክት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም ፤
በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የምስጋና ማነስ፤ የድነትን ደስታ እያጣጣመ እንዳልሆነ የሚያሳይ የሕይወት መገለጫ ነው፣ 1
ተሰሎንቄ 5፥16-18። አንድ ሰው ከጌታ ጋር ደስታን ካላሳለፈ፣ ለእግዚአብሔር በረከቶችና ቸርነት አመስጋኝ አለመሆንን
ሊያመለክት ይችላል። በአጠቃላይ፣ የክርስቲያን የድነት ደስታ አለመኖር በእግዚአብሄር ላይ ካለ እምነት፣ ተስፋ፣ ሰላም እና ምስጋና
ማጣት የሚመጣ አሉታዊ የአእምሮ እና የልብ ሁኔታ ነው።
1.2 የመንፈሳዊ እድገት አለመኖር

• የመንፈሳዊ እድገት አለመኖር ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት ነው።


ክርስቲያናዊ መንፈሳዊ እድገት ክርስቶስን የመምሰል እና ከእግዚአብሔር ጋር
ያለውን ግንኙነት የማጠናከር ሂደትን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን
ያለማቋረጥ መማር እና መተግበር እና አምላካዊ ልማዶችን ማዳበርን ያካትታል።
በመንፈሳዊ አለማደግ ምልክቶች ለእያንዳንዱ ግለሰብ በተለያየ መንገድ ሊገለጡ
ይችላሉ፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የሚታዩ አንዳንድ የተለመዱ
ምልክቶች አሉ።
በዓለማዊ
የጸሎት እና ክርስቶስን
የመንፈስ ምኞቶች የፍቅርና
የመጽሐፍ የሚመስል
ፍሬ ተጽእኖ ርኅራኄ
ቅዱስ ባሕርይ
አለማፍራት ውስጥ ማነስ
ጥናት ማነስ አለማሳየት
መኖር
የመንፈስ ፍሬ አለማፍራት በዓለማዊ ምኞቶች ተጽእኖ ውስጥ መኖር

• የመንፈሳዊ እድገት ማነስን ያሳያል። • (1 ዮሐንስ 2፡15-17) “ዓለምን ወይም


• በ (ገላትያ 5፡22-23) ጳውሎስ ስለ መንፈስ በዓለም ያሉትን አትውደዱ። ማንም ዓለምን
ፍሬዎች ሲናገር ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ቢወድ የአብ ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፤''
ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ይላል።
የውሃት እና ራስን መግዛትን ይናገራል። • አንድ ሰው ከአምላካዊ ፍላጎት ይልቅ ዓለማዊ
• እነዚህ ፍሬዎች በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ምኞቶችንና ተድላዎችን የሚከታተል ከሆነ
ከጎደሉ፤ የመንፈሳዊ እድገት እጥረት መኖሩን መንፈሳዊ እድገት እንደሌለው ያሳያል።
ያመለክታል።
የጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማነስ ክርስቶስን የሚመስል ባሕርይ አለማሳየት

በመንፈሳዊነት ለማደግ ከቀዳሚ መንገዶች አንዱ ጸሎትና


መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ነው። አንድ ሰው እነዚህን
የትምህርት ዓይነቶች ችላ የሚል ከሆነ የመንፈሳዊ
እድገትን እጥረት እያሳየ ይሔዳል።
• በማንኛውም መልኩ የቃሉ ተማሪ አለመሆን
አለመታዘዝ ማለት ነው። • በ (1ኛ ዮሐንስ 2፡6) ላይ ሲናገር፤ “በእርሱ
• 1ቆሮ 13፥11“ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እኖራለሁ የሚል ሁሉ እርሱ በተመላለሰበት
እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ መንገድ ሊመላለስ ይገባዋል” ይላል። አንድ ሰው
ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ፤” ክርስቶስን የሚመስል ባህሪ ካላሳየ የመንፈሳዊ
እድገት እጥረት እንዳለ ያሳያል።
• ክርስቲያናዊ ት/ትን ለመማር መምረጥ ወይም
አለመምረጥ በሞትና በሕይወት መካከል ያለ በእድገት
የመቀጠል ወይም ያለመቀጠል ጉዳይ ነው፡፡
የፍቅርና ርኅራኄ ማነስ

• በ (1ኛ ቆሮንቶስ 13) ላይ ጳውሎስ ስለ ፍቅር


ከመልካም ምግባሮች ሁሉ የላቀ እንደሆነ
ተናግሯል።
• አንድ ሰው ለሌሎች ፍቅር እና ርህራሄ
ከጎደለው፤ የመንፈሳዊ እድገት እጦት ያሳያል።
ለሌሎች ሸክም የሌለው፤ የክርስቶስ ልብ
የሌለው፣ ሌሎችን ማገልገል የማይችል
ይሆናል።
1.3 እውነተኛ ደቀመዝሙርነትን አለመለማመድ

 የደቀ መዝሙርነት ሕይወት ራስን


መካድ ማለት ነው።
• ራስን መካድ ማለት ራስን እንዳልተፈጠሩ መቁጠር ማለት ሳይሆን፣ ክርስቶስን ማስቀደም
ማለት ነው፡፡
• እውነተኛ ደቀመዝሙርነት ሕይወትን አለመለማመድ የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት
ነው።
• በመጀመሪያ እኛን ለደቀ መዝሙርነት የጠራን መምህር ራሱን የካደነው፤ እርሱ በመለኮት
መልክ ሲኖር ሳለ፣ የባሪያን መልክ ያዘ (ፊሊ 2፡5-11) ፡፡ እንዴት ያለ ራስን መካድ ነው!
ይሄ ሁሉ ታዲያ ግድ ሳይኖርበት በፈቃዱ ነው፡፡ ራስን መካድ ልክ እንደ ጳውሎስ ዘሩን፣
ሹመቱን፣ ሃይማኖታዊ ቅንአቱንና በሕግ ፈጻሚነቱ አለኝ የሚለውን ጽድቅ መተው ማለት
ነው (በፊልጵ 3፡8-12)፡፡
ክርስቶስን ለመከተል ስትወስን ምን የካድከው ነገር አለህ? የዘርህንና የጎሳህን የበላይነት፣
የፆታ ትምክትህን፣ ባለ ጠግነትህን፣ እውቀትህን፣ ጉልበተኛነትህን፣ የቤተ እምነት ወገናዊነትህን፣
ምነድን ነው የጣልከው? የጣልን የመሰለን የሚያስጥል ብዙ የሕይወት አጋጣሚ ስላልገጠመን ነው
እንጂ ብዙ ጊዜ ሳንጥል የምንገኝ ነን፡፡
የትኛውንም ነገራችንን ሳንጥል ራሳችንን ሳንክድ
የክርስቶስ ባሕርይ ሊታይብን አይችልም::
(ማቴ 19፡16-22)
የኢየሱስ ክርስቶስን እትብት ቆራጭ ስብከቶችን ደጋግመን ስላልሰማናቸው በአደባባይ ስብከቶች
ከሕይወት መንገድ እንዳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባናል (ማቴ 5-7)፡፡ ራስህን ያልካድክ ባል ለሚስት
አስቸጋሪ ነህ፤ ራስሽን ያልካድሽ ሚስት ለባል አስቸጋሪ ነሽ፤ ራስህን ያልካድክ አዋቂ፣ ላልተማረው
ወዳጅህ አስቸጋሪ ነህ፣ ራስህም ያልካድክ መጋቢ፣ ሽምግሌ፣ ወንጌላዊ፣ ለምእመንም ሆነ አብረውህ
ለሚያገለግሉ ሁሉ ጭንቅ ነህ፡፡ ራስህን በክርስቶስ ውስጥ ለማግኘት ከፈለግህ ራስህን ካድ (ፊል 3፡10-
12)፡፡ አብዛኛዎቻችን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ራሱን ባዶ በማድረግ የወደደንን ጌታ ከነኮተታችን
እንዴት ልንከተለው እንደፍራለን? እርሱን መከተል የሚቻለው እናትን አባትን፣ ሚስትና፣ ልጆችን፣
ወንድምና እህትን እንዲሁም የራስን ሕይወት ከጌታ በላይ አስበልጦ ባለማየት ነው፡፡
ደቀመዝሙርነትን አለመለማመድ
Cont…
 የደቀመዝሙርነት ሕይወት የግል መስቀልን በመሸከም ስለ
ክርስቶስ ዋጋ መክፈልም ነው።

የክርስትና ጥሪአችን አንደኛው አካል የየራሳችንን መስቀል መሸከም ነው፡፡ ኢየሱስ የዓለሙ ኃጢአት
ሁሉ ተጠራቅሞ የተገለጠበትን መስቀል ተሸክሞአል፡፡ የኢየሱስን መስቀል እኛ መሸከም አንችልም፡፡
ይሁን እንጂ የየራሳችንን መስቀል የመሸከም ጥሪ ደርሶናል፡፡ (ሉቃ 14፡27)፡፡ መስቀል መሸከም
የትዳር ችግር አይደለም፣ እንዲህ ዓይነቱ ችግር ጊዜ ጠብቆ መፍትሄ ያገኛል፡፡ የመሥሪያ ቤት ችግር
አይደለም፤ እንዲህ ዓይነቱ ችግር ወይ በመሥሪያ ቤት ለውጥ፣ አለበለዚያም በደምዎዝ እድገትና
በሹመት መልስ ያገኛል፡፡ የጤንነት መጉደልም አይደለም፣ ጤና ማጣት ወይ በፈውስ አለዚያም
በሞት የህማም ስቃይ ይቀራል፡፡ የገንዘብ ማጣት አይደለም፣ ያጣም ያገኛል ያገኘም ያጣል፡፡
እነዚህማ በኃጢአት ውጤት የተጠቃ የሰው ልጅ ሁሉ፣ የሚሸከመውና የሚፈራረቁበት ችግሮች
ናቸው፡፡ የክርስቲያን መስቀል ግን አያቋርጥም፣ ተገላገልኩትም አይባልም፡፡
መስቀል መሸከም ስለ ክርስቶስ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡ የእርሱ ከመሆናችን የተነሳ
ከሰውና ከሰይጣን፣ ከራሳችንም የሚደርስብንን ተቃውሞ በሞት እንኳን ለማሸነፍ
የምናደርገው ትንንቅ ነው፡፡ ፈቃዱን ለመፈጸም የኛን፣ የሰይጣንንና የዓለምን ፈቃድ
እምቢ በማለት የምንከፍለው ዋጋ ነው፡፡ ለኢየሱስ በፍጹም ሕይወት ለመገዛት ስንል
የምንከፍለው ማናቸውም ዋጋ ነው፡፡ እርሱን የመከተላችን ውሳኔ የሚያደርስብንን
መከራ መቀበል ማለት ነው፡፡
በስንፍናዬ ዝቅተኛ ማርክ የሚሰጠኝ አስተማሪ ወይም በሥራ ባለ መትጋቴ
የደመወዝ ጭማሪ የሚከለክለኝ አለቃዬ መስቀሌ አይደለም፡፡ በባሕሪዬ አለመለወጥ
የሚኮንኑኝ ያላመኑ እናት፣ አባት፣ ዘመዶችና ጎረቤቶች ቢኖሩኝ መስቀሌ ሊሆኑ
አይችሉም፡፡ ይሄ ሁሉ የሚደርስብኝ ግን የጌታ በመሆኔና በጽድቅ በመኖሬ ከሆነ እነርሱ
መስቀሎቼ ናቸው፤ እሸከማቸዋለሁ፡፡
1.4 የቃሉ ስልጣናዊነት መሸርሸር

• የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር ለግል ህይወታችን ያለውን ሆነ እርሱን በኑሮአችንና


በአገልግሎችን እንዴት ደስ ማሰኘት እንዳለብን ያሳየናል፡፡
• የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት የሚያበላሸውን ስህተት ለማረም
መንገድ ያሳየናል፡፡ የመንፈሳዊ ህይወት ደረጃችን፣ የክርስትና ህይወት ግብ ምን እንደሆነ
ያስተምረናል፡፡
• ለዚህ ነው መዝሙረኛው ሲናገር “ህግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን” ነው ያለው፣
መዝ. 119፥105፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተፃፉና ህይወት
ሰጪ በመሆናቸው ለመንፈሳዊ ዕድገት ትልቅ ሚና አለው፡፡
አማኝ በግል መንፈሳዊ ሕይወቱ የሚያድገው የቃሉ ስለጣናዊነት በምንም
ሳይሸረሸር በሕይወቱ ሲሰራ እንጂ ልዩ ልዩ መጣጥፎችን በማገላበጥ አይደለም፡፡
ከቃሉ ስልጣን ውጪ የሆነ ሕይወትም ሆነ አገልግሎት አንድን አማኝም ሆነ
አገልጋይ ወደ ስህተት ለመምራትና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ ለማውጣት ትልቅ
አስተዋጽኦ አለው፣ ዮሐ. 1፥14፣ ኤፌ. 1፥13፣ ያዕ. 1፥18፣ ዮሐ. 17፥17።

ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሰው በቃል ዕውቀት ማደግ ዋነኛ ነገር ስለሆነ ራሱን በቃል
ዕውቀት ማደጉንና አለማደጉን ሁሌ መመርመርና መፈተሽ ተገቢ ነው፡፡
1.5 በትጋትና በጽናት አለመጸለይ

• በጥንቷ ቤተክርስቲያን ታሪክ ለግል መንፈሳዊ ሕይወት ጸሎት ቁልፍ ሚና ነበረው።


• ለወንጌል መስፋፋትና ቤተክርስቲያን ተከላም ፀሎት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በጥንቷ ቤተክርስቲያን
አማኞች ውሳኔ ለመስጠት፣ ሐዋ.ሥራ 1፥15-16፣6፥1-6 እና ወንጌልን በኃይልና በብርታት መመስከር
ይችሉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በብርቱ ይጸልዩ ነበር፣ ሐዋ.4፦23-31፡፡
• ለአንዲት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ፀሎት የሙቀት መለኪያ (thermometer) እና የሙቀት
ማመጣጠኛ (thermostat) ነው፣ ይህ ማለት የመንፈሳዊ ህይወት ሙቀት መጨመርና መቀነስ
የሚወሰነው በእግዚአብሔር ህዝብ ፀሎት ነው ማለት ነው፡፡ ፀሎት ከኃላፊነት ማምለጫ ሳይሆን
ለእግዚአብሔር ችሎታ የምንሰጠው እውነተኛ ምላሽ ነው፡፡
• በፀሎታችን ትጋትና ጽናት ከሌለበት ውጤት አናመጣም፡፡ ምክንያቱም ያለ ፀሎት የኛ
ሕይወት እና አገልግሎት ስኬታማ መሆን አይችልምና፡፡
1.6 ለሚጠፉት ያለን ፍቅርና ርኅራኄ አናሳ መሆን

