Download as ppt, pdf, or txt
Download as ppt, pdf, or txt
You are on page 1of 46

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ

ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
የሰልጣኞች የስነምግባር ደንብ / Code of Ethics/
ሥነ-ስርዓት አፈፃፀም መመሪያ
መስከረም 2016ዓም
አዲስ አበባ
መግቢያ
የሰልጣኝ ስነምግባር በአንድ የተወሰነ ስልጠና ተቋም ስልጠና ለሚወስዱ ሰልጣኞች ህግና ደንብ
አክብረው እንዲማሩና በስልጠና ተቋም ውስጥ ሁሉን አቅፍ አዎነታዊ ተሳትፎ እንዲኖራችው፤
ተቋማዊ ሥርዓት፣እንዲሰፍን የስልጠና ጥራት እንዲረጋገጥ እና ምቹ የመማር እና ማስተማር
አካባቢን ለመፍጠር የተቋቋሙ ህጎችን፣ እና ደንቦችን ያካተተ ሲሆን ሰልጣኞች የላቀ ስብእና
እንዲላበሱና በስልጠና በስራ መስክ ላይ ውጢታማ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው። በማሰልጠኛ ተቋም፣
በሙያ ማሰልጠኛ ፕሮግራም ውስጥ፣ የሰልጣኞች ዲሲፕሊን የሰልጣኞችን ባህሪ፣ የስራ ስነምግባር
እና አጠቃላይ ሙያዊ እድገት ለመቅረጽ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የሥነ-ምግባር መመሪያ ዓላማ
1. በሥነ-ምግባር የታነጸ ሰልጣኝ ማፍራትና መልካም ሥነ-ምግባር በማስፈን ዉጤታማ ሥራ እንዲሰራ ማስቻል፡፡
2. የሥነ-ምግባር ጉድለቶች እንዳይፈፀሙ ማስገንዘብ ተፈጽመዉም ሲገኙ እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችል ሥርዓት
መዘርጋት፡፡
3. ሰልጣኞች የስነ-ምግባር ደንቦችን በሚገባ አዉቀዉና ተረድተዉ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ በማሰልጠኛ ተቋሙ
ውስጥ ቆይታቸዉ በመልካም ሥነ-ምግባር ተገንብተዉ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
4. ሰልጣኞች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸዉን ያለእንከን ሊመሩ ይቻላቸዉ ዘንድ
5. ስለሥነ-ምግባርና የሥነ-ምግባር ጉድለቶች ምንነት ተረድተዉ ከደንብና ሥርዓት ዉጭ በሚሆኑበት ጊዜ
ሊወሰድባቸዉ ስለሚችል እርምጃ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ፡፡
የመመሪያው አስፈላጊነት

ሰልጣኞችን የስነ ምግባር ደንብን እንዲያከብሩ፣መመሪያዎችን እንዲከተሉ፣


እና በስልጠና ሂደቱ ላይ ሙያዊ ብቃት እንዲያሳዩ ማድረግ ነው።
የመመሪያው ይዘት
ይህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በ2016 ዓ/ም ተዘጋጅቷ
የጸደቀ የሰልጣኞች ሥነ-ምግባር መመሪያ ደንብ ሲሆን በውስጡ ስለሥነ-ምግባርና በሥነ-ምግባር
ጉድለቶች ምክንያት እንደ ጥፋተቸው መጠን በሰልጣኞች ላይ የሚወሰደው የዲስፕሊን ቅጣት ዓይነቶች
ይዞዋል፡፡

ርዕስ
ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የቲክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና ቢሮ የሰልጣኞች ሥነ-
ምግባር መመሪያ code of ethics ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡
የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ስር


በሚገኙ 14 ማሰልጠኛ ተቋማትና አንድ የልህቀት ማእከል ሰልጣኞች ላይ ተፈፃሚነት
ይኖረዋል:
ምዕራፍ አንድ

የሰልጣኞች ሥነ-ምግባር ጠቅላላ ድንጋጌዎች

 አጭር ርዕስ

 ትርጓሜ
ክፍል ሁለት
መብቶችና ግዴታዎች
የሰልጣኞች መብቶች፡

1.በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ አካዳሚክ ኮሚሽን ባወጣው የስልጠና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በነፃነት
የመማር፣የመጠየቅ፣የመመራመር፣የመረዳዳት የማወቅ ሳይንሳዊና ጥበባዊ ክህሎትን የማሳደግ፣ልቆ የመገኘት፤
2.በመማሪያ ክፍል፣በማሰልጠኛ ተቋሙ ግቢና በህብረተሰብ ውስጥ ለመማር አመቺ ሁኔታን የማግኘትና የመጠቀም፡
3.በማሰልጠኛ ተቋሙ ግቢ ውስጥ ህገ-መንግስታዊና ሰብዓዊ መብታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ የመኖር፡
4.በማሰልጠኛ ተቋሙ ጉዳዮች ላይ በህጋዊና በሰላማዊ አግባብ አቋማቸውን በነፃነት የማራመድ፡
5.ማንኛውንም አይነት አድሎ ወይም ትንኮሳ እንዳይደርስባቸው ህጋዊ ከለላን የማግኘት፡

6. በማንኛውም የሰልጣኝና የአሰልጣኝ ግንኙነት የፍትህና ፍትሀዊነት ተጠቃሚ የመሆንና ለመማር የሚያነሳሳ መልካም ተቋማዊ ድባብን የማግኘት፡
7. ስለአካዳሚያዊ ብቃታቸው በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ በተደነገጉ መርሆችን በማሰልጠኛ ተቋሙ አካዳሚክ
መመዘኛዎች መሰረት የመመዘን ኢ-ፍትሀዊ ምዘና ሲፈፀም ቅሪታን በማሰልጠኛ ተቋሙ ስርዓት መሰረት
በሰላማውና ህጋዊ መንገድ የማቅረብና ፍትህን የማግኘት፡
8. ግልጽነት ባለው ስርዓት መሰረት የአሰልጣኞችና ሌሎች አካዳሚክ ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀም መሙላትና የአፈፃፀም
ግምገማው ላይ በመሳተፍ አስተያየት የመስጠት፡
9. በትምህርት ማህደራቸው ውስጥ የሚቀመጡ መረጃዎች በሚስጥር ስለሚጠበቁበትና ለሌላ ወገን ስለሚገለፁበት
ሁኔታ የሚወስን አስተማማኝ ስርዓት ተጠቃሚ የመሆን፣
10.የሰልጣኙ የጋራ ጥቅሞችን በህጋዊ መንገድ እንዲጠበቁ ለማስቻል አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቋቋመና የማሰልጠኛ
ተቋሙን ሰልጣኞች በሙሉ በአባልነት በሚያቅፈው የማሰልጠኛ ተቋሙ ሰልጣኞች ህብረት አባል የመሆን፡

11.በማሰልጠኛ ተቋሙ ደንብና ሥርዓት መሰረት በግልም ሆነ በማህበራቸው አማካይነት በማሰልጠኛ ተቋሙ
መገልገያዎች የመጠቀም፡
12. በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ድንጋጌዎችና የማሰልጠኛ ተቋሙ ስራ አመራር ቦርድ በሚያወጣቸው መመሪያዎች መሰረት
በማህበራቸው ወይም በተወካዮቻቸው አማካኝነት በተለያዩ ኮሌጆች ስልጠናዊ/ትማህርታዊ/ እና አስተዳደሪያዊ ስብሰባዎች ላይ
የመሳተፍ

13. የፈተና ውጤትን በወቅቱ የማየት ቅሬታ ካለ የማቅረብ

14. የፈተና ውጤት / Grade Report/ በወቅቱ የመቀበልና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች በማቅረብ አግባብነት ያለው የትምህርት
ማስረጃ በግዜ የማግኘት፡

15. የየሰሚስተሩን የመጨረሻ የፈተና ፕሮግራም በቂ በሆነ ጊዜ /ቢያንስ ከአንድ ሳምንት በፊት /የማወቅ፡

16. ማንኛውም መደበኛ ሰልጣኝ የወጪ መጋራት ውል ከፈረመ ወይንም ለአገልግሎቱ የሚገባውን ክፍያ በቅድሚያ እስከፈፀም
ድረስ ኮሌጁ የሚሰጠውን የህክምናና የመዝናኛ አገልግሎቶችን የማግኘት፡

