Download as pptx, pdf, or txt
Download as pptx, pdf, or txt
You are on page 1of 40

በተሞክሮ

ቅመራና ማስፋት
ሂደት ላይ
ስልጠና ለመስጠት
የተዘጋጀ አጭር ማንዋል
ከዚህ ግምገማዊ ስልጠና ይገኛል ተብሎ
የሚታሰብ ዕውቀትና ክህሎት
• ምርጥ ተሞክሮ ምን ማለት እንደሆነ
• እንዴት ሊቀመር እንደሚችል
• እንዴት ሊስፋፋ እንደሚችል
• የመቀመርና የማስፋት ስትራቴጂው ምን እንደሆነ
• ስለሚፈጠሩ አደረጃጀቶችና ስልቶች፣ ወዘተ.
.
በምርጥ ተሞክሮ ልየታ፣ ቅመራና ማስፋት ሂደቶች ላይ ያጋጠሙ
ውስንነቶች
• በሁሉም ደረጃዎች የግንዛቤ እጥረት መኖሩ፤
• የተቀመረውን ተሞክሮ ወደ ተግባር አለመለወጥ፣
• ሰነዱ ተዘገዘጅቶ ከተሰራጨ በህዋላ ክትትል
አለማድረግ፤
• የመቀመርና የማስፋት ሥራውን በዕቅድ አለመምራት፤
• ተስፋፍቶ የተገኘውን ለውጥ በመረጃነት አለመያዝ፤
• በጥቃቅን ለውጥ/ውጤት መርካት፤
በዚህ ጽንሰ-ሐሳብ መሠረት ምርጥ ተሞክሮ የሚለው
የጥራት ደረጃን ብቻ የሚወክል ሳይሆን ስኬትን
ለማምጣትና ችግሮችን ለመፍታት ጥቅም ላይ የዋለ
ቴክኒካዊ አሠራርን የሚያመለክት ነው፡፡
ተከስተው የነበሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ማድረግ
የሚቻልበት ስልትም ነው፡፡

ምርጥ ተሞክሮ እጅግ በጣም አነስተኛ በሆነ ሀብትና ጥረት


እንዲሁም ወጥ በሆነ የአሠራር ቅደም ተከተል የላቀ
ውጤታማነት የሚመጣበት ዘዴ ነው፡፡
ምርጥ ተሞክሮ በቦታና በጊዜ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ
አንፃራዊ እንጂ ፍፁም ነው ማለት አይቻልም፤ እንዲሆንም
አይጠበቅም፡፡
በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ፍፁም የሆነ ምርጥ ልምድ የለም፡፡
ይሁንና የወቅቱን ችግሮች በመፍታት ረገድ ዜጎችን እንዲያረካ
ይጠበቃል፡፡
የምርጥ ልምድ መምረጫ መርሆዎች
ምርጥ ተሞክሮን የማላመድና የማስፋት ሥራ ሲሰራ
የመምረጫ መርሆዎችን ከግምት ውስጥ ማስቀመጥ የግድ
ስለሚል እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
. ይሰራል ተብሎ በተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ
ስኬታማ የመሆን መርህ፤
- ሁሉም ነገር በጊዜ የተገደበ ነው
- በውድድር ማዕበል አሸናፊ መሆን
- ለወቅታዊ ችግር ወቅታዊ ምላሽ መሻት

• በተገልጋዩ ዘንድ አዎንታዊ ምላሽ


የማግኘት/ተገልጋይ ዜጋውን የማርካት መርህ፤
አገልግሎት ከተሰጠ ወይም ምርት ከቀረበ በህዋላ
- በተገልጋዩ ዘንድ ተመራጭ የመሆን ጉዳይ
- ድጋፍና ትብብር የማግኘት ጉዳይ
• በመጠንና በጥራት ከሁሉም የላቀ የማድረግ መርህ፤
መጠን - ሁሉን ተገልጋይ/የሚፈለገውን ያህል ምርት/ሰፊ ሽፋን
ጥራት - አገልግሎት…. ከአቀባበል ጀምሮ
- ምርት… ተፈላጊ/ከሁሉም የተሻለ…
- አቅርቦት….. የተገዙ ዕቃዎች፣ ……

• የፈጠራ ጥበብ የመጨመር መርህ፤


- ውበት መስጠት፣ መቀባባት፣ አሳምሮ ማቅረብ/ማምረት፡-
(ኮብል ስቶን ግንባታ)

