Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 71

የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎችን በመስኖ

ማምረት

ለእንስሳት ልማት ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በተለይ


የተዘጋጀ
ታህሳስ 2009
ሆለታ ምርምር ማዕከል
ተስማሚ የመስኖ ዉሃ
¾}hhK< S•ማጠጫ ዓይነቶችን
°îªƒ ´`Á­ መምረጥ
‹“ ›S^[ƒ
1. የመስኖ መገልገያ ማሽነሪ ለመምረጥ ታሳቢ ጉዳዮች

1.1. የሚለማው ዝርያ ዓይነት፣ የአፈር፣ የውሃ፣ እና የመሬት አቀማመጥ

1 . የሰብሉ ዝርያ እና አያያዝ


2 . የአፈር ሁኔታ፡-
ሀ. የአሸዋማነት ዓይነት፣ ጥልቀት፣ አንድ-ወጥነት
ለ. ውሃ ስርገት ፍጥነት እና የመሸርሸር አደጋ
ሐ. ጨዋማነት እና ውስጣዊ ተንጠፍጣፊነት
3. የመሬት አቀማመጥ፡- ተዳፋትነት እና አጓጉሌ አቀማመጥ
4. የውሃ አቅርቦት
ሀ. የዉሃ ምንጩ እና የአቅርቦት ፕሮግራም
ለ. የውሃ ብዛት/ብቁነት እና አስተማማኝነት
ሐ. የውሃ ጥራት፡- የኬሚካል እና ሌሎች ጠጣር ነገሮች ይዘት
5. የአየር ንብረት ሁኔታ
6. የደራሽ ጎርፍ ስጋት መኖር
7. የከርሰ-ምድር ውሃ ጥልቀት
8. የኃይል አቅርቦት እና አስተማማኝነት
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

1. ታሳቢ ጉዳዮች ...


1.2. የኢኮኖሚ እና ሶሻል ሁኔታ
1. የሚያስፈልገው የካፒታል ሁኔታ
2. የብድር አገልግሎት እና የወለድ ሁኔታ
3. የማሽነሪ አቅርቦትና የግልጋሎት ዘመን
4. የወጭ እና የዋጋ ግሽበት ሁኔታ
ሀ. የኃይል፣ ኦፕሬሽን እና ዕድሳት ወጭዎች ሁኔታ
ለ. የጉልበት ወጭ (የሰለጠነ፣ ያልሰለጠነ)
5. የአካባቢው መንግስታዊ/ሕዝባዊ ተቋማትና ሕዝብ ትብብር፣ ጤናማ ግንኙነት
6. የሰለጠነ እና የጉልበት ሰራተኛ መኖር/አለመኖር
7. የአካባቢው ኗሪ እና መንግስት የሚጠብቀው ግልጋሎት/ጥቅም
ተስማሚ የመስኖ ዉሃ
¾}hhK< S•ማጠጫ ዓይነቶችን
°îªƒ ´`Á­ መምረጥ
‹“ ›S^[ƒ
2. አማራጭ የመስኖ ዉሃ ማጠጫ መገልገያ ዓይነቶች

2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS


1. Basin Irrigation
2. Border Strip Irrigation
3. Furrow Irrigation
2.2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS
1. Hand-Move or Portable Sprinkler System
2. Side Roll System
3. Traveling Gun System
4. Center Pivot and Linear Move Systems
2.3. TRICKLE IRRIGATION SYSTEMS
1. Drip irrigation
2. Bubbler irrigation
3. Micro-spray irrigation
4. Subsurface irrigation
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS
2.1.1. Basin Irrigation
• Basin irrigation is a type of surface irrigation in which water is applied to
a completely level ("dead-level") area enclosed by dikes or borders.
• Used successfully for both field (+ pasture) and row crops.
• Basin floor may be flat, ridged or shaped into beds, depending on crop &
cultural practices. Level basins simplify water management
• Basin shape (ገበቴ) need not be rectangular or straight sided
• Basin size is limited by available water stream size, topography, soil
factors, and degree of leveling required.
• Basin size could be quite small or as large as 15 ha
• Basin irrigation is most effective on uniform soils, precisely leveled, when
large stream sizes.
• High efficiencies are possible with low labor requirements.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS …
2.1.1. Basin Irrigation …
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS …
2.1.2. Border strip Irrigation
• Border strip irrigation uses land formed into strips, level across the
narrow dimension but sloping along the long dimension, and
bounded by ridges or borders.
• Water is turned into the upper end of the border strip, and
advances down the strip.
• High irrigation efficiencies are possible with this method of
irrigation, but there is a difficulty of balancing the advance and
recession phases of water application.
• Border strip irrigation is one of the most complicated of all
irrigation methods.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS …
2.1.2. Border strip Irrigation…
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS …
2.1.3. Furrow Irrigation
• Furrows are sloping channels formed in the soil, whereby
infiltration occurs laterally & vertically through the wetted
perimeter of the furrow.
• Furrow lengths are optimized by intake rates & stream size.
• Design & management related parameters are controllable so
furrow irrigation systems can be utilized in many situations, within
the limits of soil uniformity & topography.
• With runoff return flow systems, furrow irrigation can be a highly
uniform and efficient method of applying water.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2.1. SURFACE IRRIGATION SYSTEMS …
2.1.3. Furrow Irrigation
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS


• In sprinkler irrigation, water is delivered through a pressurized pipe
network to sprinklers, nozzles or jets which spray the water into the air,
to fall to the soil in an artificial "rain".
• The basic components of any sprinkler systems are:
1. a water source,
2. a pump to pressurize the water,
3. a pipe network to distribute the water throughout the field,
4. sprinklers to spray the water over the ground, and
5. valves to control the flow of water.
• There are 4 types of sprinkler irrigation system:
1. Hand-Move or Portable Sprinkler System
2. Side Roll System
3. Traveling Gun System
4. Center Pivot and Linear Move Systems
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …
2.1. Hand-move or portable sprinkler system
These systems employ a lateral pipeline with sprinklers installed at regular
intervals. The lateral pipe is made of aluminum, with 6, 9, or 12 meter
sections, and special quick-coupling connections at each pipe joint.
• The sprinkler is installed on a pipe riser so that it may operate above the
crop being grown
• The risers are connected to the lateral at the pipe coupling, with the length
of pipe section chosen to correspond to the desired sprinkler spacing.
– The sprinkler lateral is placed in one location and operated until the desired water
application has been made.
– Then the lateral line is disassembled and moved to the next position to be irrigated.
• This type of sprinkler system has a low initial cost, but a high labor
requirement.
• It can be used on most crops, though with some, such as corn, the laterals
become difficult to move as the crop reaches maturity.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …


2.1. Hand-move or portable sprinkler system …
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …


2.1. Side roll system
• This system is a variation on the hand-moved lateral
sprinkler line. The lateral line is mounted on wheels,
with the pipe forming the axle (strengthened pipe &
couplers are used).
• The wheel height is selected so that the axle clears the
crop as it is moved.
• A drive unit, usually an air-cooled gasoline-powered
engine located near the center of the lateral, is used to
move the system from one irrigation position to another
by rolling the wheels.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …


2.1. Side roll system …
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …
2.3. Traveling Gun System
• This system utilizes a high volume, high pressure sprinkler ("gun")
mounted on a trailer, with water being supplied through a flexible
hose or from an open ditch along which the trailer passes.
• The gun may be operated in a stationary position for the desired
time, and then moved to the next location. However, the most
common use is as a continuous move system, where the gun
sprinkles as it moves.
• The trailer may be moved through the field by a winch and cable, or
it may be pulled along as the hose is wound up on a reel at the edge
of the field.
• These systems can be used on most crops, though due to the large
droplets and high application rates produced, they are best suited to
coarse soils having high intake rates and to crops providing good
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …


2.3. Traveling Gun System …
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ
2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS …
2.4. Center Pivot and Linear Move Systems
• The center pivot system consists of a single sprinkler lateral supported
by a series of towers. The towers are self-propelled so that the lateral
rotates around a pivot point in the center of the irrigated area.
• The time for the system to revolve through one complete circle can
range from a half a day to many days.
• The longer the lateral, the faster the end of the lateral travels and the
larger the area irrigated by the end section.
• The high application rate at the outer end of the system may cause
runoff on some soils.
• Since the center pivot irrigates a circle, it leaves the corners of the field
unirrigated (unless additions of special equipment are made to the
system).
• Center pivots are capable of irrigating most field crops, but usually been
used on tree and vine crops.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

2. SPRINKLER IRRIGATION SYSTEMS


2.4. Center Pivot and Linear Move Systems
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

3. TRICKLE IRRIGATION SYSTEMS


• Trickle irrigation is the slow, frequent application of water
to the soil though emitters placed along a water delivery
line.
• There are 4 types of trickle irrigation system:

3.1. Drip irrigation


3.2. Subsurface irrigation
3.3. Bubbler irrigation
3.4. Micro-spray irrigation
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

3. TRICKLE IRRIGATION SYSTEMS …


3.1. Drip irrigation applies the water through small emitters
to the soil surface, usually at or near the plant to be
irrigated.
3.2. Bubbler irrigation is the application of a small stream
of water to the soil surface. The applicator discharge rate
(up to 250 liters per hour) exceeds the soil's infiltration
rate, so the water ponds on the soil surface. A small basin
is used to control the distribution of water.
3.3. Micro-spray irrigation applies water to the soil surface
by a small spray or mist. Discharge rates are usually less
than 120 liters per hour.
¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

3. TRICKLE IRRIGATION SYSTEMS …

Drip irrigation, Bubbler, Micro-spray


¾}hhK<
ተስማሚ S•ማጠጫ
የመስኖ ዉሃ °îªƒ ´`Á­‹“ ›S^[ƒ
ዓይነቶችን መምረጥ

3. TRICKLE IRRIGATION SYSTEMS …


3.4. Subsurface irrigation
• is the application of water below the soil surface.
• Emitter discharge rates for drip and subsurface irrigation
are generally less than 12 liters per hour.
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

Best bet grass species

Rhodes grass (Chloris gayana)


Sudan grass (Sorghum sudanense)
Blue panic (Panicum antidotale)
Buffel grass (Cenchrus ciliaris
Gamba grass (Andropogon gayanus)
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
1. ዝሆኔ ሣር (Pennisetum purpureum)
መግለጫ፡-
የዝሆኔ ሣር የናፒየር ሣር በመባልም ይታወቃል፡፡ ከሰንባች የመኖ ሣር
ዓይነቶች የሚመደብ ሲሆን ወደ አፈር ጠልቀዉ የሚገቡ ጠንካራ ሥሮች
አሉት፡፡ እንደ አፈሩ ለምነትና እንደ ሥነ-ምህዳሩ ሁኔታ ከ 2 ሜትር እስከ
6 ሜትር የሚደርስ ቁሜት ሲኖረዉ፣ ሰፋፊ (ከ 20-40 ሳ.ሜ. ዲያሜትር
ያላቸዉ) እና ረጃጅም (አንድ ሜትር ሊደርሱ የሚችሉ) ቅጠሎች አሉት፡፡
አመራረት
የዝሆኔ ሣር በአገዳና በሥር ቁርጥራጭ ይባዛል፡፡ የአገዳ ቁርጥራጭ
የምንጠቀም ከሆነ ለዚህ ዓላማ የሚዘጋጀው አገዳ ቢያንስ ሦስት
አንጓዎች ሊኖሩት የሚገባ ሲሆን በመትከያ ቦይ ዉስጥ በ45
ድግሪ ተጋድሞ መተከል አለበት፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
1. ዝሆኔ ሣር (Pennisetum purpureum) …
መግለጫ፡-
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
1. ዝሆኔ ሣር (Pennisetum purpureum)
አመራረት …፡-
• የዝሆን ሣር ታርሶ በደንብ የለሰለሰ አፈርን ይፈልጋል፡፡ እንደ መሬቱ ሁኔታ
ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ቢታረስ ይመረጣል፡፡
• ከተከላ በፊት 25 ሣ.ሜ ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ቆፍሮ ማዘጋጀትና ከዚያም ዝናብ
በተረጋጋና ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ ሲዘንብና አፈሩ በቂ እርጥበት ያለዉ መሆኑን
ካረጋገጡ በኋላ መትከል ይገባል፡፡
• የአገዳም ሆነ የሥር ቁርጥራጮችን 2/3ኛን ክፍል ከአፈር በታች በመቅበርና
1/3ኛውን ክፍል ከአፈር በላይ በማድረግ መትከል ቁርጥራጩ እንዳይደርቅ
ይከላከላል፡፡
• በተከላ ወቅት በመስመር ውስጥ በቁርጥራጮች መካከል ያለው ርቀት ከ50-100
ሳ.ሜ. መሆን እንዳለበትና በመስመሮች መካከል ደግሞ የአንድ ሜትር ርቀት
ቢኖር የተሻለ ነው፡፡
• በዚህ ስሌት በሄክታር ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ ቁርጥራጮች ያስፈልጋሉ ማለት
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
1. ዝሆኔ ሣር (Pennisetum purpureum)
አጠቃቀም፡-
• የዝሆን ሣር በአብዛኛዉ ታጭዶ ለእንስሳት የሚቀርብ የሣር አይነት ነው፡፡ ይህም
በተለምዶ “Cut and Carry” የሚባለው የአጠቃቀም ስልት ነው፡፡ የሰብሉን የቆይታ
ዘመን ሊያሳጥር ስለሚችል ሣሩን በተተከለበት ዓመት አጭዶ አለመጠቀም
ይመረጣል፡፡
• ሰብሉን አጭዶ መጠቀሙ በሁለተኛው ዓመት ቢጀመር የሚመከር ሲሆን አጨዳዉም
ከተካሄደ በኋላ በፍጥነት ማገገም እንድችል በቂ ውኃ ማጠጣት ያስፈልጋል፡፡
በሚታጨድበት ጊዜ ከመሬት በላይ ከ5-10 ሣ.ሜ የሚደርስ የገቦ ቁመት በማስቀረት
ቢሆን የተሻለ ነዉ፡፡
• እንዳ የአፈር እርጥበት ሁኔታ ከአጨዳ በኋላ በየስድስት ሣምንታት ወይም የዋናዉ
አገዳ ቁመት አንድ ሜትር ሲሆን እያጨዱ ለእንስሳት ማቅረብ ይቻላል፡፡
• የመስኖ ውኃ አቅርቦት እጥረት ባለበት ጊዜ ሰብሉን ማጨድ አይመከርም፤ ይህም
የሰብሉን የአገልግሎት ዘመን ለማራዘም ይጠቅማል፡፡
• ማዳበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በሄ/ር እስከ 8 ቶን ፍግ መጨመር፤ ወይም
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
2. ሮደስ (Chloris gayana)
መግለጫ፡-
የሮደስ ሣር በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በስፋት
የሚታወቅ በመስኖ ሊለማ የሚችል የሣር ዓይነት ነዉ፡፡ ቁመቱ
እስከ 90 ሣ.ሜ. የሚደርስ ሲሆን ሥሮቹም እስከ አምስት ሜትር
ወደ አፈር ጠልቀዉ መግባት የሚችሉ ናቸዉ፡፡