17. ከትምህርት ጋር አግባብነት ያላቸውን ሀሳቦች የማቅረብ፣የመከራከርና የመወያየት፡

18. ከማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብ ጋር ለሚፈጠሩ ማንኛውም የዲስፕሊን ግድፈቶች (አለመግባባቶች) አግባብነት ያለው ፍትህ
የማግኘት እና በተገቢው አካል የመዳኘት፡
19. በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ በሚቋቋሙ የሰልጠኞች ክበባትና ሌሎች አግባብነት ባላቸው
አደረጃጀቶች (ለምሳሌ የዲስፕሊን፣የመዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ፣የፀረ-ኤድስ፣የጤና
የአካባቢ፣የስፖርትና የመዝናኛ ወዘተ…ውስጥ በአመራርነትም ሆነ በአባልነት የመሳተፍ፣

20. በማሰልጠኛ ተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በእኩልነትና በፍትሀዊነት ማግኘት፣

21. በማሰልጠኛ ተቋሙ ህገደንብ/ Legislation/ የተካተቱትን መብቶች በአግባቡ የመጠቀም፡

22. በጥፋተኝነት በሚከሰስበት ጊዜ የተከሰሱበትን ወይም የተጠረጠሩበትን ጉዳይ በተመለከተ


የበኩላቸውን ማስረጃና ክርክር የማቅረብ፡

23. በአካዳሚክና አስተዳደራዊ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ በሰላማዊ ሁኔታ የመወያየትና ሐሳብ የመስጠት
ብሎም ፓናል ውይይት የማዘጋጀት፡
24. በስራቸውና በችሎታቸው መሰረት ያለምንም አድልዎ የመገምገምና የግምገማዉ ውጤታቸውን የማወቅ፡ቅሬታ
ካላቸውም ስርዓትን ተከትሎ የፈተና ወረቀቶቻቸውና የተገመገሙባቸው ስራዎቻቸው እንደገና እንዲታይላቸው
የማመልከት ውጤቱንም የማወቅ፤
25.በማሰልጠኛ ተቋሙ ህገደንብ/Legislation/ መሰረት በማንኛውም የመማር ማሰተማርና አገልግሎት
የሚሰጥበት መስክ በብሄር በፆታ፣በሀይማኖት በፖለቲካ ወይም በሌላ ወገንተኝነት ምክንያት አድልዎ
የማይደረግባቸው መሆኑን መረዳት፣ከተደረገባቸውም ለሚመለከተው የአመራር አካል ቅሬታቸውን የማቅረብና
ምላሽ ማግኘት፤
26.ቤተ-ሙከራዎችና ወርክሾፖች እንዲሁም ሌሎች ስልጠናቸውን ሊያግዙ የሚችሉ የማሰልጠኛ ተቋሙን
ወይም የሌሎች ተቋማትን በሚመለከተው አካል ክትትል የመጠቀም መብቶች አሏቸው፡፡
አንቀፅ 5 የሰልጣኞች አጠቃላይ ግዴታዎች

1. ስልጠና ይጀመራል በተባለው የጊዜ ገደብ በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ በአካል ተገኝቶ ወይም በማሰልጠኛ ተቋሙ በይነ መረብ
(Online Registration) የመመዝገብና አስፈላጊውን ፎርማሊቲዎች አሟልቶ ስልጠና የመጀመር፤በክፍል የመገኘትና ስልጠናውን
በሚገባ የመከታተል
2. የቲቪኢቲ/TVET/ ዓላማዎችንና የማሰልጠኛ ተቋሙ መሪ እሴቶችን የማወቅና የመተግበር፤
3. አግባብነት ያላቸውን የሀገሪቱን ህጎች በማሰልጠኛ ተቋሙ የሰልጣኞች ዲስፕሊን መመሪያ የተቋሙን የአካዳሚክ ኮሚሽን ደንብ
እንደዚሁም ሌሎች ተፈፃሚነት ያላቸውን ህጎች የማወቅ፤የማክበርና የማስከበር በእነርሱም የመመራት
4. ከማንኛውም ማህበረሰብ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ሕገ- መንግስታዊ መብቶቻቸውን የማክበር

5. የግልም ሆነ የጋራ የሰልጣኞች ጥቅም አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ፍፁም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ቅሬታን በማሰማት በጋራ
መፍትሔ የመሻት፤
6. የማሰልጠኛ ተቋሙን የጋራም ይሁን የግል መገልገያ ንብረት በጥንቃቄ የመያዝና የመጠቀም ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት
ምክንያት የማሰልጠኛ ተቋሙን ንብረት ላይ ለሚደርሰው አደጋና ለሚከሰተው ማንኛውም ጉዳት በጋራም ሆነ በግል ተጠያቂ የመሆን
እንደዚሁም የደረሰውን ጉዳት የመተካት፤ጥፋት ያደረሰውን አካል የማጋለጥ
7. ማሰልጠኛ ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መክፈል የሚገባውን ክፍያ የመፈፀም
8. ሁልጊዜ የመገልገያ የመታወቂያ ካርድ መያዘና ለሌላ አካል አሳልፎ ያለመስጠትና በሚመለከተው አካል ሲጠየቁ የማሳየት፤
9. በተመዘገቡበት የስልጠና መስክ የተቀመጡ የብቃት መመዘኛዎችን ማሟላት፤የላቦራቶሪ፤ሪፖርቶችን እና ሌሎች በመምህራን
/በአሰልጠኞች / የተሰጡ ስራዎችን በወቅቱ አጠናቆ ማስረከብ
10.በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር ለእያንዳንዱ የበቃት አሃድ (የትምህርት ዓይነት ወይም ኮርስ) በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት
በሌክቸር በላቦራቶሪ በወርክሾፕና በመስክበ መገኘት ስልጠናው የሚጠይቀውን ተግባራትን የማከናወን፤
11.በማሰልጠኛ ተቋሙ የተደነገገውን የመግቢያና የመውጫ ሰዓት ማክበር
12.ማንኛውንም አሰልጣኝ አስተዳደር ሰራተኛ እንዲሁም የማሰልጠንና የአስተዳደር ሂደቱን የመምራትና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለውን
አካል የማክበር፤
13.ሰልፍ ባለበት ቦታ ሁሉ ሰልፍን ጠብቆ መገልገል
14.በማንኛውም ጊዜ ግቢውን ሲለቁ የተረከቡትን ንብረት በአግባቡ ቆጥሮ ማስረከብ፤ክሊራንስ በማውጣት ግቢውን በወቅቱ
መልቀቅ፤
15.ሱስ ከሚያስይዙ (ጫት፤ሲጋራ፤አልኮል ሺሻና የመሳሰሉት) ጎጂ ልማዶች ራስን መጠበቅ
16.በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት ደንብ መሰረት ለትምህርትና ለአገልግሎት ተገቢውን ክፍያ መክፈል ወይም የወጪ
መጋራትን ውል መፈረም
17.ከማሰልጠኛ ተቋሙ ውጭ ካለው ማህበረሰብ ጋር በሚኖረው ግንኙነት በመልካም ስነ- ምግባር አርአያ መሆን
18.የሌላውን ባህል ቋንቋ፤ሃይማኖት ወዘተ…. ማክበርና መጠበቅ
19.ከማንኛውም ህገ ወጥና ከስነ-ምግባር ውጭ ከሆኑ ተግባራት የመቆጠብ፤ለምሳሌ ከስርቆት አላግባብ በመጮህ ሌላውን ከማወክለ
ሕገ-ወጥ ተግባር ሌሎችን ከማነሳሳት፣ሱስ ከሚያሲዙ (ጫት፣ሲጋራ፣አልኮል ሺሻና የመሳሰሉት) ጎጂ ልማዶች.ወ.ዘ. ተ……ራስንና
ሌሎችን የመጠበቅ፤
20.አንድ ሰልጣኝ በተለያዩ ምክንያቶች መባረሩን ሲያውቅ ሰበብ አስባብ ፈልጎ ሌላውን ሰልጣኝ ይዞ ለመጥፋት ያልሆኑ ጥያቄዎችን
ማንሳት ሌሎችን መቀስቅስ ረብሻ ለመፍጠር መሞከር፤በማንኛውም ምክንያት ከሌሎች ጋር መጣላትና የመሳሰሉትን ችግሮች
ስለሚፈጥር እንደዚህ ዓይነት ሰልጠኞችን ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በመስጠት በጊዜ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው የማድረግ፣
21.በሁለት ሰልጣኞች መካከል የሚነሱ ግላዊ ጥሎችን ወደ ብሄርና ሀይማኖት በመለወጥ ግጭት ውስጥ ያለመግባት፣
22.የሚሰጡ የስልጠና የተለያዩ ስራዎችን በራስ ጥረት መስራት፣የሌላው ሰው ስራ የራሱ አስመስሎ አለማቅረብ፣ለሌላ ሰው ሰርቶ
መስጠት ወይም ከሌላ ሰው መውሰድ ወይም መኮረጅ የማይቻልና ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን የመረዳት፣
23. ማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ ባሉ የስልጠና ዘርፎች የሚፈልጉትን የስልጠና አልባሳት (ጋዎነን፤ቱታ እና የመሳሰሉትን) በተጨማሪም የደንነት
መጠበቂያ አልባሳትን በአግባቡ ለብሶ መገኘት
24.በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ የሰልጣኞችን የግል አለባበስን በተመለከተ ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍን ያልተቀዳደደ ልብስና ሽፍን ጫማን የማድረግ
ወይም የመጫማት
25. ሰልጣኞች ጠጉር ከመጠን ከ 1.5 ሴሜ በላይ ያለማሳደግ የጠጉር ቀለም ያለመቀባት ሲት ሰልጣኞችን በተመለከተ ጠጉርን ሹርባ የመሰራት ወይም
ሰብስቦ የማስያዝ
26.ማንኛውም ሰልጣኝ ከመማርያዉ ክላስ ውጭ ሄዶ ያለመገኘት፣ሌላ ሰልጣኝን አስከትሎ አለመገኘት
27.በማሰልጠኛ ተቋሙግቢ ዉስጥ ምንም ዓይነት ተቀጣጣይ ነገሮችን ያለመያዝ እና ምንም አይነት ሰው ሊጎዳ የሚችል መሳሪያ ይዞ
አለመገኘት
28.ማንኛዉም ሰልጣኝ በልላዉ ሰልጣኝ ላይ ወይ የማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብ ላይ የስነ ልቦና ጫና ሊፈጥር የሚችል መረጃን
በወረቀትም ሆነ በማህበራዊ ድህረገጥ በማሰልጠኛ ተቋሙዉስጥ ማሰራጨት ፈፅሞ የተከለከ ነዉ
29.ከማንኛውም ማህበረሰብ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ሕገ- መንግስታዊ መብቶቻቸውን የማክበር
አንቀጽ 6 ፡- የፆታ አገላለጽ፡
በዚህ መመሪያ በወንድ ፆታ የተገለጸዉ የሴትንም ፆታ ያጠቃልላል፡፡