• ፍቅርና ርኅራኄ የሰውን ልጆች ወድዶ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ለላከው እግዚአብሔር የባህርዩ
ምልክት ነው ፣ዮሐ. 3፡16፡፡ ፍቅር ከሌላው የሚልቅ ዋና የእግዚአብሔር ባህርይ ነው፡፡ …
የመንፈስ ቅዱስ ትልቁ ሚና በክርስቲያን ህይወት ውስጥ ለጠፉ ነፍሳት የእግዚብሔር ዓይነት
ርኅራኄና ፍቅር እንዲኖር ሁሌ ይሰራል፣ ሮሜ. 5፥5፣ገላ 5፥22፡፡
• ይሁን እንጂ በዚህ ዘመን ይህ ተልዕኮ ወደ ጊዜያዊ ፍላጎትና ርኅራኄ የለሽ ህይወት ዞሯል፡፡
ምክንያቱም እንደ ሌሎቹ ሁሉ የክርስቲያኖች ትኩረት ወደ ምድራዊና ቁሳዊ ወደሆነው ነገር በራስ
ህይወት ላይ ወደ ሚያጠነጥነው ተግባርና ድርጊት ተቀይሯል፡፡
• እንደ እግዚአብሔር ቃል ለሚጠፉ ነፍሳት ሁላችን ተጠያቂዎች ነን “እኔ ኃጢአተኛውን፡-
በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ
ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል ደሙን
ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ” ሕዝ.3፥18)፡፡
• ለታላቁ ተልዕኮ “ሂዱ …” የሚለው ትዕዛዝ በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ለተልዕኮ የሚያነሳሳን
ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለቤተ ክርስቲያን የሰጣት ተልዕኮ ፍጥረትን ሁሉ ደቀመዛሙር ለማድረግ
መሄድና ወንጌልን የመስበክ ተልዕኮ ነው፣ ማቴ 28፡18-20፡፡ በመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ይፈፀም
የነበረው ታላቁ ተልዕኮ ተግባር የኋላ ኋላ እየደበዘዘ መጣ፡፡
• ዛሬ በእኛው ዘመን ደግሞ ደበዘዘ ሳይሆን እየተረሳ መጥቶ ቤተ ክርስቲያን እያከናወነች ያለችበትን
ሳምንታዊ ፕሮግራሟን እንደታላቁ ተልዕኮ ቆጥራ ዋና ተልዕኮን ዘንግታ እንመለከታለን፡፡ ስለዚህ
ቤተ ክስቲያን ሚስዮናዊት ለመሆን ለጌታ ትዕዛዝ ማለትም ታላቁ ተልዕኮ ቅድሚያ በመስጠት
የራሷን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡
• ሰዎችን ለወንጌል እውነት ግድ የሚልና ጫና የሚፈጥር አገልግሎት ከሌለ ዛሬ
የምናያት ቤተ ክርስቲያን ነገ መጥፋቷ የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ ደግሞም ተፅዕኖ አልባ የሆነ
የወንጌል ስርጭትም በዚህ ትውልድ ምንም ስለማይሰራ ወንጌልን መስበክ ግደታችን
እንደሆነ ሁሉ ወዳልዳኑት ሰዎች እንድንሄድ ግድ የሚል የክርስትና ህይወት ያስፈልገናል፡፡
• በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናደርጋቸው የተለመዱ እንቅስቃሴዎች ወደ
ፑልፒቶቻችን ያላመኑ እንዲመጡ እያደረገ ስላልሆነ እኛ ከስፍራችን ተነስተን ወደ እነርሱ
እንሂድ፡፡
• ወገኖቼ ሆይ ለዘመዶቻችን፣ ጎረቤቶቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ለሥራ ባልደረቦቻችን፣
ለተማሩና ላልተማሩ፣ ለድሃውና ለሀብታሙ፣ በየአውራ ጎዳናውና እና በየመንገድ ዳር ላሉ
ሁሉ ዕዳ ስላለብን እነዚህን ወገኖችን ወደ እኛ በፍቅር አስጠግተን የምሥራቹን ቃል
እናሰማቸው ሮሜ 1፥14፣ 1ቆሮ.9፥16፡፡
2. የድህረ ዘመናዊነት ተግዳሮቶች
• ድህረ ዘመናዊነት ወቅታዊ የሆነ ትልቁ የአስተሳሰብ ዘይቤ እና ፍጹም እውነትን በአንጻራዊነት እየሸረሸረ
ያለ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ተግዳሮት ነው። በቀላል አነጋገር ድኅረ ዘመናዊነት ምንም ዓይነት ተጨባጭ
ወይም ፍጹም እውነት የሌለው በተለይም በሃይማኖትና በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ የማረጋገጫ መለኪያ
የሌለው ፍልስፍና ነው።
• ይህ አስተሳሰብ በማንኛውም የእውነት ፍለጋ ላይ ሲተገበር ምላሹ አደገኛ ይሆናል፤ ምክንያቱም ግላዊ
የአመለካከት ጉዳዮችን ከእውነት ጉዳዮች ጋር ግራ ስለሚያጋባ ነው። አመለካከት እና እውነት በጣም የተለያዩ
ነገሮች ናቸው።
• በዚህም ምክንያት የድህረ ዘመናዊነት የፈለፈላቸው የአስተሳሰብ ዘይቤዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣
የእውነት አንጻራዊንትን፣ ሉላቀፋዊ አስተሳሰብን፣ ግለኝነትን፣ እና በቴክኖሎጂ አሉታዊ ተጽእኖ ውስጥ
መዉደቅ ክርስቲያናዊ እሴቶችን እየሸረሸረ ትልቅ ተግዳሮት ሆኗል።
2.1 የድህረ ዘመናዊነት ትርጉም
• “ድህረ ዘመናዊነት” የሚለው ቃል በጥሬ ትርጉሙ “ከዘመናዊነት በኋላ” ማለት ሲሆን ከዘመናዊነት ዘመን በኋላ
የመጣውን የአሁኑን ዘመን ፍልስፍና ለመግለጽ ይጠቅማል።
• ድህረ ዘመናዊነት የሰውን ልጅ ለማሻሻል እና አለምን የተሻለች ቦታ ለማድረግ የሰውን ሀሳብ ብቻ ለመጠቀም
ለዘመናዊነት ለገባው ተስፋ ምላሽ ነው። ድህረ ዘመናዊነት ለዘመናዊነት ያለው ምላሽ፣ ፍጹም እውነት አለ
የሚለውን የአስተሳሰብ ዘይቤ በእውነት አንጻራዊነት የመተካት የአስተሳሰብ ዘይቤ ነው።
• የዘመናዊነት እምነት አንዱ ፍፁም እውነት በእርግጥ አለ የሚለው ስለነበር ፣ ድህረ ዘመናዊነት ነገሮችን
በመጀመሪያ ፍፁም እውነትን በማስወገድ እና ሁሉንም ነገር ከግለሰብ እምነት እና ፍላጎት ጋር በማነፃፀር ነገሮችን
ለመተንተን የሚፈልግ አስተሳሰብ ነው።
• የድህረ ዘመናዊነት አደጋዎች ፍፁም እውነትን በመናቅ የሚጀምር የቁልቁለት ጉዞ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ይህም
በሃይማኖት እና በእምነት ጉዳዮች ላይ ልዩነት እንዲጠፋ የሚያደርግ ሁሉም እምነት ወይም ሀይማኖት ልክ ነው
የሚል አስተሳሰብ ነው። ስለዚህም ማንም ሃይማኖቱ እውነት ነው ሌላው ሐሰት ነው ሊል አይችልም። በዚህም
መሠረት የሀይማኖት ብዝሃነትን ይቀበላል።
2.2 የድህረ ዘመናዊነት አደጋዎች

2.2.1 ሁሉንም እውነት አንጻራዊ አድርጎ ማየቱ

• በዚህ ዘመን ወቅታዊ ተግዳሮት ሆኖ እጅጉን የጎዳን የእውነትን ፍጹምነት በእውነት አንጻራዊነት
መቀየራችን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በሁለት አጥናፍ መካከል ያሉ ተቃራኒዎችን በእርቅ ለመፍታት
በምናደርገው ጥረት እውነትን በፍቅር እንነጋገር እያልን እውነትን ስለ ፍቅር እንገድላታለን፡፡ አንድ
ሰው እውነት አንጻራዊ ነው ሲል በተለምዶ የሚናገረው ነገር ፍጹም እውነት የለም ማለት ነው።
''አንዳንድ ነገሮች እውነት ሊመስሉህ ይችላሉ፣ ለእኔ ግን እውነት አይደሉም ማለት ነው''። ካመንክ
ለአንተ እውነት ነው ፤ ካላመንኩ ለእኔ እውነት አይደለም ማለት ነው። ሰዎች “እግዚአብሔር ለአንተ
ካለ ጥሩ ነው፤ ግን ለእኔ የለም” የሚሉትን ነገሮች ሲናገሩ ከሰማን እውነት አንጻራዊ ነው የሚለውን
ታዋቂ እምነት እየገለጹ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
የ “አንጻራዊ እውነት” አጠቃላይ ጽንሰ-ሀሳብ አመቻማች እና ክፍት አስተሳሰብ
ነው። በመሠረቱ፣ "እግዚአብሔር ለአንተ አለ ፤ ለኔ ግን አይደለም" ማለት የሌላው ሰው
ስለ እግዚአብሔር ያለው ፅንሰ-ሀሳብ የተሳሳተ ነው ማለት ነው። ነገር ግን እውነት ሁሉ
አንጻራዊ ነው ብሎ ማንም አያምንም። ማንም ጤነኛ ሰው፣ “የስበት ኃይል ለአንተ
ይሠራል፣ ለእኔ ግን አይሠራም” በሚል እና ምንም ጉዳት እንደማይደርስ በማመን
ረዣዥም ሕንፃዎችን ለመዝለል አይደፍርም፤ ምክንያቱም አንጻራዊ ስላልሆነ።
• "እውነት አንጻራዊ ነው" የሚለው አረፍተ ነገር እራሱን የሚቃወም መግለጫ ነው።
ነገር ግን፣ ሁሉም እውነት አንጻራዊ ከሆነ፣ ያ አረፍተ ነገር ራሱም አንጻራዊ ነው፣
ይህም ማለት ሁልጊዜ እውነት ነው ብለን ማመን አንችልም ማለት ነው።
አደጋዎች
Cont…
2.2.2 አንጻራዊ የሆኑ አንዳንድ መግለጫዎችን ከፍጹም እውነት መለየት
አለመቻሉ
በክርስትና ፍጱም እውነት የሚጠቃበት አንዱ መሠረታዊ ችግር፣ ብዙ ሰዎች ማንኛውንም የእግዚአብሔርን ወይም
የሃይማኖትን ጥያቄ ወደ የአመለካከት ቦታ ይወስዳሉ፣ ፍጹም እውነት የሚጠቃው በዚህ መንገድ ነው። ክርስቲያኖች
የሚናገሩት (መጽሐፍ ቅዱስም የሚያስተምረው) ርዕሰ ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን እውነት አንጻራዊ እንዳልሆነ የሚያሳይ
ነው። ተጨባጭ አካላዊ እውነታ እንዳለ ሁሉ ተጨባጭ የሆነ መንፈሳዊ እውነታ አለ ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር
የማይለወጥ ነው ሚልክያስ 3፥6።

• ጲላጦስ ኢየሱስን "እውነት ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው፣ ዮሐንስ 18፥38፣ “ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን?
አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ
ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው" ዮሐንስ 18፥37 ። እውነት በጲላጦስ
ፊት በደንብ ግልጽ ሆኖ ይታይ ነበር። ብቸኛው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ በዚያ ቅጽበት ለእሱ እውነት መሆኑን ነው
የምናየው። በዚህም መሠረት እውነት ንድፈ ሀሳብ ወይም ስሌት አልነበረም የተገለጠ ነው፤ በመካከላችን የሚኖር
እግዚአብሔር እውነት ነው።
አደጋዎች
Cont…
2.2.3 መለኪያ ስለሌለው ለብዝሐነት (Pluralism) አስተሳሰብ
እውቅና መስጠቱ
ፍጹም እውነት የሚለው የድህረ ዘመናዊነት አደጋ በብዙነት (Pluralism) አስተሳሰብ የክርስትናን እምነት እየጎዳ ይገኛል።
ፍፁም እውነት ከሌለ፣ እና በተለያዩ እምነቶች እና ሀይማኖቶች መካከል ትርጉም ያለው፣ ትክክል/የተሳሳተ መለያየት የሚቻልበት
መንገድ ከሌለ፣ ተፈጥሯዊ መደምደሚያው ሁሉም እምነቶች እኩል ተቀባይነት እንዳላቸው መቆጠር አለባቸው የሚል ነው።
• በድህረ ዘመናዊነት ውስጥ ለዚህ ተግባራዊ አፈጻጸም ትክክለኛው ቃል “ፍልስፍናዊ ብዝሐነት” ነው። በብዝሐነት፣ የትኛውም
ሀይማኖት እራሱን እውነተኛ እና ሌሎች ተፎካካሪ እምነቶችን ሀሰት፣ አልፎ ተርፎም የበታች አድርጎ የመናገር መብት የለውም።
እነዚህ ተራማጅ (Radical) የድህረ ዘመናዊነት አደጋዎች አንጻራዊ እውነት፣ የማስተዋል ማጣት እና የፍልስፍና ብዝሃነት
የእግዚአብሔርን ቃል በሰው ልጆች ላይ እውነተኛ ስልጣን እንደሌለው እና እራሱን እንደ እውነት የማሳየት ችሎታ እንደሌለው
በአንድነት በክርስትና ላይ ተግዳሮት ሆነዋል።
አደጋዎች
Cont…

2.2.4 ክርስትና ለድህረ ዘመናዊ አደጋዎች የሚሰጠው ምላሽ ምንድን ነው?


ክርስትና ፍፁም እውነት ነው፣ አንጻራዊ አይደለም። እንዲህ ዓይነቱ አቋም ከድህረ
ዘመናዊነት ትዕቢት እና አለመቻቻል ጩኸቶችን ያስነሳል። ነገር ግን፤ እውነት የአመለካከት ወይም
የፍላጎት ጉዳይ ባለመሆኑ፣ በእውነት ሲመረመሩ፣ የድህረ ዘመናዊነት መሠረቶች በፍጥነት
ይፈርሳሉ። በዚህም መሠረት ክርስትና አሳማኝ እውነት መሆኑን ይገልጣል።
በመጀመሪያ፣ ክርስትና ፍጹም እውነት እንዳለ ይናገራል። እንዲያውም ኢየሱስ አንድ ነገር ለማድረግ እንደተላከ
ተናግሯል፡ “ለእውነትም ሊመሰክር” መጥቷል፣ ዮሐንስ 18፥37። ድህረ ዘመናዊነት ምንም እውነት መረጋገጥ የለበትም
ይላል ፣ ግን አቋሙ እራሱን የሚያሸንፍ ነው። ምንም እውነት መረጋገጥ የለበትም የሚለው ሐሳብ ቢያንስ አንድ ፍጹም
እውነት እንዳለ ያረጋግጣል ። ይህ ማለት ድኅረ ዘመናዊነት በተዘዋዋሪ በፍጹም እውነት ያምናል ማለት ነው።
ሁለተኛ፣ ክርስትና፣ በክርስትና እምነት እና በሁሉም እምነቶች መካከል ትርጉም ያለው ልዩነት እንዳለ ይናገራል።
ትርጉም ያለው ልዩነት የለም የሚሉ ሰዎች በትክክል ልዩነት እያደረጉ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል። እውነት ነው
ብለው በሚያምኑበት እና በክርስቲያኑ እውነት የሚናገሩትን ልዩነት ለማሳየት እየሞከሩ መሆኑን ማወቅ ይገባናል።
በመጨረሻም፣ ጳውሎስ ለኢስጦኢኮች እና ለኤፊቆሮስ ፈላስፎች ሲናገር ፤ “ስለዚህ የድንቁርናውን ዘመን አሳልፎ
አሁን ሰዎች ሁሉ በየቦታው ንስሐ እንዲገቡ እግዚአብሔር ለሰው ይናገራል” (ሐዋ. 17፥30) ብሏል። የጳውሎስ
መግለጫ “ይህ ለእኔ እውነት ነው፣ ለእናንተ ግን እውነት ላይሆን ይችላል” የሚል አልነበረም። ይልቁንም፤ እሱ ብቸኛ
እና ሁለንተናዊ ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ነበር። የትኛውም የድህረ ዘመናዊነት አራማጆች ጳውሎስ
ተሳስቷል የሚል እምነትም ሆነ ሀይማኖት ትክክል አይደለም ከሚለው ከራሱ የብዝሃነት ፍልስፍና ጋር እየተጋጨ
መሆኑን ማመን አለበት። አሁንም የድህረ ዘመናዊው ሰው እያንዳንዱ ሃይማኖት እኩል እውነት ነው የሚለውን ከራሱ
አመለካከት ጋር ይጋጫል።
2.3 ሉላቀፋዊነት (Globalization)
• ክርስትናችን ላይ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ እና የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ከሚገዳደሩ ወቅታዊ
ድህረ ዘመናዊነት ካፈራቸው አመለካከቶች አንዱ ሉላቀፋዊነት ነው። ተጽእኖውን
የሚያሳርፈው በተለያዩ መዋቅሮቸ ነው። ሉላቀፋዊነት በሁሉም የዓለም ክፍሎች ላይ
ተጽእኖ የሚያሳድር ድርጊት ነው። በአሁኑ ጊዜ ሉላቀፋዊነት በመረጃ መረቦች አማካይነት
የአለምን ስርአት እየቀረጸ ይገኛል። ቤተ ክርስቲያንም ተልእኮዋ በዚህ እየተጎዳ እና
አባሎችዋን መቆጣጠር እስከማትችል ድረስ ተግዳሮት እየገጠማት ነው።
• ሉልአቀፋዊነት ለክርስቲያኖች ትልቅ እድሎችን ቢሰጥም፣ ተግዳሮቶችንም አምጥቷል።
አማኞችን ለተወዳዳሪ ርዕዮተ ዓለም፣ ለቅይጥነት፣ ለቁሳዊ ነገሮች እና ለሞራል አንጻራዊነት
ያጋልጣል። ማስተዋልን፣ ባህላዊ ትብነትን/ሁሉን ተቀባይነት/፣ ጽኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መሰረትን፣ እና ለክርስቶስ ትምህርቶች እና ተግባራት ታማኝ ለመሆን ቁርጠኝነትን
ይጠይቃል። በአጠቃላይ፣ ግሎባላይዜሽን፣ በክርስትና አውድ ውስጥ፣ ለወንጌል
መስፋፋት፣ ለባህላዊ መስተጋብር እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ለመፍታት እድሎችን
ይሰጣል። አብዛኛው ሰው በሰይጣን የሉላቀፋዊነት ስሪት ውስጥ እንደሚገኝም ማወቅ
አለብን።
Globalization
Cont…
2.3.1 ሉልአቀፋዊነት (Globalization) ትርጉም

• ሉልአቀፋዊነት የማህበረሰቦችን፣ ኢኮኖሚዎችን፣ ባህሎችን እና ስርዓቶችን


በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ትስስር እና ውህደት ያመለክታል። በድንበሮች
ላይ እየጨመረ የመጣውን የሸቀጦች፣ የአገልግሎቶች፣ የመረጃ እና የሃሳቦች
ፍሰት እና የጂኦግራፊያዊ ድንበሮች አስፈላጊነት መቀነስን ያካትታል።
ከክርስትና ጋር በተያያዘ ሉልአቀፋዊነትን ስናስብ፣
በርካታ አዎንታዊ ነገሮች አሉት።

1. የወንጌል ስርጭት፡- ሉልአቀፋዊነት ክርስትና ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንዲስፋፋ አድርጓል።