• በቀላሉ መባዛት የሚችል አድርጎ የማስማማት


መርህ፤
- ግልፅ፣ ሌሎች ሊረዱትና በአነስተኛ ወጪ ሊጠቀሙበት የሚችሉት
• ለማጓጓዝ ቀላልና ወደ ሌሎች ሊሸጋገር የሚችል
አድርጎ የማስማማት መርህ
- በአካል ከሚሆን በሞዴል፣ ወይም በምስል ወይም በትረካ

• የአፈጻጸም ደረጃው ለተጠቃሚዎች ትርጉም እንዲሰጥ


የማድረግ መርህ፤
- ባለጉዳይን በቀን ሳይሆን በሰዓት መቅጠር

እነዚህን መሰረት በማድረግ ምርጥ የተባሉ ተሞክሮዎችን


መምረጥና ማስፋፋት ይቻላል፡፡
የምርጥ ተሞክሮ መገለጫ ባህርያት
ባህርያቱ በተለያየ ወቅት የተለያየ መስፈርት ሲቀመጥላቸው
የቆየ ቢሆንም፤ አንዳንድ ጸሐፍት በሚከተለዉ
መልኩ ይገልጹታል፡-
• ተሞክሮው በቀላሉ ሊሰራ፣ ሊለካ፣ አግባብ ባለው
ሃብትና ጊዜ ሊከናወን እና ውጤት ሊያመጣ የሚችል
መሆኑ፤

- በአሠራር፣ በአኗኗር፣ ወዘተ. ለውጥ የሚያመጣ


• ስራ ላይ ከሚውልበት የስራ ባህርይ ጋር ተስማሚ መሆኑ፤
- ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፀጥታ(ኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ)፣ ወዘተ. ሥራ
• በወቅቱ ካለው ህብረተሰብ ባህልና እሴት ጋር በቀላሉ
የሚላመድ መሆኑ፤
- በአቅም መደገስ፣ በበዓል ቀን መስራት፣ …
• በማንኛውም ቦታ የመስፋፋት ዕድል ያለው መሆኑ፤
- ምርትን የሚጨምር/ ተገልጋይን የሚያረካ

• ከያገባኛል ባዮች ጋር ውጤታማ ትብብር መፍጠር


ማስቻሉ፤
- የሚያቀራርብ፣ ለትብብር የሚጋብዝ

• ልምዱ ከብሔራዊ እስከ ከባቢያዊ መስተዳድር


ያሉ አመራሮችን ድጋፍ ማግኘት የሚያስችል
መሆኑ የሚሉት ናቸዉ፡፡
ሌሎች ጸሃፍት ደግሞ የምርጥ ተሞክሮ ባህርያትን በሚከተለው
መልኩ ይገልጹታል፡-
1. የለውጡ ተጽዕኖ አድማስ ሠፊ መሆኑ፤
2. ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው መሆኑ፤
3. በአቅም ሊገዛና ደጋግሞ መጠቀም ሲያስፈልግ ተጨማሪ
ወጪ የማያስወጣ ሊሆን የሚገባው መሆኑ፤
4. ፈጣን እና ስር ነቀል ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑ፤
5. ተፅእኖው ወይም የግብ ስኬቱ ሊቀለበስ የማይችል እና ለረዥም
ጊዜ የሚቆይ መሆኑ፤
1. የለውጡ ተጽዕኖ አድማስ ሠፊ መሆን፣
የለውጡ አድማስ ሠፊ የሆነ ሲባል ለውጡ በሁለት፣ በሶስት፣
በአራት፣….. እጥፍ የሚንፀባረቅ፣
ተጨባጭ የሆነና ሠፋ ወዳለ አካባቢ/የህብረተሰብ ክፍል ሊዳረስ
የሚችል ለውጥ ማለት ነው፡፡
- በአንድ ክፍል ከሚማሩት ተማሪዎች ውስጥ 5% ውጤታቸውን ማሻሻል ከማለት 5 እጥፍ
ብሎ መነሳት

2. ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው መሆኑ፤


አንድ ውጤታማ አፈፃፀም በምርጥ ተሞክሮነት ሊወሰድ ከሆነ
ቢያንስ ከተቋማት መካከል ከፍተኛ የአፈፃፀም ለውጥ ያመጣ ሊሆን
ይገባዋል፡፡
- ተገልጋዩ ከሚፈልገው/ተቀ 㓫 ሙ ካስቀመጠው ዝቅተኛ የጥራት ደረጃ የበለጠ
3. በአቅም ሊገዛና ደጋግሞ መጠቀም ሲያስፈልግ ተጨማሪ
ወጪ የማያስወጣ ሊሆን የሚገባው መሆኑ፤
ምርጥ ተሞክሮ በመጠቀም ስርነቀል ለውጥ በዘላቂነት
ማምጣት የሚቻለው አቅምን ያገናዘበ (affordable) እና
ቀጣይነት ያለው (Sustainable) ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡
- የተፈጥሮ ማዳበሪያ/ኮምፖስት፣ ፈርኒቸር፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች
- የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ሥራዎች- በዘልማድ ከምናወጣው ያልበለጠ
4. ፈጣንና ስር-ነቀል ለውጥ ሊያመጣ
የሚችል መሆኑ፣
የምርጥ ተሞክሮ ሌላው ባህርይ ፈጣንና ሊታመን የማይችል ለውጥ
በአጭር ጊዜ ማስመዝገብ ማስቻሉ ነው፤ ይኸውም፡-
በዓመት ያልቅ የነበረውን ሥራ በወራት፣ በቀናት፣ በሰዓታት፣ ወዘተ.
ውስጥ ለመፈፀም ማስቻሉ ነው፡፡
(ለአብነት አይ.ሲ.ቲ.)
- ፋክስ፣ ኢ-ሜይል፣ ቪ-ኮንፈረንስ፣ ስኩል ኔት፣ ሽቦ አልባ ስልክ፣ ወዘተ.
- ጽሁፍን በእጅ፣ በታይፕ፣ በኮምፒዩተር፣………..
- የገጠር መንገድና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራዎቻችን
5. የግብ ስኬቱ ሊቀለበስ የማይችልና ለረዥም ጊዜ የሚቆይ
መሆኑ፣(Social Tranasformation)
ከሁሉም የላቀ ለውጥ ያመጣ ምርጥ ተሞክሮ ሲባል ለአጭር
ጊዜያት ውጤት የሚያሳፍስ እና በማግስቱ የሚፈራርስ
ማለት አይደለም፡፡
ይልቁንም በፅኑ መሰረት ላይ እንደ ተገነባ ቤት ለረዥም ጊዜ
የሚቆይ ፋይዳ ያለው ለውጥ ማለት ነው፡፡
- በከተሞች ባለሃብትን የመሳብ እንቅስቃሴ
ምርጥ ተሞክሮን ከመቀመርም ሆነ ከማስፋት በፊት ከዚህ
በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በጥልቀት ማጤንና
በእርግጥ ተሞክሮ መሆኑን መመዘን ይጠይቃል፡-
• ብዙ ተጠቃሚዎችና ባለድርሻዎች የረኩበትና
ማረጋገጫ የሰጡት መሆኑ
• የስራው ባለቤቶች/ ባለሙያዎች ሥራ ምርጥ መሆኑን
የተስማሙበትና ያመኑበት መሆኑ፤
• ያመጣው ለውጥ ሲመዘን ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑ
በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ መሆኑ፤
• ከተመሳሳይ ተቋማት ጋር ሲነፃፀር በተጨባጭ ብልጫ
ያሳየ ስለመሆኑ የተመሰከረለት መሆኑ እና
• ዘመኑ ከወለደው ቴክኖሎጅ ጋር አጣጥሞ መጠቀም
የሚቻል መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡
ማስፋት ሲባል………..
ማስፋት ማለት፡-
ምርጥነታቸው የተረጋገጡ አሠራሮችን/ ውጤቶችን ወደ ሰፊ
መልክዓ ምድራዊ አካባቢ በመውሰድ በአጭር ጊዜ፣
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በአስተማማኝና በዘላቂነት በመተግበር
አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ
የሚያስችል ልማታዊ መሰረት ማስያዝ ማለት ነው፡፡
ማስፋት፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ አዎንታዊ ተጽእኖ የሚኖራቸውን
ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመተግበር የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን
እቅድና ፕሮግራም በመንደፍ በሁሉም አካባቢዎች ሥራ ላይ
እንዲውሉ ማድረግ ነው፡፡
- ፖሊሲና ስትራቴጂን ወደ ተግባር እንዲለወጥ ማድረግ