አንቀጽ 6. የሰልጣኞች ኃላፊነትን በተመለከተ

1.ሰልጣኞች ይህንን የሥነ-ምግባር መመሪያ በሚገባ አዉቀዉ በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡


2.ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ዉስጥ ከሥነ-ምግባር ጥስት ጋር የተያያዙ ድርጊቶች ሲፈጽሙ ለኮሌጁን
የበላይ ኃላፊ የማሳወቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
3.ሰልጣኞች ይህንን መመሪያ የመቀበልና የመፈጸም ኃላፊነት አለባቸው፡፡
ክፍል ሶስት
አጠቃላይ የሥነ-ምግባር መርሆችና የዲስፕሊን ጥፋቶች

 ቅንነት  ህግን ማክበር

 ግልፅነት  አርአያነት

 ታማኝነት  ተጠያቂነት

 ምስጢር ጠባቂነት  ህጋዊ በሆነ ሥልጣን መገልገል

 ለህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት


 ሐቀኝነት
አንቀጽ 7. ቅንነት አንቀጽ 8 ግልፅነት
በቅንነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም በግልፅነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም
ያስቀጣል፡፡ ያስቀጣል፡፡
ሀ. የማሰልጠኛ ተቋሙን ክብርና ዝና የሚጎዳ፣ የሰልጣኙንና የተቋሙን ማህበረሰብ
ሀ. ህጋዊ ለሆኑ ከማሰልጠኛ ተቋሙና ከማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብ ለሚቀርብ
የሚያዉክ ባህሪይና ተግባር መፈጸም ወይም ማሳየት፣
ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ወይም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን
ለ. የማሰልጠኛ ተቋሙን ህግና ደንብ በመጣስ ሱስ በሚያስይዝ መድሃኒት ወይም
በአደንዛዥ እፅ ሱስ በመመረዝ ወይም በልማዳዊ መጠጥ ተጽእኖ ምክንያት ስልጠናን
ለ. የማሰልጠኛ ተቋሙ የሰልጣኞች መማክርትና የተለያዩ ክበባት ለሚያስተላልፉት

በአግባቡ አለመከታተልና ተገቢ ያልሆነ አድራጎት መፈጸም፣ ዉሳኔ ተገቢዉን ማብራሪያ ወይም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን
ሐ. በግልና በማህበራዊ ህይወታቸዉ ማሰልጠኛ ተቋሙንና የማሰልጠኛ ተቋሙን ሐ. ሰልጣኞች ከስልጠና ገበታቸዉ ለቀሩባቸዉና ለሚቀሩባቸዉ ቀናት ህጋዊና
ማህበረሰብ መልካም ግምትና አመኔታ የሚያሳጣ ድርጊት መፈጸም ግልጽ መረጃ ለሚመለከተዉ አካል አለማቅረብ
መ. የተሳሳተ መረጃን በተለይም ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች በመስጠት ህገ-ወጥ ተግባራትን መ. ህጋዊና ግልጽ ባልሆኑ መንገዶች ወደ ግቢ መግባት ወይም መዉጣት ወይም
መፈጸም፡፡
ንብረት ማዉጣት ወይም ማስገባት
አንቀጽ 9፡- ታማኝነት
አንቀጽ 10 ምስጢር ጠባቂነት
በታማኝነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም ያስቀጣል፡፡
ሀ. የሀገሪቱንና የማሰልጠኛ ተቋሙን ህግና ደንብ አለማክበር
በምስጢር ጠባቂነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ
ለ. በማሰልጠኛ ተቋሙ በሰልጣኞች ወይም በሌላ አካል የሚደረግ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴን እያወቁ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም ያስቀጣል፡
በጊዜ አለማጋለጥ ወይም ተባባሪ መሆን፡ ሀ. ሰልጣኞች በትምህርት ቆይታቸዉ ከሙያቸዉ ጋር
ሐ. በማንኛውም አጋጣሚ ከማሰልጠኛ ተቋሙ የተረከቡትን ማንኛዉም ዓይነት ንብረት ወይም በተያያዘ መልኩ ወይም ከማሰልጠኛ ተቋሙ
መገልገያ በጥንቃቄ አለመያዝና ማበላሸት፣
ሥራ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚያዉቋቸዉን ሚስጢሮች
መ. የማሰልጠኛ ተቋሙን ማህበረሰብ ንብረት መስረቅ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፣
ሠ. በማሰልጠኛ ተቋሙ የሚገኙ ወይም የሚሰጡ የጋራ አገልግሎቶች እንደ ሻዉር፣ ሽንት ቤት፤ ቤተ-
አለመጠበቅና የማሰልጠኛ ተቋሙን መልካም
መጽህፍት፣ የመሳሰሉትንና ሌሎች አገልግሎቶች የጋራ መገልገያ ስለሆኑ በግል ብቻ ወይም በቡድን ስም ማጉደፍ ያስቀጣል፡፡
ብቻ መጠቀም ወይም ለመጠቀም መሞከር፡
ረ. የሌሎችን ስራ እንደራስ አድርጎ ማቅረብ ወይም ለማቅረብ ማሞከ ያስቀጣል፡
አንቀጽ 11፡- ሐቀኝነት አንቀጽ 12- ህግን ማክበር
በሐቀኝነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም በህግን ማክበር ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም
ያስቀጣል፡፡ ያስቀጣል፡፡
ሀ. የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን መፈጸም ወይም ለመፈጸም ሙከራ ማድረግ፣ ሀ. በማሰልጠኛ ተቋሙ የሚወጡ ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን አለማክበርና
ለምሳሌ፣አስመስሎ መፈረም፣ህጋዊ የሆኑ ሠነዶችን መሠረዝ፣መደለዝና አሰመስሎ አለመከታተል፡፡
መሥራት፣
ለ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ ስልጣን ባለዉ አካል የሚወጡ ልዩ ልዩ ደንቦችን
ለ. ፈተናን መኮረጅ፣ማስኮረጅ፣ከደብተር ወይም ከወረቀት መገልበጥ ወይም
ለምሳሌ እንደ የቤተ-መጽሐፍ የቤተ-ሙከራ የወርክ ሾፕ እና ሌሎች ደንቦችን
መሥራት ወይም የፈተና ወረቀትን ደልዞ ወይም ጨምሮ አሰልጣኝን በህገ ወጥ
በቸልተኝነት ሆን ብሎ መጣስ፣
መንገድ ዉጤት ለማስቀየር መሞከር፣
ሐ. ጉቦ በመስጠት ዉጤትን ለማስቀየር መሞከር ፣ ሐ. በህጋዊ መልኩ የተባረረን ሰልጣኝ ወደ ግቢዉ ውስጥ ማስገባት
መ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ዉስጥ ለሚደረጉ ነገሮች በሀሰት መመስከር፣ መ. ህጋዊ ያልሆኑ ጽሑፎችን በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ዉስጥ መበተን ወይም
ሠ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ክሊኒክ መድሀኒቶችን ለሌላ ተግባር ማዋል፣ ማሰራጨት፣
ረ. የማሰልጠኛ ተቋሙን መታወቂያ ካርድ ወይም የአገልግሎት መለያ ካርድ ለሌላ ሠ. ማንኛዉም ሰልጣኝ ማሟላት የሚገባዉን ነገር አልተደረገልኝም ብሎ ሲያስብ በግል
ግለሰብ አሳልፎ መስጠት
ወይም በተወካዩ አማካይነት በህጋዊ መንገድ ማቅረብና ምላሽ ማግኘት ሲገባዉ
ራሱንም ሆነ ሌሎችን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለአመጽ ማነሳሳት፣
ረ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ያልተፈቀደ ስብሰባ ማካሄድ፣አድማ
ማሳደም፣ለማሳደም መሞከር፣ህገ-ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ወይም ለማድረግ
መሞከር፣
አንቀጽ 13፡- አርአያነት አንቀጽ 14፡- ተጠያቂነት
በአርአያነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም ያስቀጣል፡፡ በተጠያቂነት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም ያስቀጣል፡፡