2.-ባህላዊ መስተጋብር፡- ሉልአቀፋዊነት በተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች መካከል ያለውን መስተጋብር ጨምሯል፣
ይህም ክርስቲያኖች እንዲነጋገሩ፣ ግንኙነት እንዲፈጥሩ እና እምነታቸውን በተለያዩ ሁኔታዎች እንዲካፈሉ እድል
ሰጥቷል።
3. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ልዩነት፡- ሉልአቀፋዊነት የእምነትን ዓለም አቀፋዊ ተፈጥሮ የሚያንፀባርቅ
የተለያየ እና የመድብለ ባህላዊ ክርስቲያናዊ ማህበረሰብን አምጥቷል።
4. ማህበራዊ ፍትህ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች፡- ሉልአቀፋዊነት ከክርስትና ጋር ተያያዥነት ባላቸው እንደ
ድህነት፣ ኢፍትሃዊነት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የአካባቢ ጉዳዮች ባሉ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ብርሃን
ፈንጥቋል።
5. የመረጃ እና ግብአቶች ተደራሽነት፡- ሉልአቀፋዊነት በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ የመረጃ እና የመረጃ
ተደራሽነትን አሻሽሏል።
Globalization
Cont…
2.3.2 የሉላቀፋዊነት አዲሱ የአለም ስርአት በክርስትና ላይ የሚያሳድረው
ተጽእኖ
• አዲሱ የአለም ስርአት የሉልአቀፋዊነት አስተሳሰብ የመጨረሻ ግቡ ነው። አዲሱ የዓለም ሥርዓት
በዓለም ላይ ከዓለም ኃይል ሚዛን ጋር ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ አዲስ የታሪክ ጊዜን የሚያስቀምጥ
የሴራ ንድፈ ሐሳብ የያዘ ነው። ይህ አዲስ የዓለም ሥርዓት በአንዳንዶች ዘንድ በአንድ ዓለም አቀፍ
የአስተዳደር ሥርዓት ዓለምን ለመምራት የታቀዱ የልሂቃን ቡድኖችን ያሳትፋል።
አዲሱ “የሉላቀፋዊነት ዘመን” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አዲስ የዓለም ሥርዓት የተለያዩ የዓለም
መንግሥታትን ሉአላዊ ፍላጎት ለማስወገድ ይሰራል። ይህ የሚሳካው የአንድ ዓለም የፖለቲካ ሥርዓት ወይም
አካል በመዘርጋት ነው። ይህንን ለማሳካት አንዱ መንገድ የአለምን መንግስታት የሚወስኑትን ሁሉንም
መስመሮች እና ድንበሮች በማስወገድ ነው።
• በውጤቱም፣ የሴራ ጠበብት ዓለም በአንድ አገዛዝ ሥር ትሆናለች ብለው ያምናሉ፣ ይህም መንግሥት
ለዓለም አቀፍ ሰላም እንደሚሰጥ፣ ጦርነት እንደማይኖርና ሁሉንም የፖለቲካ አለመረጋጋት
እንደሚያስወግድ ቃል ገብቷል።
Globalization
Cont…
2.3.3 ክርስትና ለሉላቀፋዊነት ያለው ምላሽ

ምንም እንኳን የሰው ልጅ ይህን ህይወት ለመቀበል እና የአእምሮ ሰላም ለማግኘት ተስፋ እንደሚያስፈልገው መግባባት
ቢቻልም ችግሩ ግን የሰው ልጅ ይህን ተስፋ በሚፈልግበት ቦታ ላይ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግልጽ
መልስ ያላቸው ናቸው። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን መንግሥታችንን ጨምሮ በሥልጣን ላይ ያሉትን እንድንታዘዝና
እንድናከብር ታዝዘናል። ነገር ግን፣ ከኢኮኖሚውም ሆነ ከሃይማኖታዊ አተያይ አንፃር፣ እንዲህ ያለው አዲስ የዓለም ሥርዓት
አንዳንድ አስከፊ መዘዞች እንዳሉት በቀላሉ ማየት እንችላለን፣
ዓለማዊም ይሁኑ ሃይማኖታዊ አዲስ የዓለም ሥርዓት እንዲመጣ የሚፈልጉ ሁሉ ጨዋነት የጎደለው መነቃቃት ውስጥ
ናቸው። ሰማያዊው ተስፋ ብቻ ዘላቂ ሰላም እና ደስታን ያመጣል፣ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ምድር ላይ ካለው ሕይወት ጋር
የተያያዙት ነገሮች ከሥቃይ፣ ከመበስበስ፣ ከቁጣው እና ከሞት ጋር የተያያዙት ነገሮች ሁሉ በዚህ ሥጋዊ ሕይወት እንደሚቀጥሉ
በግልጽ ያሳያል፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፥16፣ ዕብራውያን 9፥27።
አዎ ተስፋ ያስፈልጋል፣ ግን የሚያስፈልገን የሰማይ ተስፋ እንጂ የአዲስ አለም ስርአት የውሸት ተስፋ አይደለም።
ለአማኞች ሁሉ አንድ ተስፋ ያለው በሰማይ ብቻ ነው ፣ ዮሐንስ 14፥1-4፣ እዚህ ምድር ላይ አይደለም።
2.4 ግለኝነት (Individualism)

አሁን በተግባር እንደምንገነዘበው የቤተሰብ፣ የቤተ ክርስቲያንና የአገር ሕልውና


ድህረ ዘመናዊ የአስተሳሰብ ዘይቤ በሆነው ግላዊነት አስተሳሰብ ተጽእኖ ውስጥ ወድቋል።
ብዙዎች በግለኛ አመለካከት ተግዳሮት ውስጥ በመሆናቸው ሕብረትን እየጠሉ ወይም
እየሸሹ ነው።
• በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ በዕብራውያን 10፥24-25 ላይ፣ የመጨረሻ ጊዜ ላይ
መሆናችንን አውቀን ለፍቅርና ለመልካም ስራ ለመነቃቃት መፈላለጋችንን እና
መሰብሰባችንን እንዳንተው ይመክረናል።
ነገር ግን አማኞች በግለኝነት ተጽእኖ ውስጥ በመውደቃቸው ለሕብረት ለመተያየት
እየተነቃቁ አይደለም። በዚህ ምክንያት ትዳር እየፈረሰ ነወ፣ ብዙዎች በከፍተኛ የስነ ልቦና
ተጽእኖ ውስጥ ናቸው፣ የክርስቶስን ተልእኮ በሕብረት ለመፈጸም ቤተ ክርስቲያን
እየተቸገረች ነው።
Individualism
Cont…
2.4.1 ግላዊት (Individualism )ትርጉም
ግላዊነት ለአንድ ሰው ጥቅማጥቅሞች ከሰፊው ቡድን ጥቅማጥቅሞች የበለጠ ቅድሚያ ሊሰጠው
እንደሚገባ የሚሟገት የውሳኔ አሰጣጥ አካሄድ ነው። በሌላ አነጋገር ግለኝነት የእያንዳንዱ ሰው ፍላጎት
ከትልቅ ባህል ወይም ቡድን ፍላጎት ይበልጣል ይላል። አንድ ሰው እንደሚጠብቀው፣ መጽሐፍ ቅዱስ
የግለኝነትን ጽንፈኝነት ያወግዛል። ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚናገሩት እያንዳንዱ ሰው ሌሎችን ከራሱ
የበለጠ አስፈላጊ አድርጎ የመቁጠር ግዴታ አለበት። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት የግለሰቡን ዋጋ
በብርቱነት ይናገራሉ።

2.4.2 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግላዊነት ምን ይላል


ክርስትና ግለሰቡን እንደ ልዩ እና ውድ የእግዚአብሔር ፍጥረት አድርጎ ይመለከተዋል። እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር
አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ ዋጋ እና ክብር አለው። ይሁን እንጂ ክርስትና የማህበረሰቡን አስፈላጊነት እና ሌሎችን የማገልገልን
አስፈላጊነት ያጎላል። ክርስቲያኖች ጎረቤቶቻቸውን እንደራሳቸው እንዲወዱ እና የሌሎችን ፍላጎት ከራሳቸው በላይ እንዲያስቡ
ተጠርተዋል። ግለሰቦች የመምረጥ ነፃነት ቢኖራቸውም፣ ክርስትና ግን እነዚህ ምርጫዎች የሌሎችን መልካም ነገር ግምት ውስጥ
በማስገባት በፍቅር፣ በፍትህ እና በምሕረት መርሆች መመራት እንዳለባቸው ያስተምራል። በመጨረሻም፣ ክርስትና ግለሰቡን
በእምነት እና በአንድ ዓላማ የተገናኘ የአንድ ትልቅ ስብስብ አካል አድርጎ ይመለከተዋል።
Individualism
Cont…
በመጨረሻም፣ በግለኝነት እና በቡድን ስብስብነት መካከል ያለው ጦርነት በሰው ልጆች እና
በራሳቸው የኃጢአት ተፈጥሮ መካከል ብቻ እንደሆነ እንመለከታለን። እግዚአብሔርን ፍጹም በሆነ
መንገድ መከተል ከቻልን እና ፍጹም በሆነ አንድነት ብንኖር፣ ለግለሰቡ የሚጠቅመው ለብዙዎችም
ጠቃሚ ሆኖ እናገኘዋለን።
የግለሰቦች ትህትና እና የራስን ጥቅም መስዋዕት ማድረግ ለሌሎች ታላቅ በረከት ያስገኛል።
ለቡድኑ ርህራሄ ማሳየት እና ራስን መስዋዕት ማድረግ የተቸገሩትን ይባርካል፣ ይህም ለሰው ልጅ የላቀ
በረከትን ያስከትላል። እነዚህን ሁለቱ ሃሳቦች በዘላለም ውስጥ ፍጹም ተስማምተው እናያቸዋለን፣
ሁለቱም የተዋጁት ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲስማሙ ብቻ ነው፣ 1 ዮሐንስ 3፥1–
3።
በመሆኑም በቤተሰብ ውስጥ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የግለኝነት ራስ ወዳድነት ለሕይወትና
ለአገልግሎት እንቅፋት እንዳይሆን ማስተማር ይጠበቅብናል።
2.5 የግብረሰዶማዊነት እንቅስቃሴ

አሁን ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ የቤተክርስቲያን ስጋት የሆነና እንዲሁም በከፍተኛ ሁኔታ ዓለምን ለማጥለቅለቅ
የተነሳ በሀያላን ሀገሮች ማለትም በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ መንግስታት የሚደገፍ፤ እንዲሁም ትልቁን
ገንዘብ አበዳሪ ተቋም IMFን ጉልበቱ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለ እርኩሰት ግብረሰዶማዊነት ነው። በአፍሪካ
ሀገራት በአብዛኛው ተቃውሞን ያስተናገደው ይህ እንቅስቃሴ ለጊዜው የማረካትና እግሩን የተከለባት
አፍሪካዊት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ነች፤ እርሷ የግብረሰዶማዊነትን መብት በህገ መንግስቷ ያጸደቀች ብቸኛዋ
የአፍሪካ ሀገር ናት። በኡጋንዳ ግብረሰዶማዊ ሆኖ መገኘት ያስገድላል፣ በካሜሩን ከ6 ወር እስከ 5 ዓመት
እስራትና 350 ዮሮ ያስቀጣል፣ በናይጄርያ የግብረሰዶማዊነትን መብት ዘመቻ የሚያካሂድ ሰው 10 ዓመት
እስራት ይጠብቀዋል።
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 13 ላይ ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ
ተከልክሎአል። ከዚህ የተነሳ በአደባባይ እኔ ጌ ነኝ ( I AM A Gay) ብሎ የሚናገር አይኑር እንጂ። ነገሩ
በብዙ ትምህርት ቤቶች፣ በሕጻናት ማሳደጊያዎች እንዲሁም የጎዳና ተዳዳሪዎች የዚህ ሰለባ እየሆኑ ነው።
በተለያዩ ሁኔታ የሚቀርቡ ዝግጅቶች በሆሊዉድ ፊልሞች፣ በቲክቶኮችና ቀልዶች ነገሩን በዋዛ እንዲመለከቱ
ወጣቶችን የሚያባብል ስራ እየተከናወነ ነው።
የሚቀጥል. . .

ግብረሰዶማዊነት በቅዱስ ቃሉ እንዴት ይታያል?


• ግብረ ሰዶም የሚለው መጠሪያ የተገኘው ከመፅሐፍ
ቅዱስ ነው:: የሰዶም ስራ እንደ ማለት ነው::
በተመሳሳይ ጾታ እርኩሰት ምክንያት እግዚአብሔር
እሳት ከሰማይ በማዝነብ ገለብጦ የፈረደባቸው ከተሞች
መጠሪያ ሰዶምና ገሞራ ናቸው ዘፍ. 19 እና 2ጴጥ.
2፡ 5-6 ተመልከቱ።
የሚቀጥል. . .

• ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና። ዘሌ. 18፡22


• ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፈጽመው
ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። ዘሌ. 20፡13
• ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው
የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው
የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም
በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። ሮሜ 1፡26-
27።
ግብረሰዶማዊነትን በተመለከተ መፍትሔው ምን ይሁን?
• ክርስቲያኖች በዚህ አይነት ኃጢያት ላይ ሊኖረን የሚገባ አቋም ግልጽ መሆን አለበት፤ ነገሩን ከሌሎች የተለየ አድርገን ሰዎቹን
መጸየፍ መናቅና ፍርድን ብቻ መናገር ልክ አይደለም። እግዚአብሔር እንደማንኛውም ኃጢያተኛ ሁሉ ግብረሰዶማውያንንም
ይወዳቸዋል፤ ተጻጽተው ንስሐ ገብተው እንዲመለሱ እንጂ እንዲጠፉ አይፈልግም። ትላንትና በወንጌሉ ሀይል ሰዎችን ከዚህ
እስራት እንደፈታ ሁሉ ዛሬም ነጻ ያወጣል ፦
• “ ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን
የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ
ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ
እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።”
1ቆሮ. 6፡10-11።
• የግብረሰዶማዊነት ኃጢያት ለመንፈሳዊ ሕይወት ውድቀት ብቻ ሳይሆን በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች በስጋቸውም ቢሆን
ለኤችአይቪ፣ ለጤናማ ወሲባዊ ግንኙነት ፍላጐት ማጣት፣ ራስን ለመጥላት፣ ከሰዎች ለመገለልና ለብቸኝነት፣ ለጭንቀትና
ፍርሃት እንዲሁም ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ለዚህ ወቅታዊ ተግዳሮት መፍትሔ
የምንለው ወንጌል ከዚህ ነጻ እንደሚያወጣና ሰዎች ከዚህ አስከፊ ክፋት ሊፈቱ እንደሚችሉ ማመን አለብን፣ በቤተክርስቲያን
ስለዚህ ጉዳይ መናገር ማስተማር መምከር ሀላፊነታችን ሲሆን ወላጆችም ልጆቻችንን ከማን ጋር እንደሚውሉ አለባበሳቸው
እንዴት እንደሆነ መከታተል አለባቸው።
2.6 የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶች
• ቴክኖሎጂ የድህረ ዘመናዊነት አስተሳሰብ ማንጸባረቂያና ማስፋፊያ መሳሪያ ነው። ብዙ ሰዎች የፍጻሜው
ዘመን ሲቃረብ የቴክኖሎጂው እድገት እንደሚኖር ከቅርብ አመታት ወዲህ ሃሳብ አቅርበዋል።
ቴክኖሎጂ በህብረተሰቡ ውስጥ ፈጣን ለውጦችን ሲያመጣ፣ አንዳንድ ሰዎች የለውጡን ፍጥነት
መቋቋም ባለመቻላቸው ወደ ጎን ቀርተዋል። ያም በሰዎች ላይ ጭንቀት እና ግራ መጋባትን ፈጥሯል።
• በቤተ ክርስቲያን ውስጥም ድሕረ ዘመናዊነት እንዲስፋፋ ተጽእኖ ካደረጉ ወቅታዊ ተግዳሮቶች ውስጥ
አንዱ የቴክኖሎጂ መስፋፋት ነው። በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን አለመጠቀም እንደ ኋላቀርነት የሚታይ
ነው። ብዙዎች እግዚአብሔርን በመዝሙር ለማምለክ በመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ውስጥ ከመሆን ይልቅ
የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጽእኖ ውስጥ ወድቀዋል።
• አሁን ባለንበት ዘመን በመረጃ ፍሰቱ ፍጥነት ክርስቲያኖች በቴክኖሎጂ የመረጃ መረቦች አማካይነት
ለወሲብ ፊልሞች (Pornography) ሱሰኛ ሆነዋል ፣ ይህም የቅድስና ሕይወትና የጋብቻ ንጽሕናን
ዋጋ አሳጥቶታል፣ የሞራል እና የስነምግባር ዝቅጠት እያስከተለም ይገኛል።
የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶች
Cont…
2.6.1 ቴክኖሎጂ ለክርስትና ያለው ጉዳት እና ጥቅም
በክርስቲያናዊ እይታ ቴክኖሎጂ ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መሳሪያ ሆኖ ይታያል።
መጽሐፍ ቅዱስ ቴክኖሎጂን በግልጽ አይጠቅስም። ነገር ግን የሰዎች ድርጊት የሚያስከትለውን መዘዝ
ይጠቅሳል።
የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ዘፍጥረት፣ ሰዎች በእግዚአብሔር አምሳል
እንደተፈጠሩና ምድርን የማስተዳደር ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ያስተምራል። የቴክኖሎጂ ስራዎችን ቀላል እና
ቀልጣፋ በማድረግ የሰዎችን ህይወት ለማሻሻል መጠቀም ይቻላል፣ ቴክኖሎጂ ህይወትን የሚያድኑ
ህክምናዎችን ሊሰጥ ይችላል ፣ ቴክኖሎጂ የመገናኛ እና የመረጃ ተደራሽነትን ያሻሽላል ይህም የክርስትናን
መልእክት ለብዙ ተመልካቾች ሊያሰራጭ ይችላል ፣ ቴክኖሎጂ በአደጋ ጊዜ የእርዳታ ጥረቶችን ለማገዝ እና
ድህነትን ለመቅረፍ ይረዳል።
በሌላ በኩል የቴክኖሎጂ ጉዳቶች ስናይ እንደ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች እና የሳይበር ጥቃቶችን የመሳሰሉ
ጉዳቶችን ለማምጣት መጠቀም ይቻላል። ቴክኖሎጂ ሱስ የሚያስይዙ ባህሪያትን ሊፈጥር ይችላል ፣ ይህም
የሰው ልጅ ትርጉም ያለው መስተጋብር እንዲጠፋ ያደርጋል
የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶች
Cont…
2.6.2 ክርስቲያን ቴክኖሎጂን እንዴት ይጠቀም?