ማስፋትን በሁለት መንገድ ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡


አንደኛው ከታች ወደ ላይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጐንዮሽ
የማስፋት ስልት ነው፡፡
ከታች ወደ ላይ ማስፋት
/VERTICAL SCALING UP/
ይህ ስልት ከአንድ ግለሰብ፣ ተቋም፣ ወዘተ. የተገኙ ምርጥ
ተሞክሮዎችን ተቋማዊ መሰረት በማስያዝ ሰፊ
የህብረተሰብ ክፍልን ተጠቃሚ ለማድረግ በአጋር አካላትና
በተቋማት ተሳትፎ የሚከናወን፣
ሂደቱ በከፍተኛ አመራር የሚወሰን ተግባር ነው፡፡
- ከአንድ አርሶ አደር ወይም ቀበሌ ተነስቶ እስከ ወረዳ፣
ዞን፣ ክልል፣ አገር፣ አህጉርና አለም አቀፍ ደረጃ
የሚደርስ ልምድ ልውውጥ
- ከማይመሳሰሉ ተቋማትም ልምድ የሚቀሰምበት ስልት
ጐንዮሽ የማስፋት ስልት
/HORIZONTAL SCALING UP/
ይህ ስልት የተገኘን ውጤት፡-
- ሰፊ ስልጠና በመስጠት፣
- አጋዥ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም፣
- አስፈጻሚ የልማት ሃይሎችን በማዘጋጀትና መሰል
ዘዴዎችን በመጠቀም ተሞክሮ የሚስፋፋበት፤
ሂደቱ በተጠቃሚው አካል የሚወሰን ስልት ነው፡፡
- ተመሳሳይ ወደ ሆኑ ግለሰቦች/ተቋማት/ማህበራት/አካባቢዎች…….
ማስፋት ለምን አስፈለገ?
በአሁኑ ወቅት የማስፋት ሥራ በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ
ፕሮግራም በተለይም በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ትግበራ
የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በሁሉም የመንግስት ተቋማት
ተፈፃሚ እንዲሆኑ ማድረግና የዜጎችን ሁለንተናዊ ፍላጎት
ማሟላት ጊዜ የጠየቀው ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይኸውም፡-
ከኢኮኖሚ፣ ከማህበራዊና ከመልካም አስተዳደር ጠቀሜታ አንፃር ሲታይ
ሀ. ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ አንጻር