በተለያዩ ሥነ-ምህዳራት የሚላመድና በአጭር ጊዜ ዉስጥ


በመስፋፋት የተዘራበትን መሬት መሸፈን የሚችል የሣር ዓይነት
ሲሆን በተለይ ለድርቆሽ ዝግጅት በስፋት ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
2. ሮደስ (Chloris gayana)
መግለጫ:-
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
2. ሮደስ (Chloris gayana)
ተመራጭ ዝርያና የዘር ምንጭ
• ካላይድና ማሳባ የሚባሉትን የሮዳስ ሣር ዓይነቶች በዝናብ አጠር
አካባቢዎች መስኖን በመጠቀም ማልማት እንደሚቻል
ተረጋግጧል፡፡
• የመነሻ ዘሩን ከተለያዩ የምርምር ማዕከላት፤ ከግል ዘር አባዥ
ድርጅቶች፤ ከአካባቢ ገበሬና ከመንግሥት የችግኝ ጣቢያዎች
ማግኘት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
2. ሮደስ (Chloris gayana) …
የአመራረት ዘዴ፡-
• ሮደስ የሚዘራበት ማሣ በደንብ ታርሶ የለሰለሰ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከዚያ 25
ሳ.ሜ. የሚራራቁ የመዝሪያ ቦዮችን ማዘጋጀትና ከዚያም ዘሩን በቦዮቹ ውስጥ
መዝራት ነዉ፡፡
• የዘር መጠን በሄ/ር እንደ ዘሩ ጥራት የሚለያይ ቢሆንም ከ5-10 ኪ.ግ መጠቀም
እንደሚቻል የተለያዩ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
• የተዘራውን ዘር በአፈር በስሱ ማልበስ የሚያስፈልግ ሲሆን ዘሮቹ በጓልና በአፈር
ዉስጥ በጥልቀት እንዳይቀበሩ ጥንቃቄ ያሻል፡፡
• በመስኖ የሚለማን ሮዴስ በማንኛውም ጊዜ መዝራት የሚቻል ሲሆን፤ በዝናብ
ከሆነ ዝናብ እንደዘነበ ቀደም ብሎ መዝራቱ ይመከራል፡፡ አረም በሚበዛባቸው
አካባቢዎች በመጀመሪያ በእጅና በመኮትኮቻ በመጠቀም አረሞቹን ማስወገድ
ወሳኝ ነው፡፡
አጠቃቀም:- የመሬት ችግር በሌለበት በስፋት በመስኖ ማምረትና በድርቆሽ መልክ
አዘጋጅቶ መጠቀም ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
3. ፓራ ግራስ (Brachiaria mutica) …
መግለጫ፡-
• ፓራ ግራስ በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ሊለሙ ከሚችሉ የሣር
ዓይነቶች ተመራጩ ነው፡፡
• በተለያዩ የአፈር ዓይነቶች ላይ መብቀል የሚችልና
አሲዳማነትንም የሚቋቋም ሣር ነዉ፡፡
• በሰፋፊ እርሻዎች ላይ ቋሚ ግጦሽን ለማቋቋም የሚጠቅም
ሲሆን አነስተኛ ይዞታ ባላቸዉም ገበሬዎች ከውሃ ማቆር ጋር
በማቀናጀት ለቆርጦ ምገባ ዘዴ ሊለማ ይችላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
3. ፓራ ግራስ (Brachiaria mutica) …
ተመራጭ ዝርያና የዘር ምንጭ:-
• በደብረ ዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል የተመረጠዉን
የብራኪያሪያ ዝሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ለመነሻ የሚሆን
የግንድ/የሥር ቁርጥራጭም ከዚሁ ማዕከል ማግኘት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
3. ፓራ ግራስ (Brachiaria mutica) …
የአመራረት ዘዴ፡-
• ዘር የምንጠቀም ከሆነ ተሰብስቦ ከ6-12 ወራት ተከዝኖ የቆየዉን መጠቀሙ የሚመከር
ነዉ፡፡ አዲስ የተሰበሰበ ዘር የብቅለት ደረጃው አነስተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል፡፡
• በሄክታር ከ5-10 ኪ.ግ ዘር መጠቀም ሲቻል የብቅለት ደረጃዉን ለማሻሻልም ከተዘራ
በኋላ በአፈር ማልበስ አስፈላጊ ነው፡፡ በመስኖ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ መዝራት የሚቻል
ሲሆን በዝናብ ከሆነ ግን ዝናብ በተረጋጋ ሁኔታ መጣል ሲጀምር ቀደም ብሎ
መዝራቱ/መትከሉ የሚመረጥ አካሄድ ነዉ፡፡
• ፓራ ገራስ በተለይ ረግረጋማ ቦታዎችና ረባዳ ማሳዎች ላይ መመረት የሚችል አለያም
በቂ መስኖ ዉሃ ባለበት ቆላማ አካባቢ መልማት የሚችል ዘላቂ ሳር ነው፣ ለውርጭና
ድርቅ ግን ተጋላጭ ዝርያ ነው፡፡
• ለተሻለ የመኖ ምርት በመጀመሪያው ዓመት 100 ኪ.ግ. ዳኘና 100 ኪ.ግ. ዩሪያ ከዚያም
በየዓመቱ 100 ኪ.ግ ዩሪያ መጠቀም የምርታማነት ወቅቱን ያራዝማል፡፡
• በመጀመሪያ ዓመት የአረም ቁጥጥር ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን ሣሩ እየተስፋፋ ሲሄድ
ግን የአረም ችግር እምብዛም አሳሳቢ ስለማይሆን እንደ አስፈላጊነቱ ተከታትሎ የአረም
ቁጥጥሩን ማከናወን ይገባል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
3. ፓራ ግራስ (Brachiaria mutica) …
አጠቃቀም :-
• ፓራ ገራስ እንደማንኛውም ሣር ዕድሜው በጨመረ ቁጥር
የንጥረ-ነገር ይዘቱ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡
• በመሆኑም እንደአካባቢው ሁኔታ ሳይቀነጭር በፊት በቅጠላማ
የእድገት ደረጃዉ (በግምት 100% ድረስ ሲያብብ) አጭዶ
በመመገብ ወይም በድርቆሽ መልክ አዘጋጅቶ በመከዘን በዕቅድ
መጠቀም ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
4. ብሉ ፓኒክ (Panicum antidotale) …
መግለጫ፡-
• ይህ የሣር ዓይነት ከህንድ የተገኘ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን ጨምሮ
በብዙ አገሮች እንደሚላመድ ተረጋግጧል፡፡
• በወረር ምርምር ማዕከል ተገምግሞ ምርታማ እንደሆነና በመስኖ በስፋት
ሊለሙ ከሚችሉ የሣር ዓይነቶች አንዱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ተመራጭ ዝሪያና የዘር ምንጭ
• በወረር ምርምር ማዕከል ተገምግሞ የተመረጠዉን ዝሪያ መጠቀም
ይቻላል፡፡
• ለመነሻ የሚሆን ዘርን ከዚሁ ማዕከልና ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር
ተቋም (ILRI) እንዲሁም ከሌሎች የግል ዘር አባዥ ድርጅቶች ገዝቶ
መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታም ስላለ ይህንንም አማራጭ መሞከር
ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
4. ብሉ ፓኒክ (Panicum antidotale) …
መግለጫ፡-
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ ሣር ዝርያዎች