ሀ/ ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ በመልካም ሥነ-ምግባር ግንባር ቀደም በመሆን ሀ. ለግጭት የሚገፉፉና አሰነዋሪ የሆኑ ነገሮችን በቃል ወይም በጽሁፍ በመማሪያ ፣በመጸዳጃ በቢሮዎች
የሚጠበቅባቸዉን መልካም አርአያነት አለማሳየት እና በዚህ መመሪያ የተመለከቱትን መርሆች ግድግዳዎች፣በመዝጊያዎች፤ በመስኮቶችና በቁም ሳጥኖች ላይ መጻፊ፣ስዕል መሳል ወ.ዘ.ተ. ያስቀጣል፡፡

አለማክበር ወይም መጣስ፣ ለ. ሥር የሰደደ የጥላቻ ባህሪይ በማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብና በአካዳሚክ ስታፍ ላይ ማሳየት ወይም
ማንጸባረቅ፡
ለ/ ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ የማሰልጠኛ ተቋሙ ስምና ክብር የሚያቀል
ሐ. የማሰልጠኛ ተቋሙን ሠራተኞችና አሰልጣኞች መልካም ስምን በሀሰት በጹሁፍ ወይም በሌላ መንገድ
መተማመንና መልካም አንድነት የሚያጠፋ ተግባርና እንቅስቃሴ ላይ መሰማራት፣
ሊያጎድፍ የሚችል ድርጊቶችን መፈጸም፡፡
ሐ/ ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ ኢዴሞክራሲያዊ የሆነ እና በሀይልና በጉልበት ላይ መ. በመደራጀትና ረብሻን በማነሳሳት የስልጠና ክፍለ ጊዜዎች እንዳይካሄዱ ማድረግና የማሰልጠኛ
የተመሠረተ ግንኙነትን ከማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብ ጋር መመስረት፣ ተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ማስተጎጎል፡፡
ሠ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ግቢ ዉስጥ በዘር፣በብሔር፣በፖለቲካ ልዩነት፣በሃይማኖት፤ በቀለም ክፍፍል
ወ.ዘ.ተ. ፈጥሮ መሳደብ መደባደብና ግጭቶችን መፍጠር
ረ. በምዘና ወቅት ከወረቀት መስራትና ይህንን ሊያስቆሙ ከሚንቀሳቀሱ ፈታኝ አሰልጣኞች/ግለሰብ ጋር
ግብግብ መፍጠር ወይም ለመደባደብ መሞከር
ሰ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ሴት ሰልጣኞችን አስገድዶ መድፈር ወይም ለመድፈር ሙከራ
ማድረግ፣
ሸ. ከማሰልጠኛ ተቋሙ አሰልጣኞችና ሠራተኞች ጋር እንዲሁም እርስ በርስ ጥል ፈጥሮ መደባደብ፣መሳደብና
አንቀጽ 15፡- ህጋዊ በሆነ ሥልጣን መገልገል
ማንጓጠጥ፣
ህጋዊ በሆነ ሥልጣን መገልገል ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች መፈፀም
ቀ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ድምጽ ያለዉን ወይም የሌለዉን የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘትና ጉዳት
ያስቀጣል፡፡
ለማድረስ መሞከር
ሀ. የማሰልጠኛ ተቋሙ መማክርት አባላትና የሰልጣኞች ክበባት ተጠሪዎችና ኃላፊዎች በአግባቡ
በ. ሴት ሰልጣኞችን በንግግር፣ በጽሁፍ፣በኃይል ወ.ዘተ. ማስፈራራት፣ መዝለፍ፣ ማስቸገር ፣ማስጨነቅና ወሲባዊ
እንዲገለግሉ የተሰጣቸዉን ኃላፊነት በህግ ከተሰጣቸዉ የስልጣን ገደብ ዉጭ አላአግባብ መጠቀም፤
ትንኮሣ ማካሄድ፣
ለ. የመማክርት አባላትና የክበባት ተጠሪዎችና ኃላፊዎች ሥራቸዉን ከህግና ደንብ ወይም መመሪያን
ተ. የሰልጣኙን ሥነ አእምሮ ሊጎዱ የሚችሉ ኃይለ-ቃሎችን በመጠቀም (ለምሳሌ ሴት ሰልጣኞችን ፣የአካል
መሠረት በማድረግ አለመሥራት ፤
ጉዳትን፣የሰዉነት አቋምን፣ከባህል ጋር ግንኙነት ያላቸዉን ነገሮች ወዘተ) ምክንያት በማድረግ ሰልጣኙ
ሐ. የሰልጣኞች መማክርት አባላትና የክበባት ተጠሪዎችና ኃላፊዎች ሥልጣናቸዉን የግል ጥቅም
የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማዉ ማድረግ
ለማግኘት ማዋል፤
ቸ. የማሰልጠኛ ተቋሙ የጋራ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማበላሸት ለምሳሌ መዝጊያ ፣ መስኮት፣በር፣የዉሃ
አንቀጽ 16፡- ለህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት
ቧንቧዎችንና የሻዉር ዕቃዎችን መስበርና ማበላሸት እንዲሁም የመጻህፍት ሰነዶችን መቅደድ እና መስረቅ
ለህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ መስጠት ሥር የሚገኙትን መርሆች በመተላለፍ የሚከተሉትን ጥፋቶች
ነ. የማሰልጠኛ ተቋሙን ንጽህናና ጽዳት የሚጎዱ ድርጊቶች፣ለምሳሌ አበቦችን መንቀል አጥር ማፍረስ፣ በመማሪያ
መፈፀም ያስቀጣል፡፡
ክፍሎች አካባቢ ሽንት መሽናት ወይም መፀዳዳት፣
ሀ. ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በሚኖሩት/በስልጠና ላይ እያሉ ወቅት በሀገራዊና
ኘ. በላይብረሪና በመማሪያ ክፍሎች አከባቢ ሌሎችን በሚያዉክ መልኩ ድምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ ወይም
በአከባቢያዊ በሆኑ አንገብጋቢና አስቸኳይ ሁኔታ ተፈጥሮ ከመንግስትና ከአከባቢ ማህበረሰብ በሚቀርቡ
መነጋገር፤
የድጋፍና የትብብር ጥያቄዎችን መተባበር እየተቻለ ሆን ተብሎ ጥያቄዎን አለመቀበልና የዜግነት ምላሽ
አ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ግቢ ዉስጥ ግልጽ የሆነ ወሲብ ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ መያዝ
አለመስጠት ፡
ክፍል አራት
የዲሲፕሊን ጥፋትና የእርምት እርምጃዎች
የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማና አፈጻጻም
በማሰልጠኛ ተቋም ሰልጣኞች ላይ የሚወሰድ የዲስፕሊን ቅጣት
በማሰልጠኛ ተቋም ሰልጣኞች ላይ የሚወሰድ የዲስፕሊን ቅጣት
አፈጻጸም
ዓላማ
ሰልጣኞች ማድረግ የሚገባቸዉን ባለማድረጋቸዉ ወይም ማድረግ
በሰነ-ምግባር የታነፁ ሰልጣኞችን ለማፍራት፡
የማይገባቸውን በማድረጋቸው ስለጥፋታቸዉ በፍትሃብሔር ወይም
ሰልጣኞች የሥነ-ምግባር ግድፈቶችን እንዳይፈጽሙ ለማስተማርና በወንጀል ወይም በሁለቱም ህጎች ተጠያቂነታቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ
ፈጽመዉ ሲገኙ በማረም ተገቢዉን የእርምት እርምጃ ለመዉሰድና ያደረሱት ጥፋት ወይም የዲስፕሊን ጉድለት በዚህ የሥነ-ምግባር መመሪያ
የማይታረሙ ሆነዉ ሲገኙ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ፡፡ መሠረት ተገቢዉን የቅጣት እርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡
በዲስፕሊን ጥፋት የሚፈጸሙ ቅጣቶችን በማናቸዉም ፍርድ ቤት
የሚሰጠዉን ዉሳኔ ሣይጠብቁ ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
የዲስፕሊን ቅጣት ዓይነቶች
ቀላል የዲስፕሊን ቅጣት ዓይነቶች ከባድ የዲስፕሊን ቅጣቶች