ቴክኖሎጂን ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ስንኮርጅ ላለንበት


የእድገት ደረጃ ተስማሚ የሆነውን ቴክኖሎጅ በጥንቃቄ
መምረጥ ተገቢ ነው፡፡
ይህም በአጭር ጊዜና ባነሰ ወጭ ልምድን በማስፋትና
ውጤታማነትን በላቀ ደረጃ በማረጋገጥ፣ በጥራትና በዋጋ
ተወዳዳሪ መሆን ያስችላል፡፡
- መሠረተ ልማት፡- ስልክ፣ መንገድ፣ መብራት፣ ውሃ………
- የሩዝ፣ የቢራ ገብስ፣ የእንሰት፣ ወዘተ. ምርት እንደ ተሞክሮ
ለ. ከማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር
በማህበራዊ ዘርፍ የሚታዩ ሰፊ ጉድለቶችን ለመሙላት
በአንዳንድ አካባቢዎች እንደታየው ህብረተሰቡን በጉልበት፣
በገንዘብ፣ በማቴሪያልና በሃሳብ አጋዥ፣ ብሎም በውጤቱ
ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጎ ማሰለፍ ይቻላል፡፡
- ት/ቤቶች፣ ኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ጽ/ቤቶች፣ ግድቦች፣ ወዘተ.
- የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እንቅስቃሴዎች
ሐ. ከመልካም አስተዳደር አንጻር
መልካም አስተዳደርን በማስፈንና የዲሞክራሲ ስርአትን
በመገንባት ሂደት የሚደረገውን ጥረት ለማፋጠን፤ ብሎም
የህዝቡን የደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ ምርጥ ተሞክሮዎችን
በማስፋት መጠቀም ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር የስርአቱ ደንቃራ
የሆነውን የኪራይ ሰብሳቢነት አባዜ ለመዋጋት ፈር ቀያሽ
ይሆናል፡፡
- ልማትን ለማምጣት፣ የህዝቡን ደህንነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ
የማስፋት መርሆዎች
(Principles of Scaling up)
እንደ William Easterly አቀራረብ መርሆዎች
እንደሚከተለው ይጠቀሳሉ፡-
• ስኬታማ የሆኑ ልምዶችን ማስፋት (Scale up
success not failure)
አንገብጋቢ (የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ፣ የተቋም፣
ወዘተ.) ችግር ሊፈቱ የሚችሉትን፣
- ቁልፍ ችግሮችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥ
- መሬትን ማስፋት ይቻላል?
- ናፍጣን ከከብት ሽንት
- መስፈርቶችን ልብ ይሏል፡ የተጠቃሚ ይሁንታ፣ የባለቤቶች እምነት፣ በተግባር
የተፈተሸ፣ ብልጫ ያለው፣ ከቴክኖሎጂው ጋር የሚጣጣም……
• እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ብለን ያሰብነውን ብቻ
ሳይሆን በተሻለ ሊሰራ የሚቻለውን መምረጥ
(Don’t scale up what you think is
most important, scale up what you do
best)
- አቅምን ያገናዘበ ፡- የንግድ ባንክ ዘመናዊ አስተያየት መስጫ
- ካዳስተር ፡- የመሬት ልየታ፣ ፋይል ጠፋ አይባልም፣ የግብር
ስርዓት፣
- የአካባቢ ሁኔታ ፡- በበዓላት ቀን መሥራት
• ዝቅተኛ ወጪ የሚጠይቀውንና አስተማማኝ ግብዓት
ያለውን መምረጥ፤
(you can scale up only what requires cheap,
abundant inputs; you cannot scale up
something that depends on expensive, scarce
inputs)
- በአካባቢ ቁስ የሚሰሩትን፡- በብረት የተሠራውን በቅርቀሃ፣ በድንጋይ፣ በእንጨት፣ ወይም
በሌላ ማቴሪያል
- የኃይል ምንጮች ፡- ከሰል፣ እንጨት፣ ፀሐይ፣ ባዮጋዝ
(ከእበት፣ ከሰው እዳሪ)፣ HEP……….
• ባለው የሰው ሀይልና ማቴሪያል በቀላሉ
የማስፋት መርህን መከተል
(Things that you make routine are
among the easiest to scale up)
- በተመሳሳይ ተግባር የተሰማሩትን፣
- በጥቃቅን የተደራጁትን፣
- ስልጠና ያገኙ/ልምድ ያላቸውን ሰዎች መጠቀም (ቁሳ ቁሱንም)

• ከማስፋት ሂደት በኋላ ውጤታማ መሆኑን


መገምገም፤
(Evaluate whether you are successful after
scaling up)
- ልምዱን ካስፋፋው ጋር ሆኖ አፈፃፀሙን የመቃኘት፣
- እንደገና የማስፋፋት፣
- እንደገና የማሻሻል መርህ
ምርጥ ተሞክሮን በማስፋት ሂደት ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ
ዘዴዎችና አደረጃጀቶች
የማስፋት ዘዴዎችና አደረጃጀቶች እንደ ተቋሞቹ የሥራ
ባህርይና የቴክኖሎጂ ይዘት የሚለያይ ቢሆንም የጋራ ሊሆኑ
ከሚችሉት ውስጥ የተወሰኑት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
ሀ. አደረጃጀት
. የአመራርና አስተባባሪ ግብረ ሀይል
(Leadership and Coordinating Committee)
- የመ/ቤት ኃላፊዎችና ም/ኃላፊዎች፣ ሂደት መሪዎች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ ርዕሳነ መ/ራን፣
የጤናና የግብርና ተጠሪዎች፣ የሪፎርም ባለሙያዎች፣ ወዘተ.