ጠቅለል ባለ መልኩ ክርስትና በሃላፊነት እና በስነምግባር ከተጠቀምንበት ቴክኖሎጂ


ጠቃሚ መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ያስተምራል። ሆኖም ግን ሊያስከትሉ የሚችሉትን
አሉታዊ ውጤቶች በመገንዘብ ቴክኖሎጂን እግዚአብሔርን በሚያከብር እና የሌሎችን
ደህንነት በሚደግፍ መንገድ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ብዙ የቅዱሳት መጻህፍት
ምንባቦች በዘመኑ መጨረሻ ስለሚሆነው ነገር ያመለክታሉ። ከሁሉ የሚበልጠው
ምልክት ኢየሱስ በማቴዎስ 24፥14 የተናገረው እና በማቴዎስ 28፥19-20 እንድንሰብክ
ያዘዘን ወንጌል መስበክ ነው።
3 የዘረኝነት እና ብሔርተኝነት ተግዳሮቶች
በአገራችን ያለችውን ቤተ ክርሰቲያን በከፍተኛ ሁኔታ እየከፋፈለ እና
ተልእኮአችንን በጋራ እንዳንወጣ ካደረጉን አስተሳሰብ ተግዳሮቶች ውስጥ
አንዱ ዘረኝነትና ብሔርተኝነት ነው። ይሕ አመለካከት በአገራችን
ክልላዊነትን፣ ትምክህተኝነትን፣ የማንነት ቀውስን፣ እርስ በርስ በጥርጣሬ
መተያየትን፣ አድሎአዊነትን፣ ጥላቻን እና ደም መፋሰስን እያስከተለ
ይገኛል። ቤተ ክርስቲያንም የነዚህ አስተሳሰቦች ሰለባ በመሆን ለብሔር እና
ዘር ጥብቅና እየቆመች እና በከፍተኛ ጥላቻ ጉዳዮች በፍርድ ቤቶች እየታዩ
ያሉበት ሁኔታ አለ። ይህን ወቅታዊ ተግዳሮት ለመስበር ትክክለኛዋ ተቋም
ቤተ ክርስቲያን ስለሆነች ልትነቃና ልታስተምር ይገባታል። በመሆኑም
በዚህ ክፍለሰ የዘረኝነትና የብሔርተኝነት ተግዳሮቶችን እንመለከታለን።
ዘረኝነት
Cont…

3.1 የብሔርተኝነትና ዘረኝነት ትርጉም


ብሔርተኝነት (Ethnicity) የአንድ የተወሰነ ቡድን ወይም የሰዎች ስብስብ እርስ በርስ የሚያገናኝ
ባህላዊ ባህሪያት ያለው አስተሳሰብ ነው ።
ጎሳ እና ዘር ተዛማጅ ጽንሰ-ሀሳቦች ሲሆኑ የብሔር ጽንሰ-ሀሳብ የተመሰረተው በህብረተሰቦች
ባህላዊ ሃሳብ ውስጥ ነው፤ በተለይም አንድ ማህበረሰብ በጋራ እኩል በሚጋሩት ብሔር፣ ጎሳ፣
ሃይማኖታዊ እምነት፣ የጋራ ቋንቋ፣ ወይም ባህላዊ አመጣጥ ውስጥ ተለይቶ ይታወቃል,።
ዘር (Race) ግን በተለየ መንገድ ስነ ሕይወታዊ (Biological) ባህሪ ያለው የቆዳ ቀለም ወይም
የፊት ባህሪያት ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብ ነው። ብሔር እውነተኛ ወይም ምናባዊ ታሪካዊ ትስስርን
ለማረጋገጥም የሚያገለግል ቃል ነው።
ዘረኝነት
Cont…
3.2 የብሔር ተኮር ፣ ዘር ተኮር እና ጎሳ ተኮር ጽንፈኝነት
 ብሄር ተኮርነት የአንድ ጎሳ ቡድን ከሁሉም የላቀ ነው ብሎ ማመን እና ሁሉም ሌሎች ብሄረሰቦች ከራሳቸው ጋር በተያያዙ መልኩ
መመዘን አለባቸው በሚል አመለካከት ያደገ አስተሳሰብ ነው። ወደ ከፍተኛ ኩራት እና ለሌሎች ግድየለሽነት የሚመራ የእምነት ስርዓት
ነው። ዘር ብዙ ጊዜ የጎሳ አካል ስለሆነ፣ በዚህ ትስስር ብሔር ተኮርነት በአብዛኛው ከዘረኝነት ጋር የሚያያዝ ሆኖ ይታያል።
መጽሐፍ ቅዱስ ብሔር ተኮር ጽንፈኝነት ኃጢአት ነው ይላል። ሁሉም ወንዶችና ሴቶች በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥረዋል፣ ዘፍ 1፥26–
27፤ 9፥6 ፣ ምንም እንኳን ያ ምስል በኃጢአት የተበላሸ ቢሆንም። እግዚአብሔር ለማንም አያዳላም፣ ዘዳ 10፡17፤ የሐዋርያት ሥራ
10፥34። ኢየሱስ ሕይወቱን ለአንድ ዘር፣ ባህል ወይም ነገድ አሳልፎ አልሰጠም፣ ነገር ግን በሞቱ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ
ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ዋጃቸው፣ ራዕይ 5፥9። ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስ አይሁድንም፣ አሕዛብንም፣ ዓለምን
ሁሉ ለማዳን እንደ መጣ ይነግሩናል፣ ገላትያ 3፡28፣ ቆላስይስ 3፡11።
 ጎሰኝነት ከአቃፊነት (Inclusiveness) ይልቅ ለአግላይነት (Exclusiveness) ምክንያት ሲፈልግ ወይም የበላይነትን ለመያዝ
ሲታገል ክርስትና አደጋ ውስጥ ይወድቃል። አብያተ ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ቤተ እምነቶች አንዳንድ ጊዜ በጎሰኝነት ይከሰሳሉ።
ለቡድን ታማኝ መሆን ምንም ስህተት የለበትም፣ ነገር ግን ከፍተኛ ታማኝነታችን ለክርስቶስ እና ለተጻፈው ቃል መሆን አለበት።
በተለያዩ የክርስቲያን ቡድኖች መካከል የአስተምህሮ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ይጠበቃል፣ ነገር ግን የትኛውም ልዩነት ወደ መንፈሳዊ
ኩራት ሊመራ አይገባም።
ዘረኝነት
Cont…
3.3 ለሀገር ታማኝ መሆንና መሰጠት (Patriotism)
ብዙ ሰዎች ለትውልድ አገራቸው እና ለተሰደዱባቸው አገሮች የተወሰነ ታማኝነት ይሰማቸዋል። የትውልድ አገርን መውደድ
ተፈጥሯዊ ነው፣ በመሆኑም በዚህ መልኩ ስናይ አገር ወዳድ ብሔርተኝነት (Nationalism) በራሱ ምንም ችግር የለውም። መጽሐፍ
ቅዱስ ስለ አገር ወዳድ ብሔርተኝነት (Nationalism) ጥሩም ሆነ መጥፎ ምሳሌዎችን ይሰጣል። የጥንቷ እስራኤል የብሔር
ብሔረሰቦች ባሕል ነበራት፣ እናም የእግዚአብሔር ሐሳብም ነበር፣ መዝሙር 137፥4–6 ። አብራምን ቤቱን ጥሎ እግዚአብሔር
ወደሚያሳየው ምድር እንዲሄድ ሲጠራው፣ እግዚአብሔር ለአምላክገዝ ሕዝብ መሠረት እየጣለ ነበር፣ ዘፍጥረት 12፥1-4።
3.4 የዘረኝነት እና የብሔር ትምክህተኝነት አስከትሎቱ
ብሔር ተኮር ወይም ዘረኝነት ሥነ ምግባር የጎደለው ቢሆንም፣ የብሔር ማንነትን ማረጋገጥ ግን ኃጢአት ላይሆን ይችላል።
ብዙዎች ግን የብሔር ማንነት ጠንከር ያለ ስሜት ማግኘቱ የብሔራዊ ማንነት ስሜትን ሊጎዳ ይችላል እናም በተቃራኒው። ሌሎች
ደግሞ የአንዱ ትርጉም ያለው እና ጤናማ ማረጋገጫ ሌላውን አይጎዳውም ወይም አይቀንስም ብለው ይከራከራሉ። በሌላ አገላለጽ፣
አንዳንዶች ክልላዊ ወይም የብሔር ማንነቶችን ከማስፋፋት ይልቅ ጠንካራ ብሔራዊ ማንነትን ማሳደግ ጥሩ አንድነትን ያመጣል ብለው
ሲያስቡ፣ ሌሎች ደግሞ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን የባህል፣ የሃይማኖትና የቋንቋ መገለጫዎችን ማፈን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ
የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ይከራከራሉ። እነሱን መፍቀድ እንደ ክርስቲያኖች ከብሔር ተኮር ወይም ከዘረኝነት የፀዳ አቋም
ለማዳበር የትኛው አካሄድ እንደሚረዳን መጠየቅ አለብን።
ዘረኝነት
Cont…
3.4.1 ጽርንፈኛነት እኔነት (Egoism) ያስከትላል
የብሔር ብሔረሰቦች እና የዘመኑ ሥነ-መለኮቶች የሚዳበሩት በራስ ወዳድነት ወይም እኔነት እይታ ነው። እኔነት (Egoism)
ከልክ ያለፈ በራስ የመተማመን ስሜት የሚመራ፣ ከልክ ለራስ ትኩረት መስጠት ነው። እኔነት (Egoism) በራስ ላይ መጠመድ ነው
፣ነገር ግን በራስ የመተማመን ስሜት ላይኖረው ይችላል። ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ አንጻር የሰው ልጅ ራስ ወዳድ የመሆን ዝንባሌ
ምንም አያስደንቅም። እሱም መጽሐፍ ቅዱስ የሚቃወመው አስተሳሰብ ነው።
የትምክህተኝነት መሰረቱ እኔነት ነው። እኔነት (Egoism) በመጨረሻ የሚመራው በትዕቢት እና እራስን ከፍተኛ ትኩረት
ሊሰጠው እንደሚገባ በማሰብ ወይም ሙሉ በሙሉ ራስን በቅነት ሲሆን ይህም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ የሆነ አመለካካት ነው።

3.4.2 ብሔርተኝናትና ዘረኝነት ልዩነትን ማስፋቱ


ልዩነት በመሠረቱ ልዩነት ነው። ልዩነት ማለት በሰዎች መካከል ያለው ልዩነት በዘር፣ በባህል፣ በፆታ ላይ የተመሰረተ፣ ወዘተ
ልዩነት ነው። ልዩነትን የፈጠረው የእግዚአብሔር ተግባር በባቤል ግንብ ላይ ተፈጽሟል፣ ዘፍ 11፥9። ከዚያ ጀምሮ የሰው ልጅ
በምድር ላይ ተሰራጭቷል በመሆኑም አንድ ቋንቋ ያላቸው ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው የመኖር እድል አግኝተዋል። ከጊዜ በኋላ
ባህሎች፣ ዘሮች እና ክልላዊ ዘዬዎች ብቅ አሉ እና አሁን የምናውቀውን ልዩነት አስከትሏል።
ዘረኝነት
Cont…
3.5 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ብሔርተኝነትና ዘረኝነት
አያያዝ ምን ያስተምራል?
መጽሐፍ ቅዱስ ብሔርተኝነትን የሚያስተምረው በክርስቶስ ያሉ አማኞች የሚኖሩበት ብሔር ምንም ይሁን ምን የአገሪቱን ሕግ እንዲታዘዙ
ነው። በዚህ ምድር ላይ መጻተኞች ሳለን መንግስታችንን፣ ሀገሮቻችንን እና ማህበረሰቦቻችንን በተቻለ መጠን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሳንጥስ
መደገፍ አለብን፣ ሐዋ. 5፥29። እስራኤላውያን ባለመታዘዛቸው ወደ ባቢሎን በግዞት በተወሰዱ ጊዜ፣ በግዞት የነበሩት ዕብራውያን ለትውልድ
አገራቸው ምንም ዓይነት ብሔራዊ ስሜት ቢሰማቸ፣ ሕይወታቸውን በባቢሎን መምራትና ለሚኖሩበት ሕዝብ ሰላም መጸለይ ነበረባቸው፣
ኤርምያስ 29፥7። የተወሰነ ደረጃ ያለው ብሔርተኝነት ስህተት አይደለም።
እንዲያውም እኛ በምንኖርበት ማህበረሰብ ዘንድ ጥሩ የምንሆንበት አንዱ መንገድ ነው። ወንድና ሴት ልጆቻችንን ማኅበረሰባችንን ከክፋት
እንዲከላከሉልን፣ ምሳሌ 24፥11 ፣ አገር እንድትለማ በበጎ ወገንተኝነት ግብራችንን ለመክፈል፣ ማር. 12፥17 እና በውስጡ የተከበረውን ማክበር
እንድንችል ሮሜ 13፥7 ጥሩ እሴት ለመገንባት በጣም ጠቃሚ ነው። ክርስቲያኖች ግን ምድራዊ ብሔርተኝነት ጊዜያዊ መሆኑን ሁሌ ማስታወስ
አለባቸው፣ ሰማያዊ ዜግነት ለዘላለም ነው። ትልቁ ታማኝነታችን እና ዋና ግዴታዎቻችን ለማያልፍ ለዚያ ሰማያዊ መንግስት ናቸው፣ ዳንኤል
2፥44፤ 6፥26፤ 7፥14፤ ሉቃስ 1፥33።
ብሔርተኝነት ለክርስቶስ እና ለመንግሥቱ ያለንን የመጀመሪያ ታማኝነት እንዲያበላሽብን ስንፈቅድ እንሳሳታለን። በእግዚአብሔር ቤተሰብ
ውስጥ ዳግመኛ የተወለዱት ሁሉ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ናቸው፣ ፊልጵስዩስ 3፥20።
3.6 ብሔርተኝነትና ዘረኝነትን የማስወገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ

3.6.1 የኢየሱስነሰ ምሳሌነት መከተል


ፊልጵስዩስ 2፥1-11 ስለ እኔነት የሚናገር አንዱ ክፍል ነው። ቁጥር 3–4 ላይ እርሱ አምላክ
ቢሆንም ራሱን ዝቅ አድርጎ የሰውን ሕይወት በመምራት በእኛ ምትክ በሞተልን በኢየሱስ ክርስቶስ
ምሳሌነት ላይ ተመስርተን የሌሎችን ጥቅም መመልከት አለብን።

ትህትና ማለት ራስን ማዋረድ ወይም በራስ መተማመን ማጣት አይደለም። ትሑት መሆን ማለት
የራሳችንን ፍላጎት ችላ ማለት ወይም የራሳችንን ድንበር አንጠብቅም ማለት አይደለም። ይልቁንም
ትሕትና ስለ ራሳችን ትክክለኛ ትርጉም መስጠት ማለት ነው። እኛ ለራሳችን አንጨነቅም፣ ይልቁንም
የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት እንጨነቃለን ማለትም ነው። በመሆኑም ለሌሎች ጥቅም ሲባል የራሳችንን
ምርጫ ለመሠዋት ፈቃደኞች ነን ማለት ነው።
ዘረኝነትን ማስወገድ Cont…

3.6.2 ራስን ማገልገል ከሁሉ የላቀ ግብ እንዳልሆነ መገንዘብ


በዋነኛነት በትዕቢት ለሚነሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም የእግዚአብሔር ክብር እንደጎደላቸው ያስታውሰናል፣ ሮሜ 3፥23።
እያንዳንዳችን ኃጢአተኞች ነን፣ የኃጢአት ባሪያዎች ነበርን፣ በበደላችን ሙታን ነበርን፣ ስለዚህም አዳኝ የሚያስፈልገን ነን፣
ዮሐንስ 8፥34፤ ሮሜ 6፥15–23፣ ኤፌሶን 2፥1–5።
ህልውናችንን የሚያጸድቅ እና ለህይወታችን ትርጉም የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እኔነት (Egoism) በመጨረሻ
ሰዎችን ባዶ ያደርጋል።