ዘላቂ ሣር …
4. ብሉ ፓኒክ (Panicum antidotale) …
የአመራረት ዘዴ
• ይህ ሳር የሚዘራበትን ማሳ ደጋግሞ ማረስና ማለስለስ
ያስፈልጋል፡፡ በመስመር ለመዝራት 1 ሜትር በማራራቅ ከ2-3
ኪ.ግ. ዘር በሄክታር፤ በብተና ደግሞ ከ6-7 ኪ.ግ. ዘር በሄክታር
መጠቀም ይቻላል፡፡
• የናይትሮጅን እና ፎስፌት ማዳበሪያ 30 በ30 ኪ.ግ. ድበልቅ በዘር
ጊዜና በየአጨዳ ጊዜ መለገስ፤ ወይንም የተብላላ ፍግ 5-15
ቶን/ሄክታር በየአጨዳ ወቅት መጨመር ምርታማነቱን ያሻሽላል፡፡
አጠቃቀም
• ይህ ሳር ለግጦሽም ሆነ ለድርቆሽ አጠቃቀም የተመቸ ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

Best bet legume species

Alfalfa (Medicago sativa)

Siratro (M. atropurpureum)

Stylo (Stylosanthes guyanensis)


ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

1. አልፋልፋ (ሉሰርን)
• መግለጫ:- አልፋልፋ ቁመቱ እስከ አንድ ሜትር ተኩል የሚደርስ፣ ቅጠላማ
እና በፕሮቲን፣ ቪታሚን እና ሚኒራሎች የበለጸገ ዘላቂ የአባዝር ዝርያ ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

1. አልፋልፋ (ሉሰርን)
ተስማሚ ሥነ-ምህዳር: -
አልፋልፋ ሰፊ የሥነምህዳር ተላማጅነት አለው፡፡ ስለሆነም ከባህር ጠለል በላይ 1000
ሜትር ከፍታ ባላቸው ቆላማ ወረዳዎች እስከ 2500 ሜትር ከፍታ ባላቸው
ደጋማ አካባቢዎች ሁሉ አልፋልፋ ሊለማ እና ጥሩ ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡
• ለበለጠ ውጤት አልፋልፋ ጥልቀት ያለው አሸዋማ (ገምቦሬ፣ አቦልሲ) ይፈልጋል፡፡
• ወሃ የሚያቁር መሬት ለአልፋልፋ ሰብል አይስማማውም፣ ሥር ለሚያበሰብስ
በሽሽታ ከማጋለጡም አልፎ ናይትሮጅን የማቆሪያ አካሎቹን በመጉዳት በዚህ
ማዕድን ራሱን እንዳይችል ያደርገዋል፣ ውርጭ እንዳይቋቋምም ያዳክመዋል፡፡
• አልፋልፋ ከ ኮምጣጣ ቀይ አፈር ይልቅ ወደ ጨዋማ ወይም አማካይ የአፈር ዓይነት
ያደላል፡፡ የአልፋልፋ ሥሮች ወደመሬት ጠልቀው ስለሚሄዱ ድርቅ የመቋቋም
ችሎታው ከፍተኛ ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

1. አልፋልፋ (ሉሰርን) ...


• አመራረት፡- ለአነስተኛ የከብት እርባታ ለምሳሌ የጓሮ መኖ ለማልማት በሚፈለግ
ጊዜ አልፋለፋ በከብት በረት አካባቢ እንዲለማ ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም 1ኛ)
በተለያየ መንገድ ከተከማቸ ውሃ መጠቀም ያስችላል 2ኛ) ፍግ በቅርብ ስለሚገኝ
ጉልበት ይቀንሳል 3ኛ) አብዛኛው የመኖ አጠቃቀም በድጎማ መልክ እንደመሆኑ
ለመመገብ የሚወስደው የትራንስፖርት ዋጋ እና ድካም ይቀንሳል፡፡
• አልፋልፋ በደንብ ታርሶ በለሰለሰ እና በተጠቀጠቀ ማሳ ቢዘራ መልካም ነው፡፡
ለድጎማ አጠቃቀም አልፋልፋ በነጠላ (አንድ-ወጥ አዝመራ) ስለሚዘራ የዘር
መጠኑ በመስኖ ከሆነ ከ 10 እስከ 20 ኪ. ግ. በሄክታር:: በዝናብ ብቻ የሚለማ
ከሆነ ደግሞ ከ 6 እስከ 12 ኪ.ግ. በሄክታር ሊዘራ ይገባል፡፡
• የማዳበሪያ ፍላጎት: በሚዘራበት ጊዜ 40 ኪ. ግ በሄክታር ፎስፌት መለገሥ
• የምርት መጠን: የመኖ ምርት ከ 7 እስከ 17 ቶን ድርቆ መኖ በአንድ ሄክታር
(በመስኖ አመራረት) ያስገኛል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

1. አልፋልፋ (ሉሰርን) ...


አጠቃቀም:-
የአልፋልፋ ሰብል መታጨድ የሚጀመርበት ወቅት ቢያንስ የሰብሉ 50 ከመቶ ካበበ በኋላ
ሲሆን እጅግ ቢዘገይ ሰብሉ ሙሉ በሙሉ አብቦ ፍሬ መያዝ ሲጀምር መታጨድ አለበት፡፡
• አልፋልፋ በፕሮቲን የበለጸገ እንደመሆኑ አብዛኛው አጠቃቀም ለታላቢ ላሞችና ጥጃዎች
በድጎማ መልክ እርጥቡን አጭዶ መመገብ:: አለዚያም በድርቆሽ መልክ አዘጋጅቶ በመኖ
መጋዘን መከዘንና ለዘወትር ቀለብ (ገለባና አገር በቀል ድርቆሽ) መደጎሚያ ማዋል ነው፡፡
• የአልፋልፋ የዋና ዋና አልሚ-ምግብ ይዘት፡ 22.7 ኪ.ግ ፕሮቲን (ናይትሮጅን)፣ 4.54
ኪ.ግ. ፎስፎረስ እና 27.24 ኪ.ግ. ፖታሲዬም በ አንድ ሺህ ኪሎ ግራም ደረቅ መኖ
እንደሆነ ይገመታል፡፡
• የአልፋልፋ አመጋገብ ባህል ብዙውን ጊዜ በየቀኑ እርጥቡን ነዶ እያጨዱ በማለቢያ ስዓት
በመመገቢያ ገንዳቸው ላይ በማቅረብ እየታለቡ እንዲመገቡ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ልማድ
ያደረጉ ላሞች ተረጋግተው ይታለባሉ፡፡
• የአልፋልፋ ሰብል በተለይ በመስኖ ከታገዘ በየ 2-3 ወራት ለአጨዳ ስለሚደርስ ዓመቱን
ሙሉ የመኖ አቅርቦት አይቋረጥም፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

2. ስታይሎ (Stylosanthes guyanensis)


መግለጫ፡-
• ይህ ዘላቂ የአባዝር መኖ በመስኖ ሊለማ የሚችል ሲሆን
በመካከለኛ ደረጃ ጥራቱና የደረቅ ነዶ ምርቱ ይታወቃል፡፡
በቆላማና እርጥበታማ ቀይ አፈር (አሲዳማ) አካባቢዎች በተለይ
በደንብ የሚላመድ የመኖ ሰብል ዓይነት መሆኑም ሌላው ተወዳጅ
ገጽታው ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

2. ስታይሎ (Stylosanthes guyanensis) ...