 በምክርና በቃል ማስጠንቀቅያ  ለአንድ ሴሚስተር ከስልጠና ገበታ የሚያሳግዱ


 የዕሑፍ ማስጠንቀቂያ  ለአንድ ዓመት (ሁለት ሴሚስተር) ከስልጠና
 ማሕበራዊ አገልግሎት (ግቢ ማጽዳት፡ችግኝ ገበታ የሚያሳግዱ
 ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከስልጠና ገበታ
መትከል፡ቤተመፃህፍት፡ ማገልገልና ሌሎችም)
የሚያሳግዱና
 ለመጨረሻ ጊዜ ከስልጠና መርሀ ግብር
የሚያሰናብቱ ናቸው፡፡
18.3፡- ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች
ሀ. በምክር፣ በቃል ማስጠንቀቂያዎች እና በማሕበራዊ አገልግሎት የሚታለፉ የሥነ-ሥርዓት ግድፈቶች
•ህጋዊ ከሆኑ የማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብ ለሚቀርብ ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ ወይም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን፡፡
•የማሰልጠኛ ተቋሙን መማክርትና የተለያዩ ክበባት ለሚያስተላልፉት ዉሣኔ ተገቢዉን ማብራሪያ ወይም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን፡፡
•ሰልጣኞች ከትምህርት ገበታቸዉ ለቀሩባቸዉና ለሚቀሩባቸዉ ቀናት ህጋዊና ግልጽ መረጃ ለሚመለከተዉ አካል አለማቅረብ ፣
•በማሰልጠኛ ተቋሙ የሚወጡ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን አለማክበርና አለመከታል፤
•ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ በመልካም ሥነ-ምግባር ግምባር ቀደም በመሆን የሚጠበቅባቸዉን መልካም አሪአያነት አለማሳየት
•የማሰልጠኛ ዕቃዎችን በተገቢዉ ቦታ ያለማስቀመጥ /ያለመመለስ/
•በምግብ ቤት ዉስጥ እጅን መታጠብ
•በመማሪያ ክፍሎች፣በአዳራሾችና በአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ወንበሮችና ጠረጴዛዎችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር
•ዉሃና የኤሌክትሪክ ሃይል ያለአግባብ መጠቀም /ማባከን/
•በማሰልጠኛ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ያሉ አትክልቶች መርገጥ/መቁረጥ/
11.በመማሪያ ግድግዳዎች፣ ህንፃዎች፣ መስኮቶች፣ በሮችና፣ወ.ዘ.ተ. ላይ ስዕል መለጠፍና ጹሑፎችን መጻፍ
12.በእጅና ፊት መታጠቢያ ቦታዎች ላይ ልብስ ማጠብ፤
13.ሌሎች መስል የሥነ-ምግባር ችግሮችና ግድፈቶች
14.በምግብ ቤቶችና በሌሎችም የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ የአገልግሎት ተራን አለመጠበቅ፤
15.ከሰልጣኝ ምግብ ቤት ዉጪ በሌላ ምግብ ቤት (የመምህራን እና ሰራተኞች) ሲመገቡ መገኘት
16.የራስን ንጽህና አለመጠበቅ
17.አግባብ ያላቸዉ ክፍሎች ጥሪ ሲያደርጉ አለመቅረብ፡፡
18. ፀጉርን በተመለከተ ማንኛውንም ዓይነት የፀጉር ቀለም መቀባት በሐኪሞች ቦርድ ካልተፈቀደ በስተቀር ቆብ/ኮፍያ/ባርኔጣ መጠቀም፣
ጸጉርን ማንጨባረር የማይፈቀድ ሲሆን ለወንድ ተማሪዎች የፀጉር ርዝመት ቢበዛ 1.5 ሳ.ሜ. ያልበለጠ ሆኖ በውስጡ ምንም አይነት
ቅርጽ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡
19. አለባበስን በተመለከተ ሆነ ተብሎ ወይም ልብሱ ሲመረት የተቀደደ ወይም በማንኛውም ምክንያት
የሰውነት አካላትን የሚያጋልጥ አለባበስ መልበስ እንዲሁም ሱሪን ዝቅ በማድረግ የውስጥ ቁምጣን
ማሳየት ሴት ሰልጣኞችንም በተመለከተ ከጉልበት በላይ ያጠረ ቀሚስ ከወገብ በላይ እምብርትን
እንዲሁም ጡትን አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ መልበስ ሌላን ሰው ሊረብሽ የሚችል ከፍተኛ ሸታ ያለው
ሽቶ ዲዮድራንት ሎሽን መቀባት ድምፅ የሚሰጥ ጫማ እና ክፍት ጫማ አድርጎ ቤተ-
መፅሐፍት፣ መማሪያ ክፍል እና ቤተ-ሙከራ አካባቢ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው
20. የሚለበሰው ሱሪ የውስጥ ቁምጣን የሚያሳይ፣ የማህበረሰቡን ወግና ባህል የጣሰ መሆን ፈጽሞ
የተከለከለ ነው።
ለ. የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የሥነ-ሥርዓት ግድፈቶች