. የባለሙያ ቡድን (Expert Group)


- እንደ ተቋሙ ባህርይ ተሞክሮዎችን የሚያፈላልግ፣ የሚያሰባስብ፣ የሚቀምር፤ ስልት ነድፎ
የሚያስፋፋና ክትትል የሚያደርግ ቡድን
ለ. የአተገባበር ስልት
• ምርጥ ተሞክሮ ያላቸውን አካላት በመጋበዝ የአቻ ለአቻ
ትምህርት እንዲለዋወጡ ማድረግ (አንድ ለብዙ ወይም ብዙ
ለብዙ ተሞክሮዎችን ማስተላለፍ)
- መድረክ ማመቻቸት፣ ባለሙያ መጋበዝ

• የተቀመሩ ተሞክሮዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት


የሚያስችል ኮንፈረንስ ማካሄድና አፈጻጸሙን መከታተል፡፡
- ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን አካላት ማሳተፍ
• ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት ተሞክሮዎችን በፎቶ ግራፍ፣
በግራፍ፣ በሞዴል፣ ወዘተ. አቀነባብሮ ለህዝብ እይታ
ማብቃት፤
(Exhibition Presentation)
- ሲምፖዚየምና ፓናል ውይይት
- የኤግዚቢሽን ተሞክሮ
• ተሞክሮዎችን በጥልቀት መመርመርና መረዳት
(Understand the Full Scale Intended)
- ቡድኑ ከመንቀሳቀሱ በፊት ጀምሮ
• የሚስፋፉባቸውን ቦታዎች በማስተዋል መምረጥ
(Select Participating Sites)
• አስፈላጊ ፋሲሊቲዎችን ማሟላት
(Organize and Equip the Team)
- እንደ ሥራው ጠባይ ስቴሽነሪ፣ ማጓጓዣ፣ ልዩ ልዩ ወጪዎች፣ ወዘተ.

• መተግበርና ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ


(Implementation and Close Follow up)
- እንዳይዘነጋ፣ እንዳይበላሽ፣ ዓላማውን እንዳይስት፣ ከሁሉም በላይ ተገልግዮችን እንዲያረካ
• ሞዴል መጠቀም (Use the Model)
- በጋራ መምከርና ከስምምነት መድረስ
- የሐሰት ሞዴል እንዳይሆን፣ ሙሉ ድጋፍ ማድረግ
አብነት፡- መቄትን እንደ ዞን
• አፈጻጸሙን መቀመርና እንደገና ማሻሻል (Document
Progress and Updating)
• ተሻሽሎ የተቀመረውን ሥራ ላይ በማዋል ተገቢውን ክትትል
ማድረግ፤
• ልምድ ካለውና ድጋፍ ከሚሰጠው አካል ጋር የቅርብ ግንኙነት
በማድረግ መገምገም፤
ምርጥ ተሞክሮን ለማስፋት መሟላት ያለባቸዉ ቅድመ
ሁኔታዎች
ምርጥ ተሞክሮዎችን ከማስፋት በፊት የሚከተሉትን ቅድመ
ሁኔታዎች ስራ ላይ ማዋል ይገባል፡፡
• አስቀድሞ በብቃት የተነደፈ እቅድ
(Adequate planning)
- አሳታፊ፣ ከሀገራዊ/ክልላዊ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ፣ በውጥረት የሚፈፀም፣
በመርሃ ግብር የተደገፈ፣ የሚሻሻል፣

• የፖሊሲ ድጋፍ (Policy Support)


• በየፈርጁ (በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ)
• የአመራር ቁርጠኝነት
(Leadership Commitment)
- የሞት የሽረት ጉዳይ
- አመፀኛ የሆነ፣ እያለ ማጣቱ የሚሰማው፣ ልምድ አፈላልጎ
እንዲስፋፋ ጥረት ማድረግ

• ጠንካራ የግንኙነት መረብ - ፈፃሚ፣ አስፈፃሚ፣ ተባባሪ


(Strong & Networked relationship)
- ጥሩው ሥራ የጋን መብራት እንዳይሆን
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከቱትን አቅጣጫዎች በድምር ወይም
በተናጠል ሥራ ላይ በማዋል በአጭር ጊዜ በሁሉም አካባቢዎች
የታሰበውን ልማት ዕውን ማድረግ ይቻላል፡፡

በተለይም የለውጥ ትግበራን ምርጥ ልምዶች በማስፋት


ሂደት የተለያዩ ተለዋዋጭና ልዩ ባህርያትን ማገናዘብ ተገቢ
ይሆናል፡፡

ለዚህም ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን አስማምቶ


የስኬታማነቱን ዘለቄታ ለማረጋገጥ ከበሳል አመራርና
ባለሙያ እጅግ የላቀ ጥረት ይጠበቃል፡፡
---------------- /////// ------------------

You might also like