ተመራጭ ዝርያና የዘር ምንጭ
• በኢትዮጵያ በመደበኛው የዝርያ አለቃቀቅ ዘዴ ወጥቶ የተመዘገበ ዝሪያ የለም፡፡ ሆኖም
በባኮና በዓለም ዓቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም ለኢትዮጵያ ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ
ዝሪያዎች ተለይተው የታወቁ ስለሆነ የሰብሉን መነሻ ዘር ከነዚህ ተቋማት ማግኘት
ይቻላል፡፡
አመራረት፡-
• ስታይሎ በዘር የሚራባ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በተፈጥሮ ግጦሽ ላይ በመዝራትና የተጐዱ
አፈሮችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ጠቄሜታ አለው፡፡
• ስታይሎ በተለይ አሲዳማ አፈርን የሚወድ በመሆኑ ለዚህ ዓይነት አፈር ማቅኛ ተመራጭ
ዘላቂ የአባዝር መኖ ዝርያ ነው፡፡
• ከመዘራቱ በፊት ዘሩን በብርጭቆ ወረቀት መፈተግ የብቅለት ደረጃውን እንደሚያሻሽል
ተረጋግጧል፡፡ የስታይሎን ዘር ዝናብ ከመጣሉ በፊት በደረቅ አፈር መዝራት ይቻላል፤
ወይም ልክ ዝናብ እንደዘነበ ቀደም ብሎ መዝራቱ ይመከራል፡፡
• በመስኖ ከሆነ ግን በማንኛውም ጊዜ ሊዘራ ይችላል፡፡ የዘር መጠን በሚመለከት በሄ/ር እስከ
5 ኪ.ግ መጠቀም እንደሚቻል ተረጋግጧል፡፡ የፎስፈረስ ማዳበሪያ አስፈላጊ በመሆነ
በዓመት 100 ኪ.ግ ዳፕ መጨመር እንደሚገባ ይመከራል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

2. ስታይሎ (Stylosanthes guyanensis)


አጠቃቀም፡-
• ስታይሎ በመጀመሪያው ዓመት ማስጋጥ ወይም ቆርጦ መመገብ
አይመከርም፡፡ ከሁለተኛው ዓመት ጀምሮ እንስሳትን በማስጋጥ፣
ቆርጦ በማቅረብ ወይም በድርቆሽ መልክ በማዘጀት መጠቀም
ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

3. ሲራትሮ (Macroptilium atropurpureum)


መግለጫ፡-
• ሲራትሮ በመስኖ ሊለሙ ከሚችሉ የቅጠላ ቅጠል መኖ ዓይነቶች አንዱ
ነው፡፡ ይህ የመኖ ሰብል ከፍተኛ ፕሮቲን ያለው ሲሆን በድርቆሽ መልክ
ተዘጋጅቶ በድጐማ መኖነት ሊያገለግል የሚችል ነዉ፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

3. ሲራትሮ (Macroptilium atropurpureum) ...


ተመራጭ ዝሪያና የዘር ምንጭ
• በምርምር ተለይቶ የተመዘገበ ዝሪያ በኢትዮጵያ ባይኖርም
በተለያዩ ማዕከላት ሙከራ ተደርጐባቸው በምርታማነታቸዉና
በተላማጅነታቸዉ የተለዩ ዝሪያዎች አሉ፡፡
• በባኮና በወረር ምርምር ማዕከላት የነዚህ ዝሪያዎች መነሻ ዘር
በየዓመቱ ይመረታል፡፡
• ስለዚህ መነሻ ዘሮቹን ከእነዚህ ማዕከላት ማግኘት ይቻላል፡፡ ኤዴን
ፍልድ አግሪሲድ ኢንተርፕራይዝ የተባለ የመኖ ዘር አምራች
ድርጅትም የተወሰነ ዘር በየዓመቱ የሚያመርት ስለሆነ ከዚህም
ድርጅት ለመነሻ የሚሆን ዘር ማግኘት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

3. ሲራትሮ (Macroptilium atropurpureum) ...


የአመራረት ዘዴ፡-
• ሲራትሮ በደንብ ታርሶ የለሰለሰ አፈር ይፈልጋል፡፡ ሰብሉን ዝናብ
ከመጀመሩ በፊት በደረቅ አፈር ወይም ልክ ዝናብ እንደዘነበ በጊዜ
መዝራት ይቻላል፡፡ የዘር መጠን በሄክታር እንደዘሩ የጥራት ደረጃ
የሚለያይ ሲሆን ከ2-6 ኪ.ግ. ዘር መጠቀም ይቻላል፡፡
• ሲራትሮን በመስመር መዝራት የሚመረጥ ሲሆን በመስመሮች መካከል
ያለው ርቀት 50 ሳ.ሜ. መሆን እንዳለበት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
• ለሲራትሮ የፎስፎረስ ማዳበሪያ መጠቀም የሚያስፈልግና በዓመት
100 ኪ.ግ. ዳፕ መጠቀም እንደሚገባ ይመከራል፡፡ የሲራትሮ ማሣ
ከአረም የፀዳ መሆን ያለበት ሲሆን በተለይ በመጀመሪያው ዓመት
የአረም ቁጥጥር ካልተደረገ ምርታማነቱ ስለሚቀንስ ይህንን በወቅቱ
ማከናወን ይገባል፡፡
ለመስኖ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የዘላቂ አባዝር ዝርያዎች

3. ሲራትሮ (Macroptilium atropurpureum) ...