1.ከላይ የተጠቀሱትን አንዱን የሥነ-ምግባር ጉድለቶች ፈጽሞ በቃል ማስተንቀቂያና በምክር የታለፈ ሰልጣኝ ያንኑ ወይም ተመሣሣይ የሥነ-ምግባር
ጉደለቶች ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ሲገኝ፡፡
2.የማሰልጠኛ ተቋሙን ህግ ደንብ በመጣስ ሱስ በሚያስይዝ መድሃኒት ወይም በአደንዛዥ እጽ ሱስ በመመረዝ ወይም በልማዳዊ መጠጥ ተጽዕኖ
ምክንያት ትምህርትን በአግባቡ አለመከታተልና ተገቢ ያልሆኑ አድራጎት መፈጸም ፡፡
3.በግልና ማህበራዊ ህይወታቸዉ ኮሌጁንና የማሰልጠኛ ተቋሙን ማህበረሰብ መልካም ግምትና አመኔታ የሚያሳጣ ድርጊት መፈጸም፡፡
4.የተሣሣተ መረጃን በተለይም ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች በመስጠት ህገ-ወጥ ተግባራትን መፈጸም፡
5.ህጋዊና ግልጽ ባልሆኑ መንገዶች ወደ ግቢ መግባት ወይም መዉጣት ወይም ንብረት ማዉጣት ወይም ማስገባት
6.በማንኛዉም አጋጣሚ ከማሰልጠኛ ተቋሙ የተረከበውን ማንኛዉም ዓይነት ንብረት ወይም መገልገያ በጥንቃቄ አለመያዝና ማበላሸት፡፡
7.በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ወይም የሚሰጡ የጋራ አገልግሎቶችን እንደ ሻዉር፣ ሽንት ቤት፣ ቤተ-መጻህፍት፣የመሳሰሉትንና ሌሎች
አግልሎቶችን በግል ወይም በቡድን መጠቀም ወይም ለመጠቀም መሞከር፡፡
8. ሰልጣኞች በትምህርት ቆይታቸዉ ከሙያቸዉ ጋር በተያያዘ መልኩ ወይም ከማሰልጠኛ ተቋሙሥራ ጋር በተያያዘ መልኩ
የሚያዉቋቸዉን ሚስጢሮች አለመጠበቅና የማሰልጠኛ ተቋሙን መልካም ስም ማጉደፍ
9. የማሰልጠኛ ተቋሙን መታወቂያ ካርድ ወይም የአገልግሎት መለያ ካርድ ለሌላ ግለሰብ አሣልፎ መስጠት
10. በማሰልጠኛ ተቋሙ ወስጥ ስልጣን ባለዉ አካል የሚወጡ ልዩ ደንቦችን ለምሳሌ እንደ ቤተ-መጻሐፍት፣ ቤተ- ሙከራ እና ሌሎች
ደንቦችን ሆን ብሎ መጣስ
11. ህጋዊ በሆነ መልኩ ከማሰልጠኛ ተቋሙ ከተባረረ በኃላ በማሰልጠኛ ተቋሙ ውስጥ ማቆየት እንዲሁም በህጋዊ መልኩ የተባረረዉን
ሰልጣኝ ወደ ግቢዉ ውስጥ ማስገባት እና ሰልጣኝ ያልሆነዉን ግለሰብ ማስገባት
12. ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ የማሰልጠኛ ተቋሙን ስምና ክብር የሚያቃልል፣ መተማመንና መልካም አንድነት የሚያጠፋ
ተግባርና እንቅስቃሰ ላይ መሰማራት
13. በላይብረሪና በመማሪ ክፍሎች አካባቢ ሌሎችን በሚያዉክ መልኩ ድምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ ወይም መነጋገር
14. ሥር የሰደደ የጥላቻ ባህል በማሰልጠኛ ተቋሙ ማህበረሰብና በአካዳሚክ ስታፍ ላይ ማሣየት ወይም ማንጸባረቅ
15. በመግቢያ በር፣ በቤተ መጻሀፍት፣ በፈተና ክፍል ወ.ዘ.ተ የመታወቂያ ካርድ ወይም የአገልግሎት መለያ ካርድ ሲጠየቅ ለማሣየት ፈቃደኛ አለመሆን
16. በመማሪያ ክፍሎች፤ በመመገቢያና በስብሰባ አዳራሾች ዉስጥ ሲጋራ ማጨስ
17. ወደ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የመጨረሻ መግቢያ ሰዓት ተብሎ (2፡30) በማሰልጠኛ ተቋሙ የተደነገገ የሰዓት ገደብን አለማክበር፡፡
18. በማሰልጠኛ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ጫት ይዞ መግባት /ሲጠቀሙ መገኘት/
19. በመማሪያ ክፍሎች፤ በአብያተ መጻህፍት፣ በሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችና ግድግዳዎች እንዲሁም ወንበሮች ጠረጼዛዎች ላይ መጻፍ /ስዕል
መሳል/ወዘተ
20. አንድ ሰልጣኝ በሌላዉ ላይ መዛት፣ መሣደብና ማስፈራራት
21. አግባብ ያላቸዉ የኮሌጅ አካላት ወይም ኃላፊዎች የሚያወጧቸዉን መመሪያዎችና የሥነ-ሥርዓት ደንብ አለማክበር
22. የግልና የጋር ጤንነትን ሊጎዱ የሚችሉ ድርጊቶች መፈጸም (ክፍል ዉስጥ ማጨስ፤ አልኮል መጠጣት፤ጫት መቃምና ወዘተ)
23. ግቢ ዉስጥ ባልተገባ ቦታ መጸዳዳት
24. ከላይ በዚህ አንቀጽ የተጠቀሱትን ጥፋት ሲፈጽሙ እያዩ ለሚመለከተዉ ክፍል አለማሳወቅ
25. በማሰልጠኛ ተቋሙ ዉስጥ የምዘና፣ የስብሰባ፣ የምዝገባ ምዘናና የምረቃ ወ.ዘ.ተ. ጊዜን ማወክ
26. ሌሎች መሰል የሥነ-ምግባር ጉድለቶች መፈጸም፡፡
18.4፡- ከባድ የዲስፕሊን ቅጣቶች
ሀ. ለአንድ ሴሚስቴር ከማሰልጠኛ ተቋሙ የሚያሳግዱ ቅጣቶች

1.ከላይ ከተጠቀሱት አንደኛዉን የሥነ-ምግባር ጉድለቶች ፈጽሞ በጹሑፍ ማስጠንቀቂያ የታለፈ ሰልጣኝ ማንኘዉም ወይም ተመሳሳይ ሥነ-ምግባር ፈጽሞ
ሲገኝ
2.የሀገሪቱንና የማሰልጠኛ ተቋሙን ህግና ደንብ አለማክበር
3.በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ በሰልጣኞች ወይም በሌላ አካል የሚደረግ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴን እያወቁ በጊዜ አለማጋለጥ ወይም ተባባሪ መሆን
4.ፈተናን መኮረጅ፣ ማስኮረጅ፣ ከስልክ፣ከደብተር ወይም ከወረቀት መገልበጥ ወይም መሥራት ወይም የፈተና ወረቀትን ደልዞ ወይም ጨምሮ ከመምህራን
ዉጤት ለማስቀየር መሞከር
5.በማሰልጠኛ ተቋም ዉስጥ ለሚደረጉ ነገሮች በሀሰት መመስከር
6.የማሰልጠኛ ተቋሙን ክሊኒክ መድሃኒቶችን ለሌላ ተግባር ማዋል
7.ሰልጣኞች በማሰልጠኛ ተቋም ቆይታቸዉ ኢ-ዲሞክራሲያዊ የሆነ እና በኃይልና በጉልበት ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን ከማሰልጠኛ ተቋሙማህበረሰብ
ጋር መመስረት

•ለግጭት የሚገፋፉና አሰነዋሪ የሆኑ ነገሮቸን በቃል ወይም በጹሑፍ በመማሪያ፣ በመኖሪያ፤ በመጸዳጃና በቢሮዎች ግድግዳዎች፣መዝጊያዎች መስኮቶችና
ቁም ሳጥኖች ላይ መጻፍ፣ ወዘተ
9. የኮሌጅ ሠራተኞችንና መምህራን መልካም ስም በሀሰት በጹሁፍ ወይም በሌላ መንገድ ሊያጎድፍ የሚችል ድርጊቶችን መፈጸም
10.ሴት ሰልጣኞችን በንግግር፣ በጽሁፍ በኃይል ወዘተ ማስፈራራት፣ መዝለፍ፣ ማስቸገር፣ ማስጨነቅና ወሲባዊ ተንኮሳ ማካሄድ
11. የሰልጣኞች ሥነ-አእምሮ ሊጎዱ የሚችሉትን ኃይለ ቃሎችን በመጠቀም (ለምሳሌ ሴት ሰልጣኞችን የአካል ጉዳትን፣
የሰዉነት አቋምን፣ ከባህል ጋር ግንኙነት ያላቸዉን ነገሮችን ወዘተ) ምክንያት በማድረግ ሰልጣኙን የዝቅተኝነት ሰሜት እንዲሰማዉ
ማድረግ
12.የማሰልጠኛ ተቋሙን ንጽህናና ጽዳት የሚጎዱ ድርጊቶችን ለማሳሌ አበቦችን መንቀል አጥር ማፍረስ፣ በመማሪያ ክፍሎች አከባቢ
ሽንት መሽናት ወይም መጸዳዳት
13.የተለጠፉ ህጋዊ ማስታዋቂዎችን ማንሣት፣ መቅደድ፣ መደለዝ ወይም ማበላሸት
14. በአጥር ዘሎ መግባት ወይም መዉጣት
15. በስካር መንፈስ በግቢ ዉስጥ በማንኛዉም ቦታ ረብሻን መፍጠርና መጥፎ ሥነ-ምግባር ማሣየት
16. የአልኮል መጠጦችን በግቢ ዉስጥ አስቀምጦ መገኘት ወይም ሲጠቀሙ መገኘት
ለ. ለአንድ ዓመት ከማሰልጠኛ ተቋሙየሚያሰግዱ ቅጣቶች

