Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 10

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ

የስራ አስኪያጅ ፑል መሰረታዊ ፓርቲ የ2016 በጀት


ዓመት የ3ተኛ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
መግበያ

መ/ፓርቲያችን በ2016 በጀት ዓመት 4ተኛ ሩብ ዓመት


ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው የህዋስ ውይይት፣የአባላት አቅም
ግንባታ ፣ አባላትን ማፍራት ፣ኮር ምልመላ ወዘተ ተግባራትን
ከመላው አባላቱ ጋር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ስለሆነም በዚህ ሪፖርት የተግባራቱን አፈጻጸም ከሞላ ጎደል
ለማካተት ተሞክሯል፡፡
በሪፖርቱ የተካተቱ የዋና ዋና ግቦች
 አባላት አቅም ግንባታ ስራ ይሰራል

 ወርሃዊ ክፍያ እንዲገባ ይደረጋል

 አዲስ አባላት ወደ ፓርቲው ይቀላቀላሉ

 ሁሉም አባላት በስራቸዉ ላይ ግንባር ቀደም በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን ተግባር ቀልጣፋ ማድረግ

 በየደረጃው ኮር በመፍጠር የልማት ሀይሉን ወደ ፊት ሊመራ የሚችል ጠንካራ ሃይል በየደረጃ እየፈጠሩ ማድረግ

 የፓርቲችን ህገ-ደንብ ከማስጠበቅ አንፃር የውስጥ ፓርቲ ዲሞክራሲ ተግባራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል፤

 የፓርቲችን መዋቅር ጠንካራ የሰራዊት ክንፍ ሆኖ እንዲወጣ የመዋቅሩን መረጃ ተጨባጭነት በተገቢው
በማረጋገጥ በማደራጀትና የመረጃው ወቅታዊነት በየሩብ ዓመቱ ማረጋገጥ ፡፡
የዋና ዋና ግቦች አፈጻጸም

በሩብ ዓመቱ ለ188 አባላት አቅም ግንባታ ስራ ለመስራት ታቅዶ

 ለ25 የመ/ፓርቲና ህዋስ አመራሮች የፓርቲ ፕሮግራምና ህገ ደንብ ላይ የአንድ ቀን ስልጠና ከፓርቲ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ተሰጥቷል

 የፑላችን አባላት የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ሲሆን በዚህም የነበሩ ዓሉታዊ አስተሳሰቦችን ለማስተካከል
ረድቷል፡፡

 በ6 ህዋስ የታቀፉ 188 አባላት በየወሩ በሚዘጋጀው የህዋስ ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ታቅዶ የህዋሶችን አፈጻጸም
እንደሚከተለው ለማስቀመጥ ተሞክሯል

 በቋሚነት የሚወያይ/ሳያቆራርጥ የሚወያይ 4

 የሚያቆራርጥ 2

በ9 ወር 10 ጊዜ ውይይት መደረግ ሲገባው ከፍተኛ 7 ቢቻ ነው የተወያየው


አቅም ግንባታ ስራ የቀጠለ

 በ3 ወር ውስጥ ከ188 አባላት ብር ወርሃዊ ክፍያ 30431.43 (ሰላሳ ሺ አራት መቶ ሰላሳ


አንድ ብር ከአርባ ሶስት ሳንቲም) ለመሰብሰብ ታቅዶ ሁሉንም በፐርሰንት በፔሮል ገቢ
ለማድረግ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ደረሰኝ ለአባላት በወቅቱ ከማድረስ አንጻር
የነበረብንን መሰረታዊ ችግር በንጽጽር ለመፍታት ተሞክሯል

 አዲስ ከተመለመሉ 14 አባላት ውስጥ 10 ወደ ፔሮል ስርዓት የገቡ ሲሆን የቀሩት 4ቱም
ከግንቦት ወር ጀምሮ ለመክፈል ፎርም ፈርመዋል
አዲስ አባላት ወደ ፓርቲው ይቀላቀላሉ

 በ3 ወር ውስጥ 5 አባል ለመመልመል ታቅዶ 4 የተመለመለ ሲሆን ሁሉም


የፓርቲያችንን ፕሮግራም ህገ-ደንብ እንዲወያዩ ተደርጎ ወደ ሙሉ አባልነት
ተቀላቅለዋል

• ሁሉም አባላት በመንግስት ስራ ላይ ግንባር ቀደም ማድረግ


 አባላት በየሴክተራቸው የመንግስት ስራቸውን በግንባር ቀደምትነት እንዲመሩት
ለማስቻል በየወቅቱ የአገልግሎት አሰጣጥ አጀንዳ ተደርጎ ውይይት እየተደረገበት
ይገኛል በዚህም አባላት በየተቋማቸው ለውጥ እንዲያመጡ አግዟል ለአብነት መሬት
አስተዳደር እና ሲቪል ምዝገበና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት መጥቀስ ይቻላል
በየደረጃ ከፍተኛ፤ መካከለኛ ዝቅተኛ አመራር ኮር በመፍጠር ሠራዊቱን ወደ ፊት ሊመራ የሚችል ጠንካራ ሃይል በየደረጃ እንዲፈጠሩ ማድረግ

 የኮር ልየታ ስራችን አሰራርን የጠበቀና ስራን/ተግባርን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን በየህዋሱ ተለይቶ
እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ በመሰረታዊ ፓርቲ ጸድቆ ለፓርቲ ጽ/ቤት ገቢ ተደርጓል በዚህም

 በከፍተኛ ---

 መካከለኛ ----

 ዝቅተኛ ----
የፓርቲ ህገ-ደንብ ከማስጠበቅ አንፃር የውስጥ ፓርቲ ዲሞክራሲ ተግባራ በተመለከተ

መረጃ ከማደረጀት አንጻር በንጽጽር ከዚህ ቀደም


በተሻለ ሁኔታ ለማደረጀት ጥረት እየተደረገ ሲሆን
ጥራት ከማስጠበቅና የተሟላ ከማድረግ አንጻር ብዙ
ይቀረናል
ያጋጠመ ችግር

 የመ/ፓርቲና የህዋስ የግንኙነት ጊዜ መቀራረጥ


 የመ/ፓርቲ ዓመራሮች በየተመደቡበት ህዋስ በአግባቡ አለመደገፍ
 የአባላት ምልመላ ተግባር በአንዳንድ ጽ/ቤቶች ካለው የሰራተኛ ቁጥር አንጻር የሚቀር መሆኑ
 የፓርቲ ቅጻቅጾችን በጥራት አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ አለማድረስ
 የህዋስ የውይይት ጊዜ አባላት በተሟላ ሁኔታ አለማሳተፍ እና የውይይት አጀንዳ አለመቅረጽ
 የዘርፍ ኃላፊዎች የዘርፋቸን ዕቅድ አዘጋጅተው የሰሩትን ስራ ሪፖርት ለሰብሳቢው ገቢ ያለማድረግ
ማጠቃለያ

•በቀጣይ የተሰሩ ስራዎችን ለማጠናከርና የቀሩ ስራዎችን


ለማጠናቀቅ በመሰረታዊነት ከላይ የተገለጹ በተለይ ደሞ
ከአመራር ጋር ተያይዞ የተስተዋሉ ችግሮች መቀረፍ ያለባቸው
ሲሆን ከዚህ አንጻር የፓርቲ ጽ/ቤትና የደጋፊ ዓመራር ሚና የጎላ
እንደሆነ መ/ፓርቲው ያምናል፡፡
•ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ችግሮችን በጋራ ሆነን ለመፍታት
ከምንጊዜውም በላይ ጠንከረን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡

You might also like