3.6.3 ማምለክ ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ መሆኑን መገንዘብ


መመለክ ያለበት እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ እሱ በጣም አስፈላጊ ነው፣ የእርሱን ቦታ ልንወስድ በፍፁም አንችልም። ወይ
ራሳችንን ከፍ አድርገን በማሰብ የሁሉም ትኩረት ማዕከል እንድንሆን ይገባናል ብለን እናምናለን ወይም ደግሞ በሁሉም ሰው
እንዳንተማመን በሚያደርገን በቆሰለ ሁኔታ ውስጥ በመኖር እንሰቃያለን። እኔነት (Egoism) የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ
ነው። ነገር ግን ከኃጢአት የተወለደ ጭንቀት ነው። ትምክህተኝነትን ውድቅ በማድረግ፣ ክርስቲያኖች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር
እንዲሰጡ ተጠርተዋል። ከሰጠን ፍቅር እኛ ሌሎችን መውደድ አለብን፣ ዮሐንስ 13፥34–35። እኛ የተጠራነው ሌሎችን
ከራሳችን በላይ እንድናደርግ፣ ሌሎች ሰዎችን እንድንንከባከብ እና ፍላጎቶቻቸውን እንድናሟላ ነው።
ዘረኝነትን ማስወገድ Cont…

3.6.4 ልዩነትን በማክበር አንድነትን መጠበቅ

እንደ ዘር፣ ባህሪ እና ባህል ያሉ የሰዎች ልዩነቶችን ማከበር፣ መታገስ እና በክርስቶስ አንድ የመሆን
ግባችን ውስጥ መካተት አለባቸው፣ ዮሐንስ 17፥20–23። ነገር ግን፣ ልዩነት ወደ ጣዖትነት ሲቀየር፣
ጌታን ኢየሱስን ሳይሆን ራሳችንን እናሳያለን። እያንዳንዱ ልዩነት እንደ ቅዱስ ሲቆጠር፣ ራስ ወዳድነት
ገዥ ይሆናል በመሆኑም ፤ አንድነት ለግለሰብ ግላዊ ምርጫ መስዋዕት ይሆናል። ከአንድነት ይልቅ የግል
ምርጫችንን ከፍ ስናደርግ ከይቅር ባይነት እና አቃፊነት ይልቅ እራስበቅነት እና ኩሩ እንሆናለን፣ ኤፌሶን
4፥32 ፣ ፊልጵስዩስ 2፥4።
4 የሐሰት ትምህርት እና የሐሰት አሰራር
• በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከየትኛውም ዘመን ይልቅ ይህ ያለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ባለ
አእምሮ የእግዚአብሔር የሆነውን እውነተኛ አስተምህሮ በቅዱስ ቃሉ በመፈተሽ መቀበል የተዘነጋበት
ዘመን ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች፡፡ በእውነተኛ እና በደንብ በቅዱስ ቃሉ ተፈትሾ በተሰራ
አስተምህሮ እና በክርስቶስ ፍቅር በመቃጠል ብቻ በእውነት ላይ ያልተመሠረተ የተልእኮ አፈጻጸም
ሚዛኑን መጠበቅ እጅግ ያስፈልጋል። ቃሉ ላይ ትኩረት የማድረግ አተያይ አንዳንድ ጊዜ ጠባብ በሆነ
እይታ ውጫዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ስርአቶች ላይ ብቻ በማተኮር የጸጋን የመለወጥ ተፈጥሮ እና
የመንፈስ ቅዱስን ውስጣዊ አሰራርን ቤተ ክርስቲያን ችላ እንድትል ሲያደርጋት ይታያል ።
• በሌላ በኩል ደግሞ በቃሉ የማይመራ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ልምምድ ላይ የተመሠረተ የመንፈሳዊነት
አተያይ አንዳንድ ጊዜ በቃሉ ወደ ማይደገፍ ስሜታዊነት ሊመራ ይችላል። ይህም በቅዱሳት መጻሕፍት
ተጨባጭ እውነት ላይ ጠንካራ መሰረት የሌለው እና ወደ አስተምህሮ ስህተቶች ሊያመራ ይችላል።
በዚህም መሠረት በአንዱ አመለካከት ላይ ከመጠን በላይ ማጉላት የሁለቱም አካሄዶችን ጥንካሬዎች
ሙሉ በሙሉ ያላካተተ ሚዛናዊ ያልሆነ እምነት ያስከትላል።
4.1 የሐሰት ትምህርት ወይም ኑፋቄ

• የሐሰት ትምህርት ወይም ኑፋቄ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን


እያጠቃ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ በ 1 ጢሞ 3፥15-16 ሲገልጽ፣ የሐሰት መምህራን
በትምህርታቸው ብዙዎችን በበረዙበት የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያንንን በእውነት መገለጥ ከሐሰት
ትምህርት መምህራን መጠበቅ እንደሚገባው ለጢሞቴዎስ የአደራ መመሪያ ሰጥቷል።
• ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህንን አደራ ለጢሞቴዎስ ሲሰጥ በዘመኑ የነበረውን የኖስትሲዝም እና
የአይሁድ ሕግ ትምህርትን ባሕሪ በመግለጽ ነበር።
• በኛም ዘመን የተለያየ ገጽታ ያላቸው የሐሰት ትምህርቶች እና የሐሰት አስተማሪዎች የቤተ
ክርስቲያንን ጤናማ አስተምህሮ እየበረዙ ይገኛሉ። በዚህ ትምህርትም ላይ የኑፋቄ አራማጆችና
የመናፍቃንን ትርጉም እና የአገራችንን ቤተ ክርስቲያን እየጎዱ ያሉትን ወቅታዊ ኑፋቄዎች ተግዳሮት
እንመለከታለን።
4.2 የኑፋቄና መናፍቅነት ትርጉም

• መጽሐፍ ቅዱሳችን ስለ ኑፋቄና ስለ መናፍቅነት በግልጽ ይናገራል። በዚህም መሠረት የሁለቱንም


ትርጉም እንመለከታለን።ኑፋቄ ማለት ከእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ውጪ የሆነ
ቤተ ክርስቲያንን ከእውነት የሚያስወጣ ማንኛውም የሐሰት ትምህርት ማለት ነው።
• በሌላ በኩል ደግሞ ኑፋቄን ወይም የሐሰት ትምህርትን ስለሚያስፋፉ ግለሰቦችም ተጠቅሷል።
የሐሰት ትምህርትን ወይም ኑፋቄን የሚያስፋፋ ግለሰብ ደግሞ መናፍቅ ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ
በቲቶ 3፥10-11 ላይ በተለያዩ የትርጉም መጽሐፍት ስለ መናፍቃን ሲገልጽ “ከፋፋይ”፣
“አስጨናቂ ሰው” እና “መከፋፈልን የሚያነሳሳ ሰው” በማለት ትርጉም ይሰጡታል።
4.3 ስለ ኑፋቄና መናፍቃን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያ

• በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሲወጣ ትክክለኛው ምላሽ በመጀመሪያ እሱን
ለማረም መሞከር ሲሆን ፣ ነገር ግን ከሁለት ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆነ ከእሱ ጋር
ምንም ግንኙነት እንዳይኖር ከቅዱሳን ሕብረት ማግለል እንደሚገባ ይነግረናል። በዮሐ. 17፥22-23
መሠረት የክርስቶስ እውነት አማኞችን አንድ ያደርጋል ነገር ግን ፣ መናፍቅ በባህሪው ከእውነት ጋር በሰላም
አብሮ መኖር አይችልም። እንዲሁም በስደት ውስጥ በተለያየ ቦታ ተበትነው ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት
በሐሰት ትምህርታቸው እያጠቁ ስላሉ መናፍቃን በ2 ጴጥ 2፥1 ሐዋሪያው ጴጥሮስ ሲያስጠነቅቅ፣ የዋጃቸወን
ጌታ የካዱና በፍጥነት የሚዛመት ኑፋቄን በቅዱሳን ሕብረት መካከል ሆነው አሹልከው የሚያስገቡ ሐሰተኛ
ነቢያትና መምህራን እንዳሉ ቅዱሳንን አስጠንቅቋል። ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው መናፍቅነት የኢየሱስን
ትምህርት የሚክድ ማንኛውም ነገር ነው።
• እነዚህ ጥቅሶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን መናፍቅነት የሚገልጹትን ሁለቱንም ገጽታዎች ማለትም
እግዚአብሔር የሰጠውን ትምህርት መካድ እና የፈጠረውን አካል መከፋፈልን የሚዳስሱ ናቸው።
4.4 ወቅታዊ የኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያንን እየጎዱ ያሉ ኑፋቄዎች

• የከርስቶስ አካል ከኑፋቄና ከመናፍቃን እንዴት እንደሚጠበቁ ማሰብ በጣም አስፈላጊ ነው።
በፊልጵስዩስ 2፥2-3 ከመናፍቅነት ስለ መጠበቅ ጥሩ መነሻ ነጥብ ሲሆን ራሳችንን ለእግዚአብሔር
ቃል ስልጣን ስናስገዛ እና እርስ በርሳችን በፍቅር እና በመከባበር ስንነጋገር መለያየት እና
መናፍቅነት ይቀንሳል።
• ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአገራችንን ቤተ ክርስቲያናት እየከፋፈሉ ያሉ የሐሰት አስተማሪዎች
(መናፍቃን) በፍቅርና በመከባበር በመነጋገር እውነተኛውን ትምህርት ከማጽናት ይልቅ
የክርስቶስን አካል ጤንነት በሐሰት ኑፋቄ እየበከሉና በተለይም አዲሱን ትውልድ ከጤናማ
አስተምህሮ እና ልምምድ እንዲያፈነግጥ እየተጉ ይገኛሉ።
4.4.1 የካልቪን ትምሕርት

ካልቪኒዝም፣ የተሐድሶ ሥነ-መለኮት በመባልም የሚታወቀው፣


በተጽእኖ ፈጣሪው የፕሮቴስታንት የሃይማኖት ምሑር ጆን ካልቪን (1509-
1564) ስም የተሰየመ ሥነ-መለኮታዊ ሥርዓት ነው። በሁሉም የሕይወት
ዘርፎች በተለይም በመዳን ጉዳዮች የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት ያጎላል።
የካልቪኒዝም አንዳንድ ቁልፍ መርሆዎች እንደሚከተለው ተገልጸዋል።
አጠቃላይ ብልሹነት፡-
ቅድመ ሁኔታ የሌለው ምርጫ፡-
የተወሰነ የኃጢያት ክፍያ፡-
የማይታለፍ ጸጋ፡-
የቅዱሳን ጽናት፡-
1. አጠቃላይ ብልሹነት፡- ካልቪኒዝም በውድቀት ምክንያት የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ተበላሽቶ ራሱን ማዳን ወይም
እግዚአብሔርን በራሱ መምረጥ እንደማይችል ያስተምራል። ይህ ትምህርት በድነት ውስጥ መለኮታዊ ጣልቃገብነትን
አስፈላጊነት ያጎላል።
2. ቅድመ ሁኔታ የሌለው ምርጫ፡- ካልቪኒዝም እግዚአብሔር በሉዓላዊ ፍቃዱ የተወሰኑ ግለሰቦችን ለድነት ይመርጣል፣
ምንም ዓይነት ብቃት ወይም ከሰዎች ምላሽ ላይ በመመስረት ሳይሆን በራሱ ዓላማ እና ፀጋ ብቻ እንደሆነ ይናገራል።
3. የተወሰነ የኃጢያት ክፍያ፡- ይህ አስተምህሮ፣ አንዳንድ ጊዜ ልዩ ቤዛነት እየተባለ የሚጠራው የኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል
ላይ የከፈለው የመስዋዕትነት ሞት ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ የተመረጡትን ወይም በእግዚአብሔር የተመረጡትን ግለሰቦችን
ብቻ ለማዳን ታስቦ እንደሆነ ይናገራል።
4. የማይታለፍ ጸጋ፡- ካልቪኒዝም እግዚአብሔር የማዳን ጸጋውን ለግለሰብ ለማራዘም ሲመርጥ የማይታለፍ እና ውጤታማ
እንደሆነ ያስተምራል። የእግዚአብሔር ጸጋ በመጨረሻ የሰውን ተቃውሞ አሸንፎ የተመረጠውን ሰው ከእርሱ ጋር ወደ ማዳን
ግንኙነት ይስባል።
5. የቅዱሳን ጽናት፡- “አንድ ጊዜ የዳነ ሁልጊዜም የዳነ” በመባል የሚታወቀው ይህ ትምህርት እግዚአብሔር የመረጣቸውና
ያዳናቸው እስከ መጨረሻው ድረስ በእምነት እንደሚጸኑ ይናገራል። እውነተኛ አማኞች መዳናቸውን ሊያጡ አይችሉም።
ካልቪኒዝም በፕሮቴስታንት ሥነ-መለኮት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን የተለያዩ የተሐድሶ እና
የፕሪስባይቴሪያን አብያተ ክርስቲያናት እምነትን ቀርጿል። እሱም የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት፣ የሰውን
ርኩሰት፣ እና የእግዚአብሔር ጸጋ በድነት ውስጥ ያለውን ፍፁም አስፈላጊነት ያጎላል። እነዚህ እምነቶች
ካልቪኒስቶች የእግዚአብሔርን ሥራ በዓለም እና በክርስቲያናዊ ሕይወት እንዴት እንደተረዱት ሥነ-
መለኮታዊ እና ተግባራዊ አንድምታ አላቸው።
በዚህ የካልቪኒዝም ትምህርት መሠረት ማስተዋል የምንችለው የእግዚአብሔር ጸጋና
ሉአላዊ ፈቃድ ከአማኙ ፈቃድ በላይ ከፍተኛ ቦታ የያዘ በመሆኑ አማኞች ደህንነታቸውንና ሌሎች
መንፈሳዊ ልምምዶችን ከራሳቸው የሚጠበቀውን ድርሻ በመዘንጋት በእግዚአብሔር ላይ ማሳበብ
እንዲለምዱ ያደርጋል። ይህንን ትምህርት በመለጠጥ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የሚያስተምሩ የሐሰት
መምህራን የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ እያበላሸ ይገኛል። በተለይም በእግዚአብሔር ሉአላዊነት እና ጸጋን
ለጥጦ ማስተማር አዲሱን ተውልድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወዳልሆነ እምነትና ልምምድ እየመራ ይገኛል።
ከዚህ በመቀጠል የካልቪኒዝምን የተለጠጠ ገጽታ ግንዛቤን ለመፍጠር እንደሚከተለው እንመለከታለን።
4.4.2 ሃይፐር-ካልቪኒዝም ወይም ሐይፐር ግሬስ አስተምህሮ
• ሃይፐር ካልቪኒዝም ወይም ሃይፐር ግሬስ የሚሉት ቃላት የእንግሊዝኛ ቃላት ሲሆኑ በአማርኛ አቻ ፍቺያቸው የተለጠጠ
የካልቪኒዝም ወይም ልዕለ-ጸጋ የሚል ትርጉም አላቸው። ሃይፐር-ካልቪኒዝም ማለት እግዚአብሔር የተመረጡትን
በሉዓላዊ ፈቃዱ እንደሚያድናቸው ማመን ነው። ድነት የሚገኘው አንድ ሰው ወንጌል ሳይመስከርለት፣ ስብከት
ሳይሰበክለት በእግዚአብሔር ሉአላዊ ጸጋ ብቻ ነው የሚል ጽንፈኛ ትምህርት ነው። በዚህም መሠረት ሃይፐር-ካልቪኒስት
የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት አጽንዖት በመስጠት የሰውን በድነት ሥራ ውስጥ ያለውን ድርሻ አሳንሶ ያሳያል። የሰውን
በድነት ስራ ውስጥ ያለውን ድርሻ ስንል እንደ ንስሐ እና ኃጢአት መናዘዝ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ ትምህርቶችን የሚያገል
ጽንፈኛ ትምህርት መሆኑን ለመግለጽ ነው።
• ሃይፐር ካልቪኒዝም ወይም የተለጠጠ የካልቪን አስተምህሮ በአሁኑ ወቅት በአገራችን በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ
ፈጣሪነት በመጠቀም ትውልዱን ከእውነተኛው አስተምህሮ እንዲያፈነግጡ እያደረገ ያለ የአስተምህሮ ተግዳሮት እየሆነ
ይገኛል። አንዳንድ አገልጋዮችም የዚህ ትምህርት ሰለባ መሆናቸውን እያየንም ነው። በዚህ ትምህርት ተጽእኖ ውስጥ የገቡ
ወጣቶቻችን የቅድስና ሕይወት እያሽቆለቆለም ይገኛል። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ይህንን ትምህርት በመለየት
በማስተማር ትውልዱን የመጠበቅ ኃላፊነቷን ልትወጣ ይገባ ዘንድ እንደ ወቅታዊ የሐሰት ትምህርት ተግዳሮት እዚህ
ተነስቷል።
የሃይፐር-ካልቪኒዝም ግልጽ የሆነ ስህተት
ለጠፉት ወንጌል የመስበክ ፍላጎትን የሚገታ መሆኑ ነው።
አብዛኛዎቹ የሃይፐር-ካልቪኒዝም ሥነ-መለኮትን የያዙ አብያተ ክርስቲያናት ወይም ቤተ እምነቶች የሰው
መዳን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው የሚል፣ ክርስቲያናዊ ኃላፊነትን የመወጣት
ቅዝቃዜ ተለይተው ይታወቃሉ። እግዚአብሔር ለጠፉት ያለው ፍቅር ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ ነገር ግን
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የተለጠጠ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት አረዳድ በቅድመ ውሳኔው
(Predestination) እና የተመረጡት በእሱ ሉአላዊና ሊቋቋሙት በማይችሉት ጸጋ (Irrisistable grace)
የዳኑትን ብቻ መምረጡ እና ባለመመረጣቸው ለጠፉት ያለው ቁጣው የሃይፐር ካልቪኒስት ዋና እና
መሠረታዊ ወንጌል ነው። ሲጠቃለል የሃይፐር-ካልቪኒስት ወንጌል የእግዚአብሔር የተመረጡትን ማዳን እና
የጠፉትን መኮነን መግለጫ ነው። በዚህም መሠረት ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ቅድመ ውሳኔ ሕይወትና ሞት
የሚመደብባቸው ከሆነ ወንጌልን ማወጅ አያስፈልግም የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አመለካከት ብዙዎችን
መርቷል።
መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ እንደሚያስተምረን እግዚአብሔር የአለም ሁሉ ሉዓላዊ ገዥ ነው ዳንኤል 4፥34-35 ፣
ይህም የሰዎችን መዳን ይጨምራል ኤፌሶን 1፥3-12 ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት፣ መጽሐፍ ቅዱስ
የጠፉትን ለማዳን ያነሳሳው እርሱ ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር እንደሆነ ያስተምራል ኤፌሶን 1፥4-5፣ ዮሐንስ 3፥16፣ 1
ዮሐንስ 4፥9-10። በተጨማሪም እግዚአብሔር የጠፉትን የማዳን ዘዴ ለሁሉም ያለ ልዩነት በሚታወጅ የድነት
ወንጌል አዋጅ እንደሆነ ያስተምራል። ምክንያቱም እምነት ቃሉን ከመስማት እና ከመቀበል ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው
፣ ሮሜ 10፥14-15። የክርስቶስ አምባሳደሮች እንደመሆናችን መጠን ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁ
"መለመን" አለብን 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20-21።
የሃይፐር ካልቪኒዝም ወይም ሐይፐር ግሬስ አስተማሪዎች አማኝ
ሐጢአቱን እንዲናዘዝ ፈጽሞ አያስፈልግም ይላሉ።
ኃጢአት፣ ያለፈው፣ አሁን ያለው እና ወደፊት የሚመጣው፣ አስቀድሞ የተሰረየለት መሆኑን
ያረጋግጣሉ። አንዳንድ አገልጋዮችም የዚህ ሐሰት ትምህርት ሰለባ በመሆን በጸጋና በእውነት መሐል
ያለውን ሚዛን ያልጠበቀ ትምህርት ሳንመረምር እያስተማርን እንገኛለን። በመሆኑም ከዚህ የስህተት
ትምህርት ቅዱሳንን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ የትምህርቱን ይዘትና ባህሪውን መግለጽና ግንዛቤ
መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ አያጠያይቅም ። የከፍተኛ ጸጋ ትምህርት፣ እግዚአብሔር ወደ እኛ
ሲመለከት፣ የሚያየው ቅዱስና ጻድቅ ሕዝብ ብቻ እንደሆነ ይናገራል። የከፍተኛ ጸጋ ትምህርት
መደምደሚያ እኛ ከሕግ በታች እንዳልሆንን በኢየሱስ ትምህርት ተገልጦልናል በመሆኑም አማኞች
ለኃጢአታቸው ተጠያቂ እንደማይሆኑ ፣ እና በዚህም የማይስማማ ማንኛውም ሰው ፈሪሳዊ የህግ ሰው
ነው በማለት ይገልፃሉ። በአጭሩ፣ የጸጋ አስተማሪዎች የአምላካችንን ጸጋ ለራሳቸው ፈቃድ
ያጣምማሉ።
ሐይፐር ካልቪኒዝም ወይመሰ የልእለ ጸጋ ትምህርት የቃሉን ስልጣን እና
አማኞችን የመለወጥ ኃይል ይክዳል።