አጠቃቀም፡-
• ሲራትሮን በመጀመሪያ ዓመት በማስጋጥም ሆነ በቆርጦ ምገባ ዘዴ
መጠቀም አይመከርም፡፡
• ምርት የመውሰዱ ሂዴት በሁለተኛው ዓመት መጀመር እንደሚገባ
ይመከራል፡፡
• መቆረጥም ያለበት ዝናብ ባለበት ወቅት ሲሆን ተቆርጦ ከጠወለገ
በኌላ በድጐማ መኖነት፤ ወይም በድርቆሽ መልክ አዘጋጅቶና ከዝኖ
ሲፈለግ ለድጎማ መኖነት ማዋል ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

1. ሰስባኒያ (Sesbania sesban)


መግለጫ፡-
• ሰስባኒያ እስከ አሥር ዓመት በምርት ላይ መቆየት የሚችል ሁለገብ
የአባዝር ዝርያ ሲሆን በፕሮቲን የበለጸገ የቅንጠባ መኖ ዛፍ ነው፡፡
• ለሰስባኒያ አመች የሆኑ የአመራረት ስልቶች፡- የጓሮ መኖ፣ በሰብል
ድንበር አኳያ፣ ከምግብ ሰብል ጋር በስብጥር፣ የቡና ጥላ በመሳሰሉት
ፈርጀ-ብዙ አጠቃቀም ስልቶች ሊለማ ይችላል፡፡

ተስማሚ ሥነ-ምህዳር፡-
• ሰስባኒያ ሰፊ የሥ-ነምህዳር ተላማጅነት አለው፡፡ ስለሆነም ከባህር
ጠለል በላይ 1000 እስከ 2400 ሜትር ከፍታ ባላቸው ደጋ እና ወይና
ደጋ አካባቢዎች ሁሉ ሊለማ ይችላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

1. ሰስባኒያ (Sesbania sesban) ...


አመራረት:
• አዘራር፡- ሰስባኒያ በቀትታ ዘር በመዝራትና በችግኝም ሊለማ ይችላል፡፡ ዘሩ ጠጣር
በመሆኑ በቶሎ እንዲበቅል መፈተግ ያስፈልገዋል፡፡ አፈታተጉም በሳልፈሪክ አሲድ
ለ30 ደቂቃ መዘፍዘፍና ከዚያም በንጹህ ውሃ አለቅልቆ በጥላ ስር ማድረቅና መዝራት
ነው፡

• በችግኝ መዝራት ተመራጭ ነው፡፡ ችግኙ ከዝናብ ወርህ ሁለት ወር ቀደም ብሎ


መፍላት አለበት፡፡

• በዘር ፍሬ መዝራት የሚመረጠው በቤት ዙሪያ ወይም በሰብል ድንበር እንደ አጥር
በረድፍ ማልማት ሲፈለግ ነው፡፡ በዚህ አካሄድ 50 ፍሬ በ አንድ ሜትር ርቀት ሂሳብ
ወይንም ከ 2 እስከ 3 ፍሬዎች በ 5 ሳ.ሜ. በተራራቁ ትንንሽ ጉድጓዶች መትከል፡፡

• በስብጥር አዝመራ፡- የሰስባኒያ ዛፎች በተተከሉበት ረድፍ መካከል ሰብል ለማልማት


ሲፈለግ በረድፎች መካከል ያለው እርቀት ከ 4 ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

1. ሰስባኒያ (Sesbania sesban) ...


• የምርት መጠን፡ ሰስባኒያ በሄክታር ከ 3000 ኪሎ ግራም በላይ
የቅጠል ድርቆሽ እና ከዚህ በተጨማሪ ከ 7000 ኪ.ግ. በላይ
የሚመዝን የአጥር ጨፈቃ ወይንም የማገዶ እንጨት ያስገኛል፡፡

• አጠቃቀም፡ ለአነስተኛ የከብት እርባታ ተስማሚ የሆነ የድጎማ


መኖ ሲሆን ለሰብል ተረፈ-ምርትና ለአገር በቀል ድርቆሽ
መደጎሚያ ከ 0.5–1.0 ሜትር ቁመት በየ 6–8 ሳምንት እየተቆረጠ
በአብዛኛው በእርጥብ መኖ መልክ አለያም ለትንሽ ስዓታት
በማጠውለግ ከዘወትር መኖ ጋር ይቀርባል፡፡ በድጎማ አመጋገብ
የዘወትር ራሽንን ከ20–30% ቢሆን መልካም ነው ነገር ግን አዋጭ
ከሆነ ከዚህ መጠን በላይ ከፍ ቢልም የሚያስከትለው የጤና ጉዳት
የለም፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

1. ሰስባኒያ (Sesbania sesban) ...


ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

2. ማክራንታ (Sesbania macrantha)


• መግለጫ:- ማክራንታ አጭር ዕድሜ ያለው የሰስባኒያ ዝርያ ዛፍ
ሲሆን ከዘላቂው ሰስባኒያ (ሰስባኒያ ሰስባን) የሚለየው ከሦስት ዓመት
የማያልፍ አጭር ዕድሜ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ የአመራረት ሥልቱ
ከሰስባኒያ ሰስባን ጋር ተመሳሳይ ነው:- የጓሮ መኖ, በአጥርና በሰብል
ድንበር, ከምግብ ተክሎች ጋር በስብጥር ሊለማ ይችላል፡፡
• ተስማሚ ሥነ-ምህዳር፡- ማክራንታ በእርጥብ ወይና ደጋ ሥ-
ነምህዳር የበለጠ ተላማጅነት አለው፡፡ ከባህር ጠለል በላይ 600 እስከ
2000 ሜትር ከፍታ ባላቸው ሞቃታማ እና ዝናባማ አካባቢዎች
ግዙፍ አስተዳደግና የመኖ ይዘት አለው፡፡
• እጅግ ፈጣን ታዳጊ በመሆኑ እንደ ሌሎች ዓመታዊ ሰብሎች በመሰኖ
በመጠቀም በዓመት ከሦስት እስከ አራት ጊዜ እየዘሩ በማጨድ
ዓመቱን ሙሉ መኖ ማምረት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

2. ማክራንታ (Sesbania macrantha)...


• አዝመራ: ማክራነታን በቀላሉ ዘር በቀጥታ በመዝራት ማልማት
ይቻላል፡፡ የዘር መጠን በማሳው ለምነትና በዝናቡ መጠን ይወሰናል፡፡
በመስመር መዝራት ተመራጭ ነው፡፡
• በአካባቢው በቂ ዝናብ ካለ ወይንም መስኖ መጠቀም ከተቻለ በመስመር
መካከል 1 ሜትር እና በተክሎች መካከል ደግሞ 0.5 ቢሆን መልካም ነው፡፡
• ተክሉ እየገዘፈ ሲሄድ በመስመሩ አቅጣጫ አንድ ተክል እየዘለሉ
መቁረጥና ማሳሳት፣ የተቆረጠውንም አጠውልጎ በድጎማ መልክ
ለእንስሳት መመገብ ይቻላል፡፡ የተብላላ ፍግ ከ 5 እስከ 10 ኩንታል
በሄክታር በመለገሥ ምርቱን በብዙ እጥፍ ማሳደግ ይቻላል፡፡
• የምርት መጠን: ማክራንታ እንደ ዓመታዊ የመኖ ሰብል ከተመረተ 3000
ኪ.ግ. የቅጠል ድርቆሽና 6000 ኪ.ግ ማገዶ እንጨት በሄክታር በየሦስት
ወር ያስገኛል፡፡ ስለዚህ በመስኖ ከሆነ አራት ጊዜ በማምረት ምርቱ ከ12
ኩንታል ያላነሰ የቅጠል ድርቆሽ መኖ ማምረት ይቻላል ማለት ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

2. ማክራንታ (Sesbania macrantha)...