1. ከላይ የተጠቀሱትን የሥነ-ምግባር ግድፈትን ወይም በጽሑፍና አንድ ሴሚስቴር ቅጣት የታለፉ ሰልጣኞች ማንኛዉም ወይም ተመሳሳይ የሥነ-
ምግባር ጉድለት ፈፅመው ሲገኝ
2.የማሰልጠኛ ተቋሙን ክብርና ዝና የሚጎዱ፣ የሰልጣኙንና የማሰልጠኛ ተቋሙን ማህበረሰብ የሚያዉክ ባህሪይና ተግባሪ መፈጸም ወይም ማሣየት
3.ህጋዊ ያልሆኑ ጹሁፎችን በማሰልጠኛ ተቋም ቅጥር ግቢ ዉስጥ መበተን ወይም ማሰራጨት ወይም መለጠፍ
4.ማንኛዉም ሰልጣኝ ማሟላት የሚገባዉን ነገር አልተደረገልኝም ብሎ ሲያስብ በግል ወይም በተወካይ አማካይነት በህጋዊ መንገድ ማቅረብና ምላሽ
ማግኘት ሲገባዉ ራሱንም ሆነ ሌሎችን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለአመጽ ማነሳሳት
5.በመደራጀትና ረብሻን በማነሳሳት የስልጠና ክፍለ ጊዜዎች እንዳይካሄዱ ማድረግና የማሰልጠኛ ተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴን ማስተጓጎል
6.በፈተና ወቅት ከስልክ፣ከወረቀት መስራትና ይህንን ሊያስቆሙ፣ ከሚንቀሳቀሱ ፈታኝ መምህራን ወይም ግለሰብ ጋር ግብግብ መፍጠር ወይም
ለመደባደብ መሞከር
7. ከማሰልጠኛ ተቋሙመምህራንና ሠራተኞች ጋር እንዲሁም እርስ በርስ ጥል ፈጥሮ መደባደብ፣ መሳደብና ማንጎጠጥ
8. የኮሌጅ የጋር መገልገያ ቁሳቁሶችንና የሻዉር ዕዋዎችን መስበርና ማበላሸት እንዲሁም የመጻህፍት ሰነዶችን መቅደድ
9. በተቃራኒ ፆታ መፀዳጃ ቤት ዉስጥ መገኘት
10. የማሰልጠኛ ተቋሙን ፀጥታና ሰላም ለማደፍረስ መሞከርና ማደፈረስ
11. ያለአግባብ የመምህራንን ወይም የሌሎችን ሠራተኞች ወይም የማሰልጠኛ ተቋሙን የማናጀመንት አባላት ከማሰልጠኛ ተቋሙሥራቸዉ ጋር
በተያያዘ ሥም ማጥፋት
12. የሌላ ሰዉ የምርምር ጹሑፍ ወይም ሥራ በሙሉም ሆነ በከፊል በመገልበጥ እንደራሱ ሥራ አድርጎ ማቅረብ ወይም ለማቅረብ መሞከር
ሐ. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከስልጠና ገበታ የሚያሰግዱ ቅጣቶች
1. የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን መፈጸም ወይም ለመፈጸም ሙከራ ማድረግ ለምሳሌ አስመስሎ መፈረም፣ ህጋዊ የሆኑ ሰነዶችን መሠረዝ፣ መደለዝና አሰመስሎ መሥራት
2. በማሰልጠኛ ተቋም ግቢ ዉስጥ በዘር፣ በብሔር ፤በፖለቲካ ልዩነት በሀይማኖት፣ በቀለም ክፍፍል ወ.ዘ.ተ. ፈጥሮ መሳደብ፣መደባደብ ፣ግጭቶችን መፍጠር
3. በዚህ መመሪያ የተመለከቱትን መርሆች አለማክበር ወይም መጣስ

መ. ለመጨረሻ ጊዜ ከማሰልጠኛ ተቋሙየሚያስባርሩ ቅጣቶች


• በማሰልጠኛ ተቋም ቅጥር ግቢ ዉስጥ ሴት ሰልጣኝን አስገድዶ መድፈር ወይም ለመድፈር ሙከራ ማድረግ ፡፡
• ለሁለት ተከታታይ የስልጠና ዓመታት የሚያሳግዱ ከባድ ጥፋቶችን ፈጽሞ በተወሰደዉ እርምጃ መሻሻል ሳያሳይ ለሁለተኛ ጊዚ ማንኛዉንም ተጨማሪ ጥፋት መፈጸም
• ድምጽ ባለዉ ወይም በሌለዉ መሣሪያ የኮሌጅ አባል የሆነ ግለሰብን መጉዳት ወይም ለመጉዳት ሙከራ ማድረግ
• ሆን ብሎ የማሰልጠኛ ተቋሙን ንብረት ለማጥፋት መሞከር ወይም ማጥፋት
•ማንኛዉንም የስርቆት ተግባር መፈጸም ወይም በድርጊቱ መተባበር እንዲሁም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ
•የአንድን ግለሰብ ብሔር ወይም ሀይማኖት በማንቋሸሽ ፀያፍ ቃል መሠንዘር ወይም በተለያዩ ቦታ ጽፎ መገኘት
•በፈተና ወቅት ለሌላ ሰልጣኝ መፈተን ወይም ለራስ ማስፈተን
•በማሰልጠኛ ተቋም ቅጥር ግቢ ዉስጥ የግብረ -ስጋ ግንኙነት መፈጸም
•በማሰልጠኛ ተቋም ቅጥር ግቢ ዉስጥ አደንዛዥ አጽ ወይም ድራግ መጠቀምና ይዞ መገኘት
•በማሰልጠኛ ተቋም ቅጥር ግቢ ዉስጥ ያልተፈቀደ ስብሰባ ማካሄድ፣ አድማ ማሳደም፣ ለማሳደም መሞከርና ህገ-ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ወይም ለማድረግ መሞከር
አንቀጽ 19፡- ተመራቂ ሰልጣኞች የዲስፒሊን ግድፈትን ፈጽመዉ ሲገኙ የሚወሰዱ የማስተካከያ
እርምጃዎች
ተመራቂ ሰልጣኞች ማለት፡- የመጨረሻ ዓመት ሰልጣኞች ሲሆኑ የመጨረሻዉን መንፈቅ ዓመት ትምህርት ተፈትነዉ ለመመረቅ
የተዘጋጁ እጩ ምሩቃን ጥፋት ሲፈጽሙ የጥፋቱን ሁኔታ በመመልከት በሚከተለዉ መልኩ የሥነ-ምግባር እርምጃ መዉሰድ
ያስፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት ከላይ በአንቀጽ 18 (አሥራ ስምንት) ስር የተደነገጉ ቅጣቶች እንዳሉ ሆነው፡-
19.1 በቃል ማስጠንቀቂያ የሚታለፉ ተብለዉ የተጠቀሱትን በቃል ማስጠንቀቂያ
19.2 በጹሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚታለፉ ተብለዉ የተጠቀሱትን በጹሁፍ ማስጠንቀቂያ
19.3 ለአንድ ሲሚስቴር የሚያስቀጡ ጥፋቶች ፈጽሞ ሲገኝ ለአንድ ሴሚስቴር ከመመረቅ እንዲዘገይ ይደረጋል፡
ለአንድ የትምህርት ዓመት ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱ ከባድ ጥፋቶች፣እንዲሁም ለሁለትየትምህርት ዓመት ከትምህርት ገበታ
የሚያሳግድ ከባድ ጥፋቶች የተባሉትን የፈጸመ ተመራቂ ሰልጣኝ ለሁለት ተከታታይ ሴሚስተር /አንድ ዓመት /ማንኘዉንም
የትምህርት ማስረጃ ይያዝበታል፡፡የድጋፍ ደብዳቤም ይከለከላል፡፡
19.5 ተመራቂ ሰልጣኝ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከማሰልጠኛ ተቋሙ ሙሉ በሙሉ ሊያሳግድ የሚችሉ የስነ-ምግባር
ግድፈት የፈጸመ ተመራቂ ሰልጣኝ ለሁለት ዓመታት ማንኛዉንም ዓይነት የትምህርት ማስረጃ ይያዝበታል፡፡ የድጋፍ
ደብዳቤም ይከለከላል ወይም ይታገድበታል፡፡
19.6 በዚህ መመሪያ ዉስጥ ከተጠቀሱት ዉጪ ሰልጣኞች አንዳንድ ከፍተኛ ጥፋቶችን ቢፈጽሙ ኮሌጅዉ በሰልጣኞች
ደህንነትና ጥበቃ ክፍል፣ በሰልጣኞች ዲስፕሊን ኮሚቴ፣ በት/ት ክፍሉ ተጠሪዎችና በተጨማሪ አግባብ ባላቸዉ መደበኛ
የህግ ክፍሎች እንዲታይ ሊያደርግ ይችላል፡፡
19.7 በአካዳሚክ ዉጤት ማነሰ ምክንያት፣ በዲሲፕሊን ግድፈት ምክንያት ከማሰልጠኛ ተቋሙ እንዲታገዱ የተደረጉ
ሰልጣኞች ያለበቂ ምክንያት በግቢዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀሱ ቢገኙ የመልሶ ቅበላ (Readmission) ጥያቄያቸዉ ይሰረዛል፡፡
አግባብ ባለዉ የህግ አካል ቀርበዉ ዉሣኔ ይሰጥባቸዋል፡፡
አንቀጽ 20፡- የዲስፒሊን ክስ አመሰራረትና እርምጃ አወሳሰድ
1. ክስ ማንኛውም የኮሌጅ ማህበረሰብም ሆነ ሰልጣኝ ለስልጠናም ሆነ ለማህበራዊ አገልግሎት ከሄዱባቸው ተቋማት፣ ግለሰቦችና
የአከባቢው ማህበረሰብ ከበቂ ማስረጃ ጋር ለኮሌጁ ዲን ሊያቀርብ ይችላል፡፡
2. የማሰልጠኛ ተቋሙ ዲንም የቀረበውን ክስ ለዲሲፕሊን ኮሚቴው በጽሑፍ እንዲደርስ ያደርጋል፡
3. የዲሲፒሊን ኮሚቴ ተከሳሽ ሰልጣኝ ክሱ በጽሁፍ እንዲደርሰውና ቀርቦም እንዲከላከል ወይም እንዲከራከርና ማስረጃ (የጽሁፍ፣የቃል
ወይም የሰው ምስክር) እንዲያቀርብ ማድረግ አለበት፡፡
4. የዲስፕሊን ኮሚቴ ከከሣሽም ሆነ ከተከሣሽ የሚቀርቡ ማስረጃዎችንና ምስክሮችን በመሰብሰብና በማጣራት ላይ የተመረኮዘ ዉሣኔ
መስጠት ወይም የውሳኔ ሀሳብ ለዲኑ ማቅረብ አለበት፡፡
5. የዲሲፒሊን ኮሚቴ የመጨረሻ የክሱን ውሳኔ ለተከሳሽ ሰልጣኝ በጽሁፍ እንዲደርሰው ማድረግ አለበት፡
6. በጥፋተኝነት የተወሰደዉን ማንኛዉም እርምጃ ተከሣሽ በዉሣኔዉ ላይ ቅሬታ ካለዉ በአንድ ሣምንት ጊዜ ዉስጥ ለኮሌጁ ዲን
ማቅረብ ይችላል፡፡ ቅሬታዉም ከዲኑ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ምላሽ ካላገኘ በኮሚቴው የተሰጠው ዉሣኔ የፀና ይሆናል፡፡
ክፍል አምስት
መረጃ በመስጠት መተባበር
አንቀጽ 21፡- በጥቆማ ስለማሳወቅ