የከፍተኛ ጸጋ አስተምህሮ ሰባኪዎች ብሉይ ኪዳንን እና አሥርቱን ትእዛዛት ለአዲስ ኪዳን


አማኞች የማይጠቅሙ ናቸው በማለት ይቀንሳሉ። እንዲያውም ኢየሱስ ከትንሣኤው በፊት
የተናገራቸው ቃላት የብሉይ ኪዳን አካል እንደሆኑ እና እንደገና ለተወለዱ አማኞች እንደማይተገበሩ
ያስተምራሉ። ግን ይህ እውነት ነውን? በማርቆስ 13፥31 ኢየሱስ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን
አያልፍም” ብሏል። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት አብ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ፣ “ሁሉን
የሚያስተምራችሁ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል” በማለት ቃል ገብቷል ፣ ዮሐንስ 14፥26።
የኢየሱስ ቃሎች ለአማኞች የማይሠሩ ከሆነ ለምን እነርሱን ማስታወስ ያስፈልገናል?
የልእለ ፀጋ (Hyper grace) ትምህርት እውነትን ከስህተት ጋር ለመደባለቅ ጥሩ
ምሳሌ ነው
የእግዚአብሔር ጸጋ ውበት እና ኃይል ላይ አጽንዖት መስጠት ጥሩ ነው ፤ ነገር ግን አንዳንድ አስተማሪዎች ጳውሎስ "ሙሉ
የእግዚአብሔር ምክር" ብሎ ሐዋርያት ሥራ 20፥27 ላይ የጠራውን ችላ ይላሉ። ለምሳሌ ክርስቲያኖች በአምላክ ይቅር
መባላቸው እውነት ነው። ይህ ማለት ግን ኃጢአታችንን መናዘዝ የለብንም ማለት አይደለም። በያእቆብ 5፥16 መሠረት
ኃጢአታችንን ለእያንዳንዳችን መናዘዝ ካስፈለገን ለምንድነው ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናዘዝ የማያስፈልገን? ምክንያቱም
እያንዳንዱ ኃጢአት በመጨረሻ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስሐሆነ ነውስሐሆነ፣ መዝ. 51፥ 4 ።እንዲሁም፣ በ1 ዮሐንስ 1፥9
ኃጢአትን መናዘዝን በተመለከተ ለአማኞች ግልጽ መመሪያ ይሰጣል። “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን
ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” በሚለው ቃል ይጀምራል።
ይህ ያለ ኃጢአት መናዘዝ የኃጢአት ይቅርታታ ማግኘት እንደማንችል የሚያመለክት የምክንያት እና ውጤት መግለጫ
ነው። በደም የተገዛን የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን ከሲኦል ለመዳን ኃጢአታችንን መናዘዝ አንቀጥልም።
ከአባታችን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመሥረት እንናዘዝ እና ንስሐ እንገባለን። እኛ “በአቋማችን ጻድቅ ነን” ግን “በእርግጥ
ኃጢአተኞች” ነን። ይህንን መከራከሪያ ለመቃወም፤ የልእለ-ጸጋ ሰባኪዎች የዮሐንስ መልእክቶች ለአማኞች የተጻፉ መሆናቸውን
ይክዳሉ። ይሁን እንጂ (1 ዮሐንስ 2፥1) እንዲህ በማለት ይጀምራል:- “ልጆቼ ሆይ፣ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን
እጽፍላችኋለሁ። ነገር ግን ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።''
ዮሐንስ በግል ለሚያውቃቸው አማኞች እየጻፈላቸው ነው። ያመኑት ወዳጆቹ ኃጢአት ሊሠሩ እንደሚችሉ እና ሲሠሩ መናዘዝ
እንደሚያስፈልጋቸው ያመለክታል።
የልእለ ጸጋ ሰባኪዎች መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን በኃጢአታቸው ፈጽሞ አይወቅሳቸውም ይላሉ። የጎለመሱ
ክርስቲያኖች ይህን ስህተት ወዲያውኑ ሊገነዘቡት ይገባል። እያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ኃጢአትን በሠራ ጊዜ የመንፈስ
ቅዱስ ታላቅ ወቀሳ ተሰምቶታል። ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን “የእውነት መንፈስ” ሲል ጠርቶታል (ዮሐ. 15፥26)። እውነት
በራሱ ፍቺው ውሸትን አይታገስም። የእውነት መንፈስ በሚያምን ልብ ውስጥ ሲኖር (1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19) ፤ እውነት ባልሆነ
ነገር ላይ እምነትን ያመጣል።

ለማጠቃለል፣ የልእለ ጸጋ ሰባኪዎች የሚያስተምሩት የተወሰኑ ሐሳቦች ትክክል ቢሆኑም ስህተቶች አሉባቸው። የዳንነው
በጸጋ ነው እንጂ በሥራችን አይደለም ኤፌሶን 2፥8-9። የእግዚአብሔርም ጸጋ ድንቅ፣ ታላቅ እና ነጻ ነው (1ኛ ጢሞቴዎስ
1፥14)። ነገር ግን፤ የልዕለ ጸጋ ትምህርት ከተቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር ተስማሚ እና ተመጣጣኝ አይደለም። ኢየሱስ
በሁለቱም “ጸጋና እውነት” የተሞላ ነበር (ዮሐንስ 1፥14)። ሁለቱ ስስ ሚዛኖች ናቸው፤ እና በሁለቱም በኩል ያለው ጫፍ
የሐሰት ወንጌልን እና አሰራርን ሊያስከትል ይችላል። ሁልጊዜ ማንኛውንም አዲስ ትምህርት “ከእግዚአብሔር ሙሉ ምክር” ጋር
ማወዳደር እና ከእውነት ትንሽ የራቀ ማንኛውንም ትምህርት ችላ ባለማለት በእውነተኛ ትምህርት መሞገትና ቤተ ክርስቲያንን
መጠበቅ መማር አለብን (1 ዮሐንስ 4፥1፣ ሐዋ. ሥራ 20፥28) ።
4.2 የሐሰት አሰራር ልምምድ

• የሐሰት አሰራር የምንለው በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ አሰራር ሽፋን በቤተ ክርስቲያን የሚደረግ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ልምምድ ነው። በአገራችንም ወቅታዊ ተግዳሮት በመሆን አማኞች
እውነተኛውን ኢየሱስ እንዳይመለከቱ ግርዶሽ ሆኗል። ሐሰተኛ ፈውሶች፣ ምልክቶችና ድንቆችን
የመፈለግና ዋናውን እግዚአብሔርን ''በመንፈስና በእውነት'' ያለመፈለግ ልምምዶች እየሰፉ
ይገኛሉ።
• መንፈስ ቅዱስ የእውነት መንፈስ ስለሆነ በእውነት የሚሰራ መሆኑን መገንዘብ አለብን።
የልምምዶቹ ጥራት ችግር ብዙ ገጽታዎች አሉት። ይህም ከቤተ ክርስትያናት፣ ከአገልጋዮች እና
ከምእመናን አንጻር መመርመር የምንችለው ነው። እንደ ቤተ እምነታችን የእምነት አንቀጽ መሠረት
የጸጋ ስጦታዎችን አሠራር የምናምን ሲሆን በቅንነት መመርመር መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመሆኑ፣ (1
ተሰ 5፥19) አንዳንድ ወቅታዊ የሆኑ የሐሰት አሰራር ተግዳሮቶች እዚህ ማንሳት አስፈልጓል።
4.2.1 የፈውስ ልምምድ

በኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያን ለከፍተኛ የሐሰት አሰራር የተጋለጠ አገልግሎት ሲሆን፤ ወቅታዊ


የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮትም ነው። ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ በምንመለከትበት
ጊዜ የህዝቡ የፈውስ አገልግሎት ፍላጎት ለሀሰተኛ ፈውሶች እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ
የፈውስ ልምምዶች ምክንያት ሆኖ እንመለከታለን ። በተጨማሪም ውጤቱ እንደሚያሳየው፣
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተውን አዎንታዊ የፈውስ ዓላማ ብዙዎቹ በአእምሯቸው
ቢያምኑም፣ በመካሄድ ላይ ያሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የፈውስ ልምምዶች አሉታዊ
መዘዝን በተግባር አስከትለዋል። በዚህ መሠረት አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስን የፈውስ እይታ
እየፈለጉ ቢሆንም በተግባር ግን ተግዳሮቶች እያስከተሉ ነው።
4.2.1.1 የፈውስ ልምምዶች ሐሰተኛ አሰራር ገጽታዎች

አብዛኞቹ በአዎንታዊ መንገድ እንደተቀበሉት፣ የፈውስ ምንጭ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ነገር
ግን ልምምዱ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ላይ እንዳልሆነ ማየት እንችላለን ፣ ዮሐ. 16፥13-
15። ብዙ ወቅታዊ በመንፈስ ቅዱስ ስም በመካሄድ ላይ ባሉት አሉታዊ የሐሰት የፈውስ
ልምምዶች ብዙ ክርስቲያኖች አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳደረባቸው ይታያል። በተጨማሪም ፈውሱ
እግዚአብሔርን ለማክበር እና ለማያምኑት ወንጌልን ለመመስከር በአዎንታዊ መንገድ ጥቅም ላይ
ይውላል በማለት ብቻ ብዙዎች ባለመመርመር ለሐሰት አሰራር እንደተጋለጡ ከሁኔታዎች
መረዳት ይቻላል።
4.2.1.2 የቤተ ክርስቲያን ፈውስ አገልጋዮች ሹመት እውቅና ለሐሰት የፈውስ አሠራር
ያበረከተው ሚና
የፈውስ አገልጋዮች እንደሚገልጹት፣ ሁሉም ስጦታቸውን ከአገልግሎታቸው ልምምድ፣ ከተገልጋዮች
ምስክርነት፣ የቤተክርስቲያን ፈቃድ እና የሹመት እውቅና በመነሳት እያገለገሉ እንዳሉ ይናገራሉ። ነገር ግን
እዚህ ጋር በቅንነት ለመተናነጽ መነሳት ያለበት ጥያቄ ፣ ከልምምዱ የተገኘው ምስክርነት እና ቤተክርስቲያን
ባላት ስልጣን በባለ አደራነት በጥራት እየተካሄደ ያለው አገልግሎት ጥሩ ገጽታ ያለው ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ያልሆነው የሐሰት የፈውስ ልምምድ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ ያለው ለምንድን ነው? ይህ የሚያሳየው
የፈውስ ምስክርነት እና የፈውስ አገልጋዮች ተልዕኮ ላይ ችግር እንዳለ ነው።
በሌላ በኩል ሁሉም አገልጋዮች አገልግሎታቸው ከእግዚአብሔር ነው ብለው ይከራከራሉ፣ በዚህ
መሠረት ሰዎች እየፈለጉና እየተከተሏቸው ነው። ውጤቱ እንደሚያሳየው በቤተክርስቲያን ላይ ያለው ውጥረት
እውነተኛ ልምምድ እና የውሸት የፈውስ ልምዶችን በተመለከተ ያለው ግራ መጋባት ነው። የሚፈወሱ ሰዎች
የሚሰጡት ምስክርነት ደስተኞች ሆነው ሲፈወሱ እግዚአብሔርን ያከብራሉ ፣ የፈውሱ ምስክርነት
ለእግዚአብሔር ክብር ነው በማለት የማስታወቂያ ስራ ይሰራሉ ። ነገር ግን ለእግዚአብሔርን ክብር
የሚያመጣው ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ማንሳት እንችላለን።
4.2.1.3 ወቅታዊው የፈውስ ልምምድ በመጽሐፍ ቅዱስ
እውነት ሲመዘን

• መጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ 19፥10 ሲገልጽ፣ ኢየሱስ የጠፋውን ይፈልጋል በመሆኑም የጠፋውን
ሲያድነው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ያለውን ደስታ እንመለከታለን። በተጨማሪም
አገልጋዮቹ በእግዚአብሔር ከማመን ይልቅ በፈውስ አገልግሎታቸው ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ያልሆነውን በእምነታቸውና የተናገሩት ቃል ሁሉ ስልጣናዊ ሆኖ እንደሚሰራ የማወጅ ስሁት
ልምምድ እንመለከታለን ፤ ይህም የሚያሳየው በታመመው ሰው እምነት እና በራሳቸው እምነት
ያምናሉ። ይህም በፈውስ አገልግሎታቸው የሚከሰትን ችግር ወደ ታመመው ሰው እምነት ማጣት
ላይ ማላከክ እና ከኃላፊነት የመሸሽ ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል። እግዚአብሔር ስጦታውን
ከኃላፊነት ጋር እንደ ሰጣቸው አያምኑም።
• በ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥4-11 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥28) ስንመለከት፤ “የፈውስ ስጦታዎች” ተብሎ
የተገለፀው መንፈሳዊ ስጦታ ነው። ወንጌሎች አብዝተው ክርስቶስ በፈውስ ስጦታ እንዳገለገለ ያሳያሉ፣
ማር. 1፥14፣ ማር. 1፥32-34። አሥራ ሁለቱን፣ ሰባውን በላካቸው ጊዜ የእግዚአብሔርን መንግሥት
ለመስበክ ብቻ ሳይሆን ድውያንን ይፈውሱ ዘንድም ነበር (ማር. 6፦7-13፣ ሉቃስ 10፥7-9)።
በተጨማሪም የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመፈወስን ስጦታ ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ማስረጃዎችን
አሳይቷል፣ ሐዋ. 3፥7፣ 5፥12–16፣ 8፥7፣ 19፥12፣ 28፥8። በተጨማሪም ያዕቆብ በሽማግሌዎች
የተሸከመውን የፈውስ አገልግሎት ይጠቅሳል፤ (ያዕቆብ 5፥16)። በሌላ በኩል፤ ኢየሱስ በ (ማቴ
24፥14) ከክርስቶስ ዳግም መምጣት በፊት ያለው የወንጌል ስብከት እንደሆነ ተናግሯል። ወንጌል ወደ
አካላዊ ፈውስ መልእክት መውረድ የለበትም። የክርስቶስ ደም የሚያድነን ከኃጢአት እንጂ ከሥጋዊ
ድካም አይደለም። ኢየሱስ ዛሬ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ አስደናቂ ተአምራትን ለማበረታታት እንዳልሞተ
ማወቅ ያለብን ሲሆን ፤ የፈውስ አገልግሎትም በቤተክርስቲያን ውስጥ በዓላማ የተሰጠ ነው።
ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ የፈውስን ስጦታ ቢያስተምርም፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የሐሰት የፈውስ
ልምምድ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተስፋፍቷል። ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ዓላማ እና ሐሳብ የፈውስ አገልግሎትን እየተለማመዱ ነው። እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የፈውስ ስጦታን
በዓላማ እና በሃላፊነት እንደሰጠ እና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት መሠረት መተግበርም አለበት ብለን እናምናለን።
ቤተክርስቲያን ከፈውስ አገልጋዮች ጋር ለመገናኘት ለእንግዳ ማረፊያ የሚከፍለውን የገንዘብ ዘረፋ፣ የፈውስ ስጦታን
የሚወክሉ ቁሶችን መሸጥን የመሳሰሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አሰራርን ማስወገድ አለባት። መጽሐፍ ቅዱስ ፈውሱ
ወንጌልን ለመመስከር እንደሆነ ያስተምራል ፤ ለገንዘብ ዓላማ ግን አይደለም (ሐዋ. 3)።
4.2.2 የእምነት ቃል እንቅስቃሴ የሐሰት አሠራር
ልምምድ
• የእምነት ቃል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ልምምድ ወቅታዊ እና እጅግ አደገኛ ከክርስትና የእውነት
መገለጥ የራቀ ሐሰተኛ አሠራር ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያናትም ሾልኮ እየገባና ብዙዎችን እየማረከ
ይገኛል።
• የእምነት ቃል ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ፣ ቤተ እምነታዊ ፣ መደበኛ ድርጅታዊ ወይም
ተዋረድ የሌለው አንደ ሁኔታው የሚገለጥ ልምምድ ነው። ይልቁንም እንደ ኬኔት ሃጊን፣ ቤኒ ሂን፣
ኬኔት ኮፕላንድ፣ እና ፍሬድ ፕራይስ ባሉ በርካታ ታዋቂ ፓስተሮች እና አስተማሪዎች ከፍተኛ
ተጽዕኖ የተደረገበት እንቅስቃሴ ነው። በአገራችንም በስፋት እየተተገበረ ያለና መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ያልሆነ ልምምድ በመሆኑ ግንዛቤ መፍጠር በጣም አስፈላጊ ነው።
4.2.2.1 የእምነት ቃል እንቅስቃሴ ልምምድ ገጽታ

• የእምነት ቃል እንቅስቃሴ እምብርት “በእምነት ኃይል” ላይ ማመን ነው። ቃላቶች እምነት-


ኃይልን ለማምጣት ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ይታመናል፣ ስለዚህ በትክክል
የሚያምኑትን የቅዱሳት መጻሕፍት ተስፋዎች (ጤና እና ሀብት) ይፈጥራሉ ብለው
የሚያምኑትን በማወጅ ይለማመዳሉ ። የእምነት ኃይልን የሚገዙ ናቸው የሚባሉት ሕጎች
ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድ ውጭ ሆነው እንደሚሠሩ እና፣ እግዚአብሔር ራሱ ለእነዚህ
ሕጎች ተገዢ ነው ብለው ያስተምራሉ። ይህ እምነታችንን እና እራሳችንን ወደ አምላክ
ከመቀየር የዘለለ ነገር እንደሌለው ያሳየናል።
• ከዚህ በመነሳት የእነርሱ ሥነ-መለኮት ከቅዱሳት መጻሕፍት የበለጠ እየራቀ ይሄዳል። እግዚአብሔር የሰው
ልጆችን በሥጋዊ አምሳሉ እንደ ትናንሽ አማልክት እንደፈጠረ ይናገራሉ። ከውድቀት በፊት ሰዎች የእምነት
ኃይልን በመጠቀም ነገሮችን ወደ ሕልውና የመጥራት ችሎታ ነበራቸው ይላሉ። ከውድቀት በኋላ ሰዎች
የሰይጣንን ተፈጥሮ በመላበስ ነገሮችን ወደ ሕልውና የመጥራት አቅም አጥተዋል በማለት ይገልፃሉ ።
• ይህንን ሁኔታ ለማስተካከል ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ትቶ ሰው ሆነ፣ በመንፈስም ሞተ፣ የሰይጣንን
ባሕርይ በራሱ ላይ ወሰደ፣ ወደ ሲኦል ገባ፣ ዳግመኛ ተወልዶ፣ በእግዚአብሔር ባሕርይ ከሙታን ተለይቶ
ተነሣ። ከዚህ በኋላ፤ እግዚአብሔር በመጀመሪያ እንዳሰበው ትንንሽ አማልክቶች እንዲሆኑ በአማኞች
ውስጥ መገለጡን እንዲደግም ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ላከ የሚል ትምሀርት ነው የሚያስተምሩት።
• የእምነት ቃል አስተምህሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘውን ግምት ውስጥ እንደማያስገባ ግልጽ
ነው። የግል መገለጥ ዋና ሲሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነት አለመቀበል እንደዚህ ዓይነት ከንቱ
እምነቶች ጋር ለመምጣት በጣም የታመነ ነው ፣ ይህም የመናፍቃን ባህሪው አንድ ተጨማሪ ማረጋገጫ
ነው።
4.2.2.2 የእምነት ቃል አንቅስቃሴን ልምምድ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
እውነት

የእምነት ቃልን መቃወም መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ቀላል ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ብቻውን
የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ፈጣሪ ነው (ዘፍ 1፥3፣ 1 ጢሞቴዎስ 6፥15) ስለዚህም እምነት አያስፈልገውም፣
እርሱ እርሱ ሁሉን ቻይ የሚታመን አምላክ ነው፤ (ማር. 11፥22 ፣ ዕብራውያን 11፥3)። እግዚአብሔር
መንፈስ ነው፣ ሥጋዊ አካልም የለውም (ዮሐ. 4፥24)። ሰው ግን የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል
ነው (ዘፍ 1፥26-27፣ 9፥6) ፤ ይህ ግን ትንሽ አምላክ ወይም መለኮታዊ አያደርገውም። መለኮታዊ
ተፈጥሮ ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ክርስቶስ ዘላለማዊ ፣ አንድያ ልጅ እና የእግዚአብሔር አንድያ
አካል ነው ፣ (ዮሐንስ 1፥1-2፣14፤15፣18 ፣ 3፥16 ፣ 1 ዮሐንስ 4፥1፣ ቆላስይስ 2፥9) ። ሰው በመሆን
ኢየሱስ የሰማይን ክብር ለሰው ሰጠ፣ ነገር ግን አምላክነቱን አልሰጠም (ፊልጵስዩስ 2፥6-7)፣ ምንም
እንኳን ሰው ሆኖ በምድር ሲመላለስ ስልጣኑን መከልከልን ቢመርጥም።
4.2.3 ቅይጥነት (የአለማዊነት ብረዛ) ተግዳሮት

• ቅይጥነት ወይም የአለማዊነት ብረዛ የአገራችንን ቤተ ክርስቲያን እየተገዳደረ ይገኛል።


ከክርስቲያናዊ አተያይ ቅይጥነት አሉታዊ ነው ምክንያቱም የክርስትና እምነትን ንጽህና ሊያዳክም
ወይም ሊያበላሽ ይችላል። ክርስትና ለእግዚአብሔር ብቻ መሰጠትን አስፈላጊነት ያጎላል
በመሆኑም፣ ሌሎች አማልክትን ወይም ሃይማኖታዊ ድርጊቶችን ከመከተል ያስጠነቅቃል። ነገር
ግን በአሁኑ ወቅት አገራችን ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን ከባህል እና ከምእራቡ አለም አለማዊነት
ጋር የተጋቡ ቅይጥ ልምምዶች ተጽእኖ ውስጥ በመግባቷ ምስክርነቷ እየተበላሸ ይገኛል።
በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የቅይጥነት ገጽታ ያላቸውን ልምምዶች በመፈተሽ በጊዜው የማስተማር
እርምጃ መውሰድ አለባት።
4.2..3.1 ቅይጥነት ወይም የአለማዊነት ብረዛ ምንድነው?
ከቅዱሳት መጻሕፍት ውጭ ያሉ ምንጮችን ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል በሆነ መንገድ መጠቀም ቅይጥነት
የሚያድግበት መንገድ ነው። ይሕም ከባሕል ጋር የተቀየጠ እውነትን የሚያመቻምች ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል። ክርስትና
በእያንዳንዱ ባህል ላይ ለመፍረድ የቆመ በመሆኑ ለእድገቱ የማይጣጣሙ የአገላለጽ ዘይቤዎችን በማጥፋት እና ለተከታዮቹ አዲስ
ህይወትን የሚያመጣ እምነት ነው።
ክርስቶስን በማመንና በመለወጥ የሚጀምር እና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ምጽዓት ለዘላለም በክብር የሚያኖር
ጥራት ያለው ህይወት ነው። በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የባህል መነቃቃት ውስጥ ያለው የማንነት ትርጉም ፍለጋ
በክርስትና የተገኘውን የማንነት ትርጉም በርዞታል።
ስለ ማንነት ትርጉም ፍለጋ ስንል ክርስቲያኖች በክርስቶስ ካገኙት ክርስቲያናዊ ማንነት ውጭ ማንነታቸውን በባህላቸው፣
በብሔር ማንነታቸው ውስጥ ለመግለጽ ሲፈልጉ እና ጠንካራ የሆነ ስሜታቸው ከክርስትናው ማንነታቸው በላይ ሲገልጹ ቅይጥነት
ወደ ሕይወታቸው ይገባል። በአገራችን ውስጥም ቤተክርስቲያን በዚህ አይነት አመለካከት አሰየተጠቃች ነው። ቤተክርስቲያን
በክርስቶስ ልዩ መገለጥ የተመሠረተች ሲሆን አማኞች ታማኝነታቸው ለክርስቶስ መሆን ሲገባው ለተወለዱበት ባህል እየተከራከሩ
በመሆኑ ቅይጥነት እየገባ ይገኛል። ቅይጥነት ወይም የአለማዊነት ብረዛ ወቅታዊ የሆነ ተመሳስሎ የሚገባ እውነትን የሚበርዝ
አመለካከት ነው።
4.2.3.2 ቅይጥነትን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት

ክርስትና ቅይጥነት (የአለማዊነት ብረዛ) የተለያዩ ሃይማኖታዊ እምነቶች እና ልማዶች


መቀላቀል እንደሆነ ያስተምራል። መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን
እንዳይከተሉ ወይም ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩ ያስተምራል፣ ዘዳ 12:30-31።
በአዲስ ኪዳን ሐዋርያው ጳውሎስ በ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፥14-15 ላይ ክርስቲያናዊ ልማዶችን
ከአረማዊ ልማዶች ጋር እንዳንቀላቀል ያስጠነቅቃል። በጥቅሉ የክርስትና እውነት ልዩ ሲሆን
ቅይጥነት ደግሞ የክርስትናን እምነት እንደሚያዳክም እና ወደ መንፈሳዊ ግራ መጋባት
እንደሚመራ ያስተምራል። ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት እንዲቀጥሉ እና
እምነታቸውን ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር እንዳይቀላቀሉ ይበረታታሉ።
5. የአመራር ተግዳሮቶች
• በአመራር ተግዳሮቶች የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ናቸው። ቤተክርስትንያን ማንን ትመስላለች ቢባል
መልሱ መሪዎችን ነው፡፡ መሪዎች በቤተክርስትያን ላይ በትምህርት፣ በምሳሌነት፣ በውሳኔና በአመለካከት
ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አላቸው፡፡ መሪነት ቀላል ተግባር አይደለም፡፡ መሪነት የጌታ ኢየሱስን ፈለግ መከተል
ነው፡፡
• መሪነት እኛ በምናስበውና በምናውቀው እሴት መኖር ሳይሆን እግዚአብሔር ባስቀመጠው መስፈርት ውስጥ
መኖር ማለት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ስለመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሪነት ትክክለኛውን መለኪያ መስፈርት ያስቀመጠበት
ክፍል (የማቴዎስ 20፥25-28) ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል “ታላቁ የመሪነት ትእዛዝ” ክፍል ይባላል፡፡
• ጌታችን ኢየሱስ እንዳለው መጸሐፍ ቅዱሳዊ መሪነት ከአለማዊ አመራር የተለየ ነው፡፡ የራሱ ጠባይ፣ መልክ፣
እሳቤና እሴቶች ያሉት ነው፡፡ በክፍሉ እደታየው ልክ ሁለቱ ደቀመዛሙርትና እናታቸው እንዳደረጉት፤
የቤተክርስትያን አመራር ለብዙ አለማዊ፤ ማህበራዊና ባህላዊ አመለካከቶች የተጋለጠ ነው፡፡ መሪነትን ሲያስቡ
ብዙዎች የሚያቀርቡት፤ የሚረዱትና የሚተገብሩት እውቀት ከቃሉ የተቀዳ ሳይሆን ከሌላ ቦታ የመጣ ነው፡፡
5.1 የመሪ ምርጫ ችግሮች