• አጠቃቀም:- ለአነስተኛ የከብት እርባታ ተስማሚ የሆነ የድጎማ
መኖ ሲሆን ለሰብል ተረፈ-ምርትና ለአገር በቀል ድርቆሽ
መደጎሚያ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
• ማክራንታ እስከ ሦስት ዓመት መቆይት የሚችል መለስተኛ ዘላቂ
ቢሆንም የሚሻለው የአመራረት ዘዴ እንደ ዓመታዊ ሰብል
በሦስተኛው ወር እድሜ ማበብ ሲጀምር ከሥሩ መድምዶ
መቁረጥና በሁለት ቀን ፅሐይ አድርቆ ቅጠሉን ማራገፍና
መሰብሰብ ከዚያም የቅጠል ድርቆሹን በዶንያ ከትቶ መከዘን፡፡
• የቅጠል ድርቆሹን እንደአስፈላጊነቱ በድጎማ መልክ የዘወትር
መኖውን (ገለባና አገር በቀል የሳር ድርቆሽ) 20–30% በሆነ መጥኖ
መመገብ መልካም ነው፡፡ ይህም የአጠቃቀም መጠን ከአዋጭነት
አንጻር እንጅ በብዛት መመገብ ጎጂ ጎን የለውም፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

Fast growing Sesbania: 9 t DM/ha Sesbania leaf hay

Var. DZF-092
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

3. ሊዩኪንያ (Leucaena pallida)

• መግለጫ: ሊዩኪኒያ ዘላቂ የአባዝር ዛፍ ሲሆን ቁመቱ እስከ 20 ሜትር ይደርሳል::


ሊዩኪኒያ ቅጠሉ እና ለስላሳ ቅርንጫፎቹ በእንስሳት የተወደዱ በፐሮቲን ይዘቱም
የበለጸገ የቅንጠባ መኖ ዛፍ ነው፡፡
• የማቆጥቆጥ ችሎታው ከፍተኛ በመሆኑ በተለይ በመሰኖ በመጠቀም በዓመት ከሦስት
ጊዜ ባላነሰ በመቁረጥ ለድጎማ መኖ ማዋል ይቻላል፡፡

• ተስማሚ ሥነ-ምህዳር፡- ሊዩኪኒያ ለእርጥብ ወይና ደጋ ሥ-ነምህዳር ከባህር ጠለል በላይ


እስከ 2000 ሜትር ከፍታ ላላላቸው ሞቃታማ አካባቢዎች ይበልጥ ተስማሚ ነው፡፡
• ሉኪኒያ አንዴ በአስተማማኝ ከለማ በኋላ ድርቅ መቋቋም ይችላል፤ ስለሆነም ዓመታዊ
የዝናብ መጠናቸው 400 ሚሊ ሜትር በሆነ ዝናብ-አጠር አካባቢዎች ሊለማ ይችላል፡፡
• ውርጭ ግን አይቋቋምም፡፡ ውሃ የማይቆምበት መለስተኛ ተዳፋት ያለው መሬት፣
ኮምጣጤ (አሲዳማ) ያልሆነ አፈር ይበልጥ ይስማማዋል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

3. ሊዩኪንያ (Leucaena pallida)...


• አዝመራ: የሊዩኪኒያን ዘር በቀጥታ በመዝራት ማልማት ይቻላል፡፡ ነገር ግን
ተመራጩ ዘዴ በችግኝ ማምራት ነው፡፡ በዘር ለማልማት ሲፈለግ የዘር መጠን ከ 4 –
7 ኪ.ግ. በሄክታር ሲሆን በየመስመሮች መካከል ከ 2 – 2.5 ሜትር ሊሆን ይገባል፡፡
• ዘር መፈተግ፡- የሉኪኒያ ፍሬ ጠጣር ቆዳ ስላለውና ቶሎ ስለማይጎነቁል ከ 60 እስከ
80 ዲግሪ ሴልሸስ በሞቀ ዉሃ መዘፍዘፍ ያስፈልጋል፡፡ አለዚያም በሳልፊዩሪክ አሲድ ለ
10 ደቂቃ በመዘፍዘፍ ቆዳውን በማቃጠል ብቅለቱን ማፋጠን ይቻላል፡፡
• በተጓዳኝ ሕዋስ ማከም፡- ሉኪኒያ ተጓዳኝ የራይዞብየም ባክተሪያ ዝርያ መራጭ
በመሆኑ ከዘሩ ጋር ታሽጎ በሚመጣ የማከሚያ ዱቄት በትንሽ ስኳር በጥብጦ ዘሩን
በማሸት ማከም ያስፈልጋል፡፡
• የማዳበሪያ ፍላጎት፡- በአሲዳማ አፈር የሚለማ ከሆነ ኖራ በመጨመር
የአሲዳማነቱን ብርታት መቀነስ ያስፈልጋል፡፡ እንደአመችነቱ የተብላላ ፍግ
በመስመሮች አኳያ ከ 10 – 20 ኩንታል በሄክታር በመለገስ እድገቱን ማፋጠንና
ምርታማነቱን መጨመር ይቻላል፡፡
• ተጓዳኝ ሰብሎች፡- በመስመሮች መካከል የምግብ ሰብሎች፡ የመኖ አባዝር ወይንም
እንደ ቡና የመሳሰሉ ቋሚ ተክሎች ማልማት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

3. ሊዩኪንያ (Leucaena pallida)...


የምርት መጠን: ሉኪኒያ ከቅንጠባ መኖ ዝርያዎች ሁሉ ለብዙ ዓመታት ምርታማ ሆኖ
በመቆየትና ለብዙ ጥምር ጥቅም (መኖ፣ ማገዶ፣ ወረቀት ስራ፣ የቡና ጥላ፣ ሕያው
አጥር አና እነዲሁም እምቡጥ ቅጠሉና ፍሬው ለሰው ምግብ) ስለሚውል በአንደኛ
ደረጃ ተመራጭ ነው፡፡
• የድረቆ መኖ ይዘቱ ከሥሩ አካባቢ ሲቆረጥ 50 ቶን በሄክታር፤ በ75 ሳንቲ ሜትር
ቁመት ሲቆረጥ ደግሞ 40 ቶን በሄክታር እንደሚሆን ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
• አጠቃቀም:- ሉኪኒያ በመጀመሪያው ዓመት ፈጥኖ አያድግም ስለዚህም ለጥቅም
የሚደርሰው በሁለተኛው ዓመት ነው፡፡ ሉኪኒያ በየ 80 - 100 ሳንቲ ሜትር ቁመት
በየ 6 እስከ 8 ሳምንታት ጊዜ እየተቆረጠ በድጎማ መልክ ለአመንዘኪ እንስሳት
ይቀርባል፡፡
• ከሌሎች የቅንጠባ መኖ ዝርያዎች በተለየ ሉኪኒያ የአቅርቦት መጠን ገደብ አለው፤
ይኸውም ከየቀኑ አጠቃላይ ራሽን ውስጥ ከ 25–30% መብለጥ የለበትም፡፡ ከዚህ ልክ
ከበለጠ ግን የጉረሮ እጢ እብጠት እና የቆዳ ጸጉር መርገፍ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ
መውሰድ ይገባል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

3. ሊዩኪንያ (Leucaena pallida)...