1.ማንኘዉም ሰልጣኝ በዚህ መመሪያ ዉስጥ የተካተቱትን መርሆዎችን የሚጻረር የሥነ-ምግባር ጉድለት መፈጸሙን በማንኛዉም
መንገድ ካወቀ ወይም ከተመለከተ ጉዳዩን ለሚመለከተዉ ክፍል ማሣወቅ አለበት
2.የሚያቀርበዉ ጥቆማ እዉነተኛ፣ ያልተዛባ፣ ከበቀል የፀዳ፣ አሣሣች ያልሆነ ምክንያታዊ በሆነ እምነት ላይ የተመሠረተ መሆን
ይኖርበታል፡፡
3.ጥቆማ አቅራቢዉ ከማንኛዉም የበቀል ጥቃት የመጠበቅ መብት አለዉ፡፡
4.ጥቆማ አቅራቢዉ ማንነቱ እንዳይገለጽ ከፈለገ ማንነቱ በሚስጢር መያዝ አለበት፡፡
አንቀጽ 22፡-የመተባበር ግዴታ

ማንኛዉም ሰልጣኝ ለዲስፕሊን ሥራ የሚያሰፈልገዉንና የሚጠየቀዉን መረጃ በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 23፡- መመሪያዉን ስለማሻሻል

በተጨማሪም ማንኛውም ተማሪ በማሰልጠኛ ተቋሙ የተዘጋጁትን የተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያዎችና


ሌሎች አስተዳደራዊና አካደሚያዊ ሕጎችን የማወቅና የመተግበር እንዲሁም በማናቸውም ምክንያት ሲጣሱ
ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት። መመሪያዎቹም በቤተ መጽሐፍትና ለተማሪዎች
በሚመቹ የተለያዩ የማሰልጠኛ ተቋሙ ክፍሎች ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። ይህ መመሪያ አስፈላጊ ሆኖ
በተገኘበት በማናቸዉም ጊዜ ሊሻሻል ይችላል
አንቀጽ 24፡ የተማሪዎች የዲሲፒሊን ኮሚቴ

የዲሲፒሊን ኮሚቴው የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል


ሀ/ የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ቢሮ ኃላፊ------------------------------------------ሰብሳቢ
ለ/ አንድ የሠራተኛ ተወካይ --------------------------------------------------------ፀሐፊ
ሐ/ አንድ የአሰልጣኞች ተወካይ------------------------------------------------------አባል
መ/ ሁለት የሰልጣኘ ተወካዮች/ቢያንስ 1 የሴት/-----------------------------------አባል
ሠ/ አንድ የሰልጣኝ ካውንስል---------------------------------------------------------አባል
ረ/ አንድ አካዳሚክ ኮሚሽን ----------------------------------------------------------አባል

ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለአካዳሚክ ኮሚሽን /ለትምህርት ጉባኤ/ይሆናል፡፡


ኮሚቴው የስራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል ፡፡አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለአንድ ተጨማሪ የስራ ዘመን ሊሰየሙ ይችላሉ፡፡
አንቀፅ25 ፡ የኮሚቴው ስልጣንና ተግባር

11.1. ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት በኮሚቴው ፊት ቀርቦ ሊጠየቅ ይገባዋል


11.2. ውሳኔ የሚወሰነው ኮሚቴው ከ50 በላይ ሲገኙ ይሆናል
11.3. ኮሚቴው ከሚወስናቸው ውሳኔዎች ውስጥ ተማሪን ከነጭራሹ ከማሰልጠኛ ተቋሙየሚያስወጣ ውሳኔ ሲኖር
በማሰልጠኛ ተቋሙአካዳሚክ ኮሚሽን /ለትምርት ጉባኤ /ቀርቦ ይፀድቃል፡፡ከዚህ ውጪ ሌሎች የኮሚቴው ውሳኔዎች
የማሰልጠኛ ተቋሙ ውሳኔዎች ይሆናሉ፡፡
11.4. በዲሲፒሊን ኮሚቴ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ለተፈፃሚነታቸው የሰልጣኝ ካውንስል ኃላፊ ክትትል ያደርጋል፡፡
11.5. በማንኛውም ሠልጣኝም ሆነ በማሰልጠኛ ተቋሙየስታፍ አባል በራሱ የእውቀት ደረጃ ህግና ደንብ ሲጣስ ካየ
ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ

1. በዚህ መተዳደሪ ደንብ ውስጥ ከተገለፁት ውጪ አንዳንድ ጥፋቶች ከዲሲፕሊን ኮሚቴ


በተጨማሪ አግባብ ባለው መደበኛ የህግ ክፍል እንዲታዩ ይደረጋል፡፡
2. በአጠቃላይ የሠልጣኞች የማሰልጠኛ ተቋሙ ቆይታ የህይወት ታሪክ ለቀጣሪው ክፍል
ሪፖርት ይደረጋል፡፡
እናመሰግናለን

You might also like