• የቤተ ክርስቲያን አመራር ተግዳሮቶች የመሪነት ችግሮች እየጨመሩ እንዲሔዱ እና የመሪ ምርጫ
ችግሮች እንዲከሰቱ አድርገዋል። በኢትዮጲያ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ምርጫ ሲካሔድ
በመመዘኛ መስፈርትነት የሚቀርበው የጢሞቴዎስ እና የቲቶ መጽሐፍት ላይ የተቀመጡ መመዘኛ
መስፈርቶችን መጠቀም ነው። ይሔ መሆኑ ጥሩ ሆኖ ሳለ ግን፤ መሪነት አካባቢ የሚፈጠሩ
ችግሮችን መለየት ምርጫውን የቤተ ክርስቲያንን እድገት ሊያስቀጥል በሚችል መልኩ በማድረግ
ለማከናወን ይጠቅማል። በቤተ ክርስቲያን የሚከሰቱ የመሪነት ችግሮችንም ከጢሞቴዎስ እና ቲቶ
መመሪያዎች ጋር አያይዞ መጠቀም ችግሩን በእውቀት ለመፍታት ይጠቅማል። የመሪነት ችግሮች
አለማቀፍ፤ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ባህሪ አላቸው፡፡
አለም አቀፍ ችግሮች የመሪነት ችግሮች የሚባሉት የገንዘብ እጥረት፣ ግጭቶች፣ መድከም
(Burnout)፣ መንፈሳዊነት ማጣት፣ በስራ የተወጠሩ መጋቢ መሪዎች መኖር፣ እድገት
የሚያስከትላቸው ችግሮች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሪነት ለባህላዊና ለአለማዊ አመለካከቶች መጋለጡ፣
መሪነትን ከፖለቲካ ካለው አመለካከት ለመለየት አለመቻል፣ መሪነትና አስተዳዳሪነት መደባለቃቸውና፣
ባህላዊ አመለካከቶች ወደ መሪነት መምጣቸው ናቸው፡፡
የአፍሪካ የመሪነት ችግሮች የሚባሉት ደግሞ፤ ብዙኅነት፣ ብሔርተኝነት፣ ጎሰኝነትና ቡድተኝነት፣
አገልግሎትና የግል መንፈሳዊነት ሳይጣጣም ሲቀር፣ መሪዎች የህዝብን ፍላጎት ከማጤን ይልቅ
በራሳቸው የግል ዝናና ጥቅም ላይ ማተኮራቸው፣ በትምህርት ያልሰለጠኑ መሪዎች መኖራቸው እና
መሰል ሌሎች ችግሮች ናቸው።
የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያሉ የመሪነት ችግሮች ደግሞ፣ የሰለጠኑ መሪዎች አለመኖር
(አብያተክርስትያናት ሪሰርች)፣ መሪዎች በራሳቸው ላይ ያተኮሩ መሆናቸው፣ የመሪዎች በራሳቸው ላይ
የሚያደርሱት ችግር፣ በሚያገለግሉት ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ችግር፣ በቤተክርስትያን አመራር ላይ
የመጡ የባህል እና የአለማዊነት ችግር፣ እና መሪዎች ራሳቸው ላይ ያለመስራት ችግሮች ናቸው።
የቤተክርስትያን እድገትና የመሪዎች ቁጥር አለመጣጣም፣ የእድገት አለመኖር መሪዎችን ተስፋ
ማስቆረጡ፣ ከተገቢው በላይ የሚደክሙ መሪዎች ተተኪ መሪዎች እንዳይኖሩ ማድረጋቸው፣ የማይሰሩ
ዳተኛ መሪዎች የቤተክርስትያንን እድገት ማዳከማቸው ፣ በትምህርት ያልዳበሩ መሪዎች በቤተክርስትያን
ላይ የሚያስከትሉት ተፅዕኖ፣ ከሚያስፈልገው ጊዜ በላይ ተመርጠው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ሊመሩ
የሚጥሩ መሪዎች፣ የመሪዎች ስልጠናና የቤተክርስትያን ፍላጎት አለመጣጣሙ፣ በአግባቡ ያልተመረጡ
መሪዎች የመሪነት ቦታ መያዛቸው፣ ከመሪነት ተግባራቸው የወረዱ ቀደምት መሪዎች ከመሪነት አካባቢ
ላለመጥፋት የሚያደርጉት ጥረት፣ ተተኪ አለማፍራት እና መሰል ችግሮች ትልቅ ተግዳሮት ሆነው የቤተ
ክርስቲያንን እድገት እየጎዱ ናቸወ
5.2 የብቃትና ክህሎት ማነስ
• የብቃትና ክህሎት ማነስ አንዱ የመሪነት ተግዳሮት ነው። መሪነት ኀላፊነት ነው፡፡ የመሪነት ሀላፊነቶች
ግንኙነታዊ፤ መዋቅር ነክ እና ራዕይ ነክ ሀላፊነቶች ናቸው፡፡ መሪ ከሚመራው ከሚያሳድገው እና
ከሚያስለጥነው ሰው አንፃር ከሌሎች አብረው ከሚያገለግሉ፤ ከሌሎች መሪዎች እና በአጠቃላዩም
ከማህበረሰቡ አንፃር የሚያከናውኗቸው ሀላፊነቶች ሲገኙ ፤ እነዚህ ኀላፊነቶች የግንኙነት ኀላፊነቶች ይባላሉ፡፡
• ሌላው መሪ ተቀዳሚ ተግባሩን፤ ጥሪውንና ፀጋውን የሚተገብርባቸው መዋቅራዊ ኀላፊነቶች አሉት፡፡ በአጥቢያ
ደረጃ እነዚህን የመሰሉ ኀላፊነቶች ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡
• ሌላው መሪ የመሪነት ባህሪውን ይበልጥ የሚገልጥበት ትልቁ ተግባር ከሌሎች አስቀድሞ የወደፊቱን
መመልከቱና አስፈላጊ የሆነ ዕቅዶችን መንደፉ፤ ሰዎችን ስለወደፊቱ ራዕይ ትግበራ ማሳወቅ፤ ማነሳሳቱና
ሰዎችም የወደፊቱን እንደሚሆን እንዲያምኑትና እንዲቀበሉት ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
• ስለሆነም መሪዎች ከግንኙት፤ ከመዋቅር እና ከራዕይ ጋር የተያያዘውን ተግበራቸውን በቅጡ ሊተገብሩት
ይገባል፡፡
የመንፈሳዊያመን መሪዎች ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የአገልግሎቶች ሀላፊነቶች በመባል
ይታወቃሉ። ቀጥተኛ የአገልግሎት ሀላፊነቶች የሚባሉ፤ መሪው በተሰጠው የፀጋ ስጦታና
በተቀበለው ጥሪና ፀጋ መሰረት በማድረግ የሚከያከውናቸው የአገልግሎት ተግባር ሲሆን
ጸጋውን መሰረት በማድረግ የሚያከውናቸው ናቸው፡፡ ቀጥተኛ ያልሆኑ የመሪነት አገልግሎት
ሀላፊነቶች መሪዎች በተሠጣቸው ፀጋ መሰረት አድርጎ ከሚያከናውናቸው ተግባራት
በተጨማሪ ሚያከናውኑት የአመራር አላፊነቶች ሲሆኑ እነዚህ ከአስተዳደር ከመዋቅርና መሰል
ነገሮች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
6. መፍትሔዎች

6.1 ጠንካራ የክርስቲያናዊ ትምህርት ስርአተ ትምህርት ማዳበር

• ጠንካራ የክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት የቁሳቁስ፣ ግብዓቶች እና የማስተማሪያ ዘዴዎች ስብስብ


መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትን በሁሉም የትምህርት ዘርፎች ያዋህዳል። የዚህ ዓይነቱ ሥርዓተ
ትምህርት የሚያተኩረው በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች እና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሲሆን
ዓላማውም በተማሪዎች ውስጥ ክርስቲያናዊ እሴቶችን፣ እምነቶችን እና ሥነ ምግባሮችን ለማሳደግ
ነው።
የጠንካራ ክርስቲያናዊ ሥርዓተ ትምህርት ጥቅሞች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

• 1. የተሻሻለ መንፈሳዊ እድገት፡- ክርስቲያናዊ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስና


ትምህርቶቹ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል፣ ይህም ወደ መንፈሳዊ እድገትና ከእግዚአብሔር
ጋር የጠበቀ ዝምድና እንዲመሠርቱ ያደርጋል።
• 2. የሞራል እና ሥነ ምግባራዊ እድገት፡- የክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎችን ስለ ሐቀኝነት፣
ታማኝነት፣ ርኅራኄ፣ ይቅርታ እና ኃላፊነት በማስተማር የሞራል እና የስነምግባር እድገትን ያበረታታል።
• 3. ወሳኝ የማሰብ ችሎታ፡- የክርስትና ትምህርት ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መርሆች ከነባራዊው
ዓለም ሁኔታዎች እና ከሥነ ምግባራዊ ችግሮች ጋር እንዲተገብሩ በመርዳት ሂሳዊ አስተሳሰብን እና
ችግሮችን የመፍታት ችሎታን ያበረታታል።
• 4. በእምነት ላይ የተመሰረተ የአቻ ማህበረሰብ ግንባታ፡ አማኞች ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው
እኩዮቻቸው ጋር ጓደኝነትን ያዳብራሉ፣ በክርስቲያናዊ አካሄዳቸው ድጋፍ እና ማበረታቻ በሕብረት
ይሰጣሉ።

• 5. ለአገልግሎት መዘጋጀት፡- የክርስቲያናዊ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎችን ለተለያዩ ክርስቲያናዊ


አገልግሎት እድሎች ለማዘጋጀት ይረዳል፤ ለምሳሌ የመጋቢነት አገልግሎት፣ የሚስዮናዊነት አገልግሎት
እና ሌሎች የክርስቲያናዊ አገልግሎት ዘርፎች። በአጠቃላይ፣ ጠንካራ ክርስቲያናዊ ሥርዓተ ትምህርት
የእግዚአብሔርን ትምህርቶች በሁሉም የሕይወት ዘርፎች የሚያዋህድ እና ምእመናንን ለኢየሱስ
ክርስቶስ ታማኝ ሆነው በዓለም ውስጥ ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እውቀት፣ ችሎታ እና እሴት
የሚያስታጥቅ አጠቃላይ ትምህርት መስጠት ይችላል።
6.2 የአቃቤ እምነት ቡድን ማቋቋም

አቃቤ እምነት ክርስትናን ከውጭ ጥቃት መከላከል እና መጽደቅን የሚመለከት የስነ-መለኮት ክፍል
ነው። ዓላማውም ለክርስትና እምነት እውነትነት አመክንዮአዊ መከራከሪያዎችን እና ማስረጃዎችን
ለማቅረብ እና በእሱ ላይ ለሚነሱ ትችቶች እና ተቃውሞዎች ምላሽ ለመስጠት ነው። በቤተክርስቲያን
ውስጥ የአቃቤ እምነት ቡድን መገንባት በብዙ መንገዶች ይረዳል፡-
• 1. የአማኞችን እምነት ማጠናከር፡- አማኞች ለእምነታቸው ምክንያት የሆኑትን ዕውቀትና
ግንዛቤን ስናስታጥቅ የበለጠ በራስ የመተማመን መንፈስ እና የመከላከል አቅምን ያጎናጽፋሉ።
• 2. የጠፉትን መድረስ፡- በክርስትና ላይ ተጠራጣሪ ወይም ጥላቻ ካላቸው ጋር እንድንገናኝ
ይረዳናል። ምክንያታዊ የሆኑ ክርክሮችን እና ማስረጃዎችን በማቅረብ ሰዎች የወንጌልን እውነት
እንዳያስቡ የሚከለክሉትን የእውቀት መሰናክሎች ለማስወገድ መርዳት እንችላለን።
• 3. ለባህላዊ ተግዳሮቶች ምላሽ መስጠት፡- ባህላችን በክርስትና ላይ ጥላቻዉ እየጨመረ በሄደ
ቁጥር ለባህላዊ እና አእምሮአዊ ተግዳሮቶች ምላሽ የሚሰጥ ቡድን መኖሩ አስፈላጊ ነው።
• 4. የወንጌል ስርጭትን ማሻሻል፡- አቃቤ እምነት ሀይማኖታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ተጠራጣሪ
(Skeptical) በሆነ ባህል ወንጌልን በብቃት እንድናስተላልፍ ይረዳናል። ለእምነት ትክክለኛ
ምክንያቶችን በማቅረብ ወንጌልን ከሰዎች ሕይወት ጋር ያለውን ጠቀሜታ በተሻለ ሁኔታ
ማብራራት እንችላለን።
ሲጠቃለል፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የአቃቤ እምነት አገልግሎት መጠቀም እና የአቃቤ እምነት ቡድን
መገንባት የምእመናንን እምነት ለማጠናከር እና ከስህተት ለመጠበቅ፣ የጠፉትን ለመድረስ፣ ለባህላዊ
ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት እና የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማሻሻል አስፈላጊ ነው።
6.3 ጠንካራ ጸሎትና የቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት

ክርስትና በፍፁም የተመልካች ስፖርት እንዲሆን ታስቦ የተሰጠ ሕይወት አይደለም፡፡


በመሆኑም የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊም ነው።
አነስተኛ የቡድን ጥናት በጣም ውጤታማ ከመሆኑ የተነሳ ኢየሱስ ሐዋርያት ተብለው
የሚታወቁትን ሰዎች ለማሰልጠን ተጠቅሞበታል (ሉቃስ 6፥12–16፤ ማር. 4፥34) ።
ይህም ክርስትና ጥሩ ግንኙነት ያለው እንዲሆን ታስቦ ነው።
በመጀመሪያ፣ በራሳችን እና በእግዚአብሔር መካከል ባለው ግንኙነት ላይ፣ ሁለተኛ፣
በራሳችን እና በዙሪያችን ባሉት ሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ሚዛን የሚያስጠብቅ
ነው። ትንንሽ ቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በየሳምንቱ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት
ተመልካቾች ከመሆን ለመንፈሳዊ እድገት በተሰጠ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ባለው ማህበረሰብ
ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎች እንድንሆን ያደርገናል።
• አማኞች የክርስቶስ አካል ናቸው (ሮሜ 12፡5) ። ስለዚህም እኛ በምድር ላይ የእርሱ
እጆችና እግሮች ነን፤ የእርሱን ሥራ የምናስቀጥል ነን:: (1 ቆሮንቶስ 12፡4–12፣ ሮሜ 12፡
4–8 እና ኤፌሶን 4፡11–13) ለሰውነት የተሰጡ ስጦታዎችን ዘርዝሯል። ብዙ ሰዎች
እነዚያን ስጦታዎች መለየትና መግለጽ የሚጀምሩበት ትንሽ ቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
ናቸው።
• የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታችንን ስናገኝ እና ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች አማኞች ጋር
ያለንን ግንኙነት ስናጠናክር (ቆላስይስ 2፡7)፣ በትምህርት ቤታችን፣ በአከባቢያችን እና
በስራ ቦታ ላሉ ሰዎች ወንጌልን ለመስበክ እና ለመካፈል በተሻለ ሁኔታ እንዘጋጃለን።
6.4 ጠንካራ መጋቢያዊ እንክብካቤና ማማከር ማጠናከር

የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና የምክር አገልግሎት በቤተ ውክርስቲያን ዉስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች ሲኖሩ
ለመርዳት አስፈላጊ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ተግዳሮቶች ከግል መንፈሳዊ ችግሮች ጋር እና
በክርስቲያን ማህበረሰቡ ውስጥ ባሉት ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክር
ተግዳሮቶችን ከመፍታት አንጻር ያለዉ ጥቅም፡-
• 1. ስሜታዊ ፈውስ እና መንፈሳዊ እድገትን ያበረታታል፡ - የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክርን
ያበረታታል፤ በጸሎት እና በምክር ከመንፈሳዊ የዉስጥ ስብራት መፈወስ፤በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት
እና በግል ምክር በመንፈሳዊ እንዲፈውሱ ሊረዳቸው ይችላል፡፡
• 2. ግንኙነትን ያሻሽላል፡- የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክር በቤተሰብ አባላት፤ በመሪዎች እና
በቤተሰቦች መካከል በተለይም በግጭት ወቅት መካከል የመግባቢያ ግንኙነትን ለማሻሻል ይረዳሉ፡፡
• 3. ማኅበረሰቡን ያሻሽላል፡- የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክር በቤተክርስቲያን ማህበረሰብ
ውስጥ ጠንካራ ግንኙነቶችን ለመገንባት፤ በአስቸጋሪ ጊዜያት አንዳቸው ለሌላው ፍቅር እና ፍቅርን
የሚያበረታቱ ጠንካራ ግንኙነቶችን ለመገንባት ይረዳሉ፡፡
• 4. ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ያበረታታል፡- የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክር መንፈሳዊ፤
አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነትን ጨምሮ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን በማቆየት እና በማስተዋወቅ
ላይ ያተኩራሉ፡፡ ይህ ግለሰቦች ፍጻሜና ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖሩ ሊረዳ ይችላል፡፡
በአጠቃላይ የመጋቢያዊ እንክብካቤ እና ምክር፤ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተለያዩ ተፈታታኝ
ሁኔታዎችን እና ግጭቶችን ለማሸነፍ፤ ፈውስ፤ እድገትን እና አንድነትን የሚያስተዋውቁ የተለያዩ
ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለማሸነፍ ይረዳሉ፡፡
6.5 ስልታዊ እቅድ መንደፍ

• ጥሩ የቤተክርስቲያኗ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማዘጋጀት በመንፈሳዊ ፈተናዎች ከመወሰድ ሊረዳ


ይችላል፡፡ ቤተክርስቲያኗ በዋና እሴቶቻቸው እና ግቦች ላይ ያተኮረች መሆኑን መሪዎች ሀብቶችን
እንዴት እንደሚመደቡ እና ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገሮች በተመለከተ መረጃ እንዲሰጡ ሊረዳ
ይችላል፡፡
• በተጨማሪም፤ በጥሩ ሁኔታ የተሠራ የስልታዊ ዕቅድ እምነትን፤ ተጠያቂነትን እና ትብብር
በቤተክርስቲያኑ ማህበረሰብ ውስጥ መተማመንን ለማጎልበት እና ግንኙነቶችን ለማጠንከር ሊረዳ
ይችላል፡፡
• በመጨረሻም ጠንካራ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላት በእምነታቸው
እንዲጠነክሩ መርዳት፤ ቤተክርስቲያኗ ሁኔታዎችን ከመለወጥ እና ተልእኮውን መወጣት
እንደምትችል ማረጋገጥ ይችላል፡፡
ማጠቃለያ

• ቤተ ክርስቲያን የአማኞች ሰብሰብ መሆኗኗ ተልዕኮዋም አንዱ ደቀመዛሙርት እያስተማረችና በጥበብም


እየገሰጸች ወደ በሳል የክርስትና ሕይወት ውስጥ በማምጣት ክርስቶስን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡
• አመቺው መንገድ አማኞችን በተለያየ አይነት የአገልግሎት መንገድ በማስተማር፤ በመምከር በመገሰጽ ከዘመኑ
ተግዳሮት በመጠበቅ ለጌታ ቀን እንዲበቁ እደሆነ መገንዘብ ይገባል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያን መሪዎች
ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው አማኞች በመከታተል ተገቢውንና ትክክለኛውን የእግዚብሔር ቃል
እንዲመገቡ፣ በራሳቸው መጽሀፍ ቅዱስን የማጥናት ልምድ እንዲያዳብሩ፣ በጸጋቸው እርስ በእርስ አገልግሎትም
መደጋገፍ እንዲችሉ ብሎም ለአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንና ለምድራችን መፍትሔ የሚያመጡ ሆነው እንዲዘጋጁ
ሁኔታዎችን ሁሉ ማመቻቸት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም አማኞች አገልግሎት
ነውና (ኤፌ 4፡16)፡፡ ይህንን በቅንነት ተግባራዊ የምታደርግ ቤተ ክርስቲያን በሳል አማኞችን በማፍራት ወይም
በክርስቶስ ፍጹም የሆነን ሰው ለእግዚአብሔር በማቅረብ ረገድ የማታሳፍር ትሆናለች (ቆላ 1፡28-29)፡፡

You might also like