...
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

4. የርግብ አተር (Pigeon pea)

መግለጫ:- የእርግብ አተር ጥንድ ጠቀሜታ ያለው በአብዛኛው ከዓመታዊ የአባዝር


ዝርያዎች የሚመደብ ዝርያ ሲሆን ፍሬው ለሰው ምግብ፤ ቅጠሉ ደግሞ
ለድጎማ መኖ ያገለግላል (ሥዕል 15)፡፡
• ተስማሚ ሥነ-ምህዳር፡- የእርግብ አተር ለቆላማ ዝናብ-አጠር (አማካይ ዝናብ ከ
500 – 800 ሚ.ሜትር) አካባቢዎች የሚሰማማ ሰብል ነው፤ ውርጭ ግን
አይቋቋምም፡፡ በተጨማሪም በአሲዳማ አፈር ዓይነት መልማት ይችላል፡፡
• አዝመራ: የእርግብ አተር ከ 4 – 6 ኪ.ግ. ዘር በሄክታር በቀጥታ በመዝራት
ይለማል፡፡ በመስመር መዝራት ተመራጭ ስለሆነ በየመስመሩ መካከል 1 ሜትር
አራርቆ መዝራት ይገባል፡፡
– የማዳበሪያ ፍላጎት፡- ለምነቱ ለተዳከመ ማሳ ፎስፌት ማዳበሪያ ከ 20 – 40
ኪ.ግ. በሄክታር መለገስ ይዘቱን ያሻሽለዋል፡፡
– የዘር ሁኔታ፡- የእርግብ አተርን ዘር መፈተግ ወይንም በባክተሪያ ማከም
አያስፈልግም፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

4. የርግብ አተር (Pigeon pea)...

• ምርታማነት፡- የእርግብ አተር መኖ ይዘት በሄክታር እስከ 12 ቶን


ድርቆ መኖ ይደርሳል፡፡
• አጠቃቀም፡- ለመኖ የታቀደ የእርግብ አተር ሰብሉ ፍሬ ማፍራት
እንደጀመረ ከመሬት 25 -50 ቁመት ላይ በማጨድ አርጥቡን
ቀረጣጥፎ መመገብ ያስፈልጋል፡፡
• ፍሬውን ለሰው ምግብ ማዋል ከተፈለገ ዘር ያልያዙ ቅርንጫፎችን
በመመልመል ለእንስሳት መኖ በማዋል መብሰል የጀመረውን ፍሬ
ግነ በእሸትነቱ ወቅት አለዚያም ደርቆ ከታጨደ በኋላ ለሰው
ምግብነት ማዋል ይቻላል፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

4. የርግብ አተር (Pigeon pea)...


ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

5. ትሪ ሉሰርን (Chaemacytisus palmensis)

• መግለጫ:- ትሪ ሉሰርን ዘላቂ የአባዝር ዛፍ ሲሆን ጠቀሜታው


ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ዋናው ጠቀሜታው ለቅንጠባ መኖ ሲሆን
በተጨማሪም ለህያው አጥር፣ ለንብ ቀሰም እና ግንዱ ደግሞ
ለማገዶ ወይንም ለቀላል ግንባታ ሥራዎች ሊውል ይችላል፡፡
• ተስማሚ ሥነ-ምህዳር፡- ትሪ ሉሰርን ሰፊ የሥነምህዳር
ተላማጅነት አለው፡፡ በይበልጥ ግን በቂ እርጥበት ባላቸው ወይና
ደጋ እና ደጋ ሥ-ነምህዳር ከባህር ጠለል በላይ እስከ 3200 ሜትር
ከፍታ ላላቸው ቀዝቃዛ አካባቢዎች ነው፡፡
• ስለዚህም ውርጭ ይቋቋማል፡፡ ትሪ ሉሰርን አንዴ በአስተማማኝ
ከለማ በኋላ ድርቅ መቋቋም ይችላል፤ አሲዳማ እና እምብዛም
ለም ባልሆኑ ማሳዎች ላይም መልማት ይችላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

5. ትሪ ሉሰርን (Chaemacytisus palmensis)...

• አዝመራ: ትሪ ሉሰርን ዘር በቀጥታ በመዝራት ማልማት ይቻላል፡፡ ነገር ግን


ተመራጩ ዘዴ በችግኝ ማልማት ነው፡፡ ለጥምር አዝመራ አጠቃቀም በመስመሮች
መካከል ሰብል ለማልማት ሲፈለግ በየመስመሮች መካከል ያለው እርቀት መስፋት
ስላለበት እስከ 4 ሜትር ሊሆን ይገባል፡፡
• ዘር መፈተግ፡- የትሪ ሉሰርን ፍሬ ጠጣር ቆዳ ስላለውና ቶሎ ስለማይጎነቁል በሚፈላ
ውሃ ውስጥ ከ 8 እስከ 10 ደቂቃ መቀቀል ያስፈልገዋል፡፡
• በተጓዳኝ ሕዋስ ማከም፡- ትሪ ሉሰርን ተጓዳኝ የራይዞብየም ባክተሪያ ዝርያ መራጭ
በመሆኑ ከዘሩ ጋር ታሽጎ በሚመጣ ማከሚያ በትንሽ ስኳር በጥብጦ ዘሩን በማሸት
ማከም ያስፈልጋል፡፡
• የማዳበሪያ ፍላጎት፡- ለምነቱ በተዳከመ ማሳ የሚለማ ከሆነ እንደአመችነቱ የተብላላ
ፍግ በመስመሮች አኳያ ከ 10 – 20 ኩንታል በሄክታር በመለገስ እድገቱን ማፋጠንና
ምርታማነቱን መጨር ይቻላል፡፡
• ተጓዳኝ ሰብሎች፡- በመስመሮች መካከል የምግብ ሰብሎች፡ የመኖ አባዝር ወይንም
እንደ ሎሚ እና አቮካዶ የመሳሰሉ የደጋ ተክሎች ጋር አሰባጥሮ ማልማት ይቻላል፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

5. ትሪ ሉሰርን (Chaemacytisus palmensis)...

• አጠቃቀም፡- ትሪ ሉሰርን በመጀመሪያው ዓመት ፈጥኖ አያድግም ስለዚህም


ለጥቅም የሚደርሰው በሁለተኛው ዓመት ነው፡፡ ቁመቱ 1 ሜትር ሲደርስ በየ
6 – 8 ሳምንታት ጊዜ እየተቆረጠ በድጎማ መልክ ለአመንዘኪ እንስሳት
ይቀርባል፡፡
• የትሪ ሉሰርን የአቅርቦት መጠን ገደብ የለበትም፤ ስለዚህም አዋጭ እስከሆነ
ድረስ በርከት አድረጎ ለእንስሳት መመገብ ጎጂ ጎን የለውም፡፡ ነገር ግን
በአብዛኛው በውስን መሬት ስፋት እንደ ጓሮ መኖ ስለሚለማ አቅርቦቱ
በድጎማ መልክ ቢሆን መልካም ነው፡፡
• በጅማሮ አቅርቦት እንስሳት ወዲያውኑ ፈቅደው ላይበሉት ስለሚችሉ ከ 10
እስከ 15 ቀናት የማለማመጃ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ የየቀኑን አቅርቦቱ ከሁለት
በመክፈል ግማሹን ጥዋት፣ ግማሹን ደግሞ ወደማታ መመገብ መልካም ነው፡፡
ለመስኖ አመራረት የሚስማሙ የቅንጠባ መኖ አባዝር ዝርያዎች

5. ትሪ ሉሰርን (Chaemacytisus palmensis)...


መጨረሻ

አመሰግናለሁ

You might also like